✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Открыть в Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
194
Подписчики
Нет данных24 часа
-27 дней
-530 дней
Архив постов
ነቢያዊ ምክር!
ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿يَا عَائِشَةُ لَا تَرُدِّي الْمِسْكِينَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ، يَا عَائِشَةُ أَحِبِّي الْمَسَاكِينَ وَقَرِّبِيهِمْ ؛ فَإِنَّ اللَّهَ يُقَرِّبُكِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ﴾
“ዓኢሻህ ሆይ! ምስኪንን በባዶ አትመልሺ። የተምር ክፋይም (ስጥተሽ ) ቢሆን እንጂ። ዓኢሻህ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ። አቅርቢያቸውም። አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።”
ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 235
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ለማን ነው የምትሞተው?
~
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎም አሁንም ትግል ትግል የሚሉ አሉ፣ ከግንድ ያታግላቸውና። ወጣት ሆይ! ይሄንን በህዝብ፣ በብሄር ስም እየማለ ወደ ጦርነት የሚጠራህን፣ ለእልቂት የሚጋብዝህን የደም ነጋዴ አትስማ። ለእናትህ ኑር። እናትህ አንተን አጥታ የምትሆነውን መሆን በአይነ ህሊናህ ተመልከታት። አታሳዝንም ወይ? ለራስህ ኑር። ለቤተሰብህ ኑር። ለማን ነው የምትሞተው? ያገራችን ፖለቲከኛ ተቆርቋሪ መስሎ እየሰበከ ህዝብን ከህዝብ እያጋጨ ለራሱ ስልጣንና ጥቅም አንተን ቤዛ የሚያደርግ መ ~ ሰ ~ ሪ ፍጡር ነው። ካንተ በፊት ካለቁት ትምህርት ውሰድ። ዛሬ ማን የሚያስታውሳቸው አለ? ቤተሰቦቻቸውን ማን ዞሮ ያያቸዋል? ከጦርነቱ መጨረሻ ላይ ሲማግድህ የነበረው አካል የስልጣን ወንበር ላይ ሲቀመጥ አንተ ምናልባት ከተረፍክ የሆነ መያድ ጋር ተነጋግሮ ዊልቸር እና ክራንች ነው የሚስሰጥህ። ለኣኺራህ አትፀድቅ፣ ለዱንያህ አያልፍልህ። ለማን ነው የምትሞተው ታዲያ?
ይልቅ ዞር ዞር ብለህ ሰርተህ ለመልለወጥ ጣር። ኑሮህን አሸንፍ። ራስህን ቻል። ቤተሰብህን አግዝ። ለራስህ፣ ለቤተሰብህ ስትል እወቅበት። ለገዛ ወገኑ የሞት ድግስ እየደገሰ የሚጋብዝ የማንም ጣ.ሳ ራ ስ መጫወቻ አትሁን። በቃ በለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አቡ ሙዓዝ (Abu muaz)
የቢላል መስጂድን ፕሮጀክት ያቀፈ ፒዲ ኤፍ
አስራጩልን ምንም እንኳ ታዋቂ ሰው ባይኖርበት የአሏህ ቤት ነው ተውሒድና ሱና ነው የሚተላለፍበት አጅር ታገኙበታላቹህ ሼር አርጉልን ለሰወች ተራሽ ይሁንልን ሱና፣ተውሒድ ቢሄር የለውም
ምን አለ ባለ ቻናል፣ግሩፖች ሼር፣ፎርዋርድ አርጋቹህት ተደራሽ ቢሆንና ቢገነባ መቸም አሕባሽ ሸር አያደርግልንም ።
t.me/geradobilalmesjid
Repost from فتاوى الشيخ صالح الفوزان حفظه اللّه
🛑 حكم خـروج المـرأة دون إذن زوجهـا إذا كان مسـافر و بينهما خــلاف ⁉️
الشيخ صالح الفوزان حفظه اللهhttps://t.me/alfawzan12 #شارك_وانفع_غيرك ✅
ጫት
~
ጫት የዲን፣ የጤና፣ የቤተሰብ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ህይወት፣ የሃገር እድገት ፀር ነው። በጫት የተነሳ ትውልዱ ወኔው የፈሰሰ፣ ሞራሉ የላሸቀ የወጣት ጡረተኛ ሆኗል። የጫት ሱስ ወንድም በገዛ እህቱ ላይ፣ ወላጆች በገዛ ልጃቸው ላይ፣ ጎረምሶች በገዛ ወላጆቻቸው ላይ እንዲጨክኑ አድርጓቸዋል። በሰው ፊት ተገርፈው፣ ክፉ ደግ አይተው፣ እንቅልፍ አጥተው፣ ተንገላተው የሚያገኙት ገንዘብ ከጉዳት በስተቀር አንድ ቁም ነገር ለሌለው ነገር እንደ ዋዛ መበተን የጭካኔ ጥግ ነው። በዚህ የተነሳ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ለአመታት በሰው ሃገር ደክመው ያጠራቀሙት ጥሪት እንዲሁ መና ቀርቷል። የጫት ጉዳት ከሚገለፀው በላይ የከፋ ነው።
ለችግሩ መባባስ አንዱ ሰበብ ደዕዋ ላይ ያሉ ሰዎች የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ባገናዘበ መልኩ ተገቢ ትኩረት ሰጥተው አለማስተማራቸው ነው። አሁንም በሚገባ ልንነቃ ይገባል። የወገናችን ጉዳት የሚያመው፣ ከልቡ መቆርቆር ያለው ሁሉ! በሚችለው መድረክ ሁሉ ከዚህ መርዛማ ቅጠል ሰዎችን ሊያስጠነቅቅ ይገባል። በዚህ ቅጠል የተለከፉ ወገኖችን ከሱስ ማውጣት ቢያቅተን እንኳ ቢያንስ ልጆቻቸውን በሚጠብቁበት መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ብናደርግ ቀላል ስኬት አይደለም።
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ኪታብ በተስሚዕ መቅራት ለምትፈልጉ የሱና እህቶች በሙሉ ብስራት ይዘን ብቅ ብለናል እንኳን ደስ አላችሁ !!! እያልኩ የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች ስገልፅላችሁ የዓቂዳህ ፣ የፊቂህ ፣ የሲራ እና ከሎغا የሶርፍ ናቸው
🔰 ከዓቂዳህ ኪታቦች 🔰
➡️ ኡሱሉ ሰላሳህ
➡️ ቀዋዒዱል አርበዓህ
➡️ ኹዝ ዓቂደተክ
➡️ ፊርቀቱ ናጂያህ
➡️ ኪታቡ ተውሒድ
🔰 ከፊቂህ ኪታቦች 🔰
➡️ አርባዒን ሐዲስ
➡️ ረውዶቱ አል ባዲኢን
➡️ ሹሩጡ አሶላህ
➡️ ሰፊነቱ ነጃህ
➡️ ሰፊነቱ ሶላህ
➡️ ሙኽተሶሩ ሶغር
➡️ ሹጃዓ
➡️ ባፈضል
🔰 ከሲራ ኪታቦች 🔰
➡️ ኹላሶቱ ኑሪል የቂን
➡️ ኡርጂዘቱል መዒያህ
♻️ ማሳሰቢያ ♻️
ትምህርት ቤታችን ማስተናገድ የሚችለው የተማሪ ብዛት እስከ 30 ተማሪዎች ብቻ ነው ምክንያቱም በድምጫ ስለሆነ የሚሰጠው አቅማችን እስከዚህ ብቻ ነው ስለዚህ ሳይሞላባችሁ ፈጥናችሁ ለመመዝገብ ሞክሩ
🔹የትምህርት ቤቱ ሕግ እና ደንብ 🔹
1, ወደ ት/ት ቤቱ ሲመጡ ትምህርቱን ከልብ ፈልገው መሆን አለበት
2, ሰዓት ማክበር
3, ትምህርቱ ሲሰጥ በጥሞና መከታተል
4, የቤት ስራውን በደንብ ሙራጂዓ አድርጎ መገኘት
5, መምህር ማህበር
6, እርስ በርስ መዋደድ መከባበር
7, በጥቃቅን ምክንያት አለመቅረት አሳሳቢ ጉዳይ ከገጠማችሁ አስፈቅዳችሁ መቅረት
8, ያለ ፍቃድ ከ3 ቀን በላይ የቀረ ከትምህርት ቤቱ ይባረራሉ
9, የትምህርት ቤቱን ሕግ ደንብ አለመጣስ
🔹 ትምህርቱ የሚሰጠው ከመغሪብ ጀምሮ ኢንሻ አሏህ
🔹ባይበዛም ለሸበካ የታሰበች ትንሽየ ክፍያ አለው 25 ሪያል ብቻ ነው
ከላይ በሰፈረው የተስማማ ለትምህርት ፍላጎት ያለው ሰው ሳይሞላ ፈጥነው ይመዝገቡ እንዳያልፋችሁ
➡️ ማሳሰቢያ ትምህርቱ ለሴቶች ብቻ ነው !!!
ትምህርቱ የሚሰጠው በወንድም ጀማል አሕመድ አቡ ሳዳት ነው
ለመመዝገብ በዚህ ያናግሩን ↓↓↓
@abu_sadat_jemal
💥አስተውል💥
🧣ቆንጆ ሴት ብታገባ ቆንጆ ልጆችን ታገኝ ይሆናል ውበት ጀነት አያስገባም እወቅ በተርቢያ በዲን ግንዛቤ የተገነቡ ልጆች ግን አደብ ባላትና ዲን ባላት ሴት እንጅ ላታገኝ ትችላለህ ሞዴል አግብተህ ሞዴል እንዳትወልድልህ !!
💍=====የትዳር ትልቁ አላማ ራስህን ወደ አላህ የሚያቃርብ አጋዥ ማግኘት ነው።
ዐልይ ረዲየላሁ ዐንሁና እና ፋጢማ ረዲየላሁ ዐንሀ _በተጋቡ ማግስት የአላህ መልዕክተኛ (ሰላለሁ ዐለይሂይ ወሰለም) ወደ ቤታቸው በመሄድ ዐልይን ባለቤትህን እንዴት አገኘሀት ?
ሲሉ ጠየቁት እርሱም አላህን_ ለመገዛት ጥሩ ረዳት ሆና አገኘኋት ብለው መለሱ. ።
💍ትዳርን አላህን የማመፅ ሳይሆን እረሱን የማፍቀርና የመገዛት ምርጡ መንገድ መሆኑን ተገንዘብ !!!
➪አግባ......
ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ
እንዲህ ይላል: -
🌹« ለመኖር አስር ቀናቶች ቢቀሩኝና ከአስር ቀናቱ እንዳለቁ እንደምሞት ባውቅ እናም (ሚስት) ለማግባት ጊዜ ባገኝ ፊትናን ፈርቼ አገባ ነበር ።»
[ሰዒድ ቢን መንሱር አስሱነን 493]
ኢትዮጲያ ላሉ ጡላበል ኢልሞች ምክር ቢኖረኝ
በህጋዊ የመን ሂዱና ከስር በምጠቅስላችሁ መራኪዞች እውቀትን ቅሰሙ!
1, ቦታውን በዐደን ከተማ አቅራቢያ በለህጅ ሙሀፈዛ ፊዩሽ በምትባል አካባቢ ያሳረፈ ዳሩል ሀዲስ “ፊዩሽ” አንጋፋው የሸይኽ ሙቅቢል ተማሪና ሀጁሪን ጨምሮ የመን በአሁን ሰዐት ላሉ ኡለሞችነኣ መሻይኾች አስተማሪና ሸይኽ የሆኑት የሸይኽ አብደረህማን አል አደኒይ መርከዝ ነው።
ይህን መርከዝ የመን ካሉ ከሌሎች የሱና መራኪዞች የሚለየው ነገር፡
#አንደኛ: አከባቢው ባለው የፀጥታ መረጋጋት
#ሁለተኛ: “ፊዩሽ” የተሰኘችው መንደር ሰፋ ያለች መንደር ከመሆኗ ጋር እንደ ስሟ ሁላ ሰዎቿም በመርከዙ ህግ ስነስርዐት የምትተዳደር በመሆኗ ሌሎች ቦታ የማይገኝ ስነስርዐት እዛ የሚገኝ መሆኑ ለዩ ያደርጋታል።
* በመንደሯ ውስጥ ያሉት ነዋሪዎች 100% በሚባል ወይም በቀረበ መልኩ ሰለፍይ ተማሪዎች በመሆናቸውና ከአላህ በታች መርከዙ በሚያደርገው ጠንካራ ቁጥጥር ከስር የሚዘረዘሩት ተግባሮቶች በ 0% የሚገኙ መሆናቸው እጅግ የበለጠ ልዩ ያደርገዋል።
ለምሳሌ፡ በመንደሯ ውስጥ፡
1, በግልፅ ሸሪዐን የሚፃረር መጠጥ ቤትም የሆነ የንግድ ቦታ የለም።
ለምሳሌ፡
የመን የምትገኝ መንደር እንደመሆኗ፡
- ጫት መቃም
- ሲጋራ ማጬስ
እና የመሳሰሉትን እዛ መንደር ስትገባ የመን መሆንህን ትረሳለህ በተዐምር ቃሚና አጫሽ አታገኝም።
2, ሴት ልጅ ፊቷን ሳትሸፈን ወይም ያለ ኒቃብ መውጣት አትችልም።
ይህ ብቻ ሳይሆን በየሱቁና በየመንገዱ በየ ንግድ ቦታው ተጋፍታ አረ የምን ተጋፍታ ተገኝታ ሁላ ስትገዛ በተዐምር
በመንደሯ ውስጥ አትመለከትም። መብቷን ለመጋፋት ሳይሆን መብቷንና ክብሯን ለመጠበቅ ሲባል ወንዶች ተሯሩጠው እሷን እንዲኸድሙ ብቻ የተደረገ ትልቅ ለሴቶቻችን የተደረገ ክብር ነው።
3, አዛን ከተባለ ቡሐላም ሆነ ከየ ሰላት አውቃቱ ቡኋላ መንደሯ ውስጥ ገባያ ቦታዎች ተከፍተው ማግኘት ዘበት ነው። ከተገኘም ይቀጣል ለዛም ሲባል በመንደሯ ውስጥ በሚገኙ ሰፈሮች ላይ ከአዛን በፊት الصلاة الصلاة
ይበቃል ወደ ሰላት ወደ ሰላት እያሉ በማይክ የሚጣሩና የሚያስታውሱ መኪናዎችን መርከዙ ይልካል።
እና ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ እንኳን የመን ላይ አለም ላይ በሌሎች ቦታ ሰምቼ የማላውቀው ድንቃድንቅ ነገሮችን የያዘች ድንቅ መንደር ነች።
ነገር ግን ፡ ሁሉንም ካወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል እንደተባለው ስለመንደሯ በዚሁ ልቋጨው።
እስካሁን ሳወራ የነበረው በመርከዟ ስም ስለተሰየመችው ስለመንደሯጂ ስለራሷ ስለመርከዟ አይደለም!
ስለመርከዟማ ከኔ በላይ እዛው ያለው ሰው ሻይ ቡና እያለ ሰፊ ጊዜ ወስዶ ካላጫወታችሁ እኔ በዚህች ደካማ ቀለሜ ዘርዝሬ አልዘልቃትም።
ግን ትንሽ ይነገረን ካላችሁ ትንሽ ልበላችሁ፡
* ዳሩል ሀዲስ ቢል ፊዩሽ*
_ ቀደም ብዬ እንደነገርኳችሁ መርከዟን የመሰረቷት ታላቁና አንጋፋው የሸይኽ ሙቅቢል ተማሪ የሆኑት አብደረህማን ቢን መርዒ አል-አደኒ ሲሆኑ በድካሜ ስለሳቸው ለመናገር ቀለሜም ሆነ ቦታዬ በቂ ስላልሆነ ስለሳቸው ትውልድ ጀምሮ እስከ አሰቃቂ አሟሟታቸው ድረስ በሚገርም ሁኔታ ከስር በማስቀምጠው ሊንክ ሸይኻችንና አስተማሪያችን የሆነው የሳቸው አንጋፋ ደረሳ አቡ ፋሪስ አብደረህማን አስ-ሰቃፍ ( عزاؤنا في شيخنا عبدالرحمن بن مرعي العدني رحمه الله)
وقفات - وعبر - وعظات
وفضح مؤامرة الاغتيالات
በሚል ርዕስ የፃፋትን ኪታብ ያንብቡ!
https://t.me/Yemen_Kutub/822
እሳቸውም በጠማማ ኸዋሪጆች ከተገደሉ ቡኋላ የሳቸውን ቦታ የራሳቸው ወንድም የሆኑት የሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን ፣የሸይኽ ሙቅቢል እና የሌሎች በርካታ የሳዕድ ኡለሞች አንጋፋ ተማሪ የሆኑት አል-ኡሱሊይ አል-ፈቂህ ብለው ኡለሞች የሚቀፅሏቸው ሸይኻችንና አብዱሏህ ቢን መርዒ አል-አደኒ ተረከቡ።
እስካሁንም ድረስ ከአንጋፋ ትላልቅ የሸይኽ ሙቅቢል ተማሪዎችና የራሳቸው ተማሪዎች ጋር በመሆን መርከዟን በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ አማናቸውን ተወጥተው ከተለያዩ ሀገራት በሺዎች የሚቆጠሩ መሻይኾችን አውጥተው አስጠቅመው እንደላኩ እዛው ያለ ተማሪ ምስክር ይሆናቸዋል።
* መርከዝ ፊዩሽ ላይ ያሉ ተማሪዎች ብዛት ስንት ነው?
👌መርከዛችን ፊዩሽ ላይ ያሉ የአስተማሪዎች ብዛት ከ 1200 በላይ………
👌ፊዩሽ ላይ ያሉ የተማሪዎች ብዛት ከ18000ሺ በላይ
🎙ሸይኻችን አብደላህ አል መርዕይ
- ከራሳቸው አንደበት ድምፃቸውን ለመስማት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://t.me/ibnuidris_teppi/2411
* ፊዩሽ ላይ የሚሰጡት ደርሶች ምን ምንድን ናቸው?
- በመጀመሪያ من باب النصيحة ከኢትዮ ወደ ፊዩሽ የሚመጣ ሰው ቋንቋ ትምህርትን ለሁለት ነገር ሲባል እዛው ጨርሶ ቢመጣ የተሻለ ነው።
አንደኛ: የሀገራችን የቋንቋ ትምህርት ሌሎች ሀገራቶች ካለው የትምህርት አሰጣጥ ጋር ስለማይገናኝና እጅግ በጣም የተሻለ ስለሆነ:
ሁለተኛ: ፊዩሽ ሲመጣ ትምህርቱ የሚሰጠው በአረበኛ ስለሆነ ለቋንቋው አዲስ እንዳይሆን ሲባል ከዛው ተምሮ ቢመጣ አሪፍ ብስለት ነው።
መርከዙ ላይ የሚሰጡት ዱሩሶች በጣም በርካታ ናቸው። ከስር ከኸጥና ንባብ ጀምሮ እስከ ላይ ኢልመል ሀዲስ ዲራየተን ብሎም ሪዋየተን ሰሂሀይንን ጠቅሎ ደርስ ይሰጥበታል። ይህ ማለት በዚህ መሀል:
- ፊቅህ
- አቂዳ
- አህካም
- ሲራ
- ቋንቋ
- ሀዲስ
- ተፍሲር
እና ኡሱሎቻቸውና ሌሎችም የተለያዩ የእውቀት ዘርፎችን ያካትታል ማለት ነው።
ወደ ፊዩሽ በህጋዊ ለመሄድ ምን ያስፈልገናል?
ለዚህ ጥያቄ ከኢዳራው የተላከልን ወረቀት ስላለ ሊንኩን ተጭነው ያንብቡ
https://t.me/ibnuidris_teppi/3412
ስለሌሎቹ መርከዝም እመለስ ይሆናል ኢንሻአላህ ……….
✍️ فوائد من دفتري
የመስጅዳችንን ቦታ በገንዘብ ማጣት ብቻ ልናጣው ነው ታደጉን #የወረኢሉሙስሊሞች ! _
🎤የተከበራችሁ ወንድምና እህቶቻችን #በወረኢሉ ከተማ አስተዳደር በ2012 ጀምሮ የመስጀድ ቦታና የቢሮ ቦታ ስንጠይቅ ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጅ በሳይት ፕላን ቅየራ ምክንያት በማድረግ እስከ ክልል ባህር ዳር ድረስ በመሄድ ሳይት ፕላኑ እንዲጸድቅ ተደርጎል በዚህ ሁኔታ እያለን የወረኢሉ ሙስሊም አቅም አናሳ በመሆኑ እስከዛሬ ይህን ካርታ ማሰራት አልቻሉም፡፡ የመሰጅዱ ቦታ ብሩክ ተስፋ ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ ከዋናው አስፓልት ዳር ነው የሊዝ ክፍያ የ3,000 ካሬ መስጅድ እና 500 ካሬ ቢሮ 1,750,000/አንድ ሚሊዬን ሰባት መቶ ሀምሳ ሽህ ብር/ ፣ ይሄን ካልከፈልን ቦታው ወደ መሬት ባንክ እንደሚገባ ተነግሮናል ስለዚህ ይሄን ቦታ ከመንግስትም የመጨረሻ ውሳኒያቸውን ያሳወቁን ሲሆን በዚህም ውሳኔያቸው ካርታ በአስቼኳይ ካላወጣን የከተማው የሳይት ፕላን ቅየራ ስለደረሰ ለሚመጣው ችግር ሃላፍትና እንደማይወስዱ አሳውቀውናል ስለሆነም ማንኛውም ሙስሊም እና ኢስላማዊ ድርጅት እገዛ እንዲታደርጉልን እና የወረኢሉን ሙስሊም ማህበረሰብ ተቋማ አልባ እንዳንሆን የድርሻችሁን እገዙን ብሎ እጁን ወደ እናንተ ዘርግቷል :: የወረኢሉ ሙስሊሞች ተቋም ከመወሰዱ በፊት እንታደገው ከተወሰዴ በኋላ መጮህና ማስጮህ ለአዱኒያችንም ለአኼራችን አይጠቅመንም አሁኑ በምትችሉት ሁሉ ተረባርባችሁ አድኑልን በማለት የወረኢሉ ሙስሊም ማህበረሰብ በአላህ ስም የጠየቃችሁን ጥያቄ በምትችሉት አቤት ብላችሁ የቻላችሁ በብር ያልቻላችሁ በዱዓና ይሄን ማገዝ ለሚችሉ ወንድምና እህቶች ሸር በማድረግ እስላማዊ ግደታችሁን እንድትወጡ በአላህ ስም እንጠይቃችኋለን ! ይሄን የመስጅድ ቦታ በገንዘብ ማጣት ምክንያት ብናጣው አላህ ፊትስ ምን ይሆን መልሳችን !? ::
ውዱ ነብያችን የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህ ብለዋል " መስጅድን የገነባ ሰው አላህ ጀነት ላይ ቤት ይገነባለታል"፡ብለዋል
#በነገራችን ላይ ይሄን ብር በቅንነት
700 ሰው እያንዳንዳቼው 2500 ብር ቢያዋጡ በአንድ ጊዜ መሸፈን ይቻላል
700×2500 =175,0000
ስለዚህ ሁላችሁም ለአላህ ብላችሁ በቻላችሁት አግዙን !
@አካውንታችን በወረኢሉ ንግድ ባንክ
@ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
1000469868587
አቢሲኒያ አካውንት
@ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
87813274
#መሆኑን እየገለጽን ይሄን መስጅድ ሊዙን በመክፈል የወረኢሉን ሙስሊም እንታደገው እያልን በአላህ ስም ለምታደርጉልን ድጋፍ ሁሉ አላህ በአዱኒያም በአኼራም የተሻለውን ይመነዳችሁ ዘንዳ ዱዓችን ነው !🕌
ማሳሰቢያ :-
ለበለጠ መረጃ ከላይ የተያያዙትን ደብዳቤዎችን ይመልከቱ
https://t.me/YeZemzemMesjidJemea
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
የመስጅዳችንን ቦታ በገንዘብ ማጣት ብቻ ልናጣው ነው ታደጉን #የወረኢሉሙስሊሞች ! _
🎤የተከበራችሁ ወንድምና እህቶቻችን #በወረኢሉ ከተማ አስተዳደር በ2012 ጀምሮ የመስጀድ ቦታና የቢሮ ቦታ ስንጠይቅ ቆይተናል፡፡ ይሁን እንጅ በሳይት ፕላን ቅየራ ምክንያት በማድረግ እስከ ክልል ባህር ዳር ድረስ በመሄድ ሳይት ፕላኑ እንዲጸድቅ ተደርጎል በዚህ ሁኔታ እያለን የወረኢሉ ሙስሊም አቅም አናሳ በመሆኑ እስከዛሬ ይህን ካርታ ማሰራት አልቻሉም፡፡ የመሰጅዱ ቦታ ብሩክ ተስፋ ትምህርት ቤት ከፍ ብሎ ከዋናው አስፓልት ዳር ነው የሊዝ ክፍያ የ3,000 ካሬ መስጅድ እና 500 ካሬ ቢሮ 1,750,000/አንድ ሚሊዬን ሰባት መቶ ሀምሳ ሽህ ብር/ ፣ ይሄን ካልከፈልን ቦታው ወደ መሬት ባንክ እንደሚገባ ተነግሮናል ስለዚህ ይሄን ቦታ ከመንግስትም የመጨረሻ ውሳኒያቸውን ያሳወቁን ሲሆን በዚህም ውሳኔያቸው ካርታ በአስቼኳይ ካላወጣን የከተማው የሳይት ፕላን ቅየራ ስለደረሰ ለሚመጣው ችግር ሃላፍትና እንደማይወስዱ አሳውቀውናል ስለሆነም ማንኛውም ሙስሊም እና ኢስላማዊ ድርጅት እገዛ እንዲታደርጉልን እና የወረኢሉን ሙስሊም ማህበረሰብ ተቋማ አልባ እንዳንሆን የድርሻችሁን እገዙን ብሎ እጁን ወደ እናንተ ዘርግቷል :: የወረኢሉ ሙስሊሞች ተቋም ከመወሰዱ በፊት እንታደገው ከተወሰዴ በኋላ መጮህና ማስጮህ ለአዱኒያችንም ለአኼራችን አይጠቅመንም አሁኑ በምትችሉት ሁሉ ተረባርባችሁ አድኑልን በማለት የወረኢሉ ሙስሊም ማህበረሰብ በአላህ ስም የጠየቃችሁን ጥያቄ በምትችሉት አቤት ብላችሁ የቻላችሁ በብር ያልቻላችሁ በዱዓና ይሄን ማገዝ ለሚችሉ ወንድምና እህቶች ሸር በማድረግ እስላማዊ ግደታችሁን እንድትወጡ በአላህ ስም እንጠይቃችኋለን ! ይሄን የመስጅድ ቦታ በገንዘብ ማጣት ምክንያት ብናጣው አላህ ፊትስ ምን ይሆን መልሳችን !? ::
ውዱ ነብያችን የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህ ብለዋል " መስጅድን የገነባ ሰው አላህ ጀነት ላይ ቤት ይገነባለታል"፡ብለዋል
#በነገራችን ላይ ይሄን ብር በቅንነት
700 ሰው እያንዳንዳቼው 2500 ብር ቢያዋጡ በአንድ ጊዜ መሸፈን ይቻላል
700×2500 =175,0000
ስለዚህ ሁላችሁም ለአላህ ብላችሁ በቻላችሁት አግዙን !
@አካውንታችን በወረኢሉ ንግድ ባንክ
@ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
1000469868587
አቢሲኒያ አካውንት
@ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
87813274
#መሆኑን እየገለጽን ይሄን መስጅድ ሊዙን በመክፈል የወረኢሉን ሙስሊም እንታደገው እያልን በአላህ ስም ለምታደርጉልን ድጋፍ ሁሉ አላህ በአዱኒያም በአኼራም የተሻለውን ይመነዳችሁ ዘንዳ ዱዓችን ነው !🕌
ማሳሰቢያ :-
ለበለጠ መረጃ ከላይ የተያያዙትን ደብዳቤዎችን ይመልከቱ
https://t.me/YeZemzemMesjidJemea
ከዑመር ረ.ዐ ንግግሮች ዉስጥ..ስህተትህን የሚያሳይህ ሰው ምንም ይሁን ማን እርሱ ጓደኛህ ነው። በሀሰት እያሞገሱ በአንደበታቸው የሚሸነግሉህ ግን አጥፊዎችህ /ገዳዮችህ/ ናቸው ።
#ግጥም□የከፋው ሰው ሲሞት የደላው መች ቀረ □ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ □ሁሉም ይጓዛታል ያቺን የሩቅ ጉዞ □የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ😢
ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁላህ
የግዕዝን ቋንቋ በአማራ ክልል ሙስሊሞች ላይ ለመጫን የሚደረገውን ትግል በየትኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም
ይሁንና ስለ ግዕዝ ቋንቋ ምንነት ስንቶቻችን በሚገባ እናቃለን???
ግዕዝ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡30፥22 ሰማያትን እና ምድርን መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ተአምራቱ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ "ሊሣን" لِسَان ማለት "ቋንቋ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ አንድን መልእክተኛ ሲልክ የመጣበት ሕዝብ በሚግባባበት ቋንቋ ይልከውና በዚያ ቋንቋ ለሕዝቡ ያብራራላቸዋል፦ 14፥4 ከመልእክተኛ ማንኛውንም ለእነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በሕዝቦቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا بِلِسَانِ قَوْمِهِ لِيُبَيِّنَ لَهُمْ "ቀውም" قَوْم ማለት "ሕዝብ" ማለት ሲሆን በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ ባሕል፣ ቋንቋ፣ አኗኗር፣ ታሪክ፣ መንግሥት እና ቦታ ያለው ማኅበረሰብን ያመለክታል። በምድር ላይ ያሉት ቋንቋዎች መለያየታቸው አስደናቂ የአሏህ ተአምራቱ ነው፦ 30፥22 ሰማያትን እና ምድርን መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ተአምራቱ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ በቋንቋዎቻችን እና በመልኮቻችን መለያየት ውስጥ ለዐዋቂዎች ተአምራት አሉበት፡፡ ከእነዚህ ድንቅ የአሏህ ተአምራት መካከል ግዕዝ አንዱ ነው፥ "ግዕዝ" በዓይን "ዐ" አርገን "ግ-ዕ-ዝ" የሚለው ቃል "አግዐዘ" ማለትም "ነጻ አወጣ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ነጻነት" ማለት ነው። በአሌፍ "አ" አርገን "ግ-እ-ዝ" የሚለው ቃል "አግአዘ" ማለትም "ጀመረ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጀመሪያ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ ሀ ግእዝ፣ ሁ ካዕብ፣ ሂ ሣልስ፣ ሃ ራብዕ፣ ሄ ኃምስ፣ ህ ሳድስ እና ሆ ሳብዕ ባለ ሰባት አናባቢ ገበታ ውስጥ "ግእዝ" ማለት "መጀመሪያ" ማለት ነው። ነገር ግን ስለ ቋንቋው ግዕዝ ስናወራ የምንጠቀመው መሃል ላይ በአሌፍ ያለውን "ግእዝ" ሳይሆን መሃል ላይ በዓይን ያለውን "ግዕዝ" ነው፥ "ግእዝ" እና "ግዕዝ" ሁለት የተለያዩ ቃላት እና ፊደል ናቸው። "ዐጋዚእ" ማለት "ነጻ አውጪ" ማለት ነው፥ "ዐጋዚአን" ማለት ደግሞ "ዓጋዚእ" ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "ነጻ አውጪዎች" ማለት ነው። ዐጋዚአን የዛሬ 3 ሺህ ዓመት ገደማ ከየመን እና ደቡብ ዐረቢያ በመነሣት እና ቀይ ባሕርን በመሻገር በኤርትራ እና ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሰፈሩ የተለያዩ የሳባውያን ነገዶች እና ቋንቋ እንዲሁ በጊዜው ሰሜን ኢትዮጵያ ይነገሩ በነበሩ ቋንቋዎች ዘገምተኛ ውሕደት ናቸው። የግዕዝ ቋንቋ ሴማዊ ቋንቋ"Semetic Language" ሲሆን ጥንት ላይ እንደ ዕብራይስጥ፣ ዐረማይስጥ፣ ዐረቢኛ ከቀኝ ወደ ግራ የሚነበብ እና አናባቢ ድምጹ ባለቤት "ኡ" ካዕብ፣ ተሳቢ "አ" ግእዝ፣ አገናዛቢ "ኢ" ሣልስ ነበረ፥ "እ" ሳድስ ማስከኛ እንዲሁ "ኣ" ራብዕ መጎተቻ ነበረ። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ፍሬምናጥስ እንደ ሮማይስጥ እና ጽርዕ ከቀኝ ወደ ግራ እንዲነበብ እና በሦስት አናባቢ ድምፅ ላይ "ኤ" ኃምስ እና "ኦ" ሳብዕ ጨምሯል። ግዕዝ 35 የፊደል ገበታ ሲኖሩት በሥረ መሠረት የነበሩት ተነባቢ ፊደላት 22 ሲሆኑ 13 ፊደላት ከሌላ ቋንቋ የገቡ ሰርጎ ገብ ፊደላት ናቸው። ለምሳሌ፦ "ሸ" "ጀ" "ቨ" "የ" ወዘተ... ተጠቃሽ ናቸው፥ አ ቡ ጊ ዳ ሄ ው ዞ የያዘ "አቡጊዳ" ማለት "ፊደል" ለማለት ሲሆን ከልሳነ ግዕዝ የተነሣ ነው። ግዕዝ ጥንት በአፍሪካ ቀንድ፣ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሲያገለግል የቆየ ቋንቋ ነው፥ በአክሱም መንግሥት እና በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበር። ግዕዝ እስከ 10ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ዋነኛ የመግባቢያ ቋንቋ እና የንጉሥ ቋንቋ ነበር፥ ከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ግን ሙሉ በሙሉ መነገር አቁሞ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግርኛ እንዲሁም በማዕከላዊው ክፍል ደግሞ በዐማርኛ ተተካ። የግዕዝ ቋንቋ ለዐማርኛ ቋንቋ እና ለትግርኛ ቋንቋ ግንባዜ እንደ እንሾሽላ መዋቢያ፣ እንደ ኩል መኳያ፣ እንደ ሽቶ ለመሸተት እና ለሙያዊ ቃላት ቅመራ ግብዐት ቢሆንም ዛሬ ላይ የግዕዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንሥነ ሥርዓት ውስጥ ሃይማኖታዊ ቋንቋ ሆኗል። ዛሬ ላይ የግዕዝ ቋንቋ መማር እና ማጥናት በራሱ ችግር ያለው ሆኖ አይደለም፥ ቋንቋ የአሏህ ተአምር ነው። ነገር ግን ከቋንቋነት አልፎ ሃይማኖታዊ ይዘት ሆናል፥ ለምሳሌ፦ 1ኛ. ግዕዝ ሲጀመር "በስመ አብ" ተብሎ በትእምርተ መስቀል በማማተብ መጀመሩ፣ 2ኛ. ንባብ ለማዳበር ንባብ ቤት ውርድ ንባብ፣ ቁም ንባብ፣ ግዕዝ ንባብ እየተባለ መልእክተ ዮሐንስ፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያም፣ መልክአ ማርያም፣ መልክአ ኢየሱስ መድገሙ፣ 3ኛ እያንዳንዱ ፊደል ሃማኖታዊ ትርጉም ተሰቶ የሚነበብ ነው። ለምሳሌ፦ "ሀ" "ሀ"-ልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም" ትርጉም "የአብ አኗኗር ከዓለም በፊት ነው"። "ለ" "ለ"-ብሰ ሥጋ እምድንግል" ትርጉም "ከድንግል ሥጋን ለበሰ"። "ሐ" "ሐ"-መ ወሞተ እግዚእነ" ትርጉም "ጌታችን ታመመ ሞተ"። "መ" "መ"-ንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር" ትርጉም "የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው"፡፡ እስቲ ፍረዱ! አንድ ሙሥሊም የማያምንበትን እና ከሃይማኖቱ በተቃራኒ ያለን ከሃይማኖቱ አጥር የሚያስወጣ ድርጊት "አብ" "አምላክ ሥጋ ለበሰ" "ጌታችን ሞተ" "እግዚአብሔር" እያለ ሊደግም ነውን? በትእምርተ መስቀል ማማተብስ ኩፍር አይደለምን? ይህ ቅኝ ግዛት"Colonization" ነው። ግዕዝ እራሱ የዜማ ይዘት ስላለው ግዕዝ፣ እዝል እና አራራይ የሚባሉት "አጥኑ" መባላችን አይቀርም፥ ዝም ከተባሉ እኮ የቁርኣን ቃሪዎችን የግዕዝን ዜማ ለማጥናት ዜማ ቤት "ግቡና" ውዳሴ ማርያም፣ መስተጋብዕ፣ አርባዕት፣ አርያም ወዘተ.. በመርዋ ድምፃችሁ "ቀሽሩ" መባላቸው አይቀርም። ከዚያም ባሻገር ወጠር እና ጠጠር ያሉ የሰሜኑ ፓለቲካ አቀንቃኞች ለፓለቲካቸው መሣሪያ አድርገው ለመጠቀም እንጂ እንኳን ተራ ሰው ይቅርና ቄስ እና ደብተራስ ግዕዙን ያነበዋል እንጂ በአግባቡ መቼ ያወራበታል? ይህ ቋንቋዊ አጀንዳ ሲፋቅ እና ጭንብሉ ሲገለጥ ሃይማኖዊ እና ፓለቲካዊ ይዘት ስላለው ከወዲሁ ሁሉም ሰው መንቃት አለበት! ግሳንግሱ ከሌለ ቋንቋው እንደ ቋንቋነት አይደለም የዐማራ ክልል ይቅርና አገር ዓቀፍ አሊያም ዓለም ዓቀፍ ቢሆን አብላጫው ሕዝብ ከተስማማበት ሙሥሊም ጋር የቋንቋ ጥላቻ እና ጭፍን ፍቅር ስለሌለበት ምንም ተቃውሞ አያሰማም ነበር። አምላካችን አሏህ ከኩፋሮች ሴራ፣ ደቦ፣ ተንኮል፣ አሻጥር ይጠብቀን! አሚን። ከወሒድ የተወሰደ
📚 #أحـاديـث_نـبـويـة 📚
((لَيَكونَنَّ مِن أُمَّتي أقْوامٌ يَسْتَحِلُّونَ الحِرَ والحَرِيرَ ، والخَمْرَ والمَعازِفَ ، ولَيَنْزِلَنَّ أقْوامٌ إلى جَنْبِ عَلَمٍ ، يَرُوحُ عليهم بسارِحَةٍ لهمْ ، يَأْتِيهِمْ -يَعْنِي الفقِيرَ- لِحاجَةٍ ، فيَقولونَ : ارْجِعْ إلَيْنا غَدًا ، فيُبَيِّتُهُمُ اللَّهُ ، ويَضَعُ العَلَمَ ، ويَمْسَخُ آخَرِينَ قِرَدَةً وخَنازِيرَ إلى يَومِ القِيامَةِ)).
#الراوي : أبو مالك الأشعري
#المصدر : صحيح البخاري
📓 #شــرح_الـحـديـث 🖊
بيَّن لنا النبيُّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم أمورَ ديننا ، وأوضَحَ الحلالَ والحرامَ في الأقوالِ والأفعالِ ، وبَيَّن أنَّه بمرورِ الزَّمانِ واقترابِ قيامِ السَّاعةِ ، سيَخِفُّ الدِّينُ في قلوبِ النَّاسِ حتى يستَحِلُّون بعضَ ما حَرَّمه اللهُ.
● وفي هذا الحديثِ يُخبِرُ النَّبيُّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم بأنَّه سَيَكونُ جَماعةٌ مِن أُمَّتِه يَستحِلُّونَ بعضَ المحرَّماتِ ، والاستحلالُ هو أنْ يَفعَلَ الحرامَ بدَعْوى أنَّه حَلالٌ بالتأويلاتِ الفاسِدةِ ، ولهذا قال : «من أمتي» ، فجعَلَهم بعضَ أمَّتِه مع استحلالهم بالتأويلِ ؛ لأنَّهم لو استحَلُّوها مع اعتقادِ أنَّ اللهَ ورسولَه حَرَّماها ، لكانوا كُفَّارًا ، وخرجوا عن أمَّتِه.
● وأوَّلُ هذه المحَرَّماتِ هو الحِرُ ، وهو الفَرْجُ ، ويقصِدُ الزِّنا ، قال تعالى : {وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا} [الإسراء: 32].
● وأيضًا يستحِلُّون الحريرَ ، وهو حرامٌ على الذُّكورِ دونَ الإناثِ.
● وكذا يَستحِلُّون الخمرَ ، وهي كُلُّ ما يُسكِرُ ويُغَطِّي العَقلَ.
● ويستحِلُّون أيضًا المعازفَ ، وهي آلاتُ اللَّهوِ والموسيقا.
#وقيل : مدارُ استحلالِ هذه المحَرَّماتِ وغَيرِها على تسميةِ الشَّيءِ باسمِ غيرِه ، كمن تزوَّج امرأةً ليُحِلَّها لزَوجِها ؛ فإنَّهم يُسَمُّونه في العَقدِ زَوجًا ، وإنما هو المحلِّلُ الملعونُ ، والتَّيسُ المستعارُ ، واستحلالُ الخَمرِ بتسمِيَتِها بغيرِ اسمِها ، فيقولون : مشروباتٌ رُوحانيَّةٌ ، وغيرَ ذلك.
● ثمَّ أنْبَأَ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم عن أقوامٍ يَنزِلون إلى جَنْبِ عَلَمٍ ، وهو الجبَلُ ، يرُوحُ عليهم بسارحةٍ لهم ، أي : يَسيرُ الرَّاعي بغَنَمٍ لهم ، وهي السَّارحةُ في المراعي ، وفي أثناءِ ذلك يَأتيهم الفقيرُ يَسأَلُهم الحاجةَ ، فيَرُدُّونه ويقولون : ارجِعْ إلينا غدًا ، وهم يقصِدون بذلك رَدَّه حتى لا يُعْطوه شيئًا.
● «فيُبيِّتُهم اللهُ» ، أي : يأخُذُهم بالعذابِ وهم في وقتِ البَياتِ ؛ وهو اللَّيلُ ، ويضَعُ الجبَلَ ، أي : يُوقِعُه ، عليهم فيُهلِكُهم.
● ثمَّ قال : «ويَمسَخُ آخَرين قِردةً وخَنازيرَ إلى يومِ القيامةِ» أي : إلى مِثلِ صُوَرِها حقيقةً ، كما وقَعَ لبعضِ الأُمَمِ السَّابقةِ ، ولم يُبَيِّن في هذا الحَديثِ مكانَهم ولا ذُنوبَهم ، وإنما أفاد أن المسْخَ يكونُ في آخِرِ الزَّمانِ عند نزولِ الفِتَنِ.
#وقيل : «ويَمسَخُ آخَرين» أي : يجعَلُ صُوَرَ آخَرينَ ممَّن لم يَهلِكْ من البياتِ المذكورِ «قِردةً وخَنازيرَ إلى يومِ القيامةِ» ، وفي هذا حَضٌّ للمُسلِمِ على اجتنابِ المعاصي ؛ كي لا يقَعَ في العذابِ ومَسْخِ الصُّوَرِ.
#وفي_الحديث :
● عَلامةٌ مِن عَلاماتِ النُّبوَّةِ.
● وفيه : أنَّ استحلالَ المعاصي -مِثلُ الزِّنا والحريرِ والخَمرِ والمعازفِ- من أكبرِ الكبائِرِ.
