ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 379
مشترکین
-924 ساعت
+2477 روز
+1 42930 روز
آرشیو پست ها
+1
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የድብጠለምት ተከዜ እና ጭና ክፍለጦር በጥምረት የአገዛዙን አራ*ዊት ሰራዊት የደመሰሱት ሲሆን አገዛዙ ሙት እና ቁስለኛ ሁኖ የንዑስ ወረዳ ከተማ የሆነቸው ጥራሂና ከተማን ለቆ ወደ ደባርቅ ፈርጥጧል !!
ድል ለአማራ ፋኖ
#የተቆረጠብኝን የእግሬን ቁስል አትግለጡብኝ ሰዎች ያዩብኛል===(በአርሲ ጭፍጨፋ ሲቃይ የደረሰው ሕፃን) #ዛሬ በተኛበት ክርስቲያን ሆስፒታል ለመጠየቅ ሄደን ሕፃኑ የመለሰልን መልስ ይህ ነውና። #እጅግ በጣም ልብ የሚሰብር በአርሲ ኦርቶዶክሳዊያን ጭፍጨፋ ወላጅ እናቱንና አባቱን እንዲሁም ቤተሰቦችን ያጣ የ7 ዓመት ሕፃን ልጅ በዚህ በልጅነት አእምሮ ሰዎች እግሬ መቆረጡን እንዳያዩ ቁስሌን አትግለጡብኝ ብሎ መሳቀቁ በእንባ እንድንራጭ ያደርጋል። የሚገርመው ጥይቱ ሰውነቱን ብሶ የገባበት ሌሎች የሰውነቱ አካላት ተሰፍተወ መናገር፣ መንቀሳቀስ እና መብላት አልቻለም። #ከዚህ በተጨማሪ የተቆረጡ የሰውነቱ ክፍሎች የነገ መሳቀቂያ ከወዲሁ ሆነውለት በቁስሉ ህመም ላይ ተጨማሪ የአእምሮ ጭንቀትን ጭረውበታል።
ለማንኛውም የማንም የምንም አጀንዳ ይሁን በአጀንዳ ቀራጮችና በድርጊት ፈጻሚዎች የሚመጣው አምላካዊ ቁጣ በተሰውትና በተጎዱት ላይ ከደረሰው ሺ እጥፍ በላይ እንደሆነ ጥርጥር የለንም። ብቻ ለአሁኑ የልጁ ሲቃይና ጭንቀቱ ልብ የሚሰብር ነው። #በአርሲ ጉዳይ ላይ #ይግባኝ ለሰማይ አምላክ ብለናል #የይግባኙም መልስ ያለጥርጥር ለተጎዱት ወገኖች የሚወግን መሆኑ አይቀርም!!! ማንም ሊቀልድ ይችላል ግድ የለም ኃጥአት እየተቆጠረችለት መሆኑን አይርሳ!!!
#ተናግረንም ትርጉም ሳንናገርም ትርጉም
#ስለ አርሲ ተናግረን መቼም አንሆንም ርጉም!!!
©ዲያቆን ማርቆስ
ታላቁ ሰው አርበኛ ጫኔ ጌቴ !
የዐማራን አንበሳዊ ባህሪ በስተርጅና ዘመናቸው እንኳን አስደምመውን ሰማዕትነትን ከተቀበሉ አያሌ ዐማራዎች መካከል ትልቁ ሰው !
እንዲህም እንዲያም ብለን ግን ይሄን ህዝብ ነፃ እናወጣዋለን። ሁሉም ነገር ቀላል ባይሆንም መስተካከሉ ግን ከዐማራ አቅም በላይ አይሆንምና ይቃናል !
የዐማራ ጀግኖች እንዴት በጦር ሜዳ ወደቁ ብለን ብንጠይቅ መልሱ አንድ ነው። በውስጣዊ ባንዳ። እነ ፕሮፌሰር፣ እነ ዋዋ ጎቤ፣ እነ አሳምነው ጽጌ፣ እነ አስቻለው ደሴ፣ እነ ጫኔ ጌቴ ... ሌሎችም ጀግኖች የወደቁት በውጨኛው የጠላት ጥይት ሳይሆን በውስጥ ባንዳ ነው። አሁንም ለትግላችን ስንክሳር፣ የጠበቀ ችንካር ሁኖ የጠበቀውን እያላላ አላራምድ ያለን ይሄኛው ባንዳ ነው። ሁኖም ይሄ ታላቅ ህዝብ በታላቁ የዐማራ አብዮት ማሸነፉ አይቀርም። ከምንም በላይ ዐማራ መሆናችን አይቀርም !
የሁለት አመት የመታሰቢያ ቀን !
✍️ይድነቃቸው ሽዋንግዛዉ
+1
👉ከትናንቱ የቀጠለ አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት :-
አገዛዙ ህዝብን ለመጨፍጨፍ የጦር ጄት ወደ ምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ባሉ ቀጠናዎች እንዳመቱ ትዕዛዝ መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል።
በተለይም ቴወድሮስ ዕዝ በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ከባህርዳር እስከ ቡሬ እና በከፊል ደምበጫና እነማይ ወረዳ ባሉ አካባቢዎች ጥቃቱ ሌሊትም ሊፈፀም ስለሚችል ባትሪ ፣ እሳትና ብርሐን አንፀባራቂ ኘገሮችን ባለመጠቀም እራሱን ከጥቃት እንዲከላከል እየገለፅን የወገን ጦር አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መረጃው ለሁሉም ይዳረስ!
ህዳር 7/2018 ዓ.ም
+1
74 ኛ ክ/ጦር ጊዜያዊ መንግስት አስ/ሮች በአምስት ቀበሌወች ላይ ህዝባዊ ውይይቶች አጠናክረው ቀጥለዋል
ድርጅታችን ይፋ ባደረገው አዲስ መዋቅር መሰረት በአዲስ በተደራጀው 201ኛ ኮር 74ኛ ክፍለ ጦር እና በስሩ ባሉት የወረዳ ጊዜያዊ መስተዳድሮች የድርጅታችንን ቁመና ፣ አዲሱን መዋቅር ማስረዳትና ማደራጀት እንዲሁም ህዝባችንን ማወያየት ቀጥለናል።
ዛሬ በቀን 07/03/2018 ዓ/ም በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ጊዜያዊ አስ/ር ውስጥ የሚገኙ ነባርና በቅርቡ ከጠላት ነፃ የወጡ ቀበሌዎች ዶማ ጉናጉና፣ ይብራዛ፣ እኔሳ፣ ወረያ መስቀልእና ዞባር ይቋንዳ ቀበሌዎችን ማወያየት ተችሏል።
በውይይታችንም፦ የቀበሌ መዋቅር የሌላቸውን በማዋቀር ፣ የድርጅታችንን ወቅታዊ ቁመና በማስረዳት የግል ታጣቂውን በሻለቃ አደራጅተን የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅና በወል መሬትና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን የመጨረሻ እልባት ተሰጥቷል።
ማህበረሰቡም አጥቶት የነበረውን ነፃነቱን በማግኘቱ ደስታውን ገልፆ ይህንን ነፃነት ለማፅናት የትኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርግና መስዋዕትነትንም ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ ገልፀውልናል።
የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ህዳር 08/2018 ዓ.ም
⚫️#ሞተ_ያለው_ማነው❓ #ጀግና_አይሞትም‼️
እስኪ ትንሽ ላውራ ስለነዚያ ጀግኖች ስለጊዮኖች (2)
እኔ እናገራለሁ ጀማሪ ብሆንም ፣
ጀግና ሲሰዋብኝ እኔ ዝም አልልም ።
ሽ አለቃ ሀይሌን ሞተ ያለው ማነው ፣
ሽ አለቃ ደምስን ሞተ ያለው ማነው ፣
በከዘራ ዱላ ዲሽቃ ያመጣ ነው ።
31 ሚለዮን ከጠላት መንጋጋ ነጥቆ ያወጣውን ፣
ጥይት ሳያባክን የጁላን ኮረኔል ማርኮ ሚይዘውን ።
ሞተ ያለው ማነው ???
ሽ አለቃ ሀይሌ አለዛሬ አልሞተም ፣
ሽ አለቃ ደምስ አለዛሬ አልሞተም ፣
በነሱ ላይ አይደል የታጠቀ ሁሉም ።
አወ ሞተ አትበሉ (2)
በሰከላ ምድር ሽኔን የቀበሩ ፣
በሰከላ ምድር ባንዳንም ቀበሩ ፣
አይ እነሱን ማየት ጠላት ሲያባርሩ ።
ስማቸው ሲጠራ ጠላት ዛሬም ፈሩ ።
ኧረ እንግጠም ብለው ክንድ ከሰነዘሩ ፣
በድልነው የመጡ ሂዱውም አልቀሩ ።
የጀግንነታቸው ምንይሆን ምስጢሩ ፣
ሰከላ ተወልደው ከየት ያወቁትን እንዴት ሁነው ይፍሩ ፣
አባይን ጠጥተው ጀማንም ጠጥተው እንዴት ሁነው ይፍሩ።
በዚች እንቁ ምድር አባይ መወለዱ ሆኖናል ጀግንነት ፣
ባንዳንም ጨነቀው ጠላትም አቃተው እየተፋ ሀሞት ።
አወ ጀግና አይሞትም !!!
ሰከላም አልፌ ወደሰሜን ልሂድ ደርሰው በመጡበት ፣
ያብሬን ተኳሹ ደምስ መጣ ሲሉት (2)
ጁንታም ገደል ገባ ጠፋ የሄደበት ።
ሻለቃ ሀይሌ አይአተኳኩስ (2)
አንተንም ነጠቀን አይሞት አይሞት ።
ኧረ ተማሪዎች እውነት ተናገሩ በወልዲያ ግቢ ስለነበራችሁ ፣
መንገዱም ተዘጋ፣ካፌውም ተዘጋ ጨነቀን ያላችሁ ፣
ጀግናው ሀይሌ አይደለም ከተፍ ያለላችሁ ፣
እሱ አሳፍሮ አይደለም ግዮን የገባችሁ ፣
ጀግናው ሀይሌ እኮነው ባለውለታችሁ ።
እስኪ በነካ እጄ ይልማናን ልዳሰው ፣
እስኪ በነካ እጄ ዴንሳንም ልዳሰው ፣
የዳባሉ በሬ አይ የይልማው በሬ እንሙት ያዛቸው ።
ወደ ዴንሳ ግድም ምን ተሰራ አትበሉ ፣
ወደ ይልማ ግድም ምን ተሰራ አትበሉ ፣
ሻለቃ አንሙት እሂያ ነበልባሉ ።
እኔን የገረመኝ እኔን የደነቀኝ እንዴት ብትወልድ ነው እንዲህ ያለጀግና አይ እናት እይ እናት ።
አረ መቼም አያልቅ የዚህ ጀግና ነገር ቢነገር ቢዘመር ፣
የዳባል ተራራ፣አቮላ ተራራ፣የይልማና ምድር ሆነጅ ምስክር ።
አወ ጀግና አይ ሞትም !!!
መሞት ከሆነማ በስጋ መሞት (2)
ፈጣሪስ ሞቶ አይደል የሁሉም አምላክ ፣
ፈጣሪ ቢሞትም ነግሶ አይደለ በአለም ፣
ጀግናም በታሪኩ ይነግሳል ዘላለም ።
ኧረ የአማራ ልጅ ኧረ የአማራ ልጅ አንዴ ልንገርህ ፣
መሞትህ ካልቀረ እደነዚህ ጀገና ታሪክ ሰርተህ ሙት ።
መታሰቢያነቱ ሰሞኑን በሰከላ ወረዳ ለተሰዋው ለጀግናው የአባግስ እሻለቃ መሪ እሻለቃ ደምስስ
ህዳር 3/2018
ፀጋየ ብዙአየ ኢትዮጵያ፣ አማራ፣ጎጃም፣ሰከላ፣ከጣሊያ ልጃምበራ 💪💪
08/ዐ3/2018 ዓ.ም
+2
የህዝብ አደረጃጀቱ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው!!
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ብሩኬ ደምሴ ክፍለጦር በመንዝጌራ ምድር ወረዳ 018 አናዝ ቀበሌ እና 019 ቀበሌን ጨምሮ በተለያዩ የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ቀበሌዎች ላይ የህዝብ አደርጃጅቶች ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው። በመሆኑም ከትግላችን ጎን ለጎን የማህበረሰብ አደረጃጀት ወቁቱን የጠበቀም ከመሆኑም በላይ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ትግላችን ከቀበሌ ወደ ወረዳ እያሳደግን በተለይም የማህበረሰብ አደረጃጀት ወሳኙ ምዕራፍ ስለሆን ወደ ማይቀርው ድላችን ለማደግ ሌት ተቀን እየሰራን እያደራጀን በአንድነት እንሔዳለን።
አማራ ጠሉን የአብይ አህመድ አረመኔያዊ ስራት ዘመን የወለደውን የታሪክ ጠላታችንን በተባበረ ክንዳችን አብርን በአንድነት እንመክራለን፣እንወያያለን፣እንደራጃለን፣እናቅዳለን፣ጠላትን በገባበት ገብተን ድባቅ እንመታለን።
መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
ህዳር 08/ዐ3/2018 ዓ.ም
የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እየከዳና እየኮበለለ ፋኖን እየተቀላቀለ ያለ መሆኑ ይታወቃል::
በዚህም የ104ኛ ኮር 16ኛ ክፍለጦር ሞርተር ተኳሽና ሁለት የክፍለጦሩ ስታፍ አባላቶች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 8/2018 ዓ.ም
👉የድል ዜና
በትላንትናው ዕለት በኤፍራታና ግድም ወርዳ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኋይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ ዕዝ ዓፄ ዘርዓያእቆብ ፩ኛ ኮር የ7/ለ70 ክፍለ ደመላሽ ሻለቃና የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ቃኘዎች በትላንትናው ዕለት ኦፕሪሽን መስራታቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
ሆኖም የአማራ ፋኖ የነፃነት ትግል ከጀመረበት ሰዓት ጀምሮ ሁልግዜም ውጊያ ላይ የምትውለው እንደለመደችዉ በታሪክ ላይ ታሪክ እየሰራች የጀግንነት ልኳን እያሳየች ትገኛለች። በመሆኑም የ7ለ70 ክፍለ ጦር ቃኚዎችና የደመላሽ ሻለቃ ከአጣዬ 3 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ ተረተር በተባለዉ ቦታ ላይ በነበረዉ ዉጊያ ድልን ተቀናጅተዋል።
በአዉደ ዉጊያዉም ህዝብን መቆሚያና መቀመጫ ያሳጠዉ የሀገር ጠባቂ ነኝ ባዩ የአብይ ወንበር አጠባቂ የብርሀኑ ጁላ ወታደር የ103ኛ ኮማንዶ እና ሆድ አምላኩ የአማራን ህዝብ በገንዘብ የሸጠዉ ሚኒሻ ጋር በመሆን ከአሳምነው አናብስቶች በአደረጉት ውጊያ ሙትና ቁስለኛ ከማድረግ በላይ ትልቅ ኪሳራ እንዲደርስበትም አድረገውታል።
በመሆኑም አርጋ ከበደን ለማጀብ የመጣው ኃይል የቀርው ህይወቱን ለማትረፍና የፋኖን በትር መቆቋም ሲያቅጠው እግር አዉጪኝ ብሎ ፈርጥጦ ወደ መጣበት ተመልሷል። በዚህም አዉ ደዉጊያ ትንታጎቹ ከጠላት በንብረትም ሆነ በአካል ብዙ ጉዳት በማድረስ ከጠላት ኃይል ድሎችን አግኝተዋል።
1. አንድ እስናይፐር ከነ ሙሉ ትጥቁ እና ከነሙሉ ተተኳሽ
2. አንድ መገናኛ እሬድዮ
3. ስድስት (6) ሙትና 12 ቁስለኛ
በማድረግ በድል በአንድዬ ክንዳቸው የድል ባለቤት ሁነዋል።
መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ💪💪💪💪💪
ህዳር 08/ዐ3/2018 ዓ.ም
የቀስተ ደመና ሻለቃ አባል የሆነው አርበኛ ንብረት 06 የጠላት ኃይሎችን ደምስሶና 04 አቁስሎ ራሱን በክብር ሰዋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ አባል የነበረው አርበኛ ንብረት ቢተው ዛሬ በቀን 08/03/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 ሰዓት የቀጋት ተብሎ በሚጠራ ቦታ ተወሽቆ የሚገኘውን ጡት ቆራጭ የብልጽግና ሠራዊት ዋርድያውን በሳንጃ ወግቶ ከገደለው በኋላ ብቻውን 6 የሚሆኑትን ደምስሶ 4ቱን አቁስሎ በክብር ራሱን ሰውቷል።
ጨፍጫፊው የብልጽግና ሠራዊት በወገኖቹ ላይ የሚያደርሰው ዘረፋ፣ ግድያና አሰነዋሪ ተግባር ያንገበገበው የጀግና ወላጅት የማሕጸነ ለምለሟ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ፍሬ የሆነው አርበኛው በጠዋት ተነስቶ ብቻውን ከጠላት ቀጠና በመግባትና ሰተት ብሎ ምሽጉ ላይ በመሄድ ዋርድያውን በሳንጃ ወግቶ በመግደል ከጠላት ምሽግ ተቀላቀለ።
እንደ ዱር አንበሳ በልበ ሙሉነት የተካነው ጀግናው አርበኛ በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት ጠላትን በጥይት አረር ይቆላው ጀመር። አንድ ለእናቱ ሽህ ለጠላቱ የሆነው የጀግኖች በረኸኞች ግርፍ የሆነው አርበኛ ንብረት በጠላት መንጋጋ መሀል ሆኖ ስድስቱን ከረሸነና አራቱን ካቆሰለ በኋላ በጠላት እጅ ላለመውደቅ እንደመይሳው ካሳ የገዛ ጥይቱን ጠጥቶ በክብር ተሰውቷል።
ህዳር 08/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ!
ዘላለማዊ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
#ሳተናው_ሻለቃ
አፋብኅ ምስራቅ አማራ ቀጠና የሚኒሊክ ዕዝ የልጅ ዕያሱ ኮር አሀድ የሆነው የየጎፍ ክ/ጦር አድስ የተመሰረተችው ሳተናው ሻለቃ ህዳር 08/2018 ዓ/ም አልብኮ 05 መሽጎ እነበረው የጡት ቆራጭ ስርዓት ዙፋን አስጠባቂ የገዛ ወገኑን በድንቁርና የሚጨፈጭፍ አድማ ብተና ሚሊሻና ፖሊስ ላይ ካፕ ድረስ ዘልቆ በመግባት የተሳካ ኦፕሬሽን የፈፀመች ሲሆን 3 አድማ ብተና ወዲያውኑ ሲሞቱ 7 አድማ ብተናና እና ሚሊሻ ከባድ ቁስለኛ ሆነው ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ንስር አማራ ከአፋብኃ ሚኒሊክ ዕዝ የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ አረጋግጣለች‼️
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
08/ዐ3/2018 ዓ.ም
+1
የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ የመሬት ዘረፋና ወረራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!
በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ከተማ የህዝብ ሃብት የሆኑ የከተማ ቦታዎች በአማራ ህዝብ ሃብት አማራውን መጨፍጨፍ በሚለው የብልፅግና አገዛዝ መርህ መሰረት ለጨረታ ቀርበዋል::
ስለሆነም አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ መሬት ዘረፋንና ወረራን አስመልክቶ ከሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሆነና በስራ ላይ ያለ መመሪያ እንዳወጣ የሚታወቅ ሲሆን ባለሃብቶች አሁንም ይሄ ጊዜ ማለፉና መንጋቱ ስለማይቀር፣ በተመሳሳይ የህዝብ ሃብትም ጊዜውን ጠብቆ ለህዝብ መመለሱ ስለማይቀር፣ የህዝብን ሃብት በህገወጥ መንገድ መግዛትና ህዝባችን ላይ ዘር ማጥፋት ለሚፈፅም አገዛዝ ለጦር መሳሪያ እና ለተተኳሽ መግዣ ገንዘብ ማስገኛ እንዳትሆኑ ስንል ጥብቅ ማስጠንቀቂያችንንና መልክታችንን እናስተላልፋለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 8/2018 ዓ.ም
ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እየተፈፀመ ያለውን የመሬት ወረራ አስመልክቶ ከምኒል ዕዝ የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ!
በሁለንተናዊ አቅሙ አከርካሪው የተመታው አገር አፍራሹ ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በተለይ ደግሞ በገንዘብ አቅሙ በከፍተኛ ሁኔታ የተዳከመ መሆኑ አለም ያወቀው የአደባባይ ሐቅ ነው::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በአማራ ህዝብ ሃብትና ገንዘብ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለው የአብይ አህመድ አገዛዝ የደረሰበትን ከፍተኛ የገንዘብ ችግር ለማስታገስ በከፍተኛ ደረጃ የህዝብ ሃብት የሆነ የመሬት ወረራና ዘረፋ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል::
በዚህም በበርካታ የቤተ-አማራ አካባቢዎች የመሬት ወረራው ተጠናክሮ መቀጠሉን በተደጋጋሚ መግለጫዎች ያሳወቅን ሲሆን አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሎ ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ባደባባይ የሚታወቁ የህዝብ የሆኑ መሬቶች ለጨረታ መቅረባቸውንና አንዳንዶቹም በአገር አፍራሽ ሆድ አደር ካድሬዎች፣ የፀጥታ ሰዎች፣ ስግብግብ ባለሃብቶች እና ህገወጥ ደላላዎች ትብብርና ጥምረት ውስጥ ለውስጥ የተሸጡም እንዳሉ ለማረጋገጥ ችለናል::
ቆቦ ከተማ በተጠቀሱት ፀረ-አማራ ሃይሎች ለዘረፋ የታጩትና ተዘርፈው በድብቅ እየተሸጡ ያሉ ቦታዎች ባደባባይ የሚታወቁና የህዝብ ሃብቶች ሲሆኑ እነዚህም፦
• ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ
• ቆቦ ከተማ እህል ሰብል
• ቆቦ ጊራና ሸለቆ መስሪያ ቤት
• ቆቦ ከተማ መናህሪያ
• ቆቦ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ
• ቆቦ ከተማ እርሻ ምርምር
• ቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ
• ቆቦ ከተማ ቅዳሜ ገበያ
• ቆቦ ከተማ የድሮው ቴሌ
እነዚህ የተዘረዘሩትና እና ሌሎችም መሰል በስም ያልተጠቀሱ የህዝብ ሃብት የሆኑ የከተማ መሬቶች የገንዘብ አቅሙ በተዳከመውና የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ መክፈል ያቃተው የብልፅግናው አገዛዝ ህዝባችንን በጅምላ ለሚጨፈጭፉና ለሚያስጨፈጭፉ ሚሊሻና አድማ ብተና የደመወዝ መክፈያ እንዲሁም የሴሰኛ ካድሬዎች ሆድ መሙሊያ ሊሆኑ እንደማይገባ በፅኑ እናምናለን::
ስለሆነም ከሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም ፋኖ የፖለቲካ ትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ህዝባችን ላይ በፓርላማና በምክር ቤት አዋጅ አውጆ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ያለ ፋሽስታዊ አገዛዝ የህዝባችንን ሃብት ለህዝባችን ማጥፊያ እንዲያደርገውና እንዲጠቀምበት ስለማንፈልግና ስለማንፈቅድ ፋኖ መሬት እንዳይመራና ለጨረታም እንዳይቀርብ አዋጅ ማወጃችን ይታወቃል::
ይሄ ጊዜ አያልፍምና አይነጋም መስሏችሁ አዋጃችንን ተላልፋችሁ የህዝባችንን ሃብት ከፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ እየገዛችሁ ያላችሁ ጥቂት ስግብግብ የመሬት ነጋዴዎችና ባለሃብቶች ብሎም ህገወጥ ደላላዎች በትግላችን ድል እንደምናደርጋችሁና የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ ለህዝብ እንደሚመለስ ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን!
ይህንን ፀረ-ህዝብ ተግባር በመፈፀም ህዝባችንን ለሚጨፈጭፍ ጠላት ደመወዝ እየከፈላችሁ እና ከክላሽ ጀምሮ እስከ ታንክና መድፍ ብሎም ጄትና ድሮን ተተኳሽ እየገዛችሁና እያቀረባችሁ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ መንገድ የገዛችሁት መሬት ቀርቶ ሌላው ሃብትና ንብረታችሁ ብሎም ህይወታችሁ አደጋ ላይ እንደሆነ ለማሳወቅም እንወዳለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 8/2018 ዓ.ም
ከአፋብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ከ109 ኮር 77 ክ/ጦር ከፍኖተሰላም ሻለቃ የተሰጠ ማስጠንቀቅያ❗️
✍️ ለመንግስት ሰራተኞች ደምወዝ መክፈል ያቃተው አረመኔው ጡት ቆራጩ መንግስት በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ቦታ ጫራታ ያወጣ መሆኑን ደርሰንበታል።
ይህን የደረሰዉ የአፋብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77 ክፍለጦር የፍኖተ ሰላም ሻለቃ ይህን ጫራታ ከወጣበት ከዛሬዋ ቀን ጀምሮ ጫራታ መጫረት እንደማይቻል ከወዲሁ እናሳዉቃለን።
ይህን ማስጠንቀቂያ በቸልተኝነት አይቶ ተላልፎ የተገኘ ማነኛዉንም ተጫራች መሬቱም ለማህበረሰቡ ተመልሶ ግለሰቡ ላይ የማያዳግም እርምጃ የምንወስድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን።
የፍኖተ ሰላም ሻለቃ!!
#የትግል_ጥሪ ‼️
ለሁሉም የኮማንዶ የአየር ወለድና የልዩ ሀይል እንዲሁም የአማራ ልዩ ሀይል ኮማንዶዎች በሙሉ፦
የአማራ ፋኖ ትግል በዚህ የሁለት አመት ተኩል ዉስጥ ከባዶ እጅ እና ከተበታተነ አወቃቀር እስከ ነብስ ወከፍ እና ቡድን እስከ ከባድ መሳርያ የታጠቀ የእዝ አደአጃጀት ደረጃ አድጓል። ይሁንና ትግላችን ብዙ ማደግና መደራጀት የሚጠበቅበት ስለሆነ የቀደመ የትግል አጋሮቻችን ከአባል እስከ ማእረግተኛ የአማራ ችግር መፈናቀልና መጨፍጨፍ ያሳስበናል የምትሉ ወገኖች ያላችሁን ልምድና ብቃት ህዝባችሁን ከጥፋት ለመታደግ እንድታዉሉት በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።
ከአማራ ክልል እስከ መላዉ ኢትዮጵያ በአሰቃቂ ሁኔታ እየፈሰሰ ያለዉን የአማራ የደም ጎርፍ ማስቆም የሁሉም ታሪካዊ አደራ ነዉና ያለቅድመ ሁኔታ እንድትቀላቀሉና ከጎናችን እንድትሰለፉ ጥሪ እናቀርባለን ።
ኑ ለአማራ ሚዛን የሆነ የኮማንዶ ሀይል እናሰልጥን እናደራጅ እንገንባ !
©አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማእከላዊ ኮማንድ አባል
08/ዐ3/2018 ዓ.ም
