ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 413
مشترکین
+2224 ساعت
+437 روز
+1 38430 روز
آرشیو پست ها
የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ በመግባት ስድስት መንደሮችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል የክልሉ መንግስት ወነጀለ። የአፋር ክልል መንግስት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ “በአስቸኳይ ካልተቆጠበ”፤ ራሱን “ከውጫዊ ጥቃት” የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስጠንቅቋል።
የአፋር ክልል መንግስት ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው፤ ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ገደማ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አማካኝነት ባወጣው አጭር መግለጫ ነው። ክልሉ በዚሁ መግለጫው “ጠብ ጫሪ” እና “ከጥፋቱ የማይማረው” ሲል የጠራው የህወሓት ቡድን፤ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 26፤ 2018 ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ “የካባድ መሳሪያ” ተኩስ መክፈቱን አስታውቋል።
ተኩስ የተከፈተባቸው አካባቢዎች በአፋር ክልል፣ ዞን ሁለት፣ መጋሌ ወረዳ፣ ቶንሳ ቀበሌ የሚገኙ አካባቢዎች መሆናቸውንም ክልሉ ገልጿል። የህወሓት ቡድን የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ ጥቃት ፈጽሞባቸዋል የተባሉት አካባቢዎች፤ ዋራዓ እና ሚልኪ የሚል መጠሪያ ያላቸው ናቸው።
“የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንዲመለሱ ቢማጸኗቸውም፤ ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል” ሲል የአፋር ክልል በዚሁ መግለጫው ላይ ወንጅሏል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከትላንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር፤ “በከሃዲነት” እና “በወንጀለኛነት” የፈረጁትን የህወሓት ቡድን “ጉጅሌ” የሚል ስያሜ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የስብሰባ_መረጃ_ባህርዳር ‼️
አገዛዙ አርብ ማለትም በቀን 28/02/2018 ዓ.ም በባህርዳር ሙሉ ትምህርት ቤቶችን ዘግቶ መምህራን እና ሰራተኞች ላይ የተለመደ ለሀጩን ሊያዝረከርክ ዝግጅቱን ጨርሶ ተፈፃሚ እንዲደረግ ለትምህርት ቤት አመራሮች ትዛዝ የሰጠ ሲሆን በሱፐርቫይዘሮች አማካኝነት የተላለፈው መልዕክት ከታች ተያይዟል
👇👇👇👇👇👇👇
ለሁሉም የግልና የመንግስት ት/ቤት መምህራን ከኬጅ_8ኛ ክፍል ሠራተኞች በ28/2/2018 ዓ,ም በመምሪያ ደረጃ ስብሰባ /መድረክ / ስላለ/ ሁሉም በሚዘጋጀው መድረክ እንድትገኙ ከወዲሁ እያሳወቅን በዕለቱ ትምህርት የለም ዝግ ነው ::ጥሪ መጠራቱን ፊርማ ተዘጋጅቶ እንዲፈርሙ ይደረግ በማይገኙት ላይ ሃላፊነቱን ት/ቤቱ ይወስዳል የስብሰባ ቦታ ስዓት ወደፊት ይገለፃል !!
ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት የንስር አማራ ምንጮች መረጃው አናብስቱ ይጠቀምበት ዘንድ አስተላልፈዋል ።
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
"እናቴን አምጡ" የሕፃኑ ታምራት አውግቸው ተማፅኖ።
EOTCMK TV ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
እናትና አባት ከተጋቡ ወደ አስር ዓመት ገደማ እንዳስቆጠሩ የቅርቦቻቸው ይናገራሉ።
ኑሯቸው በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ ነውና እንደ ሀገር እና አካበቢ ማኅበረሰብ ሁሉ የዕለት ጉርስ የዓመት ቀለብ የሚያገኙት ደረቁን መሬት አለስልሰው ፣ ከብቶች አርብተው ባገኙት ጥሪት ነው። የሕጻን ታምራት አውጋቸው ወላጆች።
የዚህ ብላቴና ቤተሰቦች በክርስትና ሕይወታቸውም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ሳይሱሙና የፈጠራቸውን ሳይማልዱ ውለው አያድሩም። እንደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መጾም ፣ መጸለይና ማስቀደስ ግዴታ መሆኑን በተግባር መፈፀማቸውንም መረጃውን ከነገሩን ከቅርቦቻቸው ሰምተናል።
የታምራት ቤተሰቦች በቀያቸው በነበሩበት ወቅት በትዳር አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ አፍርተዋል ።
አበው እንደሚሉት የቀንም ጎዶሎ አለና በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ በሚገኘው የመኖሪያ ቀያቸው ሐሙስ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ሀገር ሰላም ቀየው አማን ብለው በተኙበት ሰዓትን ቆጥሮ ለመግደል የሚፋጠን እግርና እጅ ከለሊቱ 6:00 ላይ ወደ ኦርቶዶክሳዉያኑ ቤት አመራ።
ሞት በራቸውን ያንኳኳው የታምራት አውግቸው ቤተሰቦችና ጎረቤቶቻቸው በድቅድቅ ሌሊት እየተገፈተሩ ከቤታቸው በማስወጣት ከደጃፋቸው በሚገኘው ሜዳ ላይ ደርድረው አንበረከኳቸው።
በወቅቱ ብላቴናው ከእናቱ ጀርባ ላይ እንደነበር ያዩ ምስክሮች ነግረውናል።
ታዲያ የታምራት እናት እና አስራ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች በዘነበባቸው ተኩስ ሕይወታቸውን ማትረፍ ሳይችሉ እስከ ወዲያኛው ላይመለሱ አሸለቡ።
በሰዓቱ ሕፃን ታምራት ከመሬት ወድቃ የእናትነት ትንፋሿ ሲርቀው እናቱ ከወደቀችበት እንድትነሳ ይማፀናት ጀመር።
ይህንን የሰሙ እነዛ የታጠቁ ኃይሎች ልጅነቱ ሳያሳሳቸው ወገኖቹ የቀመሱትን ጥይት እነሆ ሲሉ ተኮሱበት።
ሕፃን ታምራት አውግቸውም በደረሰበት ጉዳት መቋቋም አቅቶት ከእናትና ከብዙ ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን አጠገብ ወደቀ።
በሰዓቱ የሚደርስላቸው ባለመኖሩ የብላቴናው እግር ላይ ያሉት የደም ስሮች ተፈጥሯዊ የደም መዘዋወራቸውን ለማከናወን ተሳናቸው።
አይነጋ የለምና በአስክሬን መሀል ራሳቸውን ከአገኙት መካከል አንዲት የ8 ዓመት ታዳጊ የሰው ያለህ እያለች ትጣራ ጀመር።
አካባቢ ከማታ ይልቅ በጥቂቱም ቀን የተሻለ ነውና ሕፃናቱን ወደ ሕክምና፣ ቤተሰቦቻቸውን ደግሞ አፈር ለማቅመስ በአካባቢው ወደ ሚገኘው አጥቢያ አመሩ።
በሕፃናቱ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት አዳማ ለሕክምና ቢመጡም የታዳጊ ታምራት ጉዳት እጅጉን በማየሉ ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሊመጣ ችሏል።
ሕፃን ታምራት ከእግሩ ባሻገር ሌሎች የሰውነቱ አካላት ላይ ጉዳት ስለደረሰበት የሕክምና እርዳታ ሊደረግለት ችሏል።
ይሁን እንጂ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ በሆስፒታሉ የሕክምና ባለ ሙያዎች ትእዛዝ መሰረት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 አንድ እግሩ ሊቆረጥ ችሏል።
ይህ ብላቴና ከእግሩ መቆረጥ በተጨማሪ በቤተሰቡ ናፍቆት እየተሰቃየ ይገኛል ሲሉ አስታማሚዎቹ ይናገራሉ።
የሕመም ስቃዩን የአልቻለው ይህ ታዳጊ በአሁኑ ወቅትም "እናቴን አምጡ እያለ" ክፉኛ እንደሚያለቅስና ከፍተኛ ስነ ልቡናዊ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የሕፃን ታምራት ቤተሰቦች እና ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ቤተክርስቲያንን ብለው በአካባቢው ባለመራቃቸው ይህ አይነት አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚሉት አስታማሚዎቹ ከጥቃቱ የተረፉትን ሕፃናት ልጆችን የመንከባከብ እና የማሳደግ ኃላፊነት የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ነው ይላሉ።
በተለይም ለብላቴናው ሰው ሰራሽ እግር ፣ ወደ ጤናው ሲመለስ ትምህርትና መሰል እገዛዎችን ከቤተክርስቲያንና ከምእመናን እንጠብቃለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በተመሳሳይ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው የ8 ዓመቷ ታዳጊ የእነ ታምራት የቅርብ ጎረቤት ስትሆን በአሁኑ ወቅት በአዳማ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።
በአርሲ ሀገረ ስብከት በርካታ ኦርቶዶክሳዉያን በጭንቅ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ላሉት ልንደርስላቸው ለተጎዱት ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል መልእክታቸው ነው።
የታምራት አባት ከዚያች ምሽት በኋላ የት እንደሚገኙ ማወቅ እንደማይቻል እና እህቱ ደግሞ ቤተሰብ ጋር መሆኗን ሰምተናል።
©ማኅበረ ቅዱሳን
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
ፓዊ ያለው ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ኃይል ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ወደ እንጅባራ .ኮሶበር መስመር ተንቀሳቅሶ መገንጠያ ደርሷል የወገን ኃይል አስፈላጊውን ክትትልና ጥንቃቄ ያድርግ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል‼️
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
+7
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ99ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ፣ በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
የአርሲው ጭፍጨፋ
🛑እነዚህ አርሲ የተጨፈጨፉ አማሮች ምናቸው ነው ኦሮሞ የሚመስለው?
🛑 አርሲ ውስጥ የኦሮሞ ክርስቲያን ከየት መጣ?
🛑 የተካሄደው የኦርቶዶክስ ጭፍጨፋ ሳይሆን የአማሮች ጭፍጨፋ ነው!!
"ኢትዮጲያ አትፈርስም" የሚለው ተምኔታዊ አስተሳሰብ የፈሪዎች እና የሰነፎች ፓለቲካ ነው።
ብልፅግና ፓርቲ እና አስተሳሰቡ ኢትዮጲያ ከተሰራችበት ስሪት አንፃር ስናየው በፍፁም ሃገር አፍራሺ ነው።
በመሰረታዊነት ኢትዮጲያ ለዘመናት የእርስ በእርስ ግጭት በነበረባት ጊዜ እንኳ የማዕከላዊ መንግስቱ ደካማ አልነበረም!!
ሰዎች ኢትዮጲያ አትፈርስም ስንት ነገር ተሻግረን እዚህ የደረስን ሃገር ነን የሚል አጉል ጨዋታ ሲጫወቱ እንሰማለን።
እውነታው ግን ኢትዮጲያ በአብይ አህመድ ዘረኛ እና ጠቅላይ አገዛዝ ወደ ብተና ጫፍ እየሄደች መሆኑ ነው።
በብልፅግና አስተሳሰብ እና ርዕዮተ ዓለም ሃገር ማለት በድህነት፣በእርስ በእርስ ጦርነት፣በስደት እና በዘረኝነት የብሔር እና ብሔረሰብ ህዝቦች ላይ የሚደረሰው ሰው ሰራሺ እና መዋቅራዊ ግፍ ስኬት መሆኑን አይተናል።
ስለዚህ ብልፅግናን እንደ ህዝብ መዋጋት የማንችል እና በጋራ ቆመን የሃገሪቱን ህልውና ማስጠበቅ ካልተቻለ እመኑኝ ኢትዮጲያ እንደ ሃገር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባታል።
ብልፅግና ስለ ሰላም የሚሰብከው በሰፋቸው መሪዎች እና ልሂቃን ስም እንጅ በመላው ኢትዮጲያ ውስጥ፣በጎረቤት ሃገራት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር አገዛዙ ቅጥረኛ እና ደንታቢስ የአላዋቂዎች ስብስብ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
"ኢትዮጲያ አትፈርስም " የሚለው ተምኔታዊ ሃሳብ የፈሪዎች እና የሰነፎች ፓለቲካ ነው።
በሰላም እጦት፣በኢኮኖሚ ድቀት እና በራስ ጠልነት የተጠቃው ህዝብ በመጨረሻም አዳኙ ማን ይሆን ትላላችሁ??
ስለሆነም ሃገር ወደለየለት ፍራስራሺነት ከመግባቷ በፊት ኢትዮጲያውያን ከአማራ ፋኖ እና አገዛዙ ላይ ነፍጥ ካነሱ ሁሉ እንዲትቆሙ አደራ እላለሁ።
ሃገሩን ከባዕዳን በሚገኘው ብድር እና መሳሪያ ወገኑን የሚጨፍጭፍ መንግስት እንደት ህዝባዊ ቅቡልነት ኖሮት ሃገረ -መንግስቱን ሊያስቀጥል ይችላል??
የህዝብን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ሁሉ ባዳ እና ባንዳ በሚል አድስ ትርክት በየሰፈሩ የሚጮኸው የብልፅግና ዕጅ አስታጣቢ በየት ሞራሉ ነው የአማራ ፋኖን ሰራዊት የሚከሰው??
አብይ አህመድ እኮ የኢትዮጲያን ብሔራዊ ጥቅም እና ሉአላዊ ግዛት አሳልፎ የሰጠ ባንዳ ነው።
ታዲያ በምን ሞራሉ እና ፋኖን እና ትግሉን ሊያሸንፍ የሚችለው??
ቅጥረኝነትን እና ተገዥነት ከአሜሪካ እስከ ግብፅ እና አረብ ኤምሬት ሃገሩን ለባዕዳን ሲሰልል የነበረ ሰላቶ እንደት የህዝብ ልጆቹን እውነተኛ ትግል መቀልበስ ይችላል።
ስለሆነም ትግላችን እየፈረሰች ባለችው ሃገር ፍርስራሺ ላይ ህልውናችንን ለማትረፍ ጭምር ነው።
"ሃገሬ በሰማይ ነው" ከሚሉት ወገን አይደለንም!!
አባቶቻችን እና ቀደምቶቻችን ሃገር ሲሰራ እና ሲገነባ እንደት እንደነበር አስተምውን አልፈዋል።
እኛ ልጆቹ ደግሞ በዘረኛ እና ጠቅላይ አገዛዝ ሃገር የብተናዋ ጫፍ ላይ ስለደረሰች ደም ገብረን፣አጥንት ከስክሰን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ የጀመርነው የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል ያሸንፋል እንላለን።
ዓላማችን ብሔራዊ ንቃት ያለው ማህበረሰብ በመገንባት የህዝብንና እና የሃገርን ህልውና መታደግ ከሚችሉት ጋር በመቆም ሃገረ መንግስቱን ማስቀጠል ነው።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ጥቅምት 26-02-2018
ጋሸና ዙሪያ ላይ የደጋው መብረቅ ኮር ከየ ክፍለ ጦሮቹ በተውጣጡ ሻለቆች ጥላትን ስቦ በማስገጥና ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም በተደረገው አውደ ውጊያ በርካታ የፋሽስቱ ሰራዊትን ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ የሚኒሻና የፖሊስ አባላቶች በየግለሰብ ቤት እየተበተኑ የገቡና የተደበቁ ሲሆን ከተደበቁበት ጓዳ እየተመዘዙ በንስሮቹ ገቢ ተደርገዋል።
አውደ ውጊያው ከወትሮው በይዘቱ የተለየና በጋሸና ዙሪያ በጥላት ላይ ጠንካራ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን ከዚህ ቀደም ነፃ የወጡ ቀጠናዎችን ከማፅናት ባለፈ ተጨማሪ ቦታዎችን መቆጣጠር ተችሏል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር የሚድያ ክፍል
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
+6
ምኒልክ ዕዝ ነፃ ባወጣቸው ቀጠናዎች ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ የህዝብ አስተዳደር መዋቅር እየዘረጋ እንደሆነ ይታወቃል::
በዚህም በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ህዝብ ጋር ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ህዝቡ የመረጣቸውን አመራሮች በመሾም አራት ንዑስ ወረዳዎችን በማሰባሰብ የአምባሰል ወረዳ አስተዳደርን መስርቷል:: በቀጣይም ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላት በደምበጫ የጎመዲ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ማቻክል ግራ ቅዳምንና አማኑኤል ከተማ ላይ በጡት ቆራጩ የብልጽግና አሽከር ላይ ከፍተኛ እርምጃ ወስደዋል።
የአንድ ፋሽስታዊ ሥርዓት ሎሌ በመሆን የገዛ ወገኑን በአሰቃቂ ሁኔታ በመጨፍጨፍና በመዝረፍና አያሌ እኩይና አስነዋሪ ተግባራትን በመፈጸም የተጠመደው ወራሪው የብልጽግና ሠራዊት በየደረሰበት ሁሉ እንደ እብድ ውሻ ያገኘው ሁሉ የሚያባርረውና የሚነርተው ሆኗል።
በዛሬው ዕለትም የደምበጫዋን ዋድ አዲስ ዓለምን ለመውረር ሙከራ ያደረገው የአብይ ዙፋን አስጠባቂ በኢንጅነሩ ልጆች አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ ተመልሷል። የኢንጅነሩ ልጆችን በትር መቋቋም ያቃትው የአገዛዙ አራሙቻም የጋሪ ሰራተኞችን ስልክ ሲዘርፍ ውሏል።
በተያያዘ ዜና የማቻክሏ ግራ ቅዳምንን ለመውረር የወጣውን ጠላት ጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ ፋኖዎች ተቀብለው ግራ ቅዳምን ከተማ ላይ ላይ ፈርጣማ ክንዳቸውን ሲያሳርፉበት ውለዋል።
በተመሳሳይ ሰዓትም ጀግኖቹ የበላይ ዘለቀ ሻለቃ ፋኖዎችና የቴዎድሮስ ዕዝ ኮማንዶዎች አማኑኤል ከተማ በመግባት በጠላት ላይከፍተኛ ጥቃት ፈጽመዋል።በዚህ ግምባርም ጠላት በፔምፒና በዙ- 23 የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም በርካታ ቁጥር ያለው የጠላት ሠራዊት ተደምስሷል። በተጨማሪም አንድ የጠላት ፓትሮል ከነሙሉ ሠራዊቱ ወድሟል።
በአሁኑ ሰዓትም ጠላት አስከሬኑን በብዛት እየለቀመ ይገኛል።
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
ድል ለአማራ ፋኖ!
የአርሲው ጥቃት ሰለባ የሆነው ሕፃን ታምራት አውግቸው የቀኝ እግሩ ተቆረጠ።
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው ክርስቲያን ሆስፒታል ሲታከም የሰነበተው የአራት ዓመቱ ሕፃን ታምራት አውግቸው፥ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ቀትር ላይ በጥይት የተደበደበው እና የተመረዘው እግሩ ተቆርጧል ተብሏል።
የሆስፒታሉ ሐኪሞች እግሩ ሳይቆረጥ አሰፊላጊውን ሕክምና አድርገው ለማዳን ጥረት ቢያደርጉም፥ አልተሳካም። ሕመሙ ለሕይወቱ አስጊ እየሆነ በመምጣቱ የተነሳ እግሩን ለመቁረጥ እንደወሰኑም ለማወቅ ተችሏል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አምሐራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በመርሀ ቤቴ እና ጅሩ ቀጠና የጥላትን ሀይል ማራገፉን ቀጥሏል
==============
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ደቡብ አምሐራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ በመራሀ ቤቴ እና ጅሩ በተለያየ አቅጣጫ የመጣ ጥምር የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወደ መጣበት ተመልሷል::
ጥቅምት 24/2018 ዓ ም የፋኖ ጠንካራ ይዞታ የሆኑትን አካባቢዎች ለመቆጣጠር እቅዱን አስፍቶ ከለሚ÷ ከጀማ እና መርሀ ቤቴ በሶስት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰው የብረሃኑ ጁላ ጀበና ሰባሪ አየር ወለድ ኮማንዶ÷ አድማ ብተናና ሚኒሻ የአጼ ዘርዓ ዓይቆብ አንደኛ ኮር የአጼ ይኩኖ አምላክን እና ናደው ክፍለ ጦር ምት መቋቋም አቅቶት ወደኋላ ተመልሷል::
በተለይም ከለሚ እንሳሮ ወደ ፋኖ ጠንካራ ይዞታ የተንቀሳቀሰው የጥላት ሀይል ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ ለማጥቃት በሶስት አቅጣጫ የመጣው ይህ የጥፋት ቡድን የእቅድ ለውጥ በማድረግ ሙትና ቁስለኛውን ለማውጣት ርብርብ ሲያደርግ ውላል::
በዚህ አውዴ ውጊያ 28 የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ሲደመሰብ ከ27 በላይ ከባድ ቁስለኛ እንደነበር የውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን መረጃውን አድርሰውናል::
በሌላ ዜና ጥቅምት 25/2018 ዓ ም ከሬማ ወደ መርሀ-ቤቴ አለም ከተማ በሁለት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲጓዝ በነበረ የጥላት ሀይል ላይ በተወሰደ እርምጃ ከባድ ጉዳት ማድረስ ተችሏል::
ኦፕሬሽኑ በፊት አውራሪ ባዩ አለባቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተወሰደ ሲሆን ጥቃቱ በጥላት ላይ ከባድ ድንጋጤ ፈጥሯል::
መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
© አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼️
ወልድያ ከተማ ዙሪያ ማለትም፦ ቃሊም፣ ጃርሳ፣ አፍሪኬር፣ ገዶ በር፣ ሰዋሜዳ፣ ወይንየ፣ ስንድዱት እና በሌሎች የከተማዋ አከባቢዎች ላይ ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም ከረፋድ ጀምሮ የድሮን ቅኝት እየተካሄደ ነው።
ነውረኛው የዐብይ አህመድ ቡድን፡ ለገበያም ሆነ ውሃ ለመቅዳት፣ ወፍጮ ቤትም ሆነ ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጂድ ላይ ሰዎች ተሰብስበው ካየ የድሮን ጥቃት ሊፈፅም ስለሚችል፡ ማሕበረሰቡ ለጥቃት ከሚያጋልጡ ድርጊቶች በመቆጠብ እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክቱን ላልሰሙት አሰሙ።
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
የአሜሪካው የአማራ ማኅበር ካለፈው ሳምንት ጥቅምት 27 እስከ ህዳር 2 ቀን 2025 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሳምንታዊ ሪፖርቱን ይፋ አዳረገ።
ሪፖርቱ በአማራ ክልል በፋኖ ኃይሎች እና በብልጽግና አገዛዝ ኃይሎች መካከል ጦርነቶች ተስፋፍተው መቀጠላቸውን አመልክቷል።
በአጠቃላይ በ10 ዞኖች በሚገኙ ከ34 በላይ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የውጊያ ክስተቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መመዝገባቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።
ሪፖርቱ በሳምንቱ ውስጥ በስድስት ወረዳዎች የሲቪል ጉዳት መመዝገቡን የጠቆመ ሲሆን፣ በተለይም በራያ ቆቦ፣ በኤፍራታና ግድም፣ በደብረ ታቦር፣ ታች ጋይንት፣ ፎገራ እና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች መጠቀሳቸውን አስፍሯል።
ሪፖርቱ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ጉና፣ እንኮሌ-ዋቤ እና ሸርካ ወረዳዎች ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ግድያ፣ አፈና እና የንብረት ውድመት መፈጸሙን በዝርዝር አስፍሯል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስም በጥቅምት ወር ብቻ በምሥራቅ አርሲ ዞን 25 የእምነቱ ተከታዮች መገደላቸውን እንዳወገዘ ሪፖርቱ አስታውሷል።
“የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ድንበር አስመላሽ ኮሚቴ" ያወጣውን መግለጫ በመጥቀስ፣ ሪፖርቱ የትግራይ ኃይሎች በአላማጣ፣ ኮረም እና ራያ ባሉ አካባቢዎች ግድያ፣ ድብደባ፣ እገታ፣ የንብረት ዝርፊያና ማፈናቀል መፈጸማቸውን ከሷል። ሪፖርቱ እንዳመለከተው፣ በራያ ባላ ወረዳ 12 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ከ60,000 በላይ ሕፃናት ትምህርት ቤቶች ወደ ወታደራዊ ካምፕ በመቀየራቸው ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል።
የትግራይ ኃይሎች በራያ አላማጣ አንድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪን ማሰራቸውን፣ የመንግሥት ኃይሎች ደግሞ በሰሜን ሜጫና ፎገራ ወረዳዎች ሰዎችን አግተዋል ሲል ሪፖርቱ ገልጿል።
ሪፖርቱ፣ የተለያዩ የፋኖ አዛዥ እዝ ክፍሎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈጽመው "ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ" ማድረሳቸውን የሚገልጹ መረጃዎችን በዝርዝር አስፍሯል።
በሰሜን ወሎ ባሉ ወረዳዎች የፋኖ ኃይሎች ከአገዛዙ ኃይሎች ጋር ከባድ ውጊያ ማድረጋቸውንና በጋሸና ሆስፒታል የቆሰሉ ወታደሮች መታየታቸውን ሪፖርቱ ጠቅሷል። በላስታ፣ ዋድላ እና ጊዳን ወረዳዎችም ተመሳሳይ ከባድ ውጊያዎች ተካሂደዋል።
በደቡብ ጎንደር፦ በደራ፣ እስቴ፣ ታች ጋይንት እና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች በተደረጉ ውጊያዎች የፋኖ ኃይሎች ስኬት እንዳስመዘገቡና ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል። በተለይ በደራ ወረዳ "ጨሮ ተራራ"ን መቆጣጠራቸውን ገልጿል።
በምሥራቅ ጎጃም፦ በስናን ወረዳ፣ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አቅራቢያ በተደረገ ውጊያ ከ100 በላይ የመንግሥት ወታደሮች መገደላቸውን፣ ከ60 በላይ የጦር መሳሪያዎች መማረካቸውንና 3 ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን የፋኖ ምንጮችን ጠቅሶ አስፍሯል።
በሰሜን ጎንደር፦ በመተማ እና ቋራ ወረዳዎች በተደረጉ ከባድ ውጊያዎች በድምሩ 95 የመንግሥት ኃይሎች አባላት መገደላቸውንና ከ80 በላይ መቁሰላቸውን ሪፖርቱ ዘርዝሯል።
በሰሜን ሸዋ፦ በመርሃቤቴ፣ ሚዳ-ወረሞ እና ቡልጋ ወረዳዎች በተደረጉ ውጊያዎች የፋኖ ኃይሎች ከፍተኛ መጠን ያለው ወታደራዊ ቁሳቁስ መማረካቸውንና የመንግሥት ኃይሎች ከቱለፋ ከተማ ለቀው መውጣታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል።
የድል ዜና
የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል
በአርቤጅ መካናይዝድ በታገዘ ውጊያ ድባቅ ተመታ።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር ዛሬ በቀን 26/02/2018 ዓ.ም በወሰዱት እርምጃ ሙትና ቁስለኛ ሆነ።
ሆኖም የአገዛዙን ጡት ቆራጩ ኃይ በኤፍራታ ግድም ወርዳ ጎሳ አልፋ ምድር አካባቢ በ R P G መካናይዝድ በታገዘ ደፈጣ ውጊያ ፋኖዎች አሉበት ወደ ተባለበት እየመጣ ባለበት መረጃዎች በብርሃን ፍጥነት በሰሙት የአሳምነው ልጆች ከመሃል መዲ በመነሳት ወደ መንዝ ጓሳ ያደረገው እንቅስቃሴ ሳይሳካ በጅግኖቹ ሙትና ቁስለኛ እንዲሆን ተደረጓል። በመሆኑም አሁን በዚህ ስዓት የጠላት ኃይል በአናብስቶች በተወሰደበት እርምጃዎች ሙትና ቁስለኛውን አንቡላንስ በማሰለፍ እያጓጓዘ ይገኛል።
ይበንዲህ እንዳለ የአብይ አህመድ ጡት ቆራጩ ኃይል ኃይሉን አሁንም ከተለያዩ ቦታዎች ለመጨመር እንቅስቃሴ እያደረገ ስለሚገኝ ይህን ኃይል በገባበት ገብተን የአማራ እናት ለአንዲና ለመጨረሻ ነፃነቷን በአደባባይ የምታወጅበት ቀን ለማብሰር ሃያ አራት ሰዓት በክንደ ነበልባሎች የአሳምነው ልጅ አውደ ውጊያዎች እያደርግን እንገኛለን።
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
አዲስ ቅዳም‼️
ጠላት ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧልል‼️
እረመጧ የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ፲/አ ኤፍሬም ብርጌድ ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ በመግባት ጠላትን ቁም ስቅሉን ስታበላዉ አርፍዳለች።
ጠላት በከተማዋ መዉጫ እና መግቢያ ጨምሮ ምድሯ ላይ ሁሉ የቆፈረዉን የቁም ምሽግ በመተማመን ከአለዉ አራዊት ዉስጥ ግማሹን ከፍሎ ኬላ ዘርግቶ ለመዝረፍ ወደ አሽዋ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን በእረመጦቹ የ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ትንፋሾች ሎሊስታ ላይ ተይዞ በመቀጥቀጡ አንድ ጓዱን ገብሮ የዝርፊያ እቅዱን ሳያሳካ ወደ አድጓሚ ተራራ እንዲፈረጥጥ ተደርጓል ።
በተመሳሳይ ዘራፊ ጓዱን ለመጠበቅ ከተማዋን በቁም ምሽግ ቁፋሮ የገበጣ ሜዳ ያስመሰላት የብልፅግና እንጉዳይ ጦር የእረመጦችን ወደ አዲስ ቅዳም ከተማ መንቀሳቀስ ገና እንደሰማ ጥቅምት 6ን እያስታወሰ የመሪዎቹን "ቁም¡" የሚል ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተዉ ለጊዜዉ ነፍሱን ወደሚያተርፍባት አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።
አዲስ ትዉልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ!!!
ጥቅምት 26/2018 ዓ/ም
ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
