fa
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
3 011
مشترکین
+2324 ساعت
+367 روز
+41430 روز
آرشیو پست ها
ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎች ይድረስ!!! የወረዳ ምርጫ አስተባባሪዎች ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 1/2018 ዓ/ም በባህር ዳር ከተማ የምርጫ ስልጠና በድብቅ የሚወስዱ ናቸው።  ከ26 ቀን ጀምሮ ጥብቅ ፍተሻ አርገን ተገቢ አቀባበል እንድናደርግላቸው በማለት መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡              ከደጀን 1)  አበባው ልንገረው 2)  ይበልጣል ባዩልኝ 3)  አሞኘሽ ደቤ               ከቢቸና 1 ማርቆስ(0921328563) የምታውቋቸው ጓደኞቹ            ከደብረ ማርቆስ 1 አንሙት ጌትነትና እናንተ ጋ የያዛችኋቸው ጓዶቹ               ከድጓ ጽዮን 1)  ጥላነህ ነበረ አዲስ 2)  ልንገር እንዳሌ ደስታ 3)  ቦሰና እውነቱ እንዳለ               ከደብረ ወርቅ 1)  ለወየሁ ተመስገን ሞሴ 2)  አዲሱ ይሁኔ በላይ 3)  የሽ ጫኔ ከቤ 4) አዝመራ ጠበቃው ዳኛው            ከአምበር 1) ማስተዋል ታረቀኝ ይርሴ 2) ሁልጊዜ ታደለ 3) ስነወርቅ ታደለ ሁለቱ አግለዋል ማስተዋል ግን 2 አዲስ አስገብታ ለብልግና የምታሽቃብጥ አምበር ስራዋ ሉማሜ ማደሪያዋ(0949961004)                   ከየእድ ውኃ 1) ዮሴፍ ንጉሴ ማፈሪያ የሌለው ሆዳም ምን እንደምታረግ እናውቃለን 2) ሙሉጌታ መንግስት 3) እየሩስ እራሷን ያገለለች         ከየጁቤ 1) ከዳርዳር አሳምረህ 2) አይመር ማናየ 3) ልጃለም ጤናው 4) ይደግ አንተነህ              ከዱርቤቴ 1) ሀብታሙ አቸንፍ 2) እሱባለው አምሳሉ 3) ላቀ አይገኝ 4) መጣአለም ጌታነህ              ከቡሬ 1) አንዷለም ታረቀኝ 2) መንግስት ጌታነህ 3) ንጹህ ሰለሞን 4) ማስተዋል በሪሁን 5) ኢዛና በላቸው አለባቸው 1) ዮናስ ሞገስ 2) ዘውዴ ብሻህ 3) ይልማ አበበ                ከቁይ 1) ጽላት አበረ ፈጠነ 2) አለምነህ ፈጠነ መርሴ 3) መሰረት አለማየሁ 4) ነብዩ ላመነው እምሬ              ከግንደወይን 1) መኮነን አወቀ 2) እሱባለው ጸጋ 3) መቅደስ አየሁ 4) ጥሩዓለንም መንግስት           ከመርጦለማርያም 1) ሰለሞን ወርቅየ አስጨንቅ 2) እንደግ አግድ በዛብህ 3) አወቀ አባተ ይላቅ 4) ደመቀ ሙሉዓለም ተዋበ            ከጎዛምን 1) ዳንኤል ማኔ 2) ማናየ አለኸኝ 3) ቴወድሮስ አያሌው              ከሉማሜ 1) አዲሱ ዘሩ 2) እንቻለው አያሌው 3) ሳንበል              ከዳንግላ 1) ቴወድሮስ መኮነን 2) ታደለ ዳኛው            ከፍኖተ ሰላም 1 መለሰ ጌታነህና እናንተ የምታቋቸው ጓዶቹ               ከአማኑኤል 1 ጽዮን ዳምጤና የምታውቋቸው ጓደኞቿ               ከሞጣ 1) ተመስገን ፈለቀ 2) ታደገ ወንዴ 3) ላመስግን               ከአዲስ ቅዳምን 1) ስሜነህ እንግዳ 2) መኳንንት በላይነህ              ከረቡ ገብያ 1) ቢንያም እንቻለው ወንዳለ 2) ዝጋለ መንግስት አበበ 3) ውዴ እናውጋው በላይ                  ከባ/ዳር ሞላልኝ ደሳለው                  ከወረባቦ 1) መሀመድ ሙሳ ይመር 2) እንዳለው አበበ አላምረው 3) ሰይድ ኢብራሒም መሃመድ               ከድል ይብዛ 1) አማረ ባየ 2) ዘመናይ መንግስቴ 3) ጀጃው ገ/ማርያም 4) ቢምረው በየነ                  ከደብረ ሲና 1 1) አበበ ዳምጠው 2) ሙሃመድ መንግስቱ 3) አሊ ምትኩ               ከጃማ ደጎሎ 1) አቡሽ ፍስሃ 2) አብራክ ዘውዱ 3) ሳቦም ደመቀ ኃይሉ            ከጎንደር ዙሪያ 1) ጌታቸው ሙጨየ አቡሃይ 2) መንበሩ ሙሉ 3) ሙሉቀን ከሳው                 ከድብረ ብርሃን 1 ስመኘው አታላይና እናንተ የያዛችኋቸው ጓደኞቹ             ከመተማ 1 መሰረት ዋሲሁን መንግስቴና የምታውቋቸው ጓደኞቿ              ከኩታበር 1 ይመር አህመድና የያዛችኋቸው ጓደኞቹ               ከላይ አርማጭሆ 1 ሃጎስ ደነቀውና እናንተ የምታውቋቸው ጓደኞቹ                  ከደላንታ 1) አብርሃም ዓለሙ 2) ጌጥየ አበባው መልካም 3) ጌትነት አዳነ አዱኛ 4) ብርሃን ታርቀኝ                ከጎንደር ዙርያ 1) ታድሎ ሹመት አየለና የምታውቋቸው ጓደኞቹ                  ከዓለም ከተማ 1) አግዘው ካሳና የያዛችኋቸው ጓደኞቹ                 ከደንቢያ 1) ናትናኤል ስመኘውና እናንተ የምታውቁቸው ጓደኞቹ                ከወግራ 1 1) ፋሲል ዓለሙና የምታውቋቸው ጓዶቹ                 ከቃሉ 1 1) ቃልኪዳን ሰለሞን 2) ስመኘው አያሌው 3) አመለወርቅ የውድ 4) ሰለሞን በፍቃድ                ከቃሉ 2 1) ሁሴን ሞሃመድ 2) ብርሃኑ አውራሪስ 3) ጀማል አብዱ 4) ሙስጦፋ ኢብራሒም                ከጎንደር 04 1) መንበሩ ሙሉዓለም 2) ጌታቸው ሙጨየ                 ከመቅደላ 1) ዑስማን ሹምየ 2) አማኑኤል ዓለሙ 3) ዳንኤል ብርሃኑ 4) ሙራድ ፈጠነ ይቀጥላል...................!

ተስፋ ሲደረግ መከራ፤ ይሻሻላል ሲባል መዓት! በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ህዝቡ የለውጥ ያለህ እያለ ቢጮህም፣ በምላሹ ያገኘው ግን የባሰበትን መከራ ነው። ዛሬ የነዳጅ ዋጋ በሊትር 25 ብር ሲጨምር፣ ይህ ዝምተኛ ህዝብ ላይ የተጫነ ሌላው የሞት ፍርድ ነው። ዝምታው እስከመቼ? ኑሮ በካስማው ላይ ቆሞ፣ የቤት ኪራይና የሸቀጥ ዋጋ ጣራ ነክቶ፣ አሁን ደግሞ ነዳጅ የህዝቡን ጉሮሮ እንደተለመደው ሊዘጋ መጥቷል። ይሄ ተኝቶ የሚገረፍ ህዝብ ካልነቃ፣ ከዚህ የከፋ መዓት ገና ይወርድበታል። ዛሬ ካልተቆጣህ፣ ነገ መቆጫው ጊዜ ያልፋል። ‘ብልፅግና’ የተባለው ተስፋ፣ ዛሬ የውድመትና የጭቆና ተምሳሌት ሆኗል። ህዝብን እያደኸዩ መክበር አብቅቷል። ይሄ የመጨረሻው የስርዓቱ መቃብር መቆፈሪያ እንጂ ሌላ አይደለም። ህዝባዊ ቁጣው ሲገነፍል፣ ብልፅግና እንደ ጉም መበተኑ የማይቀር ነው። መዓቱ ሳይጠናቀቅ፣ ህዝብ ሆይ ንቃ!

#ከሣሲት_ክላስተር_ወጣቶችና_የሀይማኖት_አባቶች_ጋር_የተደረጉ_ሁለት_ህዝባዊ_መድረኮች✅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የስራ መመሪያ መሰረት በሸዋ ጠቅላይ ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች የህዝብ መድረኮች ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተደረገ ይገኛል። ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም አፋብን ባስቀመጠው የስራ አቅጣጫ መሰረት "በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተቆጣጠራቸው በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በአማራ የህልውና ጉዳይ ላይ ያተኮረ ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶችን ያሳተፈ ሁለት መድረክ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሞጃና ወደራ ወረዳ በሣሲት ክላስተር ተካሒዷል። ዛሬ ሚያዚያ 26 ቀን 2018ዓ.ም በተካሔደው መድረክ የሣሲት ክላስተር ነዋሪ ከሆኑት ወጣቶችና የሀይማኖት አባቾች ጋር ውጤታማ መድረክ መካሔዱን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር በግንባር መረጃው ገልጿል። የአፋበን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣የህግና ፍትህ አመራሮች፣ በዕዙ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ስር ያሉ የ3 ክፍለ ጦር አመራሮች፣የራንቦ ክፍለጦር ፣የ7ለ70 ክፍለጦር፣ የንጉስ ሳህስ ሥላሴ ክፍለጦር አመራሮች በመድረኩ ላይ ተገኝተዋል። ለውይይት በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ወቅታዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች መድረኩን በመሩት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የፖለቲካ መምሪያ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም

አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነዉ ዕዝ ስር ባሉ የተጉለት አውራጃ በግፍት ክላስተር ታላቅ ህዝባዊ መድረክ ተካሄደ። በተደራጀ የፖለቲካ ሥራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ህልዉናውም ይረጋገጣል።በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ህዝባዊ መድረክ ወቅታዊ የትግሉን ጉዳዮችን የአካተተ በሳል የመድረክ ዉይይት ተደርጓል። ከዕዝ አመራር ጀምሮ፣የኮር እና የክፍለ ጦር አመራሮች በመገኘት ህዝባዊ መድረኩን በመምራት ተሣትፈዋል ከአፋብን የወረደውን የድርጅቱን ሰነድ በማብራራት እና ዉይይቱን በመምራት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እና ግዴታቸውን በአግባቡ ተወጥተዋል። የዉይይቱ ተሣታፊ አርሶ አደሮች በርካታ ሀሳቦችን በመድረኩ ላይ አንስተዋል።ከተነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል ጥቂቶቹ፦ 1. የብልፅግናን የምርጫ ቀልድ የአማራው አርሶ አደር በፍፁም የማይቀበሉት መሆኑን ከህዝቡ አንደበት የተረጋገጠበት የመድረክ ዉይይት መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለበት ሆኗል። 2. ጨፍጫፊው እና አረመኔው አገዛዝ ሆን ብሎ ህዝቡ በኑሮ ውድነት እና በትራንስፖርት ችግር ምክነያት መኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በማድረግ እያሰቃየን ይገኛል።ስለዚህ ትግሉን ተባብረን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በድል ማጠናቀቅ የሁላችንም ግዴታችን መሆን አለበት። 3. የአማራ ፋኖ ከምንጊዜውም በላይ አሁን ድርጅታዊ አንድነቱን እና እርስ በርሱ በመወያየትና በመተማመን የተያዘውን ትግል በአጭር ጊዜ መቋጨትና ማጠናቀቅ አለበት በማለትም አክለው ገልፀዋል። 4. እኛ የአማራ አርሶ አደሮችን ብልፅግና በተለያዩ የጥቅማጥቅም ወጥመዶች ሊያጠምደን እና ሊያታልለን አይችልም።ምክነያቱም የአማራን አርሶ አደር በከባድ መሣሪያ ሀብት ንብረቱን እያወደመ ምረጡኝ ማለት የአገዛዙን ሽንፈቱን ያመለክታል።በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነትን አውጆብን እየፈጀን የይስሙላ ምርጫን አንቀበልም ሲሉም ሀሳባቸውን በመድረኩ ላይ አንፀባርቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሚያዚያ 25 ቀን 2018ዓ/ም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተጉለት አውራጃ በግፍት ክላስተር በተካሄደው ታላቅ ህዝባዊ መደረክ ላይ በሣል እና ዉጤታማ የመድረክ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከመድረኩ ተሣታፊዎች ለተነሱ ወቅታዊ የተለያዩ ጥያቄዎች መድረኩን ከሚመሩት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ግልፅ የሆነ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት የመድረኩ ውይይት ተጠናቋል። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!!! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሚያዚያ26/2018 ዓ/ም

18 አማራወች ተረ*ሽነው ከሸንኮራ አገዳ ጋር ታ*ቀጠሉ ! ጭፍ*ጨ*ፋው የተፈፀመው አዊ ዞን ጅግራ ውሃ የሚባል ኬላ ላይ ሲሆን በአማራ ሚሊሻና አድማ ብተና እንደሚጠበቅ ግልፅ ነው። በቀን 25/08/2
18 አማራወች ተረ*ሽነው ከሸንኮራ አገዳ ጋር ታ*ቀጠሉ ! ጭፍ*ጨ*ፋው የተፈፀመው አዊ ዞን ጅግራ ውሃ የሚባል ኬላ ላይ ሲሆን በአማራ ሚሊሻና አድማ ብተና እንደሚጠበቅ ግልፅ ነው። በቀን 25/08/2018 ዓ.ም ከባህር ዳር በመነሳት ወደ ጃዊ ሲሄድ የነበረ 18 ሰዎችን የጫነ ሀይሩፍ መኪና ጅግራ ውሃ ተብሎ ከሚጠራው የሚሊሻና አድማ ብተና ኬላ ላይ ከምሽቱ 11:30 አካባቢ የብልፅግናው አረመኔ ተላላኪ ሚሊሻና አድማ ብተና በፈፀመው ዘግናኝ ጥቃት 18ቱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ተረ*ሽነዉ ሸንኮር አገዳው ላይ ተቃ*ጥለዋል። የግድያው ምክንያት የተባለው መንገድ ላይ ለፋኖ መረጃ ሰጥታችኋል በሚል ውሃ በማይቋጥር ጥርጣሬ መሆኑ ይበልጥ ያማል። በእጥፍ ይመለሳል !

የመከላከያ ጋንታ መሪውን ጨምሮ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ....ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በተከታታይ ትኩረተ በመስጠት በየቀኑ የጠላትን ካምፕ ያለአንድ ጥይት ጩ
+5
የመከላከያ ጋንታ መሪውን ጨምሮ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ....ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በተከታታይ ትኩረተ በመስጠት በየቀኑ የጠላትን ካምፕ ያለአንድ ጥይት ጩኸት ወደ ፋኖ እየተቀላቀሉ ነው 1.አብዲ ጊዛ .....25ክ/ጦር ምክትል ጋንታ መሪ 54ኛ ክ/ጦር የገባ 2.ነገ ጋሻው ....ፓራ ኮማንዶ.54ክ/ጦር የገባ 3.ሀብታሙ ሙንየለት..74ክ/ጦር የገቡ ሲሆን 201ኛ ኮር 54ኛ እና 74ኛ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ለሰሞነኛ ጠማማ ክሶች ጫጫታ የሚሆን መቃወሚያ፤ መቶ አለቃ ዮሴፍ አስማረ ወርቁ እባላለው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል( አፋብን) ወሎ- ቤተአማራ ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ሁኜ እያገለገልኩ ያለው ወታደር ነኝ። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ለ13 አመታት በአጋዚ ኮማንዶ ክፋል በተዋጊነት ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ የተለያዩ አይነት ግዳጆችን ፈፅሜአለው። ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ደሞ በቁጥር 20 የሚሆኑ ኮማንዶዎችን በማስተባበር የክልሉን የፀጥታ መዋቅር ፣ ማደራጀት ፣ ማሰልጠን እና ማዘመን አለብን ብለን በማመን ከጀነራል አሳምነው ፅጌ ጋር በመነጋገር በጃሬ እና በቢኮሎ አባይ የመጀመሪያውን የአማራ ልዩ ሃይል አሰልጥኛለው። ሁለተኛው ዙር ደሞ በጎጃም ደብረ ማርቆስ አሰልጥነን አስመርቀናል። ከዛ በኋላ በሰኔ 15ት ግርግር ምክንያት ያለ ምንም ወንጀል ከትግል ጓደኞቼ ጋር ወደ እስር ቤት ተወረውረናል። ከወራት የእስር ቆይታ በኋላ ለተከታታይ ሶስት ዙር የአማራ ልዩ ሃይልን በብቃት አሰልጥነን አስመርቀናል። ከዛ በኋላ በነበሩ ሂደቶች ለተወሰኑ ወራት ለወታደራዊ ግዳጅ ጎንደር ጭልጋ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት ለጥምቀት ወደ ጎንደር ከተማ እንደሄድኩ "እንየ ታከለ የባህል ምሸት ቤት" ውስጥ የጎንደር የፀጥታ አመራሮች ተመቱ ተብሎ በግፍ ታስሬ አለው። ጀግናው አይበጌሬው የጎንደር ወጣት 9 ወር ሳያቋርጥ ከፖሊስ ጣቢያ እስከ ማረሚያ ቤት ድረስ ከጎኔ በመሆን በሀሳብ እና በገንዘብ ጭምር አለንልህ ብለው የምፈልገውን እያመጡልኝም ቆይቻለው። በእነሱው ጥረት በወርሀ መስከረም 2016 ዓ.ም ከእስር ቤት ወጥቼም ነበረ። ከእስር ቤት ከወጣው በኋላ ብአዴን የሹመት ማሰሪያ/መያዣ ሰጥተውኝ የነበረ ቢሆንም ታላቁ ህልሜ የነበረው የአማራን ህዝብ ማዳን ፤ ለአማራ ህዝብ መስዋዕትነት መክፈል እንጂ ለስልጣን እና ጥቅም መስገብገብ ስላልነበረ እኔ የአማራ ህዝብ አገልጋይ ባሪያው ሆኜ ነው የምኖር በማለት ከአንድ ወር በኋላ በወርሃ ጥቅምት 2016 ዓ.ም ወደ አማራ ፋኖ የተቀላልኩ አርበኛ ነኝ። ወደ አማራ ፋኖ ከተቀላቀልኩም በኋላ ከሰርዶ ኮማንዶ ልጅ እያሱ እስከ አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ በመሆን ድርጅቱ የሚሰጠኝን ማንኛውም አይነት ግዳጅ ተቀብየ እየሰራው የምገኝ በመርህና ደንብ የምመራ ፣ በንፁህ አማራነት የማምን የሻበል ዳንኤል አለሙ  ተተኪ ፣የአርበኛ ሞላ ድስየ ቃል አክባሪ፣የሜ/ጀ ውብአንተ አባተ ወንድም ፣ የቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋው መከታ ፣ የደራሲና ኮማንደር አሰግድ መኮነን ቅጥቅጥ ፣ የጀነራል አሳምነው ፅጌ አደራ ተቀባይ አርበኛ ነኝ። በትግሉ ውስጥ ለ20 አመታት ስቆይ "ለህዝብ ባሪያ ሆኖ መሞት መታደል ነው" የሚል የሁልጊዜም የማይቀር ፅኑ መርህ አለኝ። ከሰሞኑ ወደ ጎጃም ለድርጅታዊ የስራ ተልዕኮ በሄድንበት ወቅት ከድርጅታችን ላይ አንዳንድ "ጆፌ ጭልፊቶች" እየተንሳፈፉ እንዳለ እየተመለከትን እንገኛለን። የህልውና ትግላችንን እጅግ ሲበዛ አቆሽሸው ፣ እነሱም አንሰው እኛን ሊያሳንሱን የሚደክሙት ሞኞች በመሪዎችና እና በድርጅታችን ላይ መክረው በሚያሰማሯቸው መርዝ ጭነው በሚልኳቸው ቅጥረኛ አፈ ቀላጤዎች አደገኛ ትርክት በመንዛት የአማራ ፋኖን ለመከፋፈል እየሰሩ የሚገኙ "ጆፌዎች" መግቢያ ቀዳዳ ጠፍቷቸው በዛም በዚህም እየተሹለከለኩ ይገኛሉ። እንደሚታወቀው ለታላቁ የአማራ ህዝብ ልጆች የልዮ ኮማንዶ የስልጠና ጥሪ በማቅረብ ከወሎ እና ሸዋ የተሰባሰቡ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን በመያዝ በዛ ቅልጥ ባለው አደገኛ በረሃ በሚገኘው ወግዲ ወለቃ ወንዝ ውስጥ ለተከታታይ አምስት ወራት ሰልጣኞችን በማሰልጠን ፤ የአባይ ወንዝን አደገኛ በረሃ በማቋረጥ የአርበኞች መፍለቂያ ወደሆነችው ጎጃም ሸበል በረንታ እና እነማይ በመሻገር በወለቃ ወንዝ ለተከታታይ አምስት ወራት በልዩ ብቃት ስናሰለጥናቸው የነበሩ ተመራቂዎችን ከቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለጦር ጋር ለአንድ ወር በጋራ ስልጠና በመስጠት በእነማይ ለምጨን እና ዲማ አካባቢው የጠላት መድፍ ፣ ዙ-23 እና Bm -107 በእራሳችን ላይ እያፍጫጨ በደማቅ ሁኔታ ማስመረቃችን ይታወቃል። በዚህ የመጀመሪያ የአንድነት የኮማንዶ ምርቃት ወቅት ነበረ ፤ የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ወቅት ከነዛ መሐል የሆነው የአፋብን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ጠበቃ አስረስ ማረ ጋር የተገናኘነው። ከምርቃቱ በኋላ በነበሩ ሂደቶች በከፍተኛ የስራ ጫና ምክንያት ድጋሜ ለመገናኘት አልቻልንም። ድጋሜ እንገናኛለን ብየ ተስፋ አረጋለው። ከሰሞኑ የተከፈቱ የሳይቨር ሚዲያ የሴራ ፖለቲካ አራማጆች በዚህ የአማራ አንድነት ደማቸው የተንተከተከ ፣ ፊታቸው የገረጣ በአውሮፓና አካባቢው ተቀምጠው " መረጃ ከእኔ ውጪ" የሚሉ አስመሳይ የነጠላ ስር ቁማርተኞችና የትግሉ ካንሰሮች የትግሉን አከርካሪ ለመስበር በከፍተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ። በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ዘመቻ ከተከፈተባቸው ግለሰቦች መካከል ደሞ በአስቂኝ ሁኔታ የራሴን ስም ከዝርዝሩ ውስጥ አግንቼው አለው። በእርግጥ ባልፈሱበት ቂጥ..... እንደሚባለው ነው ፤ ባላደረኩት እና ባልዋልኩበት ነገር ምንም ደንታ የለኝም። መጥፎ አትስራ የአንተ ጊዜ ይመጣል ፤ ጊዜ የሰጠው ቅል .. እንደሚባለው ሆኖ እንጂ በተግባር መሬት ላይ ምንም አይነት ብልሽት እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል። የሃገሬ ፣ የደብሬ ታቦት ቅዱስ ጊዮርጊስ በሚያቀው " እኔ የማንም ፖለቲካ " ተሸካሚ አይደለውም። ነጠላውን እያደገደገ በቲክቶክ የሚቀመጥ coin ለማኝ ሁሉ የነቃው የበቃው ፖለቲካ ነኝ እያለ በህልም ያየውን እና መሬት ላይ የሌለውን ጉዳይ ዝምብሎ በትርክት ሴራ ይደረድረው ጀምሯል። "ንብ ከቆሻሻ ይልቅ ማር ጥቅም እንዳለው ለዝንብ ብታስረዳ  ምን ትርጉም አለው?? ምንም። በአንድ ወቅት የአፋብን ሊቀመንበር ዘመነ ካሴ በንግግሩ ላይ እንዲህ ሲል አደመጥኩት፦ ጥይት ያልፈራችሁ ሀሜት ወይም ወሬ ለምን ትፈራላችሁ? እኔ ባለፉት አስራ ምናምን ዓመታት የሰው ልጅ ከተፈጠረ በኋላ የታሙ ሀሜቶች በሙሉ ታምቻለዉ። ገና ወደፊት በሚፈጠሩ ሀሜቶች ሁሉ እታማለዉ። ዋናው ቁምነገር ለዓላማየ ታማኝ ነኝ ወይ? ለህዝቤስ ታማኝ ነኝ ወይ? የያዝሁት መንገድ ትክክል ነው ወይ? ቢያንስ ቢያንስ ፈጣሪየን ትንሽ እየፈራሁ ነው ወይ የሚለው ነው እንጂ አለም ተሰብስቦ መፈክር ይዞ ዘመነን  ለምን አያማም። ምክንያቱም ዓላማየ ትክክል እንደሆነ ስለማውቅ ሲል ይደመጣል። ወዳጄ ታዲያ ከዚህ በላይ መልስ ከየት እንዲመጣለህ ፈለክ? መሪየ አስረግጦ ነገረህ እኮ። በአጭሩ አላብዛባቹ በዚህ ደረጃ በማህበራዊ ሚዲያ የሚንሸራሸሩ ግጭት ጠማቂ ዘመቻዎች እኔን በፍፁም አይወክሉኝም። ድርጅታችንም በሩን ጥርቅም አርጎ ከዘጋ ወራቶች ተቆጥረዋል። የአፋብን ወሎ-ቤተአማራ ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ መቶ አለቃ @ዮሴፍ አስማረ ከትግል ሜዳ.....!!! ሚያዚያ 26/08/2018 ዓ.ም

ወደ ቃላይ ሾሊትና አካባቢው የምርጫ ካርድ ለመበተን የመጣ የጠላት ኃይል ክፉኛ መመታቱ ታወቀ።      ትናንት ሚያዝያ 25/2018 ዓ.ም  አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ንስር በለሳ ክ/ጦር ተክለ ሀይማኖቴ ብርጌድ መብረቅ ሻለቃ ጊንሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኒሊ ከተባለው ቦታ ላይ የቀጣዩን የጨበራ ምርጫ ካርድ ለመበተን በመጣ የጠላት ኃይል የተጠና ጠጥቃት ፈጽመዋል። በጥቃቱ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ከመደረጉ በላይ እቅዱን ሳያሳካ በኒሊ እስከ ጨውጫዊት በክንደ ፈርጣማዎቹ አፈሙዝ እየተገረፈ ወደመጣመበት እንዲመለስ ሆኗል።        <>  በአጠቃላይ በጥቃቱ         06 እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።          12 ቀላልና ከባድ ቁስለኛ የተደረገ ሲሆን በጓህላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።                      አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ       ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት አብነት ሞላ                ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ በሁሉም ወረዳዎች ሰፊ ህዝባዊ መድረክ ተካሄዴ። ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም በተደራጀ የፖለቲካ ሥራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል''ህልውናውምይረጋገጣል።በሚል መሪ ቃል ትናንት ሚያዚያ 25/2018 ዓ.ም በሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ተካሂዷል። አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በተቆጣጠረባቸው 1ኛ.በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እረርቲ ክላስተር፣ድሬ ቀበሌ ፣አዳማ ቀበሌ 2ኛ. አገረማሪያም ወረዳ ሲቻት ክላስተር 3ኛ. አሳግርት ወረዳ አትኳር ክላስተር 4ኛ. በከሰም ወረዳ ሰፊ ህዝባዊ መድረክ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩም በበርካታ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በመወያዬት ህዝቡ በህልውና ትግሉ ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትና ይህን አረመኔ አገዛዝ ለመገርሰስ በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ትግል ላይ ከድርጅቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። በመጨረሻም ምርጫችን ፋኖነት እንጅ የገዳያችንን ዕድሜ ሊያራዝም በሚችለው የማጭበርበር ምርጫ ላይ አንሳተፍም የሚሳተፍም ካለ ከማንኛውም ማህበራዊ ህይወት እንደ ህዝብ የምናገለው እንደሚሆን ይታወቅ በማለትና ሀሳባቸውን በመግለፅ መድረኩ መጠናቀቁን የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል አረጋግጧል። ክብር ለትግሉ ሰማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ

ባህር ዳር ከአረጋ ከበደ ቢሮ ፊት ለፊት የጣናን አየር እየኮመኮሙ በመካሄድ ላይ ያሉ የንቅናቄ መድረኮች በድምቀት እንደቀጠሉ ናቸው !! ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ
+2
ባህር ዳር ከአረጋ ከበደ ቢሮ ፊት ለፊት የጣናን አየር እየኮመኮሙ በመካሄድ ላይ ያሉ የንቅናቄ መድረኮች  በድምቀት  እንደቀጠሉ ናቸው !! ሚያዚያ 26/2018ዓ.ም በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሄራዊ ንቃት ይዳብራል በሚል መሪቃል ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 102ኛ ኮር ከሚያስተዳድራቸው ነፃ ቀጠናወች መካከል አንዱ በሆነው ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ  የመንግስት ሠራተኞች መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል ። ብልፅግና ፋኖን አፅድቸ ለምርጫ ተዘጋጅቻለሁ እያለ በሚለፋደድበት በዚህ ወቅት በቀን 25/08/2018ዓ.ም  ጣና ዳር ልጆሚ ላይ እንደህዝብ ከህልውና አደጋ ለመውጣት በሚያስችሉ ሰነዶች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል ። ▶️አዲስ ትውልድ ! ▶️አዲስ አስቸሳሰብ ! ▶️አዲስ ተስፋ ! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ደብረ ወርቅ _ሚያዝያ 25 / 2018 አ.ም.. ...የገብርየ ደም በጎጃሙ ቦንበኛ ዛሬም ደሙ ተመልሷል ። .....ሁለት የጠላትን ተሽከርካሪዎች ከደብረ ወረቅ ወደ መርጦ ለማርያም እየተጓዙ ያሉ አንድ
+2
ደብረ ወርቅ _ሚያዝያ 25 / 2018 አ.ም.. ...የገብርየ ደም በጎጃሙ ቦንበኛ ዛሬም ደሙ ተመልሷል ። .....ሁለት የጠላትን ተሽከርካሪዎች ከደብረ ወረቅ ወደ መርጦ ለማርያም እየተጓዙ ያሉ አንድ ዲሽቃ የጫነች ፓትሮል እና አንድ ኦራል መኪና ከነ ሙሉ ሀይሏ 'ሽፈሬ' በተባለች ንዑስ ከተማ ከቀኑ 6 :00 ሰዐት ላይ በቦንብ ጋይተዋል ። የ201'ኛ ኮር የ74'ኛ ክ/ጦር 4'ኛ ሬጅመንት ጦር አዛዥ ሻለቃ ፈንታሁን አለማየሁ ከሶስት( 3 ) ፋኖዎች ጋር አስደማሚ ጀብድ በመፈፀም የወንድሙን የገብርየን ደም መልሷል ። _ይቀጥላል____......

የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) በሳተላይት ቴሌቪዥን ምስረታ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ! በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚዲያ ተቋማት፣ የሕዝባችንን የህልውና ትግል፣ ሰብዓዊ መብትና ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማስከበር የአማራ ሚዲያ ካውንስልን (AMC) በማቋቋም ላለፉት ሁለት አመታት በጋራ ስንሰራ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ አሁን ደግሞ ሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ ለመመሥረት ባለፉት ሁለት ወራት በጠንካራ ዝግጅት ላይ መሆናችንን ስንገጽ በታላቅ ኩራት ነው።  ይህ ካውንስል ከሁለት ዓመት በፊት ሲመሠረት በተበታተነ መልኩ የሚደረጉ የሚዲያ ሥራዎችን ወደ አንድ ወጥና ጠንካራ የጋራ አጀንዳ (Unified Narrative) ለማምጣት እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎችንና ተቋማትን አቅም በማቀናጀት የሕዝብን ድምፅ ከፍ ለማድረግ ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየውን የመረጃ አፈና ለመስበር፣ በጨለማው ውስጥ ላለው የአማራ ሕዝብ እና ድምፅ ለሌላቸው ኢትዮጲያዊያን ድምፅ ለመሆን፣ በዲጂታልና በሳተላይት አማራጮች አማካኝነት እውነቱን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማድረስ የተቋቋመ የሙያና የትግል መድረክ ይሆናል።  ካውንስሉ ካቀዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች መካከል ቀዳሚው፣ የኢንተርኔት መቆራረጥና ሳንሱር የማያግደው፣ ኢንተርኔት በማይደርሰበትና አገዛዙ ኢንተርኔት ለዘጋበት ሕዝብና አካባቢ ለመድረስ፣ በመላው ኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ የሚሆን "የሕዝብ ድምፅ" የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ መመሥረት ነው። ይህ ጣቢያ የአባል ሚዲያዎችን ሰፊ የሕዝብ መሠረትና አቅም በማቀናጀት፣ የሕዝባችንን የታሪክ፣ የባህል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍላጎቶች የሚወክል ቀዳሚ ተቋም ይሆናል።  ይህ ታላቅ ተቋም በምስረታ ላይ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት አብረውን እንዲቆሙና እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፦ • ለሚዲያ ባለሙያዎችና ተቋማት፦ በካውንስሉ ውስጥ ያልታቀፋችሁ ሚዲያዎች የካውንስሉን አቅም በማጠናከርና የጋራ አጀንዳን በመገንባት ሂደት ውስጥ በሙያችሁ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።  • ⁠በአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እየተሳተፋችሁ ላላችሁ የህልውና ታጋዮች አብረን እንድንሰራ ጥሪ እናቀርባለን። • ለሲቪል ማህበረሰብና ሙያ ማህበራት፦ በዚህ አመራር ሂደት ውስጥ በመሳተፍ የጣቢያውን ገለልተኝነትና ሕዝባዊነት እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርባለን።  • ለባለሀብቶችና ለደጋፊዎች፦ ይህንን የመረጃ አፈና የሚሰብር የሳተላይት ፕሮጀክት ከሃሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ የታሪክ አሻራችሁን እንድታስቀምጡ ጥሪ እናቀርባለን።  • ለዲያስፖራው ማህበረሰብ፦ የትግሉ የጀርባ አጥንት በመሆን የካውንስሉን ዓለም አቀፍ ተደራሽነትና የፋይናንስ ዘላቂነት፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲኖረው በምትችሉት ሁሉ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪ እናቀርባለን። የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ለፍትሕና ለህልውና የሚደረገውን ትግል በጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር ታንጾ ለመዘገብና እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ለማድረስ ቆርጦ ተነስቷል። ይህ የመጀመሪያው እርምጃችን ሲሆን፣ በቀጣይ በዝርዝር የምናሳውቃቸው የሥራ እንቅስቃሴዎች  ታላቅ ተስፋ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠርም።  "የጋራ ድምፅ ለፍትሕና ለእውነት!"  የአማራ ሚዲያ ካውንስል (AMC) ሚያዚያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም