fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 491
مشترکین
+1024 ساعت
+847 روز
+87330 روز
آرشیو پست ها
በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች የረሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች የረሃብ
+1
በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች የረሃብ አድማ መጀመራቸው ተነገረ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ክርስቲያን ታደለና ሌሎች ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞች የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ በአድማ ላይ የሚገኙት እስረኞች “ለሕይወታቸው እጅጉን አስጊ” በመሆኑ አጣዳፊ እርምጃ በመውሰድ ሕይወታቸውን እንታደግ” ሲል ኢሕአፓ ጥሪውን አቅርቧል። ተቃዋሚ ፓርቲው ለኢትዮቲዩብ በላከው መግለጫ በማረሚያ ቤቱ የሚገኙት እስረኞች “በደልና ግፍ እየደረሰበት ላለው የአማራና ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት ነፃነትና ጥቅሞች ከመቆም ውጭ ይህ ነው የሚባል ወንጀል ሳይሰሩ መታሰራቸውን" ገልጿል። እስረኞቹ “ፍትሕ እንዳያገኙ” መደረጋቸውንም ፓርቲው በመግለጫው አስፍሯል። ኢህአፓ “ወንጀል ሳይሰሩ” በእስር ላይ ይገኛሉ ካላቸው ግለሰቦች መካከል፤የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ይገኙበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣መምህርት መስከረም አበራ፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ ዶ/ር ጫኔ ከበደ፣ መሪጌታ በላይ አዳሙ እና ዶ/ር ካሳ ተሻገር ፓርቲው የጠቀሳቸው ግለሰቦች ናቸው። ከእስረኞቹ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በሕመም ላይ የቆዩ “በቂና አስፈላጊውን የሕክምና ዕርዳታ የተከለከሉ” መኖራቸውንም ተቃዋሚ ፓርቲው አስታውቋል። በአማራ ክልል እየተካሔደ ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው ታህሳስ 03/2017 ዓ.ም. የአንጀት ድርቀት አጋጥሟቸው በመቅረዝ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሕክምና ማድረጋቸው አይዘነጋም።

መስቀል አደባባይ አደጋ ደረሰ‼️ በመስቀል አደባባይ ዛሬ አመሻሹን ድንገተኛ አደጋ መድረሱን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በርካታ አምቡላንሶች የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል እያመላለሱ ሲሆን በአካባቢው በርካታ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እንደሚታዩ የአይን እማኞች ገልፀዋል። የአደጋው መንስኤ የህዳሴ ግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ ነገ ለሚደረገው የብልፅግና የፕሮፖጋንዳ ጥሪ እና ድጋፍ ሰልፍ ልጆች ለልምምድ እየተዘጋጁ በነበረበት ወቅት መድረኩ በመደርመሱ ምክንያት መሆኑን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። የካቲት 12 ሆስፒታል ጉዳት ያስተናገዱ በርካታ ሰዎች ማየታቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል። ለተጎዱ ሰዎች መልካሙን ሁሉ እንመኛለን። ሙሉ መረጃዎችን ተመልሸ ይዥ እመጣለሁ እስከዛው ‎ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አሳዛኝ ዜና! በመስቀል አደባባይ በደረሰ የመድረክ መደርመስ አደጋ በታዳጊዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ማድረሱ ተነገረ! ገዢው የብልፅግና ቡድን፡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሕዳሴ ግድብ መመረቅን በማስመልከት ለነገ መስከረም 04/2018 ዓ/ም የድጋፍ ሰልፍ እንዲያካሂዱለት ያዘዘ ሲሆን፡ በሰልፉ ላይ ልዩ ልዩ ትርኢቶችን እንዲያሳዩ ስልጠና ሲሰጣቸው የነበሩ ታዳጊዎች ተሰብስበውበት የነበረው መድረክ ተንዶ በበርካቶች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ ማድረሱን የአይን እማኞች ለመረብ ሚዲያ ተናግረዋል። አደጋው ከደረሰባቸው ታዳጊዎች መካከል ሕይወታቸው ያለፈ እንዳለ የተናገሩት ምንጮቻችን፡ ነገ ግን ብዛታቸውን በውል ማወቅ አልተቻለም ብለዋል። አደጋው የደረሰው ዛሬ መስከረም 03/2018 ዓ/ም ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን፡ አከባቢው በፀጥታ ኃይሎች ተከቧል፡ የተደረመሰውን የመድረክ ፍርስራሽ በማንሳት በርካታ ታዳጊዎች  በአምቡላንስ ወደ ሕክምና ጣቢያ እየተወሰዱ ነው ሲሉ መረብ ሚዲያ ያነጋገራቸው የአይን እማኞች ገልፀዋል። የገዢው የብልፅግና ቡድን አመራሮች የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብ መመረቅን በማስመልከት ለነገ መስከረም 04/2018 ዓ/ም ከጧት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲያካሂድላቸው መመሪያ አስተላልፈዋል። ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥የወምበርማ ብርጌድ የስራ ግምገማ አደረገ...‼️ (መስከረም 3/2017 ዓ.ም የወምበርማ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ) አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ፭ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ
🔥የወምበርማ ብርጌድ የስራ ግምገማ አደረገ...‼️ (መስከረም 3/2017 ዓ.ም የወምበርማ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ) አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ፭ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ ብርጌድ ከፍተኛ የዕዝ አመራሮች በተገኙበት አርበኛ ዶ/ር ተሰማ ካሳሁን እና አርበኛ ሂሩይ ባዬ በተገኙበት ከብርጌድ እስከ ሻለቃ አመራሮች ጥልቅ ግምገማ አደረገ። በውይይቱም ወታደራዊ አቅምን ማጎልበት፣ የወር የስራ መልስግምገማዎችን፣ ግዳጅ አፈጻጽም፣ የሀይል አያያዝ ፣ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ግንባታ ፣ የበርጌዱ አሁናዊ ቀመናውን በተመለከተ ሰፊ አጀንዳ ከፍተው ተወያይተዋል። የወምበርማ ብርጌድ ለወራት ከጦሩ እና ከማህበረሰቡ ሲያከናውኗቸው የቆዩትን ዋና ዋና ተግባራት ሲያከናውን ቆይቶ ብርጌዱን የተሻለ ቁመናውን ለማሳደግ ጠንካራ ግምገማዎችን አካሂዷል። የ5ኛ ክፍለ ጦር የወምበርማ ብርጌድ ያለ ዕረፍ ወራቶችን እና ጊዚያቶችን ተጠቅሞ ጦሩን እና የወታደራዊ አቅሙን በከፍታ ማማ ላይ ለመስቀል ጠንካራ የስራ ክንውኖችን እያካሄደ ይገኛል። ድል ለአማራ ህዝብ!! 03/ዐ1/2018 ዓ.ም ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ሳምንታትን በወሰደው የስልጠናና ግምገማ ውጤት መሰረት ብርጌዱን በአዲስ አደራጅቷል። የአባይ ሸለቆ ብርጌድ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተቀናጀባቸውን
ዘጠነኛ ሳሙኤል አወቀ ክ/ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ሳምንታትን በወሰደው የስልጠናና ግምገማ ውጤት መሰረት ብርጌዱን በአዲስ አደራጅቷል። የአባይ ሸለቆ ብርጌድ በጠላት ላይ ከፍተኛ ድል የተቀናጀባቸውን ልዩ ዘመቻዎችና ውጊያዎችን በማቀድና በመምራት ግዳጁን በብቃት ሲወጣ የነበረው የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ዘመቻ ኃላፊ የነበረው ፶ አለቃ ምስጋናው አበበ በአዲሱ አደረጃጀት የአባይ ሸለቆ ብርጌድ ዋና ጦር አዛዥ ሁኖ ተሹሟል። ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የጀብደኛው አሳምነው ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ንጉስ አበራ 👇 ወደ ትግል ሜዳ የወረድነው የአማራ ህዝብ የትግል ሪዮት ገብቶን እንጅ ቁራሽ ዳቦ ቸግሮን አይደ
+1
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የጀብደኛው አሳምነው ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ንጉስ አበራ 👇 ወደ ትግል ሜዳ የወረድነው የአማራ ህዝብ የትግል ሪዮት ገብቶን እንጅ  ቁራሽ ዳቦ ቸግሮን አይደለም ያማራን ህዝብ እፎይታ እምናበስረው የተደረደረው መሳሪያ በሚተፋው እርሳስ እንጅ በአብይ አህመድ የቀበሌ ካድሬ ጭብጨባ አይደለም!!! በቅርብ ቀን ባንዳን እጁን ቆርጠን ለህዝባችን እፎይታን እናበስራለን። ጀግናዬ  💪 ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ለአብይ አህመድ ወንበር ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነት! ባትመጡብን ነበር እሚሻለዉ ከመጣችሁ ምን ይደረጋል እናስተናግዳለን በሚገባ💪 በተባበረዉ ክንዳችን ።
+1
ለአብይ አህመድ ወንበር ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነት! ባትመጡብን ነበር እሚሻለዉ ከመጣችሁ ምን ይደረጋል እናስተናግዳለን በሚገባ💪 በተባበረዉ ክንዳችን ።

🔥#ከአማራ_ፋኖ_ብሔራዊ_ኃይል_የተሰጠ_መግለጫ‼️ መስከረም 03 ቀን 2018 ዓ.ም ``````````````````````````````````````````` አረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከከፈተ ድፍን ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል። በእነዚህ ሁለት ዓመታት ግዜ ውስጥ አገዛዙ ያልተጠቀመው የዘር ማጥፋት እና የጦርነት ስልት የለም። አማራው ራሱን የሚከላከልበትን ጦር መሳሪያ እንዳይኖረው በማድረግ መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈፀም አስቦ በከፈተው ሁሉንተናዊ ጦርነት ህፃናትን ጨፍጭፏል። ንፁሃንን በመግደል የሽብር ተግባር አከናውኗል። ሁለንተናዊ ጦርነትን ካስፈፀመባቸው መካከል የህዝብ መገልገያ ተቋማትን አገልግሎት በማይሰጡበት ማውደም አንደኛው ነው። ይህ ውድመት ከደረሰባቸው ማህበራዊ ተቋማት መካከል ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ቀዳሚዉን ድርሻ ይይዛሉ። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ከ6000  በላይ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት እና የዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አገልግሎት በማይሰጡበት ደረጃ ወድመዋል። ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ የተባሉ መምህራን ተገድለዋል፣ በአስር ሺወች የሚቆጠሩ ታዳጊ ሴት ተማሪወች በአረመኔው ሰራዊት በጅምላ ተደፍረዋል። ይህ ሁሉ ውድመት የደረሰው የአገዛዙ ሰራዊት ትምህርት ቤቶችን በድሮን፣ በጀት፣ በመድፍ እና በሌሎች ከባድ መሳሪወች በቀጥታ በመደብደቡ፣ ተቋማቱን በቀጥታ በማፍረስ እና በማቃጠሉ እንዲሁም ሁሉም የጠላት ሰራዊት እነኝህን የትምህርት ተቋማት በካምፕነት በመጠቀሙ ነው። ይህ ወንጀል ላለፉት ለሁለት ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈፀም መዋቅሩ የፈራረሰው አገዛዝ መፍትሔ መስጠት አልቻለም። ይልቁንም ሰራዊቱ ይህንን ወንጀል እንዲፈፅም ስልታዊ እና ይፋዊ ድጋፍ እና ፈቃድ በመስጠት ላይ ይገኛል። ይህንን እና ተመሳሳይ የጠላት ተልዕኮወችን በመከላከል ታሪካዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በበኩሉ በማህበራዊ ተቋማት ላይ ውድመት የማይደርስባቸውን ወታደራዊ ስልቶችን በመጠቀም እና ሰራዊታችንም ተቋማቱ እንዳይወድሙ በመጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል። የብልፅግና ካሪኩለም ለአማራ ህዝብ ትርጉም ያለው ፋይዳ ያመጣል ተብሎ ባይታመንም በእነኝህ የአገዛዙ የጥፋት ተልዕኮወች ምክንያት ሚሊየኖች ከትምህርት ገበታ ተገልለው መሰረታዊ ዕውቀት የማይገበዩበት ሁኔታ መፈጠሩ ድርጅታችንን በእጅጉ ያሳስበዋል። በተለይም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማእከላዊ ኮማንድ ለቀናት ባደረገው ስብሰባ በአጀንዳነት ከተነጋገረባቸው ጉዳዮች መካከል የትምህርት ሁኔታ አንደኛው ነበር። በዚህ መሰረት በአጀንዳው ላይ መፍትሔ የሚያመጣ ግብረ ኃይል ስምሪት ወስዶ ጥናት አድርጎ ባመጣው የመፍትሔ ሃሳብ መሰረት ብሔራዊ ኃይሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በፊት ያወጣውን መግለጫ ገቢራዊነት በሚያረጋግጥ መልኩ ማሻሻል እንዳለበት አምኖበታል። በመሆኑም ግብረ ኃይሉ የዳሰሳ ጥናቱን መሰረት አድርጎ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ማዕከላዊ ኮማንዱ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተከታዩን ጥሪ ያቀርባል። 1) በትምህርት ጉዳይ ለሚሰሩ ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የትምህርትን ጉዳይ በመደገፍ የሚታወቁት ሴቭ ዘ ችልድረን፣ ዩኒሴፍ፣ ዩኔስኮ እና መሰል ተቋማት ለትምህርት ማስፈፀሚያ በሚል ለአገዛዙ የሚበጅቱት በርካታ ሚሊዬን ዶላር ቢኖርም ይኸው በጀት በአገዛዙ በኩል ለጦርነት ግብዓት እየዋለ ይገኛል። ስለሆነም ግብረ- ሰናይ ድርጅቶቹ ይህንን ጉዳይ እንዲያጤኑት እና ክትትል እንዲያደርጉበት ጥሪ እናቀርባለን። 2) ለመላው የአማራ ህዝብ አገዛዙ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እየፈፀመ ያለው በአማራ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ጦርነት ማስቀጠል መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። በትምህርት ተቋማት ላይ በአረመኔው ሰራዊት የደረሰው ውድመትም የዚህ አካል መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የአገዛዙ ሰራዊት የህዝብ አንጡራ ሀብት የሆኑትን ተቋማት በማውደም፣ ሴት ልጆቹን በመድፈር፣ ህዝቡንም በመዝረፍ እና ጨለማ ውስጥ ለማስገባት የሚያደርገውን የወንጀል ተግባር ያቆም ዘንድ የመከላከያ ሰራዊት ነኝ የሚለው የአገዛዙ ጠባቂ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ እና የመማር ማስተማር ተግባሩ እንዲከናወን ህዝቡ ተገቢውን ትግል እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን። 3) ለተማሪ ወላጆች እና ለተማሪወች ከላይ የጠቀስናቸው ጥቃቶች በተለይ በተማሪወች እና በወላጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ቀውስን ያስከተሉ በመሆናቸው አገዛዙን በማንኛውም መንገድ ለመታገል የቀዳሚነቱን ሚና መውሰድ ይገባቸዋል። ስለሆነም የትውልድ ክፍተት እንዲፈጠር የችግሩ ምንጭ የሆነው የአገዛዙ ሰራዊት የፈፀመው የጥፋት ወረራ በመሆኑ የአገዛዙ ወራሪ ሰራዊት ወደ መደበኛው ተልዕኮው እንዲመለስ እና ክልሉን ለቆ እንዲወጣ በየደረጃው ባለ የአገዛዙ መዋቅር በኩል ግፊት እንድታደርጉ እናሳስባለን። 4) በቀጣይ ትምህርት የሚቀጥልበትን ሁኔታ በተመለከተ ከላይ ባቀረብነው ጥሪ መሰረት የአገዛዙ ሰራዊት ክልሉን ለቆ እንዲወጣ የሚደረገውን ሰላማዊ የህዝብ ትግል እንደተለመደው በኃይል የሚያፍን ከሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት በታዛቢነት የሚያስፈፅሙት የትምህርት ተቋማትን ከወታደራዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ነፃ የማድረግ የትምህርት የሰላም ስምምነት መደረግ ይኖርበታል። ይህ ኮሎምቢያ፣ ኔፓል፣ ኮንጎ እና ፊሊፒንስን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት በነበሩ የእርስ በእርስ ጦርነቶች ወቅት ተግባራዊ ተደርጎ ተጨባጭ ውጤት የተገኘበት ነው። በመሆኑም ዓለም አቀፍ ተሞክሮወችን እና መመዘኛወችን ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዋደድ ወደ ፊት በዝርዝር በምናስቀምጣቸው መርሆወች መሰረት የሚፈፀም ስለሆነ አገዛዙ ለዚህ ጉዳይ አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ እና የወደሙ ተቋማት ተጠግነው ከፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ተግባራት ነፃ ሆነው ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ የሚመለሱበትን ሁኔታ እንዲመቻች ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን።   አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! 3/ዐ1/2018 ዓ.ም ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አይ ጋሽ አስታጥቂ ቀልድሽ አያልቅበት ደግሞ ዛሬ የየት ሃገር ሲጋራ ቅመሽ ነው አንች ዱርዩ ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ሰበር!! በአርማጭሆ በተለያዩ ወረዳዎች አገዛዙን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ የሚሊሻ አባላት በዛሬዉ ዕለት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ የፋኖ አደረጃጀትን ተቀላቅለዋል። ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በየቀኑ በሰከነ አንደበት እየመከረ የአመራር ከፍታውን እያስጠበቀ ቀጥሏል። በየ አውደ ውጊያው በደፈጣ ፣ በሽምቅ ፣ በከበባ ድምሰሳ ፣ በተናጥላዊ ጥቃት ፣ በስቦ ማስከዳት ጠላትን በከፍተኛ ፍጥነት ብትንትኑን እያወጣው ነው ። የሐይል ግንባታ ፣ የአመራር ግንባታ ፣ የፖለቲካ ግንባታ ፣ የስነልቦና ግንባታ ስራዎችን በፍጥነት እየሰራ ይገኛል ። በስቦ ማስከዳት ስልት በየቀኑ በበርካታ አካባቢዎች ከጠላት ካምፕ እየከዳ ከእነ ሙሉ ትጥቁ ወገንን የሚቀላቀለው የሰራዊት ቁጥር እየጨመረ ነው ። የኃይል ዕድገት ፣ የፖለቲካ ዕድገት ፣ የዲፕሎማሲ ዕድገት ፣ የአመራርነት ዕድገት እያሳየ ያለው ድርጅቱ ከአማራ አልፎ ኢትዮጵያውያንን ፣ የአፍሪካ ሀገራትን እና ዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት እየሳበ መጥቷል ። ከየ አካባቢው ጨቅላ ህፃናትን እያፈሰ የሚያስፈጀው ወንበዴ እና ጨፍጫፊ አገዛዝ ባለችው ትርፍራፊ ጊዜ እና ሽርፍራፊ ሳንቲም ተጨማሪ ጦርነት ገጥሞ ከእነ አካቴው ከሀገር ብን ብሎ ሊጠፋ ተቃርቧል ። የአማራ ህዝብ የመከራ ቀንበር ከህዝባችን ትክሻ ላይ የሚወርድበት ጊዜ አጭር በመሆኑ ሳይገባችሁ ፣ ተገዳችሁ ፣ በጥቅም ተታላችሁ በየአካባቢው የአብይ አህመድ የውምብድና ካምፕ ውስጥ የምትገኙ የአማራ ልጆች እና እውነተኛ ኢትዮጵያውያን አሁንም በአለቻችሁ አጭር ጊዜ ወደ ፋኖ እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !! ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳ/ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የተሳካ ድምሰሳ ድል ተቀናጀ‼️ ከጉንትር አቦ እስከ ገደብየ ከተማ አስደናቂ  ሰርቷል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዛሬ መስከረም 3/2018 ዓ/ም በጠዋት ሁለት ሰዓት ወደ ወገራ ወረዳ ጉንትር አቦ ቀበሌ  በወውጣት ጀግኖች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀው የአገዛዙ ጥምር ሀይል በጎንደሬ በጋሻው እንደ በዓል ቄጤማ ምድር ላይ ነስንሰውታል ። የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አመራሮችና አባላትን  እንዲሁም የራስ አሞራው (3ተኛ)  ኮር አሃድ ተዋጊ ጀግኖች በጥምረት በሰፊ ቀጠና የተደረገውን አውደውጊያ ጠላትን በመረፍረፍ አኩሪ ተጋድሎ ፈፅመዋል። በአውደ ውጊያው በጎንደሬ በጋሻው በኩል   ቴውድሮስ ብርጌድ ፣ አጥናፋ ብርጌድ ፣ይታየሁ ብርጌድ እንዲሁም ከራስ አሞራው 3ተኛ ኮር ሁለት ብርጌዶች ከአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ሀይል ጋር  ከጉንትር አቦ ቀበሌ እስከ ገደብየ ከተማ ድረስ በተካሄደው እልህ አስጨራሽ የጨበጣ ውጊያ ጀግኖች ድል ተጎናፅፈዋል።    የብርሃኑ ጁላው ሰራዊት አስከሬኑን እያንጠባጠበ ሲሄድ በአካል የተቆጠረን ጨምሮ 31 ላይመለሱ  የተ*ሸ* ኙ ሲሆን ከ4 በላይ የሚሆኑት ከቀላል እስከ ከባድ ቆስለው በአንቡላንስና በባጃጅ እያመላለሰ የዳባትና የደባርቅ ሆስፒታሎችን አጨናንቋል ። በአጠቃላይ ውጊያው እስከ አሁን እደቀጠለ ሲሆን ጀግኖቹ አሁን ላይ ገደብየ ከተማን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል። የብርሃኑ ጁላ ሀይል ከፍተኛ የሆነ ፖለቲካዊና ቁሳዊ ጉዳት አያስተናገደ ሲገኝ  ከአምባጊዮርጊስ እስከ ደባርቅ ከተማ ድረስ ያለውም  የአገዛዙ ሀይል በፍርሃት እየራደ ይገኛል።      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን  !!! አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ 03/ዐ1/2018 ዓ.ም ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥#ለእስረኞች_ምህረት_ተደረገ‼️ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ቀኝ ጌታ የፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ የብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አዲስ አመት
+1
🔥#ለእስረኞች_ምህረት_ተደረገ‼️ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ ቀኝ ጌታ የፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክ/ጦር  የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ የብርጌዱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት  አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በማረሚያ ለሚገኙ  ለ12(አስራ ሁለት ) ወንጀለኞች  ይቅርታ አደረገ ። አዲስ አመትን  አስመልከቶ በይቅርታ የተለቀቁ   ታራሚወች 1ኛ አለኸኝ ተረፈ 2ኛ ደሴ አትንኩት 3ኛ ሙሉ አናጋው 4ኛ ትርንጉ ጎዴ 5ኛ ይታያል በላይ 6ኛ ሽፈራው  አንማው 7ኛ አንማው ጎዴ 8ኛ  ንጉሴ  ጎዴ 9ኛ አምላኬ ባለው 10ኛ  አሳየ በላይ 11ኛ  ምንውየ ዘገየ 12ኛ ታደሰ  13ኛ ሙሉ መኮነን ይባላሉ። በሌላ ዜና የአረመኔው አብይ አህመድ ንፁሀን ላይ የሚያደርገውን መጨፍጨፍ እና ማሳደድ እንደቀጠለ ነው። ጸረ አማራው የሰው በላ ቡድን ዛሬም በደንበጫ ወረዳ ልዮ ስሙ የደገራ ሚካኤል ተብሎ በሚጠራው ቦታ አካባቢ እብስቱ እና እንቻለው  የተባሉ ሁለት ግለሰቦችን ሀገር አማን ብለው ከተኙበት ቤታቸው አፍኖ በመውሰድ ያደረሰበት አልታወቀም። ©ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ6ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት 03/ዐ1/2018 ዓ.ም ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

ፈጽሞ ውሸት ነው። ፋኖ አይደለም! ለሚመለከተው ሁሉ፦ ይኼ ልጅ ሀረር እና ድሬዳዋ ሎተሪ በማዞር ይሰራ የነበረ የዚሁ ጎጃም አካባቢ ተወላጅ ነበር። ቤተሰቦችም ይታወቃሉ። እዚያ ሲንጓለል ከርሞ ወደ ጎ
ፈጽሞ ውሸት ነው። ፋኖ አይደለም! ለሚመለከተው ሁሉ፦ ይኼ ልጅ ሀረር እና ድሬዳዋ ሎተሪ በማዞር ይሰራ የነበረ የዚሁ ጎጃም አካባቢ ተወላጅ ነበር። ቤተሰቦችም ይታወቃሉ። እዚያ ሲንጓለል ከርሞ ወደ ጎጃም መጦ አታግሉኝ ብሎ የነበረ ቢሆንም በጥርጣሬ የአፋጎ የመረጃና ደህነት መዋቅር ከለከለው። በፍጹም ለአንድ ቀን እንኳን ፋኖ ሁኖ አያውቅም፤ እንኳን አመራር ሊሆን ቀርቶ ። አሁን እጅ ሰጠ ብለው የውሸት ፕሮፖጋንዳ እየሰሩበት ይገኛሉ። የአፋጎ የመረጃና ደህነት መዋቅሩ ግለሰቡን ለተልዕኮ የገባ መሆኑን ቀድሞ ጥርጣሬ ስለነበረው ወደ አመራርነት እንዳይመጣ ተራ አባል ሁኖ ይቆይ ተብሎ እንደጠበቀው ሳይሆን ሲቀር ተመልሶ ሂዷል። ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የአገዛዙ ሹመት የመረጃ !! ዶ\ር ፍፁም አሰፋ የተባሉ የአብይ አህመድ ታማኝ ገረድ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዢ ተደርገው ተሾሙ እየተባለ ነው ። ከዚህ በፊት የፕላን ሚንስቴር በመሆን ላለፉት ሰባት ዓመ
የአገዛዙ ሹመት የመረጃ !! ዶ\ር ፍፁም አሰፋ የተባሉ የአብይ አህመድ ታማኝ ገረድ የብሄራዊ ባንክ ዋና ገዢ ተደርገው ተሾሙ እየተባለ ነው ። ከዚህ በፊት የፕላን ሚንስቴር በመሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የፋሽስቱን አገዛዝ በተላላኪነት ሲያግዙ የነበሩት ዶክተር ፍጹም አሰፋ የኦህዴድ ብልፅግና መቀለጃ እና ሀገር ማሻሻጫ የሆነው የብሄራዉ ባንክ  10ኛ ዋና ገዢ ሆነው በአብይ አህመድ መመደባቸውን አመሻሽ ላይ የወጡ የመረጃዎች ያሳያሉ። ‎ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

🔥ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ከፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ ለመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች  የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ‼️ እንደሚታወቀው አዲስ ዘመን ይዟቸው ከሚመጣቸው በጎ  ቱርፋቶች አንዱ እና ዋናው ቁምነገር ያለፈውን መርሳት የበደሉንን ይቅር ማለት እና ንሰሃቸውን ተቀብሎ ከስህተታቸው ታርመው ወደ እውነተኛ መንገድ እንዲመለሱ እና የበደሉትን እንዲክሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መንገዶችን መጥረግ መሰናክሎችን ማስወገድ እና ጎርባጣውችን ማደላደል መሆኑን ኮራችን በፅኑ ይገነዘባል። ስለሆነም አዲሱን ዘመን ምክኒያት በማድረግ ልጅ እያሱ ኮር በዋነኛነት በሚንቀሳቀስባቸው በሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ወረዳዎች  ማለትም፦ በደቡብ ወሎ ዞን፦ *^^^*^^^*** 1 በአምባሰል ወረዳ 2 በቃሉ ወረዳ 3 በተውለደሬ ወረዳ 4 በወረ ኢሉ ወረዳ 5 በደሴ ዙሪያ ወረዳ 6 በተንታ ወረዳ እና 7 በደላንታ ወረዳ በሰሜን ወሎ ዞን *^^^*^^^*** 1  በሃብሩ ወረዳ 2 በጉባላፍቶ ወረዳ በሰሜን ሸዋ ዞን *^^^*^^^*** ግሽርአቤ ወረዳ ለምትገኙ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይህ ካለ ጦርነትና ውድመት ሃገር መምራት የማይቻል  የሚመስለው ሰነፍ ስርዓተ መንግስት ለሃገር ይበጃል ብላችሁ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ  እስካሁን ባልገባችሁ መንግሥታዊ ሃገር የማፍረስ አላማ  ተሰልፋችሁ ንፁህ ደማችሁን ውድ አካላችሁንና አይተኬ  ህይወታችሁን አርክሳችሁ በማይረባ ጥቅም ተደልላችሁ ሞታችሁና ቀብራችሁ እንኳ ክብር አጥቶ እንደ ውሻ የትም ስትጣሉ ከርማችኀል እና ዛሬ ላይ ሊበቃችሁ ይገባል፡፡ ይህ የከረፋና አምባገነናዊ መንግሥታዊ ሥርዓት አሁንም ለ2018 ለቀይ ባህር እና ለአሰብ ዘምታለው በሚል መሪ ቃል ዳግሞ ማለቂያ የሌለው ጦርነት እየጎሰመ እና እየጠነሰሰ ባለው የጦርነት ድግስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ እና ዋጋ ከፋይ አሁንም እናንተ መሆናችሁን እና ለሚነሳው እሳት ለማገዶ የተዘጋጃችሁ ቤንዚን የተርከፈከፈበት ብቻ ሳይሆን የተደፋበት እንደ ደረቅ ግንዲላዎች የቀረባችሁ ከፍማችሁ ወጥ ማጣፈጫ ከሰል ሊያወጣባችሁ እና ዳር ቆሞ ሊሞቃችሁ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ስለመሆኑ ከወዲሁ ተረድታችሁ ልብ ልትሉና አይናችሁን በደንብ ገልጣችሁ ዙሪያ መለሱን በንቃት ልትመለከቱ ይገባል፡፡ ስለሆነም ኮራችን የመንግስትን የተለያዩ የፀጥታ ተቋም ለማገልገል ተሠልፈው ውድ እና አይተኬ አካል እና ነፍሳቸውን ላረከሱ ራስ ጠሎች ማለትም  ለመከላከያው ለሚሊሻው ለፖሊሱ እና ለአድማ ብተናው ኀይል አዲሱን አመት 2018 በማስመልከት የንሰሃ ጊዜ አዘጋጅተን እናንተን ወንድሞቻችንን ከነሙሉ ክብራችሁ እና ሞገሳችሁ ለመቀበል  የወሰንን ሲሆን ከወንድሞቻችን ጋር እርስ በእርስ የተገፋፋንበት እና የተገዳደልንበት ያ-ክፉ ጊዜ ጥቅም አልባ መሆኑን አምነን ይቅር ተባብለን በፍቅር ያለምንም የሃይል ተፅእኖ ለዚህ ስርዓት ሎሌ መሆናችሁን ወዲያ አሽቀንጥራችሁ ጥላችሁ ወደ ወንድሞቻችሁ እና ልጆቻችሁ እንድትመጡ እኛም በክብር ለመቀበል እና ምርጫችሁን አክብረን ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅታችንን ጨርሰን ይኸው ዛሬ ጥሪ አድርገናል፡፡ ስለዚህ እናንተም የእስካሁኑ ጉዞዋችሁ ትክክል እንዳልነበረ አምናችሁ እና ተፀፅታችሁ በ2017 እና ከዛ ፊት ከወጣችሁበት ህዝብ ላይ ራሳችሁን ፍፁም ጠልታችሁ ከጠላት ጎራ ተሰልፋችሁ ስትፈፅሙት የነበረው ዝርፊያን ጨምሮ አሰቃቂ ግፍና በደል ትክክል እንዳልነበር አምናችሁ እና ከልባችሁ ተፀፅታችሁ ህዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠይቃችሁ ከማህበረሰባችሁ ጋር ዳግም ተቀላቅላችሁ የምትኖሩበት እንዲሁም ፍላጎታችሁ ትግልም ከሆነ ከእኛ ጎን ተሰልፋችሁም ተማምነን በጋራ የምንታገልበት ሁኔታ ፈጥረን አስፈላጊ ነገሮችን እና ድጋፎችን እንደምናመቻች ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡ በመሆኑም 2017 ዓም የመጨረሻው የእርስ በእርስ ጦርነት ዘመን እንዲሆንና ዳግም እንደ ጠላት መተያየታችንን አቁመን ለጋራ ዓላማ ለአንድ ህዝብ በአንድ ሰልፍ የምንሰለፍበት እንዲሆን እየተመኘን ጥለነው የመጣነው የአሮጌው ዓመት ክፉ እሳቤን እዛው አሽቀንጥረን በአዲስ ዓመት አዲስ እና በጎ እሳቤ በመፍጠር ያ ክፉ ጥቅም አምላኪነት እና ራስ ጠልነት እንዲሁም ቅርብ አዳሪነት መንፈስ የአሮጌው ዓመት ቆሻሻ እሳቤ እና መጥፎ ጠባሳ ሁኖ የመጨረሻ እንዲሆን በፅኑ እንመኛለን፡፡ በመጨረሻም፦ ለፀጥታ ኃይሉ *^^^*^^^*^^^*^*^* ጥሪያችንን አክብራችሁ እኛን አምናችሁ ይህን የከረፋ ስርዓት ጥላችሁ በየአካባቢያችሁ ወይም በቅርበት ካሉ የልጅ እያሱ ኮር ክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ኮሮች ጋር በምስጢር በመነጋገር ስርዓቱን ተፀይፋችሁ እንደምትመጡ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን:: ለሚመለከተው ሁሉ፦ *^^^*^^^***^*^* ልጆቻችሁ ወንድሞቻችሁ ባሎቻችሁ አባቶቻችሁ እንዲሁም በጋብቻም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ቤተሰባዊም ዝምድና ወይም ጉርብትና እና አብሮ አደግነት ያላችሁ በሙሉ ይህንን ጥሪ ለሚመለከታቸው ሁሉ በአስቸኳይ በማድረስ አማራዊ ሃላፊነትቻሁን እንድትወጡ እና ወገኖቻችን ከመንግሥት ጋር ተሰልፈው ተቅበዝባዥ ሆነው ሜዳ ላይ ተጥለው እንዳይቀሩ ለወንድሞቻችን እንድረስላቸው እንላለን፡፡ መልካም የድል ዘመን ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የልጅ እያሱ ኮር የፖለቲካ ጉዳዮች መምሪያ 03/ዐ1/2018 ዓ.ም ከግንባር መረጃዎቻችን በሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk