ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 641
مشترکین
+2024 ساعت
+3787 روز
+1 08530 روز
آرشیو پست ها
ዛሬ 👌 የክብር ካባ የማረፊያ ትከሻዋን አገኘች!!
ጉምቱው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ (አባ ድፈን) በተተኪው የፋኖ አርበኛ የክብር ካባ ተደርቦለታል።
ረጅም ዕድሜ ጋሼ🙏🙏🙏
+3
#ሴት_ፋኖ፦ #የትግሉ_ሞተር፣ #የነፃነቱ_ማገር አርበኛ ፋኒት ፍቅርተ
የታሪክ ማህደር ሲገለጥ፣ የድል አውድማው ሲቃኝ፣ በጀግንነት ስም ዝርዝር ውስጥ የሴት ፋኖ አሻራ የጎላ ነው። እርሷ ለትግሉ ድምቀት ብቻ ሳትሆን፣ መላውን እንቅስቃሴ ወደፊት የምታስፈነጥር "ሞተር" ናት።
በአንድ እጇ ቤቷን፣ በአንድ እጇ ነጻነቷን የጨበጠችው ሴት ፋኖ፤ በቁጭት ስትነሳ ተራራ የምታንቀጠቅጥ፣ ስትራመድም ምድርን የምታናውጥ የጽናት ተምሳሌት ናት። ሰንቀው ለሚዘምቱት ወንድሞቿ ስንቅ ብቻ ሳትሆን፣ ለውጊያው ወኔ፣ ለድሉም ተስፋ የምትዘራ የብርታት ምንጭ ናት።
የእርሷ የትግል ሞተርነት በሁለት መልክ ይገለጣል፦
#በግንባር፦ እንደ ጥይት ተኳሽነቷና እንደ ስትራቴጂ ነዳፊነቷ፣ ጠላትን የምታስበረግግ ቆራጥ ተዋጊ ናት።
#በጀርባ፦ እንደ እናትነቷና እንደ እህትነቷ፣ የትግሉን ማገዶ አቀጣጥላ፣ ተስፋው እንዳይከስም የምታደርግ የህልውና ዋስትና ናት።
#ሴት_ፋኖ ስትታጠቅ፣ ትጥቁ የብረት ብቻ ሳይሆን የሞራልና የማንነት ጭምር ይሆናል። እርሷ በሌለችበት ትግል ውስጥ ትንፋሽ የለም፤ እርሷ ባልቆመችበት አውድማ ላይም ፅናት አይታሰብም። በእውነትም፣ የነፃነት ጉዞው ጋሪው ህዝብ ከሆነ፣ ያንን ጋሪ አድካሚውን ዳገት አስወጥታ ለድል የምታበቃው ብቸኛዋ ሞተር "ሴት ፋኖ" ናት!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር የሴት ጅግና ታጋይ አርበኛ ፋኒት ፍቅርተ
በራያ ቆቦ ከተማ ሽብርና ውጥረት ነግሷል!
በከተማዋ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ተጀምሯል።
ዛሬ የካቲት 14/2018 ዓ/ም ማለዳ በከተማዋ ወዛደር ተራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጉልበት ሰራተኞች በዱላ እየተደበደቡ በተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ወታደራዊ ካምፕ ተወስደዋል።
የራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች ልጆቻቸውን ጨምሮ ሙሉ ቤተሰባቸውን ወደ ኮምቦልቻና ደሴ እንዲሁም መውደ አዲስ አበባ እያሸሹ መሆኑ ታውቋል።
በአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለጦር ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ የኮማንዶ ምረቃ ወቅት የኮሩ ም/ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 50 አለቃ ደሞዝ ግርማ ለምሩቅ የሠራዊት አባላት ያስተላለፈው መልዕክት!!
ውድ የአማራ ልጆች፣ የዛሬ ጀግኖች፣ የነገ አሸናፊዎች
ዛሬ እናንተ በምትመረቁበት ቀን ለኔና ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአማራ ህዝብ የኩራት ቀን ነው። እናንተ በዚህ የሥልጠና ጊዜ ያሳያችሁት ፅናት፣ ትጋትና ራስን ለመሠዋትነት የማዘጋጀት መንፈስ የሚደነቅ ነው።
ኮማንዶ በአካልና በስነልቦና ጥንካሬ የዳበረ በመከራ የታሸ ወታደር ነው። የማወራው ስለ አንድ ልዩ የሠው ልጆች ወታደራዊ ክፍል ነው።የሚንቀሳቀሱት በጨለማ ውስጥ፤
የሚታገሉት በዝናብና በጭቃ፤ ሚተኙት በበረዶና በቋጥኝ ላይ ነው።ኮማንዶ ወታደር ብቻ አይደለም፤ ኮማንዶ ማለት ልዩ ወታደራዊ ስልጠና የወሠደ፣ ለከፋ ተልዕኮ ዝግጁ የሆነ፣ በአእምሮም በአካልም ጠንካራ የሆነ ተዋጊ ነው።ኮማንዶዎች በሌሊት ጨለማ፣ በጥቅጥቅ ጫካ፣ ሽው ባለ በረሀ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጥላዎች ናቸው። በዝናብ፣ በበረዶ፣ በተራራማ አካባቢም ሆነ በምድረ በዳ ማንም በማይደርስበት ቦታ ወታደራዊ ተልዕኮ ሰዓት እነርሱ ይደርሳሉ። የማይቻል ነገር የላቸውም። ምክንያቱም ኮማንዶ ማለት በማይቻል ሁኔታ ውስጥ መቻልን የሚፈጥር ጀግና ነውና።
ይሄ የሚሰራው በጓዳዊ መደጋገፍ መሆኑ መረሳት የለበትም። እናንተን ልዩ የሚያደርጋችሁ ሌላኛው ነገር በመካከላቸው ያለው ወንድማማችነት ነው። ኮማንዶ ብቻውን አይዋጋም። ከጎኑ ካለው ጓዱ ጋር ጋር አብሮ ይዋጋል። ከጓዱ እምነት ይጥላል፣ ለጓዱ እምነት ይሰጣል። ኮማንዶ ለወንድሙ ሲል ሕይወቱን ለመስጠት ዝግጁ የሆነ ነው። ኮማንዶዎች ኃይልን የሚያገኙት ከጓዳዊ እምነት፣ ፍቅር፣ አንድነት ነው።
ሌላኛው ኮማንዶ ማለት ራስን መሥዋዕት ማድረግ ማለት ነው። ከቤተሰብ፣ ከልጆች ፣ ከወዳጅ ጓደኛ መራቅን ሊጠይቅ ይችላል። ምክንያቱም እነርሱ የሚጠብቁት ነገር ከራሳቸው ህይወት ይልቅ ትልቅ መሆኑን ያውቃሉና። የሚጠብቁት ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ሰላምን ነው።
እናንተ አሁን የአማራ ፋኖ ኮማንዶ አባላት ናችሁ ናችሁ። ማዕረጋችሁ ቀላል አይደለም። ከዚህ ማዕረግ ጋር ጭቁኑን ህዝብን የመጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነትና ግዴታ አብሮ ይመጣል። እናንተ ከዛሬ ጀምሮ የአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ነውርና ጥቃት ለማስቆም ክብሩን ለማስመለስ ቃል የገባችሁ ወታደሮች መሆናችሁን አስታውሱ።
ህዝባችን፣ ቤተሰቦቻችን ዛሬ ላይ ደርሶ በከፋ መከራ ውስጥ ይገኛሉ። መብቱ እየተጣሰ፣ ንብረቱ እየተዘረፈ፣ ልጆቹ እየተፈናቀሉ፤ እርስቱ የጋጠወጥ መፈንጫ፣ ከብቱ የሽፍታ ቀለብ፣ቤቱ የምድር አራዊት ዋሻ፤ የልጆቹ ስጋ የሠማይ አሞራ ሲሳይ ሆኗል።
ይሄንን በህዝባችን ትከሻ ላይ የተጫነውን የመከራ ቀንበር የማንሳቱ ትልቁ ድርሻ በናንተ ላይ ይወድቃል።
አሁን በሥልጠናችሁ ወቅት የተማራችሁት እውቀት ጠላትን ለመግታት፣ ሕዝብን ለመጠበቅ፣ ተራራና ገደልን በእግራችሁ ለመለካት የምታውሉበት ጊዜ ከፊታችሁ ይጠብቃችኋል። አሁን ጊዜው ያንን ዕውቀት በተግባር ለማዋል ነው።
በነዚህ ከባባድ ወታደራዊ ወስልጠናዎችን ወስደው በፊቴ ከተደረደሩ ኮማንዶዎች ፊት ስቆም የማየው በስርዓት የተደረደሩ ወታደሮችን ብቻ አይደለም።
:የማየው ህዝብን የማዳን ሕልምን ነው።
:የማየው የአሸናፊነት ተስፋን ነው።
:የማየው ሠውነት ወርድና በቁመት ልክ የተሞላ ጀግንነትን ነው።
:የማየው የማይታመስ ጽናትን ነው።
:የማየው የማይናወጥ ቁርጠኝነትን ነው።
:የማየው በልበሙሉነት ለህዝብ ሊከፈል የተዘጋጀ መሠዋትነትን ነው።
:ሁላችንም ልናይ የሚገባው ህዝባቸውን የሚያፈቅሩ ልጆችን ነው።
አንድ ነገርን አትርሱ። በመከራ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻችሁም፤ እንደጅረት የፈሰሰውም ደምም እናንተን ተስፋ ያደርጋል።
እነኝህ በፅናት ከፊትለፊታችን የቆሙ ወታደሮች የተጣለባቸውን ወታደራዊ ስልጠናዎችን በሚገባ መወጣታቸውን በማረጋገጤ ቦኔት እንዲለብሱ ፈቅጃለሁ።
50አለቃ ደሞዝ ግርማ
የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር ም/ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
+7
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ከፍለ ጦር ዐሥር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ሻለቃ ልዩ ኮማንዶዎችን አሰመረቀ።
206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በሉማሜ ከተማና በፀድ ማርያም ከተማ ባደረገው አውደ ውጊያ 28 ጠላት በመደምሰስ ድል መቀናጀቱን የኮሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የካቲት 14/ 2018 ዓ.ም
=====================================
የአረመኔው ሰራዊት ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ከሉማሜ ከተማ በመነሳት በጨንደፎ ፅድ ማርያም የ34ኛ ክ/ጦር አሃድ የሆኑትን ሻለቆች ለማጥቃት ማቀዱን ተከትሎ የጠላትን እቅድ ለማክሸፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው 34ኛ ክ/ጦር በሉማሜ ከተማ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ባደረገው የማጥቃት ውጊያ የጠላትን ቅስም የሰበረ ድል አስመዝግቧል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀን 8:25 በተደረገው የማጥቃት ውጊያ 34ኛ ክ/ጦር በሉማሜ ከተማ የመሸገውን የጠላት ኃይል በጨበጣ በመፋለም ውጊያውን በድል ያጠናቀቁ ሲሆን 18 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሲደመሰሱ 9 የሚሆኑት ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሁነዋል።
በሌሊት የማጥቃት እቅዱ በተፈፀመበት ጥቃት የከሸፈበት ጠላት ከቀኑ 8:00 ሰዓት ወደ ፅድ ማርያም የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጠላትን ለሁለት ስዓታት የተፋለመው 34ኛ ክ/ጦር 10 በመደምሰስ እና 8 ከባድ ቁስለኛ በማድረግ በሌላኛው የመከላከል ውጊያ ያለምንም መስዋትነት የጠላትን ቅስም ሰብሯል።
ከጠዋቱ ጀምሮ ለ7 ሰዓታት በተለያዩ ግንባሮች አስደናቂ ትንቅንቅ የፈፀመው 34ኛ ክ/ጦር የጠላትን የመድፍና የሞርተር የዘ-23 ፍንዳታዎችን በመቋቋም እግረኛ ሰራዊቱን ሲያናውዙት የዋለ ሲሆን ከቁይና ከደብረ ማርቆስ እንዲሁም ከአምበር ከተሞች ድጋፍ ሰጭ ሰራዊት ጠላት እንዳይንቀሳቀስ ገዥ ቦታ በመያዝ የጠላትን ትስስር የቆረጠችው 24ኛ ክ/ጦር በ206ኛ ኮር ጦር አዛዦች የተሰጣትን ተልዕኮ በመቀበል ከሌሊት ጀምሮ ግዳጇን ባግባቡ ፈፅማለች።
ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከፈተበት ድንገተኛ ጥቃትና የመከላከል ውጊያ ሲፍረከረክ የነበረው ጠላት ከየትኖራ ባስወነጨፈው መድፍ 6 የቤት እንስሳትን በመግደልና የአንድ አርሶ አደር ቤት ከማውደም ውጭ በወገን ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም። የጠላትን አስክሬን እና ቁስለኛ ሲያንገዛግዙ የነበሩ አምቡላንሶች ከሉማሜ ሆስፒታል በተጨማሪ በደብረ ማርቆስ እና ደጀን ሆስፒታሎች ከባድ ቁስለኞችን ሲያመላልሱ ማምሸታቸውን ያሳወቀው የ206ኛ ኮር ወታደራዊ መምሪያ በዛሬው ተጋድሎ 28 የጠላት ኃይል ተደምስሰው 18 የሚሆኑት ከባድና ቀላል ቁስለኛ መሆናቸውን ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የአገዛዙ ሰራዊት በጥምር የጎንደር ዕዞች ተመታ!!
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክፍለ ጦር ሁሉም ብርጌድ በተሳተፋበት ውጊያ ትልቅ ድል ተገኘ❗
========================
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር፦
✅ጉና ክፍለ ጦር ሙሉ ስራ አስፈፃሜ፣
✅የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ስራ አሰፈፃሜ፣
✅የጉና ክፍለ ጦር 5ቱም ብርጌዶች(እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ፣ ገ/መሥቀል ብርጌድ፣ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ፣ አንዳቤት ብርጌድና መቅደላ አምባ ብርጌድ
✅ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
እና
የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፦
✅ተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር በጥምረት በሰሩት አኩሪ መቀናጀት ትልቅ ድል ተመዝግቧል።
የብርሃኑ ጁላ አራዊት ሰራዊት ጥምር ጦር መነሻውን ደብረታቦር ከተማ አድርጎ ሌሊት ጀምሮ ወደ ክምር ድንጋይ አቅጣጫ የወጣው የጠላት ሃይል አርሴማ፣ ጋሳይ ፣ ዘበራ እና ክምር ድንጋይ በተባሉ ቦታዎች በተደረገ አውደ ውጊያ የጀግኖች ምድር ክንደ ነበልባሎች ወሳኝ ቦታዎችን ቀድመው በመያዝ ከጠዋቱ 2:25 ጀምሮ እስከ ምሽት 12:30 ድርስ በተደረገ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ሁለት ፖትሮለል ቁስለኛ መጠኑ በውል ያልታወቀ ሙት በየ መንገዱ ሲያንጠባጥብ ውሏል።
በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ለጊዜው 2 ብሬን እና 2 M14 የቡድን መሣሪያዎች ከጠላት በምርኮ ሲገኙ፣ 1 ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ተደርጎ ተመትቷል። ክላሽና ሌሎች የምርኮና የተተኳሽ መሣሪያዎች እንደደረሱን እናቀርባለን። ሌሎች መረጃዎችም በተመሣሣይ ይደርሳሉ።
በዚህ ውጊያ ጉና ክፍለ ጦርና ተራራው ራሥ ጉና ክ/ጦር የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን👊
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክ/ጦር ሕ/ግ ክፍል
ፋኖ መምሕር ያሬድ
+3
ሰበር ጎንደር !!!
የሶስት ኮር ባሉ የክፍለጦር ሻለቃወች ጠላት ወደ ክምር ድንጋይ ለመግባት ሞክሮ Zu 23 ጨምሮ በዘፈቀደ እየተኮሰ ሲገባ ከ 50 በላይ የሚሆን ሃይሉ ከጥቅም ውጭ ሆነበት ✊✊
እንኳን ክምር ድንጋይ መግባትና መመለስ እንዳይችል ተደርግ ተከቧል። ዙ 23 ተመቶ ነዷል !!
እስከ አሁን ብዙ ነፍስ ወከፍን ጨምሮ፣ ብሬን፣ ስናይፐርን እጅግ ብዙ ተ#ተ#ኳ#ሽ ምርኮ ተገኝቷል።✊✊
ፋኖነት ✊✊
አማራነት✊✊
ብሩህ ተስፋ✊✊
ይካቲት 14/2018ዓ,ም
የብልፅግና ሠራዊት እየፈረሰ ነው !!
የአብይ አህመድ ጨፍጫፊ ሠራዊት ተሰፍ ቆርጦ እየተበታተነ ይገኛል ። አ ፋ ብ ን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ቀጠና ባህር ዳር ዙርያ ወረዳ ይጎዲና ሰቀለጥ ከመሸገው የጠላት ሃይል መካከል በዛሬው ዕለት13 የመከላከያ አባል እና 10 አድማብተና አባል በድምሩ 23 የጠላት ሀይል ከድቷል ።
ከእነ ዚህም መካከል
👇🏻
1ኛ አቢቹ አየለ
2ኛ ቸርነት ታደለ
3ኛ መንግስቱ ታደሰ
4ኛ ሙክታር አብደላ
5ኛ ጌታው አለበል
እና ሌሎች
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ።
ክፋት ለማንም !
በጎነት ለሁሉም !
አ ፋ ብ ን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የ35ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ ከብልግና ሰራዊት በመክዳት ፋኖን ተቀላቀለ!
በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ በመርሳ ዙሪያ ገንቦ በር መሽጎ የተቀመጠው የአገዛዙን ስርአታዊ መዋቅራዊ የሴራ አካሄድ ስላበሳጨኝ እና መዋቅሩ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት የተነሳ ስለሆነ ወደ ወንደሞቸ ሄጀ የአቅሜን ላግዝ ከነ ሙሉ ትጥቄ መጥቻለሁ ሲል ገልፆልናል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምኒልክ ዕዝ ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ደምሌ መኮነን
የካቲት 14 2018 ዓ ም
አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጉና ክፍለ ጦር ሁሉም ብርጌድ በተሳተፋበት ውጊያ ትልቅ ድል ተገኘ❗
========================
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር፦
✅ጉና ክፍለ ጦር ሙሉ ስራ አስፈፃሜ፣
✅የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ስራ አሰፈፃሜ፣
✅የጉና ክፍለ ጦር 5ቱም ብርጌዶች(እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ፣ ገ/መሥቀል ብርጌድ፣ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ፣ አንዳቤት ብርጌድና መቅደላ አምባ ብርጌድ
✅ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና
የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ፦
ተራራው ራሥ ጉና ክፍለ ጦር በጥምረት በሰሩት አኩሪ መቀናጀት ትልቅ ድል ተመዝግቧል።
የብርሃኑ ጁላ አራዊት ሰራዊት ጥምር ጦር መነሻውን ደብረታቦር ከተማ አድርጎ ሌሊት ጀምሮ ወደ ክምር ድንጋይ አቅጣጫ የወጣው የጠላት ሃይል አርሴማ፣ ጋሳይ ፣ ዘበራ እና ክምር ድንጋይ በተባሉ ቦታዎች በተደረገ አውደ ውጊያ የጀግኖች ምድር ክንደ ነበልባሎች ወሳኝ ቦታዎችን ቀድመው በመያዝ ከጠዋቱ 2:25 ጀምሮ እስከ ምሽት 12:30 ድርስ በተደረገ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ ሁለት ፖትሮለ ቁስለኛ መጠኑ በውል ያልታወቀ ሙት በየ መንገዱ ሲያንጠባጥብ ውሏል።
በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰ ሲሆን ለጊዜው 2 ብሬን እና 2 M14 የቡድን መሣሪያዎች ከጠላት በምርኮ ሲገኙ፣ 1 ዙ-23 ከጥቅም ውጭ ተደርጎ ተመትቷል። ክላሽና ሌሎች የምርኮና የተተኳሽ መሣሪያዎች እንደደረሱን እናቀርባለን። ሌሎች መረጃዎችም በተመሣሣይ ይደርሳሉ።
በዚህ ውጊያ ጉና ክፍለ ጦርና ተራራው ራሥ ጉና ክ/ጦር የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል።
በላይ ዕዝ
ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
አገዛዙ ጥምር ሀይል እያለ የሚጠራው የጠላት ሀይል ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰበት
===========
በዛሬው ዕለት በቀን 14/06/2018 የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር #አራተኛ ሻለቃ በሦስት አቅጣጫ ከሶንቶም፣ ከቁጭ ከተማ እና ከብርሸለቆ ተወጣጥቶ ወደ ቁጭ አክሲዮን የመጣውን የሚሊሻና የመከላከያ ስብስብ ወራሪ ግምባር ግምባሩን በማለት ወደ መጣበት አንገት አስደፍታ መልሳዋለች፡፡
የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር #አራተኛ ሻለቃ ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6፡00 ሰዓት ባደረገችው እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያ ጠላት ከ15 በላይ ሙትና በርካታ ቁስለኛውን ታቅፎ እንዲመለስ አድርጋዋለች፡፡
ወራሪው የስርዓቱ ወምበር ጠባቂ ሀይል #በአራተኛ ሻለቃ የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው የአንድ ታጋይ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት አቃጥሎ ወደ መጣበት እግሬ አውጭኝ በማለት ተመልሷል።
👉የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ክንደ ነበልባሉ 77ኛ ክ/ጦር ከመልሶ ማደራጀቱ በኋላ በአንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ በማክሰኝን፣ፍኖተሰላም ከተማ ፣ቡሬ ውንድጊ እና ቁጭ አክሲዮን ከአራት ጊዜ በላይ መደበኛና የደፈጣ ውጊያ በማድረግ በርካታ የጠላትን ሀይል በመደምሰስ ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 14/2018ዓ.ም
