NegadRas™ FX Academy
رفتن به کانال در Telegram
نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 646
مشترکین
+624 ساعت
+1367 روز
+29330 روز
در حال بارگیری داده...
کانالهای مشابه
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئن '26
ژوئن '26
+259
در 5 کانالها
مه '26
+224
در 3 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+188
در 0 کانالها
Get PRO
مارس '26
+4 258
در 8 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 19 ژوئن | +14 | |||
| 18 ژوئن | +7 | |||
| 17 ژوئن | +12 | |||
| 16 ژوئن | +11 | |||
| 15 ژوئن | +13 | |||
| 14 ژوئن | +39 | |||
| 13 ژوئن | +46 | |||
| 12 ژوئن | +17 | |||
| 11 ژوئن | +23 | |||
| 10 ژوئن | +16 | |||
| 09 ژوئن | +17 | |||
| 08 ژوئن | +6 | |||
| 07 ژوئن | +13 | |||
| 06 ژوئن | +6 | |||
| 05 ژوئن | +2 | |||
| 04 ژوئن | +5 | |||
| 03 ژوئن | +1 | |||
| 02 ژوئن | +4 | |||
| 01 ژوئن | +7 |
پستهای کانال
ቅዳሜ ጁን 20 2026 ዓም ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቲክቶክ ገፃችን ላይ ያገኙናል።
የዚህ ሳምንት የቅዳማ ምሽት እንግዳችን ወጣቱ እና በዚህ መስክ ጥሩ ስምን ለመገንባት እና በኢትዮጵያ የትሬዲንግ ሴክተር እደገት ላይ አሻራውን ለማሳረፍ እየጣረ ያለውን ታዳጊ ትሬደር @BON_Trades ን ይሆናል።
በእለቱ ያሏችሁን ጥያቄዎች: ሀሳብ አስተያየቶች በሙሉ ማቅረብ የምትችሉበትን አጋጣሚ የምንፈጥርላችሁ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከወዲሁ እንዲቀርቡላችሁ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በቲክቶክ ቪዲዮ በኮሜንት በኩል በማስቀመጥ በመድረኩ የምናካትትላችሁ የሚሆን ይሆናል።
| 2 | የሶስተኛው ሳምንት የትሬዲንግ ጉዞዋችን ውጤቶች በዚህ መልኩ ተጠናቋል።
NegadRas Community's Week 3 Updated Trade Report
በነጋድራስ ኮሚዩኒቲ የምናደርጋቸውን ትሬዶች በቀጥታ በገባናቸው ቁጥር ከዚህ በታች ባለው የጉግል ፎርማችን በኩል ትክክለኛ real time የትሬዲንግ ቪው አናሊስስ እና ቻርቶቻችንን መከታተል የምትችሉ ይሆናል።
https://docs.google.com/spreadsheets/d/1ig_vqvTbEl35D-npoURcUjTDBAU1JzR34X7ueRH_uV0/edit?gid=542769468#gid=542769468
ይህ የግልፅነት ባህል በሁሉም ኢትዮጵያዊ የትሬዲንግ ኮሚዩኒቲዎች ተለምዶ ሁሉም ግልፅነት የተሞላበት ፕሮፌሽናል የትሬዲንግ ባህልን እንፈጥር ዘንድም በያላችሁበት ኮሚዩኒቲ መሰል ክዋኔዎች የሚደረጉበትን መንገድ ጥያቄዎችን ታቀርቡ ዘንድ ለማበረታት እንወዳለን።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 385 |
| 3 | 📑 የትሬዲንግ ጆርናል (Journaling) አያያዝ
በትሬዲንግ ጉዟችን ውስጥ ትርፋማ ከሚያደርጉን ዋና ዋና ምስጢሮች አንዱ የሰራናቸውን ትሬዶች በሙሉ በጥንቃቄ መመዝገብ ወይም Journal ማድረግ ነው። ብዙ ነጋዴዎች ለቴክኒካል ትንተና ትልቅ ትኩረት ቢሰጡም፣ የራሳቸውን ታሪክ መዝግበው ባለመያዛቸው ምክንያት የሰሩትን ስህተት ደጋግመው ሲሰሩ ይታያሉ። በየቀኑ የምናደርጋቸውን ትሬዶች መመዝገብ ራሳችንን እንድንከታተል የሚረዳበትን ቀላል መንገዶች እንይ፦
ከስህተታችን እንድንማር ይረዳናል (Learning from Mistakes)፦ የከረርነውን (Loss) ወይም ያተረፍነውን ትሬድ ስንመዘግብ፣ ትሬዱ ውስጥ የገባንበትን ምክንያት፣ የተሰማንን ስሜት እና የተጠቀምነውን ስትራቴጂ አብረን እናስቀምጣለን። ይህ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ መለስ ብለን ስንገመግመው፣ የትኛው ስትራቴጂ እንደጠቀመን እና የትኛው ስሜታዊ ውሳኔ እንዳከሰረን በግልጽ እንድንለይ ያደርገናል።
የራሳችንን እድገት እንድንከታተል ያግዘናል (Track Your Progress)፦ በትሬዲንግ ውስጥ ስኬት የሚለካው በአንድ ቀን ትርፍ ሳይሆን በረጅም ጊዜ ወጥነት (Consistency) ነው። ጆርናል መያዝ ባለፉት ወራት ምን ያህል እንደተሻሻልን፣ የትሬዲንግ ዊንሬታችን (Win Rate) ስንት እንደሆነ እና በስነ-ልቦና ረገድ ምን ያህል እንደበሰልን የሚያሳይ እውነተኛ መስተዋት ይሆንልናል።
ዲሲፕሊንን ያጠናክራል (Builds Discipline)፦ አንድን ትሬድ ከመውሰዳችን በፊት ያንን ትሬድ በጆርናላችን ላይ ለመመዝገብ ሙሉ መስፈርቱን ማሟላቱን ስናረጋግጥ፣ ዝም ብሎ በዘፈቀደ የመግባት (Gambling) ልምዳችን ይጠፋል። ይህ ደግሞ በራሱ በገበያው ላይ ትልቅ መተማመንን ይፈጥርልናል።
📝 ማጠቃለያ፦ በትሬዲንግ ዓለም ውስጥ ምርጡ አስተማሪ የራስህ ያለፈ ታሪክ ነው። በየቀኑ የምታደርጋቸውን ትሬዶች መመዝገብ መጀመርህ ዛሬ ከምትሰራቸው ስህተቶች እየተማርክ ነገ ወደ ፕሮፌሽናል ትሬደርነት የምታደርገውን ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥነዋል።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 563 |
| 4 | 📑 የትሬዲንግ ጆርናል (Journaling) አያያዝ | 497 |
| 5 | #አጤሬራ_003 ፡ የትሬዲንግ 10ቱ ህግጋት
እነዚህን 10 የትሬዲንግ ህግጋት ለራስህ ታምነህ፤ ፀንተህ፤ ተግሳፅህን ጠብቀህ በተከታታይ እየደጋገምክ ማድረግ ከቻልክ የትሬዲንግ ገነትህን በር ጭላንጭል ታገኘዋለህ።
ህግጋቱን በዚህ ቪዲዮ ተመልከቷቸው። 👉 https://www.tiktok.com/@ice_ethiopia/video/7652796590930857223
በዛውም ቪዲዮው ላይ ያሏችሁን ተጨማሪ ልንተገብራቸው ይገባሉ የምትሏቸውን ያልተገለፁ ወሳኝ ህግጋት በቪዲዮ ኮሜንት በኩል አጋሩን። ከፍተኛ ኦርጋኒክ ቁጥር ያለው ላይክ ያገኘው ዩዘር የ"ነጋድራሱ" ቅፅ 1 መፅሀፍ ተሸላሚ ይሆናል።
Show some love my people.
የሶሻል ሚዲያ ሊንኮቻችንን ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ። | 590 |
| 6 | 🏛 የገበያ ማጥመጃዎች (Traps & Whipsaws)
ዋጋው ቁልፍ ቀጠናን ሰብሮ ሲወጣ፣ ብዙ ነጋዴዎች የመቀረት ፍርሃት (FOMO) ገፏፏቸው ያለ ማረጋገጫ ይገባሉ። ነገር ግን፣ ገበያው የችርቻሮ ነጋዴዎችን ፈሳሽ ገንዘብ (Liquidity) ለመውሰድ የታለመ የሐሰት ስብራት (Fakeout) በማድረግ በፍጥነት ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ይመለሳል።
እነዚህ ማጥመጃዎች በBreakout ነጋዴዎች ላይ የሚሰሩት እንደሚከተለው ነው፦
የፈሳሽ ገንዘብ አደን (Liquidity Hunt)፦ በትልልቅ ተቋማት የሚመራው "Smart Money" የራሱን ትዕዛዝ ለመሙላት ሲል ዋጋው ከቀድሞ ጣሪያ ወይም ወለል ያለፈ በማስመስል የችርቻሮ ነጋዴዎችን Stop Loss ያድናል።
ሻማው ሳይዘጋ መቸኮል (Wick Traps)፦ ዋጋው መስመሩን ሲያልፍ ብቻ በማየት መግባት ለኪሳራ ይዳርጋል። ሻማው ሙሉ በሙሉ በሰውነቱ (Body Close) ከቀጠናው ውጪ ካልዘጋ ድረስ ስብራቱ የሐሰት ወጥመድ (Wick) ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስሜታዊ ውሳኔ (Whipsaws)፦ ገበያው ጥሎኝ ሊሄድ ነው በሚል ስሜት ያለ ማረጋገጫ መጋለብ፣ በትልልቅ ተቋማት በሚዘጋጁ ወጥመዶች ውስጥ በቀላሉ እንድንወድቅ ያደርገናል።
📝 ማጠቃለያ፦ ከእነዚህ ማጥመጃዎች ለመዳን ሁልጊዜ የሻማውን መዘጋት (Body Close) መጠበቅ ወይም ዋጋው ተመልሶ ቀጠናውን ሲፈትሽ (Re-test) ማረጋገጫ አይቶ መግባት ወሳኝ ነው።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 743 |
| 7 | ይሄንን የ100 ሺ ዶላር ፈንድድ አካውንት በሁለት ዶላር ብቻ መግዛት የምትፈልጉ ካላችሁ እድሉን ተጠቀሙበት። Its not for referal or any type of income generation. ለናንተው ታስቦ clean የሆነ ሊንክ ነው የተላከላችሁ። Good Luck.
https://www.goatfundedtrader.com/gft-pay-later | 64 |
| 8 | 📉 የዕለታዊ ትሬድ ብዛትን መገደብ (Overtrading)
በትሬዲንግ ጉዟችን ላይ አካውንታችንን በፍጥነት ከሚያጠፉብን ትልልቅ ጠላቶች አንዱ Overtrading ወይም ያለመጠን ደጋግሞ ትሬድ ማድረግ ነው። ብዙ ትሬድ ማድረግ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ይመስላል፤ ነገር ግን በተግባር ግን ተቃራኒው ነው የሚሆነው። በቀን ውስጥ የምናደርገውን የትሬድ ብዛት (ለምሳሌ በቀን ከ 2 ወይም 3 ትሬድ በላይ አለማድረግ) መገደብ አካውንታችንን ከማክሰር እንዴት እንደሚጠብቀን እንይ፦
የስሜት መጋለብን ይቀንሳል (Emotional Control)፦ መጀመሪያ ላይ ኪሳራ ካጋጠመን፣ ያንን በፍጥነት ለመመለስ ስሜታዊ ሆነን ገበያውን ለመበቀል ከመጋፋት (Revenge Trading) ይታደገናል፤ እንድንረጋጋም ያደርገናል።
የጥራት ላይ ትኩረትን ይጨምራል (Quality over Quantity)፦ በቀን 3 ዕድል ብቻ እንዳለን ስናውቅ፣ ዝም ብሎ የታየንን ሳይሆን መስፈርታችንን ሙሉ በሙሉ ያሟላውን ምርጥ Setup ብቻ መርጠን እንድንገባ ያስገድደናል።
የካፒታል አያያዝን ያጠናክራል (Risk Management)፦ በቀን የምናደርገውን የትሬድ ብዛት መገደብ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከልክ በላይ በመጫን አካውንታችንን ሙሉ በሙሉ አጥፍተን ከገበያ ውጭ እንድንሆን አይፈቅድም።
📝 ማጠቃለያ፦ ስኬት ያለው ብዙ መጫን ላይ ሳይሆን ራስን መቆጣጠር ላይ ነው። የትሬድ ብዛትን መገደብ የአካውንታችንን ዕድሜ ከማራዘሙም በላይ ፕሮፌሽናል ትሬደር ያደርገናል።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 844 |
| 9 | የስኬታማ ትሬዲንግ ሚስጥር Multi-Timeframe Analysis
ብዙ አዲስ ትሬደሮች የሚቸገሩት ትሬድ በሚገቡበት ሰዓት ገበያው በድንገት ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመሄድ ኪሳራ ሲያጋጥማቸው ነው። ይህ የሚሆነው ትኩረታችንን በጣም ትንሽ Timeframe ላይ ብቻ በማድረጋችን ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ግን ትልቅ እና ትንሽ Timeframeዎችን አጣምሮ መመልከት ያስፈልጋል።
የዚህ ዘዴ ዋና ጥቅሙ የገበያውን አጠቃላይ ጉዞ መለየት ነው። በቅድሚያ በትልቁ Timeframe ለምሳሌ H4 ላይ የገበያውን ዋና አቅጣጫ መመልከት አለብህ። ገበያው ወደ ላይ ነው ወይስ ወደ ታች? ይህ ትልቅ እይታ የትኛው አቅጣጫ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለብህ ይነግርሃል።
የገበያውን አቅጣጫ በትልቁ Timeframe ካወቅህ በኋላ ወደ ትንሹ Timeframe ለምሳሌ 15M ትሄዳለህ። ትንሹ Timeframe የምትገባበትን ትክክለኛ ሰዓት እና ቦታ ለመለየት ይጠቅማል። በሌላ አነጋገር H4 ላይ አቅጣጫውን ታያለህ፣ 15M ላይ ደግሞ መግቢያህን ታስተካክላለህ።
ለምሳሌ H4 ላይ ገበያው ወደ ላይ እየሄደ መሆኑን ካየህ፣ 15M ላይ ዋጋው ትንሽ እስኪስተካከል ወይም ወደ ታች እስኪል ትጠብቃለህ። ዋጋው ሲያርፍ እና ጥሩ መግቢያ ስታገኝ ወደ ትሬድ ትገባለህ። ይህ ማለት ትልቁን ገበያ የሚሄድበትን መንገድ በመከተል አደጋህን በመቀነስ ትርፍህን ከፍ ማድረግ ትችላለህ ማለት ነው።
ይህን ዘዴ በመለማመድ አላስፈላጊ ትሬዶችን በማስቀረት በገበያው ውስጥ ያለህን እድል ከፍ ማድረግ ትችላለህ። ሁልጊዜም ትልቁን ምስል ማየት ለትንሹ ውሳኔህ መነሻ መሆኑን አትዘንጋ።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 913 |
| 10 | እንዴት አመሻችሁ ጋይስ ፡
በዛሬው የላይቭ ፕሮግራማችን በትሬዲንግ እና በሚኖሩብን ፍርሀት እንዲሁም ይህንኑ ፍርሀት ከሚፈጥረው ኮርቲሶል የተሰኘ ሆርሞን ዙሪያ እንወያያለን። መድረኩን መቀላቀል የምትፈልጉ ልጆች ተቀላቀሉን።
https://vt.tiktok.com/ZS9j5v2HqLxwh-Lo32X/ | 1 012 |
| 11 | SEASON 3 IS HERE. 🔥🔥🔥
የአድዋ ጦርነትን እና ትሬዲንግን ምን አገናኛቸው???
በዚህ ቪዲዮ ስለሊውኪዲቲ ስዊፕ ፅንሰ ሀሳብ እና ሳይኮሎጂ የአድዋ ጦርነትን አናሎጂን በመጠቀም ለማስረዳት ተሞክሯል። በእርግጥኝነት ሀሳቡን ከልቡ ያዳመጠው እጅጉን እንደሚማርበት እናምናለን።
ይህ መሰል ቪዲዮዎች ይበልጥ እየተሰሩ ይለቀቁላችሁ ዘንድ መውደዳችሁን በላይኮቻችሁ እና በኮሜንቶቻችሁ አሳዩን። Lets go my people. 🔥🔥🔥
የፖስት ሊንክ፡
https://www.tiktok.com/@ice_ethiopia/video/7651669727818960144 | 1 002 |
| 12 | ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ ፡
ትላንት ለማስታወቅ እንደሞከርነው አሁን ያላችሁበት ስቴጅ በማለፍ ወደሌቭል 3 በማለፍ ሌሎቹ ተማሪዎች የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ እና አብረን ጉዟችንን ለመቀጠል እንዲሁም ቪዲዮ ከዚህ ላይ ተነስቶባችሁ ግን ያልጨረሳችሁ ልጆችም እንድትጨርሱ ወደዲስኮርድ አፕሊኬሽን እና መማሪያ ቻናላችን ከዚህ በታች ባለው መቀላቀል ትችላላችሁ። በመቀላቀሉ ሂደት የምትጠየቁት አራት ጥያቄዎች ያሉ ሲሆን ከነሱ መሀል በእኛ IB የHFM አካውንት መክፈታችሁን የሚጠይቅና የዋሌት አይዲ ስለሚጠይቃችሁ በቅድሚያ በኛ ሊንክ ተመዝግባችሁ መጨረሳችሁን ማረጋገጥ መቻል ይኖርባቹሀል።
https://discord.gg/ENubP6J5 | 1 052 |
| 13 | 🏛 የማዕከላዊ ባንኮች ንግግሮች (Hawkish vs Dovish)
በፎሬክስ ገበያ ውስጥ የማዕከላዊ ባንክ መሪዎች መግለጫዎች የዋጋ እንቅስቃሴን በመወሰን ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህን የፖሊሲ ፍንጮች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንከፍላቸዋለን፦
🦅 1. Hawkish (ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ)
የመጀመሪያው Hawkish የሚባለው ሲሆን፣ ዋና ትኩረቱ የዋጋ ንረትን (Inflation) መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ነው። በዚህም ባንኮች የወለድ መጠንን ለመጨመር ወይም ካለበት ከፍ አድርገው ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው የሚጠቁሙ ሲሆን፣ ይህም ብዙውን ጊዜ የዚያ አገር ገንዘብ ዋጋ በገበያው ላይ እንዲጠናከር ያደርጋል።
🕊 2. Dovish (ላላ ያለ/የሚያነቃቃ የገንዘብ ፖሊሲ)
ትኩረቱን በኢኮኖሚ ዕድገትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚያደርግ ላላ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ ነው። በዚህ ወቅት ባንኮች ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ሲሉ የወለድ መጠንን ለመቀነስ (Interest Rate Cut) ወይም ሳይጨምሩ ለማቆየት ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳዩ ሲሆን፣ ይህም በአብዛኛው የአገሪቱን ገንዘብ ዋጋ እንዲዳከም ያደርጋል።
💡 ማጠቃለያ፦ እንደ ባለሀብት የማዕከላዊ ባንኮችን ቃና መከታተል የገበያውን የረጅም ጊዜ አቅጣጫ ለመተንበይ ቁልፍ መሣሪያ ነው። የንግግራቸው ቃና ወደ Hawkish ሲያዘነብል የገንዘብ ጥብቅነትን፣ ወደ Dovish ሲያዘነብል ደግሞ ማነቃቂያን በመገመት የቴክኒካል ትንተናችንን ማገዝ እንችላለን።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 106 |
| 14 | ሰላም ጋይስ፡
እንደምታውቁት ላለፉት አምስት ወራት የመጀመሪያውን የነጋድራስ ባች ተማሪዎች ስናሰለጥን የቆየን እና በዚህም ከተመዘገቡ 4000 ሺ ተማሪዎች ውስጥ ከ800 የማያንሱት የመጀመሪያ አካውንታቸውን በመክፈት ትሬዲንግ ሀ ብለው የጀመሩበት ከነሱ ውስጥ ደግሞ በጊዜ እና የተለያዩ ትምህርታዊ ፈተናዎች ያለፉ የተጣሩ 60 ተማሪዎችን በመያዝ አሁን ላይ ወደቀጥታ የትሬደርነት ጅማሬያቸው የደረሱ ልጆች በመያዝ በዚህ ባች የሰጠነውን አገልግሎት ከጫፍ ማድረስ ችለናል። በዚህም እስካሁን ትምህርቱን እየወሰዳችሁ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አሁንም ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ያልቻላችሁ ልጆች ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚጠበቁባችሁን ትምርህታዊ ሁነቶች አጠናቃችሁ ወደዲስኮርድ የሚወስዳችሁን ምዝገባ ከነገ ጀምሮ በአድሚኖቻችን በኩል እንድታደርጉ እና ይህ ሳምንት የመጨረሻ የአንደኛው ባች ምዝገባ ሳምንት እንደሚሆንና ከአሁን በኋላ በሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በኩል ካልሆነ ምንም አይነት ምዝገባ እንደማናደርግ ለማስታወስ ወደድን።
እሳክሁን በመጣንበት አካሄድ የተሰጧችሁ የጀማሪ ትምህርቶች ጥሩ እንደነበሩ እና በአገልግሎታችንም እንደተደሰታችሁ እምነታችን ነው። አሁንም በነጋድራስ የመጀመሪያ ባች ውስጥ መታቀፍና የትሬዲንግ ህይወታችሁን ከኛ ጋር ለመቀጠል የምትፈልጉ ልጆች ከላይ እንደተገለፀ ይህንኑ ስራ በሚያሳልጡ የአድሚን አባላት በኩል ከነገ ጀምሮ መቀላቀላችሁ እንዳትረሱ ለማለት ወደድን። ያሏችሁን ጥያቄዎች በኮሜንት ሳጥን በኩል እንድታሳውቁን ስንልም ለማስታወስ ወደድን።
በያላችሁበት ሰላም። | 1 246 |
| 15 | የቅዳሜ ምሽት THE INTERVIEW የተሰኘ ፕሮግራማችን ትሬደር ሶፎኒያስን ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ ይዘንላችሁ እንቀርባለን። በቲክቶክ ላይቭ የቀጥታ መድረክ ላይ ተቀላቀሉን።
https://vt.tiktok.com/ZS9jkEvDCv6wD-2NK8m/
https://www.linktr.ee/negadrasfx | 1 257 |
| 16 | የነጋድራስ የመጀመሪያ ተማራቂ ተማሪዎች የሁለት ሳምንት የትሬደርነት ጉዞ በዚህ መልኩ ተጀምሯል። እንደኮሚዩኒቲ የሚደረጉ የማርኬት አናሊስስ እና ጥሪዎችን ከነውጤቶቻችው ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ።
https://docs.google.com/spreadsheets/d/1ig_vqvTbEl35D-npoURcUjTDBAU1JzR34X7ueRH_uV0/edit?gid=542769468#gid=542769468 | 4 547 |
| 17 | #THE_INTERVIEW
#TRADER_SOFONIAS
#JUNE_13
https://www.linktr.ee/negadrasfx | 897 |
| 18 | የ Moving Average (MA) መሰረታዊ አጠቃቀም
-Moving Average (MA) የዋጋ መረጃን በተወሰነ ጊዜ ውስጥ በማማከር የሚያሳይ ቴክኒካል ኢንዲኬተር ነው። ዋና አላማው የአጭር ጊዜ የዋጋ መዋዠቅን (market noise) በመቀነስ የገበያውን አጠቃላይ አቅጣጫ ግልጽ እንዲሆን ማድረግ ነው።
ለምሳሌ፣ 50-period MA የመጨረሻ 50 ሻማዎች (candles) አማካይ ዋጋን ያሳያል። ዋጋው በተከታታይ ከ MA በላይ ከተገኘ፣ ገበያው ወደ ላይ (uptrend) እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሊያመለክት ይችላል። በተቃራኒው ዋጋው ከ MA በታች ከሆነ፣ የወደ ታች (downtrend) አቅጣጫ ሊያሳይ ይችላል።
-MA እንደ ተለዋዋጭ የድጋፍ (support) ወይም የመቋቋሚያ (resistance) መስመር ሊያገለግልም ይችላል። በጠንካራ አፕትሬንድ ውስጥ ዋጋው ወደ MA ተመልሶ ድጋፍ አግኝቶ እንደገና ወደ ላይ ሲቀጥል ብዙ ጊዜ ይታያል።
-እንዲሁም ሁለት MA በአንድ ጊዜ መጠቀም የተለመደ ነው። ለምሳሌ 50 MA እና 200 MA ሲጠቀሙ፣ 50 MA ከ 200 MA በላይ ሲቆራረጥ (Golden Cross) የገበያ ጥንካሬን ሊያመለክት ይችላል፤ 50 MA ከ 200 MA በታች ሲወርድ (Death Cross) ደግሞ የድክመት ምልክት ሊሆን ይችላል።
ጠቃሚ ምክር:-- Moving Average የዘገየ (lagging) ኢንዲኬተር ስለሆነ የወደፊት እንቅስቃሴን አይተነብይም፤ ስለዚህ ከ Price Action፣ Support & Resistance እና ከሌሎች ማረጋገጫዎች ጋር በማጣመር መጠቀም የተሻለ ውጤት ይሰጣል።
✍️ Education Department
📣Powered By : ETN Ecosystem™
🤝Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 483 |
| 19 | بدون متن... | 1 196 |
| 20 | Retail Sentiment ምንድን ነው?
የችርቻሮ ነጋዴዎች (Retail Traders) ማለት እንደ እኔ እና እንደናንተ ያሉ በየቤታቸው ሆነው አነስተኛ ካፒታል ይዘው የሚነግዱ ግለሰቦች ናቸው። Retail Sentiment ማለት ደግሞ የእነዚህ አጠቃላይ ነጋዴዎች የጋራ ስሜት ወይም አዝማሚያ (አብዛኛው ሰው እየገዛ ነው ወይስ እየሸጠ?) የሚለው ስሌት ነው።
ሁሉም ሰው ወደ አንድ አቅጣጫ ሲያይ ገበያው ለምን ይገለበጣል?
ገበያውን የሚያንቀሳቅሱት ትልልቅ ባንኮች እና ተቋማት (Smart Money/Institutions) ናቸው። እነሱ ትልቅ ትርፍ ለማግኘት የችርቻሮ ነጋዴዎችን ስህተት እና ስሜት ይጠቀማሉ። ይህ ለምን ይሆናል?
የፈሳሽነት ፍላጎት (Liquidity): ትልልቅ ባንኮች በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለመግዛት (Buy)፣ ያንን የሚያክሉ ሻጮች (Sellers) ይፈልጋሉ። አብዛኛው የችርቻሮ ነጋዴ ገበያው ሊወርድ ነው ብሎ "Sell" ሲያደርግና Stop Loss ሲያስቀምጥ፣ ባንኮቹ ያንን አጋጣሚ ተጠቅመው ገበያውን ወደ ላይ (Buy) በመውሰድ የሁሉንም Stop Loss ይበላሉ።
የመናጋት ስሜት (FOMO & Panic): አብዛኛው ሰው በስሜት ተገፋፍቶ "አሁንማ ማምለጥ የለብኝም" ብሎ በአንድ ላይ መግዛት (Buy) ሲጀምር፣ ገበያው የመጨረሻው ጫፍ ላይ ደርሷል ማለት ነው። በዚህ ሰዓት ትልልቆቹ ተጫዋቾች መሸጥ ይጀምራሉ።
ዋናው ቁምነገር (The Takeaway)
ፕሮፌሽናል ነጋዴ ለመሆን ከፈለክ እንደ "Retailer" ማሰብ ማቆም አለብህ ። ገበያው የትኛው አቅጣጫ እንደሆነ ለማወቅ Sentiment Indicators (እንደ SSI ያሉ) በመጠቀም አብዛኛው ሰው ምን እያደረገ እንደሆነ ተመልከት ::
ህጉ ቀላል ነው: አብዛኛው የችርቻሮ ነጋዴ (ለምሳሌ 80%) "Buy" እያደረገ ከሆነ፣ እርስዎ "Sell" ለማድረግ እድሎችን መፈለግ ይጀምሩ። ከተረታው ስብስብ (90% ተሸናፊዎች) ወጥተው ከባንኮቹ ጋር ይጓዙ!
✍️ Education Department
📣Powered By : ETN Ecosystem™
🤝Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 590 |
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
