ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 613
مشترکین
+1324 ساعت
+4187 روز
+1 05630 روز
آرشیو پست ها
አሸበሪው የብልጽግና አገዛዝ ኔቶርክ በመዝጋት ማሕበረሰቡን እያሰቃየ ይገኛል።
ከቀን 29/06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋው ኔቶርክና ኢንተርኔት የደብረ ኤልያስ ወረዳ ማቻክል ወረዳ ፣ጎዛምን ወረዳ አዋበል ወረዳ፣ የስናን ወረዳዎችንና አካባቢውን በማካለል እስካሁን በጸረ ሕዝቡ የብልጽግና አገዛዝ ትዕዛዝ በመዝጋት ማሕበረሰቡን ለከፋ ማሕበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል።
እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ኔቶርኩን የዘጋው በቀጠናው ለሚያደርገው መጠነ ሰፊ ዘረፋና እገታ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ ወደ ፋኖ ቀጠና የወረራ እንቅስቃሴ ለመፈጸም መሆኑን ማወቅ ተችሏል።
ለምሳሌ፦ የጮቄን ሰንሰለታማ ተራሮችና ሌሎችንም ስትራቴጅክ ቦታዎችን ለመውረር ዕቅድ መያዙን ተሰምቷል።
ጥብቅ ጥንቃቄ ‼️
የአብይ አህመድ አገዛዙ በ64ኛ ክ/ጦር ቀጠና እነማይ እና ሸበል በርንታ ወረዳ የድሮን ቅኝት፣ መድፍ እና በረካታ መካናይዝድ ሀይል በማስገባት በቀጠናው የድሮን ጥቃት ኢላማ ለመሰንዘር እየተፋጨረጨር ይገኛል።
በክፍለ ጦራችን የምትገኙ አመራር፣ አባላት እንዲሁም ህዝባችን ሆይ አገዛዙ ከሚወረውራቸው የድሮንና የከባድ መሳሪያ ቅንቡላዎች እራሳቹህን እንትጠብቁ አደራ እንላለን።
"ኔትወርክ ከመጥፋቱ በፊት ቀድመን እንጠንቀቅ"
ከኢትዮ ቴሌኮም የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን በደረሰን መረጃ መሰረት አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየሰራ ያለውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የጠላት ኃይል በእነማይ ዲማ፣ ቅድስጌ፣ መንግስቶ የቀበሀና፣ አራጢ፣ ገዳያሱ፣ ቁጥቋጥ መሰል ቦታዎች ላይ በሌሊትና መሰል ሰዓታት እንቅስቃሴ በማድረግ በፋኖ ኃይሎች ላይ ከበባ፣ ደፈጣ፣ ቆረጣና መሰል የጥቃት ኢላማን በማቀድና የጥቃት ኢላማን ለመፈፀም የኔትወርክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መወሰኑን ማረጋገጥ ችለል።
የካቲት 30/2018 ዓ/ም
የኦርዲናስ አመራሩ 2/ሁለቱን/ ጥቁር ካላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀለ‼️
የካቲት 29/2018 ዓ/ም የኦርዲናስ አመራሩ ከጠላት ካፕ በመኮብለል 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር የፋኖ አባላትን በጀብድኝነት አቀባበል ተደርጎለታል።
መካሻ ሲሳይ የተባለው የ79 ክፍለ ጦር ኦርዲናንስ የነበረ ላሊበላ/ዲላሞ/ አካባቢ ከመሸገው የአብይ አህመድ የግል ሰራዊት 2/ ሁለት ጥቁር ክላሽ/፣ 200/ሁለት መት ጥይት/ እና ሁለት ቦንብ እስከነ ትጥቁ በመያዝ የ55ኛ ክ/ጦር አባላትን ተቀላቅሏል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ‼️‼️
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
+3
ጀግናን አለማወደስ ንፉግነት ነው !!!
የአማራ ህዝብ የካቲት 29/2018 ዓ.ም ትልቅ ደስታ የተጎናጸፈበት ቀን እንደሆነ ማንም ያውቃል። ስለዚህ ይህንን ዕለት ኃላፊነት ወስደው ሲሠሩ ለቆዩ ጀግኖቻችን ክብር ይስጥላቸው። እነዚህም ጀግኖች፦
1. ድርሳን ብርሃኔ – የአፋብን ልዩ ዘመቻ
2. ኢሳያስ ደመቀ – የአሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ
3. አማን እሸቱ – የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዘመቻ አዛዥ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት አርበኞች የአፋሕድ እና ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ተወካይ ኢሳያስ ደመቀ፣ የአፋሕድ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተወካይ አማን እሸቱ እና የወሎው ማርሽ ቀያሪ ድርሳን ብርሃኔ እነዚህ ሁለት ዕዞች ወደ አንድ እንዲመጡና ችግሮቻቸውን ፈትተው እንዲዋሐዱ ሰፊ ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል። ሸዋን አንድ እንድትሆን መሥዋዕትነት ከፍለው፣ ልዩነቶችን በንግግርና በሐሳብ በላቀ መንገድ ተነጋግረው በመፍታታቸው እና ላደረጉት አስተዋጽኦ በታሪክ ላይ ሊቀመጥ እንደሚገባ ሐሳቤን ማቅረብ እወዳለሁ።
ለረጅም ዓመት የቆየውን ልዩነት በጥበብ ፈትተው እዚህ ደረጃ ላይ ላደረሱት ጀግኖቻችን በሸዋ እና በአማራ ህዝብ ስም ክብር ይስጥላቸው።
እንደነዚህ ያሉ ጀግኖችን አለማወደስ ንፉግነት ነው።
አንድነት የአሸናፊነት ምልክት ነው !!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
+3
ጀግናን አለማወደስ ንፉግነት ነው !!!
የአማራ ህዝብ የካቲት 29/2018 ዓ.ም ትልቅ ደስታ የተጎናጸፈበት ቀን እንደሆነ ማንም ያውቃል። ስለዚህ ይህንን ዕለት ኃላፊነት ወስደው ሲሠሩ ለቆዩ ጀግኖቻችን ክብር ይስጥላቸው። እነዚህም ጀግኖች፦
1. ድርሳን ብርሃኔ – የአፋብን ልዩ ዘመቻ
2. ኢሳያስ ደመቀ – የአሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ
3. አማን እሸቱ – የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዘመቻ አዛዥ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት አርበኞች የአፋሕድ እና ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ተወካይ ኢሳያስ ደመቀ፣ የአፋሕድ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተወካይ አማን እሸቱ እና የወሎው ማርሽ ቀያሪ ድርሳን ብርሃኔ እነዚህ ሁለት ዕዞች ወደ አንድ እንዲመጡና ችግሮቻቸውን ፈትተው እንዲዋሐዱ ሰፊ ሥራ ሲሠሩ ቆይተዋል። ሸዋን አንድ እንድትሆን መሥዋዕትነት ከፍለው፣ ልዩነቶችን በንግግርና በሐሳብ በላቀ መንገድ ተነጋግረው በመፍታታቸው እና ላደረጉት አስተዋጽኦ በታሪክ ላይ ሊቀመጥ እንደሚገባ ሐሳቤን ማቅረብ እወዳለሁ።
ለረጅም ዓመት የቆየውን ልዩነት በጥበብ ፈትተው እዚህ ደረጃ ላይ ላደረሱት ጀግኖቻችን በሸዋ እና በአማራ ህዝብ ስም ክብር ይስጥላቸው።
እንደነዚህ ያሉ ጀግኖችን አለማወደስ ንፉግነት ነው።
አንድነት የአሸናፊነት ምልክት ነው !!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
ይህንን የፊስቡክ ገፅ ይወዳጁት አዲስ አዲስ መርጃዎችን ያገኙበታል!!
https://www.facebook.com/share/1DTthiPht9/
Repost from ETHIO ዋዜማ
ይህንን የፊስቡክ ገፅ ይወዳጁት አዲስ አዲስ መርጃዎችን ያገኙበታል!!
https://www.facebook.com/share/1DTthiPht9/
የጥዋት ዜና ይኖረናል ከአንድነቱ ማግስት ሸዋ መከር አገር ጠነቀር ሸር ሸር ሸር ሸር እመለስበታለሁ።
ሸዋ መከረ፤ ሸዋ አጸደቀ።
የሸዋ ዕንቁዎች አንድነታቸውን ካበሰሩ በኃላ ያካፈሉን ድንቅ መልዕክት እነሆ።
ያው እንግዲህ የካቲት 29/2016 የተባረከች ቀን፣ የተቀደሰች ቀን ለህዝባችን ለአማራ ህዝብ ኩራት ነው። ጠላት ደግሞ የሚሸማቀቅበት፣ አይኑ የሚቀላበት፣ ወገናችን ደግሞ የሚደሰትበት፣ የሚስቅበት ቀን በመሆኑ እንደ አማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ሃሳቤን እገልጣለሁ ማለት ነው። እንግዲህ ለተከታታይ ቀናት ሸዋ ቤቱን ዘግቶ ሲመክር፣ ሲነጋገር ቆይቷል ማለት ነው።
አያቶቻችን እቴጌ ጣይቱ እና ዳግማዊ ምኒልክ እንዲሁም ለብዙ ዘመናት ሀገርን ሲያስተዳድሩ፣ ህዝብን ሲመሩ ያለ ልዩነት በአንድነት ያስመሰከሩበት፣ ትልቅነትን ያሳዩበት፣ ለልጆቻቸው ብዙ ነገር ያስተማሩበት... እኛ ልጆች ደግሞ ከነሱ ተምረን የነበረንን ልዩነት፣ የነበረንን መገፋት ለአጠቃላይ ለአማራ ህዝብ አሁንም በአንድነት የሚታገልበትን፣ ልዩነታችንን፣ የነበረብንን መገፋት እና በተንኮለኞች፣ በሴረኞች የተበተበብንን ትብትብ ዛሬ ቀብረናል ማለት ነው።
ዛሬ ይሄንን ታሪካዊ ቀን ለህዝባችን የምናስደስትበት እና መላው የአማራ ህዝብ ደስታውን ተቀብሎ እኛ እንደተቃቀፍነውና እኛ እንደተመካከርነው ሌሎችም በውጭም በውስጥም ትግላችንን የሚደግፉ፣ ትግላችንን ለማሻገር ሌተቀን የሚለፉ ወንድሞቻችን ይሄንን ደስታ ተቀብለው ትግላችንንም በጋራ እንድንሻገር፣ የአማራን ህዝብ መከራ ከላው ላይ እንድናነሳለት የሚል አጭር መልዕክት ነው የማስተላልፈው።
አመሰግናለሁ።
አርበኛ መከታው ማሞ
የአፋብን ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሰብሳቢ
እንግዲህ ይቺ የተባረከች እና የተቀደሰች ቀን እንድትመጣ በአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ እና በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል ደቡብ አማራ ቀጣና ሳምነው ዕዝ መካከል የነበረውን ያለመግባባት ወደ አንድ ለማምጣት ከመጀመሪያ ጀምሮ ስትደክሙ፣ ስትወጡ፣ ስትወርዱ፣ ቀን በሃሳብ ሌሊት እንቅልፋችሁን አጥታችሁ የነበራችሁ በውጪውም አለም በሀገር ውስጥም የትግል ደጋፊዎች እና ባለቤቶች መጀመሪያ እናመሰግናለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።
ከዚህ በመቀጠል መላው ህዝባችን... መላው ህዝባችን በአንድም በሌላ ከስህተታችን ባለመማር፣ ከአንድ አምራች የወጡ ልጆች እውነት ለመናገር ለአንድ አላማ የተሰለፉ ልጆችን ጎራና ጎራ ለይተው ጥይት ሲወራወሩ በመቆየታቸው፣ እኛም የትግሉ አብዮት ወይም የትግሉ ፊት አውራሪዎች መሪዎች በነበርንበት ሰዓት ይሄ ችግር መፈጠሩ እና በወቅቱ ቶሎ ብዙ ችግር ሳይፈጠር ባለመመለሳችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን። በአራቱም ግዛት ያላችሁ የትግሉ መሪዎች፣ በትግሉ ፊት አውራሪነት የተቀመጣችሁ የትግሉ ባለቤቶች ይሄ ሰላም እንዲመጣ፣ ይሄ አንድነት እንዲመጣ ስትወጡ ስትደክሙ የነበራችሁ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ፤ ለእናንተም ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ከዚህ በኋላ ሸዋ ምድር ላይ እርስ በርስ የሚታኮስ፣ እርስ በርስ የሚጓተት ወንድማማች አይኖርም። ተፈጥሯል፤ የተፈጠረውን ችግር መመለስ አንችልም፤ ድጋሚ እንዳይፈጠር ትናንትና ለአንድ አላማ የወጡ ልጆች የትም በኛ ስህተት ዋጋ በመክፈላቸው እጅግ ልባችን እያዘነ፣ በቁጭት እና በስሜት የተሻለ ስራ ሰርተን፣ የተሻለ አቀራርበን እና አዋህደን ሰራዊታችንን የሸዋን መሬት ለብልግና እሳት እናደርገዋለን። ለዚህም ከጎናችን የተሰለፍከው የማትሰለቸው፣ የማትደክመው እና ተስፋ የማትቆርጠው ህዝባችን አሁንም ከጎናችን ሆነህ ጠላትን እየመታን፣ እያንበረከክን እና እያሸነፍን ጉዞአችንን ወደፊት እንድናደርግ ታሪካዊ ጥሪ እናስተላልፋለን።
እናመሰግናለን።
አርበኛ ደሳለኝ
የአሳምነው ዕዝ ሰብሳቢ
በዚህ በተባረከ ሁላችንም በመገኘታችን ደስታችን ደስታ እጥፍ ድርብ ነው። በቅድሚያ አንድነት ምንም ምርጫ የሌለው ጉዳይ ነው። የማሸነፊያችን ቁልፍ እንደሆነ ይታወቃል፤ ያንን መሰረት በማድረግ አንድነታችንን በዛሬው እለት አጽንተናል። በቅድሚያ ግን ይሄንን አንድነት ለማየት ሲጓጉ የነበሩ፣ እንደጓጉ ህይወታቸው ያለፈ ጀግና ሰማዕቶቻችንን ማሰብ መቻል አለብን። የነሱን ራዕይ፣ የነሱን አላማ እናስቀጥላለን ብለን በገባነው ቃል መሰረት ይኸው ዛሬ አንድነታችንን መስርተን ከዚህ በፊት የነበሩ በርካታ መጓተቶችን ወደ ኋላ ጥለን ዛሬ ላይ አንድ ሆነን ለሚደግፈንና ለሚጠብቀን ህዝብ፣ ለሰራዊታችንም ጭምር ይህንን ደስታ ማብሰር እንፈልጋለን።
በዋናነት ግን ከዚህ በፊት የነበሩ የግጭት ጠባቂዎች በር ዛሬ ላይ ተዘግቷል። የአንድነት በር ተከፍቷል። አንድነታችንን መቼም ቢሆን ከዚህ በኋላ ወደኋላ ሊመልሰው የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን በዚሁ ለሰራዊታችን፣ ለደጋፊው፣ ለህዝባችን በዚሁ መልዕክቴ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ። አጠቃላይ የአፋብን አመራሮች እንዲሁም መላው የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ሰራዊት በኛ አንድነት እንደምትደሰቱ ተስፋ እናደርጋለን። ሁሉም አንድ ሆኖ ወደፊት የምንገፋበት እና ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ የመጨረሻ ምርጫችን አንድ ሆነን ይሄንን የተጋረጠብንን አደጋ፣ ጠላትን በጋራ ታግለን የጋራ ውጤት የምናመጣበት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ነንና ሁላችንም አንድ እንድንሆን... ከዚህ በኋላ ሊለያየን የሚችል አንዳችም ምድራዊ ሃይል የለም።
አመሰግናለሁ።
አርበኛ አበበ ሙላት
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ህዝብ ግንኙነት
ይህ የሸዋ ሁለት ወንድማማቾች ልዩነት ሲያስጨንቃቸው የነበራችሁ መላው የአማራ ህዝብና የሸዋ ህዝብ ብሎም የትግሉ ደጋፊዎች እንግዲህ የምትፈልጉት፣ የምትናፍቁት አንድነት መጥቷል እና እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን ማለት እፈልጋለሁ።
በመቀጠል እንግዲህ ይህ አንድነት ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን የሚችል ነው፤ ለአማራ ህዝብ ቀርቶ ለሌሎች ጭቁን ማህበረሰቦች (“ብሄር ብሄረሰቦች”) ጭምር ምሳሌ ሊሆን የሚችል፣ የአሸናፊነታችን ማረጋገጫ፣ እውነትም አንድነቱ የእውነት እየፀና፣ ቀጣይ አንዱ ትብስ አንዳችን ትብስ እየተባለ የምንቀጥልበት፣ የምንከባበርበት፣ ህዝባችንን ከፍ የምናደርግበት፣ መሪዎቻችንን የምናከብርበት እና የማሸነፊያ ቁልፋችን ሆኖ ይቀጥላል። ቀጣይ እንግዲህ ቅድም መሪዎቻችንም እንደገለጹት ህዝባችን ከጎናችን እንዲሆን፣ ደጋፊ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲሆን እና በተሻለ ፍጥነት፣ በተሻለ የትግል ስልት አሸናፊነታችንን እንድናደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ይህ ሆኖ በማየቴ በግሌም እጅግ በጣም ደስታ ተሰምቶኛል። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።
አመሰግናለሁ።
አርበኛ አከበር አስማማው
የአሳምነው እዝ ፋይናንስ ሃላፊ
+1
የኤፍራታው ፀሐይ፡ ኢሳያስ ደመቀ
የኤፍራታ ሰማይ በንጋት ጮራ መቅላት ሲጀምር፣ ተራሮቹ የጥንት የአባቶቻቸውን ምስጢር የሚያወጉ ይመስላሉ። በነዚህ ገደላገደሎችና ቁልቁለቶች መካከል ነው ወጣት የተገኘው።
ኢሳያስ ደመቀ። ኢሳያስ የኤፍራታ ልጅ ብቻ አይደለም፤ እርሱ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የጽናት ወራሽ፣ የዳግማዊ ምኒልክ የጥበብና የአንድነት መንፈስ በደሙ ውስጥ የሚመላለስ የዘመኑ ጀግና ነው። አየሩ ብርዱን ቢለቅበት፣ ፀሐዩ ቆዳውን ቢያቃጥለውም፣ ለኢሳያስ ግን የሀገር ፍቅር ትኩሳት ከሁሉም በላይ ይበረታበታል።
የአማራ ቤት መገንባት ያለበት በልዩነት አሸዋ ላይ ሳይሆን፣ በአንድነት አለት ላይ ነው የሚለው ቃሉ በሸዋ ተራሮች ላይ ያስተጋባል። እርሱ ለአማራ ምሁራን ብዛትና ለታሪኩ ክብር ሲል፣ የግል ምቾቱን ለገደሉና ለሸለቆው አሳልፎ ሰጥቷል።
በዙሪያው ያሉት ጓደኞቹና ተከታዮቹ ሲመለከቱት፣ በእርሱ ውስጥ የሚታየው ተራ የጀግንነት ስሜት አይደለም። ይልቁንም እንደ ተራራው የጸና አቋም እንደ ሸለቆው ጥልቅ የሆነ ራእይ እንደ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ያለ ክብር ይታይበታል።
ዛሬ ላይ ቆመን ስለ አንድነት ዋዜማ እንድንዘምር ስለ መጪው ብሩህ ቀን እንድንሰማ ያደረገን የዚህ ወጣት መስዋዕትነት ነው። ኢሳያስ የጥላቻን ግንብ አፍርሶ የአንድነትን ድልድይ ለመሥራት ብርዱንና ፀሐዩን የታገሰ የኤፍራታ ኮከብ ነው። ጀግንነት የግሉ የሆነች፣ የአንድነት አርበኛ! እያሉ አዛውንቶቹ በምርቃት ወጣቶቹ በዝማሬ ስሙን ያነሱታል።
በእርግጥም ኢሳያስ ደመቀ የታሪክ አደራን የተሸከመ፣ የነገውን ተስፋ የሰነቀ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። Dawit Amhara
ሁሌም አዲስ መረጃ እንዲደርሳችሁ ቴሌግራም ፒጃችን ይወዳጁን
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የኤፍራታው ፀሐይ፡ ኢሳያስ ደመቀ
የኤፍራታ ሰማይ በንጋት ጮራ መቅላት ሲጀምር፣ ተራሮቹ የጥንት የአባቶቻቸውን ምስጢር የሚያወጉ ይመስላሉ። በነዚህ ገደላገደሎችና ቁልቁለቶች መካከል ነው ወጣት የተገኘው።
ኢሳያስ ደመቀ። ኢሳያስ የኤፍራታ ልጅ ብቻ አይደለም፤ እርሱ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የጽናት ወራሽ፣ የዳግማዊ ምኒልክ የጥበብና የአንድነት መንፈስ በደሙ ውስጥ የሚመላለስ የዘመኑ ጀግና ነው። አየሩ ብርዱን ቢለቅበት፣ ፀሐዩ ቆዳውን ቢያቃጥለውም፣ ለኢሳያስ ግን የሀገር ፍቅር ትኩሳት ከሁሉም በላይ ይበረታበታል።
የአማራ ቤት መገንባት ያለበት በልዩነት አሸዋ ላይ ሳይሆን፣ በአንድነት አለት ላይ ነው የሚለው ቃሉ በሸዋ ተራሮች ላይ ያስተጋባል። እርሱ ለአማራ ምሁራን ብዛትና ለታሪኩ ክብር ሲል፣ የግል ምቾቱን ለገደሉና ለሸለቆው አሳልፎ ሰጥቷል።
በዙሪያው ያሉት ጓደኞቹና ተከታዮቹ ሲመለከቱት፣ በእርሱ ውስጥ የሚታየው ተራ የጀግንነት ስሜት አይደለም። ይልቁንም እንደ ተራራው የጸና አቋም እንደ ሸለቆው ጥልቅ የሆነ ራእይ እንደ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ያለ ክብር ይታይበታል።
ዛሬ ላይ ቆመን ስለ አንድነት ዋዜማ እንድንዘምር ስለ መጪው ብሩህ ቀን እንድንሰማ ያደረገን የዚህ ወጣት መስዋዕትነት ነው። ኢሳያስ የጥላቻን ግንብ አፍርሶ የአንድነትን ድልድይ ለመሥራት ብርዱንና ፀሐዩን የታገሰ የኤፍራታ ኮከብ ነው። ጀግንነት የግሉ የሆነች፣ የአንድነት አርበኛ! እያሉ አዛውንቶቹ በምርቃት ወጣቶቹ በዝማሬ ስሙን ያነሱታል።
በእርግጥም ኢሳያስ ደመቀ የታሪክ አደራን የተሸከመ፣ የነገውን ተስፋ የሰነቀ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።
እጅግ የሚያኮራ፣ ከንጉሶች መንደር፣
ከእነ ምኒልክ አውድማ፣ ከታላቁ ሀገር።
ከእነ ደሱ ምድር፣ መዝ ብለህ ላከኝ፣
በእነ መከታው ሰፈር፣ አብራርተህ ንገረኝ።
ፀሐይ በአማራ አድማስ ላይ ስትፈነጥቅ፣ የአፋብን ምድር በተለመደው የዝምታ ድባብ ውስጥ አልነበረችም። ይልቁንም፣ ከሩቅ የሚሰማው የእልልታና የከበሮ ድምፅ፣ የምድሪቱን ጋራና ሸለቆ እያናወጠው ነበር። ሰማዩ በአቧራና በጭስ ሳይሆን፣ በሺዎች በሚቆጠሩ የቆራጥ ልቦች ትንፋሽ የታፈነ ይመስላል።
(201ኛው) ኮር ሰራዊት፣ እንደ ንጉሡ እንደ ቴዎድሮስ ሁሉ “ሞት ይሻላል” የሚል ጽኑ ቃል በልባቸው አንግበው፣ ለታላቁ ግዳጅ ተሰልፈዋል። ይህ ስብስብ ሰራዊት ብቻ አልነበረም፤ ከጠለቀው የህዝብ ማህፀን የወጣ፣ ለማመን የሚከብድ የሰው ማዕበል እንጂ።
ከአፋብን ጎዳናዎች እስከ ቀጠናው ዳርቻ ድረስ፣ ጀግናው የአማራ ህዝብ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ ነው። አዛውንቶቹ በምርኩዛቸው መሬቱን እየነኩ “አማራ የጀመረውን ሳይጨርስ አያርፍም!” እያሉ ይገዝታሉ።
ወጣቱ በኩራት ደረቱን ነፍቶ፣ እናቶች ደግሞ በዝማሬ ልጆቻቸውን ለድል ይሸኛሉ። የታየው ትዕይንት ለታሪክ ጸሐፊዎች ብዕር የሚከብድ የሚመስል። አፋብን ዛሬ የጀግኖች መፈልፈያ ብቻ ሳትሆን፣ የፋኖ አባላቶቹ የብረት ጋሻቸውንና ወኔያቸውን ሰንቀው ወደፊት ሲገሰግሱ፣ ከኋላቸው ያለው ህዝባዊ ማዕበል የመከታ ምሰሶ ሆኖላቸዋል።
ታሪክ ዛሬም በደማቅ ቀለም እየተጻፈች ነው።
አማራ አንድ ጊዜ ቆርጦ ተነስቷል፤ የጀመረውን ትግል በድል ሳይቋጭ ወደኋላ እንደማይመለስ ደግሞ የአፋብን የውጊያ ተራራዎች ምስክሮች ናቸው።
ሰበር ዜና አጣዬ
የአሳምነው አናብስቶች ዛሬ በወሰዱት እርምጃ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል ሰፈር ውጥረት ተባብሶ ቀጥሏል!!
በታሪካዊቷ የአጣዬ ምድርና በኤፍራታ ግድም ወረዳዎች በዙሪያው በአሉት አካባቤዎች ዛሬ ረፋዱን ልዩና አስገራሚ ወታደራዊ ክስተት የአሳምነው አናብስቶች በወሰዱት መብረቃዊ እርምጃ፣ በአካባቢው የነበረው የአብይ አህመድ ኃይል ወታደራዊ መዋቅር ከፍተኛ መናወጥ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል።
ሆኖም የአብይ አህመድ አገዛዝ ጥምር ጦር ብሎ የሚመራው ኃይል ሚኒሻ፣ ፖሊስ እና አድማ መከላከያ ከላይ የመጣ ጥብቅ መመሪያ ነው በሚል ሰበብ ወደ አስገዳጅ ግዳጅ እንዲሰማሩ መደረጋቸው በሰራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
ይህን ተከትሎ በታችኛው አመራርና በደረጃው ባሉ የጸጥታ አባላት መካከል እርስ በእርስ የመነካከስ እና የትዕዛዝ ያለመቀበል ቅጭት ተፈጥሯል። በአጣዬ፣ በርግቤ እና ፈርድውሃ አካባቢዎች፣ የወንበር አስጠባቂው ኃይል የአሳምነው አናብስቶችን የክንድ ብርታት መቋቋም ተስኖታል። በተለይም በሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የአሳምነው አናብስቶች መቋቋም ባለመቻላቸው፣ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ድንጋጤና በውስጥ ሽኩቻ ውስጥ እንደሚገኙ ከስፍራው ፍኖተ አማራ ሚዲያ ምንጮችን አጋርታናለች።
+1
ሰበር የድል ዜና!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦር ድልን ተቀዳጀ።
የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ደመላሽ ሻለቃ በኤፍራታና ግድም ወረዳ ፈረዶ ውሀ ቀበሌእና ካራለጎማ ቀበሌ ተረተር በሚባለው ቦታ ላይ ከሌሊቱ 10: 00 ሰዓት ላይ ተስበው በመግባት ዛሬም እንደ ትላንቱ በቁጥር አንድ (1) ስናይፐርን፣ ሁለት(2) ጥርጥር ክላሽ እና የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቆች መማረክ ችለዋል ።
እንዲሁም የሰባት ለሰባ ክፍለጦር ስበር ሻለቃ በላይኛው ሰራንባ የሰርዶ ቀበሌ በቴሌው ጋር በመግባት ከጠዋቱ 12: 00 ሰዓት ጀምሮ የአብይ አህመድን ወንበር አስጠባቂ መከላከያ እና የብዓዴን ቅጥረኛ ሚሊሻ ሲደቁሱት አርፍደዋል።
በአውደውጊያውም የአሳምነው አናብስቶች እንደ ንስር ተወርውረው በመግባት በርካታ የአብይ አህመድ ሰራዊት በዬ ሸጡ ተዝረክርኮ እንዲቀር አድርገውታል። ሆኖም የአብይ አህመድ አገዛዝ በቁጥር የማይገለፁ ቁስለኞችንም ወደ አጣዬ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ !!
የካቲት 29/06/2018 ዓ.ም
