ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 363
مشترکین
+5424 ساعت
+2347 روز
+1 43730 روز
آرشیو پست ها
ታጋይ ይሞታል ትግል ይቀጥላል።
በጀመርነው የህልውና ትግል 30 ወራትን እያስቆጠርን ቢሆንም አለምን ያስደመሙ አያሌ ሁነቶችንና፤ በርካታ ድሎችን ብናስመዘግብም ትግል ነውና ብዙ ፈተናዎችንም አስተናግደንበታል።
ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲሉ የሞቀ ቤታቸውንና ኑሯቸውን ትተው በዱር በገደሉ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አይተኬ የሆነውን ውድ ህይዎታቸውን ገብረውበታል። የአማራ እናቶች ያፈራቻቸው ጀግና አርበኞች በደማቸው ደማቅ ታሪክ እየፃፋ ካለፉ በርካታ አርበኞች መካከል የቴዎድሮስ፤የሚኒልክ፤ የበላይ፤ የአሳምነው አናብስቶች ፋኖዎች እነ አስራት ወልድየስ፤ እነ ናሁሰናይ፤ አርበኛ ውባንተ የመሳሰሉ እልፍ ጀግኖችን ያጣን ቢሆንም በደማቻው የለኮሱት የትግላችን ሻማ ወደኋላ ላይመለስ ከትናንት በበለጠና በተፋጠነ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ጀግንነትን ከአባቶቹ የወረሰው የሚኒልክ የአስራት ወልድየስ ግብርን የተላበሰው ውጊያ ሲገባ ሳቅ ሳቅ የሚለው የትግል አባልኑ ሳይወጣ የማይሸሽ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፈለ ጦር የሰብር ሻለቃ ምክትል አዛዥ የነበር በአሁኑ ስዓት የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የቃኘች አዛዥ የጦሩ ገበሬው ዝምተኛውና አመለ ሸጋው የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የነበረው ሸጋው ግርማ በተወለደባት ቦታ ካራለጎማ ለሁለት ስዓት(2:00) ያህል ከአማራ ጠሉ አብይ አህመድ ጡት ቆራጭ አስጠባቂ አረመኔያዊ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ መደበኛ ውጊያ ከወንድሞቹ ፋኖ ጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የብልፅግናን መከላከያ 103ኛ አየር ወለድ ኃይል ሙት እና ቁስለኛ አድርጎ በመጣል በቀን 02/04/2018 ዓ.ም ውድ አንድዬ ህይወቱን ለአማራ ህዝብ ሰውቶ አልፈዋል።
ለተሰዋው ጀግናችን የዋሁ የአማራ ነፃነት የሚናፍቀው ሸጋው ግርማ ነፍስህን ልዑል እግዚአብሔር በአፀደ ገነት ያሳርፍልን። ለሰማዕቱ ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች በሰባት ለሰባ ክፍለጦር የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንመኛለን።
በስተመጨረሻም ውድ የሰባት ለሰባ አባላትና አመራሮች ሀዘናቹሁ ሀዘናችን ስለሆነ ያጣናውን ታጋይ ወንድማችን አርበኛ እንደ ስሙ ሸጋው ግርማን ከእንግዲህ የማናገኘው ስለሆነ ሰራዊቱን በማፅናናት የጀመርነውን ትግል ከግብ ለማድረስ ማሰልጠንና ማደራጀት የግድ ስለሆነ እንደነ ሸጋው ግርማ ያለ ጀግኖችን የምንፈጥርበት ሰዓት ይሆናል ።
ታጋይ ይሞታል ትግል ይቀጥላል።
@@ ታላቅ ስቦ የማስከዳት ዜና @@
የአረመኔው የአገዛዙ ሰራዊት ዛሬም እየፈረሰ የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀለ ይገኛል
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
በአፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የአገዛዙ ክ/ጦር የአገዛዙ የጉጅሌው የዝርክርኩ ብርሀኑ ጁላ ና የአብይ አህመድ ዙፋን አሰጠባቂ ጦር እየፈረሰ የጀግኖች የፋኖ ኃይሎችን እየተቀላቀሉ ይገኛል
በዛሬው ዕለትምየአረመኔው ጡት ቆራጭ የአገዛዙ ወታደሮች በገፍ እየፈረሱ ወደ ፋኖ ኃይሎች እየተቀላቀሉ ነው
በዛሬው ዕለትም ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም በምስ/ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ እንደቀንድ አውጣ ጭንቅላቱን በአንድ ኪ.ሜ ራዲየስ ቀብሮ መሽጎ ከሚገኝበት ቁይ ከተማ
1.ይስማው ማስሬ
2.ሙባረክ ሙህዬ
ከ6ኛ 602ኛ ኮር 52ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት ውስጥ ጡት ቆራጩን የአገዛዙን ሰራዊት በቃን በማለት 24ኛ ክ/ጦር የደባይ ጮቄን ሻለቃ በክብር ተቀላቅለዋል!!በ24ኛ ክፍለ ጦር ውስጥ ስቦ ማስከዳትን እንደ አንድ የትግል መርህ በመውድ ስናይፐር የቡድን መሳሪያን ጨምሮ በዚህ ወር ብቻ ከ14 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት ወደ 24ኛ ክ/ጦር የፋኖ ኃይሎች መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው!!!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ
Hailemariam Kiber Temesgen
አፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ከጎንደር ከተማ አዲዘመን ከተማ ዋና መንገድ ለ6 ቀናቶች ዝግ መሆኑን እናሳውቃለን።
ከአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር
የተላለፈ ጥብቅ መልዕክት
ፋሽስታዊውን የዓብይ አገዛዝ በመገርሰስ ህልውናችን ለማረጋገጥና መላ የሀገሪቱ ህዝቦች በነፃነትና በእኩልነት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር እፎይ ብለው የሚኖሩበትን አውድ ለማንበር ከጭፍጨፋ እና ስደት የተረፈውን ህዝባችን በማስተባበር አስከፊውን የዓብይ አገዛዝ እያፈራረስነው እንገኛለን።
በጦርነቱ የአማራ ፋኖን ማሸነፍ እንደማይቻል ተገንዝቦ ተስፋ የቆረጠው ቀቢፀኛ የዓብይ ቡድንና ተላላኪዎቹ ህዝባችን የሚያማርሩ የዘረፋና የእገታ ወንጀሎች እንዲፈፀሙ ለከሃዲዎች ግልፅ ስምሪት በመስጠትና በተለያዩ ስልቶች ለስርዓት አልበኞችና ወንበዴዎች ምቹ
ሁኔታ በመፍጠር እንዲሁም ወታደራዊ ከለላ እየሰጠ ወገናችን በእጅ አዙር ለማሰቃየት ታትሮ እየሰራ መሆኑ ታውቆ በተለይም ከጎንደር ከተማ ጠዳ ክ/ከተማ እስከ አዲዘመን በሚገኙ ልዩ ልዩ ቦታዎች ተላላፊ ተሳፋሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ የውንብድና ተግባር እንዲፈፀሙ እያደረገ የቆየ መሆኑ ይታወቃል።
የሰሜን አማራ ቀጠና ግንባር ትግልን ለላቀ ውጤት ለማብቃት ዕዛችን በላይ ዘለቀ ዕዝ ህዳር 30/2018 ዓ.ም በይፋ አውጆ የጀመረውን "ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄ" በመደገፍ ኮራችን ወደ ተግባር መግባቱን እያሳወቅን የማጥራት ተልዕኳችን አካል የሆነ በዳ/ቴዎድሮስ ቀጠና ስር የሚስተዋሉ ተላላፊ ተሽከርካሪ ላይ ዘረፈና ስርቆት በሚፈፅሙ የህዝባችን ጠላቶችና የትግላችን ሳንካ ወንበዴዎች ላይ የማጥራት ስምሪት የሚደረግ በመሆኑ ከጎንደር ከተማ አዲዘመን ከተማ ዋና አስፓልት አውራ ጎዳና ከ ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም ወላዶችና ፅኑ ህሙማን ከጫኑ አምቡላንሶችና ተሽከርካሪዎች ውጭ እስከተጠቀሰው ቀን መንገዱ ዝግ የተደረገ መሆኑን እናሳስባለን።
የተላለፈውን የመንገድ መዝጋት መመሪያ ተላልፎ ለመንቀሳቀስ የሚሞክር ማንኛውም አካል ሊደርስ የሚችል አደጋና ኪሳራ ኃላፊነቱን ራሱ የሚወስድ ይሆናል።
ጥልቅ ማጥራትና ማብቃት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጎንደር/አማራ /ኢትዮጵያ
#ከአፋብኃ_ምዕራብ_አማራ_ቀጠና_ቴዎድሮስ_ዕዝ_201ኛ_ኮር__64ኛ_ክፍለ_ጦር_ህዝብ_ግንኙነት_የተላለፈ_መልዕክት
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
በ64ኛ ክፍለ ጦር በምናስተዳድረው ቀጠና ሸበል በረንታ እና እነማይ ወረዳ በቅርብ ቀን በእነማይ ወረዳ ቢቸና ዙሪያ ሰርገን ገብተናል የተሳካ ኦፕሬሽን ሰርተናል እያሉ በውሸት የማህበራዊ ሚዲያ ስርጭት የሚያሰራጩ፣የሚያራግቡ እና የሚያናፍሱ አካላት ፍፁም ታማኝነት እና አመኔታ የሌለው በመሆኑ በ64ኛ ክፍለ ጦር ስር ካሉ "5"ሬጅመንቶች ውስጥ በአዲሱ አደረጃጀት #1ኛ_ጠቅል_ሻለቃ_እምባል የሌለ መሆኑን እንገልፃለን።
በመሆኑም በ64ኛ ክፍለ ጦር የሚደርጉ የትኛውም አይነት ኦፕሬሽኖች፣ የህዝብ ውይይቶች እና ሌሎች መሰል ተግባራት በክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ሰንሰለቱን ጠብቆ ለ201ኛ ኮር እና ቴዎድሮስ ዕዝ መርጃዎች በወቅቱ ደርሰው ለህዝባችን እና ለጦራችን ሰንሰለታቸውን ጠብቀው የሚዲያ ሽፋን እያገኙ ይገኛሉ።
ማሳሰቢያ:-
በድርጅት የሚዲያ አጠቃቀም ህግ መሰረት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት የውጊየም ይሁን የህዝብ ውይይት መሰል መድረኮች በተለያዮ የሐሰት #የFacebook አካውንቶች የሚራገቡት ፍፁም ተቀባይነት እና ውሸት መሆናቸውንን ለድርጅታችን፣ ታጋዩቻችን፣ ደጀኑ ህዝባችን እንዲሁም የአለማቀፍ ማህበረሰብ እውቅና እንዲኖረው በአክብሮት እንገልፃለን።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
መሪ ማለት የተመሪዉን ፍላጎት የሚረዳ ዉጤት ለማምጣት ማንኛዉንም ነገር ከፊት ሆኖ የሚጋፈጥ አርዓያ የሚሆን ነዉ
ወቅቱ አንድነትን የሚፈልግ ነዉ
ወቅቱ በአንድነት መቆም የሚያስፈልግበት ነዉ #አንድነት አ_ን_ድ_ነ_ት
አንዳንዱ ከነክብሩ ወደ ፋኖ ይቀላቀላል ፤ አሻፈረኝ የሚሉትን ደግሞ ከቦ በመውቀጥ በዚህ መልኩ ገቢ ይደረጋሉ።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የዘመኑን ውድ መሳሪያ ታጥቆ ፋኖን መገዳደር የተሳነው ብልፅግና በሳይበር ሚሊሻ ጩኸት ወንበር ሊያፀና መንደፋደፉን ቀጥሏል።
ከሰሞኑን የብልፅግና ባለስልጣናት አዲስ የFb ሀሰተኛ ገፆችን ስምሪት ለመስጠት በርካታ ወጣቶችን መልምሏል።
ለዚሁ ርካሽ ተግባር የተመለመሉ የእነማይ እና ሸበል በረንታ ወረዳ ሳይበር ሚሊሻ ስም ዝርዝር እና አድራሻ እጃችን ላይ ደርሷል።
ከእለት ጉርስ ለማይዘል የደም ገንዘብ ብላችሁ የውሸት ተባባሪ ለመሆን የተመዘገባችሁ ወንድሞቻችን ከዚህ አሳፋሪ ተግባር የማትቆጠቡ ከሆነ ድርጅቱ ለሚወደው እርምጃ ኃላፊነቱን የምትወስዱ ይሆናል።
መውጫ:-
የትግሉ ደጋፊ ሆናችሁ በሀሰተኛ ገፅ የምትጠቀሙ እህት ወንድሞቻችንም በመተማመን ላይ የተመሰረተ መረጃ ለመለዋወጥ እና ኃላፊነትን ለመውሰድ ያመች ዘንድ በትክክለኛ ስማችሁ ብትጠቀሙ ይመረጣል።
+3
"አማራው ዱላ እንኳን እንዳይዝ በተከለከለበት በዚህ ዘመን ከዜሮ ተነስቶ እራሱን አደራጅቶ እራሱን አስታጥቆ ዛሬ የገጠመውን የህልውና አደጋ በመከላከል ላይ ይገኛል።
በውጊያ ውስጥም እያለ በርካታ የቁርጥ ቀን ልጆቹን ሰልጥኖ ለግዳጅ ዝግጁ እያረገ ይገኛል። ብልፅግናን ፍርክስክሱ በማውጣት ከሻለቃ እስከ ብርጌድ ከብርጌድ እስከ ክፍለጦር፣ ኮርና እዝ ድረስ ሃይል እየሰበሰቡ በየአውደ ውጊያው ጀብዱ የሚፈፅሙ ልጆች እየመሩ ያሉ ጀነራሎች።
"ምስል፦የአማራ ህዝብ ጠበቃ የአፋብኃ ጀነራሎች……!!"
ዘመነ የወንድምነት የውኃ ልክ ነው!
ከድተኸው የማይከዳ፣ ጠልተኸው የማይጠላ፣ ሸንግለኸው የማይሸነግል፣ አሳምመኸው መታመሙን ችሎ የአንተን ሕመም የሚፈውስ፣ ዘወትር ከራሱ ማዶ፣ ከዛሬ ባሻገር፣ ከጎጃምነት ብቻ ሳይሆን ከዐምሓራነት አድማስ ተሻግሮ ሰፊ ደርዛም ሐሳቦች ያሉት ሰው በዚህ ዘመን ጥራ ብትሉኝ አፌን ሞልቼ የምናገርለት አርበኛ ዘመነ ካሤ ነው። በዚህ ትግል ውስጥ የእርሱን ያክል ቻይ፣ ታጋሽ አስታዋሽ አለኝታ ማግኘት መታደል ብቻ ሳይሆን መባረክም ነው። "ነቢይ በሀገሩ አይከበርም" የሚለው ቃል ሙሉ በሙሉ መተግበሪያው እኛ ዘንድ ሆኖ እንጂ ዘመነ ከሌሎቹ ወገን ቢሆን ብየ ሳስብ አሁን ለእርሱ የምንሰጠውን ቦታና ይሁንታ አስቤ አፍራለሁ።
ሰውን ማክበር ማምለክ አይደለም፣ መሪን መፍጠር ማክበርና ማስከበር የብልህና መልካም ምግባራዊ ማኅበረሰብ መለያ ነው። ባለፈው እንዳልሁት መሪን የሚፈጥረው ማኅበረሰብ ነውና ሳንፈጥረው ተፈጥሮ ያገኘነውን መሪ እንስማው፤ እንከተለው፤ እንጠብቀው። እርሱ ተናግሮት ያልተፈጸመ፣ አስቦት ያልሆነ ነገር ቢኖር እኔን ጨምሮ በዙሪያው ባለን ወንድሞቹ ደካማነት ብቻ ነው። እናም ይኸንን የውኃ ልክ የመሠረታችን ሁሉ መሠረት እናድርገው። የዚህን ትግል ሂደት ስኬትና ትግዳሮት የተዋናዮችንም ማንነት ከዘመነ በላይ የተረዳ ወይም ተረድቶ እየሠራ ያለ አካል አለ ብየ አላውቅም። ኢትዮጵያዊ ባህል፣ ጀግንነት፣ ከጓዳዊነት ያለፈ ወንድምነት፣ መንፈሳዊነት፣ ሰብአዊነት፣ አልሸነፍም ባይነት፣ ተሰሚነት፣ ደፋርነት፣ መፍትሔነት፣ ዕውቀት፣ ዕውቀት መሻት፣ ርኅራሔ፣ ቅንነት፣ አርቆ ማሰብ፣ ሰፊ ራእይ የምታይበት ሰው እርሱ ዘመነ ነው። ዘመነን የሚጠላ ሰው ሳይ በግሌ ዐምሓራንና የዐምሓራን ትግል የሚጠላ መስሎ ስለሚታየኝ ደግሜ ላየው አልፈልግም።
ወዳጆቼ መቼም እንደ ዐምሓራ እንደዚህ ወቅት የተፈተንበት ጊዜ የለም፤ በዘመናዊት የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ዘመንም እድል በሯን ከፍታልን አታውቅም። ይህ ዘመን ካወቅንበት ወደ ልእልና መውጫ ካላወቅንበት ወደ ጥልቁ መዝቀጫ ነው። በዚህ ትግል ጭቆናና እድል መገፋትና ድል ተጣምረዋል ባይ ነኝ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተቀያያሪ ሁነትና ስሜት አለበትና ትግል በባህሪው ስስ ነው። ትግሉ የብዙዎች ሲሆን ደግሞ ብዙ ስሜቶች፤ ብዙ ዕይታዎች ብዙ ፍላጎቶች ብዙ ወሳኞች ተዋናይ ስለሚሆኑ ሂደቱ ቀላል አይሆንም። በዚህ ምክንያትም ያላግባብ ዋጋ መክፈል ከዚያ ሲያልፍም የታቀደለትን ግብ መሳት እድልን ማበላሸት ሊመጣ ይችላል። በእርግጥ አሁን ላይ በግሌ ይህን ያክል የሚያሰጋ ሁነት ባላይም በተለይ የጋራ ማንነታዊ፣ ትውልዳዊ፣ ጓዳዊ፣ ወንድማዊ ስሜትና እውነትን ማስረጽ ላይ ያልተሠሩ ሥራዎች እንዳሉ ይሰማኛል። ጎንደርና ሽዋ ቤተ ዐምሓራና ጎጃም ላይ ብቻ ተወስኖ መታገል ወደፊት ለመራመድ አብሮም ለመሄድ ስለማያስችል የሰፋውን እያጠበቡ፣ የተወጠረውን እያረገቡ፣ ያበጠውን ከማፈንዳት ይልቅ አላልቶ በማፍረስ ሕዝባዊ ዘለቄታዊ ልእላዊ የሆነ የማይቀለበስና የማይመለስ ተጋድሎን ማድረግ የግዴታ ውዴታ ነው።
ይህ ሲባል በይድረስ ይድርሰ በድርምስምስ፣ በትርምስምስ ያለአግባብ፣ ያለአዋጭ ትልምና ጎዳና ባልተሰላ እሳቤ በተራ እንንክብካቤ እየተሻሹ አንድ መሆን ማለት አይደለም። በዚህ መከራና እድል በተቀላቀሉበት ትግል ውስጥ ሴረኞች ሰርጎገቦች ጥቅመኞች ሠርገው ገብተዋል። እነርሱን መጠበቅና መለየት ግዴታ ነው። ተሠርቶ ከመፍረስ ውሎ አድሮ መሠራት ይሻላል።
በዚያም ላይ ቅንነትና ጀግንነት ያላቸው ግን ስሌት ስልትና እውቀት የሚጎድላቸው በአንጻራዊ አውንታ የሚታዩ ባለቤቶችም አሉ። እነርሱም ከራሳቸው አቅምና ማንነት ጀምሮ የጉዞውን ስፋት ጥልቅት ተግዳሮትና ክብደት መረዳት አለባቸው። የተረዳውም ተረጋግቶ አቅፎ ደግሞ ማስረዳት ይጠበቅበታል። እናም ድሉም እድሉም እንዳያልፈን እየተሳሰብን እንራመድ፤ በአንድ ዐምሓራዊ ማንነታችን እንዋደድ፤ አስተዋይ ስነ ልቡና ቅን ሰብእና እንዲሁም ሕዝባዊ ቁመና ለእያንዳንዳችን ሊኖሩን የሚገቡ አዋጭ ማንነቶች ናቸው።
ቂም፣ ጥላቻ፣ ጥርጣሬ፣ ፍራቻ ፣ አሉባልታ፣ ከንቱ ውብራታ፣ ወሬኛነት፣ ቡድናዊነት፣ ርካሽ ራስ ወዳድነት፣ ባንዳነት፣ አስመሳይነት፣ ግብታዊነት፣ ተላላኪነት ያሳደገን የወለደን ሕዝብ መገለጫዎች አይደሉምና ከእኛ ይራቁ። ቅን እናስብ ስልታችንና ስሌታችን በጠላቶቻችን ላይ ብቻ ይሁን። ወንድሜ ወንድምህን እመነውና ይክዳህ። ወንድምን መጉዳት ወንጀል እንደሆነ ወንድምን መጠርጠርም ወንጀል ነው።
ዘመነ የወንድምነት የውኃ ልክ ነውና እርሱን መሠረት እናድርገው።
Banteamlak Ayalew Abate
+2
የ14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጠላት ላይ ታላቅ ድልን ተጎናጸፈ!
ታኅሳስ 02/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ የሠራዊት አባላት በዘራፊው የብልጽግና ሠራዊት ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል።
የአርሶ አደሩን ሰብል ለመዝረፍና የማሕበረሰቡን ቤት ለመበርበር በጠዋቱ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ቀበሌ ያመራውን የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት ጀግኖቹ የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ፋኖዎች አስቀድመው ደፈጣ ጥለው በመጠበቅ ከጠዋት ጀምረው እስከ ምሽት ድረስ የቋያ እሳት ክንዳቸውን ሲያሳርፉበት ውለዋል።
ሻለቃዋን በትኛታለሁ እያለ ተረቱን ሲነዛ የነበረው የብልጽግና ሠራዊት ከተጠና የከተማ ኦፐሬሽን እስከ መደበኛ የውጊያ ጥበብን የተካኑት ጀግኖቹ ጠላትን በልሳነ አፈሙዝ ሲያናዝዙት ውለው አምሽተዋል።
ከደንባ እስከ ሊባኖስ ባካለለው ቀጠና በተደረገው ውጊያ ከፍተኛ መናበብና አስደናቂ የውጊያ ጥበብ የታየበት ከመሆኑም በላይ ምሽጎች ከመሰበራቸውም በላይ በርካታ ቁጥር ያለው ጡት ቆራጩ የምርኮኛው ጁላ ሠራዊትና ሆዳም አድማ ብተና እንደ ቅጠል ረግፎ ቀርቷል።
በውጊያም
➠ ሶስት ምሽግ ተሰብሯል
➠ አንድ የአድማ ብተና የሻለቃ አመራር ተደምስሷል
➠ ከ37በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል
በአሁኑ ሰዓትም ጠላት መድፍ እያስወነጨፈ ይገኛል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
#አገዛዙ_በቢቸና_ከተማ_የሐሰት_ወሪ_የሚነዙ__የfacebook_አርበኛ_ሰራዊት_ማዘጋጀቱን_አረጋግጠናል።
ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም
በእነማይ ወረዳ ቢቸና ከተማ የሚገኘው ሆድ አደር የብአዴን አመራር በ64ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ጠንካራ አመራሮች እና የፋኖ አባላትን ለማህበረሰባችንን እና ለትግሉ ደጋፊ የተሰሳተ የሐሰት መረጃ ለማድርስ እና ለመመረዝ በቢቸና ከተማ በአገዛዙ የብአዴን አመራሮች የወር ደሞዝ የተመቻቸላቸው ግለሰቦችን ማዘጋጀቱን አረጋግጠናል።
በቢቸና ከተማ ከአማራነታቹህ ይልቅ ሆዳቹህ የበለጠባቸው ግለሰቦች የውሸት #የfacebook አካውንት በመክፈት የሐሰት መረጃ ልታደርሱ የተዘጋጃቹህ ግለሰቦች ሙሉ ስም ዝርዝር እና ልትሰሩት የተሰጣቹህ ትዛዝ ዝርዝር በእጃችን የገባ ስለሆነ በተራ ገንዘብ የታለላቹህ ግለሰቦች ከእንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ እንድታቆሙ ስንል በጥብቅ እናሳስባል።
በመሆኑም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ትዛዝ ተላልፋቹህ የሐሰት መረጃ የምታሰራጩ ከሆነ የግለሰቦችን ስም ዝርዝር ይፋ በማውጣት በግለሰቦቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑንን በጥብቅ እናስጠነቅቃለን።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ታሳስ 02/2018 ዓ.ም
፻ አለቃውን ጨምሮ 37 የጠላት ሰራዊት በጅበላ ሙተራ ሻለቃ ተደመሰሱ።
ታህሳስ 2 /2018 ዓ.ም
ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ ወደ ሊባኖስ ደምባ የተንቀሳሰው ጠላት በ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ በተደረገ ታላቅ ትንቅንቅ የአረመኔውን ሰራዊት ድባቅ ተመቷል።
ከአነጋጉ 12:00 ጀምሮ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ የጅበላ ሙተራ ሻለቃ በጥልቀት በፈፀመችው የማጥቃት ውጊያ የጠላትን ተደራራቢ 3 ምሽጎች በመስበር ጠላትን 7 ሰዓታት በመፋለም በየ ምሽጉ አጋድማዋለች።
ከደንባ ደብረ ማርቆስ ከተማ ማረሚያ ቤት ድረስ እያጣደፉ ጠላትን ያራገበችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ 37 የጠላት ሰራዊት ጨምሮ ከዘራ ይዞ ሲያዋጋ የነበረውን ፻ አለቃ በስናይፐር ጭንቅላቱን በስተው ጥለውታል።
እንደ ንስር ታድሳ በቁጭት ጠላትን የተናነቀችው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ያለምንም መስዋትነት በጠላት ላይ ድል የተቀናጀች ሲሆን እስከ ምሽት 1:00 ስዓት በወሰደው አውደ ውጊያ አስክሬን ማንሳት ያልቻለው የአረመኔው ስርዓት ከደብረ ማርቆስ ከተማ መድፍ እየተኮሰ ይገኛል ።
በመልሶ ማደራጀት ትግበራው በ206ኛ ኮር እጁ የተቆረጠበት ጠላት ጅበላ ሙተራ ሻለቃን ሶስት ጊዜ ለማጥቃት የሞከረ ሲሆን በዛሬው ትንቅንቅ ጥቃቱን መቋቋም አቅቶት 4 ኪ.ሜ ወደ ኋላ ሲፈረጥጥ በርካታ አስክሬኖችን ማንሳት አልቻለም ።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+2
የፋሽስቱ አብይ አህመድ አገዛዝ ብልፅግና የጥፋት ቡድን ሰሜን ሸዋ ዞን በግሸ ወረዳ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት በመፈፀም የ1ኛ ደረጃ ህፃናት ተማሪዎችን ገደለ::
የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በሰሜን ሸዋ ግሸ ወረዳ ልዩ ቦታው ደል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፈጸመው የድሮን ጥቃት በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ሁለት ተማሪዎች ሲሰው በርካቶች ቁስለኛ ሆነዋል::
የፋኖን ሐይል በአውደ ውጊያ ማሸነፍ ያልቻለው የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን በደል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ታህሳስ 02/2018 ዓ.ም ከጧቱ 5:00 የፈጸመው የድሮን ጥቃት ለህጻናት እንኳን የማይራራ መሆኑን በተግባር አሳይቷል::
በዚህ የድሮን ጥቃት አንድ የመማሪያ ክፍል ሙሉ በሙሉ ሲወድም ከ10 በላይ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቆስለው ወደ ህክምና ተወስደዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ ደሴ ዙሪያ ቀናቶችን ባስቆጠረ ተጋድሎ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
ምኒልክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ በደሴ ዙሪያ ወረዳ እያደረጉት ያለው ከባድ ተጋድሎ ዛሬ ታህሳስ 4/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን ጠላት ከፍተኛ የሚባል ሰብዓዊ ኪሳራ እያስተናገደ ተጋድሎው በድል ታጅቦ አሁንም እደቀጠለ ነው::
ህዳር 29/2018 ዓ.ም በደሴ ዙሪያ ወረዳ ሞቴ ከተማና አስግዶ ላይ ከባድ ጉዳትና ኪሳራ የደረሰበት ሚሊሻና የደሴ ፖሊስ በዲጋሜ ህዳር 30/2018 ዓ.ም የመከላከያ ሰራዊት ሚኒሻና ፖሊስ ጥምር ዙፋን ጠባቂ ጦር በ4 አቅጣጫ ከደሴ ከተማ በአስግዶና ሞቴ -በጉጉፍቱ አጥት መስበሪያ - በቆላ ገራዶ - በጓሳ ሜዳ ከኩታበር -በተንታ አጅባር በአራቱም አቅጣጫ ፋኖን ይዞታውንና ቀጠናውን አስለቅቃለሁ ብሎ የገባው ጠላት ባሰበው ልክ ሳይሆን በተቃራኒው በየጫካውና በየጉድጓዱ አስከሬኑ ወድቆ ቀርቷል::
በዚህም ጠላት ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን በየቦታው ወድቆ የቀረበትን አስከሬን ለማሳትና ለማውጣት ሌላ ተጨማሪ ሃይል እያስገባ እዛው እደገባ ሳይመለስ ይሄው ዛሬ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል:: ተጋድሎው አሁንም ተጠናክሮ እደቀጠለ ነው! ዝርዝር ቁጥራዊ መረጃውን በቀጣይ የምናደርስ ይሆናል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም
