ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 414
مشترکین
+1324 ساعت
+277 روز
+1 21530 روز
آرشیو پست ها
አፋብኃ ሰሜን አምሐራ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጥቅምት 17/2018ዓ.ም
01.የአማራ ፋኖ በደራ ምድር ያገኘው ዕንቁ ድል❗
✅ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር(04 ብርጌዶች፦ አሣምነው ብርጌድ፣ ቴዎድሮሥ ብርጌድ፣ ናኹሰናይ ብርጌድ እና ገብርዬ ብርጌድ)
✅ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የሁሉም ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚዎች እና አፈርዋናት ብርጌድ
✅ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚዎች እና የገብረ መሥቀል ብርጌድ ተዋጊዋ ጣይቱ ሻለቃ
👉የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት የአማራ ፋኖን ለማጥቃት ከአርብ ገበያ እሥከ ሳና ዕቅዶችን አውጥቶ በሌሊት ሲንቀሳቀስ መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ ሳና ከተማ መውጫ ላይ ባደረገው ደፈጣ ከሌሊቱ 11:00 ላይ ጠላትን አሳፍሮ መልሷል።የአገዛዙ ጭራቅ አራዊት ሰራዊት በደራ ምድር ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ ሙሉ ቀን እንደ ገብሥ ታጭዶ፣ ተከምሮ ሢወቃ ውሏል። የጠላትን ቅሥም ቀድማ በሌሊቱ የሰበረችው የትናንቷ ፈረሰኛው ሻለቃ የአሁኗ ውባንተ ሻለቃ ነች። ሳና ሚካኤል ላይ የጠላት ኃይል በነበልባሎቹ ተደምሥሧል፤ ቆሥሏል።
👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከቴሌ እሥከ ቆሚሣ፣ ከሊባኖሥ እሥከ እሥላም መቃብር ደፈጣ ይዞ ነበር። ከቆሚሳና ከእሥላም መቃብር መካከል ካለው ተራራ''ቸሮ'' ላይ ጭራቁ የአቢይ ወታደር ወደ ቆሚሳ ሲጓዝ በተቃራኒው የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ወደ ገላውዴዎሥ ሢንቀሳቀሥ መሐል መንገድ ላይ ተገናኙ። የአቢይ መከላከያ ከተራራው አናት የውቤ ልጆች በታች። መብረቅ የመታው የመሰለው የአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አለኝ ያለውን ሁሉ የመሣሪያ ዓይነት አዘነበው። ከሌሊቱ ንጋተ 11:30 ልብና ትጥቅን የታደሉት ውባንታዊያን ጠላትን በጨበጣ እንዳልነበር አድርገውታል። ጨዋታው ወደ ቦምብ ውርዋሮሽ ተቀይሯል። አይበገሬዎቹ አምሐሮች የውባንተ የግብር ልጆች ቦምብን በቦምብ መልሰዋል፣ ጠላትን አምበርክከዋል፣ የጠላትን ምቹ ቦታ ተቆጣጥረዋል። የውጊያው አድማሥ ሰፍቶ በቆሚሳ፣ ቸሮ፣ ደረባ፣ ሊባኖሥ፣እሥላም መቃብር፣ ያያ ሚካኤል ሙሉ ቀናትን ከፍተኛ ተጋድሏን ሢያደርጉ ውለዋል። ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የሞራል ሥብራትን አድርሷል። ብዛት ያለው ጠላትን ደምሥሧል። ብዛት ያለው ጠላትን አቁሥሏል። መሣሪያዎችን በዓይነት ማርኳል። አያሌ የጠላት ምሽጎችን ሰባብሯል። ከተማውን አሥለቅቋል።
በዚህ እልህ አሥጨራሽ የጨበጣ ውጊያና መደበኛ ውጊያ ጠላትን ሢፋለሙ ውለውና ሢማርኩ ውለው የጠላት ምሽግ ላይ ጠላትን ተፋልመው በጀግንነት የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችን 02 ናቸው።በጀግንነት ተፋልመው የተሰው ዕንቁ ወንድሞቻችንም አርበኛ መልካሙ ጠጋዬ(ኩርሲ) እና አርበኛ አቢዮት መኳንንት ናቸው።
👉ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ፣ ንሥር ሻለቃ፣ አፈርዋናት ብርጌድ በአርበኛ ክንዳለምና አርበኛ ታደለ ምሬ እየተመራ፣ ጣና ብርጌድ ሥራ አሥፈጻሚ፣ ጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ/ ገብረ መሥቀል ብርጌድ/አናብሥቷ ጣይቱ ሻለቃ በኢንጅነር አበራ እና በዘመቻ መልሰው እየተመራ ሁሉም በጥምረት ከገብርዬ ተራራ ጀምረው ያያ ሚካኤል፣ እሥላም መቃብር፣ ሞሻ፣ ገላውዴዎሥ ከተማ እና ዙሪያ ገባው ላይ ጠላትን ከጀርባ በመምታት ለወንድሞቻቸው ደርሰዋል። በዚህ የተናበበ ውጊያ ጠላት አንደኛው ኃይል ለሌላኛው ኃይል እንዳይደርሥ ተደርጎና ሰንሰለታቸው ተቆርጦ በተፈለገው መንገድ ተገርፈው፣ ተደምሥሠውና ቆሥለው ውለዋል። ከቀኑ 11:00 ጀምሮም ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር በሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከገረፈው የተረፈው ኃይል አምልጦ ወደ አርብ ገበያና አምበሣሜ ሢፈረጥጥ የገላውዴዎሥ ቴሌ ላይ ባደረጉት ደፈጣ ጠላት በደምብ እየተመታ ይገኛል።
👉የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሥራ አሥፈጻሚ በተዋጊው አርበኛ አመኑ ዓለምአንተ እየተመራ፣ የጉና ክፍለ ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ወንዱ አንተ አሰፋ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ሥራ አሥፈጻሚ በአርበኛ ጋሻዬ እንግዳ እየተመራ፣ የጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር/አፈርዋናት ብርጌድ/ውባንተ ሻለቃ በጥምረት ከሳና ከተማ፣ ሐዋርያት አቦ፣ ሚካኤል፣ ቴሌ፣ ኳንኮይ ገብርኤል፣ ቸሮ እና እሥላም መቃብር ድረሥ በፍጹም አንድነትና ቅንጅት ጠላትን ሢገርፉ ውለዋል። ይህኛው የጠላት ኃይልም የውባንተ ጦር ላረገፈው የጠላት ኃይል ድጋፍ እንዳይሰጥ አድርጎታል። ሳና ከተማ በጀመረው ውጊያ ጠላት የኔ ያለውን አሥከሬን ሳይቀብርና ቁሥለኛ ሣይይዝ ወደ እንጦሮጦሥ ተወርውሯል። የሆድ ዘመዶቹንም ድጋፍ እንዳይሰጥ ተደርጓል። ታሳቢ ያደረጋቸው ዕቅዶቹም በዜሮ ተባዝተውበታል።
02. እሥቴ/መካነ ኢየሱስ ከተማ
ጉና ክፍለ ጦር፦
👉እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ
ጥቋቁር አናብስቶቹ እሥቴ ዴንሳ ብርጌዶች በጉና ክፍለ ጦር ወታደራዊ አዛዡ አርበኛ አዛዥ ደሣለኝ እና በብርጌድ መሪዎቹ በአርበኛ ብርቃዬኹ ደምሴ እና አርበኛ አብራራው እየተመራ ከቀኑ 9:30 መካነ ኢየሱስ ከተማ በመግባት የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂዎችን እያምበረከኩ እሥከ ምሽት ድረሥ ውጊያ አድርገዋል። ምሽት 12:10 መካነኢየሱስ ከተማ በእሥቴ ዴንሳ አናብስት ተሞሽራለች። ከተማው ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥርም ሆኗል። ቆሪጥ የተባለችው ሆድ አደር ባንዳም እግሬ አውጭኝ ሥትል ወደ ደብረ ታቦር ፈርጥጣለች።
👉አንዳ ቤት ብርጌድ
ጭራቁ የአቢይ አሕመድ አራዊት ሰራዊት ከወለሽ ከተማ ተነሥቶ ወደ ጃራ ገዶ ከተማ ለእኩይ አላማው ሢንቀሳቀሥ በእሳት ተፈትነው ያለፈው አንዳ ቤት ብርጌድ የአገዛዙን ዘመቻ መሪ ጨምሮ 05 የአገዛዙን ዕድሜ አርዛሚዎች ሸኝቷቸዋል። የአንዳ ቤት ብርጌድን ክንድ መቋቋም የተሳነው የአገዛዙ ዕድሜ አርዛሚ ቡድን ንጹሐን አርሶ አደሮችን በጅምላ አሥሯል፣ ገድሏል፣ ሰብላቸውንም አውድሟል።
በመጨረሻም በምሥር ወጥ የተሸጠው በለጠ አንዳርጌ(ቆራጡ) ከቀኑ 8:00 ግንዳ ጠመም ላይ ያለውን የመብራት ትራንሥፎርመር በሥናይፐር ተኩሶ በመምታት አንድዶታል። በድርጊቱ የተበሳጨው የእሥቴ ሕዝብም በብሥጭት ወደ አደባባይ ወጥቷል።
ድላችን በተባበረ አምሐራዊ ክንዳችን❗
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ሀቅአለው ፀጋ አለባቸው
የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አዲሱን የቡልጋ ክፍለ ጦር መሰረተ
===============
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በከሰም ክ/ጦር ስር የነበሩ ፊት አውራሪ አስማረ ዳኘ ብርጌድና እና ተስፋ ብርጌድ በመቀናጀት የቡልጋ ክፍለ ጦርን መስርተዋል::
ይህም ክፍለ ጦር የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ የተቋማቱን የሰው ኃይል የፋይናንስ እና መሳሪያ ክምችት መሰረት ያደረገ አደረጃጀት እንዲሰራ ያስተላለፈውን መመሪያ በማሟላታቸው ተረጋግጦ ነው::
ክፍለ ጦሩ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል÷ የዕዙ አመራሮች÷ የቀድሞው ከሰም ክፍለ ጦር÷ የነበልባል ክፍለ ጦር ÷ የኃይለ ማሪያም ክፍለ ጦር አመራሮች እና የፋኖ አባላት በተገኘበት ነው::
በዚህ የቡልጋ ክፍለ ጦር ምስረታ የተገኘ የፋኖ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ምስረታ የተሰማቸውን ስሜት÷ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ እና ተቋማዊ ለውጥ የተመለከቱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል::
የክፍለ ጦሩ ምስረታ በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደ ሲሆን ክፍለ ጦሩን የሚመሩ
1ኛ ዋና መሪ _ጌታዉ ሻረዉ
2ኛ_ወታደራዊ አዛዥ _ይግረማቸዉ ዳምጠዉ
3ኛ_ም/አዛዥ ለኦኘሬሽናል_መቶ አለቃ አለሙ ወርቁ
4ኛ_ም/ አዛዥ ለአስተዳደር _ አርበኛ ኃይለማርያም ኃይለሴ
5ኛ_ም/አዛዥ ለሎጅስቲክ _ አርበኛ ፍቃደ ወርቁ
6ኛ_ዘመቻ _ አርበኛ ኃይሉ ተፈራ
7ኛ_ም/ዘመቻ _ አርበኛ መንገሽ ተፈራ
8ኛ_መረጃ እና መሀንዲስ
9ኛ_ስልጠና እና ክህሎት- ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ሸዋንግዛዉ
10ኛ_ወታደራዊ ህግ አገልግሎት _አርበኛ ደሞዝ ኃይልዬ 11ኛ-ም/ ወታደራዊ የህግ አገልግሎት ኃላፊ -አርበኛ ተገኝ አዳፍሬ
12ኛ_ኦርድናስ _አርበኛ ብሩክ ይልማ
13ኛ_ህክምና _መቶ አለቃ ወልዱ
ድርጅት ጉዳይ ፅ/ቤት
1ኛ_ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ _አርበኛ በዛወርቄ ክንፉ
2ኛ_የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ _ አርበኛ አቡሽ ኃይሌ
3ኛ_ህዝብ ግንኙነት _ አርበኛ ቦጋለ ምንዳ
4ኛ_ትምህርት እና ስልጠና _ አርበኛ ተኮላ ደግፌ
5ኛ_ፋይናስ ሀላፊ _ አርበኛ ስዩም ጌታዉ
6ኛ_ፋይናስ ም/ኃላፊ_አርበኛ ዜና ከበደ
ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች
1ኛ_አስተዳደር ጉዳይ ኃላፊ _ሃምሳ አለቃ ገረመዉ ታደሰ
2ኛ_አደረጃጀት ኃላፊ_ አርበኛ ተስፋዬ ጥላሁን
3ኛ_ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ _አርበኛ ፋኒት ቅርሴ ከበደ
4ኛ_ሀብት አሰባሳቢ _አርበኛ አበባየሁ ተስፋዬ
5ኛ_ም/ሀብት አሰባሳቢ _ አርበኛ ጎሽሜ በቀለ
5ኛ_ሰላምና የህዝብ ደህንነት ኃላፊ _ አርበኛ ሻምበል በላቸዉ
6ኛ_ሰላምና የህብ ደህንነት ምክትል ኃላፊ -አርበኛ አህመድ ኢብራሂም ሁነው ተመድበዋል::
መረጃውን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
ጥቅምት 17/ዐ2/2018 �
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አዲሱን የቡልጋ ክፍለ ጦር መሰረተ
===============
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በከሰም ክ/ጦር ስር የነበሩ ፊት አውራሪ አስማረ ዳኘ ብርጌድና እና ተስፋ ብርጌድ በመቀናጀት የቡልጋ ክፍለ ጦርን መስርተዋል::
ይህም ክፍለ ጦር የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ የተቋማቱን የሰው ኃይል የፋይናንስ እና መሳሪያ ክምችት መሰረት ያደረገ አደረጃጀት እንዲሰራ ያስተላለፈውን መመሪያ በማሟላታቸው ተረጋግጦ ነው::
ክፍለ ጦሩ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል÷ የዕዙ አመራሮች÷ የቀድሞው ከሰም ክፍለ ጦር÷ የነበልባል ክፍለ ጦር ÷ የኃይለ ማሪያም ክፍለ ጦር አመራሮች እና የፋኖ አባላት በተገኘበት ነው::
በዚህ የቡልጋ ክፍለ ጦር ምስረታ የተገኘ የፋኖ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ምስረታ የተሰማቸውን ስሜት÷ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ እና ተቋማዊ ለውጥ የተመለከቱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል::
የክፍለ ጦሩ ምስረታ በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደ ሲሆን ክፍለ ጦሩን የሚመሩ
1ኛ ዋና መሪ _ጌታዉ ሻረዉ
2ኛ_ወታደራዊ አዛዥ _ይግረማቸዉ ዳምጠዉ
3ኛ_ም/አዛዥ ለኦኘሬሽናል_መቶ አለቃ አለሙ ወርቁ
4ኛ_ም/ አዛዥ ለአስተዳደር _ አርበኛ ኃይለማርያም ኃይለሴ
5ኛ_ም/አዛዥ ለሎጅስቲክ _ አርበኛ ፍቃደ ወርቁ
6ኛ_ዘመቻ _ አርበኛ ኃይሉ ተፈራ
7ኛ_ም/ዘመቻ _ አርበኛ መንገሽ ተፈራ
8ኛ_መረጃ እና መሀንዲስ
9ኛ_ስልጠና እና ክህሎት- ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ሸዋንግዛዉ
10ኛ_ወታደራዊ ህግ አገልግሎት _አርበኛ ደሞዝ ኃይልዬ 11ኛ-ም/ ወታደራዊ የህግ አገልግሎት ኃላፊ -አርበኛ ተገኝ አዳፍሬ
12ኛ_ኦርድናስ _አርበኛ ብሩክ ይልማ
13ኛ_ህክምና _መቶ አለቃ ወልዱ
ድርጅት ጉዳይ ፅ/ቤት
1ኛ_ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ _አርበኛ በዛወርቄ ክንፉ
2ኛ_የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ _ አርበኛ አቡሽ ኃይሌ
3ኛ_ህዝብ ግንኙነት _ አርበኛ ቦጋለ ምንዳ
4ኛ_ትምህርት እና ስልጠና _ አርበኛ ተኮላ ደግፌ
5ኛ_ፋይናስ ሀላፊ _ አርበኛ ስዩም ጌታዉ
6ኛ_ፋይናስ ም/ኃላፊ_አርበኛ ዜና ከበደ
ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች
1ኛ_አስተዳደር ጉዳይ ኃላፊ _ሃምሳ አለቃ ገረመዉ ታደሰ
2ኛ_አደረጃጀት ኃላፊ_ አርበኛ ተስፋዬ ጥላሁን
3ኛ_ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ _አርበኛ ፋኒት ቅርሴ ከበደ
4ኛ_ሀብት አሰባሳቢ _አርበኛ አበባየሁ ተስፋዬ
5ኛ_ም/ሀብት አሰባሳቢ _ አርበኛ ጎሽሜ በቀለ
5ኛ_ሰላምና የህዝብ ደህንነት ኃላፊ _ አርበኛ ሻምበል በላቸዉ
6ኛ_ሰላምና የህብ ደህንነት ምክትል ኃላፊ -አርበኛ አህመድ ኢብራሂም ሁነው ተመድበዋል::
መረጃውን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
ጥቅምት 17/ዐ2/2018 �
የአደረጃጀት ዜና
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አዲሱን የቡልጋ ክፍለ ጦር መሰረተ
===============
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በከሰም ክ/ጦር ስር የነበሩ ፊት አውራሪ አስማረ ዳኘ ብርጌድና እና ተስፋ ብርጌድ በመቀናጀት የቡልጋ ክፍለ ጦርን መስርተዋል::
ይህም ክፍለ ጦር የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ የተቋማቱን የሰው ኃይል የፋይናንስ እና መሳሪያ ክምችት መሰረት ያደረገ አደረጃጀት እንዲሰራ ያስተላለፈውን መመሪያ በማሟላታቸው ተረጋግጦ ነው::
ክፍለ ጦሩ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሴንትራል ኮማንድ አባል÷ የዕዙ አመራሮች÷ የቀድሞው ከሰም ክፍለ ጦር÷ የነበልባል ክፍለ ጦር ÷ የኃይለ ማሪያም ክፍለ ጦር አመራሮች እና የፋኖ አባላት በተገኘበት ነው::
በዚህ የቡልጋ ክፍለ ጦር ምስረታ የተገኘ የፋኖ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ምስረታ የተሰማቸውን ስሜት÷ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ እና ተቋማዊ ለውጥ የተመለከቱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል::
የክፍለ ጦሩ ምስረታ በተለያዩ ዝግጅቶች የተካሄደ ሲሆን ክፍለ ጦሩን የሚመሩ
1ኛ ዋና መሪ _ጌታዉ ሻረዉ
2ኛ_ወታደራዊ አዛዥ _ይግረማቸዉ ዳምጠዉ
3ኛ_ም/አዛዥ ለኦኘሬሽናል_መቶ አለቃ አለሙ ወርቁ
4ኛ_ም/ አዛዥ ለአስተዳደር _ አርበኛ ኃይለማርያም ኃይለሴ
5ኛ_ም/አዛዥ ለሎጅስቲክ _ አርበኛ ፍቃደ ወርቁ
6ኛ_ዘመቻ _ አርበኛ ኃይሉ ተፈራ
7ኛ_ም/ዘመቻ _ አርበኛ መንገሽ ተፈራ
8ኛ_መረጃ እና መሀንዲስ
9ኛ_ስልጠና እና ክህሎት- ሃምሳ አለቃ ሰይፈ ሸዋንግዛዉ
10ኛ_ወታደራዊ ህግ አገልግሎት _አርበኛ ደሞዝ ኃይልዬ 11ኛ-ም/ ወታደራዊ የህግ አገልግሎት ኃላፊ -አርበኛ ተገኝ አዳፍሬ
12ኛ_ኦርድናስ _አርበኛ ብሩክ ይልማ
13ኛ_ህክምና _መቶ አለቃ ወልዱ
ድርጅት ጉዳይ ፅ/ቤት
1ኛ_ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ _አርበኛ በዛወርቄ ክንፉ
2ኛ_የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ _ አርበኛ አቡሽ ኃይሌ
3ኛ_ህዝብ ግንኙነት _ አርበኛ ቦጋለ ምንዳ
4ኛ_ትምህርት እና ስልጠና _ አርበኛ ተኮላ ደግፌ
5ኛ_ፋይናስ ሀላፊ _ አርበኛ ስዩም ጌታዉ
6ኛ_ፋይናስ ም/ኃላፊ_አርበኛ ዜና ከበደ
ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች
1ኛ_አስተዳደር ጉዳይ ኃላፊ _ሃምሳ አለቃ ገረመዉ ታደሰ
2ኛ_አደረጃጀት ኃላፊ_ አርበኛ ተስፋዬ ጥላሁን
3ኛ_ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ _አርበኛ ፋኒት ቅርሴ ከበደ
4ኛ_ሀብት አሰባሳቢ _አርበኛ አበባየሁ ተስፋዬ
5ኛ_ም/ሀብት አሰባሳቢ _ አርበኛ ጎሽሜ በቀለ
5ኛ_ሰላምና የህዝብ ደህንነት ኃላፊ _ አርበኛ ሻምበል በላቸዉ
6ኛ_ሰላምና የህብ ደህንነት ምክትል ኃላፊ -አርበኛ አህመድ ኢብራሂም ሁነው ተመድበዋል::
መረጃውን ያደረሰን አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል
ጥቅምት 17/ዐ2/2018 �
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮሰ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ደባይ ጮቄ ብርጌድ በደባይ ጥላት ግን ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ የህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ በመፍጠር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
ጥቅምት16/2018 ዓ.ም ደባይ ጮቄ ብርጌድ በደባይ ጥላትግን ደቤት ቀበሌ ማህበረሰብ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የብርጌድ እና የሻለቃ አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ውይይቶች አካሂዶል።በውይይቱም:-
➤ በመልካም አሰተዳደር ጉዳይ
➤የጎበዝ አለቃ የሰራ ግምገማ
➤ የተሻለ የጎበዝ አለቃ አወቃቀር
➤የቀበሌ የማህበራዊ የፍትህ ተቋም ማቆቋም
➤ ፋኖ ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶል። በውይይት መድርኩ ለተገኙት የማህበረሰብ ክፍል የብርጌድ አመራሩ የፓለቲካ ሰልጠና ተሰጥቷል።
ደባይ ጮቄ ብርጌድ በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ድርጅቱ በተለያዩ ግዳጆች የሰጣቸውን የትኛውም አይነት ግዳጅ ሲወጡ የቆዩ የብርጌዱ ተወርዎራ ኮማንዶዎችን ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም ታሀድሶ አድርጓል።
አዲሰ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲሰ አሰተሳሰብ!
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
የጎንደር ፋኖ አዛዦች ለጋራ የአማራ ዓላማ መሰባሰብን አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ፋኖ ሸንጎ የተሰጠ መግለጫ
ጥቅምት ፳፻፲፰ ዓም
በቅርቡ የጎንደር ፋኖ አዛዦች ልዩነታቸውን ወደ ጎን ትተው በአንድ የጋራ አማራ ዓላማ ለመሰለፍ የወሰኑት ውሳኔ ለህዝባችን እና ለንቅናቄያችን ታሪካዊና ተስፋ ሰጪ ጊዜን የሚያበስር ኣስደሳች ዜና ነው። ከመከፋፈልና ከግጭት
ይልቅ ራዕይን እና የጋራ ግቦችን ለመረጡት አዛዦች፣ ተዋጊዎች እና ደጋፊዎች ሁሉ ሞቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።
ይህ አጋጣሚ ትልቁ ኃይላችን ከአንድነት እንደሚመጣ ጠንካራ ማሳሰቢያ ሆኖ ያገለግላል፤ በህብረት ስንጓዝ የሚያቆመን
ሃይል የለም፤ እንደ አንድ ስንናገር ዓለም ያስተውላል። የተዋሃደ አመራር የአማራ ትግልን መሰረት ከማጠናከር ባለፈ ሰፊ አለም አቀፍ እውቅና እና ድጋፍ የማግኘት እድሎችን ያሳድጋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የትግላችን መቀናጀት፣ የጋራ ግባችን እና የዲሲፕሊን ጥረትን ሲገነዘብ የህልውና ትግላችንን እንቅስቃሴ የመደገፍ ዕድሉ ሰፊ ነው።
የጎንደር ፋኖ አዛዦች በአንድነት አመራር መሰባሰባቸው የፖለቲካ ጥበብ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ እና በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነትን ያሳያል። አዛዦቹ የጋራ ራዕይን በመከተል የአማራ ንቅናቄ የተደራጀ፣ የተቀናጀ እና ለፍትህ የቆመ፣ ደህንነት እና ዘላቂ መረጋጋት ለማምጣት ቆርጦ የተነሳ ሰራዊት መሪ
መሆናቸውን አሁን በተግባር አሰመስክረዋል። ይህ አንድነት የንቅናቄውን ስልታዊ አሰላለፍ እና የአሠራር አቅምን ያጠናክራል፣ ይህም በእቅድ፣ በሰብአዊ ጥረቶች እና በአለም አቀፍ ተሟጋችነት የተሻለ ቅንጅት እንዲኖር ያስችላል።
ለሰላም እና ለሰብአዊ መብቶች ቁርጠኛ ከሆኑ አጋሮች ጋር ለውይይት እና ለትብብር ጠንካራ መሰረት ይፈጥራል።
የአንድነቱ ውሳኔ ቢዘገይም የፖለቲካ ስኬትን ብቻ ሳይሆን የሞራል ስኬትንም ተገንዝበናል፤ በግለሰብ ልዩነቶች ላይ የጋራ ግቦች ድል ነስተዋል። ተመስገን።
የአማራ ፋኖ የወሰደዉ የአንድነት ዉሳኔ ለመላዉ አማራ የህልዉና ዋስትና ወይም ደጀን ከመሆኑም በላይ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ዉስጥ እጅግ በጣም ወሳኝ ጠንካራ የጋራ ታሪካዊ ህብረት እንደነበረዉ ምስክርነት የሚሰጥ ነዉ። ጀግኖች በፍቅር እየተላቀሱ ሲተቃቀፉ ማየት እንዴት ደስ ይላል - ከጎናቸዉ በአንድነት በነቂስ አብሮ መሰለፍ ሰዓቱ አሁን
ነዉ። ስለዚህ አንድነት ምንድን ነዉ? አንድነት ይቅርታ ነዉ። አንድነት መቻቻል ነዉ። አንድነት መተማመን ነዉ። አንድነት መሠረት ነዉ። አንድነት አንድ አማራጭ ነዉ። አንድነት ሐገር ነዉ። አንድነት አሸናፊነት ነዉ አንድነት
ድምቀት ነዉ። አንድነት ፍቅር ነዉ። አንድነት መከባበር ነዉ። አንድነት ለሌላዉ መሆን ነዉ። አንድነት ተሽሎ መገኘት ነዉ። አንድነት ሕይወት ነዉ። አንድነት ተግባር ነዉ። አንድነት ፍሬ ነዉ። አንድነት ምስክርነት ነዉ። አንድነት ሐቀኝነት ነዉ። አንድነት በልጦ መገኘት ነዉ። አንድነት ህልዉና ነዉ። አንድነት ሚስጥር ነዉ። አንድነት ጥበብ ነዉ። አንድነት ከለላ ነዉ ። አንድነት ህብረት ነዉ። አንድነት ማወቅ ነዉ። አንድነት መሰላል ነዉ። አንድነት ዉበት ነዉ። አንድነት እዉቀት ነዉ። አንድነት ዋስትና ነዉ። አንድነት ደጀን ነዉ። አንድነት አለኝታ ነዉ። አንድነት ወግ ባህል ነዉ። አንድነት ታሪክ ነዉ። አንድነት ሻማ ነዉ። አንድነት በር ነዉ። አንድነት ዉቅያኖስ ነዉ። አንድነት መኖር ነዉ። አንድነት መቻል ነዉ። አንድነት ሁሉንም ነዉ።
ይህ የአማራ ፋኖ አመራሮች አንድነት በመላው አማራ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ፤ ወደዚህ አንድነት እንዲመጡ ብዙዎች የህይወት፣ የገንዘብ፣ የጉልበትና የጊዜ መስዋእትነት የተከፈለበት፤ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ማገዝ ያልቻለው አብዛኛው ህዝብ በፀሎት እግዚአብሔርን የለመነበት አሳሳቢ ጉዳይ ነበር።
አሁን የሰማነው ዜና ተመስገን አስብሎናል። ምክንያቱም ፩ኛ የፋኖ አመራሮች አንድነት የአማራን ህዝብ ሰቆቃ እና ችግር በአጭር ጊዜ ያቃልላል፤ ፪ኛ ግንባር ላይ ያሉ አመራሮች አንድ ሲሆኑ ተበታትነው የሚሰሩ የተለያዩ የአማራ
ሲቪል አደረጃጀቶች ወደ አንድ እንዲመጡ ያደርጋል፤ ፫ኛ የአማራ ፋኖ ሰራዊት፣ የአማራ ሲቪል ድርጅቶችና በውጭ የሚኖሩ የአማራ ልጆች በጋራ ሲሰሩ የዐማራ ግፍና ሰቆቃ ያበቃል፣ የኢትዮጵያንም ትንሳዔ ያበስራል።
ሰማዕታቶቻችን ህይወታቸውን የገበሩት የፋኖ አመራር ተከፋፍሎ ለማየት አይደለም፤ ለህዝባቸው ክብር፣ ነፃነት እና ህልውና ሁሉንም ነገር ሰጥተዋል። መሪዎቹ አንድ ላይ በመሰባሰብ ይህንን የተቀደሰ ግዴታ አክብረዋል እናም በሁሉም የአማራ ልብ፣ ከጎንደር እስከ ጎጃም፣ ከወሎ እስከ ሸዋ፤ የእኛንም የዲያስፖራ ዐማራ ልጆችና ተወላጆች የነጻነት ተስፋ አድሰዋል። በተጨማሪም፣ ይህ አንድነት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰላማዊና ፍትሃዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመረጋጋት
እና ለፍትህ ከሚጥር ኃላፊነት የተሞላበት እና ያተኮረ እንቅስቃሴ ጋር ለመሳተፍ አዲስ እድል ይሰጣል። በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ይህን የተባበረ አመራር አስፈላጊውን ድጋፍ እንድንሰጠው የሚገፋፋም ጥሪ ነው። ዕውቀታችን፣ ሀብታችን ጉልበታችን እና ጽኑ እምነታችን ለትግሉ እንድናበረከትም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረ ቀስቃሽ ክስተት ነው።
ወደፊት ያለው ጉዞ ፈታኝ ይሆናል፣ ነገር ግን በአንድነት፣ በዲሲፕሊን እና በራዕይ፣ ስኬታማ እንደሚሆን የበኩላችን አስተዋጽዖ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል። በጋራ የአማራ ህዝብ በብቸኛ ትውልድ አገሩ በሰላም፣ በእኩልነት እና በደህንነት የሚኖርበትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ መፍጠር እንችላለን።
አማራዊ አንድነት ጋሻችን፣ መሳሪያችንና ብቸኛ
እጣ ፈንታችን ነው። ለህዝባችን፣ ለነፃነታችንና ለወደፊታችን አንድነት ይህ የጎንደር ፋኖ አመራር ስምምነት ትልቅ ሚና ይኖረዋል።
በመጨረሻም፣ የአማራ ህዝብ በጠላቶቹ ከተፈፀመበት ግፍና ስቃይ በተጨማሪ ሃሳዊ ፋኖና ህገወጥ ህግ አልባ ታጣቂ ቡድኖች ከፍተኛ ግፍ እየፈጸሙበት መሆኑን ስንሰማ ሀዘናችንን ልብ ሰባሪና ጥልቅ መሆኑን እየገለፅን፤ የፋኖ አመራር እንደ ደቡብ ጎንደር በለሳና እና አዲስ ዘመን ባሉ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነትና ህግ አልበኝነት ለመግታት፤ ብሎም ለማስወገድ ከህዝቡ ጋር በመተባበር ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ እና ተከላካይ የሌላቸውን እና ተጋላጭ የሆኑ
ወገኖቻችን ከውስጣዊ ብዝበዛ እና ከሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲጠብቁ አጥብቀን እናሳስባለን።
አንድነት ትግላችንን በድል ለመወጣት!
አንድነት ለፋኖ ድል አድራጊነት!
ድል ለአማራ ሕዝብ!
ዶክተር አምባቸው ወረታ /ሊቀመንበር
ማርእሸት መሸሻ / ጠቅላይ ጸሐፊ
የድል ዜና
የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት በራስ አበበ አረጋይ የትውልድ ቀየ ጅሩ ድባቅ ተመታ።
የአብይ አህመድ ኃይል በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠናው አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር አናብስቶችና በሽዋ ጠቅላይ ግዛቱ በትላንቱ ዕለት በፋኖ ኃይሎች ድባቅ መመታቱን መዘገባችን ይታወቃል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ወራዳ ኃይል በሶስት አቅጣጫ ፋኖ አለ ወደ ተባለበት ቦታ ለማፈን በአደረገው ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ከመቀጣት አልፎ ሙትና ቁስለኛ መሆኑን መዘገባችን የሚታወቅ ሃቅነ ነው። ሆኖም የአሳምነው ልጆች በትላንቱ አውደ ውጊያ የጠላትን አስከሬን አላስነሳ በማለት ከጠላት ጋር ግብግብ በመግጠም አስደማሜ ጀብድ ሰርተዋል በመሆኑም ጥምር ጦር ለአመራ ህዝብ የነፃነት ትግል ጉዞ ጉልህ ሚና እንድሚኖረው እሙን ነው።
የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል የአሳምነው አናብስቶች ፋኖዎችን ለማፈን በሚል ተስፋ ይዞ በሶስት አቅጣጫ አድማ ብተና እንዲሁም የ101 ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባላትን ብዛት ያለው ሚኒሻን በእነዋሪና በይሎ በኩል ከመራቤቴ ተነስቶ ደግሞ በአፈዘዝ በርካቶ ቆርጦ ቆላውን ከጀማ ተነስቶ በአንደኛው ግንባር ከለሚ ወርዶ ወደ ጀማ በይሎ አቅጣጫ ያለውን ኃይል ይዞ በመንቀሳቀስ አረመኔው የጠላት ኃይል በጥምሩ ጦሩ አስደማሜ በሆነ መንገድ በአማራ አናብስቶች እንደ ቆሎ አርገፍውታል። የአማራ ህዝብ ባህሉና እምነቱ እጅጉን ተወዳጅም ከመሆኑ በላይ የጠላትን አስከሬን በክብር ማህበረሰቡ በመሰባሰብ አሁን በዚህ ሰዓት እየቀበሩ ይገኛሉ።
በመሆኑ የአገዛዙ ሰራዊት በትላንቱ አውደ ውጊያ የተደመሰሰ 40//
"ቁስለኛ 25
"ሚሊሻ 4 የተደመሰሰ
"የቆሰለ ሚሊሻ 8
"በሰላም እጅ የሰጠ ሚሊሻ 3
"የቆሰለ ሻንበል "አመራር1
" የተደመሰሰ ሻንበል አመራር 1
በምርኮ የተገኘ ወታደራዊ ቁሳቁስ
"ጥርጥር ክላሽ 4
"ወታደራዊ ቦርሳ 25
"03,ዝናብ ልብስና በርከት ያሉ ተተኳሽ ጥይቶችም ተማርከዋል።
እንዲሁም በሸዋ በጠቅላይ ግዛት ዕዝ ስር የምትገኘው ራስ አበበ አረጋዊ ክፍለ ጦር አሊ ሻለቃ በኩል
01 ጥርጥር ክላሽ
01 የደረት ትጥቅ
03 ካዘና 90 ጥይት
04 የእጅ ቦንብ
04 የተደመሰሰ የጠላት ኃይል
01 መሰረታዊ ወታደር የአስር አለቃ ማዕረግ ያለው
130 የብሬን ጥይት
10 ወታደራዊ ጥርንፍ በማድረግ የተማረከ ሲሆን የአገዛዙ ኃይል የአማራ እናቶችና ሴቶች እህቶቻችን እንደፈለገ የሚደፍርበት ግዜ ያበቃል በገባበት ገብተን ይህን አረመኔያዊ ሰራዊት የእህታችንን ጡት የቆረጠውን አረመኔያዊ ወታደር ሳይውል ሳያድር በገባበት ገብተን እየደፋነው እንገኛለን ።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ
ጥቅምት 17/02/2018 ዓ.ም
#የድልዜና ሽዋ‼️
የአብይ አህመድ ኃይል በአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠናው አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር አናብስቶችና በሽዋ ጠቅላይ ግዛቱ በትላንቱ ዕለት በፋኖ ኃይሎች ድባቅ መመታቱን መዘገባችን ይታወቃል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ወራዳ ኃይል በሶስት አቅጣጫ ፋኖ አለ ወደ ተባለበት ቦታ ለማፈን በአደረገው ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ከመቀጣት አልፎ ሙትና ቁስለኛ መሆኑን መዘገባችን የሚታወቅ ሃቅነ ነው። ሆኖም የአሳምነው ልጆች በትላንቱ አውደ ውጊያ የጠላትን አስከሬን አላስነሳ በማለት ከጠላት ጋር ግብግብ በመግጠም አስደማሜ ጀብድ ሰርተዋል በመሆኑም ጥምር ጦር ለአመራ ህዝብ የነፃነት ትግል ጉዞ ጉልህ ሚና እንድሚኖረው እሙን ነው።
የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል የአሳምነው አናብስቶች ፋኖዎችን ለማፈን በሚል ተስፋ ይዞ በሶስት አቅጣጫ አድማ ብተና እንዲሁም የ101 ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባላትን ብዛት ያለው ሚኒሻን በእነዋሪና በይሎ በኩል ከመራቤቴ ተነስቶ ደግሞ በአፈዘዝ በርካቶ ቆርጦ ቆላውን ከጀማ ተነስቶ በአንደኛው ግንባር ከለሚ ወርዶ ወደ ጀማ በይሎ አቅጣጫ ያለውን ኃይል ይዞ በመንቀሳቀስ አረመኔው የጠላት ኃይል በጥምሩ ጦሩ አስደማሜ በሆነ መንገድ በአማራ አናብስቶች እንደ ቆሎ አርገፍውታል። የአማራ ህዝብ ባህሉና እምነቱ እጅጉን ተወዳጅም ከመሆኑ በላይ የጠላትን አስከሬን በክብር ማህበረሰቡ በመሰባሰብ አሁን በዚህ ሰዓት እየቀበሩ ይገኛሉ።
በመሆኑ የአገዛዙ ሰራዊት በትላንቱ አውደ ውጊያ የተደመሰሰ 40//
"ቁስለኛ 25
"ሚሊሻ 4 የተደመሰሰ
"የቆሰለ ሚሊሻ 8
"በሰላም እጅ የሰጠ ሚሊሻ 3
"የቆሰለ ሻንበል "አመራር1
" የተደመሰሰ ሻንበል አመራር 1
በምርኮ የተገኘ ወታደራዊ ቁሳቁስ
"ጥርጥር ክላሽ 4
"ወታደራዊ ቦርሳ 25
"03,ዝናብ ልብስና በርከት ያሉ ተተኳሽ ጥይቶችም ተማርከዋል።
እንዲሁም በሸዋ በጠቅላይ ግዛት ዕዝ ስር የምትገኘው ራስ አበበ አረጋዊ ክፍለ ጦር አሊ ሻለቃ በኩል
01 ጥርጥር ክላሽ
01 የደረት ትጥቅ
03 ካዘና 90 ጥይት
04 የእጅ ቦንብ
04 የተደመሰሰ የጠላት ኃይል
01 መሰረታዊ ወታደር የአስር አለቃ ማዕረግ ያለው
130 የብሬን ጥይት
10 ወታደራዊ ጥርንፍ በማድረግ የተማረከ ሲሆን የአገዛዙ ኃይል የአማራ እናቶችና ሴቶች እህቶቻችን እንደፈለገ የሚደፍርበት ግዜ ያበቃል በገባበት ገብተን ይህን አረመኔያዊ ሰራዊት የእህታችንን ጡት የቆረጠውን አረመኔያዊ ወታደር ሳይውል ሳያድር በገባበት ገብተን እየደፋነው እንገኛለን ።
መረጃዎን ያደረሰን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
ጥቅምት 17/ዐ2/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ጥቅምት 17/2018ዓ/ም
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር ደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ የአረመኔው አገዛዝ አሽከር የነበረውን
፲ አለቃ ካሊብ እንድሪስ 57ኛ ሬጅመንት ጋንታ መሪ ከነሙሉ ትጥቁ ቤርጌዱን ተቀላቅሏል።
ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ነፃ ባወጣቸው የሰሜን ወሎ ዞን መካከል በሀብሩ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች መካከል በሩጋ መነዮ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡
ዛሬ በዕለተ እሁድ በቀን 16/02/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ ሩጋ መነዮ ቀበሌ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡
በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች
1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?
* ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ
* ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ
* የትግሉ ተግዳሮቶች
* የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ
*የግል ታጣቂዎችን በማደራጀት አካባቢያቸውን ከፋሽቱና ወራሪው የአብይ አህመድ ሰራዊት እንድጠብቁ ግንዛቤ ተስጥቷል።
2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ
* በወታደራዊ ቁመና
* በፖለቲካ ተቀባይነት
* የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም
3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ
* የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት
* የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት
* ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ
4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ?
በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተሞክሯል፡፡
በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡
በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ የምስራቅ አማራ ኮር1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
ፋኖ መሀመድ ሞገስ
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
+1
እንደህዝብ ካልተከበርን እንደግለሰብ አንከበርም፤ ሁላችንም ነፃ ካልሆንን ማናችንም ነፃ አንሆንም!
[አሮጊቷ እናቴ ከእነ የልጅ ልጇ በጨለማ ታገተች]
በ1983 ዓ/ም ገና እኔኑ በማህፀንሽ ተሸክመሽ በደከምሽበት ወራት አስሮ ያንገላታሽ ጠላት ዛሬ ደግሞ በእኔ ሰበብ ከእነ የልጅ ልጅሽ ህፃን አሜን ዘወትር (የ4-ዓመት ህፃን) እንዳገተሽ ሰማሁ። ያኔ እንዳልወለድ ሞክሯል፤ ሳይሳካለት ቀርቶ ተወልጄም አድጌ አንገቱን አንቄዋለሁ።
ይህንን አረመኔ አገዛዝ ጨክነን ማስወገድ እንዳለብን አምነን ወጥተናልና መፍትሔው በእጃችን ነው። የህዝባችንን ጠላት በማስወገድ ህልውናችንን አረጋግጠን ነፃነትን እናመጣለን። አዎ ለሁላችን የሚበጀውን መርጠን መከራውን ታጋዮቹ በተለዬ እንሸከመው ይሆናል እንጂ ወደ ድል ከመገስገስ አንገደብም።
ድል ለአማራነት!
©አርበኛ ተሰማ ካሣሁን
"...የአገዛዙ ደህንነት በቁጥጥር ሥር ዋለ‼
"...አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ፩ኛ ክ/ጦር ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ የደህንነት መዋቅር ከብልፅግና ቤት ወደቀጠናው የተላከ አንድ ምልምል የደህንነት አባል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
ያለው ተሾመ የተባለ እና ከፍተኛ የመረጃ ስምሪት የተሰጠው የብልፅግና የደህንነት ምልምል ከማዘዣ ጣቢያው ከመውጣቱ በብርጌዱ ንስር የደህንነት መዋቅር በቁጥጥር ስር ውሎ የማጣራት ስራ እየተደረገበት መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
ህዝባችንን ለከፋ ጉዳት ለማጋለጥ የፋኖን እንቅስቃሴ ለመከታተልና በጠላት ለማፈን ቀድሞ ስምሪት የተሰጠ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ፀጉረ ልውጥ ሰው ወይንም በጥርጣሬ የሚያየውን የትኛውንም ሰው በመከታተል ጥቆማ እንዲሰጥ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ጥቅምት 17/2018
ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህ/ግንኙነት
ክፍል ሁለት ጎጃም ወለጋ መስመር‼
አማራ ክልል ላይ በሰላማዊ ሰልፍ ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ መሞት መፈናቀልና መሳደድ ይቁም መንግስት የዜጎችን ሰላም ይጠብቅ የሚለው ምላሽ አቶ 2015 ሀመሌ በወር ላይ በመላው አማራ ክልል አቢወት ተቀጣጠለ ፋኖ የዞን ከተሞችን ጨምሮ የወረዳ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ በዝህን ስዓት ቡሬ ከተማን ጨምሮ የቡሬ ወለጋውን መስመር እስከ አባይ ፋኖ ተቆጣጠር አባይ ላይ የወለጋ አማራ ወደ ጎጃም እንዳይሻገር ይጠብቁ የነበሩ ፌድራል ፖሊሶች ከፊሉ ለጎጃም ፋኖ እጃቸውን ሲሰጡ ግማሹ ወደ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ፈርጥጡው አመለጡ በዝህ አጋጣሚ ውስን የወለጋ ፋኖዎች ከጎጃም ፋኖ አመራሮች ጋር ለመተዋዎቅና በቀጠናው ዙርያ ለመዎያየት እንዲሁም ሎጅስቲክ ከጎጃም ለመግዛት ቁጭ ከተማ ገቡ እንዲሁም ጣቦና ሰንቶም ቀበሌዎች የወለጋ አማራ ላይ ብዙ በደል እንዳደረሱና ከዝህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡና ወደፊት አብረን እንድንሰራ አሻፈረኝ የሚሉ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰዱ ለአካባቢው ፋኖ አመራሮች አሳወቁ እነሱሞ ጥፋታቸውን አምነው በስዓቱ መከላከያ መሸነፉን ተከትሎ ከእንግዲህ እኛም ፋኖ ነን ያለፈውን ይቅርታ አድርጉልን በማለት ተማጸኑ ይቅርታም ተደረገላቸው።
በዝህን ስዓት ቡሬና ፍኖተሰላም ከተሞችን መከላከያ ተቆጣጠረ በስዓቱ ከመከላከያና ከዞን አመራሮች ጋር በድብቅ ይደዋዎሉ ነበር በውስጠ ደምብ እራሳተውን በደምብ አደራጁ የወለጋ ፋኖዎችና የጎጃም ፋኖዎች አገር አማን ብለው 2016ዓ.ም አጋማሽ ላይ ከቁጭ ከተማ በመነሳት አመሻሽ ላይ በመኪና ወደ አባይ በሚንቀሳቀሱበት ስዓት ሶንቶም ላይ ምንም ባልጠበቁበት ስዓት ጨለማን ተገን በማድረግ የደፈጣ ጥቃት ተከፈተባቸው ሁለት መኪና በቦምብ ተመታ ከ10 በላይ የወለጋ ፋኖዎችና ከ15በላይ የቡሬ ዙርያ ፋኖዎች የጥቃቱ ሰላባ ሁነው ወዲያውኑ ከ25በላ ፋኖዎች በነዝህ ካዲዎች ተገደሉ ብሬንና ስናይፐርን ጨምሮ የነፍስ ወከፍ መሳርያ ወሰዱ።
ይህንን ጀብድ መስራታቸውንና ቶሎ መከላከያ ካልገባላቸው ህይዎታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ለአለቆቻቸው ማለትም ለመከላከያ አመራሮችና ለዞን አመራሮች ወዲያውኑ ሪፖርት አደረጉ ፋኖዎች ሀይል አስጨምረው አስክሬናቸውን ቀብረው ሳይጨርሱ መከላከያ ወደ ቦታው ያለምንም ተኩስ ገብቶ ታደጋቸው።
በዝህን አጋጣሚ ከከላከያውና ከዞን አመራሮች ሽልማት ተበረከተላቸው በደምብ እንዲደራጁ ተደረጉ ቁጭ ላይ ፋኖ ከመከላከያ ጋር ሲገጥም ከጀርባ ይወጉት ጀመር በቡሬ ወለጋው መስመርም የወለጋ አማራ ከተገኘ እርምጃ ይወስዱባቸው ነበር።
በዘመቻ 100ተራሮች ፋኖ ሀይለኛ ትንቅንቅ በማድረግ ከቡሬ እስከ ቁጭ ያለውን ቀጠና ተቆጣጠረ የዛኔ ነበር ለአማራ ፋኖ ከፍተኛ አመራሮች ህግ እንዲያስከብሩልንና ሶንቶምና ጣቦን ተቆጣጥረው የቡሬ ወለጋው መስመር እንዲከፍት የተማጸነው።
መከላከያ ተቼንፎ መውጣቱን ያወቁት የሶንቶም ሚኒሾች ለአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች እኛ የናንተው ወገን ነን በብልጽግና ሴራ ነው የተሸወድነው ከአሁን በኋላ እኛም ፋኖ ነን እንታረቅ ቅለው ተማጽነው ምንም አይነት ቸወሰዱትን መሳርያ ሳይመልሱ እርቅ ተፈጸመ ምንገዱም ሊከት የሚችለው የእኛ ይሁንታ እንጅ ማንም አያስገድደንም የሚል ምላሽ መለሱ ።
ከዘመቻ መቶ ተራሮች በኋላ መከላከያ ከወራት በኋላ ቁጭ ከተማ መልሶ ሲገባ አሁንም መተው ከመከላከያ ጋር ወገኑ ተመሳሳይ ድርጊታቸውን ቀጠሉ በዘመቻ አንድነት መከላከያ ቁጭ ላይ ሲከበብ ለሊት ጠፍተው ቡሬ ሲገቡ ሚኒሻ ብቻውን ተከቦ ጧት ላይ ተኩስ ሲጀመር አሁንም እንደለመዱት የሶንቶምና የጣቦ ሚኒሾች መተው
ጀርባ ጎጃም ፋኖ ላይ ተኩስ በመክፈት አንድም ሚናሻ ሳይጎዳ ይዘዋቸው ወደ ሶንቶም ሄዱ።
በዝህ ተደጋጋሚ ድርጊት የተበሳጩት የወለጋ ፋኖች እኛ ገብተን ህግ እናስከብራለን የህዝባችንን ምንገድም እናስከፍታለን ብለው ሲነሱ የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች ከለከሉ ጉዳዩን በውይይት እንጅ በሀይል አይደለም የምንፈታው አሉ ያው አሁንም መከላከያ ቁጭ እስኪገባ ማለት ነው።
ይህ ሁሉ እሹሩሩ እስከ መቼ ነው?
የወለጋ ፋኖ እነዝህን ሁለት ቀበሌዎች በ30ደቂቃ ውስጥ መቆጣጠር እዬቻለ የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮችን ላለማስቀዬም ብቻ ህዝባቸው የጣለባቸውን አደራ እዬተወጡ አይደለም።
የጣቦና የሶንቶም ሰንኮፍ እስካልተነቀለ ድረስ የወለጋ አማራ ህዝብ ወደ ጎጃም ገብቶ ምንም አይነት ግብዓት ይዞ መመለስ አይችልምና ይህንን እሾህ ለመንቀል ሁሉም አማራ የድርሻውን ይወጣ ትላለች ቢዛሞ ሚዲያ።
