ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 312
مشترکین
+17324 ساعت
+2467 روز
+1 36830 روز
آرشیو پست ها
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ድቾ ቀበሌ ሻሽበር ከተማ ላይ ታላቅ ጀብዱ ፈፅማ ውላለች።
የበረሀዋ ፈርጥ አፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ አበጀ ጥበቡ ብርጌድ በዛሬው እለት ማለትም ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም ከንጋት 12:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7:00 ሰዓት ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ገዳ ኮማንዶ፣ኮሬ ነጌኛ፣ጋቻና ሲርና ፣ሚሊሻ ና ፖሊስ ጋር ባደረገችው ተጋድሎ ታላቅ ጀብድ መፈፀም ችላለች ።በተጋድሎውም 66 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ቁጥሩ ለመቁጠር የሚያዳግት ቁስለኛ በማድረግ ሶስት ምሽጎችን በማስለቀቅ ተራራ ላይ ሰቅላ ቁም ስቅሉን ስታሳየው ውላለች ።ሙሉለሙሉ ይደመስሱኛል በማለት ጭንቀት ውስጥ የገባው የሺመልስ ግብስብ በተለያዩ አቅጣጫዎች ባደረገው የድረሱልኝ ጥሪ ከቱሉጋና፣ከጊዳ አያና ከወረዳው ማለት ነው ፣ከጉትን እንድሁም ከኡኬ ና ከነቀምት ያለየለለ ኃይሉን አሟጦ ሲመጣ ወደኋላ ሲያፈገፍጉለት የፈሪ በትር ሆድ ይገትር እንድሉ የሁሌም ተግባሩ የሆነው የኦሮሙማው ስርዓት ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሰራዊቱ እንደደረሰ ቤት ማቃጠል፣ንብረት ማውደም ና በመዝረፍ በርካታ ሰዎችን በማፈናቀል ግፍ ፈፅመዋል።አሁንም የነውር መገለጫው የሆነውን ተግባሩን እሰከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ቤት በማቃጠል ላይ ነው ።
ጠላት ምሽግ የተሰበረባቸው ቦታዎች
1) ስላሴ ሰፈር
2) ጎጃም ሰፈር
3) ቀበሌ
4)ረጋሳ ፎቅ ናቸው።
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቢዛሞ ዕዝ
አበጀ ጥበቡ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ ብርሌው ስብሀት
ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም
🔥#ሰበር_ዜና‼️
ጠዶት ሚካኤል ላይ የጠላት ኃይል አልቋል!
ዛሬ ታህሳስ 14/2018 ዓ/ም በምስራቅ አማራ ቀጠና መርሣ ዙሪያ ልዩ ቦታው ጠዶት ሚካኤል ላይ አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ባደረገው ከባድ ተጋድሎ የጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ልክ እንደ ደረቀ ዛፍ ቅጠል እረግፈዋል።
በውጊያው ከተገደሉ የአገዛዙ ወታደሮቹ መካከል የተመረጡ ጥቂት የአስከሬን ምስሎችን ተመልከቱ‼️
©መረብ ሚዲያ
#እጅ_ስጥ_ለአብይ_ወንበር_አትለቅ‼️
/ዐ4/2018 ዓ.ም
#ሰበር_ሰበር_የድል_ዜና #ሞት_አይፈሬው_206ኛ_ኮር_ከጠላት_ጉሮሮ_
27 ክላሽ ማርኳል"
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ሞት አይፈሬው 206ኛ ኮር በተለያዩ ግንባሮች በዛሬው ዕለት ባደረገው ተጋድሎ እጅግ አስደናቂ በሆነ ትንቅንቅ ከጠላት ጉሮሮ 27 ክላሽ ማ*ር*ኳል።
በራሱ ፍላጎት እየተክለፈለፈ ከአምበር ከተማ በመነሳት ወደ ጃማ ከተማ በማቅናት ጥቃት ለማድረስ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ የ206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስና ደጃች ተድላ ጓሉ ሻለቃ በፈፀሙት የማ*ጥ*ቃት ው*ጊ*ያ ጠ-ላ-ትን ከምድር ደባልቀው 27 ክላሽ ፣በርካታ ካዘና፣የደረት ትጥቅና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁስ ማ-ር-ከ-ዋል።
ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀትር 6:00 ስዓት በወሰደው ጠንካራ ውጊያ ጠላትን ያጋደሙት የ206ኛ ኮር አሃዶች 45 በላይ ጠላት የደ-መ-ሰ-ሱ ሲሆን ከ22 በላይ የጠላት ኃይል ከባድ ቁ-ስ-ለ-ኛ ሁነዋል።
የአረ-መ-ኔ-ው ሰራዊት፣አድማ ብተና እና ሚኒሻ በታ-ጨ-ደ-በት ውጊያ ጠላትን ቅስም በመስበር አስደናቂ ጀብድ የፈፀመው 34ኛ ክ/ጦር ተደጋጋሚ ድል ያስመዘገበ ጠንካራ ክ/ጦር ሲሆን በዚህ ስዓት 15 የጠ-ላ-ት ከባድ ቁ-ስ-ለ-ኞች በጫካ ወድቀው እንደሚገኙ ታውቋል።
በተያያዘ ውጊያ 206ኛ ኮር የ14 ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሐንዲስ ከሻለቆች ጋር በመቀናጀት ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ማርዘነብ ከተማ ላይ በደረሰው የጠላት ኃይል ላይ በፈፀሙት ፈጣን ማጥቃት ተመሳሳይ ድል የተገኘ ሲሆን የአረመኔው ሰራዊት ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዶ 23 አ-ስ-ክ-ሬን ተሸክሞ ተመልሷል።
አዲስ ትውልድ !አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የቀሰተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎችና የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር ባዳረገቱ የተቀናጀ ኦፐሬሽን ለዘረፋ ወደ ማርዘነብ ቀበሌ በወጣው የብልጽግና ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ፈጽሟል።
ታኅሳስ 14/2018 ዓ.ም
ሕዝብን በዘረፋና ውንብድና ተግባሩ እያማረረ የሚገኘው የብልጽግና ሥርዓትና ወራሪ ሠራዊቱ የተለመደ የወንብድና ተግባሩን ለመፈጸም በጠዋቱ ወደ ማርዘነብ ታዳጊ ከተማ ቢንቀሳቀስም ግብራቸው እንደስማቸው ከከፍታው ሰማይ ከፍ ብሎና ደምቆ የሚታየው ቀስተኞቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎችና ነበልባሎቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር ጥምር ጦር አባላት ባደረጉት በዲሽቃ የታገዘ የተቀናጀ ኦፐሬሽን በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።
ውጊያው የገወጥ ቤተ ክርስቲያንና ማርዘነብ ከተማ ጫፍ ላይ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የክፍለ ጦሩ ኮማንዶ ሻለቃ አባላት በሌላ አቅጣጫ የጠላት እንቅስቃሴና የኃይል ጭማሪ እንዳይኖር መንገድ በመዝጋት ውጊያው ስኬታማ እንዲሆን አድርገዋል።
በዚህ ውጊያም ሁለት ፓትሮል አስከሬንና በርካታ ቁስለኛ ተነስቷል።
በተጨማሪም ይህ የሌባ ቡድን በተለመደው የዘረፋ ተግባሩ የበርካታ ነዋሪዎችን ሀብት ንብረት ዘረፋ ፈጽሟል።
ለአብነት ያክልም፦
➠ ሁለት የመድኃኒት መደብሮች ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋል፤
➠ ሁለት ኩንታል ስንዴና ቁጥሩ ያልታወቀ ገንዘብ
➠ በግብር እና ጤና መድኅን ስም በርካታ ግለሰቦች ያለ ሕጋዊ ደረሰኝ ተዘርፈዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የአስተዳደር መምሪያ አላፊ አርበኛ ሱጦታው ዳኛው (ባሻ)ብዙ ያልተባለለት ዝምተኛ ሚሳኤል ፤ብዙ ያልተወራለት የፋኖነት ምልክቱ ዛሬ አይደለም በዛ በጭንቁ ወቅት በወያኔ ዘመን ፍትህ ርዕትህ ለማስፈን በአፈሙዘኛ ቋንቋ እምቢ ባይነቱን ያቀጣጠለ እና የመራ ጀገና ቅድመ እና ድህረ 2008 ዓ.ም በጽናት የወያኔን አገዛዝ በመፋለም ጠራርጎ ወደ መቀሌ እንዲመሽግ ያደረገ የወንድ ማርከሻ።
በጎንደር የሚደረጉ የፋኖ አደረጃጀቶች ሁሉ ቀዳሚ የሆነው አርበኛ ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ቤተሰቦቹን ልጆቹን ጭምር በማሰለፈ በጽናት የትግሉን ሚዛን እያሰጠበቀ የሚገኝ ባለግርማ ሞገሱ ገምሻራው አልሞ ተኳሽ አርበኛ ነው።
አርበኛ ባሻ ከዛም በፊት እና ከሰሜኑ ጦርነት እስከ አሁኗ ሰአት ድረስም ከነባር ጓዶቹ ጋር በመሆን በጫካ እንደመነነ ያለ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጥርን እስከ የቀድሞው ጎንደር ዕዝ ዛሬም በበላይ ዕዝን ያደራጀ እና አስፈሪ የጎንደር የፋኖ ጦር የገነባ ዛሬም በጽናት አገዛዙን እየተፋለመ ጀግንነት ሞራል እየሰጠ ያለ ስመጥር አርበኛ ነው።
የትግሉ ሚዛን አስጠባቂዎች የአማራነት ከፍታ መገለጫዎች የፋኖነት ልዕልና ገላጮች በፉከራ በሽለላ በሆይ ሆይታ ተንጋግተው ወደ ትግል ያልገቡ ነባር ስመጥር ከሆኑት አርበኞቻችን መካከል ማህፀነ ለምለሟ የጎንደር አማራዋ እናት ያበቀለችው አክተሩ ገምሻራው አርበኛ ባሻ ሱጦታው✊
ቆቦ ከተማ መሬት ወረራ ላይ የተሰማሩት የብልፅግና ካድሬዎች ዘረፋቸው በተጨባጭ ማስረጃ ተጋለጠ!
ምኒልክ ዕዝ ባለፉት ጊዜያቶች በመመሪያ የተደገፈ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥበት የኖረውና አገዛዙ በሰፊው ተሰማርቶበት ያለው የመሬት ወረራና ዘረፋ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ የህዝብ ሃብት የሆነው ሁለገብ አዳራሽ የፋኖን መመሪያ በመጣስ አቶ ደጀኔ መንገሻ የተባለ ግለሰብ አረብ አገር ለሚኖር ወንድሙ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር እንደገዛው ለማወቅና ለማረጋገጥ ችለናል::
አዳራሹ የተሸጠበት የገንዘብ መጠን ከፍ ያለ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች የገለፁ ቢሆንም ይፋ ከሆነው ከዚህ 100000000 (አንድ መቶ ሚሊየን) ብር ገንዘብ ውስጥ 80000000 (ሰማኒያ ሚሊየን) ብሩን ገቢዎችና ሌሎች ቢሮዎች የሚያውቁት ሲሆን 20000000 (ሃያ ሚሊየን) ብሩ በየደረጃው ላሉ የብልፅግና ካድሬዎችና ለደላላ የተሰጠ ገንዘብ ነው:: መጠኑ ያልተገለፀ ገንዘብም በየደረጃው ላሉ የመከላከያ አመራሮች እንደተሰጠ ለማወቅ ችለናል::
ቆቦ ከተማን ጨምሮ በራያ ቆቦ ህዝብ ሃብት እንደተገነባና በደርግ ዘመን ውድቀት ተጀምሮ በኢህአዴግ ዘመን መባቻ 1984 ዓ.ም እንደተጠናቀቀና አገልግሎት እንደጀመረ የሚነገረው ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ ዛሬ ላይ የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ "የአማራን ህዝብ በአማራ ህዝብ ሃብት" በሚል መርህ መሰረት መሬት ሽጦ በሚገዛው ጦር መሳሪያና ተተኳሽ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው ፋሽስታዊ አገዛዝ መጠቀሚያ ሆኗል::
በዚህም ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ በፋኖ ትግል ተንኮታኩቶ የገንዘብ አቅሙም ሊጠገን በማይችል ሁኔታ የወደቀ ሲሆን ይህንን የገንዘብ ችግሩን ለመፍታት በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ላይ የመሬት ወረራና ዘረፋ እየፈፀመ በህገወጥ ጨረታና ሌሎች መንገዶች እየሸጠ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የህዝብ ሃብት የሆነውን ቆቦ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው ገንዘብ የተከፋፈሉና በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠባቸው የቆቦ ከተማ እና የሰሜን ወሎ ዞን አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፦
1.አቶ ከድር ሙስጠፋ ---- የሰሜን ወሎ ዞን ብልፅግና ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-ሻምበል እንዳየነው በተባለ ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
2.አቶ ሃይለአብ ወንድሙ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ 6000000 (ስድስት ሚሊየን) ብር
-ንጉስ አያሌው ጌታሁን በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና እስጢፋኖስ እምሩ ዘለቀ በተባለ ግለሰብ 2.5 ሚሊየን እና 1 ሚሊየን በድምሩ 3.5 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
3.አቶ ይርጋ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ሃላፊ 6200000 (ስድስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሙሉ ታከለ ገ/ስላሴ በተባለች ግለሰብ 5.3 ሚሊየን ብር እና መቅደስ መለሰ ይመር በተባች ግለሰብ 9 መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኞች ከስር በማስረጃነት ተያይዘዋል::
4.ዶ/ር አዲሱ ወዳጆ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሬት አስተዳደር ፅ/ቤት ሃላፊ 1000000 (አንድ ሚሊየን) ብር
-መሳይነሽ ደጀን ተገኘ በተባለች ግለሰብ 1 ሚሊየን ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
5.አቶ አበበ ይመር ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ 200000 (ሁለት መቶ ሽ) ብር
-ሁለት መቶ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
6.አቶ ሙለታ መሃመድ ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ልማት ባንክ ቡድን መሪ 150000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
-አንድ መቶ ሃምሳ ሽ ብር በግል አካውንቱ በስሙ የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
7.አቶ ሃይለማርያም አትክልት ---- የቆቦ ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ፅ/ቤት ም/ሃላፊ 100000 (አንድ መቶ ሽ) ብር
-ደሳለ ፈንታው መንገሻ በተባለ ግለሰብ መቶ ሽ ብር የተላለፈበት የባንክ ደረሰኝ ከስር በማስረጃነት ተያይዟል::
8.ቦታውን ያሻሻጠው ደላላ ወይም ግለሰብ 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር
በአጠቃላይ ለፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ካድሬዎች 14650000 (አስራ አራት ሚሊየን ስድስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የተሰጠ ሲሆን 5350000 (አምስት ሚሊየን ሶስት መቶ ሃምሳ ሽ) ብር የህዝብን ሃብት ደላላ ሆኖ ላሻሻጠው ግለሰብ የተሰጠ ገንዘብ ነው::
በመጨረሻም የአማራ ህዝብ ሆይ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ነውና ብሂሉ ግፈኞች ተመቸን ብለው በጉልበት ሃብትህን ተቀራምተው ታንክና መድፍ ጄትና ድሮን ታጥቀውበት ብሎም ለአራዊት ሰራዊታቸው ደመወዝ እየከፈሉበት መልሰው አንተው ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀሙበት እንደሆነ አለም ያወቀው ሐቅ ነውና በትግልህ ነፃነትህን በነፃነትህ ፍትህና ርትዕን ትጎናፀፍ ዘንድ ዛሬም መልክታችንን እናስተላልፋለን!
በመጨረሻም ግፈኞች መሬቱን ተሸክመውት የትም አይሄዱምና "የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ የህዝብ ነው!" የሚለው መመሪያችን እንደተጠበቀ መሆኑን እየገለፅን ህዝባችን ከግፈኞችና ይሄ ጊዜ የማያልፍና የማይነጋ ከመሰላቸው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰዎች ህገወጥ መሬት ባለመግዛት ራሳችሁን ከክስረት ብሎም ከጥፋትና ተጠያቂነት እንድትታደጉ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን!
ማስታወሻ፦ በሌሎች የቤተ-አማራ አካባቢዎችም ላይ ያሉ የመሬት ወረራና ዘረፋዎች በጥብቅ ክትትላችን ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ ሲሆን ማስረጃዎች እንደደረሱን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
ታላቁ እና ታሪካዊው ድብር ጨጨሆ መድኃኔዓለም በመከላከያ ሰራዊት ተዘረፈ!
በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በላይ ጋይንት ወረዳ የፈለገ ፀሐይ በቅሎ አግት ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዝግ ሙዳየ ምፅዋት በመከላከያ ሰራዊት ዘረፋ እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል።
ነፍሰጡር እናቶችንና ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደል፣ የስምንትና የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ልጆችን ሳይቀር ሴቶችን በደቦ መድፈር፣ አዝመራ ማውደም ልዩ መገለጫው የሆነው መከላከያ ሰራዊቱ ከደቡብ ጎንደር ዞን ካቢኔዎች ጋር በጋራ በመሆን በታላቁ እና በታሪካዊው ድብር ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ፍተሻ በሚል ሰበብ፡ ተጓዥ መንገደኞች ለደብሩ የሚሰጡትን ምፅዋትን ጨምሮ በዝግ ሙዳይ ምፅዋት የተቀመጠን ገንዘብና ሌሎች የቤተክርስቲያኗን ሀብት መዝረፉን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ወታደሮቹ ከሙዳየ ምፅዋቱ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኗ ታሪካዊ ቅርሶችንም ዘርፈው መውሰዳቸው ነው የታወቀው።
በ5ኛው ክፍለዘመን እንደተመሠረተች የሚነገርላት ቤተክርስቲያኗ ከሁለት ዓመታት በፊት አገዛዙ ከሕወሓት ጋር ባደረገው ጦርነት የመድፍ ጥቃት ተፈፅሞባት የነበረ ሲሆን፡ አሁን ደግሞ በመከላከያ ሰራዊቱ እና በዞኑ ካድሬዎች የተቀናጀ የዘረፋ ጥቃት ተፈፅሞባታል።
የቀድሞ ነገስታቶች በስጦታና በእጅ መንሻነት ለቤተክርስቲያናት የሰጡትን የወርቅና ሌሎች ውድ ስጦታዎችን ቤተክርስቲያኗ እስከ ዛሬ ጠብቃ ያቆየች ሲሆን፡ እነዚህ ውድ ስጦታዎች በአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች እየተመዘበሩ በአለም አቀፍ ገበያዎች ላይ መቅረባቸው ሲዘገብ መቆየቱ ይታወቃል።
መረብ ሚዲያ
➩ጥብቅ ማሳሰቢያ ለዱርቤቴ ከተማ ነዋሪዎች ከአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር የተላለፈ መመሪያ
በአፈሙዝ የተሸነፈው የብልፅግና ቡድን በጦር ሜዳ ያጣውን ድል በተራ ፕሮፖጋንዳ ለመሸፈን በየ ቦታው በግብስብስ ሰራዊት ብዛት እየታጀበ ህዝቡን እየሰበሰበ የተለመደ የውሸት ትርክቱን ሲነዛ እያስተዋልን ነው ይህ ሁናቴ መሬት ላይ ያለውን ሽንፈቱን ከመቀበል ባያድነውም ግን የብልፅግና አመራሮችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን ለመሰንዘር ማህበረሰቡ እንዳይጎዳ እያልን ትተናል ።
በነገው እለትም በባንዳዎች ፊት አውራሪ አረጋ ከበደ የተመራ ልኡክ ዱርቤቴ ከተማ ማህበረሰብን ለመሰብሰብ እንደተዘጋጀ ደርሰንበታል
ስለዚህ ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍል በየቤቱ እንዲቀመጥ እያሳሰብን ባንዳውን ለመቀበል ዝግጅት የምታደርጉ የኮሚቴ አባት
1,ታከለ አዲስ
2,ታደለ አላምረው
3,አለሙ በቀለ
4,አማረ ይግዛው
5,አብየ አቤልነህ
6,ጥላሁን የኔነህ
7,እመቤት ሰማው
8,ይሁኔ ፀሀይ
9,አዲሱ አበይ
10,የምስራች ታፈረ
11,አየነው አዲስ
12,ብዙአየሁ ፈጠነ
ከምታደርጉት ድርጊት እንድትቆጠቡ እያሳሰብን ማታቆሙ ከሆነ ድርጅታዊ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እንድታውቁ ይሁን ።
የአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛክ/ጦር
የብአዴን ባለሃብት አጨብጫቢዎች ስልካችን busy አታድርጉት እንጅ !
" ቅድም ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ ፣
አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ። ይላል አማራው !
የNBC Ethiopia (National Media S.C.) የቦርድ አባላትና ዋና ባለአክሲዮኖች ከምኔው አክቲቪስቶችንና ጋዜጠኛ ነን ባዮችን ቤት ማንኳኳት ጀመራችሁ? ጉዳዩ እኮ የአማራ ህዝብ ህልውና እንጅ የግለሰብ ጥቅም ጉዳይ አይደለም። በደንብ ወደ ውስጥ ሳንገባ ገና በአንድ ሻት ጋዜጠኛን ከተኛበት ቀስቅሰህ አድነኝ ብለህ የምትድንበት የማርያም መንገድ የለህም እኮ።
የአማራ ህዝብ ያለ እነዚህ የብአዴን ባለሃብቶች ነበረ፤ ለወደፊትም ይኖራል። የእነሱ ቢዝነስ ግን በአማራ ህዝብ ላይ ብቻና ብቻ የተንጠለጠለ ነው። እናማ አማራውያን እነዚህ ፊት ተሰላፊ የብአዴን ባለሀብቶች ምን እየሰሩ ነው የሚለውን በዝርዝር እንሄድበታለን። አክቲቪስት አያድንህም፤ ከእንቅለፉ ቀስቀሰህ የለሁበትም ያልከው ጋዜጠኛ አያድንህ...ስግብግብ ከርሳም ሁላ።
ከግብፅ የሚመጣው ኦማር ዘይት ቡሬ ከሚመረተው ዘይት በዋጋም በጥራትም እንደሚሻል እያወቅን ዝም ስንል ንግዳችሁን ለአማራ ህዝብ በጎ አድራጎት አድርጋችሁ የምትቆጥሩት ነገርስ የማይገርመን ይመስላችኋል እንዴ?
አማራ ሁኖ በአማራ ህዝብና በአማራ ምርት ሀብት ከሰበሰበ በኋላ ከአማራ ጠላቶች ጋ አብሮ የሚሰራ ሁሉ ለአማራ ጠላቱ እንጅ ወገኑ ሊሆን ከቶ አይችልም። ሌላው ቀርቶ የክልሉ ህዝብ እንዳይጠቀም እንኳን ግብር የሚከፍሉት ድሮን አየገዛ አማራ ህዝብን ለሚጨርሰው የፌደራል መንግስት እንደሆን እኮ የአደባባይ ሚስጥር ነው።
ዛሬ እኔና እኛ ከዚህ ሚዲያ የለንበትም እያለ ጥሩንባ የሚያስነፍው የብአዴን ባለሃብት እኮ የመጀመሪያ ጥፍቱ የአማራ ህዝብ የራሱ ሚዲያ ያስፈልገዋል በሚል እንደዛ ላይ ታች ሲወረድና ሲወጣ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ ከርሞ ስልታዊ በሆነ መንገድ ሚዲያ አቋቁሞ ለጠላት ያበረከተ ስብስብ ነው ( ማበርከቱን በግልፅ ባናውቅም በተከላካዮቹ በኩል እንደሰማነው ከሆነ ማለቴ ነው )። የአማራ ባለሃብት የተባለ ሁሉ በእያንዳንዱ አማራ ትዝብት ውስጥ ከወደቀ ከርሟል። የኦሮሞ ተፈናቃዮችን መጠለያ ሰርቶ ሲሰጥ አማራ ምድር ላይ ምን አድርጓል? የአምቦን ትምህርት ቤት ማጠናከሪያ ረብጣ ገንዘብ ሲያሸክም አማራ ምድር ለይ ምን አድርጓል..... እያልን ብንዘረዝር የምናተርፈው እህህህ ማለት ብቻ ነው።
ለማንኛውም ልክ እንደ አቶ በላይነህ ክንዴ ሁሉ ሌሎች ባለአክሲዮኖች የሚመሯቸው ድርጅቶች በኢኮኖሚው ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላቸው።
በመረጃዎቻችን መሠረት የቁልፍ ባለቤቶቹና የድርጅቶቻቸው ዝርዝር እነሆ፦
1. አቶ በላይነህ ክንዴ (የቦርድ ሰብሳቢ)
ድርጅት፦ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ (BKG)
ዋና ዋና ሥራዎች፦ ፊቤላ የምግብ ዘይት፣ ሒልተን አዲስ አበባ፣ ሊዩ ትራክ መገጣጠሚያ፣ የቡና ኤክስፖርት እና የከባድ ጭነት ትራንስፖርት።
2. አቶ ታደሰ ምሕረቴ (ባለአክሲዮን/ባለቤት)
ድርጅት፦ ወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ (Wereta International Business PLC)
ዋና ዋና ሥራዎች፦ የሰሊጥና የጥራጥሬ ኤክስፖርት፣ የቮልቮ (Volvo) መኪናዎችና የኬዝ (Case IH) ትራክተሮች ተወካይና አስመጪ፣ እንዲሁም ሰፊ የትራንስፖርት ዘርፍ።
3. አቶ ዘመነ ሳሙኤል (የቦርድ አባል)
ድርጅት፦ ዘመነ ሳሙኤል ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ (Zemene Samuel International)
ዋና ዋና ሥራዎች፦ በሰፊው የሚታወቁት በጎማ (Tires)ና በመኪና መለዋወጫዎች አስመጪነት ነው። የበርካታ ዓለም አቀፍ የጎማ ብራንዶች ወኪል ናቸው። በተጨማሪም በሪል ስቴት እና በሆቴል ዘርፍ ኢንቨስትመንት አላቸው።
4. አቶ ታደሰ አማረ (የቦርድ አባል)
ድርጅት፦ ታደሰ አማረ አስመጪና ላኪ (Tadesse Amare Import & Export) ዋና ዋና ሥራዎች፦ በዋነኝነት በቅባት እህሎች (ሰሊጥ) ኤክስፖርት እና በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አስመጪነት ይታወቃሉ። በአማራ ክልል ሰፊ የግብርና ኢንቨስትመንት ካላቸው ባለሀብቶች አንዱ ናቸው።
5. ዶ/ር ወንድወሰን አምሳያ (የቦርድ አባል)
ድርጅት፦ ኢትዮ-ፓክት (Ethio-Pact)ና የተለያዩ የማማከር ድርጅቶች
ዋና ዋና ሥራዎች፦ እሳቸው ከንግዱ ይልቅ በስትራቴጂካዊ አመራርና በማማከር (Consultancy) ዘርፍ ይሳተፋሉ። በተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮችና ኢንሹራንሶች) ውስጥ የቦርድ አባልነትና የባለአክሲዮንነት ድርሻ አላቸው።
6. ወ/ሮ ፈቲያ መሐመድ (የቦርድ አባል)
ድርጅት፦ ኤፍ ኤም ጀነራል ትሬዲንግ (FM General Trading)
ዋና ዋና ሥራዎች፦ በኢምፖርትና ኤክስፖርት ዘርፍ በተለይም የፍጆታ ዕቃዎችን ወደ ሀገር በማስገባት የሚታወቁ ባለሀብት ናቸው። በንግድና ዘርፍ ማኅበራት ውስጥም ንቁ ተሳትፎ አላቸው።
ሌሎች የብዴን ተሰላፊ መካከለኛ ባለሃብቶች
1. አቶ ዮሐንስ ለገሰ (Yohannes Legesse)
ድርጅት፦ ዮሐንስ ለገሰ አስመጪና ላኪ (Yohannes Legesse Import & Export)
ዘርፍ፦ በቅባት እህሎች ኤክስፖርት እና በግንባታ መሣሪያዎች አስመጪነት የሚታወቁ ባለሀብት ናቸው። በንግድ ማኅበረሰቡ ውስጥ ሰፊ ተሰሚነት አላቸው።
2. አቶ ዓለሙ በቀለ (Alemu Bekele)
ድርጅት፦ ዓለሙ በቀለ ጠቅላላ ንግድ
ዘርፍ፦ በተለይ በከባድ መኪናዎች መለዋወጫ (Spare parts) እና በተለያዩ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አስመጪነት የሚታወቁ ሲሆን፣ በሚዲያ ዘርፉ ላይም ቀደም ብለው ኢንቨስት ካደረጉ ባለሀብቶች አንዱ ናቸው።
3. አቶ ጌታቸው አሰፋ (Getachew Assefa - ከወረታ ትሬዲንግ ጋር በተያያዘ)
ዘርፍ፦ በግብርና ምርቶች ኤክስፖርት እና በሎጂስቲክስ ዘርፍ ትልቅ ድርሻ ያላቸው ባለሀብት ናቸው።
4. የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች
ምንም እንኳን ድርጅቶቹ (ባንኮች) በቀጥታ አክሲዮን ባይገዙም፣ በእነዚህ ባንኮች ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ግለሰቦች በግላቸው በNBC Ethiopia ውስጥ አክሲዮን አላቸው። ለምሳሌ፦
የአቢሲኒያ ባንክና የአዋሽ ባንክ ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች የሆኑ የተወሰኑ ግለሰቦች በዚህ የሚዲያ ተቋም ውስጥም እጃቸው እንዳለ ይነገራል።
5. ሌሎች የንግድ ድርጅቶች (ተቋማዊ ባለአክሲዮኖች)
ከግለሰቦች በተጨማሪ አንዳንድ ድርጅቶች በራሳቸው ስም አክሲዮን ገዝተዋል ተብሎ ይታመናል። የተለያዩ የትራንስፖርትና የጭነት ድርጅቶች፦ ከበላይነህ ክንዴና ወረታ ትሬዲንግ ጋር በኔትወርክ የተሳሰሩ ትናንሽና መካከለኛ የትራንስፖርት ኩባንያዎች፣ አስመጪና ላኪ ማህበር አባላት፣ በሰሊጥና በቡና ኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ ሌሎች 15 የሚጠጉ መካከለኛ ባለሀብቶች።
ተመልከቱ እነዚህ የአማራ ተወላጅ የብአዴን ባለሃብቶች ናቸው እንግዲህ OMN ስለተጠላብህ፣ ፋና ስለተናቀብህ፣ ኢቲቪ አይንህን ለአፈር ስለተባለብህ በዚህ አማራጭ ሚዲያ ተጠቀም በማለት ሚዲያውን መስርተው ለአማራ ጠላት አስረክበናል የሚሉን።
እንደዚህ ከሆነማ ምንም የማያውቀው ሚሊሻ በምን ሒሳብ ይፈረድበታል እንዴ ?
የሆነው ሁኖ አማራዬ ጠላትህን እየመዘገብህ !
ይኸነው የሸበሉ
አዲስአበባ የወጣት ገሀ''ነም ሆናለች። ሰሞኑን እጅግ በርካታ ወጣቶች በጅምላ እየታፈሱ በመታሰር ላይ ናቸው!
በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ ጡረታ ወጥቶ የራሱን ህይወት የሚመራ ፣ ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌለው ቤተሰቤን ፣ እሱ ከሚኖርበት ሰፈር ጠራርገው ያሰሯቸውን የአማራ ወጣቶች ''አደራጅ ነህ'' ብለው ፈርጀውት ከታሰረ ሳምንታት ማለፉን አሁን ሰማሁ!😥
ሌላው በየትኛውም አካባቢ ታፍነው ድምፃቸው የጠፉ ሰዎችን መረጃ ያላችሁ ወገኖች እየሰማነው ካለው አሳዛኝ እርምጃ መታደግ የሚቻልበት ሁኔታ ካለ ቢያንስ ወደሚዲያ በማውጣትና መረጃውን በማጋራት እንድትተባበሩ ለመጠቆም እወዳለሁ!
በተጨማሪም ፦ በጣት የምትቆጠሩትና ፍትህ ለተነፈጉት በነፃ ጥብቅና በመቆም ታሪክ የማይዘነጋው ስራ እየሰራችሁ ያላችሁ የህግ ባለሙያዎችም ፣ ምንም እንኳ አድካሚ ጫና ውስጥ መሆናችሁ የሚታመን ቢሆንም በተቻለ መጠን በየማጎሪያ ካምፖቹ የታሰሩትን ትጎበኟቸው ዘንድ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ !
© ዘሪሁን ገሠሠ
ምስል ከማህደር
+1
የምርኮኛው ሰራዊት ከነኦራሉ ጋይቷል ‼️
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 66ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሻለቃ በቀን 13/04/2018 ዓ.ም በሰሩት አስደናቂ ኦፕሬሽን የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ሎሌዎችን ድባቅ በመምታት ተደጋጋሚ ጀብድ ፈፅመዋል።
የበሰበሰው አገዛዝ ሰራዊቱን በየጊዜዉ እየገበረ ስልጣኑን ለማራዘም እየተፍጨረጨረ ቢገኝም ከሽንፈት ግን አልዳነም። ይሁንና በዛሬዉ አዉደ ዉጊያ ጠላት ወደ ጃሂማላ ቀጠና ለሁለተኛ ጊዜ ለመግባት ሲሞክር ሰሌን ዉሃ ከተባ ቦታ ላይ በደረሰበት ከባድ ምት ከ34 በላይ ሰራዊቱ ተደምስሶበታል። እንዲሁም ከ20 በላይ ከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
አንድ #ኦራል መኪና እስከ ጫነዉ ሬሽንና ተተኳሽ በዲሽቃ ተመትቶ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ተችሏል።
ሌላዉ ከጥቅም ዉጭ የሆነዉን ኦራል ለመዉሰድ ከጃዊ ወደ ጦርነት ወደ ተካሄደበት ቀጠና የመጣዉ ክሬን መኪና በነበልባሎቹ 1ኛ ሻለቃ ተቃጥሎ ከጥቅም ዉጭ ሆኗል፣ የክሬኑ ሾፌርም መማረኩን የ66ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ከግንባር ዘግቦታል።
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
#ሰበር_የድል_ዜና‼️
#64ኛ_ክፍለ_ጦር_በሸበል_በረንታ_ወረዳ__በደፈጣ_ጥቃት_ወረጎ_እና_አካባቢው_ቀበሌ_ታሪክ_ሰረቷል።
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ ማህበረሰቡን በመልሶ ማደራጀት የሰለጠየ ጠንካራ ወታደራዊ ኃይል በማደራጀት እና በመገንባት በረካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
64ኛ ክፍለ ጦር በሸበል በረንታ ወረዳ እያደራጀ ባለው ግዙፍ ኃይል ስጋት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ተቅበዝባዥ ኃይል በቀጠናው የሚገኘው የፋኖ አባላትን ለማጥቃት በየዕዱኃ ከተማ መሽጎ ከሚገኘውን የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት ጨለማን ተገን በማድረግ በቁጥቋጥ ቀበሌ የፋኖ አባላትን ለማጥቃት ምክሮ ሳይሳካለት ቀረቷል።
በቁጥቋጥ ቀበሌ የገባውን የአገዛዙ አረመኔ ሰራዊትን ድጋፉ ለማድረግ ከየዕዱውኃ ከተማ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ተጨማሪ ኃይል በመያዝ በጉዞ ላይ የነበሩ በአንድ ፖትሮል እና በአንድ ላንድ ክሎዘር አመራር እና አባላት የጫነ ተሽከረካሪ በጉዞ ላይ እንዳሉ #በወረጓ እና አካባቢው ቀበሌ ልዩ ቦታው #ደረቅ_ወንዝ በተባለ ቦታ #64ኛ_ክፍለ_ጦር_5ኛ_ሬጅመንት በወሰደው የደፈጣ ጥቃት በፖትሮል ላይ የነበሩ የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አመራር እና አባላት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል።
በሸበል በረንታ የዕዱውኃ ከተማ ወደ ቁጥቋጥ ሲንቀሳቀስ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተሰራው የደፈጣ ጥቃት ከተደመሰሱት የአገዛዙ አረመኔዊ ሰራዊት አባላት ውስጥ:-
➤ሻምበል ሰለሞን የሻለቃ (ሬጅመንት )አዛዡ እና አንድ ጋንታ መሪ ፓትሮል ላይ እንዳሉ ተመተው የሞቱ
➤1ሚሊሻ እና 4 የመከላከያ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል የገቡ
➤ሆሲፒታል ከገቡት አምስቱ ቁስለኞች ውስጥ ሚሊሻውን ጨምሮ 2ቱ የመከላከያ አባላት መሞታቸውን አረጋግጠናል። የቀሩትም የመትረፍ እድል እንደሌላቸው ከውስጥ የመረጃ ምንጮቻችን ተሰምቷል።
➤አንድ ፖትሮል እና አንድ ላንድ ክሎዘር ተሽከረካሪ በደፈጣ ጥቃቱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
ፋኖ ይበልጣል ጌቴ
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
+1
♦በእነ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ቧያለው የክስ መዝገበ ላይ ከመጋረጃ የመሰከረው ግለሰብ ማነው?
በእነ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ከመጋረጃ ጀርባ የመሰከረው ግለሰብ መቶ አለቃ አሰፋ አድማሱ መሆኑ ተረጋገጠ። ግለሰቡ በምዕራብ ጎጃም ዞን የቋሪት ወረዳ ተወላጅ ሲሆን እስከ 2016 ዓ.ም ታህሳስ አጋማሽ ድረስ በገረመው ወንዳወቅ ብርጌድ የፋኖ አባል ነበር።
ግለሰቡ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊና የቀድሞው የባህርዳር ከንቲባ ድረስ ሳህሉ የቅርብ ዘመድ ሲሆን ከዚሁ ባለስልጣንም ሽልማት ተቀብሏል። ከዚህ በተጨማሪም በእስር ላይ ከሚገኙት የምክር ቤት አባሉ ከአቶ ክርስቲያን ታደለ ጋር የቅርብ ዘመድም መሆኑ ተገልጿል። አቶ ክርስቲያን ታደለ ምርጫ ሲወዳደሩ ምርጫውን አሸንፈው የምክርቤት አባል እንዲሆኑ ቅስቀሳ ሲያደርግ ነበር።
ይሁን እንጅ ግለሰቡ ጥቅም ፈላጊ በመሆን በመንግስትም በታጋዮቹም ዘንድ ለመመስገን ጥረት ያደርግ እንደነበር የቅርብ ማስረጃዎች አሉ። በዚህም በቋሪት፣ በፍኖተ ሰላምና በባህርዳር ቤትና ሌላ ንብረት ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ፋኖን በመክዳት ከመንግስትና ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እየሰራ ይገኛል።
በነገራችን ላይ ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የተለየ ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል።
ግለሰቡ ለፍትሕ ሚኒስቴር ቃል በገባኸውና እኛ ባልንህ መሰረት አልመሰከርክም፤ ይህንን ያደረከው ደግሞ ከተከሳሾች ጋር ተደራድረህ ነው የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት እንደሆነ የዐቃቤ ሕግና የደህንነት ምንጮች አረጋግጠዋል።
ከመጋረጃ ጀርባ የመሰከረው ይህ ግለሰብ ሊታሰርና ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችልም ተገልጿል።
