ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

🌱📖"بناء الذات بنور الوحي

🌱📖"بناء الذات بنور الوحي

Открыть в Telegram

🌱📖 ራስን በወህይ ብርሃን መገንባት ቁርኣንና ሐዲስን የሕይወታችን መሪ በማድረግ፣ ማንነታችንን የምንቀይርበትና በእውቀት አብረን የምናድግበት ልዩ መድረክ! 📖🌱 📖 የቁርኣን አንቀጾችንና ውብ የነብዩን  ሐዲሶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንተገብራቸዋለን? 🌱 እስላማዊ ስነ-ምግባርን እንዴት እንላበስ? 🤝 በጋራ የምንማማርበትና አብረን የምንለወጥበት

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
500
Подписчики
-324 часа
-77 дней
+3430 дней
Архив постов
✏ አሊፍ ስለ ረሱል ሁብ... 💔  〰 በመጨረሻው እስትንፋስ... በሞት አፋፍ ላይ የተሰጠ ልብ የሚነካ አደራ! የረሱል (ﷺ) ህመም ክፉኛ በረታ፤ ትኩሳቱ ከብዷቸዋል፣ ራሳቸውን እያጡ ይነቃሉ። ከጎናቸው ውድ ባለቤታቸው እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ) እግራ ላይ አስደግፋቸው ...ያቺ ሰዓት ነፍሳቸው ከስጋቸው ልትለይ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ የቀሩባት እጅግ አስጨናቂ ሰዓት ነበረች...  «اِتَّقُوا اللهَ فِي النِّسَاءِ... فَإِنَّهُنَّ عَوَانٍ عِنْدَكُمْ» «አደራችሁን በሴቶች ጉዳይ አላህን ፍሩ! አደራችሁን ለሴቶች መልካም ሁኑ!» 💔  ስብሓነላህ! እህቴ ሆይ ልብ በይ... ከእሳቸው በፊት እንደ ከብት የምትሸጠውን፣ በህይወት በአፈር ውስጥ የምትቀበረውን ሴት አንስተው ንግስት ያደረጉሽ እሳቸው ናቸው። በሞት ጣር ውስጥ፣ ህይወታቸው ልትወጣ በቀረበችበት በዚያች የመጨረሻ እስትንፋስ እንኳ አንቺን አልረሱሽም! «አደራ ሴቶችን!» ብለው ስለ አንቺ ክብር አደራ ብለው አለፉ። ለሴት ልጅ እንዲህ ያዘነ፣ እንዲህ የተጨነቀ፣ እስከ መጨረሻው የህይወት ቅጽበት ድረስ በአደራ ያስቀመጣት ማን አለ?! ታዲያ እህቴ ሆይ... እሳቸው በመጨረሻው እስትንፋሳቸው አንቺን ሳያስረሱሽ ከሄዱ... አንቺ ዛሬ በዚህ በተከበረው የጁምአ ምሽት እሳቸውን እንዴት ትረሻቸዋለሽ?! ያንን ውለታቸውን ሳታስቢ እንዴት ይነጋል?! ሴትነታችንን ላከበረው፣ በሞት አፋፍ ላይ ላሰበን ውድ ነቢይ የፍቅር ምላሽ እንስጥ!  📿 اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

أَلَمْ يَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ هُوَ يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَأْخُذُ الصَّدَقَاتِ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ [....................]
Anonymous voting

ኑሩ ሰባህ 🩵
አላህ ሙስሊም አድርጎ ወደ ዚች ምድር እንዳመጣን በሱ ዲን ላይ ሆነን እሱን ታዘን ሞተን ጀነት ከሚያገኙት ያድርገን!
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

... وَاللَّهُ أَيَّدَهُ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ الَّذِينَ كَفَرُوا السُّفْلَىٰ ۗ وَكَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا ۗ وَاللَّهُ [....................]
Anonymous voting

🥀ሶባሐል ኸይር .... ብቸኝነት የዘላለም ህይወታቹ አይሆንም በስደት እንደተንከራተታቹ አትኖሩም በአገር ቤት ናፍቆት አትሞቱም የምትወዱን ሰዎች እየናፈቃቹ አትቆዩም ሰባሐል ኸይር ☺ ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ተደቡር ...♡ «وَفَتْحٌ قَرِيبٌ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ» “(ከአላህ ዘንድ የሚገኝ እርዳታ)፣ የቅርብ የሆነም ድል (እፎይታ) አለ፤ ምእመናንንም (በምስራች) አብስራቸው
ተደቡር ...♡
«وَفَتْحٌ قَرِيبٌ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ»
“(ከአላህ ዘንድ የሚገኝ እርዳታ)፣ የቅርብ የሆነም ድል (እፎይታ) አለ፤ ምእመናንንም (በምስራች) አብስራቸው።”
〰  አሁን ካለንበት ጭንቀት ሰላም ማጣት ፣ተስፋ መቁረጥ ፣ፍርሃት ፣መሸነፍ ...... የመውጫ ቀናችን መች ይሁን ወይስ እንዲው ጨላማ እንደሆነ ህይወቴ ምታልቀው?  መቼ ነው አለፈለት  የምባለው እኔም የደስታ እምባ የሹክር የተህሚድ እምባ ማነባው  መች ነው የናፈኳቸውን ማገኘው ....!?🥹 አሁን ላይ የሁላችንም ከራሳችን መናገገሪያ ጉዳይ ነው ።ግን ይህን ጭንቀታችን ለመገርሰሰ አላህ ምን አላ "እርዳታው (እፎይታው) ቅርብ ነው " ቅርብ ሆነ ማለት የሆነ ጉዳይ የጠበቀ ነው ያንተን መጠንከር እና ሰብር እና ያሲከሰት አንተጋ ይደርሳል ።ቅርብ ነው አዎን ሩቅ አይደለም እንደምናስበው መሆን አይሳነንንም ኢንሻአላህ 🩵 "ሙእሚኖችን አብስራቸው " ሲባል ደሞ አሁንም እፎይታው ራቀ ብለን ተስፋ እንዳንቆርጥ  ነው ሩሱልን እነዲህ ያሉት! አብሹሩ ሁሉም ሚስተካከልበት ሙራዳቹ ሚሞላበት ቀን ቅርብ ነው ❤‍🩹🤞🏿
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي [....................]
Anonymous voting

ኑሩ ሰባህ 🩵
በህይወታችን ውስጥ ብዙ ቀናት አሉ ተስፋ ቆርጠን መሄጃ አተን እግራችን የተሳሰረበት ለማን ተናግረን ችግራችን ማቅለል እንዳለብን ግራ የገባን ! ግና አላህ የመሰለ አምላክ እያለን ሰውን ማሸት የለብንም ሰበቡን አድርሰን "ተስፋችንን እሱ ላይ ... መጽናኛችን እሱ ብቻ "ይሁን ያኔ ብዙዎቹ የህይወት ጨለማ ክፍሎች በብርሃን ይሞላሉ🌅።
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

🫀🧠 ቁርአን ሲያናግረኝ part 44 እኔ:- "አላህዬ... የዚህ አለም የትግልና የዱንያ ሩጫ አላስቆም አለኝ። የዕለት ተዕለት ስራው፣ ንግዱ እና የገንዘብ ፍለጋው አእምሮዬን ሞልቶት ከእነሱ ጋር ስንከራተት አንተን ማስታወሻና ማምለኪያ ጊዜዬን እየቀማኝ ነው። ቆይ አላህዬ... በዚህ ሁሉ የዱንያ ጫና ውስጥ ሆኜ እውነተኛ ስኬታማ ሰው መሆን የምችለው እንዴት ነው? 🥹💔" ቁርኣን:- رِجَالٌۭ لَّا تُلْهِيهِمْ تِجَٰرَةٌۭ وَلَا بَيْعٌ عَن ذِكْرِ ٱللَّهِ وَإِقَامِ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءِ ٱلزَّكَوٰةِ ۙ يَخَافُونَ يَوْمًۭا تَتَقَلَّبُ فِيهِ ٱلْقُلُوبُ وَٱلْأَبْصَٰرُ "አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የኾኑ ሰዎች (ያጠሩታል)፡፡" (አን-ኑር: 37) ተደቡር አላህ ስራ አትስሩ፣ ንግድ አታድርጉ አላለም፤ ነገር ግን የዱንያው ሩጫና የገንዘብ ጥረቱ ከዋናው የህይወት አላማህ አውጥቶ እንዳያታልልህና እንዳያስቀርህ ያስጠነቅቅሃል። እስኪ አያቷን በአጭሩ ተደቡር እናድርጋት፦ «رِجَالٌۭ لَّا تُلْهِيهِمْ تِجَٰرَةٌۭ وَلَا بَيْعٌ» "ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ሰዎች..." እውነተኛ እና ጠንካራ ስብዕና ያላቸው ሰዎች በስራቸውና በቢዝነሳቸው ቢዚ ቢሆኑም፣ ለፈጣሪያቸው ያላቸውን ቦታ በፍጹም አይረሱም። ስራቸው ከአላህ ማስታወሻና ከመስገድ አይከለክላቸውም። عَن ذِكْرِ ٱللَّهِ وَإِقَامِ ٱلصَّلَوٰةِ "አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ..." አዛን ሲል የስራህን ሊንክ Pause አድርገህ ከጌታህ ጋር ኮኔክት ማድረግህ ያንተን የልብ ሰላም እና የስራህን በረካ ያበዛዋል። يَخَافُونَ يَوْمًۭا... "ቀንን የሚፈሩ የኾኑህ..." ዓይናቸው ያለው ጊዜያዊው ጥቅም ላይ ሳይሆን፣ ልቦችና ዓይኖች በሚገለበጡበት ትልቅ ቀን ላይ ነው። የመጨረሻው አላማቸው የአላህ ውዴታ ነው። ስለዚህ ወንድሜ... ዱንያን በእጅህ ያዝ እንጂ ልብህ ውስጥ አታስገባት! ንግድህንና ስራህን አክናውን፣ ግን ሶላትህና የአላህ ማስታወሻህ አይበላሽ። የስራህ በረካ የሚጨምረውና ልብህ እፎይ የሚለው ከጌታህ ጋር ያለህን ኮኔክሽን ስታጠነክር ብቻ ነው!
በርታልኝ የኔ ወንድም🤌
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ኑሩ ሰባህ✨
ያሳሰበብህን፣ የጨነቀህንና ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ሁሉ ለአላህ አስረክበህ እረፍት አድርግ። አላህ ያቀደልህ ነገር አንተ ካቀድከው በላይ ውብ ነው።
ከእድገት ማዶ🌱
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ሀላል ፍቅርን...ከ ሀራም ግንኙነት ርቀህ ፣ ልብህን ለ አላህ አስረክበህ ጠብቅ። የተፃፈልህ ሰው አይሸሽም ፣ ጊዜው ሲደርስ በሀላል መንገድ ይመጣል 🤌 ከ አላህ የተገኘ ፍቅር ልብን አያሳዝንም ፣ እንደ ኢባዳ ይሆናል ።
አላህ ሆይ ሀላል የሆነውን አቅርብልን ሀራም የሆነውን ከኔ አርቅልን 🤲
@Quran_post18

አላህ ማለት ነስር ያጣ የመሰለን ሓጃችንን ኩን ብቻ ብሎ የሚረታ….በአንድ ቃሉ ያልነበረውን በነበር ውስጥ የሚያስገኝልን ሀያል ጌታ ነው። አብሽሩልኝ🤍
ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

✏ ኢሊፍ ስለ ረሱል ሁብ... 💔 〰 ልብ የሚሰብር ብቸኝነት፣ የከበደ ሀዘን በጠላበት ወቅት... የውጭ ጋሻቸው የነበሩትን አጎታቸውን አቡ ጣሊብን በሞት ተነጠቁ፤ ብዙም ሳይቆዩ ደግሞ የውስጥ መጽናኛ
✏ ኢሊፍ ስለ ረሱል ሁብ... 💔  〰 ልብ የሚሰብር ብቸኝነት፣ የከበደ ሀዘን በጠላበት ወቅት... የውጭ ጋሻቸው የነበሩትን አጎታቸውን አቡ ጣሊብን በሞት ተነጠቁ፤ ብዙም ሳይቆዩ ደግሞ የውስጥ መጽናኛቸው፣ እንባቸውን የምታብሰው፣ በጭንቅ ሰዓት «አላህ አያዋርድህም» እያለች የምታረጋጋቸው ውድ ባለቤታቸውን እናታችን ኸዲጃን (ረ.ዐ) አጡ። ያ አመት በታሪክ «ዓመተል ሑዝን» (የሀዘን አመት) ተብሎ ተሰየመ!   ልብ በሉ... ሰው በተከታታይ ሁለት ክፉኛ የሚወዳቸውን ደጋፊዎቹን ሲያጣ ተስፋ ይቆርጣል፣ ከአለም ይገለላል፣ ይሰበራል። ሀቢቡና ግን ልባቸው በሀዘን ተሰባብሮ፣ እንባቸው እንደ ጅረት እየፈሰሰም...  ~ ለራሳቸው ሀዘን አልተቀመጡም! ~ ህመማቸውን እያስታመሙ ወደ ጧኢፍ ተጉዘው በድንጋይ ተወገሩ፣ ደማቸው ፈሰሰ!  ይሄ ሁሉ ስቃይና መከራ ለማን ነበር? እኔና አንተ/አንቺ ዛሬ ያለ ምንም ድካም «ላ ኢላሀ ኢለላህ» እንድንል፣ ይህ ንፁህ እስልምና በእጃችን በሰላም እንዲደርስ እኮ ነው! እሳቸው ተርበው፣ ተሰድበው፣ ተደብድበውና የነፍስ ሀዘን እያቃሰቱ እኛን ከጀሀነም እሳት ለማዳን ለሊት ከቀን ደከሙ። 😭  «ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱለላህ!» 🤍  እሳቸው በዛ ሁሉ የሀዘን መዓበል ውስጥ ሆነው እኛን ዲን ለማድረስ ሳያቆሙ ሲደክሙ... ታዲያ እኛ ዛሬ በሰላም፣ በምቾት እና በድሎት በጁምአም ቀን ላይ ሆነን የእሳቸውን ስም ሳናሰማ እንውላለን 🌿 በረሱል (ﷺ) ላይ ሰላዋት በማውረድ ውለታቸውን እናስታውስ፦  📿اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

የሆነ ቀን አይናፍቃቹም .... ለጌታቹ ታዛዥ ባሪያ በፈርድ በሱና መሽጉል የተራጋጋ ሰው የልብ ሰላም ያለው 🤍 ከልቡ ፈገግግ የሚል 😊 ወንጀልን የራቀ ሀዘን ማይሰማው የቁርአን ሰው ብቻ ምርጥ ህይወት እይናፍቃቹም!?🥹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ኑሩ ሰባህ 🩵
〰 አይናችም እውር ቢሆን ፣መስማት ባንችል ፣መረመድ ብያቀተን ፣ እጆቻችን ሽባ ቢሆኑ ፍላጎቶቻንን መግለፅ ቢሳነን በሰላም አየር ማስገባት ማስወጠት ብንከለከል ይህች ሀያት ለኛ ከባድ ነበርች ግን የአላህ ኒእማ ተቆጥሮ የሚያልቅ አደለም! አልሀመዱሊላህ እያመፅነው ለሚትታገሰን ጌታ 🥹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ሰዎች ባለፈ ማንነታቹ አልተናገሯቹም 💔 ?? 〰አዎ ትላንት ወንጀልን ተዳፍረን ነበር ፣ብዙ ድነበር አልፈን ነበር ፣ልባች ደርቆ ከመልካም ታውረን ነበር .... ወንጀልን አግበስብሰን 🥹 ~ግና አሁን ሁሉም ተቀየረ የትላንት ማንነታችን ትላንት ነው! ዳግም ላይመለስ ሄዷል ሁሉም ገብቶን ወደ ጌታችን ደጃፍ እየተሽቀዳደምን እሱም በመምጣችን ተቀብሎ ተደስቶ ትላንታችን ይቅር ብሎን ሳለ ታዲያስ ስለምን ብላቹ ዛሬ ላይ ስለትናት እያነሳቹ ምታሸማቁን ጌታችን አንኳ ያላደረገው 😔 አደብ ያስፈልጋል ወላሂ እኛ ቢሳካልን እኮ የትላንት ሀያታችን ከእድሜያችን ባነሳነው ❤‍🩹 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

🍂አንዳንድ ቀናት ንዴት ፣ሀዘን ጭንቀት ሀሳብ ይሆናሉ የሆነ ቀናት ደሞ በማልቀስ ብቻ የምናሳልፋቸው ቀናት አሉ ግን ይቺ ህይወት ሆነችና ስለ ሁሉም ነገር አልሀምዱሊላህ ❤‍🩹 እያልን ህመማችንን ዋጥ ማድረግ አለብን! ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ [....................]
Anonymous voting

ኑሩ ሰባህ 🩵
〰 ምን አለ ወንጀል ስነስራ ፍርሃታችን ገዝፎ ጌታችን ማመጽ በተውን.... ቅጣቱን በፈራን 🥹 ይሁሉ ሰላም ማጣት ጭንቀት ሀዘን ሁሉ ባላገኘን! ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat

ቆይ መች ነው እነደማስበው አይነት ሰው ምሆነው?😔 〰ሁላችንም በውስጣችን የምነስለው ማንነት (ስራ ትመርት ላይ ጎበዝ ፣ዲኑ ላይ ጠንካራ ቁርአን ሚያዘወትር ፣ወንጀል ሚርቅ ፣ሰኞ ሀሙስ ሚፃም ለይል የሚነሳ ለቤተሰቦች ሰናይ መልካም ሰው "አስቦ ሚያወራ" ፣ ዱኣ ላይ ጎበዝ፣አዋብ የሆነ ....) ታዲያ ያን ማንነት እንድንሆነ ምን ከለከለን ?🥹 🤲🏻ኢላህዬ አንተ ወላሂ የውስጥ አዋቂ ነህ ሰበብያውን በማድረስ ያሰብ ነው እንድንሆነ አንተው እርዳን ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ 🌱@Binaulzat