fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 136
مشترکین
+224 ساعت
+4237 روز
+1 19130 روز
آرشیو پست ها
ሰበር ዜና የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል ሚጦ ዙሪያ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ድባ*ቅ ተመ*ትቶ 11 ሙ*ት 2ፓትሮል ቁስ*ለኛ ታቅፎ ወደመጣበት ተመለሰ ✊ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አጥናፋ ብርጌድ እና የቴውድሮስ ብርጌድ አንድ ሻለቃን በማቀናጀት የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርየ አድማሱ ተህሳስ 23/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ በወገራ ወረዳ ሚጦ ቀበሌ ዙሪያ ባደረጉት አውደ ውጊያ የአገዛዙ ቅልብ ሀይል #አስራ_አንዱን(11) በሙ*ት አጥቶ #ሁለት(2) #መፖትሮል_መኪናና ቁስ*ለኛውን ታቅፎ ገደብየ ከተማ ገብቷል ። የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሰሞኑን ወደ ጎንደሬ በጋሻው ቀጠና በሌሊት በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት የፋኖ ቤተሰብ፣ የፋኖ ደጋፊ፣ የፋኖ አርሶ አደር አደረጃጀት ናቹህ በማለት የጦር መሳሪያቸውን ለመዝረፍና ቤታቸውን ለማቃ*ጠል ከብታቸውን ለመንዳት የሞከረ ቢሆንም የጎንደሬ በጋሻው አባላት ከፍተኛ መከላከልና ማጥቃት ገጥሞት እየተመታና እየተዋረደ ይገኛል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! በአርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ ተህሳስ 24/2018 ዓ/ም

ሰበር ዜና! የአገዛዙ ዘራፊ ሀይል ሚጦ ዙሪያ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር  ድባቅ ተመትቶ ተመለሰ ። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ  ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር  ጎንደሬ በጋሻው  ክፍለ ጦር  አጥናፋ ብርጌድ  እና የቴውድሮስ ብርጌድ አንድ ሻለቃን በማቀናጀት የክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ማርየ አድማሱ   ተህሳስ 23/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ  ሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት  ሰዓት ድረስ  በወገራ ወረዳ ሚጦ ቀበሌ ዙሪያ ባደረጉት አውደ  ውጊያ የአገዛዙ ቅልብ ሀይል      አስራ አንዱን በሙት  አጥቶ ሁለት  መፖትሮል ኪናና ቁስለኛውን ታቅፎ ገደብየ ከተማ ገብቷል ። የአገዛዙ ወንበር  አስጠባቂ  ሰራዊት ሰሞኑን ወደ ጎንደሬ በጋሻው ቀጠና በሌሊት በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ሀብትና ንብረት የፋኖ ቤተሰብ፣ የፋኖ  ደጋፊ፣  የፋኖ አርሶ አደር አደረጃጀት ናቹህ በማለት  የጦር መሳሪያቸውን ለመዝረፍና  ቤታቸውን  ለማቃጠል  ከብታቸውን ለመንዳት የሞከረ ቢሆንም  የጎንደሬ በጋሻው  አባላት  ከፍተኛ  መከላከልና ማጥቃት ገጥሞት እየተመታና እየተዋረደ ይገኛል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!! በአርበኛ  ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ   ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም

ለወጡለት አላማ ውድ የሆነችውን ህይወት መስጠት ከጀግንነትም በላይ ጀግንነት ነው። 🕯🕯 ዝክረ ሰምአታት ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም 🕯 ___🕯🕯____ ቆራጡ ፡ቀኝ አዝማች ይታገሡ አዳሙ እጄን ለጠላት አልሰጥም ብሎ በኩራት ጠላትን እረፍርፎ እራሡን ሠምአት ያደረገ የእኛ ዘመን ዳግማዊ አፄ ቴድሮስ ነው። " ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው ምንይሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው። ታህሳስ 24//2017 ዓ ም የዛሬን ቀን የናደው ክፍለ ጦር ዋና ጦር አዛዥ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አዳሙን በክብር ሰምኣት የተቀበለበት ቀን ነው። ይህ ትግል ለእውነት ሲሉ ከውጣ ውረድ ባለፍ አንድያ ነፍሳቸውን ሰተው አልፈዋል መውደቅን ፣መቁሠልን ፣መድማትን ከምንም የማይቆጥሩት ጀግኖች እንደ ቀኝ አዝማች ይታገሡ አዳሙ አይነት ብዙ ዕልፍ ዐላፍ ለጠላት እጅ መስጠት ነውር መሆኑን የተገነዘቡ ለክብርና ለማንነት መውደቅን ለነፃነት መፋለምን ማሸነፍን ግባቸው ያደረጉ ብዙ ጀግኖች ተፈጥረዋል። ብዙ እልፍ አላፍ ጀግኖች ከትናንት እስከ ዛሬዋ ደቂቃ ድረስ የቀኝ አዝማች ይታገሡ አዳሙን የትግል አደራ ተሸክመው ለቃላቸው እየታመኑ በተኩስ ድምፅ የሚሠክሩ ለሰምኣትነት የተዘጋጁ የትግልን አላማ የትግልን መዳረሻ አውቀውና አስበው የሚራመዱ ጀግኖች ታሪካቸውን በደምና በ አጥንታቸው እየፃፉ የሚልፉ አናብስቶች ተፈጥረዋል። "አይለቀስ በስማቸው አይቀለድ በደማቸው፣ ወደቁ አይላቸውም ያቆሙት ህዝባቸው። ያቆዩልን ንፁህ ስምን ያኖሩልን ነፃ ሀገርን፣ እንጠብቀዋለን ሞተን እየኖርን። ነፃነቱን መርጦ እልፍ ሞት የናቀ፣ ለውነት ተሰልፎ ለውነት የወደቀ። ልክ እንደ ጥንቶቹ እንደጀግኖቻችን፣ ለህዝብ መቆም ነው ምን ጊዜም ትግላችን። ህዝብን የማይጠላ ፅንፈኛ ያልሆነ፣ በመገንጠልን ሳይሆን ባንድነት ያመነ። ሀይማኖት አክባሪ ፍትህ ያስቀደመ፣ በደሙ ነጠብጣብ ሀገሩን ያቆመ። የፅናት ተምሳሌት የነፃነት ጮራ፣ ስማችን ፋኖ ነው ነገደ አምሀራ። ትናንት እነሱ አልፈው በንፁህ ደማቸው ታሪክን ፅፈዋል፣ ጠላት ሞቱ ቢልም በልባችን ማህደር ህያዋን ሆነዋል ። 🕯🕯 ጀግኖች ሁሌም በልባችን ትኖራላችሁ🕯🕯 🕯🕯ታሪክ እናወሳለን ሠማዕታትን እዘክራለን ትግል ይቀጥላል 🕯🕯 ታህሳስ 24//04//18 ዓ ም

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ፊውታራሪ ክፍለጦር በትናንትናው እለት ታህሳስ 22/2018 የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ምዕራብ ጎንደር የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ከተማ ነጋዴ ባህር በማድረግ አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታትና የፋኖ ቤተሰብ፣የፋኖ ደጋፊ በሚል አጀንዳ በሰበባ ሰበቡ ለመዝረፍ እና ጀኖሳይድ ለመፈፀም ወደ ጃኖላ ማርያም እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ነበልባሎቹ የመይሳው ካሳ ልጆች የፊውታራሪ ክፍለጦር ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ በአርበኛ ባበይ በሬ እየተመራ ቀድሞ መረጃውን በመከታተል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ፤ ጠላት ወደ ቀጠናው ከገባ በኃላ ሙት ወረዳ ላይ ከበባ በማድረግ አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ የድረሱልኝ ጥሪ እየቀባጠረ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ እየተዝረከረከ ያሰበውን ሰይጣናዊ ተግባር አንዳችም ነገር ማይደርግ ሳይችል አፍሮና ተቀጥቅጦ ወደ መጣበት ሊመለስ ችሏል። በአውደ ውጊያው የተገኘ ድል: ሙት = 22 ቁስለኛ = 13 የተማረከ 1 ሚኒሻ እስከ ሙሉ ትጥቁ እና 7 የነፍስ ወከፍ ክላሽ ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ ታህሳስ 24/2018 Anid Amhara

🔜 ኮሌኔል ጌትዬ ሸዋ ምድር ላይ ላይመለስ ተ-ሸ-ኝ-ቷ-ል💪
🔜 ኮሌኔል ጌትዬ ሸዋ ምድር ላይ ላይመለስ ተ-ሸ-ኝ-ቷ-ል💪

እናንተም "ካላጠፋናችሁ መኖር አንችልም" ትሉናላችሁ፤ እኛም የመጥፋት አደጋ ተጋርጦብናልና ካልጠነከርን፣ ካልተደራጀን፣ ካልመከትን፥ ሊያጠፋን፣ ሊያወድመን፣ ከታሪክ ማህደር ሊሰርዘን አለብን ብለን እና
+1
እናንተም "ካላጠፋናችሁ መኖር አንችልም" ትሉናላችሁ፤ እኛም የመጥፋት አደጋ ተጋርጦብናልና ካልጠነከርን፣ ካልተደራጀን፣ ካልመከትን፥ ሊያጠፋን፣ ሊያወድመን፣ ከታሪክ ማህደር ሊሰርዘን አለብን ብለን እናምናለን። ስለዚህ እኛን ለማጥፋት፤ በቅድሚያ እነዚህን አናብስቶች ማለፍ ይጠበቅባችኋል። "ጥሩ ትዘላለህ፣ ነገር ግን ከዚህ አታመልጥም!" እንደተባለው ማለት ነው። እኛም ደግሞ እንድህ በማለት እንናገራለን፥ እኛም አንጠፋም፣ እናንተም አትጥፉ፣ ለሁሉም ይበቃል፣ ምን ይባላል ጥ'ፉ!!! *ምን ያደርጋል ክፉ!* ክፉ ከነ ክፋቱ ይኑር ይባላልኮ ጎበዝ። ምን ይሰራል መጠፋፋት። መሬቱ እንደሆነ፣ ሰፊ ነው። ሰው ነው ያጣነው። መሬቱ የጠበበን የመሰላችሁ አእምሮአችን ውስጥ በተቀመጠው Negative አስተሳሰብ ነው።

ፍትሕ ሚኒስትሯ “በማንነትና በፖለቲካ አቋም ብቻ ፍርድ ቤት ያቆምነው ሰው የለም” ስትል በአማራ ሕዝብ ላይ ተሳለቀች! በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ግለሰቦች የፍርድ ሂደት መጓተት በፓርላማ ጥያቄ አስነስቷል። ጥያቄው የተነሳው ዛሬ ሐሙስ ታህሣሥ 23/2018 ዓ/ም በተካሔደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር የተባለው የበይነ መረብ ሚዲያ ዘግቧል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር አበባው ደሳለው “ከ2 ዓመት ከ6 ወር በላይ” ታስረው የሚገኙ የአማራ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ላይ ላቀረበው ክስ የፍትህ ሚኒስቴር ማስረጃ “ማቅረብ ባለመቻሉ ፍትህ አጥተው” እንደሚገኙ አመልክተው፡ ሚኒስቴሩ ማስረጃና ምስክር ማቅረብ ካልቻለ ክሱን “እንዲያቋርጥም” መጠየቃቸውን ዘገባው አመላክቷል። ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጠችው የፍትሕ ሚኒስትሯ ሐና አርዓያስላሴ “በማንነትና በፖለቲካ አቋም ብቻ ፍርድ ቤት ያቆምነው ሰው የለም” ስትል በማንነቱ ምክኒያት በተገኘበት ሁሉ እየተሳደደ በጅምላ በሚታሰረው የአማራ ሕዝብ ላይ ስትሳለቅ ውላለች። አዲስ አበባን ጨምሮ የአማራ ሕዝብ በክልሉና ከክልሉ ውጭ በተገኘበት ቦታ እየተሳደደ በጅምላ መታሰሩና ይሄው የጅምላ እስር ለሁለት ዓመታት ተባብሶ መቀጠሉን መረብ ሚዲያ ከዚህ ቀደም በሰራቸው ዘገባዎች ለሕዝብ ማድረሱ አይዘነጋም። የማቆያ ቦታዎች ሁሉ ሞልተው፡ የነጋዴዎችን ሼድና የእህል መካዘኖችን በመከራየት በርካታ ንፁኋን ወገኖች በማንነታቸው ተለይተው በጅምላ የሚታጎሩባት ሀገር የፍትህ ሚኒስቴር ምኒስትሯ "በማንነቱ አስረን ፍርድ ቤት ያቆምነው አንድም ሰው የለም" በሚል በሕዝብ ላይ "ምን ታመጣላችሁ" አይነት ስላቅ መሳለቋን ነው መረብ ሚዲያ ምክር ቤቱ ካሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል የተመለከተው። "ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ይቀዳል" እንዲሉ ማንነታቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በገፍ ታስረው እስከ ቶርችና አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸውና ፍትሕ አጥተው እየተንገላቱ እያለ፡ ነገር ግን "በማንነቱ አስረን ፍርድ ቤት ያቆምነው ሰው የለም" በሚል የተዘባበተችው የፍትሕ ሚኒስትሯ ሐና አርዓያስላሴ፡ የትዳር አጋሯ የሆነው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ደግሞ፡ አገዛዙ ድሮንና ሌሎች የጦር መሣሪያዎችን ተጠቅሞ በአማራ ክልል በንፁኋን የሚፈፅመውን የዘር ፍጅት ለመደበቅ ሎቢስቶችን ቀጥሮ የገፅታ ግንባታ ለማሰራት ሲሞክር ታይቷል። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና ነገሩ በሕግ ማስከበር ስም በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ስላለው ጭፍጨፋ አለም አቀፉ ማሕበረሰብ እየተገነዘበ ነው።

ስለሌሎች መኖርን የተማርንባቸዉ አማራዎች!!! " ለራስ ቅድሚያ የመሰጠት አስገዳጅ ተፈጥሯዊ ባህሪን አሸንፈው ለአማራ ህልውና ትግል ራሳቸውን አሳልፈው ከሰጡ ጀግኑች መካከል ፦ 1 አስር አለቃ ኤፍሪም አጥናፉ እና 2 ፋኖ አዲሱ ቢተውን የመጀመሪያዎች ናቸው። እኔ በብዙ መንገድ ሳስበው የእውነተኛ የዓላማና የትግል ሰው መሆናቸው የተገነዘብሁት በተወለዱበት ቀጠና ጎጃም አገው ምድር አከባቢ ስስ የፓለቲካ እሳቤ ያለበት እንደመሆኑ መጠን ማንም እኔነኝ ያለ ፓለቲከኛ የማይረዳውን የፓለቲካ እሳቤ ተረድተው ቀድመው ነቅተው አከባቢው ለማንቃት የሄዱበት ርቀት በጣም የሚገርም የሚደንቅ ነበር።እኔና ኤፍሬም አጥናፋ በሰኔ15ቱ አብረን ታስረን በነበርን ጊዜ ስለአከባቢው የትግል ሁኔታ መክረን ነበር ከዚያም አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፋ ፍ/ቤቱ ነፃ ተብሎ ከስር ቤት ከወጣ በኃላም ከአማራ ህዝባዊ ሀይል አመራሮች መካከል አርበኛ ጥላሁን አበጀን እንዲያገኛው በማድረግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሬለት ነበር። እሱም ለትግል ካለው ፍላጎት እና ተነሳሽነት አንፃር በአማራ ህዝባዊ ሀይል ስም በተለያዩ ከተሞች ወጣቶችን ወታደራዊ ስልጠና እንዲያሰለጥን በአርበኛ ዘመነ ካሴ እውቅና ተሰጦት ወጣቶችን በማሰልጠን ትግሉን እንዲቀላቀሉ ያደረገ ጀግና ነው ።በዚህ የስልጠና ወቅትም ወደ ጎጃም አገው ምድር ዳንግላ አከባቢም ስልጠና ማስጀመር እንዳለበት እኔንና ጓዶቹን እሰር ቤት ከተፈታ በኃላ ለመጠየቅ በመጣበት ወቅት ደግመን ተነጋግረን በተነጋገርነው መሰረት ወደ ዳንግላ አከባቢው አቅንቶም ከአገኛቸው የትግል አጋሮች መካከል አንዱ ፋኖ አዲሱ ቢተው ነው። እነዚህ ሁለት ወንድሞቼም በአከባቢው ለወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና መሰጠት ጀመሩ።አሰር አለቃ ኤፍሪም አጥናፉና ፋኖ አዲሱ ቢትዉ ሁለቱን ለየት የሚያደርጋቸው ተፈጥርሯዊ የሆነው የሰው ልጅ ለራሱ ቅድሚያ የመስጠት አስገዳጅ ተፈጥሯዊ ባህሪን አሸንፈው፤ ይብዛም ይነስም ለመርህ ተገዝተው ፤ዝቅ ብለው ወጣቱን ለማሰልጠን በመወሰን ያነቁትን ወጣት ፤የወጡትን የወረዱት መከራና ስቃይ ሳስብ ለእኔ ልዩ የትግል አርማ ናቸው።! ለከፈላችሁት መሰዋትነት ሁሌም በአማራ የህልውና ተጋድሎ ስም ሲንዘክራቸሁ እኖራሉን። ለወደቃችሁለት የተቀደስው ዓላማችሁ ዳር ለማድረስ የድርሻችን ለመወጣት ቃላችን አክብረን በቃላችን ተገኝተን እየታገልን እያታገልን እንገኛለን። ትግላችን ቀራኒዎ ድረስ ነው። ዝክረ ሰማዕታት ለጀግኖቻችን። @highlight አርበኛ ስለሺ ከበደ

ዲሽቃ ጠምዶ ሲሮጥ የነበረው መኪና ከነ ወታደሩ ተዘይሯል::ኮሌኔሉም ተከርብቷል። መገን ሸዋ መርሓቤቴ አውራጃ ደራ‼️ ሽመልስ ንጉሴ 23/ዐ4/2018 ዓ.ም

የአማራን ህዝብ ጥቃት ለመከላከል የወሰንነው ከዛሬ 15 አመት በፊት ጀምረን ነው ። ወደ ተግባር የገባነው 🔥 አርበኛ ዘመነ ካሴ 💪
የአማራን ህዝብ ጥቃት ለመከላከል የወሰንነው ከዛሬ 15 አመት በፊት ጀምረን ነው ። ወደ ተግባር የገባነው 🔥 አርበኛ ዘመነ ካሴ 💪

አድነታችን ኋይላችን ነው አንድነት የሰው ልጅ ለተመሳሳይ አላማ እና እቅዶችን ይዞ ከተነሳ አሸናፊነትን የበለይነትን ለመውሰድ አንድ መሆን መብት ሳይሆን ግዴታ ነው ። የአማራ ፍኖ ሁሉም ሰው ከሞቀ ቤቱ የወጠነው ለነፃነት እና ለፍትህ ነው ። ስለዚህ በአንድ ተሰባስቦ ድርጅት መስርቶ በመርህ እና በአሰራር ተደራጅቶ በአንድ የእዝ ሰንሰለት መጓዝ ግዴታ ነው ። አንድ ስንሆን ሀይልም ብርታትም ይኖረናል አሸናፊም እንሆናለን ይሄም በመረዳት ሰፊ ሀሳብን ይዘን እየተጓዝን አንድ ሆነን ሀሳባችንን ማሳካት ግድ ይለናል። አማራ ያልታገለበት ትግል የለም ስለሆነም አንድነት ላይ መስራት ይጠበቅብናል ። እስከ አሁን አማራ የራሱ ድሮጅት ባለመኖሩ በጀምላ ተረሽኗል ፣ተፈናቅሏል ፣ ንብረቱን ተዘርፋል እዲሁም በጀምላ ተደፍሯል ይህ ሁሉ በደል ሲደርስበት ቅሬተውን ሊቀርብበት የሚችል ድርጅት አለመኖሩ ነው ። ስለሆነም መደራጀት ማሸነፍ ግዴታ ነው ። አማራው የራሱ ህልውና አደጋ ሲጋጥመው ሊቆረቆሮ የሚችል ድርጆት ያስፈልገዋል ። ይሄን በመረዳት የአማራ ፋኖ ተሰባስቦ ድርጅት መስርቶ ብልፅግናን ብናሸንፍም የተመሠረተው ድርጅት የአማራ ህልውና ጠባቂ ሆኖ መቀጠል አለበት አንድ መሆን ግዴታ ነው ያልኩት ከዚህ በመነሳት ነው። የአማራ ፋኖ ብሶት የወለደው የጀግና ስብስብ እደሆነ ይታወቃል እናም አፋብኋ እና አፋህድ ሁለቱ ድርጅቶች ቤታቸውን ዘግተው ወደ አንድ መተው ወጥ ድርጅት ከተመሰረተ የአማራን ትግል የሚደግፍ ሁሉ አድነቱን ሲሰማ ሁሉም ሰው ሻማ ያበራል ። በዚህም ትግል መሰዋትነት እየከፈሉ ያሉ ታጋዎች የውስጥ ደስታቸው ፈቅሎ በመውጣት በአለም አደባባይ ደስታቸውን እደሚገልፁ ሙሉ እምነት አለኝ ። በዙዚህ ትግል የተሰው የጀግኖች ቤተሰቦችም አንድነቱን ሲሰሙ የለበሱትን የሀዘን ልብስ እደኩራት ያውታል ምክንያቱም ቤተሰቦቻችን የተሰውለት ትግል ዳር ይደርሳል ብለው ተስፋ ይኖራቸዋል ትግሉም ሲጠናቀቅ ጀግንነት እና አሸናፊነት ይሰማቸዋል ስለዚህ የአንድነት ጠቀሜተውን ዘርዝሮ መግለፅ ይከብዳል። የቆሰሉት ወድሞቻችን አንድነቱ ሲመጣ በተሰውት አጥንት እና ደም መሰዋትነት በኛ መቁሰል ነው አንድነቱ የመጠው በማለት ይደሰታሉ ። እየታገልንም ያለነው ለመሞት እና ለመቁሰል እራሳችንን አዘጋጅተን እጠብቃለን ስለሆነም ይሄን በመረዳት አንድ መሆን አስፈላጊ ነው። ሁሌም አማራነት አርበኛ ኤፍሬም ባዩ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን ሰጠ!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው። ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦ *የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ *ጓዳዊ ዝምደና *ባህል እና ጨዋነት *ድርጅትና የድርጅት ምንነት *የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች *ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ  በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር  የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት  በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር አባላት በስልጠናው የአማራን የሞኖር ነፃነት በቅርቡ እንዲሚያበስሩ እርግጠኛ እየሆኑ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሚሰጣቸውን ማነኛውምንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ  የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው ታህሳስ 23/04/2018 ዓ.ም