ተዝኪራህ | Tazkirah | تَذْكِرَة
Открыть в Telegram
🎀ሴት ልጅ የዲን እውቀቶችን ሳታውቅ ስትቀር ◈1_ባሏን ታደክማለች ◈2_ልጆቿን ታበላሻለች ◈3_ኡማውን ታጠፋለች ►ኢብኑል-ቀዩም (رحمه الله تعالى) ለዛ እውቀት ተማሩ ባረከአሏሁ ፊኩም።
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
5 539
Подписчики
Нет данных24 часа
+517 дней
+33630 дней
Архив постов
^ቲክቶክ^
كم رأينا من امرأة كانت تستحي، فلما جاء "تيك توك" نزع عنها حياءها، فبدأت تكثر الكلام مع الرجال، ويا له من ضرر عظيم!
➮ ስንትና ስንት ሴቶችን አየን ቀድሞ በእፍረት የታወቁ፣ ነገር ግን "ቲክቶክ" በመጣ ጊዜ እፍረታቸውን የገፈፋቸው፤ ከወንዶችም ጋር ማውራትና መቀለድ ያበዙ፤ ይህም እንዴት ያለ ትልቅ ጉዳት ነው!
◈እናማ እህቶቼ ይሄን 'ቲክቶክ' ተጠንቀቁ!
አይ እኔ ጥሩ ነገር ነው ምሰራበት ልንል እንችላለን ግን ብዙዎቹ በዚህ ምክንያት ገብተው ነው ገደል የገቡት!
◉ ወሏህ ስንት ሰው አይየን በቲክቶክ ምክንያት ከሱና የወረደን ስንት እህቶችን አየን በዲን ስም ወተው ወንድ እራሱ ለመናገር የሚያፍረውን ቃል ስናገሩ ያውም ወንድና ሴቱ ቤተሰበሰበበት 'ሱብሀናሏህ' ስንቱን አውርተን እንችላለን!
🔖ቲክቶክ የማትጠቀሙ አሏህን አመስግኑ እና ፅናትም እንድሰጣችሁ ለምኑት፣የሚትጠቀሙ ደግሞ በቻላችሁት ያክል ለመውጣት ጥረት አድርጉ አሏህም ከዚህ ቆሻሻ እንድያወጣችሁ ለምኑት?
⚠️ የቲክቶክ አደጋዎች:-
⓵ከቁርአን ማራቅ
⓶ከዝክርና ከሶላት ማራቅ
⓷የልብ ጠንካራነትና እምነት መዳከም
⓸የጊዜ መባከን
⓹ሪያእ (ለሰዎች መታየት መውደድ)
⓺የሴቶችና የወንዶች አውራ ሰውነትን መመልከት
⓻ወንጀል ማስፋፋት
⓼ሐሜትና ሰዎችን ፣ሙዝቃና ዘፈን፣መንዙማና ነሽዳ የመሳሰሉት መላመድ የመሳሰሉ አደጋዎች አሉት ይሄን ለመጥቀስ ያክል ነው ተቆጥሮ አያልቅም።
مع السلامة
✍️ወንድማችሁ አቡ ሱፍያን (ኢብኑ አብደሏህ)
📲 ቻናል፦ t.me/nesiheti_linisa
Repost from 📡 ኢብኑ ተይሚያህ - Ibn Taymiyyah (የእውቀት ማእከል)
📡 ዐቂደቱ አህሊሱናህ የተሰኘው ኪታብ ሙሉ ደርስ ሪከርዶች፦
👆በመርከዙ ለሁለተኛ ዙር የተቀራ!
📚 የኪታቧን pdf ለማግኘት
https://t.me/ibnuteimiyya/611
https://t.me/ibnuteimiyya/611
ክፍል👉❶
https://t.me/ibnuteimiyya/612
https://t.me/ibnuteimiyya/612
ክፍል👉❷
https://t.me/ibnuteimiyya/613
https://t.me/ibnuteimiyya/613
ክፍል👉❸
https://t.me/ibnuteimiyya/614
https://t.me/ibnuteimiyya/614
ክፍል👉❹
https://t.me/ibnuteimiyya/615
https://t.me/ibnuteimiyya/615
ክፍል👉❺
https://t.me/ibnuteimiyya/616
https://t.me/ibnuteimiyya/616
ክፍል👉❻
https://t.me/ibnuteimiyya/617
https://t.me/ibnuteimiyya/617
ክፍል👉❼
https://t.me/ibnuteimiyya/618
https://t.me/ibnuteimiyya/618
ክፍል👉❽
https://t.me/ibnuteimiyya/619
https://t.me/ibnuteimiyya/619
ክፍል👉❾
https://t.me/ibnuteimiyya/620
https://t.me/ibnuteimiyya/620
ክፍል👉❿
https://t.me/ibnuteimiyya/621
https://t.me/ibnuteimiyya/621
ክፍል👉❶❶
https://t.me/ibnuteimiyya/622
https://t.me/ibnuteimiyya/622
ክፍል👉❶❷
https://t.me/ibnuteimiyya/623
https://t.me/ibnuteimiyya/623
ክፍል👉❶❸
https://t.me/ibnuteimiyya/624
https://t.me/ibnuteimiyya/624
ክፍል👉❶❹
https://t.me/ibnuteimiyya/625
https://t.me/ibnuteimiyya/625
ክፍል👉❶❺
https://t.me/ibnuteimiyya/626
https://t.me/ibnuteimiyya/626
ክፍል👉❶❻
https://t.me/ibnuteimiyya/627
https://t.me/ibnuteimiyya/627
ክፍል👉❶❼
https://t.me/ibnuteimiyya/628
https://t.me/ibnuteimiyya/628
ክፍል👉❶❽
https://t.me/ibnuteimiyya/629
https://t.me/ibnuteimiyya/629
ክፍል👉❶❾
https://t.me/ibnuteimiyya/630
https://t.me/ibnuteimiyya/630
ክፍል👉❷⓪
https://t.me/ibnuteimiyya/631
https://t.me/ibnuteimiyya/631
ክፍል👉❷❶
https://t.me/ibnuteimiyya/632
https://t.me/ibnuteimiyya/632
ክፍል👉❷❷
https://t.me/ibnuteimiyya/633
https://t.me/ibnuteimiyya/633
ክፍል👉❷❸
https://t.me/ibnuteimiyya/634
https://t.me/ibnuteimiyya/634
ሙሉ ደርሱ ከነ ኪታቡ በአፕ የተዘጋጀውን ለማግኘት ከስር ያለውን ይጫኑ
https://t.me/ibnuteimiyya/635
https://t.me/ibnuteimiyya/635
🔖አድስ ደርስ ልንጀምር ነው ግቡ
https://t.me/nesiheti_linisa?livestream=5807aa8e3154d90906
🌟 አስደሳች ዜና 🌟
📖 ተከታታይ የደርስ ጥሪ 📖
🔖ትዕግስት (ሶብር) በኢስላም ውስጥ ያለው ቦታ እና ምንነቱ በስፋት የሚዳሰስበት ልዩ የኦንላይን ትምህርት ተዘጋጅቶላችኋል።
📚 «ቃዕደቱ ፊ አስ-ሰብር»
«قاعدة في الصبر»
✍🏻 አዘጋጅ፦ ሸይኹል ኢስላም አብኑ ተይሚያህ
🎙 አቅራቢ፦ ኢብኑ አብደሏህ
🗓 ቀናት፦ ዘውትር ቅዳሜ እና እሁድ
⏰ ሰዓት፦ በኢትዮ ማታ 3:00
📲 ቻናል፦ t.me/nesiheti_linisa
📖 PDF፦ https://t.me/nesiheti_linisa/1449
🔖 በሰፊው ሼር ይደረግ! 🔄
Repost from የሙመይዓ መንጋ ጥመት በመረጃ ሲጋለጥ⓵
✍ ጨለማ ምን ቢያደቀድቅ በአንድ አምፖል - እውነት ሲገለጥ ውሸት ይሸሻል!
ክፍል ሁለት (02)
4ኛ, እንዲህ ብሏል፦ «ትላንት እኛ የፈጠርነውን አጥር ካልገባችሁ ብላችሁ ሀገር ሲያምሱ፣ የሰለፊዮችን አንድነት ሲያፈራርሱና ዳዕዋ ሲበትኑ ይህ የሸሪዓ መመሪያ የት ነበር? ዛሬ የጨነቀ እለት ስብሰባ ተቀምጦ "እንዋደድ" ማለት ምን ያህል የጽናትና የመርህ ችግር እንዳለባቸው ያሳያል።»
👆ለዚህ የደነበረ አስተሳሰብ የምሰጠው መልስ፦
አንደኛ፦ ሰለፍዮች ሀቅን ወደ መከተል እንጂ ወደ አስተሳሰባቸው አይጣሩም። ወደ አስተሳሰባቸው የሚጣሩት ኢኽዋኖች፣ አህባሾች፣ ሙመይዖች ወዘተ...የመሳሰሉት የቢድዓ ሰዎች ናቸው። ሰለፍዮች ወደ ሰለፍያ ነው የሚጣሩት።
ሁለተኛ፦ ሰለፍዮች የሀቅን አንድነት አያፈራርሱም። የሰለፊያ ዳዕዋንም አይበትኑም። ሚያፈራርሱት የቢድዓ አስተምሮን ያነገበ ዳዕዋን ነው። የኢኽዋን፣ የአህባሽ፣ የሀጁሪያ፣ የሙመይዓ ወዘተ ... የቢድዓ ሰዎችን ዳዕዋ ባጢላቸውን በማጋለጥ እና ህዝበ ሙስሊሙን ከነሱ በማስጠንቀቅ ነው ሚያፈራርሱት። ይህ ደግሞ የቁርአን ስራ ነው ለዛ ነው እኮ አል'ፉርቃን ተብሎ የተጠራው። የመልክተኛውም ﷺ ስራ ነው።
قالت الملائكة «من أطاع محمدًا فقد أطاع الله ومن عصى محمدًا فقد عصى الله ومحمدٌ فرق بين الناس» رواه البخاري
ሶስተኛ፦ የሀገራችን የሰለፍያ ዑለሞች ከድሮም «ለአላህ ብሎ በመዋደድ፤ በሱና አሊሞችና በሰለፊዮች መካከል ፍቅርና ትብብርን ማጠናከር፤ ወደ ጥላቻና ጭቅጭቅ ከሚወስዱ ነገሮች መራቅ እንደሚገባ» ብለው ሲያተምሩ ከርመዋል ሰነባብተዋል። መግለጫው ላይ ስታገኘው አዲስ የጀመሩት መስሎህ ከሆነ ይህ የራስህ የአረዳድ ችግር ነው።
አራተኛ፦ «...ወደ ጥላቻና ጭቅጭቅ ከሚወስዱ ነገሮች መራቅ እንደሚገባ» የሚለው ነጥብ በኢኽዋን እና በሙመይዓ አባባል መልኩ እንዳትርደው። ለጥላቻ እና ጭቅጭቅ የማያደርሱ ነገራቶችን በማወቅም ባለማወቅ ወደዛ በማድረስ የሚጣሉ እና የሚጨቃጨቁ አንዳንድ ሰዎችን ለመገሰፅ ነው።
5ኛ, እንዲህም ብሏል «ትላንት ባልተከሰተና ባልነበረ ነገር፣ በጥርጣሬና "እንዲህ አስቦ ነው" በሚል ምናባዊ ምክንያት የሱና ወንድሞችን ሲበድሉና ሲፈርጁ የነበሩት እነዚህ አካላት፤ ዛሬ ልዩነቱ ወደራሳቸው መንደር ሲገባ "ወደ ቁርዓንና ሐዲስ እንመለስ" ማለታቸው የግብዝነት ጥግ ነው። ትላንት ያወለበለቡትን የልዩነት ባንዲራ ዛሬ ለምን ማውረድ ፈለጉ?»
👆 ለዚህ ሸውራራ ሀሳብ የምሰጠው መልስ፦
አንደኛ፦ የሰለፍያ ዑለማኦች ባልተከሰተ ነገር እና በጥርጣሬ ሰለፍዮችን ከሱና አያስወጡም። ከሱና የሚያስወጡበት መንገድ ከበደል እጅግ የራቀና ሸሪዓዊ መርሆዎችን ላለመጣስ በተሟላ ጥንቃቄ የሚደረግ ነው። ሰዎችን እጃቸው በፃፈው፣ ምላሳቸው በተናገረው፣ በአዋዋላቸው፣ በተቋማቸው፣ በአጋሮቻቸው ወዘተ ነው የሚለኩት። ከዚህ የተለየ ነገር አለ የምትል ከሆነ
هاتوا برهانكم إن كنتم صادقين
ሁለተኛ፦ ሰለፍዮች ከፍ አድርገው ያውለበለቡት የሰለፍያ ባንዲራን ዝቅ አያደርጉም። ከነሱ መካከል ይህንን የሚያደርግ አካል ካለ ልክ እንደ ዐ/ከሪም አላህ እሱን አስወግዶ ሌላ ጀግናን ይተካበታል። የሰለፍያ ባንዲራ ግን ከፍ ብላ መውለብለቧ አይቀርም። የቢድዓ ሰዎች መዋረዳቸውም አይቀርም።
6ኛ, እንዲህም ብሏል፦ «...ይህ ነጥብ በጀመዓው ውስጥ ከፍተኛ ስጋትና የቁጥጥር ሽሚያ መኖሩን ያመላክታል። ነገር ግን የመስጊዶችና የመርከዞች ጉዳይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የጋራ ሀብት እንጂ የአንድ ቡድን ግል ንብረት ባለመሆኑ፣ በዚህ መልኩ ግድግዳ አጥሮ "አትስጡ አትቀበሉ" ማለት ዘላቂና ተቋማዊ መፍትሔ ሊሆን አይችልም።»
👆 ለዚህ ቁንስልነት የነገሰበት ሀሳብ የምሰጠው መልስ፦
አንደኛ፦ የቁጥጥር ሽሚያማ ያለው ኢኽዋንና ሙመይዓ ዘንድ ነው። የመጅሊሱን ስልጣን ተገን አድርገው በየአካባቢው ያሉ መስጂዶችን እየተቆራመቱ ለአጨብጫቢዎቻቸው እያስረከቡ ያሉት እነሱ ናቸው። አታይም?! አትሰማም?!
ሁለተኛ፦ ዑለማኦች በመግለጫው ላይ «በመርከዞችና በመስጊዶች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት» የሚለውን ያስቀመጡት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ እንደዚህ አይነት የማይመለከቷቸው ጉዳዮች ላይ ጣልቃ በመግባት በየቦታው ጀመዓን የሚከፋፍሉ አንዳንድ ሰዎችን ለመገሰፅ ነው።
ሶስተኛ፦ "የመስጊዶችና የመርከዞች ጉዳይ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የጋራ ሀብት እንጂ የአንድ ቡድን ግል ንብረት ባለመሆኑ፣..." ብለሀል። ተው እንጂ! የትኛውም ፊርቃ የሰራውን መስጂድ ለሰለፍዮች ክፍት እንደማያደርግ ግልፅ ነው። ታዲያ በየትኛው ሒሳብ ነው የሰለፍዮች መስጂድ ለሁሉም የጋራ የሚሆነው?!
7ኛ እንዲህም ብሏል፦ «"ሳይሆን አይቀርም" በሚል ድንበር አላፊ ስም ማጠልሸትና መፈረጅ አንጻር ይህ ሙሉ በሙሉ አዲስ አካሄድ ነው። ድፍን ህዝብንና ጥንቃቄ የሚያደርጉ ኡለሞችን በቢድዓና በተምዪዕ ሲፈርጁ የትኛውን ታላቅ ዓሊም አማክረው ነበር? ...»
👆 ለዚህ ውሸታም ሀሳብ የምሰጠው መልስ፦
አንደኛ፦ የዑለማኦች መግለጫ "በሱና የሚታወቁ (ወንድምና እህቶችን) ፈጥኖ ከመፈረጅ መጠንቀቅ፤ ይህ ተግባር መከፋፈልንና ፊትናን ስለሚያስከትል፣ ጉዳዩን ወደ ታላላቅ ኡለሞች መመለስ እንደሚገባ፤" የሚል ነው።
ሁለተኛ፦ ይህ ቀድሞም የታወቀ እና የሰለፍዮች የፀና አቋም ነው። ድሮም የሰለፍያ ዑለማኦች የትኛውንም ግለሰብ በችኮላ የፈረጁበት አጋጣሚ የለም። ከመሬት ተነስተህ ባዶ እጅህን የድሮ አቋማቸውን ቀየሩ ትላለህ?! ከመረጃ ጋር አያይዘህ የድሮውን አቋም የምትለውን አጋልጥ። ወይስ በመግለጫ የቀረበ ነገር ሁሉ አዲስ አቋም ይመስልሀል? ይህ ትልቅ የአስተሳሰብ ክፍተት ነው።
ሶስተኛ፦ ሰለፍዮች የትኛውን ድፍን ህዝብ፤ የትኛውን የሱና ዐሊም ነው በቢድዓ እና በተምዪዕ የተቹት?! ግለፃቸውና ይታዩ፤ ይመዘኑ። በትክክል ሙመይዖች ከሆነ ይህ ሰለፍዮችን የሚያስወቅስ አይደለም። አገሌን ተቹ ብለህ ሳትጠቅስ መተቸታቸውን ብቻ መቃወም አይገባህም።
አራተኛ፦ የሀገራችን የሰለፍያ ዑለማኦች ግለሰቦችን እና ሰዎችን ለመተቸት (ጀርህ እና ታዕዲል) በቂ ናቸው። በዚህ ስራ ለመሰማራት የትኛውንም ዐሊም ማማከር አይጠበቅባቸውም። ዑለማኦችን አማክሩ የታባሉት ተራ ሰለፍዮች በራሳቸው እንዳይፈርጁ ነው።
አምስተኛ፦ የሙነወር ልጅ ነው በየሰፈሩ የተብዲዕ ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ሲያነሳሳ የነበረው። ቡታጀራ ላይ እንዲህ ሲል ተናግሯል «አንተም እኔም በሰፈራችን የሆነ ያየነው ሰው ያየነው ችግር ላይ ሙብተዲዕ ነው ልንል እንችላለን!» ተመልከት!
ይቀጥላል....
|| የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/aredualelmumeyia
https://t.me/aredualelmumeyia
ኡኽታ🌸
ሰዎች ቢርቁሽ አትጨነቂ አላህ ካንቺ ጋር
እስካለ ድረስ ብቻሽን አይደለሽም
"የሰዎችን ልብ ለማስደሰት ሳይሆን
የአላህን ውዴታ ለማግኘት ኑሪ"
📚 የዲን እውቀትዎን በቤቶ ይገንቡ!
ከቤታችሁ ሆናችሁ በቀላሉ ዲናዊ እውቀቶችን፣ ትምህርቶችንና ማብራሪያዎችን ማግኘት ከፈለጉ፡
🔹 ትምህርቶችን ለመከታተል
🔹 ጥያቄና መልሶችን ለማግኘት
🔹 ጣፋጭ ሙሀደራዎችን ለማግኘት
👇 ከታች ካሉት ዝርዝሮች/ሊንኮች አንዱን ይጫኑ!
➮ሌላ ምርጫ የኪታብ:-
❶ ቃዕዳቱ ፊ አስ-ሰብር (የኢብኑ ተይሚያህ) [ስለ ሰብር]
❷ መዲከሉ አሽ-ሸይጣን (የሸይኽ ሁሰይን) [ሸይጣን ወደ ሰዎች የሚገባበትን መንገድ የሚገልፅ]
ለ ❶ ቁጥር ;-👍
ለ ❷ ቁጥር:-👌
