ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Открыть в Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
195
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-730 дней
Архив постов
ጥያቄ፦ተሀጁድ እና ተራዊህ በአንድ ሌሊት መስገድ እንደት ይታያል?? 🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አቡ ሓቲም

"ሐቀኛውና ባጢል ያነገበውን ለይተህ እንድታውቅ የሚያስችልህ ጠቃሚ ሸሪዓዊ ዕውቀት ብቻ ነው። ብዙ ሰዎች ከሸሪዓዊ ዕውቀት ከመራቃቸው እና ችላ ከማለታቸው የተነሳ ሲዘበራረቁ ዐይተናል። ድምጹን ከፍ አድረጎ ጯሂ ሁሉ ተከታይ ሆነዋል።" ሸይኽ ሙቅቢል ረሂመሁላህ [ቀምዑ አልሙዓኒድ(2/550)]

"ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው የፆመኛውን ያህል ምንዳ አለው።" የአላህ መልእክተኛ ﷺ

በጀነት የተበሰሩ አስሩ ሶሓባዎች
በጀነት የተበሰሩ አስሩ ሶሓባዎች

የምእመናን እናቶች
የምእመናን እናቶች

ኻሚነኢ በሚዛን ላይ ~ ይህንን ማስታወሻ ለመፃፍ የተገደድኩት ሰውየው ሶሐቦችን አይሳደብም እያሉ የሚከላከሉ ስላየሁ ነው። በዚህና መሰል አካሄድ ከነዚህ አካላት የሚከላከሉና ለህዝባችን እንደ ጀግናና ጤነኛ አድርገው የሚያስተዋወቁ እስካሉ ድረስ ስለ ጉዳዩ መናገራችን ይቀጥላል። በቅርቡ አንዱ ከሺ0 ውስጥ ሶሐቦችን የሚሳደቡት ጥቂቶቹ ናቸው ብሎ አይቻለሁ። ይሄ ግልፅ ውሸት ነው። የሺዐ ታላላቅ ዑለማኦች በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩትን በቅርቡ አሳልፌያለሁ። ወደተነሳሁበት ስመለስ፦ 1. ኻሚነኢ በተጨባጭ ሶሐባ ይሳደባል :- በዚህ ላይ አንዳንዶችን የሸወዳቸው - ምናልባት ተሸወደው ከሆነ - የሆነ ጊዜ ኻሚነኢ ዓኢሻን አትሳደቡ የሚል ይዘት ያለው ንግግር አውጥቶ ስለነበር ነው። ስለ ሺዐዎች እምነት የሚያውቅ ሰው በእንዲህ ዓይነት ነጠላ ንግግር ብቻ አይሸውድም። ሁሌም መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር ከሺ0 መሰረታዊ እምነት ውስጥ አንዱ ተቂያ እንደሆነ ነው። ተቂያ ማለት አቅም ደከም ሲል፣ የማይመች ሁኔታ ሲገጥም ወይም አስፈላጊ ብለው ሲያምኑ እምነታቸውን ለመደበቅ ውሸትን የሚጠቀሙ መሆናቸው ነው። ይሄ የሚፈቅዱት ብቻ ሳይሆን የሃይማኖታቸው ዋና ክፍል ነው። መረጃ ልጥቀስ። ጀዕፈሩ ሷዲቅ እንዲህ ብሏል ይላሉ፦ "إنَّ تسعة أعشار الدِّين في التقيَّة، ولا دين لمن لا تقيَّة له" ​"ዘጠኝ አስረኛው (90%) ሃይማኖት ያለው በ'ተቂያ' (አስመስሎ በማቅረብ) ውስጥ ነው፤ ተቂያ የሌለው ሰው ደግሞ ሃይማኖት የለውም።" "التقيَّة ديني ودين آبائي، ولا إيمان لمن لا تقيَّة له" "ተቂያ ሃይማኖቴ የአባቶቼም ሃይማኖት ነው። ተቂያ የሌለው ሰው ኢማን የለውም።" [ኡሱሉል ካፊ፣ ኩለይኒ፡ 2/217] በዚህ መልኩ መዋሸትን እምነታቸው ያደረጉ ሰዎችን ለመስለሐ ሲሉ የሚናገሩትን ከመርሃቸው ወጣ ያለ ንግግር ከቁም ነገር መውሰድ አይገባም። ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ " الرَّافِضَة أَجْهَلُ الطَّوَائِفِ وَأَكْذَبُهَا وَأَبْعَدُهَا عَنْ مَعْرِفَةِ الْمَنْقُولِ وَالْمَعْقُولِ وَهُمْ يَجْعَلُونَ التَّقِيَّةَ مِنْ أُصُولِ دِينِهِمْ ، وَيَكْذِبُونَ عَلَى أَهْلِ الْبَيْتِ كَذِبًا لَا يُحْصِيهِ إلَّا اللَّهُ ، حَتَّى يَرْوُوا عَنْ جَعْفَرٍ الصَّادِقِ أَنَّهُ قَالَ : التَّقِيَّةُ دِينِي وَدِينُ آبَائِي ، و " التَّقِيَّةُ " هِيَ شِعَارُ النِّفَاقِ ؛ فَإِنَّ حَقِيقَتَهَا عِنْدَهُمْ أَنْ يَقُولُوا بِأَلْسِنَتِهِمْ مَا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ وَهَذَا حَقِيقَةُ النِّفَاقِ " . "ራፊዳዎች (ሺዓዎች) ከሁሉም አንጃዎች ይልቅ በጣም መሃይም፣ ውሸታሞች እና ዘገባዊም ሆነ አዕምሮአዊ እውቀትን ከማወቅ በጣም የራቁ ናቸው። እነርሱ 'ተቂያን' (እውነታን መደበቅን) ከሃይማኖታቸው መሠረቶች አንዱ ያደርጋሉ። በአላህ እንጂ ሌላ ሊቆጥረው የማይችልን ውሸት በነቢዩ ቤተሰቦች ላይ ይዋሻሉ፤ እንዲያውም ጃዕፈር አል-ሳዲቅ 'ተቂያ የኔና የአባቶቼ ሃይማኖት ነው' ብሏል ብለው እስከማውራት ይደርሳሉ። 'ተቂያ' ደግሞ የን F ^ ቅና ምልክታ ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ዘንድ እውነታው በልባቸው የሌለውን በምላሳቸው መናገር ነውና፤ ይህም ፍጥጥ ያለ ን F ^ቅና ነው።" [መጅሙዑል ፈታዋ፡13/263] ወደ ኻሚነኢ ስንመጣም በተግባር ሶሐቦችን በን F ^ቅና፣ በሸፍጥ፣ በክህ ^ደት ይወነጅላል። ይሄው በያይዝኩት መረጃ ላይ ዝርዝሩን ማየት ትችላላችሁ። ሶሐቦችን የዐሊይን ኺላፋ የሰረቁ ናቸው እያለ ነው። 0ብዱራሕማን ብኑ ዐውፍን ደግሞ በሴራና በአታላይነት ይወነጅላል። ሶሐቦችን የሚሳደብን ሰው ተግባሩን ገልፆ ያወድሳል። በኑ ኡመያን ባጠቃላይ፣ 0ብዱላህ ብኑ ዙበይርን የሚሳብበት መረጃው ላይ ተያይዟል። እነዚህ ነውረኛ ተግባራቱ በራሱ ኪታብ ላይ መኖራቸው ከተረጋገጠ በኋላ ኻሚነኢ ሶሐባ አይሳደብም ማለት ምንድነው ስሙ? 2ኛ. ኻሚነኢ ሙስሊሞች የጨፈ^ ጨፈ ነው። በሶሪያ፣ በዒራቅ፣ በሊባኖስ፣ በየመን ጠርዘኛ ቡድኖችን አደራጅቶ እልፍ አእላፍ ሙስሊሞችን ያስጨረሰ ነው። ይሄ ጥፋቱ ቀላል ሆኖ ነው ለሱ የምትከራከሩት? 3ኛ፦ ኻሚነኢ እንደማንኛውም የሺዐ መሪ አህለ ሱና ሙስሊሞችን ከኢስላም የሚያስወጣ ነው። አህለ ሱናን የየዚድ ጦር ብሎ ሲገልፅ ነበር። የዚድ እነሱ ዘንድ ሙስሊም አይደለም። ከዚህም ባሻገር "በሶሪያ የምናካሂደው ውጊያ በኢስላም እና በክህ ^ ደት መካከል የሚደረግ ውጊያ ነው" ብሏል። ልብ በሉ! አንደኛ ሶሪያ ላይ ከበሻር አልአሰድ ጎን ሆነው እየተዋጉ እንደሆነ እየገለፀ ነው። ሁለተኛ በነሱ እየተጨ ^ፈጨፉ ያሉት ሶሪያውያን ሙስሊሞች አይደሉም እያለ ነው። አንተ ለሱ ሞት ታዝናለህ፣ ሽንጥህን ገትረህ ትሟገታለህ። እሱ ግን የየዚድ ተከታይ ብሎ እንደ ሙስሊምም አይቆጥርህም። እነዚህን የሶሐባ ጠላቶች የሚመለከት በፃፍኩ ቁጥር የምትከፉና በውስጥ እየመጣችሁ የምትሳደቡም አላችሁ። ሺዐን እያወደሱ ለህዝባችን የሚያስተዋውቁ አካላት ተግባር ሳይጎረብጣችሁ የነሱ መጋለጥ ካመማችሁ ምንም ማድረግ አልችልም። እንዲህ አይነት ሁኔታ እስካየሁ ድረስ መፃፌ ይቀጥላል ኢንሻአላህ። (ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 19/1447) = የቴሌግራም ቻናል:- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ ~ ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ። * አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦ يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ “አንተ ልቦችን ገለባባጭ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ።” * በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ. “አንተ የጂብራኢል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁንም የቅርቡንም የምታውቀው አላህ ሆይ!ባሮችህ ሲወዛገቡበት በነበረው ነገር አንተ ትፈርዳለህ፡፡ ከሐቅ ለሚወዛገቡበት ነገር ምራኝ፡፡ አንተ የፈለግከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመራለህና፡፡” [ሙስሊም] * ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት። اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ "አላህ ሆይ! እኔ ጀነትን እለምንሀለሁ። ከእሳትም ባንተ እጠበቃለሁ።" * የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦ اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي. "አላህ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ።” * ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ "አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ አንተን በሚመስገን እና አንተን ባማረ መልኩ በመገዛት ላይ አግዛኝ።" * ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል። * ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦ اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ. "አላህ ሆይ! በዱንያም መልካምን፣ በኣኺራም መልካም ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።" = * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

ብረትን ማን ሊያጠፋው ይችላል?ተባሉ "የራሱ ዝገት"

አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡(71الأحزاب)
አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡(71الأحزاب)

ጥቂት ነጥቦች ስለ ኢዕቲካፍ! ~ * ትርጓሜው፦ ለአላህ ዒባዳ ለመፈፀም በማሰብ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው። * ብይኑ፦ በቁርኣን በሱና የተረጋገጠ ሙስተሐብ (የተወደደ) ዒባዳ ነው። ስለት ለተሳለበት ሰው ግዴታ ይሆናል። አዕቲካፍ ለሴቶችም የተፈቀደ ነው። * አላማው፦ ልብንም አካልንም ስብስብ አድርጎ በዒባዳ መጠመድ ነው። ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ከትርፍ ወሬ፣ ከትርፍ ቅልቅል፣ ከትርፍ እንቅልፍ መቀነስ ይገባል። * ጊዜው፦ አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ በረመዷንም ይሁን ከረመዷን ውጭ መፈፀም ይቻላል። በላጩ ጊዜ ግን ረመዷን ነው። ከረመዷንም የመጨረሻዎቹ አስሮቹ የበለጡ ናቸው። * ቦታው፦ ለወንድም ይሁን ለሴት መስጂድ ውስጥ ብቻ ነው። * የጀመረ ሰው መጨረስ ግዴታ ነው? የሚያስገድድ ማስረጃ የለም። * ዝቅተኛው ጊዜ ምን ያህል ነው? ገደብ የለውም። ያሰኘውን መጠን ያክል ነይቶ መቀመጥ ይችላል። * ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ለመፀዳዳት መውጣት ይችላል። የታመመን ለመጠየቅ፣ ጀናዛ ለመሸኘትና መሰል ጉዳዮች ግን አይወጣም። ግንኙነት፣ ግብይት፣ ስራ መስራት አይቻልም። ኢዕቲካፍ ላይ እያለ የታመመ ሰው መታገስና መቆየት የሚችል ከሆነ መውጣት የለበትም። * የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር መግባት የፈለገ መቼ ይጀምር? የረመዷን 20ኛው ቀን ከመጥለቋ በፊት ቢሆን መልካም ነው። * የሚወጣበት ደግሞ ረመዷን ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ሲገባ ነው። ወላሁ አዕለም። = IbnuMunewor

ወሩ በፍጥነት እየሄደ ነው! ~ ወሩ በገፋ ቁጥር መስጂዶች እየጎደሉ ነው። መሆን የነበረበት ረመዳን በቀነሰ ቁጥር ትጋታችን ሊጨምር ነበር የሚገባው። የኸይር ገበያ ፀሐዩ ሲያዘቀዝቅ ይበልጥ ጉጉት መጨመር ሲገባ እኛ ግን መቀዛቀዛችን ነው እየባሰበት ያለው። ኢብኑ ረጀብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ "ወራችሁ መጉደል ይዟል። ስለሆነም ራሳችሁን ልክ መጠናቀቂያ ላይ እንዳላችሁ በማሰብ ስራ ጨምሩ። ምክንያቱም እያንዳንዱ ወር ምትክ ይኖረዋል። የረመዳን ወር ግን ለሱ ከየት ምትክ ይኖራችኋል?!" [ለጣኢፉል መዓሪፍ፡ 183] ደግሞም እንወቅ! ወደ መጨረሻው አስር እየገባን ነው። ይሄ ማለት የወሩ በላጩ ክፍል ማለት ነው። ይሄ ማለት ለይለተል ቀድር የሚገኝበት ክፍል ማለት ነው። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዳለችው ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመጨረሻው አስር ሲገባ እጅግ በተለየ መልኩ ትጋታቸው የሚጨምርበት፣ ቤተሰባቸውን ጭምር የሚቀሰቅሱበት፣ ሌሊቱን ከእንቅልፍ ርቀው በዒባዳ የሚነቁበት ክፍል ነው። = IbnuMunewor

أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْمُفْسِدُونَ وَلَكِن لَّا يَشْعُرُونَ (البقرة12) ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
أَلَا إِنَّهُمْ هُمُ الْمُفْسِدُونَ وَلَكِن لَّا يَشْعُرُونَ (البقرة12) ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡

ኢብኑል ቀዪም ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦ "የፅናት ባለቤቶች ከመጀመሪያው የዒባዳ እንቅስቃሴያቸው ይልቅ ፍፃሚያቸው ላይ እጅግ ጥረትን ይጨምራሉ" [መዳሪጁ ሳሊኪን (3/118)]