✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Открыть в Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
193
Подписчики
-224 часа
-47 дней
-630 дней
Архив постов
ለአንድ ጉደይ ሁለት አይነት ፍርድ!!
ይህ ቀይ ለባሸ፣ ባለስልጣን (የኛው ሀገር ትምህርት ሚኒስቴር ወይም የሀገራችን አየር መንገድ ስዎች ውስጥ አንዱ ይመስለኛል)፤ ፊት ለፊቱ የቆሙትን ጥንዶች እንዲህ ሲል ያናግራቸዋል"የዱሮው ኢስላማዊ አልባሳት እኮ አሁን ላለንበት ዘመን የሚመጥኑ እና ከጊዜው ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም። 21ኛው ክፍለ ዘመን የስልጣኔ ቁንጮ ነው ስለዚህ በዚህ የስልጣኔ ዘመን ላይ እንዴት ወደኋላ 1447 አመት ተመልሳችሁ ወግ አጥባቂ በመሆን ይህን ጊዜ ያለፈበትን ልብስ እንዴት ትለብሳላችሁ" በማለት ሲጠይቃቸው
ጥንዶቹም "ምን አልክ ወንድማችን "በማለት ለተሰነዘረባቸው ጥያቄ ዘወር ሲሉ ክብር ሚኒስትራችንም ሰዎቹ እስላም ሳይሆኑ የካቶሊክ አማኞች ሁነው በማግኘቱ "ይቅርታ እስላሞች መስላችሁኝ ነው በማለት ይቅርታውን አቀረበ።
የእኛ ሀገር ሙስሊም ጠል የህዝብ እንደራሲዎች እና የመንግስት ሹመኞች እንደዚህ ናቸው።
ስለዚህ አጥብቀህ ታገል!!!!!
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
ይሄ ከምንዳዎቻቸው ምንም አይቀንስም። ወደ ጥመት የተጣራ የተከተለው ሰው አምሳያ ወንጀሎች ይኖሩበታል። ይሄ ከወንጀሎቻቸው ምንም አይቀንስም።” ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል። አሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብን ወደ ኸይበር የሁዶች በላኩ ጊዜም እንዲህ ብለዋል - ﷺ - ፡-
ادعهم إلى الإسلام وأخبرهم بما يجب عليهم من حق الله تعالى فيه، فوالله لأن يهدي الله بك رجلا واحدا خير لك من حمر النعم
“ወደ ኢስላም ጥራቸው። በሱ (በኢስላም) ውስጥ የሚጠበቅባቸውን የአላህን ሐቅም ንገራቸው። በአላህ ይሁንብኝ! ባንተ አማካኝነት አንድ ሰው አላህ ቢያቀናልህ ላንተ ከቀያይ ግመሎች የበለጠ ነው።” በሶሒሕነቱ ላይ ተስማምተውበታል።
እነዚህ አንቀፆችና ትክክለኛ ሐዲሦች ሁሉም በዘመናዊ የብዙሃን መገናኛ መንገዶች ወደ ጠራው አላህ መጣራትን ያካትታሉ። ድስኩር ማድረግ፣ መፅሐፍ ማዘጋጀት፣ የፅሑፍ መልእክቶች፣ የስልክ ንግግሮች እና ሌሎችም የማድረሻ መንገዶች አላህ ኒያውን ላጠራለት፣ ጠቃሚ እውቀትንና በሱ መስራትን ላደለው በዚህ ውስጥ የሚገቡ ናቸው።
ከአላህ መልእክተኛ- ﷺ - “ስራዎች ሁሉ በእሳቤዎች ናቸው” ማለታቸው በርግጥም ተዘግቧል። [በሶሒሕነቱ ላይ ተስማምተውበታል።] ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህም ብለዋል፡- “አላህ ወደ ቅርፆቻችሁ (መልኮቻችሁ) አይመለከትም። ይልቁንም ወደ ልቦቻችሁና ወደ ተግባሮቻችሁ ነው የሚመለከተው።” ሙስሊም በሶሒሓቸው ዘግበውታል። [መጅሙዑ ፈታዋ፡ 5/292-295] ነፃ ትርጉም ነው የተጠቀምኩት።
ጫፍ ይዘው ለጥጠው የሚያራግቡ እንደሚኖሩ ስለምገምት እዚህ ላይ እንዲሰመርልኝ የምፈልገው የፅሑፌ አላማ የምናምንበትን አናራምድ የሚል አይደለም። አላማዬ የሚፈቅደው በሚከለክለው ላይ ሲያሸሙርና ሲሳለቅ፤ የሚከለክለው ደግሞ የሚፈቅደውን ከመንሃጅ ጋር አያይዞ ሲነካካ ስላየሁ ጉዳዩን ዑለማዎቹ በያዙት መጠን እንድንይዘው ማስታወስ ብቻ ነው። አንድን ነገር "አይፈቀድም" ብለን ስንፅፍ ወይም ስንናገር እሱን ተመርኩዘው ጉዳዩን በወርድም በቁመትም የሚለጥጡ ሰዎችን ስታይ ተጠያቂነቱ እንዳያጣቅስህ ያሰጋሀል። ስለዚህ በመፍቀድም ሆነ በመከልከል የሚያምኑበትን ማራመድ፣ ስህተት ነው የሚሉትን መሞገትን በተመለከተ ጥንትም የነበረ፣ ወደፊትም የሚቀጥል ሐቅ ነውና ነገሩን በዚህ አግባብ በልኩ ብንይዘው ጥሩ ነው ለማለት ነው፡፡
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
የፎቶና ቪዲዮ ጉዳይ በልኩ ቢያዝ
~~~~~~~~~~~~~
ምስልን በተመለከተ አስፈሪ ሐዲሦች መምጣታቸው በተጨባጭ የሚታወቅ ነው። እነዚህን ማስረጃዎች በመመርኮዝ በርካታ ዑለማዎች ፎቶን ይከለክላሉ። ከመሆኑም ጋር ከምናከብራቸው ዑለማዎች ውስጥ ጭምር ፎቶን ወይም ተንቀሳቃሽ ምስልን የሚፈቅዱም እንዳሉ የሚታወቅ ነው። ይህንን መጠቆም የፈለግኩት ጉዳዩን በልኩ እንድንይዘው ለማስታወስ ያክል ነው። ዑለማዎች የተለያዩ ሃሳቦች ከሚሰነዝሩባቸው ጉዳዮች መካከል ሚዛን እንደሚደፋ ያመንበትን ከማራመድና እርምት ከመለዋወጥ በዘለለ ለስላቅ፣ ለተረብና የሌሎችን መንሃጅ ጥያቄ ውስጥ ለመክተት ማጣቀሻ አድርጎ ማራገብ እራሳችንን ነው የሚጎዳን። ደግሞም በአንድ ጉዳይ ላይ የተራራቀና በዳይ ፍርድ ስናንፀባርቅ መጣረስ (ከራስ ጋር መጋጨት) ነው የሚገጥመን። የምስል ጉዳይ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል። የሚፈቅዱ ዑለማዎች ላይ ጣት ሳንቀስር የእነሱን አቅጣጫ በተከተሉ ሰዎች ላይ ዘመቻ የምንከፍት ከሆነ ትዝብት ላይ ይጥለናል። በስፋት የምንጠቀምባቸው ማህበራዊ ሚዲያዎች ለመጠንቀቅ በሚያስቸግር መልኩ በምስል የታጨቁ ናቸው፡፡ እንመርጣለን ብንል እንኳ በፌስቡክ ምስሎች ያሉባቸው ማስታወቂያዎች ይመጣሉ፡፡ የቴሌግራምና ዋትሳፕ ባክግራውንድ ደብዘዝ ያሉ ምስሎችን የያዘ ነው፡፡
ለመታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ፣ ወንጀለኛን ለማደን፣ ለወሳኝ ሰነዶች፣ ወዘተ ላሉ አስገዳጅ ጉዳዮች በተመለከተ ምስል መጠቀምን የሚከለክሉ ዑለማዎችም ጭምር ይፈቅዳሉ። በአሁኑ ሰዓት ለመስለሓ ሲባል ምስልን የሚፈቅዱ ዓሊሞች በዝተዋል። በቻናል የሚቀርቡ፣ እንደ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ዙም፣ ወዘተ ባሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች በቪዲዮ እየቀረቡ የሚያስተምሩ በተጨባጭ አሉ። ስም የማልዘረዝረው ለብዙ ሰው አይሰወርም በሚል ነው። በሌላ ሃገራት የተሰሩ በጎ ስራዎችን ሂደትና አፈፃፀም በምስል አያይዛችሁ አቅርቡልን በማለት ማስረጃ የሚጠይቁ አሉ። እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች (ዶሩራ ወይም ሐጃ) ሳያስቀምጡም የፎቶ ወይም የቪዲዮ ምስሎችን መጠቀምን የሚፈቅዱም አሉ።
ምስልን በመከልከል የሚታወቁት ሸይኽ ኢብኑ ባዝ የከፋውን ችግር ለመከላከል ዝቅ ያለውን መፈፀም እንደሚቻል የሚጠቁመውን መርህ በመመርኮዝ በቴሌቪዥን ቀርቦ ማስተማር እንደሚቻል የተናገሩበት አለ። ፈትዋቸውን ባያይዘው የተሻለ መሰለኝ፡-
“ወደ ሐቅ ለመጣራት፣ የሸሪዐ ብይኖችን ለማሰራጨት፣ ሺርክና መዳረሻዎቹን ለመግለፅ፣ ከዚህና ከሌሎችም አላህ ከከለከላቸው ነገሮች ለማስጠንቀቅ የማስታወቂያ መንገዶችን መጠቀም ያለ ጥርጥር ከትልልቅ ሃላፊነቶች ውስጥ ነው። እንዲያውም ከግዴታዎቹም እጅግ የጠበቀው ነው። እነሱ (የማስታወቂያ መንገዶች) ለሐቅ ላዋላቸውና በሃይማኖቱ ላይ የሚጎድለውን ለመሙላትና ያለበትን የአላህን ሐቅ ለማወቅ ለተጠቀማቸው ከትልልቅ የአላህ ፀጋዎች ውስጥ ናቸው። በቴሌቪዥን ላይ መውጣት ከፊል ዓሊሞች የሚቸጋገሩበት እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ይህም ምስል መሳልን በጥብቅ በመከልከልና ሰዓሊዎችን በመርገም ላይ ትክክለኛ ሐዲሦች ስለተዘገቡ ነው። ነገር ግን በሱ (በቲቪው) የሚወጣው ወደ ሐቅ ለመጣራት፣ ኢስላማዊ ብይኖችን ለማሰራጨትና በጥፋት ሰዎች ላይ ምላሽ ለመስጠት ከሆነ በዚህ ላይ ችግር እንደሌለበት ከፊል ዓሊሞች አምነዋል። ይህም “ሁለት ጥፋቶችን አንድ ላይ ለማለፍ ካልተቻለን የከፋውን ለማለፍ ዝቅ ያለውን መፈፀም ይቻላል። ሁለት ፋይዳዎችን አንድ ላይ ማግኘት ካልተቻለ ዝቅ ያለውን በማሳለፍ ከፍ ያለውን ማግኘት ይገባል” የሚለውን ሸሪዐዊ መርህ በመተግበር ነው።
መሪዎችንና ዑለማዎችን በሚገጥሙ በርካታ ጥፋቶችና ጥቅሞች ላይም ተመሳሳይ ብይን ይሰጣል። ከሁሉም ጥፋቶች መዳን ካልተቻለ ይበልጥ አደገኛና ወንጀሉ የገዘፈ ከሆነው ለመዳን ሊታገሉ ይገባል። ጥቅሞችም ላይ እንዲሁ ሁሉን ማሳካት ካልተቻለ በተቻለ መጠን የበለጠ ከፍ ያለውን ከዚያም የሚከተለውን ሊያረጋግጡ ግድ ይላቸዋል። ለዚህም ከቁርኣንና ከሱና ብዙና የተለያዩ ምሳሌዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ እንዲህ የሚለው ነው፡-
وَلا تَسُبُّوا الَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ فَيَسُبُّوا اللَّهَ عَدْوًا بِغَيْرِ عِلْمٍ
“እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን (ጣዖታትን) አትስደቡ። ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና።” [አልአንዓም፡ 108]
በትክክለኛ ሐዲሥም ነቢዩ - ﷺ - ለዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ “ወገኖችሽ ከክህደት (ከወጡ) ቅርብ ጊዜያቸው ባይሆን ኖሮ ከዕባን አፍርሼ በኢብራሂም መሰረቶች ላይ እገነባት ነበር” ብለዋታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህንን መነሻ በማድረግ ወደጠራው አላህ ለመጣራት እና ሐቅን ለማዳረስ በቴሌቪዥን መቅረብ አላህ ለሰዎች በሰጣቸው እውቀት፣ ግንዛቤ እና ፍፃሜዎች (ዐዋቂብ) መሰረት ሊለያይ ይችላል።
አላህ ልቡን የከፈተለትና እውቀቱ የሰፋለት ሰው ሐቅን ለማሰራጨትና የአላህን ተልእኮዎች ለማድረስ በቴሌቪዥን መቅረቡን ካመነ በዚህ ላይ ወንጀል የለበትም። ከአላህም ዘንድ ምንዳ አለው። ነገሩ አሻሚ የሆነበትና ልቡን ለዚህ ያልከፈተለት ሰው ይቅርታ እንዳለው (መዕዙር እንደሆነ) ተስፋ እናደርጋለን። ነብዩ- ﷺ - “የሚያጠራጥርህን ተው፤ ወደማያጠራጥርህ ሁን” ብለዋልና። እንዲሁም “መልካም ማለት ነፍስ የረጋችበት፣ ልብ የተረጋጋበት ነው” ብለዋልና። የሐቅ ሰዎች በቴሌቪዥን መቅረባቸው የአላህን ሃይማኖት በማሰራጨትና በጥፋት ሰዎች ላይ ምላሽ ለመስጠት ከሚያችሉ ትልልቅ ሰበቦች ውስጥ ነው። ምክንያቱም ከወንዱም፣ ከሴቱም፣ ከሙስሊሞችም፣ ከከሃዲዎችም አብዛኛው ሰው ይከታተለዋልና። የሐቅ ሰዎችም በሐቅ የሚያውቁትን ሰው ሲመለከቱ ይረጋጋሉ። ከሱ በሚገኘውም ይጠቀማሉ። እንዲሁም በዚህ ውስጥ የጥፋት ሰዎችን መፋለም እና መስካቸውን ማጣበብ አለበት። በርግጥም አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ
“እነዚያም በኛ መንገድ ላይ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን። አላህም በእርግጥ ከበጎ ሰሪዎች ጋር ነው።” [አልዐንከቡት፡ 69]
እንዲህም ብሏል፡-
ادْعُ إِلَى سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ وَجَادِلْهُمْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ
“ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳፄ ጥራ። በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው።” [አነሕል፡ 125]
ጥራት ይገባውና እንዲህም ብሏል፡-
وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِمَّنْ دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ
“ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሰራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?” [ፉሲለት፡ 33]
ነብዩም - ﷺ - “በመልካም ነገር ላይ ያመላከተ የፈፃሚው አምሳያ ምንዳ አለው” ብለዋል። ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁንና እንዲህም ብለዋል፡-
من دعا إلى هدى كان له من الأجر مثل أجور من تبعه لا ينقص ذلك من أجورهم شيئا، ومن دعا إلى ضلالة كان عليه من الإثم مثل آثام من تبعه لا ينقص من آثامهم شيئاً
“ወደ ቅናቻ (ሁዳ) የተጣራ ሰው የተከተለው ሰው አምሳያ ምንዳዎች ይኖሩታል።
በዚህ አለም ሰው ባለብዙ ፊት እየሆነ ነው
የባህሪ ለውጥ ምክንያቶች
~
አንዳንዴ ለዘመናት በመልካምነት የምናውቃቸው ሰዎች የማናውቃቸው እስከሚመስለን ድረስ ባህሪያቸው ተቀይሮ ለመሸከም የሚከብዱ ይሆናሉ። ምክንያቱ ምን ይሆን? የችግሮቹን መንስኤዎች ማወቅ ለማስታመም፣ ለማለፍ፣ ለመረዳት፣ ... ያግዘናል። የሰዎችን ባህሪ ከሚቀይሩ ነገሮች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።
1- ስልጣን፦
ስልጣንና ኃላፊነት ሲያገኙ የሚቀየሩ ብዙ ሰዎች አሉ። የሚያውቁትን እንደማያውቁት ይሆናሉ። ንቀትን ንቃት ያደርጋሉ። ውለታ ይረሳሉ።
2- ስልጣን ማጣት፦
ከስልጣንና ኃላፊነት ሲነሱ በብስጭት፣ በቁጭት እየተብከነከኑ ለሩቁ ቀርቶ ለቅርብ ሰዋቸው ጭምር ባህሪያቸው የሚፈትኑ ይኖራሉ።
3- ሃብት፦
ትሁትና ደግ የነበሩ ሰዎች ሃብት ካገኙ በኋላ ትእቢት፣ ንቀትና ኩራት የሚባሉ ነውሮችን ጌጥ የሚያደረጉ የዋሆች አሉ።
4- ድህነት፦
አግኝቶ ማጣት ትልቅ ህመም አለው። ድህነት ሲዳብሳቸው መልካም ባህሪያቸው ከገንዘባቸው ጋር ጥሏቸው የሚጠፋ ሰዎች አሉ። መቼም አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው።
5- ሱስ፦
በሱስ በመጎዳታቸው የተነሳ ከጊዜ ጊዜ ትእግስት እንደ ቁምጣ እያጠራቸው የሚሄድ፣ ይሉኝታ የማያውቁ፣ "ሰው ምን ይለኛል?" የማይገዳቸው ሰዎች ቁጥራቸው ከብዙም የበዛ ነው።
6- ሃሳብ፦
የሰው ልጅ በህይወቱ ለተለያዩ ሃሳቦች መጋለጡ የሚጠበቅ ነው። የሃሳብ መደራረብ፣ የአእምሮ መወጠር ደግሞ የሰው ባህሪ ላይ ግልፅ ተፅእኖ ያሳድርበታል።
7- ህመም፦
ህመም ባህሪን ይቀይራል። ያነጫንጫል። ከሰው ቀርቶ ከእንስሳ፣ ከግድግዳ ጋር ሁሉ ያጋጫል።
8- እርጅና፦
እርጅና እንደ ልጅ ያደርጋል። እንዲያውም ሊብስ ይችላል። ልጅን ተቆጥተህ ታስደነግጠዋለህ። ከእርጅና ጋር የሚመጣ ክፉ ባህሪ ግን ለገላጋይ አይመችም። እርጅና ላይ ሌሎች ገፊ ችግሮች ሲደረቡበት ደግሞ በቡሃ ላይ ቆረቆር ይሆናል።
ምንጭ፦ አብዛኛው ሃሳብ ከሸይኽ ዐብደላህ አልፈውዛን (ሚንሐቱል ዐላም፡ 10/295 - 296) የተወሰደ ነው።
Ibnu Munewor
🌿🌿🌿🍃ጉድ!! 🍃🌿🌿🌿
እየታዘባችሁ ነው ግን ያለንበትን ተጨባጭ?
ወንድምና እህቶች፤ ወላሂ ታዝባችሁ ከሆነ እንደ ሙስሊም ያለንበት ተጨባጭ አሳፋሪ ነው።
Almost የሚታመን ጠፋ። በቃሉ የሚገኝ ሙስሊም ቁጥር እየተመናመነ ነው። ከሰሞኑ ብንታዘብ እንኳ ከማክሮ ኢኮኖሚክ ለውጡ በፊት የተሻሻጡትን እቃ ብር ከፍለው ሲያበቁ ስላልወሰዱ ብቻ እቃ ጨመረ ብለው ቃላቸውን የሚያጥፉ ብዙ ነበሩ።
የሆነ ሙስሊም ባለሙያ ፈልጋችሁ የሆነ ነገር ታዙትና ለሳምንት የቀጠራችሁን ነገር ዛሬ ነገ እያለ ለወር ራሱ አያደርስም። በዚህ የተነሳ ለትብብር ብለን ስናዛቸው ሲያዝጉን ገንዘባችንን ከፍለን ለምናሠራው ነገር ቢዝነስ ነውና ወደ ሌላ አማራጭ ለመሄድ እንገደዳለን።
እንዲህ አይነት በቃሉ የማይገኝ ሙስሊም ባለሃብት፣ ባለሙያና የቢዝነስ ሰዎች ከመብዛታቸው የተነሳ፤ አሁን አሁን ብዙ ሰው «እኔ ከሙስሊም ይልቅ… እነዛን አምናለሁ!» የሚል እየበዛ ነው። የሚገርመው ደግሞ ለማስመሰል አንዳንድ ቦታ ላይ እነዛ ቃላቸውን ጠብቀው ይገኛሉ።
እኔ በፊት ከ"ሙስሊሙ ይልቅ" ሲሉ የኛው ሙስሊሞቹ እቆጣ ነበር። "አይባልም!" እል ነበር። ግን ጀለብያ፣ ጺምና መሰል ኢስላማዊ ገፅታ ተላብሰው እያጭበረበሩ የሚኖሩ ከመብዛታቸው የተነሳ፤ እሴታችን ቀስ በቀስ እየጠለሸ ነው። በዚሁ ከቀጠልን አደጋ ላይ ነንና ዱዓቶች፣ መሻይኾች… ሁሉም የድርሻውን ተወጥቶ ወደ እሴቶቻችን እንመለስ።
በፊት «ኢስላም ካበለ ቀን ዘነበለ!» ነበር የሚባለው። ያኔ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ከእናቱ ልጅ ይልቅ ሙስሊሙን ባዳ እያመነ ብርና አማና ያስቀመጥ ነበር። ዛሬ ግን ነገሩ… የተገላቢጦሽ እየሆነ ነውና ይታሰብበት።
አላህ ወደ ዲናችንና ወደ ውቡ ኢስላማዊ እሴታችን ይመልሰን።
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿
🔻እየሱስ ስአምላክ ላለመሆኑ 10 ወሳኝ ማስረጃዎ'ች‼
1- እየ'ሱስ ክር'ስቶስ #ሁሉን_አዋቂ አልነበረም፡፡ ‼
እንደሚታወቀው አምላክ ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ ከዕውቀቱ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም፡፡ እ'የሱስ ክርስ'ቶስ ግን እንደ መፅሀፍ "ቅዱ'ስ" ገለፃ ይህንን መስፈርት አያሟላም፡፡
✅" ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ #ልጅም [ኢየሱስ ክርስቶስም] ቢሆን ከአባት [ከእግዚአብሔር] በቀር #የሚያውቅ_የለም።"
(የማርቆስ ወንጌል 13:32)
2- እየሱስ ክርስቶስ አንዲትም ጊዜ #እኔ_አምላክ_ነኝ ብሎ አያቅም‼
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር እጅግ ብዙ ቦታዎች ላይ አምላክነቱን ሲያውጅና ሲገልፅ እንመለከታለን!
እየሱስ ክርስቶስ ግን በተቃራኒው ስለዚህ ጉዳይ ትንፍሽ አላለም፡፡
እስኪ ከብሉይ ኪዳን ለአብነት እንመልከት‼
✅" እግዚአብሔርም አለው። #ሁሉን_ቻይ_አምላክ_እኔ_ነኝ፤ ብዛ፥ ተባዛም፤ "
(ዘፍጥረት 35:11)
✅" አለውም። የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 46:3)
✅"እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ። ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው። "
(ኦሪት ዘጸአት 16:11,12)
✅" ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር #አምላክህ_እኔ_ነኝ። "
(ኦሪት ዘጸአት 20:2)
3- እየሱስ በአዲስ ኪዳን የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል‼
እራሱ መፅሀፍ "ቅዱስ" እንደሚነግረን ደግሞ #የሰውን_ልጅን_ማመን_እንደሌለብን ይነግረናል‼
✅" ኢየሱስም። ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 8:20)
✅" ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን። ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 9:6)
✅" የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።"
(የማቴዎስ ወንጌል 12:8)
✅" ለደቀ መዛሙርቱ። የሰው ልጅ በሰው እጅ ይሰጥ ዘንድ አለውና እናንተ ይህን ቃል በጆሮአችሁ አኑሩ አለ።"
(የሉቃስ ወንጌል 9:44)
ሌላ ቦታ ባይብልን ስናነብ ደግሞ የሰው ልጅ መታመን እንደሌለበት ይነግረናል፡፡
✅(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 146)
----------
1፤ ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ።
2፤ በሕይወቴ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3፤ ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ።
4- እየሱስ ክርስቶስ የነበረው ስልጣንና ሀይል የእርሱ አልነበረም፡፡‼
✔ " ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥"
(የዮሐንስ ወንጌል 13:3)
✔ " እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 12:49)
✔" እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 5:30)
✔ " ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 7:16)
🔻
እየሱስ አምላክ ላለመሆኑ ምስክር ከሚሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው እየሱስ በራሱ አንደበት "#እኔ_አምላክ_አለኝ" ብሎ መናገሩ ነው፡፡
➍. እውነተኛ ኣምላክ ብቻ የሆንክ አንተን የላክኸውንም እየሱስ ክርስቶስ ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ሂወት ናት
( የዬሐንስ ወንጌል 17:3)
🔻እየሱስ አንድ አምላክ ብቻ የሆንከው አንተ ነህ ፡ አንተ ብቻ ነህ አምላክ እኔ የተላኩኝ መልክተኛህ ነኝ እያለ ለምን ክርስቲያኖች በተቃራኒው አንተ አምላክ እንጂ መልዕክተኛ አይደለህም አሉት?
➎. " ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ። በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ #አይደለም፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 12:44)
🔻እየሱስ ሲናገር እኔን መከተል ማለት የላከኝን አምላክ መከተል እንጂ እኔን ማምለክ አይደለም እያለ እየተናገረ ምነው ክርስቲያኖች ያለቦታው ቦታ ሰጥተው ከፍ አድርገው እሱኑ ተገዙት?
➏. " ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።"
(የማርቆስ ወንጌል 10:18)
🔻እየሱስ ቸር መባል እንኳ አልፈልግም እሱ የአምላክ መጠሪያ ነው ካለ፡ ምነው ታዳ ክርስቲያኖች ከእየሱስ አስተምህሮ ውጭ ሆነው ያለቦታው ቦታ ሰጥተው እየሱስን ቸር በማለት ተገዙት?
➐. እኔ #ከራሴ ኣንዳች ላደርግ #አይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳሎ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ኣልሻምና
( የዬሐንስ ወንጌል 5:30)
የራሱ ስልጣን የሌለው ፍጡር እንደት አምላክ ነህ ተብሎ ይመለካል? ኧረ እናስብ ሰዎች!!
አይበልጥም መልክተኛም ከላከዉ #አይበልጥም፡፡
(ዩሀንስ 13:16)
🔻እየሱስ እኔ መልዕክተኛ ነኝ ፡ መልዕክተኛ ደግሞ ከላከው ከአምላኩ አይበልጥም እያለ በይፋ እየተናገረ እንደት ክርስቲያኖች አንተ እራስህ አምላክ ነህ ካንተ በላይ ማንም የለም በማለት በተቃራኒው ተረዱት?
➒. ""ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰኣት ግን የሰማይ መላእክትም ልጅም ቢሆን ከኣብ በቀር የሚያውቅ የለም"
(ማርቆስ ወንጌል 13፡32)
🔻እየሱስ የትንሳዔ ቀን መቼ እንደሆነ አላውቅም እያለን ነው፡፡ እሷን የሚያውቀው አንድ አምላክ ብቻ ነው እኔ አላውቅም እያለ እንደት ክርስቲያኖች እየሱስ ሁሉን አዋቂ ጌታ ነው ብለው ሊያመልኩት ቻሉ?
ሁሉን የማያውቅ አምላክ አምላክ ይሆናልን? አስቡበት!!
➓. "የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ"
(ኤፌ 1፡17)
የተወሰደ🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿
"በአላህ ንግግር ልፍረድልሽ ወይስ በኢማሙ ሻፊዒ ንግግር"
ሲላት.....
"በኢማሙ ሻፊ ንግግር ፍረድልኝ; ኢማሙ ሻፊዒ የአላህ ንግግር ተረድተው ነው የፈረዱት: አንተ ግን በዚያ ልክ ልትረዳው አትችልም!!" አለችው።
🔻እዚህ ጋ ነው የተቸገርነው፦
ሁሉም ቁርኣን ሓዲስ እንደ ሚከተል ይሞግታል፤ ሁሉም እሱ ሐቅ ላይ ባላንጣው ባጢል ላይ እንዳለ ይሞግታል፤ ሁሉም ራሱ የዲን ጠባቂ ተቃራኒው የሱና ጠላት አርጎ ይሞግታል።
ለዚህ ሁሉ ብቸኛው መፍትሔ………
🔻የቁርኣንንና የሐዲሥ አስተምህሮት በሰለፎች ግንዛቤ ሊሆን ይገባል አለበለዚያ ሁሉም አቅሉን ያስገባበታል።
🔻ዕንቁ የነበሩ ቀደምቶቻችን ዲኑን የተረዱበትን ግንዛቤ መንገድ ይዞ መጓዝና መከተል ለኺላፍ መፍትሄ ነው።
🔻لا يصلح آخر هذه الأمة إلا بما صلح به أولها
🔻الكتاب والسنة على فهم السلف
▣ በድብቅ የተቀዳው የድምፅ ፋይል ሙሉውን
⌚️ 6:08:38 ሰዓት
📌 ለእውነት ፈላጊዎች ይቺ ፋይል በቂ መረጃና ማስረጃ ናት!
➩ አድምጣችሁ ፍረዱ ማን እንደተቀየረ
➩ ለተሚዮች የኡስታዝቻችሁ ውሸት ተገንዘቡ በምን እንደተስማሙ አድምጡ
- እንደ መርከዙ ሰዎች ያሉ ሰዎች ላይ መለያየት ኢጅቲሓዲይ ነው
- የመርከዙ ሰዎች ተብዲዕ ማድረግ አለማድረግ ሊያጣላን አይገባም
◍ O Altemiyun Listen the lies of your Teachers
https://t.me/Menhaje_Selef/21
https://t.me/Menhaje_Selef/
Repost from المَنهجُ السَّلفي لــيس لـه بَديل
#ከኣሕባሾች መንደር
እንዲህ እውነት እውነቷን ብትናገሩ ይሻላል በጥፋታችሁ ላይ የሌለ ውሸት ከመጨመር
አሏህ ከኣውቆ ኣጥፊነት ይመልስህ¡
በወልይ ስም የ‘ዙሁር ውዱዑ የተደረገበት ውሃ ጎርፍ ሆኖ ደረሳ ወስዶብኝ ያቃል…’ ሌላም ሌላም ለጆሮ መስማት የሚከብዱ ቅጥፈቶችን የሚነዙ ሰዎች መስማት የተለመደ ነው ነገር ግን ነቢዩ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) አስቀድመው…
ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
﴿يَكُونُ فِي آخِرِ الزَّمَانِ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ، يَأْتُونَكُمْ مِنَ الْأَحَادِيثِ بِمَا لَمْ تَسْمَعُوا أَنْتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ، فَإِيَّاكُمْ وَإِيَّاهُمْ، لَا يُضِلُّونَكُمْ وَلَا يَفْتِنُونَكُمْ﴾
“በመጨረሻው ዘመን ደጃሎች ቀጣፊዎች ይኖራሉ። እናንተም አባቶቻችሁም ያልሰማችኋቸውን ሐዲሶች ያመጡላችኋል። አደራችሁን ተጠንቀቋቸው። እንዳያጠሟችሁ። እንዳይፈትኗችሁ።”
ሙስሊም ዘግበውታል፡ 7
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የተከበራችሁ እህት ወንድሞች
እንደ ተለመደው በየ ሳምንቱ የደዕዋ ፖሮግራማችን እንደቀጠለ ነው
ዛሬ ደግሞ አዲስ ዜና የ ሀዚሂ ደዕወቱና ወዐቂደቱና ኮርስ ይሰጣል
የሼይኽ ሙቅቢል ሪሳላ
እንዳያመልጣችሁ
🎙በ ኡስታዝ ዐብዱ አልጀባር ሀፊዘሁሏህ
ደዕዋም ይኖራል
ዛሬ ማታ
በኢዮ 3:00⌚️
በሳዑዲ 9:00⌚️
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/+c8E_ovQaoLkyNTRk
https://t.me/+c8E_ovQaoLkyNTRk
በራያ ሙስሊሞች ዙሪያ ለተደቀኑ ችግሮች የመፍትሄ ሐሳብ
ሠ.ሚድያና ማህበራትን ማቋቋም
ሚድያ የሌለው ህዝብ ድምፅ የለውም። በዚህ ዘመን ከሁሉም በላይ ከፍተኛ አቅም ያለው መሳርያ ሚድያ ነው። የሚድያ ሀይል ተበዳይን በዳይ፣ በዳይን ተበዳይ፣ ቀይን ነጭ፣ ነጭን ቀይ አድርጎ ማቅረብ የሚችል ነው። ሚድያ የሌለው ህዝብ እውነት ቢይዝ እንኳን አሸናፊ መሆን አይችልም። የነጻነት ታጋዩ ማልክሎም ኤክስ ስለ ሚድያ እንዲህ ብሏል «ሚድያ በመሬት ላይ ከፍተኛ ሀይል ያለው ተቋም ነው፤ እነሱ (ሚድያ) ንፁሁን ጥፋተኛ፣ጥፋተኛው ደግሞ ንፁህ የማድረግ አቅም አላቸው ፤ ይህም ሀይል ነው። የብዙሀና አዕምሮ እንዲቆጣጠሩ አስችሏቸዋል።»
የሳተላይት ሚድያ ማቋቋም ባንችል እንኳን በማህበራዊ ሚድያ ድምፃችን ማሰማት ይኖርብናል። በፌስቡክ፣ዋትስአብ፣ቲውተር፣ዩትዩብ፣ ቲክቶክና ሌሎች የማህበራዊ ሚድያ አውታሮችን በመጠቀም ህዝባችንን ማንቃት እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ታሪካችን እና ማንነታችን እንዲያውቁ ማድረግ ይገባናል።
የምናደርገው እንቅሰቃሴው የሙስሊሙን ትግል የሚደግፍ፣በሙስሊሞች መካከል መቀራረብን የሚያመጣ መሆን
ይኖርበታል።
ሙስሊሙን ሊወክሉ የሚችሉና ችግሮቹን የሚፈቱ ሲቪል ማህበራትና የበጎ አድራጎት ተቋማት መመስረት ይኖርበታል።
የቲሞችንና ሚስኪኖችን የሚረዳ፣ መስጂዶችና መድርሳዎችን የሚገነባ በሙስሊሞች መካከል መቀራርብ የሚፈጥር አቃፊ ተቋም መመስረት አስፈላጊ ነው።
ታሪክ፣ማንነትና ባህል የሚያጠና የሚያስጠና ተቋም በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ተፅኖ መፍጠር እንደሚችል የሀረር ሙስሊሞችን መመልከት ይቻላል። የራያ ሙስሊሞች ጠንካራ ተቋም ሰላልመሰረትን ታሪካችን፣ማንነታችን
እየጠፋና በሌሎች እየተዋጠ በመምጣቱ ሙስሊሙ የባለቤትነት ስሜት እንዳይፈጠርበት አድርጓል።
ጠንካራ ማህበራት ቢኖሩን ከላይ የጠቀስናቸው መፍተሔዎች በቀላሉ ማስፈጸም እንችል ነበር። ሰለዚህ ህዝበ ሙስሊም ኢስላማዊ ተቋማትን እንዲመሰረቱ የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል
Repost from የራያ ሰለፍዮች ቻናል
ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዴህ ይላሉ
አንድ ሰው በሚሰራው ወንጀል ምክኒያት
ከአሏህ ዘንድ ያለው ክብር እና ልቅናው ይወርዳል
አልፍም ከሰወች ዘንድም የተዋረደ ይሆናል
ስለዚህ በተቻለን መጠን ወንጀልን እንራቅ
“ዝምታ ከጥበብ ነው፤ነገር ግን የሚተገብሩት ጥቂቶች ናቸው።”
አቡ ደርዳእ رضي الله عنه
[ ኢብኑ ዐብዱል በር /ጃሚዑ በያኑል-ዒልም ]
የሙሐመድኑር ቤተሰቦች፦
1- ኡስታዝ ሙሐመድሲራጅ መ/ድ ኑር
3- ኡስታዝ ዐብዱልጀባር ሙ/ድ ኑር
3- ኡስታዝ ዐብዱሶመድ ሙ/ድ ኑር
4- ኡስታዝ አንዋር ሙ/ድ ኑር
5- ኡስታዝ ሰዒድ ሙ/ድ ኑር
ተመልከት!!! የመጀመሪያው ልጅህ በመጥፎውም በጥሩውም ለተከታይ ወንድሞቹ አርአያ ይሆናል።
