fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 379
مشترکین
-924 ساعت
+2477 روز
+1 42930 روز
آرشیو پست ها
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር! ሻለቃ መሪው በፋኖዎች በቁጥጥር ስር ዋለ! ህዳር 05/2018ዓ.ም በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ
+2
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር! ሻለቃ መሪው በፋኖዎች በቁጥጥር ስር ዋለ!         ህዳር 05/2018ዓ.ም በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር ተከዜ ክፍለ ጦር መረጃን በማነፍነፍ የ61ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሻለቃ ምክትል መሪ የሆነው መቶ አለቃ በእውቀቱ ምስጋናው ከድልብ ወደ ግዳን ወረዳ ሙጃ ማርያም ከተማ በሚወስደው መንገድ ዴንሳ ከተማ ላይ በተከዜ ክፍለ ጦር ፋኖዎች ህዳር 04/2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል። ይህ ግለሰብ ላስታ ወረዳ ኩልመስክ ከተማ ላይ ከዚህ በፊት ስምንት ንፁሃንን የረሸነና ያስረሸነ፣የብዙ ወጣቶችን አካል ያጎደለ፣የአባውራ ሴቶችን የደፈረ፣ህዝባዊ መድረክ ላይ በይፋ ኩልመስክ ከተማን ጥቁር አለብሳታለሁ እያለ ማህበረሰቡ ላይ ግልፅ የስነ ልቦና ጫና ያደርስ የነበረ፣ከነጋዴው ብሎም ከማህበረሰቡ ሙስና የሚቀበልና የግል ጥቅሙን የሚያግበሰብስና ፍፁም ስነ ምግባር የጎደለው ጥቁር አማራ ነበር። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለጦር  ቃል አቀባይ ፋኖ ኢንጅነር አማረ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ      ህዳር 05/ 2018 ዓ.ም

የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አላማው አድርጎ የገባው የኦሮማው ጨፍጫፊ ስርአት ሙህራንና የተማረውን አካል ታርጌት አድርጎ መግደል ስራው ሁኗል፡፡ አማራ እንዳይማር፡የተማርው እንዲባርረና እንዲገደል፡ተቆርቋ
የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አላማው አድርጎ የገባው የኦሮማው ጨፍጫፊ ስርአት  ሙህራንና የተማረውን አካል ታርጌት አድርጎ መግደል ስራው  ሁኗል፡፡ አማራ እንዳይማር፡የተማርው እንዲባርረና እንዲገደል፡ተቆርቋሪ እንዳይኖርውና ወደ ድንጋይ ዘመን እንዲለወጥ ሆን ተብሎ እየተሰራ ነው፡፡ ይህን ዶክተር ሌሊት ከቋሪት ገበዘማሪያም ወደገጠር  ወይበይኝ በሌሊት ወጥተው ከቤቱ አውጥተው እረሽነውታል፡፡ምንም ምክንያት የላቸውም፡፡አማራ ነው ፣ፋኖን ሊያክም ይችላል በሚል ነው፡፡

አስቸኳይ የድሮን አሰሳ መረጃ፦ 👉በመላው ቴዎድሮስ ዕዝዝ በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ የድሮን ኀሠሣ መኖሩ ይታወቃል። አሁን ከቀኑ 6:15 ሰዓት ላይ መሸንቲና አካባቢው፣ ሙገር፣ ብራቃት፣ ቆጋ አ
አስቸኳይ የድሮን አሰሳ መረጃ፦ 👉በመላው ቴዎድሮስ ዕዝዝ በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ የድሮን ኀሠሣ መኖሩ ይታወቃል። አሁን ከቀኑ 6:15 ሰዓት ላይ መሸንቲና አካባቢው፣ ሙገር፣ ብራቃት፣ ቆጋ አሙሲት፣ ገርጨጭ፣ ሳንጊ፣ አፈሳ እና ፋግታ ለኮማ አካባቢዎች የድሮን ቅኝት መኖሩን የአሻራ ምንጮች ገልፀዋል። ስለሆነም አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን።

የግብርና እና የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ጋር ውይይትተካሄደ ። ህዳር 04/2018 ዓ.ም ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64 ክ/ጦር የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር አመራሮች በእነማይ ወረዳ
+5
የግብርና እና የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ጋር ውይይትተካሄደ ። ህዳር 04/2018 ዓ.ም ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64 ክ/ጦር የእነማይ ወረዳ ጊዜያዊ መንግስት አስተዳደር አመራሮች በእነማይ ወረዳ ከሚገኙ የግብርና እና የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ጋር ጥልቅ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ መድረኩ የተገኙት ባለሙያዎች የአገዛዙ ኃይል እኛን በሐሰት ትርክት ከፋኖ ሀይሎች ጋር ለመነጠል እያካሄደ ያለው ተግባር ተገቢ አለመሆኑን በማንሳት አገዛዙ በግብረና እና ጤና ባለሙያዎች ላይ እያካሄደ ያለው ተግባር ትክክል እንዳልሆነ በውይይት መድርኩ የተገኙት ባለሙያዎች ተናግረዋል። ህዝባችንም ሆነ የትኛውም አካል ከዚህ በሗላ የግብርና እና የእንስሳት ባለሙያ ከየትኛውም ፖለቲካ ገለልተኛ መሆናቸውን በማንሳት እኛ ሞያተኞች እንደማንኛውም አካል በፈለግነው ቦታ ተንቀሳቅን በሙያችን ህዝባችን ማገልገል አለብን በማለት በግልፅ ተናግረዋል። ከዚህ በሆላ የትኛውም ባለሙያ በሐሰት ትርክት ከፋኖ ሀይሎች ጋር በማገናኘት ከህዝባችን ጋር ተቀራርበን እንዳንሰራ የሚያደረግበት ምክንያት አይኖርም በማለት ህዝባችንን እንደበፊቱ በሙያቸው እንደሚያገለግሉ በውይይት መድረኩ ተናግረዋል። መድርኩን የመሩት በየተዋርድ ያሉ የኮር፣ የክፍለ ጦር እና የወረዳ ጊ/መንግስት በጥምረት ሲሆን የአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአማራ ህዝብ ላይ አገዛዙ እየፈፀመው ያለውን ግፍ እና በደል በተመለከተ ትምህርት ግልፅ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!      ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት    ህዳር 05/2018ዓ.ም

🔶 ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አርሴማ ላይ በጠላት ኃይል ላይ ጥቃት ፈጸመ።         በትላንትናው እለት ህዳር 4/2018 ዓ.ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ፭ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ቃኘው ብርጌድ ፤ ታድሎ ብርሃን ክ/ጦር ጅብ አስራ ማርያም ብርጌድ እና ጥቁር አንበሳ ክ/ጦር ቃኘው ሻለቃ በመቀናጀት ምንዝሮ ልዩ ስሙ አርሴማ ከተባለው ቦታ ላይ በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ላይ ጥቃት አድርሰዋል።       በጥቃቱ ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው ሰራዊቱ ቁስለኛውንና አስከሬኑን በመተው ወደ ጠዳ ከተማ ፈርጥጦ ገብቷል።   በዚህም የተነሳ ቁስለኛውንና አስከሬኑን ለማንሳት ተጨማሪ የጠላት ኃይል ከጠዳ ከተማ ተነስቶ ውጊያው ከተካሄደበት ቦታ በመድረስ በወገን ሃይል ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ተኩስ የከፈተ ሲሆን ነበልባሎቹ ፋኖዎች የለመደውን የሽንፈት ካባ አከናንበውታል።       በውጊያው ከተገኙ ድሎች መካከል                **  06 የሞተ                 ** 08 ክፋኛ የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል።   ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን። አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ   ህዳር 05/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ ጦር ጅጋ ሻለቃ በቀን 04/03/2018ዓ/ም በእለተ ሀሙስ ከገነት አቦ እና ከቋሪት የመጣዉን ጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ ወንበር አስ
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ ጦር  ጅጋ ሻለቃ በቀን 04/03/2018ዓ/ም በእለተ ሀሙስ   ከገነት አቦ እና ከቋሪት የመጣዉን ጡት ቆራጩ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ  ወራሪ ሀይልን የጅጋ ሻለቃ በወሰደችዉ እርምጃ በ 3 አቅጣጫ የበታተኑት ሲሆን በዚህም ዉሎ 17 የስርዓቱ ወንበር አስጠበቂ እስከወዲያኛዉ ሲሸኝ 11 ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ማድረስ ተችሏል:: የፋኖወችን ምት መቋቋም ያቃተዉ ወራሪዉ ሀይል 1 ንፁሀን ሲመታ ከፋኖተ ሰላም ብረት ለበስ (ፒቲር) የጦር ተሽከርካሪ ይዞ መጦ በከበባ ሲወቃ የዋለዉን የአብይ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ከመደምሰስ አድኖታል ፡፡ አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ  ተስፋ!!!! እስከ ምፅዓት አማራ !!! © ፍስሀ መኮነን

በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ደንቡን ቀበሌ  ንፁሀን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ ። አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር  አካል በሆነው ዘመነ ሻለቃ በሚያስተዳድረው  ደንቡን ቀጠና አሸባሪው ከሌሊቱ 9:00 እንቅስቃሴ ያደረገ ቢሆንም ሁሌም የዘመነን ሻለቃ ልጆችን ክንድ መቋቋም ያቃተው አረመኒያዊ ፋሽስቱ እና ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ሰራዊት ንፁሀንን በአደባባይ ረሸነ፡፡ ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ሰራዊት የመጣበት አላማ ሳይሳካለት ሲቀር ምንም አይነት ከትግሉ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ግለሰቦች እና የትምህርት ቤት ጠበቂን ጨምሮ በመረሸን  አረመኒያዊ ተግባባሩን ፈፅሟል፡፡ ይህን አረመኔያዊ ፋሽስቱ ስርዓት  አማራን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት  እየሰራ መሆኑን በማወቅ  አማራ የሆነ ሁሉ በየትኛውም መንገድ ሕዝባችንን ለማዳን  በሚችለው  ሁሉ ሊታገል  ይገባል፡፡

የአሳምነው ክፍለጦር እና የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ድል አስመዘገቡ:: የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር እና የምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር አ
የአሳምነው ክፍለጦር እና የዞብል አምባ ክፍለጦር አሃዶች በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ድል አስመዘገቡ:: የምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር እና የምስራቅ አማራ ኮር 2 ዞብል አምባ ክፍለጦር አሃዶች ዛሬ ህዳር 4/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ ወሳኝ ወታደራዊ ቦታ የሆነችውን በቅሎ ማነቂያ ለማጥቃትና ለመቆጣጠር የመጣን ጠላት ሙትና ቁስለኛ አድርገው ወደመጣበት ወልድያ ዙሪያ መልሰውታል:: በተጋድሎው የአሳምነው ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ እና ዞብል አምባ ክፍለጦር 7ኛ ሻለቃ በጥምረት የመጣውን ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ አድርሰው ወደመጣበት በመመለስ ቁልፍ ወታደራዊ ይዞታቸው የሆነችውን በቅሎ ማነቂያ አስከብረዋል:: የፋሽስቱ ብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እንደተለመደው የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ መድፍ በማስወንጨፍና ድብደባ በመፈፀም ንፁሃን ላይ ጉዳት ከማድረስ ባሻገር ቤትና ንብረት እንዲሁም እንስሳቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ በቀል ሲበቀል ውሏል:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ!

አስቸኳይ ማሳሰቢያ፦ 👉በመላው ቴዎድሮስ ዕዝዝ በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ሁሉ የድሮን ኀሠሣ መኖሩ ይታወቃል። 👉1.)ድሮን ከጣለች በኋላ ወዲያው አደጋው ወደ ተከሠተበት ቦታ ብዙ ሁኖ ርቀትን ሳይጠብቁ መሄድ  ለተጨማሪ ጥቃት ያጋልጣል 👉2.)የተከሠተ አደጋ ወይም የቆሰለ ሰው ካለ በትቂት ሰዎች የማግለል ሥራ መሠራት አለበት። 👉3.)ድሮኗ አንድ ጊዜ ጥላ በሁለተኛው ወዲያው ተመልሳ ስለምትጥል የትኛውንም ለጥቃት አጋላጭ መንገድ አለመጠቀም ጥሩ ነው። 👉4.)ችግሩ ወደ ተከሠተበት ቦታ ሲሄድ ብልጭታ የሚያጋልጡ ዕቃዎችን አኑሮ መሄድ። 👉5.) የተጎዳ ሰው ካለ በፍጥነት አንሥቶ መውጣት ያስፈልጋል።

🚨የአባይ ሻለቃ አመራሮች እና አባሎች ውይይት አካሂደዋል... (ሕዳር 4/2018 ዓ.ም) (አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር የአባይ ሻለቃ ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን
+1
🚨የአባይ ሻለቃ አመራሮች እና አባሎች ውይይት አካሂደዋል... (ሕዳር 4/2018 ዓ.ም) (አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር የአባይ ሻለቃ ውስጣዊ እና ውጫዊ ችግሮችን ለመፍታት ከሻለቃ አመራር እስከ ጋንታ መሪ በመሆን አባላቱን በመሰብሰብ ሰፋ ያለ አጀንዳቸውን ከፍተው ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም የስነልቦና ግባታዎችን፣ የአሰራር ግምገማዎችን እና ለትግሉ አራማጅ ሀሳቦችን በውይይቱ አጀንዳ ቀርጸው፣ ሻለቃዋን የተሻለ ቁመና ለማስያዝ ግምቢ ሀሳቦችን የሻለቃ አመራሩ ለአባላቱ አስገንዝበዋል። የአባይ ሻለቃ አባላትም የተነሱ ሀሳቦችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ ተያያዥ ሃሳቦችን ጠቅሰው የውስጥ እና የውጭ ችግሮችን ፈትተው ለግዳጅ ዝግጁነታቸው ገልጸዋል። የሻለቃዋ አመራሮችም ከአባላቱ የተነሱ አንኳር አንኳር ሀሳቦችን ምላሽ ሰጥተው፣ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ስብሰባውን ቋጭተዋል። 🚨ዘገባውን ያደረስኋችሁ ፋኖ ጋዜጠኛ አይቸው ጌታሰው ነኝ።

👉ከላይ እስከታች፣ከልሂቅ እስከ ደቂቅ፣ከማኅበር እስከ መዋቅር፣ከግል እስከ ማኅበር፣ 👉ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ከሰሜን እስከ ደቡብ፦ ያሉ አንድነታችን በመከፋፈል አንቀው የያዙን የቤታችን ጥቅል ደዌያት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦ 👉ዘረኝነት፦በሰፈር፣በመንደር፣መቧደን። 👉መለያየት፦የቤተ ክርስቲያንን አንዲትነት፣ሐዋርያዊትነ፣ኲላዊትነት፣ቅድስትነት መዘንጋት። 👉አስመሳይነት፦እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ከማለት ይለቅ በማስመሰል በለበጣ መኖር፣ከእውነት በስተጀርባ መሆን። 👉ስግብግብነት፦በቃኝ አለማለት፣ልክ መጠን የለሽነት ለልላው ገድ የለሽ መሆን። 👉ቅናት፦በሙያ፣በዕውቀት መቅኔት፣በሁሉም አይነት ሥጋዊ መቅናት መብሰልሰል። 👉ክህደት፦አምናለሁ እያሉ እንደ ኢአማኒ መኖር።ሀልወተ እግዚአብሔርን፣ምረረ ገሀነመ እሳትን ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መርሳት። 👉ፌዝ/አሉቧልታ፦በወንጌል ማፌዝ፣በመቅደሱ ማፌዝ፣በምእመናን ስቃይ ማፌዝ፣በሁሉም ማፌዝ። 👉ሌሎችን መናቅ፦ከአፍንጫ ባልዘለለ መረዳት ንፍት ማለት። 👉ዘመናዊ ፊት ኋላቀር ልብ መሆን፦በጣም የገባው ለመምሰል መሞከር ግን ፊትን፣ልብስን፣ምላስን ብቻ ማዘመን። 👉ዓላማ የለሽነት፦እንደ ቡሆ ዕቃ ወደ አጎረሱት ማሰብ እንጂ የሚኖርለት የሚሞትለት ኦርቶዶክሳዊ ዓለማ የሌለው መሆን። 👉አቋም የለሽነት፦ሁሉ እንደ ውኀ ስፍር የሚገለብጠው ወለሌ መሆን። 👉ንፍገት፦እኔ ብቻ ማለት ሌላውን መግፋት አቅምም አቋምም ያለውን መጥላት። 👉ካድሬነት፦ዘመን የወለደውን ንጉሥ የወደደውን ተቀበል እያሉ ለሥጋዊ ጥቅም መኖር። 👉ባንዳነት፦ሃይማኖት፣እውነት፣ፍትህ፣ዕሴት፣ታሪክ፣..ሲጠፋ ዝም ማለት። 👉እግዚአብሔርን መድፈር፦እግዚአብሔርን እንደ አጎቱ ማየት፣ቤተ መቅደሱንም እንደ አጎቱ ቤት መመልከት።ቅድስና አልባ መሆን። 👉ልማዳዊ አገልጋይነት፦በእምነት፣በዕውቀት፣በመረዳት ያልተመሠረተ የልማድ አገልግሎትን ማሳለጥ፣የልማድ ማኅሌታይ፣የልማድ ሰባኪ፣የልማድ ቅዳሲ፣የልማድ፣ባራኪ..ብቻ መሆን። 👉ጣዖታዊነት፦ግለ ሰቦችን ከእግዚአብሔርና ከእውነት በላይ ማከባበር።ፊቱ ለወዛ ሀብቱ ለበዛ ማድላት። 👉ግላዊነት፦ኅብረተ ቤተ ክርስቲያንን መርሳት፣እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል በሚል አህያዊ ብሂል መኖር። 👉ጥቅመኝነት፦ሁሉንም ከጉርሻ አንጻር መለካት፣ወንጌሉንም፣መስቀሉንም..ገበያ ማድረግ። 👉ውሸታም/ሐሰተኝነት፦እውነቱን በውሸት ለውጦ መኖሩ፣እያወቁ አለመናገር፣አስመስሎ ማለፍ። 👉አድሎአዊነት፦ለሰፈሬ ለመንደሬ ማለት፣ቤተ ክሮስቲያንን በእኩል ሚዛን አለማየት፣ድሀን መጥላት፣ወንጌልን መግፋት። 👉ፈሪሳዊነት፦ጻድቅ ለመምሰል መሞከር፣ውስጠ ተኩላ ሁኖ እያለ የእግዚአብሔር ሰው፣መናኝ አገልጋይ ለመምሰል መሥራት። 👉ዘራፊነት፦መማለጃ፣እጅ መንሻ መቀበል፣ንስሓን በግላዊ ንዋይ መቀየር፣ንዋየ እግዚአብሔርን መዝረፍ። 👉ሴረኝነት፦ቂመኛ፣ነገረ ሠሪ ሴረኛ መሆን፣እውነቱን ለማድበስበስ ነገር መፍተል። 👉ሰዱቃዊነት፦በምድር ሰውን በሰማይ እግዚአብሔርን መርሳት፣ትንሣኤ ሙታን እንደሌለ አድርጎ መኖር፣ሥጋዊነትን ምድራዊነት አይለፋችሁ ማለት። 👉አድመኝነት፦እውነትን ለማማሰን በቡድን ማወክ። 👉ሽንገላ፦በቃላት እየተካካቡ መኖር፣ብፁዕ ብፁዕ ክቡር ክቡር እየተባባሉ እየተወዳደሱ እየተቦዳደሱ መኖር። 👉ድንቁርና፦ለዕውቀት ፊትን ማዞር፣በባዶው መነፋፋት፣ 👉ሁሉን አውቃለሁ ባይነት፦ሳያውቁ እንደ ረቂቅ ሰው ለመቆጠር መንቆለጳጰስ። 👉ትወዝፍት፦ምንዝር ጌጥን ማብዛት፣መነሳንሱን፣አሸንክታቡን፣ማሰፋፋት። 👉አድርባይነት፦ባለ ጊዜን ለማስደሰት ጅራት እየቆሉ መኖር፣ቄስ ሞገሴነት። 👉ሲሞናዊነት፦መንፈሳዊ ሹመትን፣ክህነትን፣ሙያን በጉቦ መሸጥና መግዛት፣ 👉ሆዳምነት፦ሆድ ከሞላ ለምእመኑ ለወገኑ አለማሰብ። 👉ነውር አክባሪነት፦ነውርን መለማመድ እና እንደ ጸጋ እንደ ክብር ማየት፣ግድ የለሽ መደዴ መሆን። 👉ደላላነት፦አቃጣሪ ቀባጣሪ መሆን፣ሰውን ሳይቀር መሸጥ፣ክህነትን፣መሸጥ፣በወንጌል መሸቀጥ። 👉ፍቅረ ሲመት፦ለሹመት መንገብገብ፣ተሹሞ አለመሥራት።የተሻለ አሳቢዎችን  መግፋት። 👉ሕያው ምውት፦በሕይወት ያሉ ግን ለሞተና ለሚሞት ጉዳይ የሚጨነቁ ልቅ ዝርግ ሥጋውያን ብቻ መሆን። 👉ዓለማዊነት፦በዓለም ላይ ያለው ሁሉ አይለፈኝ ማለት፣ከመቅደሱ ሕይወት ይልቅ ምዕራቡን እና አውሮፓውን መናፈቅ። 👉ተሳላቂነት፦ዐይኑ በፈረጠ እጅ እግሩ በተቆረጠ መዘበት፣ቧልተኛ ቀልደኛ ብቻ መሆን። 👉ተላላኪነት፦እዚያም እዚያም መልከፍከፍ፣ነገር መጫን፣ጉዳይ ማስፈጸሚያ ብቻ መሆን። 👉ዝንጉነት፦የተሾሙበትን፣ያመኑበትን፣የቆሙበትን፣የተወከሉበትን ዓላማ መርሳት። 👉ትዕቢት፦ሁሉን መናቅ ከእኔ በላይ ላሳር ማለት፣መታጀር፣መጀነን፣የተዘጋ የተመረጋ መሆን። 👉የመሳሰሉት ደዌያት ናቸው አንቀው ይዘዉ አላንቀሳቅሰን ያሉን። 👉ማሳሰቢያ እነዚህ ደዌያት እኔን የመሰሉትን ነው እንጂ ደኅነኞቹን አይመለከቱም። “ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም  ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡”፪.ጢሞ.፬፥፲ 👉ከምእመናን ይልቅ ዓለምን የሚወዱ መምህራን ካህናት ጳጳሳት ምእመናንን ከዓለም ለይተው ለመንግሥተ ሰማይ ማብቃት አይቻላቸውም። 👉መንኖ ጥሪትን፣ኀዲገ ዓለምን፣ሞትን፣ትንሣኤ ሙታንን መለማመድና ራስን መቆጣጠር አስፋላጊ ነው 👉ከዓለም አይደላችሁም ያለን የክርስቶስ ቃል ዓለም የእኛ መስላን እንዳንሸወድና ጥላን በመከተል የሕይወት ጊዜያችንን በሞት እንዳንጨርስ ነው፡፡ 👉በዚህ ትብትብ ደዌ የተያዝን ሁላችንም  ከደዌያችን እንላቀቅና ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና አንድ ሁነን እንናገር። © የኔታ ገብረመድኅን እንዬው

ቢዛሞ (ወለጋ)‼️ በኔትወርክ ምክንያት ዘግይቶ የደረሰን ምስል። መስከረም 6/2018 ዓ/ም የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊት በምስራቅ ቢዛሞ (ወለጋ)  ኪራሙ ወረዳ አማራ ወደ ሚኖሩበት ቀበሌዎች በከባባድ መሳሪያ ታጅቦ ቢገባም  የበረሀ ቋያወቹ የአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ በሻለቃ ሀብታም ጥላሁን የምትመራዉ ይበልጣል መኮነን አዲስ አለም ክ/ጦር  ጡት ቆራጩን ሰራዊት አይገጡ ቅጣት ቀጥታ ሬሳዉን እንኳን ሳያነሳ ወደ ኪራሙ ከተማ እንዲፈረጥጠ አድርገዉታል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሀይል (አፋብኃ) ቢዛሞ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ህዳር 4/2018 ዓ/ም

ዐማሓራ ለቁጥር የሚያዳግት ማርኮ ታጣቂ አዲስ ትውልድ ገንብቷል። የሚቀረው የሚቀርውን የቤት ስራ ሰርቶ በፍጥነት ማጠናቀቅ ብቻ ነው!!

የጥንቃቄ መረጃ‼ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በዛሬው ዕለት ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ አባይ ምንጭ ትምህርት ቤት የየክፍሉን ስም ጠሪ መምህራን  በመሰብሰብ በዬ ክፍላቸው እዬዞሩ ምንነቱ የማይታወቅ መዳኒት የደም ማነስ መዳኒት እያላቹህ ለተማሪውች አከፋፍሉና ይዋጡት መባላቸውንና መምህራኑ ምንነቱ ያልታወቀ መዳኒት ለተማሪዎች አናከፋፍልም ማለታቸውን ተከትሎ መምህራኑ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራርያ ያስተናገዱ ሲሆን በመጨረሻም የጤና ባለሟያዎች መተው ለተማሪዎች ማከፋፈላቸውና ብዙ ተማሪዎች ምንነቱ ያልታወቀ መዳኒት አንወስድም ብለው ከትምህርት ለቀው መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ይህ መዳኒት ሰከላ ወረዳ ላይ ተሞክሮ የታሰበውን ግብ ከመታ ወደ ሌሎች ወረዳዎች እንደሚሰራጭ የደረሰን መረጃ ያመላክታልና ይህንን ምንነቱ ያልታወቀ መዳኒት ሁሉም ማህበረሰባችን ባለመውሰዱ ጤናቹህን እንድትጠብቁ እናሳስባለን። ህዳር 04/2018ዓ.ም     ቢዛሞ ሚዲያ

አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በልጁ "አርበኛ ጌትነት መሳፍንት" መስዋዕትነት አስመልክቶ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!
+2
አርበኛ መሳፍንት ተስፉ በልጁ "አርበኛ ጌትነት መሳፍንት" መስዋዕትነት አስመልክቶ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ!

ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራሳቸውን ነፃ አውጥተው ፋኖን የሚቀላቀሉ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ ነው። ከፋሽስቱ ሰራዊት እየፈረሱ ፋኖን የሚቀላቀሉ ሰራዊቶች የ12ኛ እና የ93ኛ ክፍለ
+1
ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራሳቸውን ነፃ አውጥተው ፋኖን የሚቀላቀሉ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ ነው። ከፋሽስቱ ሰራዊት እየፈረሱ ፋኖን የሚቀላቀሉ ሰራዊቶች የ12ኛ እና የ93ኛ ክፍለ ጦር የሆኑት ሰራዊቶች የብልፅግናን ጭቆና ከትከሻቸው ላይ አራግፈው በመጣል ወደ አማራ ፋኖ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮርን የሚቀላቀሉ የፋሽስቱ ሰራዊቶች ከቀን ቀን ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል። በጥቅምት ወራት የመባቻ ማግስት እስከ ህዳር አራት የፋሽስቱን ስርዓት እየከዱ የደጀን ክፍለጦርን የተቀላቀሉ ሀይሎች ስድስት ደርሰዋል። ራሳቸውን ከሞትና ከጥፋት በመታደግ የፋሽስቱን ስርዓት አገልጋይነትን በመጠየፍ የብልፅግናን ቤት ንቀው ወደ ህዝብ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። የስርዓቱን አስከፊነትና ጨፍጫፊነት የመሰከሩ ሲሆን" ከአሁን በኋላ የፋሽስቱን ወበር ለማስጠበቅ የሜንገብረው የህይዎት ዋጋ የለም።" ሲሉ ገልፀዋል።  አስቀጥለውም በፋሽስቱ ስርዓት ውስጥ ተጨቁነውና ተደፍጥጠው ያሉ ወታደሮች ባገኙት አጋጣሚ ፋኖን ይቀላቀሉ እራሳቸውን ነፃ ያውጡ" ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 4/2018 ዓ.ም

ህፃን እዮብ ነፍስህ በአፀደ ገነት ትረፍ! በቀን 26/02/2018 ዓ ም ከ109ኛኮር 99 ክፍለጦር ጋር ማቻከል ወረዳ ላይ ግራ ቅዳምን ከምትባል ቀበሌ ከተማ ላይ ከአብይ አራዊት ሰራዊትጋ በተደረገዉ
ህፃን እዮብ ነፍስህ በአፀደ ገነት ትረፍ! በቀን 26/02/2018 ዓ ም ከ109ኛኮር 99 ክፍለጦር ጋር ማቻከል ወረዳ ላይ ግራ ቅዳምን ከምትባል ቀበሌ ከተማ ላይ ከአብይ አራዊት ሰራዊትጋ በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ዉጊያ ላይ የፋኖን በትር መቋቋም ያቃተዉ ጡት ቆራጩ ሀይል ሞርተር በማስወንጨፋ የ5 ዓመት ህፃን እዮብ ዋጋን ሂዎት ቀጥፏል! እዮባ ነፍስህ በአፀደ ገነት ትረፍ😭

ህዳር 04/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት በንፁሀን በማህበረሰቡ ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ በመረዳት የአገዛዙን ሀይል በመክዳት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64
+2
ህዳር 04/2018 ዓ.ም በሸበል በረንታ ወረዳ የሚገኘው የአገዛዙ ሰራዊት በንፁሀን በማህበረሰቡ ላይ እየፈፀመ ያለውን ግፍ በመረዳት የአገዛዙን ሀይል በመክዳት አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በዛሬው እለት ፋኖን መቀላቀል ችለዋል ። 1ኛ.እንደሽው ሙሉቀን ሸበል በረንታ ጎይ ቀበሌ 2ኛ.ሀይማኖት አባይ ሸበል በረንታ አባራ ቀበሌ 3ኛ.አየነው አለሙ ዳግላ አጋጋ ቀበሌ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ እያየን መቆየት አልቻልንም ከወገኖቻችን ጋር  መሰለፍ አለብን ቀሪ ጊዜያችንን ደግሞ ለአማራ ህዝብ መስዋት መክፈል አለብን በማለት ወደ ወገናቸው ተቀላቅለዋል። ሐብታሙ የሱፍ የቴድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 04/2018 ዓ.ም