fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 130
مشترکین
-824 ساعت
+887 روز
+1 19430 روز
آرشیو پست ها
የድል ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለበሰባ ክፍለ ጦር ቃኘዎች በአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ መከላከያ እና ሚኒሻ ባንዳ የእናት ጡት ቆራጩ አረመኔያዊ ኃይል ማታ በዛሬው ዕለት ጥቃት በማድረግ ድልን ተጎናጽፈዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌት ተቀን እየሰራ ያለው የብልፅግናው አሽከር የመደመር ፍልስፍና ባለቤት ተብየው አብይ አህመድ አሊ አማራን ከምድር ገፅ ለማጥፋት በአደራጀው ኃይል ዛሬ ማታ 4:00 ላይ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ቃኘዎች በኤፍራታ ግድም ወርዳ ፈረዶሀ ቀበሌ መሽጎ የነበረውን ባንዳ ሚሊሻ እና የአብይ አህመድ ጡት ቆራጭ መከላከያ ላይ መብረቃዊ ጥቃት በፈፀሙት አውደ ወጊያ 1 , መስፍን እሸቱ ሌመን ቀበሌ 2 , ተረፈ ገብሬ ፈረድዉሀ ቀበሌ 3 , ቻለዉ ዘነበ ፈረድዉሀ ቀበሌ 4 , አጥላዉ እሸቴ አላላ ቀበሌ 5 ,በድሉ አላላ ቀበሌ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻ ላይ ከባድ ቁስለኛ በማድርግ የአማራን የመኖር ነፃነት በነበልባ ክንዳቸው ባሌትነታቸውን አረጋግጠዋል። እንደሚታወቀው አብይ አህመድና የስርዓቱ አስፈፃሚ ብአዴን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል የአሳምነው አናብስቶችን አይተኪ ክንዳቸውን መቋቋም ሲያቅተው ንፁሃን በማፈን ሴት እናቶቻችን በመድፈር በከተማና በገጠር የሚኖሩ ማህበረሰብ በአስገዳጅ ሁኔታ እያሰቃየ አማራ የሚባል ትውልድ በአማራ ግዛትና እና በመለው ኢትዮጵያ እንዳይኖር በተላያዩ የሚዲያ አውታሮች በአሰማራቸው ጀሌዎች ከትላንትናው ዛሬ ላይ አድማሳቸውን አስፍተው የጥላቻቸወን ጥግ እያሳዩን ይገኛሉ። ሁኖም ይህን የምተ አረመኔያዊ ስርዓት እኛ የአማራ ፋኖዎች አባቶቻችን በአወረሱን የትግል ስልትና ጥበብ  አንድየ ነፍሳችን ለአማራ ነፃነት  በተለያዩ የአውደ ዉጊያ ቦታዎች እየመከትንና እየተፋለምን የበላይነት እየወሰድን እንገኛለን። በመጨረሻም ከትናንት ዛሬን በአንድነት አበክርን በመስራት ይህን የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሚኒሻና የብልሃኑ ጁላ የሴት ልጅ ጡት ቆራጩን መከላከያ ኃይል በሰፋራችን በተወለድንባት ቦታ መጦ ደፍሮናልና  በገባበት ገብተን የመኖር ነፃነት በቅርቡ ለመላው አማራ የምናበስር ይሆናል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው ታህሳስ 17/04/2018 ዓ.ም

ሰሞኑን ወለጋ ምድር ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ  ሻሾበር ከተማ ገዳ ኮማንዶ የተባለው ጨፍጫፊ ሰራዊት በመከላከያና ሚኒሻ ታጅቦ ከገባ በኋላ ከ130 በላይ ወገኖቻችንን በማገት ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ይወስዳቸዋል ከታጋቾችም መካከል ነፍሰ ጡር፣ህጻናትና ሽማግሌዎች በብዛት ይገኙበታል ይህንንም ተከትሎ አካባቢውን  የተቆጣጠረ የመሰለው ገዳ ኮማንዶ አማራውን በነጻነት ለመጨፍጨፍ ይመቸው ዘንድ መከላከያ አካባቢውን ለቆ ይውጣልኝ ሲል ለበላይ አመራሮቹ አመልክቶ አመሻሹን መከላከያ ጓዙን ጠቅሎ ወደ ቱሉ ጋና ከተማ ወጣ። ይህንም ተከትሎ የከተማው የአማራ ማህበረሰብ ከተማውን ለቆ ሸሸ በአገዛዙ ከፍተኛ እምነት የተጣለበት የገዳው ምልምል ኮማንዶም በለሊቱ የአማራውን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ እዬተዘጋጀ ባለበት ስዓት የወገን ሀይል በተቀናጀ መልኩ በጧቱ ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት በስዓታት ውስጥ አራት ምሽጎችን በመስበር የተረፉትን ወደ አንድ አቅጣጫ በመሰብሰብ እያጠቃ በነበረበት ስዓት ጫጫታው ተበራከት ያ በሀይል ውጣ ተብሎ የነበረው መከላከያ ወደ ቦታው እንዲገባና ከሞት የተረፉትን እንዲታደጋቸው ጥሪ አቀረቡ በዝህም መከላከያ በዙ 23 ሽፋን መከላከያ ወደ ቀጠናው መግባቱን ተከትሎ የወገን ሀይል ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ተደረገ። በመከላከያ ሽፋን የተረፈው ልዩ ሀይል ከተማው ላይ የወገኖቻችንን ቤት ምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ ማቃጠል ሀብት ንብረቱን ወደ ጊዳ አያና መጫኑን በመከላከያ ሽፋን ቤታቸውን ዘግተው ያልወጡ እናቶችንና ህጻናትን በነጻነት አረዱ የአካባቢው ማህበረሰብም መከላከያው ይውጣልን እኛ እራሳችንን እንከላከላለን ብለው ቢማጸኑም ሰሚ ጠፋ። ከ10 ያላነሱ ወገኖቻችንም ቤታቸው በር ላይ በገዳ ኮማንዶ በመከላከያ ሽፋን ታረዱ ዛሬም ይህኑ ተግባራቸውን ለመፈጸም በመከላከያ ታዝለው ወደ ዋጃ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር የአይን እማኞች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል።

ሰበር ዜና! ቡሬ ወረዳ ቁጭ ከተማ ላይ ስብሰባ ለማድረግ ታጅቦ የመጣው የብልፅግና አመራር በ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር ብት*ን*ት*ኑ ወጥቷል። ፋኖ ይችላል👊✊
ሰበር ዜና! ቡሬ ወረዳ ቁጭ ከተማ ላይ ስብሰባ ለማድረግ ታጅቦ የመጣው የብልፅግና አመራር በ109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር ብት*ን*ት*ኑ ወጥቷል። ፋኖ ይችላል👊✊

ለ አማራ ሕዝብ የሚጨነቅ አሚመስለዉ በድኑ ብአዴን ...የአማራን ሕዝብ 26billon ዘርፎታል.... ..
+6
ለ አማራ ሕዝብ የሚጨነቅ አሚመስለዉ በድኑ ብአዴን ...የአማራን ሕዝብ 26billon ዘርፎታል.... ..

በትናትናው ዕለት ከቀኑ 6 ሰአት የእናት ጡት ቆራጭ የዲፖ ማከማቻው የዞን ከተማ ከሆነችው ፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 የደሮው ገቢያ አካባቢ ላይ ወጣት ታመነ ዓለሙ የአሰልጣኝ ኮማንዶ ይታይህ ዓለሙ
+1
በትናትናው ዕለት ከቀኑ 6 ሰአት የእናት ጡት ቆራጭ የዲፖ ማከማቻው የዞን ከተማ ከሆነችው ፍኖተ ሰላም ከተማ ቀበሌ 02  የደሮው ገቢያ አካባቢ ላይ  ወጣት ታመነ  ዓለሙ የአሰልጣኝ ኮማንዶ ይታይህ ዓለሙ ታናሽ ወድም እንዳለ የተባለውን አጥቦ አይለብስ ባንዳ የሚኒሻ አመራሩን በጂንፎ ሽመል አናቱን  በመምታት  መሳሪያውን ማርኮ ወደ ቆንጆወቹ ተቀላቅሏል፡፡ አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!

#ብልፅግና_የሚያደርገው_የሽብር_ተግባር‼ ዛሬ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 #ከቲሊሊ ከተማ አቅራቢያ አዲስ አለም ቀበሌ ላይ አበባው አንዷለም የተባለ ባለ ባጃጅ በጠዋቱ ተነስቶ ተራ ለ
+2
#ብልፅግና_የሚያደርገው_የሽብር_ተግባር‼ ዛሬ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12:00 #ከቲሊሊ ከተማ  አቅራቢያ አዲስ አለም ቀበሌ ላይ አበባው አንዷለም የተባለ ባለ ባጃጅ በጠዋቱ ተነስቶ ተራ ለመያዝ ደፋ ቀና እያለ ባለበት ንጋት አሸባሪው ቡድን ባጃጁን በማስቆም ልጁን ረሽነዉ ባጃጁንም አቃጥለዉበታል። ምንታገለው ላለመጥፋትነው።ሰርተን እንዳኖር፣ወጠን እንዳንገባ ስለተከለከልነ ነው።

የአረመኔው ሰራዊት የ3 አመት ህፃን አግቷል ። የፋኖ ልጅ ነህ በሚል ህፃን ሰለሞን በቀለን ቋሪት ወረዳ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ታውቋል። በዚች ሃገር በሰላም ለመኖር ፣ ሰርተህ ለመለወጥ ፣ ፍትህ
የአረመኔው ሰራዊት የ3 አመት ህፃን አግቷል ። የፋኖ ልጅ ነህ በሚል ህፃን ሰለሞን በቀለን ቋሪት ወረዳ ላይ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ታውቋል። በዚች ሃገር በሰላም ለመኖር ፣ ሰርተህ ለመለወጥ ፣ ፍትህ ለማግኘት መፍተሔ የሚሆነው የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል ፈለግን መከተል ነው ። አሸባሪው ማን እንደሆነ ሰፊው ህዝብ ይፈርደናል ። 17/04/2018 ዓ/ም

#ጥብቅ_ጥንቃቄ‼️ በሰሜን ሽዋ # ዛሬ በደብር ብርሃን በሁሉም የሰሜን ሽዋ ወርዳዎች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እንዲሁም #ኤፍራታ ግድም ወረዳ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ #የድሮን_ቅኝት ተካሂዷል። መረጃውን ሸር በማድረግ ለፋኖ አመራር እና አባላት እንዲሁም ህዝባችን ጥብቅ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። 17/ዐ4/2018 ዓ.ም

#እጅ_አንሰጥም‼️ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን እጅ እናሰጣለን እንጂ እጅ አንሰጥም💪 አርበኛ ያለው አዱኛ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ አዛዥ በወቅታዊ ጉዳይ ያስተላለፈው መልዕክት‼️ 16/ዐ4/2018 ዓ.ም

#inbox በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የአማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት እየፈፀሙብን ነው  ከለምንም ምክንያት ከግቢው ውስጥ ለምን መንገድ አትለቅም፣ለምን ታየኛለህ በሚል ተልካሻ ምክንያት በጣም ብዙ ተማሪዎች ተደብድበናል የስነ ልቦና ጫናም እየደረሰብን ነው። መፍትሔ ባይገኝም ለህዝብ አየር ላይ ብታውሉልን?

#አብዮቱ አማራን ከፀረ አማራ ሀይሎች ጥቃት ይጠብቃል!!!    ታህሳስ  13/2018 ዓ/ም  አዲስ ቅዳም ከተማ ላይ ጠርቶት በነበረዉ ፀረ አማራነት  ስብሰባ በታላቁ ነፃነት ወዳድ ህዝባችን እንቢተኝነት እና የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክ/ጦር በሰራችዉ ልዩ ኦፕሬሽን ጉዳትን በማስተናገድ ከፍ ያለ ዉርደትን ተከናንቦ ወደ መጣበት የፈረጠጠዉ ፀረ አማራዉ የብልፅግና ስብስብ አዲስ ቅዳም ከተማ በሚገኘዉ ህዝባችን ላይ የበቀል ተግባር መፈፀም ጀምሯል። በዚህም  መሰረት ከሁለት ቀን በፊት ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ተጠራርቶ በነጭ ልብስ እየተጀቦነ  የተሰባሰበዉን  ደም መጣጭ የካድሬ ጥርቅም  በአለም አደባባይ አዋርዶ የሸኘዉን ነፃነት ወዳድ የአዲስ ቅዳም ከተማ  ሕዝብ ከፋኖ ትግል ጋር የሚያገናኝ የተለያዩ ታፔላዎችን እየለጠፈ  መደብደብ ፣ ማንገላታት ፣ማዋከብ መጀመሩን እና  ዛሬ ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ብቻ ከ80 በላይ የሚሆኑ ወገኖቻችንን  ወደ ማጎሪያ ቦታ መዉሰዱን ማረጋገጥ ችለናል። አብዬቱ አማራን ከፀረ አማራ ሀይሎች ጥቃት ይጠብቃል!!! አንድ አማራ! ዝንተዓለም አማራ! አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ🙏 ታህሳስ 16/2018 ዓ/ም

የልጅ እያሱ ኮር አሃዶች በጥምረት አምባሰል ላይ በበርካታ ግንባሮች ባደረጉት ተጋድሎ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: ልጅ እያሱ ኮር በሁሉም የአምባሰል አካባቢዎች በበርካታ ግንባር የብልፅግናዉ አራዊት ሰራዊት የፋኖን ይዞታዎች እቆጣጠራለሁ በሚል ቅዥት የማጥቃት እንቅስቃሴ እያደረገ ያለ ሲሆን በልጅ እያሱ ኮር ስር የሚገኙት ክፍለ ጦሮች ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ አድርገው በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ወደመጣበት መልሰው ድል አስመዝግበዋል:: ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክ/ጦር ከጊሸን ወደ ደልባ እና ጅጎዶ ለመቀሳቀስና ለመቆጣጠር አስቦ የማጥቃት ውጊያ ቢከፍትም በመከላከል ብሎም መልሶ ማጥቃት በማድረግ ድባቅ መተዉ ወደ መጣበት እንድመለስ አድርገዉታል። በሌላኛው ግንባር መነሻዉን ከውጫሌ ከተማና ከማርየ ያደረገ ጠላት ያለ ያለለ ሃይሉን ተጠቅሞ ወደ ድብል በምድር በመካናይዝድ ታንክና መድፍ ታግዞ በሰማይ በአየር ሃይል ድሮን ታግዞ ማጥቃት ቢያደርግም በ24ኛ ክፍለ ጦር ድብል ላይ እየተመታ ይገኛል:: እንድሁም በትናትናዉ ዕለት ማለትም ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የልጅ እያሱ ኮር የኮር ቃኝ በወርጊሳ ከተማ ደፈጣ በመጣል ከመርሳ ወደ ዉጫሌ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን እያጓጓዘ ባለበት በደፈጣ ዉጊያ የአገዛዙን ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻዉ ድልና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበር ክንዳችን! አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፩ኛ ኮር ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ታሕሣሥ 16/2018ዓ.ም ✔️ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር  እና የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች በጋራ  መቀመጫውን ግንዳ ጠመም ከተማ አድርጎ የነበረው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሻውን ግንዳ ጠመም በማድረግ ወደ ማሕደረ ማርያም ከተማ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ሠዓት የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር መተሬ ወንዝ በወሰደው የደፈጣ መብረቃዊ  ምት ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል። ከቀኑ 9:00 በደፈጣ የጀመረው ውጊያ አድማሱን አሥፍቶ ወደ መደበኛ ውጊያ ተቀይሯል። በዚህ ውጊያ የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርን አግዘዋል። በዚህ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሆነ ቁሳዊ፣ አካላዊና ሞራላዊ ኪሳራ ደርሶበታል። ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎችም፦ ጨባ መንደር፣ ናዳ፣ ዕማ ወተት ጊዎርጊሥ፣ ዳዋ መድኃኒዓለም፣ ክሬቸር፣ ማሕደረ ማርያም፣ መተሬና ሌሎች ቦታዎች ናቸው። በዚህ ውጊያ የአራዊት ሠራዊቱ ዕቅድ ከሽፎበታል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን👊 ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ አረጋ አንሙት

ቀን፡15/4/2018 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ!!! ካለፉት አምሳ ዓመታት ጀምሮ እየተፈራረቁ ኢትዮጵያን እየመራን ነው ብለው ከዙፋኑ ላይ የቆዩት እና አሁንም እየመራ ያለው ስርዓት መነሻቸው እና የስልጣን እርካታቸውን የሚገልፁት በአማራ ጠልነት ነው።የጥፋታቸው መጠን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ቢሆንም ሕግን ከለላ በማድረግ በአማራ ሕዝብ ላይ በመንግስታዊ መዋቅር አቅማቸው የፈቀደውን ያክል በደል ያልፈፀመ የለም። በደርግ ዘመነ መንግስት ነጭ ሽብርና ቀይ ሽብር እያለ የአማራን ምሁራን ና ወጣቶች በጅምላ እረሽኗል ጨፍጭፏል።በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት ደግሞ ያለ ስሙ ስም እየሰጠ አማራ ጨቋኝ ነው አማራ ነፍጠኛ ነው እያለ በውስጥ ለውስጥ የአማራን ምሁራንና ቀድመው የነቁትን በስውርም በቀጥታም ሲገድልና ሲጨፈጭፍ እንድሁም የሐሰትና የትርክት ሐውልቶችን በማቆም የአማራ ሕዝብ በኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ የተጠላና በተገኘበት ሁሉ የሚገደልበትን ሴራ ሲጠነስስለት ኖረ የማደጎ ሌጁ ለሆነው ለብልፅግና በአማራ ምስለኔዎች አማካኝነት ለኦህዴዱ ብልፅግና ተላልፎ ከተሰጠ እነሆ ስምንተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ የኦህዴዱ ብልፅግና ከሌሎች ስርዓቶች ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከሱ በፊት የነበሩት በስውር፣በተዘዋዋሪና ለሀገር የሰሩ በማስመሰል አማራውን በማዋከብ የሚያደርጉትን ጭፍጨፋ የብልፅግናው ስርዓት ደግሞ በማን አለብኝነት በግልፅ በአማራ ሕዝብ ላይ አይደለም ከዝህ በፊት ሊፈፀም ቀርቶ ወደፊት እንኳን በአለም ላይ ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ በአማራ ሕዝብ ላይ የግፍ ግፍ ፈፅሟል እየፈፀመም ይገኛል።በተለይ ደግሞ ባለፉት ሰባት ዓመታት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ በሚንቀሳቀስበት የቢዛሞ ቀጠና እና በመላው ኦሮሚያ ክልል አማራን ከክልሉ ለማጥፋት ያልተጠቀመው ኃይል የለም፡፡ ኦግ ሼኔ አልችልለት ሲል የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እሱም አልችል ሲል እራሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እያለ የሚጠራው የአብይ አህመድ የግል ወንበር ጠባቂ እናት እና እህቱን ደፋሪው እንድሁም የእናቱንና የእህቱን ጡት ቆራጩን ሰራዊት ቢያሰልፍም የአማራ ፋኖን ምት መቋቋም አልቻለም። ከሰምኑ አገዛዙ የአብይ አህመድ የግል ሰራዊትን እና የሽመልስ አብዲሳ ልዩ ኃይል፣ገዳ ኮማንዶን እንድሁም ሪጴ ሎላእ ና ሚሊሻን ቢያሰልፍም ጠብ የሚል ውጤት ባለማምጣቱ፤ አሁን እንደ አዲስ የጀመረው ዘመቻ ደግም የፋኖን በትር መቋቋም ሲያቅተው ሕፃናትን፣ሴቶችን፣ነፍሰጡር እናቶችን ፣አረጋዊያን እና አቅመ ደካማዎችን ስብሰባ በማለት  ልጆቻችሁ(ፋኖ) ተነኩን እናንተን ነው የምንጨፈጭፋቹህ በማለት ወደ ማጎሪያ ቤት በማስገባት  በሕዝባችን ላይ የማያባራ ግፍ እየተፈፀመበት ይገኛል። ሌላው እነ ሽመልስ አብዲሳ የአማራን በጋራ እናጥፋ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ከበፊትም በነሱ ትዕዛዝ በጫካ ይንቀሳቀሱ የነበሩ እና ኦግ ሸኔ የሚባል የዳቦ ስም ተሰጥቷቸው የነበሩት ከሰሞኑ በበርካታ ሁኔታ ወደ ጉድጓዳቸው ወይም ወደ እናት ድርጅታቸው የኦህዴድ ብልፅግና እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡ ይህም በተናጠል ሁነው ማሳካት ያልቻሉት በጋራ ጥምረት ፈጥረው በሕዝባችን ላይ እልቂት ለመፈፀም የጋራ ስምምነት ፈፅመዋል።ይህን ስምምነት የፈፀሙትም ከሰሞኑ ከታህሳስ 05/2018-ታህሳስ 10/2018 ዓ/ም ከጨፌ ኦሮሚያ ከአዳማ ፣ከምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት፣ከምዕራብ ዕዝ የብልፅግና መከላከያ ጀነራሎች በተገኙበት በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው እና የብልፅግና መከላከያ  ምዕራብ ዕዝ መቀመጫ ኡኬ ከተማ ላይ ባካሄዱት ስብሰባ ነው።በስብሰባውም የምስራቅ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ብልፅግና ከሚያሰማራው ኃይል ውጭ የታጠቀ ኃይል በዞናችን መኖር የለበትም ሲል፤ ከጨፌ ኦሮሚያ ወይም ከአዳማ የመጣው ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አማርኛ ተናጋሪ መኖር የለበትም መጨፍጨፍ እና ማጥፋት አለብን በሚል ተስማምተዋል።ይህ ውሳኔ ከትናት የቀጠለው ነገም ፀንቶ የሚቀጥለው የሞት አዋጅ ነው፡፡ለዚህም በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ላይ ፋኖ በወሰደው እርምጃ የተደናገጠው ጨፍጫፊው ሰራዉት በቀበሌው ውስጥ የሚኖረውን የአማራ ማህበረሰብ ሴት ወንድ፣ ህፃን አዛዉንት ሳይል በአሰቃቂ ሁኔታ እየረሸነ ይገኛል፡፡ቤት እና አዘምራውንም በእሳት ተቃጥሏል፡፡    ከዝህ በመቀጠል እንደ አማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛም ዕዝ የሚከተሉትን መልዕክቶች ማስተላለፍ እንፈልጋለን 1.ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖር አማራ በተለይ ቢዛሞ ቀጠና በሙሉ እኔ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ እና ፋኖም አይደለሁም በማለት እራስን ከማታለል ወጥቶ ከፈፅሞ መጥፋት እራስን ለማዳንና ለመከላከል ከምንጊየውም በላይ እራሱን እንዲያዘጋጅ እና በአካባቢው ባለው የፋኖ መዋቅር ውስጥ በመግባት እንዲታገል ጥሪ እናቀርባለን።ጊዜው አማራነት ወንጀል ወንጀል የሆነበት ነውን፡፡ 2፣የተከበርከው የኦሮሞ ማህበረሰብ እኛ የአማራ ፋኖዎች ግፍን ተፀይፈን እንጅ ግፍ ለመፈፀም አለመውጣታችንን አለም ያወቀው ነው፡፡ ስለዝህ አሁን በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ስሙ ከኦሮሞ አብራክ የወጣ ይሁን እንጅ አይደለም ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረቦች ቀርቶ ለኦሮሞው ማህበረሰብ አንዳችም የጠቀመው የለም።ባለፉት ስምንት ዓመታት ልክ እንደሌሎች ማህበረሰብ ለኦሮሞውም ሕዝብ መታገት፣መገደል፣መፈናቀል እና የንብረት ውድመት ነው የደረሰበት፡፡ ይባስ ብሎ ከሌሎች ኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በኢትዮጵያዊነቱ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዳይሄድ ይህ ስርዓት የኦሮሞ ነው እያለ በአለም ላይ አይደለም ታይቶ ለሰሚው የሚሰቀጥጥ ግፎችን የፈፀመው ስርዓት የእሮሞ ሕዝብ እንደፈፀመው በማድረግ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማያስቀጥል የጥላቻ ግንብ እየገነባልህ መሆኑን በመረዳት በጥቅምም በስልጣንም እያታለለ ሌጆችህን ግፍ እንድፈፅሙ የሚገፋፋውን ስርዓት አምርረህ እንድትታገል እና የተቃውሞ ድምፅህን እንድታሰማ ጥር እናቀርባለን።                                  3,በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ያላቹህ የአማራ ሚዲያ ባለሙያዎች ጋዜጤኞች፣የማህበረሰብ አንቂዎች፣ፖለቲከኞች እና ምሁራኖች ቢዛሞ(ወለጋ) ውስጥ በሚኖረው አማራ አየተፈፀመ ያለውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማድረስ አማራዊ ግዴታቸሁን እንድተወጡ ጥሪ እናስተላልፋለን። ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ ።

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ  ውሎ ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ___፩ አፋብኃ ቴዎድሮስ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር የጠላት ሀይልን እየደመሰሰው ይገኛል። ዳጋዳሞት ፈረስቤት ከተማ የመሸገው ጡትና ምላስ ቆራጩ የብርሃኑ ጁላ ወራሪ ሀይል ወደ ሰቀላና  የተለያዬ የገጠር ክፍሎች ለመንቀሳቀስ ቢሞክርም በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር በደጋዳሞት ሻለቃ  አከርካሪውን ተሰብሮ ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ ፈርጥጧል። ክንደ ነበልባሎቹ 99ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ሻለቃ እግር በግር በመከተል በትናንትናው ዕለት በቀን 15/04/2018 ፈረስ ቤት ከተማ ዘልቀው በመግባት የጠላትን ሀይል መውጫ መግቢያ ሲያሳጡት የዋሉ ሲሆን በርካታ የጠላት ሀይልም ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። _፪ ወንበር አስጠባቂው ሠራት በደፈጣ ተመታ። ቀን 16/04/2018  ዓ/ም አፋብኀ ምዕ/አ/ቀ/ ቴዎድሮስ -እዝ 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦር ተወርዋሪ  ኮማዶ ሀይል አረመኔ  ሰራዊት ላይ የተሣካ  የደፈጣ ጥቃት ፈጽማለች። የአብይ አህመድ አሊ ዙፋን አስጠባቂ ሠራዊት ከዲላሞ ወደ ዝህቭስት ሬሽን ለማቀበል በሚንቀሳቀስበት ወቅት  ዳግሳ አቦ ተብሎ ከሚጠራ ቦታ መብረቃዊ ጥቃት ደርሶበታል።በጥቃቱም 17 አረመኔ  ሰራዊት  ሲገደሉ፣ ቀሪውን መንጋ  ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ  ተችሏል። ___፫ የ109 ኮር 88ኛ ክ/ጦሯ 2ኛ ሻለቃ ለ3ኛ ጊዜ የጠላትን የወረራ ዕቅድ ቀልብሳ መምታት ችላለች። መነሻውን ከወምበርማዋ ሽንዲ ከተማ ያደረገው የአብይ አህመድ ዘር ጨፍጫፊ /Genocider/ ቅጥረኛ ሠረዊት የአርሶአደሩን ንብረት ለመዝረፍ ከንጋቱ 10 ሠዓት አካባቢ ጀምሮ ወደ አንከሻ ጎጉሳዋ ድንጉሻ ቀበሌ ተንቀሳቅሷል። አይበገሬዋ 2ኛ ሻለቃም የጠላትን የእንቅስቃሴ መረጃ አጤና ገዢ ወታደራዊ ቦታ ላይ በማድፈጥ ብርቱ ክንዷን አቅምሳ በመጣበት መንገድ አሯሩጣ መልሳዋለች። የአርሶ አደሩን ንብረት ለመዝረፍ የቋመጠው የጠላት ሀይል  ለ3ኛ ጊዜ የተነኮሰ ሲሆን ዛሬም እነደዚ በፊቱ የወገንን ምት መቋቋም የተሳነው ጠላት ሙትና ቁስለኛውን አንጠልጥሎ ቀጠናውን በንፋስ ፍጥነት እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጧል። ___፬ ለሁለት ቀናት እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ ያደረገው 206ኛ ኮር በተለያዩ ግምባሮች ድል ተቀናጅቷል በትናትናው እለት መነሻውን ከደብረ ማርቆስ ያደረገ የጠላት ኃይል በሁለት አቅጣጫ ወደ ጮቄ ተራራ ለመውጣት ሲንቀሳቀስ የ206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ የፀድ ላይ ባደረገችው ትንቅንቅ ከ30 በላይ የአረመኔውን ሰራዊት በመደምሰስ እቅዱን በማክሸፍ ተዘርግቶ የነበረውን የጠላት ኃይል እሮብ ገበያ ከተማ እንዲሰባሰብ አድርገዋለች። ጠላት ባልጠበቀው ሁኔታ ከኋላው በደረሰበት ጥቃት ወደ ፊት መራመድ ተስኖት አስክሬኑን በፔንፔ የታገዘ ውጊያ ከፍቶ ሲለቃቅም አምሽቷል። በእሮብ ገበያ ከተማ ተሰባስቦ ያደረው ጠላት ኃይሉን አቀናጅቶ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በነብረ ገደል ወለቄ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰ ሲሆን ከንጋቱ ጀምሮ 24ኛ ክ/ጦር ስናን አባ ጅሜ ሻለቃ በአደረገችው እልህ አስጨራሽ የእጅ በእጅ ፍልሚያ ጠላትን እያብከነከነች መልሳዋለች። ተደጋጋሚ ድል በማስመዝገብ የጠላትን አስክሬን ያነባበረችው ስናን አባ ጅሜ ሻለቃ የ6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር የተውጣጣ ኃይል በመደምሰስ ጠላት መሽጎባቸው የነበሩ 4 ቦታዎች ላይ አስክሬኑን ቀብሮ እንዲመለስ አድርገዋለች። ሰራዊቱን እያዝረከረከ የሚሮጠው የአረመኔው ሰራዊት በዛሬው እለት በጅምላ የቀበራቸውን ሰራዊቱን ማህበረሰቡ በመረባረብ ከእርሻ መሬቶች እያወጣ የተለየ መቃብር ቦታ አዘጋጅቶ እየቀበራቸው ይገኛል። በተያያዘ የድል ዜና 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ፣ልዩ ኮማንዶዎችና የቀስተ ደመና ሻለቃ በመቀናጀት ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ማርዘነብ ቀበሌ በመሸገው የአረመኔው ሰራዊት ላይ በፈፀሙት የከበባ ጥቃት ጠላትን በተኛበት ድባቅ መተውታል። ሰዓታትን በወሰደው ድንገተኛ ማጥቃት በተኛበት የተቀጠቀጠው የአረመኔው ሰራዊት ከደብረ ኤልያስ ከተማ በዙ-23 የታገዘ ኃይል በመጨመር አንድ አይሲዙ አስክሬን፣3 አምቡላንስ እና 3 ፓትሮል ቁስለኛ በማንሳት ወደ ደብረ ኤልያስ ተመልሷል። የጠላትን አሰላለፍ እና እቅድ በማጥናት ከፍተኛ ድል እየተቀናጀ የሚገኘው 206ኛ ኮር ፣በጃማ፣ በወለቄ፣በማርዘነብ፣በፀድ ባደረገው ፍልሚያ ከ165 በላይ የጠላት ኃይል መደምሰሱ ተረጋግጧል። ____፭ መብረቁ የጠላት እራስ ምታትሁኖ ቀጥሏል። ከሰዴ ወረዳ በሌሊት በተለያዩ አቅጣጫ በመዉጣት ወደ አፍቀራ ቀበሌ ወጦ የነበረዉ የጠላት ሀይልን የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር እየቀጠቀጠ በመመለስ ቄሳጤ ማሪያም የምትባል ቦታ ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 7:00 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ ተችሏል በተደረገው ማጥቃት የጠላት ሀይል የመከላከያ አመራሮች ጨምሮ ከ11 በላይ አስክሬን መነሳቱን በርካታ ቁስለኛ ሲጎጎዝ እንደነበር ከአካባቢው ባሉ ነዋሪወች ማረጋገጥ ተችሏል። የፋኖን ሀይልን መቋቋም ያቃተዉ የጠላት ሀይል ሰዴ ወረዳ ከተማ ላይ በመሆን የአዲስ አለም ቀበሌ የ1ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ተቋምን በሞርተር በመደብደብ አዉድሟል። ___፮ ስቦ ማስከዳት የአብይ እና የብርኃኑ ጁላ ጦር እየፈራረሰ ነው በደጋ ዳሞት ወረዳ ከ23ኛ ክፍለ ጦር በቀን 15/04/2018 ዓ.ም ሁለት መሰረታዊ ወታደር እያንዳንዳቸው ጥቁር ክላሽ በመያዝ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ደጋ ዳሞት ሻለቃን ተቀላቅለዋል :: 1ኛ . መሰረታዊ ወታደር አድነው እንየው         ...1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 91ጥይት 2ኛ.መሰረታዊ ወታደር ንግሩ ደመቀ      ..... 1ኛ ሬጅመንት ሻምበል 3 ጥቁር ክላሽ እና 110 ጥይት  በመያዝ ተቀላቀለዋል ::  በተያያዘ ከጠዋቱ 1:00 አካባቢ ፈረስ ቤት ከተማ አናብስቶቹ የደጋ ዳሞት ሻለቃ ወደ ከተማ በመግባት በቴክኒክና ሙያ አካባቢ በተቀመጠው  የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በቁጥር ያልታወቀ ሙት እና ቁስለኛ በማድረግ ያለምንም መስዋትነት ቀጠናውን ለቀው ወጥተዋል። __፯ በቢቸና ከተማ 04 ቀበሌ የባጃጅሹፊሮች  በአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። በቢቸና ከተማ የሚገኘው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት በፋኖ ምት ተስፋ በመቁረጥ ንፁሀን አማራዎች ላይ አፈሙዝ በማዞር ንፁሀንን በመግደል አረመኔዊ ተግባሩን እያሳየ ይገኛል። የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:15  3(ሶስት) የባጃጅ ሹፊሮች ላይ በመተኮስ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል እና ከባድ ቁስለኛ በማድርግ የንፁሀን ባጃጆችን አቃጥሏል።

1ኛ. ወጣት ምናሉ መርከቡ ይባላል የትውልድ ቦታው ሸበል በረንታ ሶሃ ተፋሰስ ቀበሌ ልዩ ቦታ ደንሲት መረዛምባ ተወላጅ ሲሆን በቢቸና ከተማ ኪዳነምህረት ሰፈር ከተማ የባጃጅ ሹፊር እየሰራ የግል ህይወቱን እየመራ ይገኝ ነበር። በመሆኑም በቢቸና ከተማ ንፁሀን በመረሸን እና በመዝረፍ የሚታወቀው የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ከምሽቱ 1:15 ቢቸና ከተማ ዲዲሱ አካባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ከእነ ባጃጁ አቃጥለውታል። 2ኛ. ሞገስ አስቻለ ቢቸና ከተማ ተወላጅ ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል ህክምና እያገኘ መሆኑ ተረጋግጦል። 3ኛ. (ይወግ) ዳዱሽ የወግ የተባለ ወጣት በቢቸና ከተማ 02 ቀበሌ አቡየ ሰፈር ተወላጅ ከጓዶቹ ጋር የባጃጅ ስራቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው እየሄዱ በአለበት ሰዓት የአገዛዙ ሰራዊት ዲዲሱ ሰፈር አልመው በተኮሱት ተኩስ ቢቸና የመጀመረያ ደረጃ ሆሲፒታል የገባ ቢሆንም ዶክተሮቹ ከባድ የአጥንት መሰበር ጉዳት እንዳለበት በማሳወቅ ከአቅማቸው ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ደ/ማርቆስ ከተማ እሪፈር ተብሎ መሄዱ ተረጋግጦል። ወጣት ደድሸው በቢቸና ከተማ በሚደርጉ ስብሰባዎች በቢቸና ከተማ እየተፈፀሙ የነበሩ ግፎችን ይናገር እንደነበር በዚህም አገዛዙ በመከታተል እርምጃ እንተወደበት ተረጋግጦል። 4ኛ.በባጃጁ ላይ አብሮ ይጎዝ የነበር ንፁሀን ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጦል። 5ኛ.ወጣት ውዱ ይበልጣል እነማይ ወረዳ ቅድስጌ ቀበሌ ተወላጅ የባጃጅ ሹፊር  ሲሆን ሰውነቱን በዱላ፣በአፈሙዝ በመደብደብ እና በመቀጥቀጥ በሰውነቱ ላይ አካላዊ ጉዳት በማድርስ ታስሮ ይገኛል። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media) - آمار و تحلیل کانال تلگرام @mezmure122124