fa
Feedback
ELEVATE SKILL

ELEVATE SKILL

رفتن به کانال در Telegram

Master Your Skills with us! 🎨Graphics Design 🎞Video Editing 📈 Digital Marketing 🌐 Web Development 📱 Application Development 🤖Robotics Telegram :- @Elevateskillsupport Instagram :- elevateskill.1 📞-+251981807055

نمایش بیشتر
1 105
مشترکین
-224 ساعت
+57 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
PART 2 | 🎓 የመጨረሻዎቹ የዩኒቨርሲቲ ቀናት... የማይረሱ ትዝታዎች ከFreshman የጀመረው ጉዞ... ሳናስበው ወደ መጨረሻው መድረስ ይጀምራል። "እኛም አምስተኛ ዓመት ደረስን?" ብለን እርስ በርሳችን እንጠያየቃለን። ትናንት ገና የግቢውን ካርታ እየጠየቅን የነበርን እኛ... ዛሬ ግን አዲስ Freshman ተማሪዎች መንገድ ሲጠይቁን እኛ እያሳየናቸው ነው። ቀኖቹ እንዴት እንዳለፉ አናውቅም... ከዚያ በኋላ የመመረቂያ ፕሮጀክት (Senior Project) ይጀምራል። በላብ... በድካም... በእንቅልፍ እጦት... አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተራችን ይበላሻል፤ ፋይላችን ይጠፋል፤ Supervisor እንደገና አስተካክሉ ይላል፤ እኛም "ከመጀመሪያ እንደገና?" ብለን እንደክማለን። ግን... አንተን ከጎንህ የቆሙት ጓደኞች አሉ። "አትጨነቅ... እንጨርሰዋለን!" የሚል አንድ ወዳጅ ሁሌም ይኖራል። ከዚያ... Defense ቀን ይደርሳል። ሌሊቱን ሙሉ ስላይዶችን እየደጋገምን... በመስታወት ፊት Presentation እየሞከርን... ልባችን በፍጥነት እየመታ... "Good morning, respected examiners..." ብለን ስንጀምር ድምፃችን ትንሽ ይንቀጠቀጣል። ጥያቄዎች... ውይይቶች... ጭንቀት... ከዚያ በኋላ... "Congratulations! You passed." ይህን አንድ አረፍተ ነገር ለመስማት ያሳለፍነውን የአመታት ጥረት ወዲያውኑ እንረሳዋለን። ከዚያ... የመጨረሻ ውጤት ይለጠፋል። Telegram Group... Department Group... Class Representative... "Result ወጣ!" የሚለውን መልዕክት ስናይ... ልባችን ከደረታችን የሚወጣ ይመስላል። ID Number እየፈለግን... አንዳንዶች በደስታ ይጮኻሉ... አንዳንዶች በዝምታ ያለቅሳሉ... አንዳንዶች ጓደኛቸውን እያቀፉ "ተመረቅን!" ይላሉ። ከዚያ የማይረሳው ሳምንት ይጀምራል... 📸 Graduation Photos... 🎉 Class Dinner... ☕ የመጨረሻ Coffee Date... ❤️ የመጨረሻ ፍቅር ቀጠሮ... 😂 የመጨረሻ አብሮ መቀለድ... "ከዚህ በኋላ መቼ እንገናኝ?" ይህ ጥያቄ በሁሉም አእምሮ ውስጥ ይመላለሳል። ከዚያ... የምርቃት ቀን ይመጣል። ጥዋት በማለዳ... ያንን ጥቁር Graduation Gown ስንለብስ... በመስታወት ፊት ቆመን ራሳችንን ስናይ... "በእውነት... ተመራቂ ሆኛለሁ?" ብለን እንጠይቃለን። ከዚያ... ከሩቅ መንገድ የመጡ እናት... አባት... እህት... ወንድም... በሕዝቡ መካከል ፊታቸውን ስናይ... ያኔ የመጀመሪያው ቀን ትዝ ይለናል። እነሱ የከፈሉት ዋጋ... ያደረጉት መስዋዕትነት... የነበራቸው ተስፋ... ሁሉም በአንድ ቅጽበት በአእምሯችን ይመጣል። አንዳንዶቻችን ፎቶ እየተነሳን... አንዳንዶቻችን ወላጆቻችንን አቅፈን... በደስታ እንባ እናነባለን። ግን... ከሁሉ የከበደው ጊዜ ገና ይቀራል። ዶርማችንን የምንለቅበት ቀን... አልጋችንን እንጠርጋለን... የተለጠፉትን ፎቶዎች እናወርዳለን... የልብሳችንን ቦርሳ እንሞላለን... በመጨረሻ... ባዶ የሆነውን ክፍል ዞር ብለን እናየዋለን። ያ ክፍል... ሳቃችንን ያውቃል... እንባችንን ያውቃል... ስንታመም ያየን ነው... ስንፈተን ያየን ነው... ስንደሰት ከእኛ ጋር የኖረ ነው። በሩን ቀስ ብለን እንዘጋዋለን... ምናልባት... ለመጨረሻ ጊዜ። ሻንጣችንን ተሸክመን... ያንን 5 ዓመት የኖርንበትን ግቢ ቀስ ብለን እየተመለከትን እንወጣለን። ከጀርባችን የሚቀረው... ሕንፃ ብቻ አይደለም። ወጣትነታችን ነው። PART 3 | 🌍 ከምርቃት በኋላ... የእውነተኛው ሕይወት ጅማሬ @elevateskill⭐️ Via//Amanuel⭐️

Welcome 🎉
+1
Welcome 🎉

🎓 ወደ ኋላ ተመልሰን እናስብ... አንድ ደቂቃ ዝም ብለን ወደ ኋላ እንመለስ። ወደ ዩኒቨርሲቲ የገባንበትን የመጀመሪያ ቀን ታስታውሳላችሁ? ያ ቀን... እኛ ለአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ነበር፤ ለቤተሰቦቻችን ግን የብዙ አመታት ድካምና መስዋዕትነት ፍሬ ነበር። አንዳንዶቹ ቤተሰቦች በሬ ሸጡ፤ አንዳንዶቹ እህላቸውን ሸጡ፤ ሌሎች ደግሞ መሬታቸውን አስያዙ። ያላቸውን ሁሉ አውጥተው "ልጄ ይማር፣ ሕይወቱ ይለወጥ" ብለው አዲስ ልብስ፣ አዲስ ቦርሳ፣ አዲስ ጫማ ገዝተው በእንባና በፈገግታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሸኙን። እኛ ግን ያኔ ሁሉንም አላስተዋልንም። በአዲሱ አለም ተውጠን ነበር። አዲስ ግቢ... አዲስ ዶርም... አዲስ ጓደኞች... አዲስ ሕይወት... ከአገር ሁሉ የመጡ ተማሪዎችን አገኘን። የተለያየ ቋንቋ፣ ባህል፣ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ከአንድ ክፍል፣ ከአንድ ዶርም ውስጥ ቤተሰብ ሆኑ። በመጀመሪያው ሳምንት ግቢውን ስንዞር የነበረው ጉጉት... የመጀመሪያው ክፍለ ትምህርት... የመጀመሪያው ሌክቸር... የመጀመሪያው ሚድ ፈተና... የመጀመሪያው ውጤት... ሁሉም ዛሬ ትዝታ ሆነዋል። ምሽት ላይ በዶርም ተሰብስበን የምናወራቸው ወሬዎች... "ነገ እናነባለን" ብለን ሌሊቱን ሙሉ ስናወራ... ከፈተና አንድ ቀን በፊት መጽሐፍ ፈልገን ስንሯሯጥ... Assignment የሚሰራውን ጓደኛ ፈልገን ስንጠራ... Group study ብለን ተሰብስበን ከ10 ደቂቃ በኋላ ወደ ቀልድ ስንገባ... በካፍቴሪያ ረጅም ወረፋ ስንጠብቅ... የወር መጨረሻ ገንዘብ ሲያልቅ "እስከ ሰኞ አበድረኝ" ማለታችን... ሁሉም... ዛሬ የምንስቅባቸው ትዝታዎች ሆነዋል። አንዳንድ ጓደኞች ከእኛ ሕይወት ውስጥ ወጡ፤ አንዳንዶቹ ግን እስከዛሬ የሕይወት ጓደኞቻችን ሆነው ቀሩ። አንዳንድ አስተማሪዎች ጠንካራ ነበሩ፤ በወቅቱ አልወደድናቸውም። ዛሬ ግን ብዙ ያስተማሩን እነሱ እንደነበሩ እንረዳለን። ይቀጥላል .........p2 @elevateskill✅                                               Via//Amanuel⭐️ .

Agent coming soon ...🤝

Video editing Master class
Video editing Master class

photo content
+5

We did it elevateskill on ebs tv

photo content
+4

የ elevateskill ምዝገባ ከጥቂት ቀናት በኃላ ተዘግቶ የ 2018 የክረምት ስልጠና ይጀመራል ።

በዚህ ክረምት ምን ለመማር /ለማከናወን//አሰባቹህ?
Anonymous voting

photo content

photo content

ሀሳብ እና ጥያቄ @elevateskillsupport

ሊጀመር 1 ስዓት ብቻ ቀርተውታል።

Repost from ELEVATE SKILL
ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ ይጠብቁን። ከወጣት entrepreneur //CEO-CO FOUNDER // በተለይ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች //ምክር ብቻ ሳይሆን የስራ እድልንም ይዞ መቷል።ምሽት 3:00 እንዳያመ
ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ ይጠብቁን። ከወጣት entrepreneur //CEO-CO FOUNDER // በተለይ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች //ምክር ብቻ ሳይሆን የስራ እድልንም ይዞ መቷል።ምሽት 3:00 እንዳያመልጣቹህ።

ሁላቹህም ይህን video እዩት። ሀሳባቹህን comment ላይ