ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 393
مشترکین
+724 ساعت
+2667 روز
+1 44330 روز
آرشیو پست ها
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለ ጦር
በጀነራል ተፈራ ማሞ የተሰየመችው ብርጌድ ሻለቃ አንድን (መብረቁ እየተባለች የምትጠራውን እንደስሟ መብረቅ የሆነችውን ሻለቃ ) ለከተማ ኦፕሪሽን ሸማቂዎቹን በመላክ አስገራሚ ጀብድ ፈፀመች።
ቀን 22/03/2018 ዓ ም የብልፅግና የዕድሜ ማራዘሚያ እየተባሉ በህዝባቸው ላይ የመከራ ቀንበር እንዲሸከም የሚያረጉ ዙፋን ጠባቂ ሚሊሻዎች ውስጥ አምስቱ (5) የሚሆኑት በመብረቁ ሻለቃ ሸማቂዎች ወደ ፈጣሪያቸው የተሸኙ ሲሆን ሶስት የሚሆኑት ደሞ በህክምና ላይ ነፍስ ውጭ ነፍስ ጊቢ ላይ እንደሚገኙ በውስጥ መረጃችን ማረጋገጥ ችለናል።
ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ኦፕሪሽን የተደረገው በአረርቲ ከተማ በቀን 19/03/2018 ዓ ም ከምሽቱ 1:45 አካባቢ ላይ መጠጥ ቤቶችን ለማዘጋት ሲንቀሳቀሱ እንደሆነ ሸማቂዎቹ ለሚዲያችን አስታውቀዋል።
ድል ለአፋብኃ
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት
ለበልባል ክፍለ ጦር ሚዲያ ክፍል
ህዳር 20/03/2018
+1
እነዚህ ሁለቱ እጅ የሰጡት ገብርሸትና ስዩም ይዘንጋው ሰሞኑን በአገዛዙ ግዴታ እንደተጣለባቸው ነው የሰማሁት 😆
ግዴታቸውም እንደነ ፀዳሉና ቆራጡ ወጣችሁ ከሚኒሻ ጋር ሆናችሁ ፅንፈኛውን ባትታገሉ እንኳ ከዚሁ ቁጭ ብላችሁ ታጋዩን በመሳደብ በማንቋሸሽ የፋኖ መሪዎችን በማጣጣል የበኩላችሁን ተወጡ ካለዚያ ጠብታ ሳንቲም አትሰጡም ተብለዋል ። እና እነዚህ ልጆች የፈለገውን ቢናገሩ ያው ተገደው ስለሆነ ምንም አይነት መልስም ሆነ ቦታ አትስጧቸው ። ስድብም ተፅፎ ነው የሚሰጣቸው ባለፈው ስዩምን ካያችሁት ተፅፎ የተሰጠውን ከስልኩ እያነበበ ሲሰድበን ነበር 🤩 አሁንም ከዛ የዘለለ አቅም የለም።
~> በነገራችን ላይ ሁለቱም ታጋይ/ተኳሽ አልነበሩም ባይሆን ገብርሸት ታጋዩን በማነቃቃት ረገድ የተሻለ ነበር ስዩም ግን በተቃራኒው የአገዛዙ ኦፒ በመሆን ወንድሞቻችን አስነጥቆናል እሱ እጅ በመስጠቱ አትርፈናል ።
ገብርሸት ምንም ውጊያ በሌለበት ካሜራ ማን ከኋላ እያስከተሉ ብሬንና ክላሽ የተኮሱ በሁለት አቅጣጫ " --ከተማ ተቆጣጠርናት የሚል ቪዲዮ ሰርተው በለቀቁበት ሰዐት በስህተት አንዲት ዶሮ አቁስሏል አሉኝ 😝 ከዛ ውጭ በየትኛውም ግንባር ተታኩሶ አያቅም!! እና እነዚህ ሰዎች እንኳን እጃቸውን ለምን እግራቸውን አይሰጡም just pass ,
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ የተላለፈ መልዕክት
ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም መካነሰላም ከተማ ውስጥ የአንድ ካህን ሚስትን ጨምሮ በድምሩ 3 እመጫት እናቶች ታፍነው ወደ ካምፕ ተወስደው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ገረድ በሆነው የፀጥታ ኃይል አባል ተደፍረው የግፍ ግፍ እንደተፈፀመባቸው በሰማሁ ጊዜ እጅጉን ማዘኔን እየገለፅኩ ህዝባችን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት እየፈፀሙ ታሪኩን እና ሀይማኖቱን እንዲሁም እሴቱን የሚሸረሽሩትን ለመታገል ጥርሱን ነክሶ ዳር እስከ ዳር ይነሳ ዘንድ ይህን የትግል ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ።
አማራ በእርስቱ፣ በሚስቱ እና በእምነቱ ማለትም በድኑ እና በማተቡ አይደራደርም። የተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊት ደግሞ በእርስት እና በማንነት ብቻ ሳይሆን በሚስት እና በሀይማኖት የመጣ ጠላት ስለመኖሩ አስረጅ ነው። የካህን (ቄስ) ሚስትን አስገድዶ የሚደፍር ኃይል በአማራ ምድር እንኳን 3 ዓመት 3 ቀን ውሎ ማደር አልነበረበትም። ይህን ያክል ጠላት በነፍሳችን ጭምር ሊጫወት የቻለው አንድ ሆነን ዳር እስከ ዳር ባለመነሳታችንና ጠላታችንን አምርረን ባለመጥላታችን ነው።
የሰሞኑ የግፍ ግፍ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ዓመታት ህዝባችን የተሸከመው የመከራ ቀንበርን ክብደት ሁላችንም የምናውቀው ነው።
ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመካነሰላም ከተማ ዙሪያ ገጠር ወረዳ መቅደላ ታዳጊ ከተማ አቅራቢያ ይሄው ኦሮሙማው ስርዓት ዘብ የሆነው ፀረ አማራ ቡድን 5 ንፁሓን ወጣቶችን መረሸኑም ይታወሳል። የልጆቻችንን የመከራ ድንኳን ሳይነቀል ድጋሜ ቀያችን ላይ የተፈፀመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፀረ አማራውን ቡድን አረመኔነት ገላጭ ነው።
ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም የተደፈሩት እናቶቻችን ለህፃናት ልጆቻቸው ፓምፕሌት እንድወስዱ በጤና ባለሙያዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ከገጠር ወደ መካነሰላም ከተማ የሄዱ መሆናቸው ታውቆ ከእንግዲህ መሰል ጥሪ ሲደረግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ለማሳሰብም እወዳለሁ። እመጫት እናቶችን እና የካህናት ሚስቶችን በመድፈር የአማራ ህዝብን ክብር እና ታሪክ ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳውን አረመኔ ቡድን ለማስወገድ የምናደርገውን የህልውና ትግል በመደገፍ ህዝባችን ለአይቀሬው ድል እንድዘጋጅ ከወዲሁ ለማሳሰብም እወዳለሁ።
የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ አብነው ታደሰ ምትኩ
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
ከህዳር ወር ጀምሮ ለመምህራን ደመወዝ እንደማይከፍል የአማራ ብልፅግና ገለፀ''።
የአማራ የህልውና ትግል ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በክልሉ ትምህርት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል። ይህን አስመልክቶም የተማሪ ወላጆች አቤቱታ በመበራከቱ እና የትውልዱ የእውቀት ድህነት አሳሳቢ በመሆኑ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ያለፉ ተሞክሮዎችን በማጥናት ከዚህ በፊት አለም ላይ የነበሩ የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴዎችን እና በወቅቱ ትምህርት ይሰጥበት የነበረውን ተሞክሮ በማየት የተሻለ በሚባል ደረጃ ውሳኔ አስቀምጦ ለአለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ሀገሪቷን አየመራሁ ነው ለሚለው አሸባሪ መንግስት አሳውቋል።
ለዚህ ጥሪ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጠውና የአማራን ሙሁራዊ ዘር ማጥፋት ፈፃሚው ብልፅግና ከአማራ ፋኖ ጋር ምንም አይነት መግባባት ላይ ሳይደርስ( ቅድመ ሁኔታዎችን ሳይቀበል ) የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ መምህራንን ፋኖ ባለበት ቀጠና ገብታችሁ ትምህርት የማትጀምሩ ከሆነ ከህዳር ወር ጀምሮ ደመወዛችሁ ይቆረጣል በማለት ለወረዳዎች ጽ/ቤትም ማስጠንቀቂያ አዘል ደብዳቤ ፅፏል።
አማራን በሰብዓዊ፣ ቁሳዊ(ኢኮኖሚያዊ)፣ ሞራላዊና ሙሁራዊ ኪሳራ ውስጥ ለማስገባት እየታተረ ያለው ብልፅግና በአማራ ፋኖ እየደረሰበት ያለውን ሽንፈት ሙሉ በሙሉ በመቀበል ከሸለቆ ውስጥ አይወጡም ወደ ተግባብታችሁ ስሩ መምጣቱን በዚህ የመምህራን ማስፈራሪያ ደብዳቤ አሳውቋል። ሽንፈቱንም አምኗል።
አማራ ያሸንፋል አሸንፏልም!!
የእ/ሳ/ም/ወ/ጊ/መንግስት ሚዲያና ኮምኒኬሽን ሀላፊ
ፋኖ ይበልጣል ጥሩነህ
+2
በሸበል በረንታ ወረዳ ከሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሂዶል።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር እና የሸበል በረንታ ጊ/መንግስት በሸበል በረንታ ወረዳ ገዳያሱ ቀበሌ ከሚገኙ ከሲቪል ሰርቫንት ሰራተኞች ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
''ምነው መጣን ብለው ቀሩሳ?'' ያልከው ሰውዬ - እስኪመጡልህ ድረስ ተከታዮቹን ጥያቄዎች እየመለስክ ጠብቃቸው!
✅ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ መሀል ሀገር ላይ ያውም 2 አመት ባልሞላ ጊዜ ራሱን አደራጅቶ ፣ አሰልጥኖና አስታጥቆ እንደአማፂ ቡድን ሳይሆን እንደመንግስት ግዙፍ የሆነ ሰራዊት የገነባ ከFaኖ ውጪ አንድ የትጥቅ ትግል ድርጅት ልትነግረኝ ትችላለህን?
✅ ባለፉት 50 አመታት ውስጥ እንኳ ከተነሱ የትጥቅ ትግል ድርጅቶች ውስጥ ኦነግ 40 አመት ኤርትራ ጫካ ለጫካ ሲሄድ ከኢትዮጵያ አንድ ወረዳ ተቆጣጥሮ ለወራት እንኳ የቆየበትን ዘመን ትነግረኛለህን?
✅ ግንቦት -7 ወይም አዴኃን አለያም ሌላ ድርጅቶች ተጨፍልቀው የFaኖን አንድ ክፍለ ጦር እንኳ ይሞሉ ይሆንን ? በአመታት የኤርትራ ቆይታቸው ማይካድራን ተሻግረው የመጡበትን ጊዜስ ልታስታውሰኝ ትችላለህን?
✅ ከዋና ከተማ ከ20-30 ኪ.ሜ ርቀት ተጠግቶ መዋጋት አይደለም ይቅርና የአንድ ቀበሌ ጎጥ ተቆጣጥሮ የምታስታውሰው ታጣቂ ሀይል ታስታውሳለህን ?
✅ አይደለም ለ3 አመታት ያለእረፍት መደበኛና የሽምቅ ውጊያ እያደረገ አቅሙንም በየእለቱ እያጎለበተ የተጓዘ ቀርቶ ለ3 ሰአት ከኢህአዴግ አገዛዝ ጋር ሲዋጋ የምታስታውሰው ኃይልስ ይኖር ይሆንን ?
✅ ህወሓትስ ከአመታት የትግል ሂደት በኃላ እግሩን ከትግራይ ክልል ያወጣው ኢህዴንና ኦህዴድ የሚባሉ ጫማዎችን ሰርቶ አይደለምን? እነዚህን መረማመጃ ጫማዎቹን ተጠቅሞ ወደ መሀል ሀገር እስከሚገባ 17 አመታት አልፈጀበትምን ?
#Faኖን የምንተቸው ትግሉ ፋታ የማይሰጥ ፣ አይን የማያስከድን ፣ በይደር የማይተው 'የህልውና ትግል' በመሆኑ ''ተቋም'' ሆኖ ፣ ከአውደ ውጊያ ይልቅ ስትራቴጂካዊ ድልን የሚቀዳጅበትን ትልቅ አቅም እንዲፈጥር ከመሻት እንጂ በአጭር ጊዜ የተጓዘው ርቀት ''ተአምር'' የሚባል መሆኑ ከማንም የተሰወረ ሆኖ አይደለም!
እናማ '' መጣን ብለው ቀሩ'' እያልክ ሙድ ለመያዝ ከመሞከርህ በፊት እጣገብህና መሀል ሀገር ያለ ሀይል መሆኑን ልታስታውስ ግድ ይልሀል። ከኤርትራ ተነስተው አይደለምና የሚመጡት!
በነገራችን ላይ ሁሉንም ነገር ትተነው 👉 For any unti-government rebel group 'existence' by itself a victory. ለአገዛዙ ደግሞ የታጣቂ ቡድኖች መኖራቸው ብቻ ከሽንፈት ይቆጠራል!
'' 10 ኃላቀር መሳሪያ የታጠቁ ጃውሳዎችን በ10 ቀን ቀበቶ እናስፈለን'' ተብሎ የተጀመረውን ጦርነት ዛሬ 3ተኛ አመቱ ላይ በተቃራኒው ሀይል በኩል የፈጠረውን ግዙፍ አቅምና ንቅናቄ መገንዘብ ካልቻልክ እውነትም ስቡ ደፍኖሀል ማለት ነው!
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ሂደቱ ላይ ምንም አይነት ችግር ቢኖርበትም እንኳ ፣ የተነሳበት ሀቀኛና የማይታበል ኮዝ ወደፊት እንጂ ወደኃላ የሚመልሰው አይሆንም!
✍ዘሪሁን ገሰሰ
በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ህዳር 13/2018ዓም በመተከል ዞን፣ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ከ50 በላይ የመተከል ተወላጅ ንጹሃን አማራዎችን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ሀይሎች(ኦነግ ሸኔ) ጨፍጭፏል።ከእነቤተሰቦቸቸው በእሳት አቃጥሏል😭
በመጀመሪያ target የተደረገው የአቶ አሞኜ ጀንበሬ ቤተሰብ ሲሆን አቶ አሞኜ ማለት ከወረዳ እስከ ፌዴራል መስሪያ ቤቶች ድረስ እየሄደ በመተከል ዞን ለሚኖሩ የአማራ ተወላጆች መብት እድሜ ልኩን ሲከራከር የኖረ ብርቱ ሰው ነበር። በበኩጂ ቀበሌ ደግሞ ዋና የሀገር ሽማግሌና አማራን ወክሎ የሚቆም ደፋር ሰው ነበር።"መተከልን እንወርሳለን"የሚሉት ኦነጎች"አባ አሞኜን ከገደልነው የመተከል አማራን ማጥፋት ቀላል ነው" በሚል ሂሳብ ለአማራ ብሔር መብት፣ህልውናና ጠበቃ የነበረውን አቶ አሞኜ ጀንበሬን በመጀመሪያ ቤቱን ከበባ በማድረግ ህዳር 13/2018 ከጥዋቱ 12:00 አካባቢ ቤቱን ዘርፈው እስከ ቤተሰቡ ጨፍጭፈዋቸዋል።ኦነጎች አባ አሞኜን ከገደሉ በኋላ"የአማራን ራስ መታነው"ብለው እየጨፈሩ ሌሎች አማራዎችንም መጨፍጨፉ ጀመሩ። ነገር ግን በበኩጂ ቀበሌ ያሉ አማራዎች ሙሉበሙሉ ተጨፍጭፈው ከማለቃቸው በፊት የአዲስ ዓለም፣የማጣ፣የሆራ፣የጭላንቆና የጉሽባጎ የአማራ፣የሽናሻና የጉምዝ ነዋሪዎች ደርሰው ከጥፋት አትርፈዋቸዋል።
በወቅቱ በአባ አሞኜ ቤት የነበሩና የተጨፈጨፉ አማራዎች
1.አቶ አሞኜ ጀንበሬ(አባት)
2.አካውንታንት ገበያው አሞኜ(ልጅ)
3.ወ/ሮ አበዜ የኔው(የአጎት ልጅ)
4.ወ/ሮ ሰፊ ወርቁ(የልጅ ሚስት) ናቸው።ለአማራ የከፈለውን መስዋዕትነት ብዙ ነው።በቡለን አማራ ከሞት የሚተርፈው፣ከእስር የሚፈታው በአባ አሞኜ ስም ነበርና።
ማስታወሻ:-የተጨፈጨፈው አማራ ቁጥር ከፍ ይበል እንጂ የሽናሻ ተወላጆችም አብረው በኦነግ ሸኔ ተጨፍጭፈዋል።
ፋኖ በጣናነሽ ጀልባ !
ትናት በ19 ከባህር ዳር ወደ ደልጊ በይፋ ለህዝበ
አገልግሎት ስራዋን የጀመረችው ጣናነሽ ፋኖ
በሚቆጣጠራቸው የጣና ሀይቅ ዳርቻወች ባረፈችበት
ወቅት የባህር ዳር ፋኖ የሆኑት ፋኖ አቤና ሳሚ የተነሱት
ፎቶ ሲሆን ፋኖ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ያከብራልም
ያስከብራልም።
ድል ለአማራ ፋኖ ✊
እሸት ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸዉን የፋኖ ሰራዊቶች በዛሬዉ ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር እሸት ክፍለ ጦር ለተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸዉን ፋኖወች በዛሬዉ ዕለት ማለትም ህዳር 20/2018 ዓ.ም አስመርቋል።
ተመራቂ ፋኖወችም ለወራቶች በአካል ብቃት፣ በተኩስ ፣ በሰልፍ እና ወታደራዊ ሳይንሱ የሚጠይቀውን እውቀት እና ጥበብ ቀስመዉ ተመርቀዋል።
በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይም የነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ አዛዥ ሻለቃ ደምሌ ጣፋጭ (ጥንቅሹ) ጨምሮ የላስታ አሳመነዉ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና የእሸት ክፍለ ጦር አመራሮች ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂዎቹ የፋኖ አባላቶችም እኛ የህልውና ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ብቻ ሳይሆን ስለ ነገይቱ ኢትዮጵያ አስበን ጭምር ነዉ የሰለጠነዉ ብለዋል።
ሰልጣኞቹ አክለዉም እኛ ሰልጥነን ለዚች እለት ስንበቃ እኔ ጎጃም፣ እኔ ጎንደሬ፣ እኔ ሸዋዬ፣ እኔ ወሎዬ እንድንል ሳይሆን አንድ ሁኑ የሚለውን የጄኔራል አሳመነው ፅጌ የኑዛዜ ቃል አክብረን በአማራነታችን ፀንተን እንቆማለን ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ተመራቂዎቹ የተሰጣቸዉን አደራ በአግባቡ እንደሚወጡ ቃለ መሃላ በመፈፀም ቃል ገብተዋል።
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ አሳመነዉ ኮር ሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ጋዜጠኛ ፋኖ ደረበ መኮንን!
"ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!"
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
በአራቱም ማዕዘን 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
የ74ክፍለጦር አመራሮች 3 ወረዳወችን ከጊዜያዊ መንግስት ጋር ውይይት ተካሄደ!
የአፋብሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ
201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የክ/ጦር አመራሩን በ3ቱ ወረዳዎች ማለትም እናርጅ እናውጋ ፣ጎንቻ ሲሶ እነሴና እና አነብሴ ሳርምድር ወረዳዎች ችግርፈች የሆነ ስምሪት በመውጣት ከሻለቃዎች እና የወረዳዎች ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ዘላቂ እና ችግር ፈች ድጋፎችን እያደረጉ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።
1. የአደረጃጀታዊ አወቃቀር ድጋፍና ግምገማ
2. የድጋፍ አሰባሰብ፤
3. የማህበረሰብ አስ/ር ስርዓት ማዘመን
4. የሰራዊት አያያዝና ክትትል በተመለከተ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።
አዲስ ተውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስተስፋ
የቴወድሮስ እዝ201ኛ ኮርህዝብ ግንኙነት
ህዳር20/2018 ዓ.ም
#ዛሬም_ከኋላ_ደጀኑ_ህዝባችን_ጋር_መክርናል!!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ቁጥቋጥ እና አካባቢው ቀበሌ ከኋላ ደጀኑ ህዝባችን ጋር እንዲሁም በእነማይ ወረዳ የረዝ፣ ሀገረ ህይወት ቀበሌ እና ደብረ ቅዱሳን ቀበሌዎች ላይ ህዳር 19/2018 ዓ.ም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በ201ኛ ኮር ስር የሚገኘው 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና ከሸበል በረንታ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች
ጋር በመሆን በሸበል በረንታ ቁጥቋጥና አካባቢው ማህበርሰብን ጋር በመገኘት ሰፋ ያለ ውይይት በማድርግ ትግሉ ያለበትን ወቅታዊ ቁመና በማስረዳት የኋላ ደጀኑ ህዝባችንን ሰንሰለቱን በጠበቀ አደረጃጀት ተዋቅሯል።
በመድርኩ የተገኙት የኋላ ደጀኑ ህዝባችን እንደተናገሩት በአገዛዙ የአብይ አህመድ አገዛዝ እንዲጠፋ የተፈረደበት የአማራ ህዝብ እራሱን አደራጅቶ ከክላሽ እንኮብ መሳሪያ ተነስቶ ዛሬ ላይ ከጠላት ያላነሰ የቡድን መሳሪያ ታጥቆ እዚህ ደርሶል። በመሆኑም እኛም ዛሬ እንደ ትላንቱ ከፋኖ አባላት ጋር በመሆን ድርጅቱ የሚሰጠንን የትኛውም አይነት ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት በእነማይ ወረዳ የረዝ፣ ሀገረ ህይወት ቀበሌ እና ደብረ ቅዱሳን ቀበሌዎች ላይ ህዝባዊ ውይይት በማድርግ የቀበሌ አመራሮችን አዋቅሯል።
➛የቀበሌ ሊቀመንበር
➛የቀበሌ ም/ሊቀመንበር
➛የቀበሌ ፀሀፊ
➛የቀበሌ ፍርድ ሸንጎ (3)
➛የቀበሌ ገቢና ሀብት አሰባሰብ
➛የቀበሌ ፀጥታና ምክትል
➛የቀበሌ የወጣት ጉዳይ
➛የቀበሌ የጎጥ ሽማግሌ (3)
➛የቀበሌ የሀገር ሽማግሌ በቀበሌ (7)
➛ህዝብ ያመነባቸው አስታራቂ የሀገር ሽማግሌዎችን አዋቅሯል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
የ206ኛ ኮር አደረጃጀት ዘርፍ መምሪያ የመልሶ ማደራጀት ተግባሩን በተቀላጠፈ ሁኔታ እየፈፀመ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ህዳር 20/2018 ዓ.ም
የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ መዋቅርን በማሻሻል ሰራዊቱን ለተሻለ ግዳጅ እያበቃ ሲሆን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ትኩረት ሰጦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን በማደራጀት ሰራዊቱን በጠንካራ ሻለቆች እያዋቀረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የህዝብ አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን አጠቃሎ በአዲስ የተደራጀው ጊዜያዊ መንግስት በኮሩ ቀጠናዎች ባሉ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ቢሮ በመክፈት አገልግሎት መጀመሩን ያረጋገጠው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ የተሰጠውን ድርጅታዊ ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ኮሩ የስራ ስምሪት ወስዶ ከተንቀሳቀሰ ጀምሮ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ያወሳው መምሪያው 24ኛ ክ/ጦርን በመልሶ ማደራጀት ተግባሩ ሙሉለሙሉ ያዋቀረ ሲሆን የክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስን ጨምሮ ቀጠናውን ሸፍነው የሚንቀሳቀሱ ጠንካራ ሻለቆችን በማደራጀት ክ/ጦሩ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃት ለመወጣት በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።
ከመልሶ ማደራጀት ትግበራው ጎን ለጎን ከአካባቢው ማህበረሰብ ፣ከሀገር ሽማግሌዎች፣ሴቶችና ነጋዴዎች እንዲሁም ከመላው ሰራዊቱ ጋር አስቀድሞ ውይይት ያደረገው 206ኛ ኮር ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የማህበረሰቡ ተሳትፎ አይነተኛ ሚና እንደነበረው የ206ኛ ኮር አደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፲አለቃ ደርሳችሁ አትንኩት ከ206ኛ ኮር የሚዲያ ክፍል ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
