NegadRas™ FX Academy
前往频道在 Telegram
显示更多
未指定国家未指定类别
4 670
订阅者
+1524 小时
+667 天
+31930 天
吸引订阅者
六月 '26
六月 '26
+286
在5个频道中
五月 '26
+224
在3个频道中
Get PRO
四月 '26
+188
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+4 258
在8个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 22 六月 | +3 | |||
| 21 六月 | +15 | |||
| 20 六月 | +9 | |||
| 19 六月 | +14 | |||
| 18 六月 | +7 | |||
| 17 六月 | +12 | |||
| 16 六月 | +11 | |||
| 15 六月 | +13 | |||
| 14 六月 | +39 | |||
| 13 六月 | +46 | |||
| 12 六月 | +17 | |||
| 11 六月 | +23 | |||
| 10 六月 | +16 | |||
| 09 六月 | +17 | |||
| 08 六月 | +6 | |||
| 07 六月 | +13 | |||
| 06 六月 | +6 | |||
| 05 六月 | +2 | |||
| 04 六月 | +5 | |||
| 03 六月 | +1 | |||
| 02 六月 | +4 | |||
| 01 六月 | +7 |
频道帖子
⏰ Kill Zones (የአደን ሰዓታት)
በፎሬክስ ገበያ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን "ምን መቼ እንደሚገበያይ" ማወቅ ወሳኝ ነው። ባንኮች እና ትልልቅ ተቋማት አልጎሪዝማቸውን የሚያንቀሳቅሱባቸው፣ ከፍተኛ Liquidity እና ፈጣን የዋጋ እንቅስቃሴ (Volatility) የሚታይባቸው ልዩ የሰዓት መስኮቶች አሉ። እነዚህ ሰዓታት Kill Zones በመባል ይታወቃሉ።
በቀን ውስጥ ትኩረት ልናደርግባቸው የሚገቡ ሁለት ዋና ዋና የ Kill Zone ሰዓታት (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)፦
የለንደን ኪል ዞን (London Kill Zone) — ከጠዋቱ 3:00 እስከ 5:00 ሰዓት፦ ይህ ሰዓት የለንደን ገበያ የሚከፈትበት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ የቀኑን ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ዋጋ (High or Low of the Day) ለመስራት የሐሰት እንቅስቃሴ (Judas Swing) የሚፈጠርበት ስውር የሰዓት መስኮት ነው።
የኒውዮርክ ኪል ዞን (New York Kill Zone) — ከሰዓት በኋላ ከ7:00 እስከ 9:00 ሰዓት፦ የኒውዮርክ ገበያ ከለንደን ገበያ ጋር የሚደራረብበት በመሆኑ፣ በከፍተኛ የገበያ መጠን የታገዙ እውነተኛ የትሬንድ ቀጣይነት ወይም መመለስ እንቅስቃሴዎች የሚፈጠሩበት ወሳኝ ሰዓት ነው።
📝 ማጠቃለያ፦ በየቀኑ 24 ሰዓት ሙሉ ስክሪን ላይ በመቀመጥ ከመልፋት ይልቅ፣ ባንኮች በሚንቀሳቀሱባቸው በእነዚህ የ Kill Zone ሰዓታት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ መገበያየት ከከንቱ ኪሳራ ይጠብቃል፤ የትሬዲንግ ጥራታችንንም በከፍተኛ ደረጃ ያሳድገዋል።✍️ Education Department 📣 Powered By : ETN Ecosystem™ 🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy ▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy
| 2 | የስድስተኛው ዙር የICE ትሬዲንግ ሳይኮሎጂ የአንድ ወር ኮርስ ተሳታፊዎች እያደረጉ የሚገኙትን የሪሰርች ፕረዘንቴሽን ትቀላቀሉ ዘንድ ተጋብዛቹሀል።
https://vt.tiktok.com/ZS9jKfVg2d2sg-lsZVt/ | 247 |
| 3 | የመጀመሪያው የነጋድራስ ባች ተመራቂ ተማሪዎች በትሬዲንግ ሳይኮሎጂ የወሰዱትን ስልጠና በመጨረስ ዛሬ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ በቲክቶክ መድረካችን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያየው በሚችል መልኩ የጥናት Thesisሳቸውን የሚያቀርቡልን ይሆናል። ተማሪዎቻችን ምን ያህል ተምረዋል የሚለውን እንዲሁም እናንተም ላታውቁዋቸው የምትችሏቸውን ሀሳቦች እየተማማርን እናሳልፍ ዘንድ በዚህ ፕረዘንቴሽን ላይ ትገኙ ዘንድ ተጋብዛቹሀል።
ጁን 21 ከምሽቱ 2፡30 ጀምሮ | 798 |
| 4 | THE INTERVIEW የተሰኘው ሰርክ ቅዳሜ የምናዘጋጀው ፕሮግራማችን ዛሬ ደግሞ @bon_trades ይዞላችሁ መቷል። ያሳለፋቸውን ውጣ ውረዶች፤ ያገኛቸውን እውቀቶች እና ስለትሬዲንግ ጠልቀን የምናወጋበት ይሆናል።
ሁላችሁም በቀጥታ መድረኩ ላይ ተገኝታችሁ ያሏችሁን ጥያቄዎች፤ አድናቆቶች፤ ሙግቶችም ሆኑ ማንኛውም ተያያዥ ሀሳቦች ማቅረብ የምትችሉ ይሆናል። Let's Go Guys.
https://vt.tiktok.com/ZS9jce11cTUVu-5cJPl/ | 865 |
| 5 | ቅዳሜ ጁን 20 2026 ዓም ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በቲክቶክ ገፃችን ላይ ያገኙናል።
የዚህ ሳምንት የቅዳማ ምሽት እንግዳችን ወጣቱ እና በዚህ መስክ ጥሩ ስምን ለመገንባት እና በኢትዮጵያ የትሬዲንግ ሴክተር እደገት ላይ አሻራውን ለማሳረፍ እየጣረ ያለውን ታዳጊ ትሬደር @BON_Trades ን ይሆናል።
በእለቱ ያሏችሁን ጥያቄዎች: ሀሳብ አስተያየቶች በሙሉ ማቅረብ የምትችሉበትን አጋጣሚ የምንፈጥርላችሁ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከወዲሁ እንዲቀርቡላችሁ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በቲክቶክ ቪዲዮ በኮሜንት በኩል በማስቀመጥ በመድረኩ የምናካትትላችሁ የሚሆን ይሆናል። | 902 |
| 6 | የሶስተኛው ሳምንት የትሬዲንግ ጉዞዋችን ውጤቶች በዚህ መልኩ ተጠናቋል።
NegadRas Community's Week 3 Updated Trade Report
በነጋድራስ ኮሚዩኒቲ የምናደርጋቸውን ትሬዶች በቀጥታ በገባናቸው ቁጥር ከዚህ በታች ባለው የጉግል ፎርማችን በኩል ትክክለኛ real time የትሬዲንግ ቪው አናሊስስ እና ቻርቶቻችንን መከታተል የምትችሉ ይሆናል።
https://docs.google.com/spreadsheets/d/1ig_vqvTbEl35D-npoURcUjTDBAU1JzR34X7ueRH_uV0/edit?gid=542769468#gid=542769468
ይህ የግልፅነት ባህል በሁሉም ኢትዮጵያዊ የትሬዲንግ ኮሚዩኒቲዎች ተለምዶ ሁሉም ግልፅነት የተሞላበት ፕሮፌሽናል የትሬዲንግ ባህልን እንፈጥር ዘንድም በያላችሁበት ኮሚዩኒቲ መሰል ክዋኔዎች የሚደረጉበትን መንገድ ጥያቄዎችን ታቀርቡ ዘንድ ለማበረታት እንወዳለን።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 2 887 |
| 7 | 📑 የትሬዲንግ ጆርናል (Journaling) አያያዝ
በትሬዲንግ ጉዟችን ውስጥ ትርፋማ ከሚያደርጉን ዋና ዋና ምስጢሮች አንዱ የሰራናቸውን ትሬዶች በሙሉ በጥንቃቄ መመዝገብ ወይም Journal ማድረግ ነው። ብዙ ነጋዴዎች ለቴክኒካል ትንተና ትልቅ ትኩረት ቢሰጡም፣ የራሳቸውን ታሪክ መዝግበው ባለመያዛቸው ምክንያት የሰሩትን ስህተት ደጋግመው ሲሰሩ ይታያሉ። በየቀኑ የምናደርጋቸውን ትሬዶች መመዝገብ ራሳችንን እንድንከታተል የሚረዳበትን ቀላል መንገዶች እንይ፦
ከስህተታችን እንድንማር ይረዳናል (Learning from Mistakes)፦ የከረርነውን (Loss) ወይም ያተረፍነውን ትሬድ ስንመዘግብ፣ ትሬዱ ውስጥ የገባንበትን ምክንያት፣ የተሰማንን ስሜት እና የተጠቀምነውን ስትራቴጂ አብረን እናስቀምጣለን። ይህ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ መለስ ብለን ስንገመግመው፣ የትኛው ስትራቴጂ እንደጠቀመን እና የትኛው ስሜታዊ ውሳኔ እንዳከሰረን በግልጽ እንድንለይ ያደርገናል።
የራሳችንን እድገት እንድንከታተል ያግዘናል (Track Your Progress)፦ በትሬዲንግ ውስጥ ስኬት የሚለካው በአንድ ቀን ትርፍ ሳይሆን በረጅም ጊዜ ወጥነት (Consistency) ነው። ጆርናል መያዝ ባለፉት ወራት ምን ያህል እንደተሻሻልን፣ የትሬዲንግ ዊንሬታችን (Win Rate) ስንት እንደሆነ እና በስነ-ልቦና ረገድ ምን ያህል እንደበሰልን የሚያሳይ እውነተኛ መስተዋት ይሆንልናል።
ዲሲፕሊንን ያጠናክራል (Builds Discipline)፦ አንድን ትሬድ ከመውሰዳችን በፊት ያንን ትሬድ በጆርናላችን ላይ ለመመዝገብ ሙሉ መስፈርቱን ማሟላቱን ስናረጋግጥ፣ ዝም ብሎ በዘፈቀደ የመግባት (Gambling) ልምዳችን ይጠፋል። ይህ ደግሞ በራሱ በገበያው ላይ ትልቅ መተማመንን ይፈጥርልናል።
📝 ማጠቃለያ፦ በትሬዲንግ ዓለም ውስጥ ምርጡ አስተማሪ የራስህ ያለፈ ታሪክ ነው። በየቀኑ የምታደርጋቸውን ትሬዶች መመዝገብ መጀመርህ ዛሬ ከምትሰራቸው ስህተቶች እየተማርክ ነገ ወደ ፕሮፌሽናል ትሬደርነት የምታደርገውን ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥነዋል።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 836 |
| 8 | 📑 የትሬዲንግ ጆርናል (Journaling) አያያዝ | 731 |
| 9 | #አጤሬራ_003 ፡ የትሬዲንግ 10ቱ ህግጋት
እነዚህን 10 የትሬዲንግ ህግጋት ለራስህ ታምነህ፤ ፀንተህ፤ ተግሳፅህን ጠብቀህ በተከታታይ እየደጋገምክ ማድረግ ከቻልክ የትሬዲንግ ገነትህን በር ጭላንጭል ታገኘዋለህ።
ህግጋቱን በዚህ ቪዲዮ ተመልከቷቸው። 👉 https://www.tiktok.com/@ice_ethiopia/video/7652796590930857223
በዛውም ቪዲዮው ላይ ያሏችሁን ተጨማሪ ልንተገብራቸው ይገባሉ የምትሏቸውን ያልተገለፁ ወሳኝ ህግጋት በቪዲዮ ኮሜንት በኩል አጋሩን። ከፍተኛ ኦርጋኒክ ቁጥር ያለው ላይክ ያገኘው ዩዘር የ"ነጋድራሱ" ቅፅ 1 መፅሀፍ ተሸላሚ ይሆናል።
Show some love my people.
የሶሻል ሚዲያ ሊንኮቻችንን ለማግኘት እዚህ ጋር ይጫኑ። | 910 |
| 10 | 🏛 የገበያ ማጥመጃዎች (Traps & Whipsaws)
ዋጋው ቁልፍ ቀጠናን ሰብሮ ሲወጣ፣ ብዙ ነጋዴዎች የመቀረት ፍርሃት (FOMO) ገፏፏቸው ያለ ማረጋገጫ ይገባሉ። ነገር ግን፣ ገበያው የችርቻሮ ነጋዴዎችን ፈሳሽ ገንዘብ (Liquidity) ለመውሰድ የታለመ የሐሰት ስብራት (Fakeout) በማድረግ በፍጥነት ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ይመለሳል።
እነዚህ ማጥመጃዎች በBreakout ነጋዴዎች ላይ የሚሰሩት እንደሚከተለው ነው፦
የፈሳሽ ገንዘብ አደን (Liquidity Hunt)፦ በትልልቅ ተቋማት የሚመራው "Smart Money" የራሱን ትዕዛዝ ለመሙላት ሲል ዋጋው ከቀድሞ ጣሪያ ወይም ወለል ያለፈ በማስመስል የችርቻሮ ነጋዴዎችን Stop Loss ያድናል።
ሻማው ሳይዘጋ መቸኮል (Wick Traps)፦ ዋጋው መስመሩን ሲያልፍ ብቻ በማየት መግባት ለኪሳራ ይዳርጋል። ሻማው ሙሉ በሙሉ በሰውነቱ (Body Close) ከቀጠናው ውጪ ካልዘጋ ድረስ ስብራቱ የሐሰት ወጥመድ (Wick) ብቻ ሊሆን ይችላል።
ስሜታዊ ውሳኔ (Whipsaws)፦ ገበያው ጥሎኝ ሊሄድ ነው በሚል ስሜት ያለ ማረጋገጫ መጋለብ፣ በትልልቅ ተቋማት በሚዘጋጁ ወጥመዶች ውስጥ በቀላሉ እንድንወድቅ ያደርገናል።
📝 ማጠቃለያ፦ ከእነዚህ ማጥመጃዎች ለመዳን ሁልጊዜ የሻማውን መዘጋት (Body Close) መጠበቅ ወይም ዋጋው ተመልሶ ቀጠናውን ሲፈትሽ (Re-test) ማረጋገጫ አይቶ መግባት ወሳኝ ነው።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 081 |
| 11 | ይሄንን የ100 ሺ ዶላር ፈንድድ አካውንት በሁለት ዶላር ብቻ መግዛት የምትፈልጉ ካላችሁ እድሉን ተጠቀሙበት። Its not for referal or any type of income generation. ለናንተው ታስቦ clean የሆነ ሊንክ ነው የተላከላችሁ። Good Luck.
https://www.goatfundedtrader.com/gft-pay-later | 64 |
| 12 | 📉 የዕለታዊ ትሬድ ብዛትን መገደብ (Overtrading)
በትሬዲንግ ጉዟችን ላይ አካውንታችንን በፍጥነት ከሚያጠፉብን ትልልቅ ጠላቶች አንዱ Overtrading ወይም ያለመጠን ደጋግሞ ትሬድ ማድረግ ነው። ብዙ ትሬድ ማድረግ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ይመስላል፤ ነገር ግን በተግባር ግን ተቃራኒው ነው የሚሆነው። በቀን ውስጥ የምናደርገውን የትሬድ ብዛት (ለምሳሌ በቀን ከ 2 ወይም 3 ትሬድ በላይ አለማድረግ) መገደብ አካውንታችንን ከማክሰር እንዴት እንደሚጠብቀን እንይ፦
የስሜት መጋለብን ይቀንሳል (Emotional Control)፦ መጀመሪያ ላይ ኪሳራ ካጋጠመን፣ ያንን በፍጥነት ለመመለስ ስሜታዊ ሆነን ገበያውን ለመበቀል ከመጋፋት (Revenge Trading) ይታደገናል፤ እንድንረጋጋም ያደርገናል።
የጥራት ላይ ትኩረትን ይጨምራል (Quality over Quantity)፦ በቀን 3 ዕድል ብቻ እንዳለን ስናውቅ፣ ዝም ብሎ የታየንን ሳይሆን መስፈርታችንን ሙሉ በሙሉ ያሟላውን ምርጥ Setup ብቻ መርጠን እንድንገባ ያስገድደናል።
የካፒታል አያያዝን ያጠናክራል (Risk Management)፦ በቀን የምናደርገውን የትሬድ ብዛት መገደብ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከልክ በላይ በመጫን አካውንታችንን ሙሉ በሙሉ አጥፍተን ከገበያ ውጭ እንድንሆን አይፈቅድም።
📝 ማጠቃለያ፦ ስኬት ያለው ብዙ መጫን ላይ ሳይሆን ራስን መቆጣጠር ላይ ነው። የትሬድ ብዛትን መገደብ የአካውንታችንን ዕድሜ ከማራዘሙም በላይ ፕሮፌሽናል ትሬደር ያደርገናል።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 200 |
| 13 | የስኬታማ ትሬዲንግ ሚስጥር Multi-Timeframe Analysis
ብዙ አዲስ ትሬደሮች የሚቸገሩት ትሬድ በሚገቡበት ሰዓት ገበያው በድንገት ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመሄድ ኪሳራ ሲያጋጥማቸው ነው። ይህ የሚሆነው ትኩረታችንን በጣም ትንሽ Timeframe ላይ ብቻ በማድረጋችን ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ግን ትልቅ እና ትንሽ Timeframeዎችን አጣምሮ መመልከት ያስፈልጋል።
የዚህ ዘዴ ዋና ጥቅሙ የገበያውን አጠቃላይ ጉዞ መለየት ነው። በቅድሚያ በትልቁ Timeframe ለምሳሌ H4 ላይ የገበያውን ዋና አቅጣጫ መመልከት አለብህ። ገበያው ወደ ላይ ነው ወይስ ወደ ታች? ይህ ትልቅ እይታ የትኛው አቅጣጫ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለብህ ይነግርሃል።
የገበያውን አቅጣጫ በትልቁ Timeframe ካወቅህ በኋላ ወደ ትንሹ Timeframe ለምሳሌ 15M ትሄዳለህ። ትንሹ Timeframe የምትገባበትን ትክክለኛ ሰዓት እና ቦታ ለመለየት ይጠቅማል። በሌላ አነጋገር H4 ላይ አቅጣጫውን ታያለህ፣ 15M ላይ ደግሞ መግቢያህን ታስተካክላለህ።
ለምሳሌ H4 ላይ ገበያው ወደ ላይ እየሄደ መሆኑን ካየህ፣ 15M ላይ ዋጋው ትንሽ እስኪስተካከል ወይም ወደ ታች እስኪል ትጠብቃለህ። ዋጋው ሲያርፍ እና ጥሩ መግቢያ ስታገኝ ወደ ትሬድ ትገባለህ። ይህ ማለት ትልቁን ገበያ የሚሄድበትን መንገድ በመከተል አደጋህን በመቀነስ ትርፍህን ከፍ ማድረግ ትችላለህ ማለት ነው።
ይህን ዘዴ በመለማመድ አላስፈላጊ ትሬዶችን በማስቀረት በገበያው ውስጥ ያለህን እድል ከፍ ማድረግ ትችላለህ። ሁልጊዜም ትልቁን ምስል ማየት ለትንሹ ውሳኔህ መነሻ መሆኑን አትዘንጋ።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 198 |
| 14 | እንዴት አመሻችሁ ጋይስ ፡
በዛሬው የላይቭ ፕሮግራማችን በትሬዲንግ እና በሚኖሩብን ፍርሀት እንዲሁም ይህንኑ ፍርሀት ከሚፈጥረው ኮርቲሶል የተሰኘ ሆርሞን ዙሪያ እንወያያለን። መድረኩን መቀላቀል የምትፈልጉ ልጆች ተቀላቀሉን።
https://vt.tiktok.com/ZS9j5v2HqLxwh-Lo32X/ | 1 207 |
| 15 | SEASON 3 IS HERE. 🔥🔥🔥
የአድዋ ጦርነትን እና ትሬዲንግን ምን አገናኛቸው???
በዚህ ቪዲዮ ስለሊውኪዲቲ ስዊፕ ፅንሰ ሀሳብ እና ሳይኮሎጂ የአድዋ ጦርነትን አናሎጂን በመጠቀም ለማስረዳት ተሞክሯል። በእርግጥኝነት ሀሳቡን ከልቡ ያዳመጠው እጅጉን እንደሚማርበት እናምናለን።
ይህ መሰል ቪዲዮዎች ይበልጥ እየተሰሩ ይለቀቁላችሁ ዘንድ መውደዳችሁን በላይኮቻችሁ እና በኮሜንቶቻችሁ አሳዩን። Lets go my people. 🔥🔥🔥
የፖስት ሊንክ፡
https://www.tiktok.com/@ice_ethiopia/video/7651669727818960144 | 1 256 |
| 16 | ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ ፡
ትላንት ለማስታወቅ እንደሞከርነው አሁን ያላችሁበት ስቴጅ በማለፍ ወደሌቭል 3 በማለፍ ሌሎቹ ተማሪዎች የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ እና አብረን ጉዟችንን ለመቀጠል እንዲሁም ቪዲዮ ከዚህ ላይ ተነስቶባችሁ ግን ያልጨረሳችሁ ልጆችም እንድትጨርሱ ወደዲስኮርድ አፕሊኬሽን እና መማሪያ ቻናላችን ከዚህ በታች ባለው መቀላቀል ትችላላችሁ። በመቀላቀሉ ሂደት የምትጠየቁት አራት ጥያቄዎች ያሉ ሲሆን ከነሱ መሀል በእኛ IB የHFM አካውንት መክፈታችሁን የሚጠይቅና የዋሌት አይዲ ስለሚጠይቃችሁ በቅድሚያ በኛ ሊንክ ተመዝግባችሁ መጨረሳችሁን ማረጋገጥ መቻል ይኖርባቹሀል።
https://discord.gg/ENubP6J5 | 1 218 |
| 17 | 🏛 የማዕከላዊ ባንኮች ንግግሮች (Hawkish vs Dovish)
በፎሬክስ ገበያ ውስጥ የማዕከላዊ ባንክ መሪዎች መግለጫዎች የዋጋ እንቅስቃሴን በመወሰን ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህን የፖሊሲ ፍንጮች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች እንከፍላቸዋለን፦
🦅 1. Hawkish (ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ)
የመጀመሪያው Hawkish የሚባለው ሲሆን፣ ዋና ትኩረቱ የዋጋ ንረትን (Inflation) መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ነው። በዚህም ባንኮች የወለድ መጠንን ለመጨመር ወይም ካለበት ከፍ አድርገው ለመቀጠል ፍላጎት እንዳላቸው የሚጠቁሙ ሲሆን፣ ይህም ብዙውን ጊዜ የዚያ አገር ገንዘብ ዋጋ በገበያው ላይ እንዲጠናከር ያደርጋል።
🕊 2. Dovish (ላላ ያለ/የሚያነቃቃ የገንዘብ ፖሊሲ)
ትኩረቱን በኢኮኖሚ ዕድገትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚያደርግ ላላ ያለ የገንዘብ ፖሊሲ ነው። በዚህ ወቅት ባንኮች ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ሲሉ የወለድ መጠንን ለመቀነስ (Interest Rate Cut) ወይም ሳይጨምሩ ለማቆየት ፍላጎት እንዳላቸው የሚያሳዩ ሲሆን፣ ይህም በአብዛኛው የአገሪቱን ገንዘብ ዋጋ እንዲዳከም ያደርጋል።
💡 ማጠቃለያ፦ እንደ ባለሀብት የማዕከላዊ ባንኮችን ቃና መከታተል የገበያውን የረጅም ጊዜ አቅጣጫ ለመተንበይ ቁልፍ መሣሪያ ነው። የንግግራቸው ቃና ወደ Hawkish ሲያዘነብል የገንዘብ ጥብቅነትን፣ ወደ Dovish ሲያዘነብል ደግሞ ማነቃቂያን በመገመት የቴክኒካል ትንተናችንን ማገዝ እንችላለን።
✍️ Education Department
📣 Powered By : ETN Ecosystem™
🤝 Partners : CryptoTalk-ET™ 🇪🇹 | ET-Netsa Apps™ | ICE™ Trading Psychology Academy
▶️ YouTube: NegadRas™ Fx Academy | 1 327 |
| 18 | ሰላም ጋይስ፡
እንደምታውቁት ላለፉት አምስት ወራት የመጀመሪያውን የነጋድራስ ባች ተማሪዎች ስናሰለጥን የቆየን እና በዚህም ከተመዘገቡ 4000 ሺ ተማሪዎች ውስጥ ከ800 የማያንሱት የመጀመሪያ አካውንታቸውን በመክፈት ትሬዲንግ ሀ ብለው የጀመሩበት ከነሱ ውስጥ ደግሞ በጊዜ እና የተለያዩ ትምህርታዊ ፈተናዎች ያለፉ የተጣሩ 60 ተማሪዎችን በመያዝ አሁን ላይ ወደቀጥታ የትሬደርነት ጅማሬያቸው የደረሱ ልጆች በመያዝ በዚህ ባች የሰጠነውን አገልግሎት ከጫፍ ማድረስ ችለናል። በዚህም እስካሁን ትምህርቱን እየወሰዳችሁ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች አሁንም ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ ያልቻላችሁ ልጆች ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚጠበቁባችሁን ትምርህታዊ ሁነቶች አጠናቃችሁ ወደዲስኮርድ የሚወስዳችሁን ምዝገባ ከነገ ጀምሮ በአድሚኖቻችን በኩል እንድታደርጉ እና ይህ ሳምንት የመጨረሻ የአንደኛው ባች ምዝገባ ሳምንት እንደሚሆንና ከአሁን በኋላ በሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በኩል ካልሆነ ምንም አይነት ምዝገባ እንደማናደርግ ለማስታወስ ወደድን።
እሳክሁን በመጣንበት አካሄድ የተሰጧችሁ የጀማሪ ትምህርቶች ጥሩ እንደነበሩ እና በአገልግሎታችንም እንደተደሰታችሁ እምነታችን ነው። አሁንም በነጋድራስ የመጀመሪያ ባች ውስጥ መታቀፍና የትሬዲንግ ህይወታችሁን ከኛ ጋር ለመቀጠል የምትፈልጉ ልጆች ከላይ እንደተገለፀ ይህንኑ ስራ በሚያሳልጡ የአድሚን አባላት በኩል ከነገ ጀምሮ መቀላቀላችሁ እንዳትረሱ ለማለት ወደድን። ያሏችሁን ጥያቄዎች በኮሜንት ሳጥን በኩል እንድታሳውቁን ስንልም ለማስታወስ ወደድን።
በያላችሁበት ሰላም። | 1 383 |
| 19 | የቅዳሜ ምሽት THE INTERVIEW የተሰኘ ፕሮግራማችን ትሬደር ሶፎኒያስን ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ ይዘንላችሁ እንቀርባለን። በቲክቶክ ላይቭ የቀጥታ መድረክ ላይ ተቀላቀሉን።
https://vt.tiktok.com/ZS9jkEvDCv6wD-2NK8m/
https://www.linktr.ee/negadrasfx | 1 450 |
| 20 | የነጋድራስ የመጀመሪያ ተማራቂ ተማሪዎች የሁለት ሳምንት የትሬደርነት ጉዞ በዚህ መልኩ ተጀምሯል። እንደኮሚዩኒቲ የሚደረጉ የማርኬት አናሊስስ እና ጥሪዎችን ከነውጤቶቻችው ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ።
https://docs.google.com/spreadsheets/d/1ig_vqvTbEl35D-npoURcUjTDBAU1JzR34X7ueRH_uV0/edit?gid=542769468#gid=542769468 | 5 323 |
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
