fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 486
مشترکین
+3524 ساعت
+997 روز
+94030 روز
آرشیو پست ها
🔥የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ በየጋግና ቀበሌ ፣ በረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ማይ አንገታም ቀበሌ ላይ ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አካሄዱ‼️ መሰከረም 12/2018 ዓ.ም 💥የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ በየጋግና ቀበሌ ከሚገኙ የማሕበረሰብ ክፍሎች ጋር ሠፊ የሆነ ውይይት አካሔደ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ፮ኛ ክ/ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ከሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ውስጥ አንዱ የጋግና ቀበሌ ነው። የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ግዙፍ ኮማንዶ ባስመረቀበት ዕለት የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድም በየጋግና ቀበሌ ከሚኖሩ የማሕበረሰብ ክፍሎች ጋር  ሠፊ የሆነ ህዝባዊ  ውይይት  አካሒዷል፡፡  በውይይቱ በርካታ ጉዳዮች የተዳሰሱ ሲሆን በዋናነትም 👉አሁናዊ የአማራ ትግል ቁመናን አስመልክቶ ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡ 👉ፋኖ ከህዝባችን ጋር ሊኖረው በሚገባው መስተጋብር ላይ በጥልቅ ተወያይተናል: 👉 በቀበሌ ደረጃ የፍትህ አሠጣጥ ሁኔታ ምን ይመስላል ወደፊትስ እንዴት መሰራት አለበት የሚሉት እና ሌሎች  ጉዳዮች በጥልቀት ተወያይተን የወደፊት አቅጣጫም አስቀምጠናል።  በውይይቱ የብርጌዱ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ  ፋኖ አንሙት አባቴነህ፣  የብርጌዱ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ ይታያል ጌታ ፣ የብርጌዱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ባዬ ሽፈራውና የብርጌዱ ም/ሰብሳቢ ፋኖ  ምንይዋብ አንበሉ የተገኙ ሲሆን ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ሠፊ የሆነ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትንታኔዎች ተሠጥተዋል ሲል የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ባዬ ሽፈራው ( ቀኜ) ገልጿል። 💥ሕዝባዊ ስብሰባ በበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ማይ አንገታም ቀበሌ! የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ከማይ አንገታም ቀበሌ ማሕበረሰብ ጋር ውይይት አደረገ። በውይይቱ የክፍለ ጦሩ የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ ፋኖ አረፋይኔ ተጎድና የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊው ፋኖ አበባየሁ ባንታምላክ የተገኙ ሲሆን በአማራ ትግል መሠረታዊ ጉዳዮችና የትግላችንን አሁናዊ ልዕልና አስመልክቶ ለማሕበረሰቡ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ሰጥተዋል። በተጨማሪም የቀበሌ መዋቅሩንም በመፈተሽ የአመራር ሪፎርም ሰርተዋል። ሁሉ ነገሩን ሳይሰስት ለሚሰጠን ሕዝባችን ያለንን እንሰጠዋለን! ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሕዝባችን! ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ6ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት 13/ዐ1/2018 ዓ.ም

ሰልፍ እንጂ ቆሞ መዋጋት የማይችለው ሰራዊት ጀነራል ለመሆን ጥሩ ዘፋኝ ወይንም ተወዛዋዥ መሆን በቂ ነው። ብርጋዴር ጀነራል ጌትንነት እንኳን ለአቅመ ጀነራልነት አበቃህ። አንተን የረዳ አምላክ የቀድሞ
ሰልፍ እንጂ ቆሞ መዋጋት  የማይችለው  ሰራዊት  ጀነራል ለመሆን ጥሩ ዘፋኝ ወይንም ተወዛዋዥ መሆን በቂ ነው። ብርጋዴር ጀነራል ጌትንነት እንኳን ለአቅመ ጀነራልነት አበቃህ። አንተን የረዳ  አምላክ የቀድሞ የሙያ  ባልደረባህን ሰማኸኝ በለውንም ረድቶት  ሜጀር ጀነርራል ሁኖ ለማየት ያብቃን። ውሻ በጅራቷ አስራ እየዞረች ያለውን የጀንነራልንነት ማዕረግ ለሰሜ ባላገሩ  አይበዛበትም።

#ሰበር ከግምባር! በአየር ወለድ ኮማንዶዎች እና በአድማ ብተና አባላት መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት በርካቶች መገደላቸው ታወቀ! ከተገደሉት መካከል አብዛኻኞቹ የአድማ ብተና አባላት ናቸው የተባለ ሲሆን፡ በውጊያው የቆሰሉትም ወደ ሕክምና ቦታ ቢወሰዱም ከወረዳና ከዞን አመራሮች በመጣ ትዕዛዝ እንዳይታከሙ መከልከላቸው ታውቋል። በዚህም ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ ሕክምና ባለማገኘታቸው ሕይወታቸው ያለፈ የአድማ ብተና አባላት መኖራቸው ተጠቁሟል። አገዛዙ በሕዝባቸው ላይ ለሚፈፅመው የዘር ማጥፋት ተባባሪ የሆኑት የአድማ ብተና አባላቱ፡ በአገዛዙ አመኔታና ክብርም አጥተው የውሻ ሞት መሞታቸውን ቀጥለዋል ነው የተባለው። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ከቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ስድስተኛ ክፍለ ጦር የተሰጠ የጥንቃቄ መልዕክት መልዕክት‼️ እንደሚታወቀው አማራን ከነሁለንተናዊ ማንነቱ ለማጥፋት አውዳሚ የሆነ የፖለቲካ ትርክት በመንዛት በአማራ ብሎም በመላው ምድረ ኢትዮጵያ በሚገኘው አማራና ትውልደ አማራ ላይ የጅምላ ፍጅት (Genocide) አውጆ ወደ ስራ ከገባ በርካታ ዓመታት ተቆጠረዋል። በዚህ መዋቅራዊ በሆነና በቀጥታ በአረመኔው የአገዛዙ ሥርዓት በሚመራ የዘር ፍጅትም አያሌ የአማራ ሕዝቦች ሙስሊም ክርስቲያን ሳይ'ለዩ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፤ መንፈሳዊ ተቋማት ወድመዋል፤ መነኮሳት፣ ካሕናት፣ዲያቆናት... ወዘተ ታርደዋል ተጨፍጭፈዋል። ይህ በወገኖቹ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ተግባር የአንገበገበው የአማራ ሕዝብም በምልዓት በመደራጀት በፈጣሪ መለኮታዊ እገዛና ባለው አማራዊ የጀግንነትና የኃያልነት ጸጋ እየታገዘ በምድርና በአየር ሊውጠው የመጣውን የአረመኔ ስብስብ እየጠረገ በጥቂት የነፍስ ወከፍ ትጥቆች ያለ የሌለ ትጥቁን እየተቀበለው ፤ አያሌ ቀጠናዎችን፤ እየተቆጣጠረ፤ ጠላትን በሁለንተናዊ ዘርፍ በማሽመድመድ መላ ሕዋሱን አፈራርሶ ቀፋፊ አጽሙና ሹል ምላሱ ብቻ እንዲቀርለት አድርጎት በደመ ነፍስ እየተወራጨ ይገኛል። ይህን ሁሉ አለኝ የሚለውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ዘመቻ አድርጎ ያልተሳከለት ይህ የሙታን ስብስብ  የሐሰት ፕሮፖጋንዳውን በመንዛት በቀረችለት ምላሱና የወሸት ድሪቶውን በሚደርትባቸው ሚዲያዎቹ ሲፏልል ይውላል። ከሰሞኑም ሕዝብን ከፋኖና ፋኖን ከፋኖ ትከፋፍልልኛለች ብሎ ያሰባትን የመጫወቻ ካርድ በመምዘዝ ታጋዩና ሕዝቡ መላ የስሜት ሕዋሳቱን ከትግሉ ላይ እንዲነቅል ለማድረግ ከፋፋይ አጀንዳ ለመስጠት አስቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህም ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ይኸው የአራዊት ስብስብ ያጯጩኸው የነበረውንና በዚህም ሰበብ ጸረ እምነቱ ዓብይ አሕመድ ወራሪ ሠራዊቱን አዝምቶ አያሌ የደብረ ኤልያስ ብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳም መነኮሳትና ሕጻናትን ለማስፈጀበትና ገዳሙንም በከባድ መሳሪያ በታገዘ ውጊያ ለማውደም የተጠቀመበትን አለም ብርሃን የሚል የሃይማኖት ፖለቲካ ዛሬም እንደ አዲስ በማንሳት በጀግናው ሠራዊታችንና በታላቁ ሕዝባችን መካከል ልዩነት ለመፍጠር ክፍለ ጦራችን በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች ማለትም በደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ኤልያስ፣ በአማኑኤል፣በደምበጫና በረቡዕ ገበያና በአካባቢው በሚገኙ አገዛዙ በተወሸቀባቸው ከተሞች  በመንዛት ሕዝብን ለማደናገር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። ፨ በተጨማሪም ይህ ዕቅዱ ተአማኒነት ይኖረው ዘንድ ንጹሐንን በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገድሉ ገዳይ ቡድኖችንም እያደራጀ መሆኑን፤ በእነዚህ በአገዛዙ የተዋቀሩ ገዳይ ቡድኖች የሚሰራው ስራም በቪዲዮና በፎቶ የታገዘ እንዲሆን በማድረግና ሚዲያ ላይ በማጯጯህ የፋኖን መልካም ገጽታ ለማጥፋት ዝግጅቱን ጨርሷል። ፨ ለአብነት ያክልም የየትኛውም ብርጌድ አባል ያልነበሩና ያልሆኑ ነገር ግን ከነሙሉ ጥቃቸው ፈንድቃ አካባቢ (የጠላት ቀጠና ላይ) አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ አስረው የሚንቀሳቀሱና ራሳቸውን ፋኖ እያሉ የሚጠሩ ነገር ግን ከላይ የጠቀስነውን የብልጽግናን እኩይ ተልዕኮ የተሸከሙ በርካታ የብልጽግና ኃይሎች መኖራቸውን ደርሰንበታል። ፨ በመሆኑም የተከበረው ሕዝባችን ይህንን የጠላት የውሸት ፕሮፖጋንዳ ከወዲሁ ተረድቶ ብልጽግና ሊነዛው በሚችለው የሐሴት ወሬ ከመወናበድ እንዲጠበቅና   አስፈላጊውንም ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ እናሳስባለን። መውጫ፦ ጸረ እምነቱ ኦሕዴድ መራሹ የብልጽግና ቡድን ለሃይማኖት ተቆርቋሪ ቢሆን ኖሮ አያሌ ገዳማትን፣ አብያተ ክርስቲያናትን፣የአብነት ትምሕርት ቤቶችንና አብያተ መስጊዶችን በቀጥታ በሚያዝዘው ወራሪ ሠራዊቱ ባላወደመ፤ መነኮሳትን፣ ካሕናትን፣ሊቃውንትን፣ ዲያቆናትን፣የቆሎ ተማሪዎችንና በወለጋ የሚገኙ ሙስሊም ወገኖቻችንን በግፍ ባልፈጃቸው፤ የተቀደሱ የአምልኮ መፈጸሚያ ቦታዎችንም የአረመኔ ሠራዊቱ ካምፕ ባላደረጋቸው ነበር። የኛ ጉዶች የአማራ ባንዳዎችም ለሆዳቸውና ለስልጣናቸው ሲሉ የደም ሰው ለሆነው የዓብይ አሕመድ የጥፋት ሰይፍ የገዛ ሕዝባቸውን አመቻችተው የሚሰጡ፤ እምነቱን፣ ማንነቱንና ባሕሉን ለወራሪ አሳልፈው የሚሸጡ፤ በንጹሐን ደም ዳቦአቸውን የሚያበስሉ ናቸው። ማንነት ባሕል፣ እምነት በእነርሱ ዘንድ ሞቶ ተቀብሯል። እምነታቸውም ማንነታቸውም ሆዳቸውና ስልጣናቸው ነው። ሁለቱም ግን በፋኖነት የድል ጉዞ እየከሰሙ፣ እየጠወለጉና ወደ ትቢያነታቸው እየተቀየሩ ይመጣሉ። እኛ ግን በወሬ የሚናድ፤ በድቡሽት ላይ የተመሰረተ የትግል መሠረት አልጣልንም። እንኳን ፕሮፓጋንዳ ሜካናይዝድም አይፈታንም። ድል የአማራ ሕዝብ! ድል ለአማራ ፋኖ! መስከረም 12/2018 ዓ.ም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ (6ኛ) ክፍለ ጦር 13/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

The Universal Declaration of Human Rights (UDHR) & International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) guarantee lib
The Universal Declaration of Human Rights (UDHR) & International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR) guarantee liberty & security. @UN @HRW @ICRC @IntlCrimCourt @ACHPR @EU @fidh_un @amnesty @EthioHRC We urge Ethiopia to respect these laws & disclose Col. Aseged Mekonnen's whereabouts! 🌎 #HumanRights #Accountability

#የህዝብ ማእበል የታየበት ውይይት በአፋብሀ ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ሀዲስ ዓለማየሁ 7 ኛ ክፍለጦር አብራጅት ብርጌድ በሚያስተዳድረው ቀጠና ዛሬ መስከረም 12 /01/2018 ዓ/ም በባሶሊበ
#የህዝብ ማእበል የታየበት ውይይት በአፋብሀ ምእራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ሀዲስ ዓለማየሁ 7 ኛ ክፍለጦር አብራጅት ብርጌድ በሚያስተዳድረው ቀጠና ዛሬ መስከረም 12 /01/2018 ዓ/ም በባሶሊበን ወረዳ ከሁሉም ቀበሌወች ከተውጣጣ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች እና የየላምገጅ ታዳጊ ከተማ ህዝብ ጋር ሁሉን አቀፍ ውይይት አድርገናል። እንደሚታወሰው የላምገጅ ከተማ ከታህሳስ 19 /2017 ጀምሮ በጠላት ቁጥጥር ስር የነበረች እና በዘመቻ ሰማእታት ሀዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር ነጻ ካወጣቸው ቀጠናወች አንዷ ናት ። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ መስከረም 12/2018 ዓ.ም በሁሉም ቀጠና የህዝብ እና የጦር ውይይቶችን እያካሄደ ይገኛል። በእነማይ ወ
+6
የአ.ፋ.ብ.ኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ መስከረም 12/2018 ዓ.ም በሁሉም ቀጠና የህዝብ እና የጦር ውይይቶችን እያካሄደ ይገኛል። በእነማይ ወረዳ  ደብረ ቅዱሳን እና ዘብች/ፈለገ ሰላም ቀበሌ በነበረው ውይይት የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል እንዴት ወደ ትጥቅ ጥቅል እንደገባ እና ለትጥቅ ትግሉ አስፈላጊ የሆኑ ሀሳቦች ተነስተው ውይይቶች ተካሂደዋል። በውይይቱ የብርጌድ አመራሮች እና የሻለቃ አመራሮች በመገኜት የአማራ ህዝብ ለሚያደረገው የህልውና ትግል ህዝባችንም ጦራችንም ዝግጁ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተ ሰጥተዋል። መስከረም 12/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ    ፣አዲስ ተስፍ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የዐማራን ዘር መጥፋት ሥርዓታዊነት የሚያሳዩ የራሱ የሥርዓቱ ሰነዶች! የዐማራ የዘር ጭፍጨፋ ስንል ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ተማርን የሚሉን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮችም ሊሞግቱን ይሞክራሉ። ዐማራ ሥርዓት መለ
የዐማራን ዘር መጥፋት ሥርዓታዊነት የሚያሳዩ የራሱ የሥርዓቱ ሰነዶች! የዐማራ የዘር ጭፍጨፋ ስንል ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ተማርን የሚሉን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮችም ሊሞግቱን ይሞክራሉ። ዐማራ ሥርዓት መለወጥ የሚያስፈልገው ለቅንጦት አይደለም። ኅልውናውን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ዘመቻ የከፈተበትንና በተጨባጭ እያጠፋው ያለውን ሥርዓት  መጋፈጥ አለበት። ሥርዓቱን በጥገናዊ ለውጥ ለማስቀጠል የትኛውንም አይነት ሙከራ ማድረግ መጥፋቱን በስምምነት መቀበል ማለት ነው። እስኪ እንደ ኤውሮፓውያን አቆጣጠር በ1994 እና በ2007 መካከል የነበረውን  የሚከተለውን የሕዝብ ዕድገት ዓመታዊ ምጣኔ ተመልከቱ። የዐማራ ሕዝብ ዕድገት ብቻ ተለይቶ ለምን 1.7%  ሆነ? በየትኛው አመንክዮ ነው በኢትዮጵያ ካሉ ነገዶች ሁሉ ተለይቶ የዐማራ ሕዝብ ዕድገት ብቻ ዝቅተኛ የሚሆነው?  የሥርዓቱ ነውረኝነት በግልጽና በተመዘገበ መንገድ ዐማራን የማጥፋቱን ሂደት ሲያሳልጥ የነገ ተጠያቂነቱን አይፈራም። ዐማራ ሊድን የሚችለው ሥርዓት ሲለዎጥ ብቻ ነው። ድል ለዐማራ ሕዝብ! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ፈጣሪ ጥንብህን አንተ አንሳልን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለ ተጨማሪ ህክምና ከሃገር መዉጣታቸዉ ተሰማ ከአወዛጋቢው የመጽሐፍ ምረቃ ንግግራቸው በኋላ አቶ ጌታቸው ረዳ ለህክምና ወደ ዱባይ አቀኑ አቶ ጌታቸዉ በ
ፈጣሪ ጥንብህን አንተ አንሳልን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለ ተጨማሪ ህክምና ከሃገር መዉጣታቸዉ ተሰማ ከአወዛጋቢው የመጽሐፍ ምረቃ ንግግራቸው በኋላ አቶ ጌታቸው ረዳ ለህክምና ወደ ዱባይ አቀኑ አቶ ጌታቸዉ በስኮር ህመም ምክንያት በተደጋጋሚ የህክምና ክትትል በተለያዩ የአለም ሃገራት ባሉ ሆስፒታሎች እያደረጉ እንደነበር ይታወሳል ፡፡ via_Ankuar ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

''(አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦር)'' ➤ ሰራዊቱ ብትንንትኑ እየወጣ ፋኖን ተቀላቀሉ... .>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>. ብረካታ የአገዛዙ ሰራዊቶች እየፈራረሱ ሙሉ ትጥቃቸውን በመያዝ ቀን በቀን የወርቅ አባይ ብርጌድን እየተቀላቀሉ ነው። ''፻/አለቃ አኑዋር'' እና 8 ጥቁር ክላሽ የታጠቁ የአረመኔው ስርዓት ወምበር ጠባቂዎች ስርዓቱን በማውገዝ እና ፋኖን ለማገዝ ተቀላቀሉ። የወርቅ አባይ ብርጌድ ዘጠኙን ከብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ ሰራዊቶችን በደማቅ አቀባብል ተቀብለዋቸዋል። ''፻/አ አኑዋር'' እንደተናገረው፦ስርዓቱ ሀገር ለመጠበቅ የወጣውን ሰራዊት ለግል ጥቅም እና ለሽፍትነት ተጠቅመውብናል፣ ለእውነት ለማንነት እና ለአንድነት እየታገለ ያለው ፋኖ መሆኑን በቦታው ተገኝቼ አረጋግጫለሁ፣ እየተዋጋን የነበረም ህዝቡ እንጅ ፋኖዎች ብቻም አልነበሩም ብሏል። የነበርሁበት የእሁዲቱ ሰራዊት በንጹሀኖች ላይ ፋኖ ናቸው በሚል የውሸት ትርክት ያለገደብ እዬታሰሩ፣ እየተረሸኑ፣ እንዲሁም ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት በመፈጸማቸው በኑጹሃኖች ላይ አንገት የሚያስደፋ ግፍ እና ሰቆቃዎች ደርሷል ሲልም አክሎ ገልጿል። ቃል ኪዳን የገባንላት እኛ የምንሞትላት ኢትዮጵያን ስርዓቱ በአንድ ብሔር ለውጧታል። እውነታውን እና ሀቁን እየተገነዘብነው ስንመጣ ሀገር ወዳዱን የአማራ ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት መሆኑን ስናውቅ የታጠቅነውን መሳሪያ ይዘን ወደ ፋኖ ተቀላቀልን ሲሉ ሌሎች ጓዶቹም ተናግረዋል። በአረመኔው ስርዓት ውስጥ ሁናችሁ የኢትዮጵያ ዋልታ እና ማገር የሆነውን የአማራን ህዝብ እየተዋጋችሁ እና እየጨፈጨፋችሁ ያላችሁ ጓዶች ራሱን ለማዳን ከሞት ለማምለጥ፣ ለህልውና እየተዋደቀ ያለውን ሀገር ወዳዱን የአማራን ህዝብ እንታደገው ተቀላቀሉ። ግምባራችንን ለጥይት፣ እኛ ተሰውተን ህዝባችንን ልንጠብቅ ገብተን ህዝባችንን እያጠፋነው ስለሆነ ከእኛ ተረድታችሁ ወደ ፋኖ ተቀላቀሉ ህዝብ እናድን ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የመጡ ወታደሮች ፻/አለቃ አኑዋር እና 8 ሰራዊቶች እምባ እየተናነቃቸው መልዕክታቸው አስተላልፈዋል። ድል ለአማራ ህዝብ!!! ፲/አ እ/ር ዘመኑ አማረ 5ኛ ክ/ጦር ህ/ግ መምሪያ ኃላፊ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የሻለቃ ዝናቡ ልገረው የዕለቱ መልዕክት : "ለአንድነት አፋችን ብቻ ሳይሆን ልባችንም ክፍት መሆን አለበት። አንድ መሆን አማራጭ ሳይሆ አሰገዳጅ የወቅቱ ፖለቲካ ነው። የህዝባችንን እና የሰራዊታችንን
የሻለቃ ዝናቡ ልገረው የዕለቱ መልዕክት : "ለአንድነት አፋችን ብቻ ሳይሆን ልባችንም ክፍት መሆን አለበት።      አንድ መሆን አማራጭ ሳይሆ አሰገዳጅ የወቅቱ ፖለቲካ ነው። የህዝባችንን እና የሰራዊታችንን ተስፋ እና ምኞት እውን ማድረግ የሁሉም ፋኖ አመራር ታሪካዊ ግዴታ ነው። በሰፈር አታሞ እየተደለቀ አማራን ነፃ እናወጣለን ብለን ለህዝባችን ብቻ ሳይሆን ለራሳችንም አንዋሸው። እውነታው የመሪዎች እጅ የሰራዊት ችግር የለብንም። አንድ ድርጅት! አንድ መሪ! አንድ ሰራዊት! አንድ ህዝብ! አንድ ባንድራ ! አንድ አገር!! አርበኛ ዝናቡ ልንገረው ደለለ ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የወንዶች ቁና አርበኛ ዘመነ ካሴ ምድሪቱን በሙሉ በተወርዋሪ ጦር እየሞላት ነው። ይኼ ድምፃቸው ብቻ ጠላትን ያርዳል!! ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአርበኛና ደራሲ አሰግድ ጥቃት የኔም ጥቃት ነው! አርበኛና ደራሲ አሰግድ መኮነን ከልጅነት እስከ እውቀት ለአማራ ሕዝብ ሲታገል የኖረ ፀሐፊና አርበኛ ነው። በአማራነቱ ግን አፈና ተፈፅሞበት እስካሁን
የአርበኛና ደራሲ አሰግድ ጥቃት የኔም ጥቃት ነው! አርበኛና ደራሲ አሰግድ መኮነን ከልጅነት እስከ እውቀት ለአማራ ሕዝብ ሲታገል የኖረ ፀሐፊና አርበኛ ነው። በአማራነቱ ግን አፈና ተፈፅሞበት እስካሁን የት እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም። አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ተቋማት ዝምታችሁን እንድሰብሩ እንጠይቃለን። ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የኢንጂነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ለወራት ያስለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ መስከረም 12/01/2018 ዓ.ም የኢንጀነር ክበር ተመስገን ብርጌድ በኮማንዶ ሙያ ያስለጠናቸውን ኮማንዶ ሰልጣኖች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ  የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች፣ የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሃይማኖት አባቶች የተገኙ ሲሆን በሰልጣኞችም በርካታ ወታደራዊ ትርዒቶች ታይተዋል። በተጨማሪም የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አምሳ አለቃ ታየ ብርሃኑ ለተመራቂዎቹ የእንኳን አደረሳችሁ የድምፅ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልክታቸዉም የአዲሱ ትውልድ የትግሉ አብሪ ከዋከብቶች መካከል አንዱ የሆነው ሰማዕት ፋኖ ኢንጅነር ክበር ተመስገን የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበት የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ላለፉት ሁለት ዓመታት በተጀመረው የአማራ ተጋድሎ አኩሪ የጀግንነት ሥራዎችን በመስራት የክብር መስዕዋትነት የሆነበት ምድር ነው ካሉ በኋላ ደንበጫ የጀግኖች ምድር የአማራ የትግል ችቦ ተለኩሶ የሚቦገቦግበት የእነ ፋኖ ኢንጅነር ክበር ተመስገን ቀዬ ዛሬም እንደ ትናቱ የኢንጅነሩን ራዕይ እና ዓላማ አስቀጣይ አዳዲስና ተተተኪ ፋኖዎችን በማሰልጠን ለምርቃት ብቁ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል:: ድል ለአማራ ፋኖ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ 6ኛ ክፍለ ጦር ፋኖ ቃል አቀባይ ዘመን ባሳዝነው ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#ሰበር_ዜና‼️ የሰሜን ጎጃም ዞን የፓለቲካ ዘርፍ ም/ኃላፊ የሆነው ታከለ ሙሉጌታ የተባለን ካድሪ ቆንጆዎቹ (አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር) ከባህርዳር መሃል ከተማ ገብተው
+1
#ሰበር_ዜና‼️ የሰሜን ጎጃም ዞን የፓለቲካ ዘርፍ ም/ኃላፊ የሆነው ታከለ ሙሉጌታ የተባለን ካድሪ ቆንጆዎቹ (አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 1ኛ ክ/ጦር) ከባህርዳር መሃል ከተማ ገብተው አንቀው አውጠውታል💪 12/ዐ1/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ከአውደ ውጊያ ውሎ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል። መስከረም 12/ 2018 ዓ.ም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል(አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ክፍ ጦር በመቄት በግንባር የአብይ ወንበር አስጠባቂን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣት ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። በተለያዩ የመቄት ወረዳ ቀበሌዎች ከህዝብ ጋር ውይይት እያካሄደ ሲሆን መስከረም 12/ 2018 ዓ/ም ከ013 ቀበሌ /ደብረከርቤ/ ህዝብ ጋር ውይይት አድርጓል።በውይይቱም የአማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ የገጠመውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ ጥቃት እና የህልውና አደጋ አስመልክቶ የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ፋኖ መምህር በሪሁን ደምሌ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ገለፃውን ተከትሎ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። የፋኖ ትግል ህዝባዊ መሰረት ያለው ነው ሲል አርበኛ ሳሙኤል አያሌው/ቁንዳል/ ማሳያዎችን በማንሳት ግልፅ ማብራሪያ ሰጥቷል።የውይይቱ ተሳታፊዎችም የገጠመንን የህልውና አደጋ በነቃ የአማራዊ ስነ ልቦና በድል እንቋጨዋለን ሲሉ ገልፀዋል። በሌላ መረጃ አንድ የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው የሚሊሻ አባል ከጓዱ ጋር ጥራሪ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ። በሰሜን ወሎ ዞን አንጎት ወረዳ በሆነችው አውን ተገኝ ከተማ መስከረም 09/2018 ዓ.ም ሌሊት በነበረው አውደ ውጊያ የጠላት ሀይል በጥራሪ ክፍለ ጦርና በተከዜ ክፍለ ጦር መደቆሱን ተከትሎ ከሞት የተረፈው የጠላት ሀይል እየፈረሰ ወደ ተለያየ የፋኖ ክፍለ ጦሮች እየገባ ይገኛል። በዚህ መሰረት አንድ የመቶ አለቃ ማዕረግ ያለው የወረዳው ሚሊሻ ከአንድ ጓዱ ጋር ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ጥራሪ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል፣የክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮችም የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 12 / 2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ቤተ-አማራ ክፍለ ጦር  በደሴ ዙሪያ ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ድል ተቀናጁ፡፡ በቀን 11/01/2017 ዓ.ም እና በቀን 12/01/2018 ዓ.ም በደሴ እና በግሸን ዙሪያ ጠላት በከባድ መሳሪያ የታገዘ ዉጊያ ቢከፍትም የቤተ-አማራዎቹ ንስሮች ከፍተኛ ድል እየተቀናጁ ይገኛሉ:: አገዛዙ አመታዊ ግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል በፋኖ መከበር የለበትም በሚል እብሪት ከደሴ ከተማ ውስጥ ጀምሮ እስከ አምባሰልና ተለያየን ዙ23ን ጨምሮ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን እየተጠቀመ ቢሆንም በነበልባሎቹ ቤተ-አማራ ልጆች በአግባቡ እየተመከተ እና በመልሶ ማጥቃት በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ይዞታቸውን በማስከበር ድል እየተቀዳጁ ይገኛሉ:: ተጋድሎው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ንጋት ጀምሮ ጠላት ከኩታበር እና ደላንታ ያመጣውን ሃይል ይዞ ውጊያ ቢያደርግም ተለያየን ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ለማፈግፈግ ተገዷል:: ጠላት በደረሰበት ሽንፈት ምክንያት እየሸሸ ባለበት ሁኔታ ንስሮቹ እንዳይከተሉት ቢራ የጫነ ተሳቢ መኪና ጎማ በመምታት መንገድ ዘግቶ ውሏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 12/2018 ዓ.ም ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎