✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል
Открыть в Telegram
ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
195
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-730 дней
Архив постов
የትግራይ ሕዝብ ስም እየተጠራ የተሰበሰበ ገንዘብ ህወሓት በየመንገዱ በዚህ መልኩ ጥሎትና ደብቆት መገኘቱ እጅግ ያሳዝናል!
የትግራይ ሕዝብ በድህነት፣ በረሃብና በጦርነት መከራ ውስጥ እያለፈ፣ በስሙ የተሰበሰበ ገንዘብ በየመንገዱ ተጥሎ ህወሓት ምን ያህል የትግራይ ህዝብ ጠላት እንደሆነ በቂ ማሳያ ነው:: የዚህ ገንዘብ ምንጭ የፌደራል መንግስት ለትግራይ ህዝብ ብሎ እየሰጠ የነበረው የክልሉ በጀትና ህወሓት ከትግራይ ህዝብ የሰበሰበው ነው::
ይህ ገንዘብ ለተራበው ምግብ፣ ለታመመው መድኃኒት፣ ለተፈናቀለው መጠለያ፣ ለተማሪው ትምህርት መዋል የሚችል ሀብት ነበር ህወሓት ግን ይሄን አላደረገውም ተደራጅቶ ከትግራይ ህዝብ ጉሮሮ እየቀማ ነበር የኖረው::
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ!
ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት ነው!
በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው!
📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ!
በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች!
በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል።
በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል።
ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል።
ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ።
እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው።
⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን!
የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን።
አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው።
በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ!
አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ».
“የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።”
📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631
ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው።
እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል።
ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል።
⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው!
🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች
💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
1000469830277
💳 2. ዘምዘም ባንክ
0005649620101
💳 3. ሂጅራ ባንክ
1000030300001
📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው።
ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ
ስልክ፦+251914718693
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ!
🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!
አሰላአለይኩም ያጀመአተል ኸይር!!!
ራያ ላይ በነበረው የሰላም ችግር ምክነያት ስርጭታችን በተወሠነ መልኩም ቢሆን መቆራረጥ አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም ኢንሻ አላህ ፕሮግራማችን ልክ እንደተለመደው የሚቀጥል ይሆናል
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
ከኢማሙ አህመድ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ነው።
https://t.me/ansuar_muhammed_0088?livestream=2cc676c15151aa8a49
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Aviation Universityየመግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎችን በሂጃብ ምክንያት ስለምን ያገላል?
♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️ ♦️
Mujib Amino
የትምህርት በር በሂጃብ ምክንያት ሲዘጋ የምንታገላችሁ እንጂ ቁጭ ብለን የምናይ ነፈዞች አይደለንም!!!
ትምህርት የሰውን ችሎታ፣ ብቃትና ዕውቀት የሚመዝንበት መስክ እንጂ፣ የእምነት መገለጫን ትኩረት አድርጎ የትምህርት እድልን የሚያሳጣበት ቦታ መሆን የለበትም።
ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና አልፈው፣ በትምህርት ብቃታቸው የመማር እድል ካገኙ በኋላ፣ በሚለብሱት ሂጃብ ምክንያት መመዝገብ እንደማይችሉ በጥላቻ ተሞልቶ በድፍረት ማሳወቅ፣ የእኩልነት መርህን፣ የሃይማኖት ነፃነትን፣ የትምህርት እድልና የተቋማት ተጠያቂነት ጉዳይ ሆኖ ግዙፍ ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ይሆናል።
ስለዚህ ሕዝባችን ጉዳዩን በትኩረት እንዲከታተል እናሳስባለን። ተማሪዎቻችንም በችሎታቸው ያገኙትን የትምህርት እድል በሕግና በፍትሕ መሠረት እንዲያገኙ ድምፃቸው እንዲሰማ መደገፍ ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በሕግ ፊት እኩል መሆናቸውንና በሃይማኖት ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች መድልዎ እንዳይደረግባቸው ይደነግጋል። አንቀጽ 27 ደግሞ የሃይማኖትን ነፃነትና እምነትን በአምልኮ፣ በአሠራርና በሌሎች መገለጫዎች የመግለጽ መብትን ይጠብቃል። ሆኖም ሕገ መንግስቱን ካለህፍረትና እየጣሰ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ለምን ስርዓት አጣ? በተለየ ሁኔታ ሙስሊም ተማሪዎችን ማጥቃቱ ለምን? ተቋም በስሙ መጀመሪያ 'የኢትዮጵያ' የሚል ግዙፍ የሁሉምና የተከበረ መጠሪያ ይዞ ለምን የትንሾችን ሃሳብ ያራምዳል?
በአሁኑ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ይፋዊ የመግቢያ መስፈርቶች የትምህርት ዝግጅት፣ የመግቢያ ፈተና፣ የዕድሜ፣ የጤና፣ የደህንነትና ሌሎች መስፈርቶችን ይዘረዝራሉ፤ በእነዚህ ይፋዊ መስፈርቶች ላይ ሂጃብን እንደ የመግቢያ መስፈርት የሚያስቀምጥ ድንጋጌ የለም! ማድረግ ከፈለጋችሁ በግልፅ ሂጃብ አይቻልም በሉና ፊትለፊት እንጋፈጣችሁ!!!
የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 1152/2019 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዳደር በግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነት መርሆች ላይ እንዲመሠረት ያስቀምጣል። እንዲሁም የ2025 የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅ 1368/2025 ትምህርትን እንደ መሠረታዊ የሰው ልጅ መብት በመገንዘብ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን እንደ ዋና መርሆች ያነሳል።
እዚህ ላይ ዋናው ነጥብ ሂጃብ ብቻ አይደለም። አንድ ዜጋ በችሎታው ካለፈ በኋላ በማንነቱ ወይም በሃይማኖታዊ መገለጫው ምክንያት የተማሪነት እድሉን እንዳያጣ ሕግ ምን ያህል ጥበቃ ያደርግለታል? የሚለው ነው። የሕገ-መንግሥቱ መልዕክትም ግልጽ ነው፤ ሴቶች በሕገ-መንግሥቱ የተሰጡ መብቶችን ከወንዶች ጋር እኩል የማግኘት መብት አላቸው።
ትምህርት እውቀትን እንጂ መድልዎን የሚደግፍ አሰራር አይደለም። ሂጃብ ለሚለብስ ሴትም ሆነ ለማይለብስ፣ መመዘኛው ችሎታ፣ ብቃትና ሕጋዊ መስፈርት መሆን አለበት። ከዛ ውጪ ያለፉ ጭቆናዎችን በዘመናዊ አለም ዉስጥ ጎትቶ ለማምጣት የሚደረግ እንቅስቃሴን እንደግለሰብ እንደማህበረሰብ እንደህዝብ ተቋሙንና አመራሮችን በትጋትና በምሬት እንታገለችኃለን!
የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ያቀረበዉን የመግቢያ ፈተና በጥሩ ዉጤት ያለፉ ተማሪዎቻችንን ከእንግት ነፃ በሆነ መልኩ በአፋጣኝ እንድትመዘግቡና ተማሪዎቻችንን ይቅርታ እንድትጠይቁ እናሳስባለን!
#ሂጃብ #ትምህርት #የሰብዓዊመብት #ፍትሕ #እኩልነት #EthiopianAviationUniversity
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
@top fans
Ethiopian Human Rights Commission
Ethiopian Airlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ
በራያ ቆቦ በኩል ከታጣቂዎች በተተኮሰ መድፍ የአራት (4) ሰዎች ህይዎት አለፈ ‼️
በራያ ቆቦ በኩል ቆቦ ከተማ አካባቢ ላይ በሻሂ ቡና ስራ ተሰማርተው የሚሰሩ አራት(4 )ንፁሀን ግለሰቦች ስራቸውን እየሰሩ ባሉበት አጋጣሚ የተተኮሰ መድፍ በላያቸው ላይ እንዳረፈባቸውና ወዳውኑ ህይዎታቸው ሊያልፍ እንደቻለ መረጃውን ከስፍራው ያሉ ነዋሪዎች አድርሰውኛል። ጉዳዩ ከተከሰተ ገና አንድ ሰአት ሆነው ያሉት ነዋሪዎች አካባቢው ላይ ንፁሀን ዜጎች ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸውም ነግረውኛል።
እባካችሁ በአካባቢው ላይ የምትኖሩ ንፁሀን የሚገባችሁን ጥንቃቄ አድርጉ !
ሰላም ለራያ ህዝብ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አሰላሙ ዐለይኩም
~
ባለፈው ሳይመቸኝ በመቅረቱ የተላለፈው ሰይድ ቁጥብን የሚመለከተው ፕሮግራም ዛሬ ምሽት 3፡00 ላይ ይኖራል።
በዚህ የቴሌግራም ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፣ ኢንሻአላህ :-
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
"የአላህ ወሊዮች አውሊያዎች እነዚያ ሲታዩ ሲመለከቱአቸው አላህ የሚታወስባቸው የሚዘከርባቸው ናቸው።"
የአላህ ወልዮች (አውሊያዎች) ማለት ጥምጣም ጠምጥመው፣ መጋረጃ ጋርደው የሚቀመጡ፣ ወይም ደግሞ ‘የኛ ወሊዬች ውዱዉ ያደረጉበት ውሃ ጎርፍ ሆኖ ሰው ይወስድ ነበር፣ የኛ ወሊዮች አንበሳ ይጋልቡ ነበር ኢትዮጵያ ተቀምጠው ሶላት ሚሰግዱት መካና መዲና ነው’ እያሉ የሰው ልጅ አዕምሮ ሊቀበለው የማይችለው ተረት ተረት የሚወራላቸው ሳይሆን ትክክለኛ የአላህ ወሊዮች መላያቸው ኢማንንና አላህን መፍራት በላያቸው የሚታይባቸው የመልእክተኛውን ሱና ሙሉ በሙሉ በላያቸው ተግብረው አርእያ በመሆን የሚታዩ ናቸው።
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
የድሮ ስርዓት ናፋቂው የከላላ ከተማ ከንቲባው ህገ ወጥ እስርና ወከባ!
የከላላ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ ጥላሁን የክርስትና እምነት ተከታይ ናቸው። ከላላ በአብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ያለበት ከተማ ቢሆንም የህዝበ ክርስቲያኑ መብት ተከብሮ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በተቃራኒው በሙስሊሙ ማህበረሰብ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የኢስላማዊ ዳዕዋ ይዘትን ጭምር ካልወሰንኩና ለምን ዳዕዋ ታደርጋለህ የሚል ከንቲባ የመጅሊስ አመራር የሆነውን ወንድም ኢዘዲን ሻፊን አስረውታል።
የከተማው ከንቲባ ይህንን ኢህገመንግስታዊ፣ አሳፋሪና ህዝብን የሚያቃቅር ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ወንድማችንን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቁት እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትም በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አመራር ጋር በመነጋገር መሠል ድርጊቶችን እንዲቃወምና የወንድማችንን መብትና የመጅሊስ ክብር እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን።
ከከላላ ሙስሊሞች
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የማለዳ መልእክት (48)
~
መጅሊስ በታሪኩ ከመንግስት ተፅእኖ ነፃ ሆኖ አያውቅም። ለዚህ ዋናው ምክንያት መጅሊሱ ላይ የሚቀመጡ አካላት ባህሪ ሳይሆን የፖለቲከኞቹ ፍላጎትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህሪ ነው። ከዚያ የሚቀመጡ ሰዎች ድባቡን ያዩና ከ "አየር ንብረቱ" ጋር ራሳቸውን ያስማማሉ። የ1987ቱ የአንዋር መስጂድ ብጥብጥ ምክንያት ከጥቅም ግጭት ባለፈ የመንግስት አካላት ፍላጎት ከጀርባ ነበር። በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ አካላት የተሻለ የመንግስት ድጋፍ እንዳላቸው ያስቡ ነበር። ኋላ ላይ አሕ^ባሽ ከሊባኖስ ተጋብዞ የገባውም ከመጅሊስ ሰዎች ፍላጎት ባለፈ የመንግስት ፍላጎት ስለነበር ነው።
ዛሬ ላይ ያለው የፖለቲካውን ነፋስ ተከትሎ የመጣው የመጅሊስ ለውጥም ያለቀለትና የማይነካ አይነት አይደለም። ነገ ሊቀየር ይችላል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ አንዳንድ ደስ የማይሉ ሽታዎች ያሉ ይመስላል። መጅሊስ ላይ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ይህንን ተገንዝበው ለህዝባችን ዐቂዳውን ማስተማር ላይ ወይም ለማስተማር ምቹ ድባብ እንዲኖር ማድረግ ላይ መሬት የረገጠ ስራ ሊሰሩ ይገባ ነበር። ነበር የምለው በተግባር እየሆነ ስላላይደለ ነው። በተለይ አማራ ክልል ላይ ከ'ኮስሞቲክ' ስራዎች በመውጣት ዛሬ ላይ ቆፍጠን ብሎ መስራት ይሻል ነበር። ነገሮች ቢቀያየሩ ተፅእኖው ከሌሎች አካባቢዎች ይለያል።
ሌላው ቢቀር ለተሻለ መስለሓ ብላችሁ የገባችሁ ወገኖች ራሱ ከልብ በመመካከር ህዝብ ላይ ብትሰሩ መልካም ነው። ጊዜው አሁንም አልረፈደም። ብዙ መራመድ የሚያስችላችሁ አቅም ባይኖራችሁ እንኳ በአቅማችሁ ልክ የምትችሉትን ሳትሰሩ ጊዜው እንዳያልፍ ብታስቡበት ይሻላል። እውነት ለመናገር በተበላሸ ዐቂዳውም ቢሆን ሳይልፈሰፈስ ቆፍጠን በማለት እና መሬት የወረደ ስራ በመስራት በኩል ከመጅሊስ ተቋማት የተባረረው አሕ^ባሽ የተሻለ ትጋት አለው። አሕ^ባሽ የመጅሊሱ መዋቅር በእጁ ሳለም ያለምንም ይሉኝታ ህዝብን ለመለወጥ እስከ ደም ጠብታ ታግሏል። የያዘው ዐቂዳ ክር^ፋትና የመንግስት ዓይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ነው ወደ ህዝብ ልብ ከመግባት እንቅፋት የሆነበት።
ከመሆኑም ጋር ለብልሹ ዐቂዳው በመዋደቅ ላይ ከመጅሊሱ ደጅ ርቆም አልቆመም። ዳግም ከተመለሰም ከቀደመው የበለጠ እንደሚጠቀምበት ይጠበቃል። ያ እንዳይሆን ወይም እውን ቢሆን እንኳ ጉዳት ለመቀነስ ደግሞ ፖለቲከኛ ተደግፎ መተኛት ሳይሆን ህዝብን ትክክለኛውን አስተምህሮት ማስታጠቅ ነው የሚገባው። የሹማምንትን ጫና ለመጋፈጥ ወይም ለመቀነስ ትክክለኛው መንገድ ደሞ ከአላህ በታች ህዝብን ማንቃት ነው ሁነኛው ስራ። አላህ ልብ ይስጠን።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 02/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የእውቀትን መራራነት ለአፍታ እንኳን ያልቀመሰ ሰው እድሜውን ሙሉ የድንቁርናን ውርደት ይጎነጫል።በወጣትነቱ ጊዜ እውቀት ያመለጠው ሰው ላመለጠው (ለቀረው) ሕይወቱ አራት ግዜ የጀናዛ ተክቢራ አድርጉበት (እንደ ሞተ ቁጠሩት)።
ኢማም አሽ-ሻፊኢ ረሂመሁሏህ
ይህ ግጥም ዕውቀት ለማግኘት የሚከፈል ትዕግስት እና ድካም ከጊዜያዊ መራራነቱ ይልቅ የዕድሜ ልክ ክብርን እንደሚያጎናጽፍ፣ የወጣትነት ጊዜ ደግሞ ለዕውቀት ቀዳሚው እና ወሳኙ ወርቃማ ዕድሜ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።
Repost from Ansuar Muhammed {አንሷር ሙሐመድ} Official Channel
👁👁👁👁አስደሳች ዜና
የአወሊያ የጤና ማዕከል መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ካደረገው የአል - በስር ኢንተርናሽናል ፍውንዴሽን ጋር በመተባበር ነፃ የሆነ የአይን ሞራ ገፋፋ ህክምና ከ መስከረም 4 እስከ 7/ 2019 አ.ል ይሰጣል።
👉በመሆኑም ከጳግሜ አንድ ጀምሮ ዊንጌት ተሻግሬ በሚገኘው የአወሊያ ጤና ጣብያ መጥተው መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስንገልፃላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
👉ለበለጠ መረጃ
+251911599329
+251912410372
👉ይደውሉ
እባክዎ መረጃውን share ያድርጉ
Telegram
@cataract2026
ሰበር መረጃ :- የደሴ ከተማ አስተዳደር አሻጥር ተጋለጠ‼️
የደሴ ከተማ አስተዳደር ያፀደቃቸው አዳዲስ የመንገድ ስያሜዎች የህዝብን አብሮነት የሚፈትኑ ናቸው ተባለ‼️
#ደሴ|| ደሴ ከተማ የኢትዮጵያ የባህል፣ የታሪክና የንግድ ማዕከል፣ የወሎዋ እንብርትና መናገሻ ናት። ከተማዋ ከትውልድ ትውልድ የተሻገረ የኑሮ ስልት፣ የሰላም ማህደር እና የበርካታ ህዝቦች አብሮነት መገለጫ የሆነች ታሪካዊ ቦታ ነች።
ይሁን እንጂ ባለፉት ጊዜያት የከተማዋ አስተዳደር አካላት ያደረጓቸውና ህዝብን በግልጽ ያላካተቱ ውሳኔዎች በተለይም የጎዳናዎች፣ የአደባባዮችና የአስፓልቶች ስያሜ ለውጦች ማህበረሰቡን በእጅጉ እያሳሰቡና እያስከፉ ይገኛሉ።
ይህ ጉዳይ ከስም ዝውውር የዘለለ፣ የህዝብን አክብሮት፣ የጋራ ታሪክ እና የበርካታ አሥርት ዓመታት አብሮነት የሚፈትን አደገኛ አካሄድ በመሆኑ ጥልቅ ትንተና የሚሻ ነው።
ማንኛውም የከተማ አስተዳደር እድገትና ለውጥ መሰረት መሆን የሚገባው የነዋሪውን ፍላጎት፣ የባህል እሴቶችና የጋራ ስምምነት ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት። ዛሬ ግን በደሴ ከተማ የሚታዩት የአደባባይና የመንገድ ስያሜ ለውጦች ከህዝብ እውቅና ውጪ፣ ከማህበረሰቡ ሰፊ ውይይትና ይሁንታ በተነጠለ መልኩ፣ በአመራሩ የጠባብ ፍላጎት ብቻ የሚከናወኑ ሆነው ተስተውለዋል።
ህዝብን ባሳተፈና ግልጽ በሆነ አሰራር ፋንታ በግልጽ አድሎአዊነትና የህዝብን ድምጽ በቸልተኝነት ማለፍ በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ላይ ትልቅ ስጋት የሚደቅን የሰዓት ቦምብ ከመቅበር ጋር የሚተካከል ነው።
የደሴ ከተማ ስያሜዎችና ታሪካዊ አካባቢዎች በዘመናት ሂደት ውስጥ ከህዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ ከባህሪው እና ከማህበራዊ ትስስሩ ጋር የተሳሰሩ ናቸው። አመራሮቹ ግን ያልበላቸውን እያከኩ እና በህዝብ ዘንድ ምንም አይነት ጥያቄና ፍላጎት በሌለባቸው ጉዳዮች ላይ አላስፈላጊ ውዝግቦችን መፍጠራቸው ከተማዋን ወደ ማህበራዊ አለመረጋጋት ሊያመሩ የሚችሉ የተሳሳቱ ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች (Priorities) ላይ ተጠምደዋል የሚያሰኝ ነው።
በጣም የሚያሳዝነውና የህዝቡን ስሜት የሚጎዳው አንኳር ጉዳይ የአካባቢው የስያሜ ስርጭት ነጸብራቅ ነው። ደሴ የበርካታ ሃይማኖቶችና የሰላም መኖሪያ ስትሆን የአብላጫውን ማህበረሰብ ማንነትና ታሪክ ፍጹም ባላማከለ መልኩ ሚዛናዊነት የጎደለው አካሄድ መከተሉ ነው።
በከተማዋ ውስጥ እንደ ስላሴ በር፣ቅዱስ ገብርኤል ናንጉሥ ሚካኤል የመሳሰሉ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እምነትና ታሪክን ብቻ የሚያንጸባርቁ ስያሜዎች በስፋት ሲሰጡ በከተማዋ ታሪክና እድገት ውስጥ የማይተካ አሻራ ያለው እንዲሁም የአብላጫውን ህዝብ ድምጽና ማንነት የሚወክለውን የሙስሊሙ ማህበረሰብ አስተዋጽኦ የሚያሳይ አንድም ትርጉም ያለው ስያሜ አለመኖሩ ነው።
ይህ ድርጊት አብላጫውን ህዝብ በግልጽ የመናቅ፣ የማሳነስና የጋራ ባለቤትነት ስሜቱን የመገዳደር ያህል የሚቆጠር ነው። ህዝብን በእምነቱና በማንነቱ መለያየት፣ ማግለል ወይም መብቱን አለማክበር የከተማውን አመራሮች አቅጣጫ ማጣት የሚያሳይ የዝቅጠት ጥግ ነው።
አመራር ማለት የህዝብ አገልጋይና የሰላም ዋስትና መሆን እንጂ በህዝብ ላይ መፈንጨትና ማህበራዊ ውጥረት መፍጠር አይደለም የደሴ ከተማ አመራሮች ይህንን ስህተት አሁንም አረጋግጠው የህዝብን ሰላም፣ አብሮነትና የጋራ ታሪክ ከግምት በማስገባት የተወሰዱትን አድሎአዊ ውሳኔዎች መገምገም እና ፍትሃዊና አካታች መፍትሄዎችን መፈለግ አለባቸው።
አረንጓዴ ለበሰው በምስሉ የሚታዩት የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የበላይ ጠባቂ የክርስትና እምነት አባት ሲሆኑ ከአመታት በፊት በሞት የተለዩ ናቸው።
#የደሴዎቹ #መውሊድ #አክባሪዎች #ውርደት።
ድነል ኢስላም የሰው ልጅ ማህበራዊ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን የቁምነገሮች ሁሉ ማዕከል እና የክብር መገለጫ ነው ይሁን እንጂ ዛሬ በደሴ ከተማ በመውሊድ አከባበር ስም እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ሀይማኖትን ለግል ወይም ለቡድን ፍላጎት ማዋል ከሁሉም በላይ ደግሞ ድንን መቀለጃ ማድረግ ሆኗል።
ድን ነው ብለው በያዙት እና በሚያራምዱት አካሄድ ፖለቲካ ይመስል የእምነቱ ባለቤት ያልሆኑ ወይም ከጉዳዩ ጋር ፍጹም ንክኪ የሌላቸውን አካላት ፎቶዎች እስከ መስቀል መድረሳቸው ምን አይነት ዝቅጠት እና ድንቁርና እንደሆነ ለማየት በቂ ነው።
ሰውን ባትፈሩ ቢያንስ አሏህን መፍራት እና ሀይማኖትን ከዚህ አይነት ውርደት መጠበቅ አያዳግትም ነበር። የቢድአ ተግባር አቅጣጫ ሲያስት ድኑን በዚህ ልክ ማሳነስ እና ማውረድ ምን የሚሉት አሳፋሪ አካሄድ ነው?
እስኪ እንጠይቃቸው የትኛው የሀይማኖት ተከታይ ነው ባከበረው የእምነት ስርዓት ላይ ከእምነቱ ተቃራኒ ወይም ውጭ ያሉ ሰዎችን ምስል ለጥፎ ያዩት? አላማችሁ የነብዩን (ሰ.ዓ.ወ) መውሊድ ማክበር ከሆነ ከዚህ ድርጊት ጋር ምን አገናኘው? የሌለ ባዕድ አቀንቃኝ ባህል አምጥቶ መዝቀጥ እና መዘባረቅ ለዲን ክብር የሚሰጠው ቦታ ምን ያህል ራቁቱን እንደቀረ የሚያሳይ ነው።
ዲንን መቀለጃ ማድረግ በዱኒያም ሆነ በአኼራ ለከባድ ውርደት ይዳርጋል ህዝብን ማሳቅቅ፣ የሀይማኖቱን ክብር ማጉደፍ እና ህዝብን ማሳሳት ታሪክ ይቅር የሚለው ስህተት አይደለም። ዛሬ ዝም ተብሎ የሚታለፍ ከሆነ ነገ ዲኑ የሚለወጠው በሰዎች ፍላጎት ልክ ነው። ስለዚህ ይህንን እጅግ አሳፋሪ እና ፀረ-እምነት የሆነ አካሄድ አጥብቀን ልንቃወመው እና የዲናችንን ክብር ከሰዉ ሰራሽ ውርደት ልንጠብቅ ይገባል።
