ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر3 678
مشترکین
+2624 ساعت
+3797 روز
+1 10930 روز
آرشیو پست ها
<< በህልውና ትግሉ አንድ እጁን ያጣ ቢሆንም፡ ስለ አማራ ሕዝብ ሲል ዛሬም በጦር ግምባር እየተዋደቀ የሚገኘው የጉናው የጦር ጠበብት ))
.....................................................
ይሄንን የአማራይቱ ልጅ የጉና እንቁ ጀግና ተዋወቁት!👇
የልጅ አዋቂው አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ይባላል። የዘረ ውባንተ ፍሬ ነው።
በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከትዱር ቤቴ ካለ ድፍን አራት ዓመታትን አስቆጥሯል። በሰሜኑ ጦርነት ከጋሳኝ እስከ ጋሸና በርካታ ምሽጎችን የደረመሰ ተወርዋሪ ጀግና ነው።
አልሞ ተኳሽ ባለ ስናይፐሩ የት አለ ከተባለ እሱ ይምጣ ይባላል። የስናይፐሩ ጠበብት የኢንፎርቲው ጌታ ነው።
የአይኖቹ እይታቸዉ እንደ ንስር ነዉ ወኔው እና ጀግንነቱ እንደ አንበሳ ነው። ምላጭ የሚስብባቸዉ ጣቶቹ ለጠላት የተፈቀዱ ነዉ የሚመስሉት ፣ አይኖቹ እንደ አጉሊ መነፀር አቅርበዉ እና አርቀዉ እንዲያሳዩ ለሱ ብቻ ተፈቅደዋል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ የገደለውን ጠላት ለማወቅ በካዝናው ስንት የስናይፐር ጥይት ይዞ ነበር ብሎ መጠዬቅ ብቻ በቂ ነው።
ጦሩን በወኔ በማነቃቃት በጉና ሰማይ ስር ለሚገኘው የጦር አበጋዝ ሁሉ የወኔ ስንቅ ነው።
የቅንጦት ኑሮ ያላሸነፈዉ ጀግንነት ፣ በሀብትና በፀጋ ያልተበረዘ እና ያልደበዘዘ ወኔ ዛሬም በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል።
የረገፉ ወርቅ እጆች ከትግሉ አላሸሹትም ዛሬም በጦር ሜዳ ከጠላት ጋር እየተዋደቀ ይገኛል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ!!
በአሁኑ ሰአት በአፋብኃ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ውስጥ ቁልፍ እና ወሳኝ ከሆኑ አርበኞች አንዱ አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ነዉ። በትግሉ ሜዳ አሁን ድረስ እየተዋደቀ ያለ አርበኛ ጭምር ነዉ።
ከብሬን እስከ ስናይፐር ፣ እንዲሁም ዲሽቃ አበጥሮ የሚተኩስ እና የክላሹ መሃንዲሱ ዛሬም በአንድ እጁ ጠላትን አበጥሮ የሚመታ ባለንስር አይኑ ለመጣ ለሄደዉ ጠላት ሁሉ የዕግር ዕሳት ሆኖ ቀጥሏል። በዕርግጥ ብዙዋቹ እንደ ታድሎ አዳምጤ አካላዊ ጉዳት ያስተናገዱ ቢኖሩም እሱ ግን አካላዊ ጉዳቱ ከትግሉ አላሸሸውም። በአንድ እጁ ተኩሶ ጠላትን የሚመታ እና የሚያስጨንቀው አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ብቻ እና ብቻ ነው።.
በነገራችን ላይ በአርበኛ ታድሎ አዳምጤ የትዉልድ ቀዬ እስቴ መካነየሱስ የተወለደዉ እና የአርበኝነት ምልክት የነበረዉ አርበኛ ሙላቴ በአንድ እጁ በመታገል እና ተኩሶ በመምታት ወደር የማይገኝለት ጀግና ነበር።
ስአርበኛ ሙላቴ የዚህ ትግል ችቦ ለኳሽ አርበኛ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ እሱን የሚመስል ባለ አንድ እጅ ጉራማይሌ ተኳሽ ተክቶ ሂዷል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ መተኩስ ብቻ ሳይሆን የሰራዊቱ የወኔ ስንቅ ፣ የሞራል ምልዕክት እና የፅናት ተምሳሌት ጭምር ነዉ።
ውድ ታላቁ የአማራ ህዝብ ሆይ ይህ አርበኛ ከእነ ፀዳሉ ደሴ ፣ ቆራጡ አንዳርጌ ጋር አብሮ የተገለ ታጋይ ነዉ።
ታዲያ ሁለቱ ባንዳዎች ህዝብን ዘርፈዉ የዘረፉትን ተቀምጠዉ ለመብላት ዕጅ ሲሰጡ አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ግን በአንድ እጁ እየተዋጋ ቀጥሏል። ፅናትን ከአርበኛ ታድሎ ያልተማሩ ሌቦች ዛሬ ላይ የአማራ ህዝብ መሳቂያ እና መሳለቂያ ሲሆኑ ባለአንድ እጁ ተኳሽ ግን እኔ ዕጅ ከምሰጥ ብሞት ይሻለኛል በማለት ከጠላት ጋር ተናንቆ ይገኛል።
የውብአንተ ልጅ ፣ የገብርየ ልጅ ፣ የቴወድሮስ ትንፋሽ መሆን በዚህ ልክ ነው።
ጎንደሬነት የሚለካዉ በእነዚህ ጀግና አርበኞች እንጂ በባንዳዎች አይደለም።
በአንድ እጁ ከሚታገለዉ አርበኛ በላይ የሚከበርም ሆነ የሚወደድ አርበኛ የለም። ሊኖርም አይችልም።
አማራነት መገፋት መሆኑን የሚገልፅ አርበኝነት ከዚህ በላይ የለም። በአንድ እጅ መታገል አማራ ምን አይነት የጭቆና ቀንበር ላይ እንዳለ የሚያሳይ ግልፅ ነገር የለም።
"ጠላት ሲመጣ ገዳይ ወንበዴ፣
ከፊት ይቀድማል ታድሎ አዳምጤ" የተባለለትን ጀግና!✊
ጀግናው ድል ለአንተ እና ለጓዶችህ!🙏
በአውደ ውጊያ የተሸነፈው አገዛዝ በንፁሃን ላይ የድሮን ቦንቦችን በማዝነብ የጦር ወንጀል በመፈፀም ላይ ይገኛል።
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የበላይ ዘለቀ እዝ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በፈፀሙት ልዩ ተጋድሎ ከደቡብ እና ማእከላዊ ጎንደር በርካታ ወረዳወች የተጠራረገው የአገዛዙ ሰራዊት መሬት ይዞ መዋጋት ሲሳነው እና ከፍተኛ መፍረክረክ ሲደስርስበት ታይቷል።
ይሁን እንጅ ይህ የሽብር አገዛዝ ሆን ተብሎ በታቀደ ሁኔታ ህዝብን በመጨፍጨፍ በሽብር መንገድ ወታደራዊ ሽንፈቱን ለመቀልበስ አስቦ ብዙ ንፁህን ላይ በተለይም የደብረ-ታቦር ከተማ ህዝብ እና የህዝብ ተቋማት ላይ ተከታታይ የድሮን ድብደባወችን አድርጓል።
ትላንት የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ዒላማ የተደረገ የወገን ኃይል በሌለበት በቀቢፀ ተስፋነት ባደረጋቸው የድሮን ጥቃት እና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያወችን በመጠቀም ሲቪሊያንን ጨፍጭፏል።
በዚህም ደብረ-ታቦር ከተማ ላይ ብቻ ከግማሽ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ 16 ጊዜ በላይስትራቴጅክ ድሮኖችን በመጠቀም የአረመኔነት ባህሪውን አሳይቷል።
በዚህ ጥቃት:-
1.የፈርጣ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ
2.የገብርየ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ
3.የዞን ጤና መምሪያ
4.የዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ፋይናንስ ቢሮ
5.የቴዎድሮስ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ማህበራዊ ተቋማትን እና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት አውድሟል። በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እና በየቤታቸው የነበሩ የከተማ ነዋሪወችንም በድሮን ጨፍጭፏል።
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትን ጨምሮ አገዛዙ በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ጥቃት የሚያሳስባቸው ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተቢዉን ሁሉ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
አገዛዙ መሰል የጥፋት ተግባራትን ማቆም የሚችለው ከስልጣኑ ሲወገድ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያደርገውን ፀረ-አገዛዝ ተጋድሎ አጠናክሮ ይቀጥላል።
ነፃነት በነፃ አይገኝም፤ ድል በጽናት እንጂ በለቅሶ አይመጣም!"
ለተገፋኸውና ዛሬ በጠላት የግፍ አገዛዝ ሥር ላለኸው መላው አማራ ህዝብ ፤ ወንድሞቼና እህቶቼ! ዛሬ በመላው አማራ ግንባሮች የምናየው ድርጊት አንድ ትልቅ እውነትን ያረጋግጣል። ያገሬ ሰው "ሊታረድ የቀረበ በሬ ይበልጥ ይፈራገጣል" ይላል። የብልፅግና ሰራዊት በፋኖ ልጆችህ ክንድ ፊት ለፊት መጋጠም አቅቶት ጀርባው ሲሰበር፣ ዛሬ ፊቱን ወደ አንተ አዙሮ ገበያ በማገድ፣ ስንቅ በመከልከልና መንገድ በመዝጋት ይፎክራል።
ይህ የጥንካሬ ምልክት ሳይሆን፣ መሸነፉን አምኖ በሕዝብ ሆድ ላይ ጦርነት የከፈተ የቁም ሙት ድንፋታ ነው። ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል" መንግሥት ነኝ የሚለው ኃይል ዛሬ በመላው አማራ እንደ ሽፍታ የገበሬውን ከብት የሚነዳ፣ እህሉን የሚዘርፍና የሕፃናትን መድኃኒት የሚከለክል "የመንገድ አዳኝ" ሆኗል።
አገሩንና ሕዝቡን የሚጠብቅ ሰራዊት ሳይሆን፣ የገበሬውን ድስት ሰላይ ሆኗል። ይህ የሚያሳየው ጠላት የሎጂስቲክስና የሞራል ስብራት እንደገጠመው ነው። ሰራዊቱ ስንቅ አጥቶ በየደጁ የዘረፋ ስምሪት ከጀመረ፣ ውድቀቱ የሰዓታት ጉዳይ መሆኑን እወቁት። ጠላት ዛሬ ቤቱን መዝጋት ያቃተው፣ ያንተን ገበያና መንገድ ለመዝጋት መሞከሩ የውርደት ውርደት ነው።
አማራ በጠላት ዛቻ አይንበረከክም !
በተለያዩ ግንባሮች ገበያውን በመዝጋትና የከተማና የገጠር ትስስርን በማቋረጥ ሊያስርቡህ ይሞክራሉ። ነገር ግን የጥቁር አንበሳ ዘር የሆነው አማራ ለሆዱ ብሎ ለጠላት አይንበረከክም። ሕዝባችን ሆይ! ነፃነት በነፃ አይገኝም። ዛሬ የሚደርስብህ የግፍ እስራትና የንብረት ዘረፋ የነፃነትህ ዋጋ ነው። አማራጮችን ተጠቀም፤ ባለህ ተካፈል፤ በጎጥህና በጎረቤትህ ተረዳዳ።
ጠላት "በላህም አልበላህም መቃብርህ መቆፈሩ አይቀርም" የሚለውን የፋኖን ክንድ ስለፈራ፣ ያንተን እንጀራ ለመቀማት መሞከሩ መጨረሻው መቃረቡን ያሳያል።
፫. ለሰራዊቱ የቀረበ ማስጠንቀቂያ፦
የሕዝብን እህል የምትዘርፉና እናቶችን የምታስለቅሱ የብልፅግና ቅጥረኞች ሆይ! "የሰው ወርቅ አያደምቅ" እንደሚባለው፣ የዘረፋችሁት ከብትና እህል መጨረሻችሁን ያፋጥነዋል። ዛሬ በደራ ሕዝብ ላይ የምታሳዩት ትዕቢት ነገ በቁም ለፍርድ ይዳርጋችኋል።
ይህ የጨለማው መጨረሻ ነው። "የሞት ሞቱን" የሚፈራገጠው ጠላት ድንፋታው ቢበዛም፣ እኛ ፋኖዎችህ ደግሞ ከጎንህ ነን። ሰለልኩላም ሆነች ሌሎች የደራ አካላት የአንድ አካል ብልቶች ናቸው። ጥቃቱ የጋራ ነው፤ ድሉም የጋራ ይሆናል። በአንድነት እንጽና፣ በአንድነት እንመካከር። ሸለቆውም፣ ሜዳውም፣ ተራራውም ለጠላት ሲኦል፣ ለእኛ ግን የድል አውድማ ይሆናል!
ድል ለአማራ ሕዝብ!
የአፋብን ም/ል ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ራስ ስለሺ አበረ
ጠላት ለግጃጅ ይዟቸው የነበሩ የሲቪል መኪኖች ጥሎ ፈረጠጠ።
ከኪንፋዝ በገላ ወረዳ ወደ አምባ ጊወርጊስ ከተማ በትናንት ዕለት የካቲት 4/2018 ዓ/ም ከሰዓት እየተንቀሳቀሰ የነበረ የአገዛዙ ቅልብ ሀይል በወገራ ወረዳ ልዩ ስሙ ሳንቃ ጥቅም ከተባሉ ቦታ በጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ቴውድሮስ ብርጌድ አባላት በደፈጣ እርምጃ ተወሰደበት።
የቴውድሮስ ብርጌድ አባላት በወሰዱት ርምጃ በርካታ የመከላከያ አባላት ሙትና ቁስለኛ የሆኑ ሲሆን ቀሪው እግሬ አውጭኝ እየፈረጠጠ ወደ ከተማው በመግባት ህይወቱን ሲያተርፍ ከሁለት ሳምንት በላይ ለግጃጅ ተይዘው የነበሩ አራት የጭነት መኪኖች በጀግኖቻችን በማስለቀቅ ለባለ ሀብቶች እንዲመለሱ ተደርጓል ።
ህልውናችንን በተባበረ ክንዳችን !!!
አርበኛ ታድሎ ደሴ (ካስትሮ ) የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር ህ/ግን /ኃላፊ
+1
🔸🔸 መብረቅ ክ/ጦር በአርኖ ጋርኖው ውጊያ የጠላትን ድሽቃ ከጥቅም ውጭ አደረገ።
በትላንትናው እለት የካቲት 04/2018 ዓ.ም አፋብን በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር መብረቅ ክ/ጦር አርኖ ጋርኖ ከተማ ላይ ሲቀጠቅጡት ውለዋል።
🔸በአፋብን በላይ ዘለቀ እዝና አፋብን ጎንደር ጠቅላይ እዝ በጥምረት ደብረታቦር ላይ የደረሰበትን ከፍተኛ ምት መቋቋም ያቃተው ጠላት እስትፋሱ እንዳይቋረጥ ለማድረግ ድጋፍ ሰጭ ኃይል ከአዘዞ ያንቀሳቀሰ ሲሆን ይህ ኃይል አልፎ እንዳይሄዮ በመብረቆቹ ፋኖዎች እንፍራዝ አርኖ ጋርኖ ከተማ ላይ ያላሰበው ጥቃት ተከፍቶበት ውሏል።
🔸 ውጊያው ለሰዓታት የቆየ ሲሆን የጠላት ድሽቃም በመብረቁ አልሞ ተኳሽ ከጥቅም ውጭ እንዲሆን ተደርጓል።
🔸 ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።
🔸 ቁስለኛው በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ለህክምና እንደገቡም ማወቅ ተችሏል። አቅዶት የተነሳበትን ድጋፍ የመስጠት እቅድ ሳያሳካ መቅረቱም ታውቋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
የካቲት 05/2018 ዓ.ም
፭) የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌወችን እና መርሆወችን እንዲሁም ዓለም አቀፍ የጦር ህግጋትን የተከተለ አሰራር ይተገበራል።
፮) ይህንን አዋጅ ጥሶ የተገኘ ማንኛውም የድርጅቱ አመራር እና አባል ወይም ሌላ አካል ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል።
ረ) የሕዝቡ፣ የሀገር ሽማግሌወች እና የኃይማኖት አባቶች ሚና
በየቀጠናው ያለው ህዝብ፣ የሀገር ሽማግሌወች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና ሌሎች ተሰሚነት ያላቸው ግለሰቦች በጠላት የፀጥታ እና የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ያሉ ግለሰቦች በዚህ አዋጅ መሰረት አፈሙዛቸውን ወደ ዋናው ጠላት እንዲያዞሩ ካልሆነም ሰላማዊ ኑሯቸውን እንዲኖሩ እና የአማራው ኃይል ፍፁም ህብረት እንዲኖር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቃል።
በመጨረሻም የአማራ ልጆች በጋራ ተባብረን ህዝባችንን ሊያጠፋ የተነሳውን ጠላት እናስወግድ ዘንድ አንድነት እና ህብረት ያስፈልገናል እና ወደ አማራ የምንተኩሰው ጥይት እንዳይኖር እና አንድ ጠላት ላይ ብቻ አነጣጥረን እናሸንፍ ዘንድ ኑ እንላለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
Amhara Fano National Movement:
ኑ ጠላትን በጋራ ታግለን የአማራን ህዝብ ሕልውና እናረጋግጥ!
የካቲት 05 ቀን 2018 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተላለፈ የምህረት አዋጅ
ሀ) መግቢያ:
አረመኔው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ ለመጣል የጀመረውን ጦርነት ለማሳካት ይችል ዘንድ በርካታ አረመኔያዊ ተግባራትን ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል።
የአማራን ህዝብ ያለ ልዩነት ለመፍጀት አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ እየተጠቀመ ያለው አገዛዝ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጂኦ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን በማገልገል በፈጠረው የማውደም አቅም ተማምኖ በከፈተው ጦርነት ራሱ እየተለበለበበት ይገኛል።
የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ከሚጠቀምባቸው ስልቶች መካከል ነባሩን የብአዴን መዋቅር በመጠቀም ባሰባሰበው የምሊሻ እና የአድማ ብተና ኃይል ከፋኖ ጋር እንዲዋጋ እና ህዝባችን በሁለት ጎራ ተሰልፎ እንዲጠፋፋ የሞከረበት መንገድ አንደኛው ነው።
በአንድ ህዝብ መካከል እና በኢትዮጵያዊያን መካከል እንዲሁም ቀጠናዊ ጦርነቶችን በማስነሳት ለአፍሪካ ቀንድ የቀውስ ዘበኛ የሆነውን አገዛዝ በወንድማማችነት እና በጥበብ በማስወገድ የጋራ መንግስት መመስረት እንደሚገባን በተደጋጋሚ ጥሪወች ስናስተላልፍ የቆዬን መሆኑ ይታወቃል።
በተለይም ከሰሞኑ ደግሞ ጠላት በአንድ በኩል የህዝብ መገናኛ መስመሮችን በመዝጋት ንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እያደረገ በሌላ በኩል ደግሞ ብሔራዊ አጀንዳ ያለው እና ለሀገር ብሔራዊ ተልዕኮ የተሰለፈ በመምሰል የሚያደርገውን የማደናገሪያ ስልት በንቃት በመከታተል የፋኖ ሰራዊት በወሰዳቸው እርምጃወች ወራሪው የብልፅግና ኃይል ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ገብቷል።
የድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መወለድ ያስገኘው የአንድነት መንፈስ ለተገኙ ወታደራዊ ድሎች ቁልፍ ሚና ተጫውቷል። የድላችን ምስጢር ያለው አንድነታችን ላይ መሆኑም በተግባር ተረጋግጧል። ድርጅታዊ አንድነታችንን በጠበቀ መልኩ ከኢትዮጵያዊያን እና ከቀጠናው ኃይሎች ጋር የሚደረግ ትብብር አገዛዙን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ ወሳኝ ሂደት መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝባዊ ዓላማችንን የተጋራን ጋር በመርህ የምናደርገው ትብብር እና አንድነት የአረመኔውን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር ትልቅ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው።
ይህንን ተከትሎ ባቀረብነው ወገናዊ ጥሪ በርካታ የአገዛዙ አገልጋይ የነበረ ምሊሻ፣ አድማ ብተና እና የመከላከያ ኃይል የወገንን ኃይል እየተቀላቀለ ይገኛል።
ስለሆነም ዛሬም አገዛዙን በማገልገል ላይ ለምትገኙ የምሊሻ፣ የአድማ ብተና፣ የመደበኛ ፖሊስ፣ መከላከያ እና በሌሎች የአገዛዙ ታጣቂ አደረጃጀቶች ውስጥ ላላችሁ ተመሳሳይ ጥሪወችን እናስተላልፋለን።
ይህንን ጥሪ ያስተላለፈው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር በጉዳዩ ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ጥሪዉን በመቀበል ወገናቸውን ለመካስ ለሚፈልጉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እና የካድሬ መዋቅር የምህረት አዋጅ አውጇል።
ለ) የምህረት አዋጁ የተላለፈላቸው የአገዛዙ መዋቅር አካላት:-
፩) በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና አመራር አባላት
፪) ምሊሻ፣ ሰላም አስከባሪ እና በሌላም ስያሜ ብልፅግና ያደራጃቸው ታጣቂወች
፫) የክልል አድማ ብተና እና መደበኛ ፖሊስ አባላት
፬) በሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም በየቀጠናው የተሰማሩ እግረኞች እና የአገዛዙ መኮንኖች
ሐ) የምህረት አዋጁን ማውጣት ያስፈለገበት ምክንያት
ሶስት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ጊዜ በቀረው የጦርነት ሂደት በግልፅ መገንዘብ እንደሚቻለው የብልፅግና መዋቅር በአማራ ህዝብ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ድቀት ላይ ስልጣኑን ከማራዘም ያለፈ ለአማራ ህዝብ የሚጠቅም አንድም አጀንዳ የሌለው በመሆኑ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በተለያዬ ጎራ የተሰለፍን የአማራ ልጆችም እንደ የአንድ እናት ልጆች በመቀናጀት የህዝባችንን ህልዉና ማስጠበቅ ከእኛ የሚጠበቅ ተግባር ነው። በመሆኑም:-
፩) ለአማራ ህዝብ ሁለንተናዊ መብት እና ነፃነት እንጅ ለአብይ አህመድ ወንበር መፅናት የሚወድቅ የአማራ ወጣት መኖር ስለሌለበት፤
፪) ህዝባችንን በጅምላ ለሚጨፈጭፍ አገዛዝ በማገልገል የዘቀጠ ታሪክ ውስጥ ራስን ከማግኘት ይልቅ ለነፃነቱ የሚዋደቅን ኃይል በመቀላቀል ደማቅ ታሪክ መፃፍ ታሪክ የጣለብን ግዴታ በመሆኑ፤
፫) ህዝብን ታግሎ ያሸነፈ አገዛዝ እንደሌለው ሁሉ አብይ አህመድም የአማራን ህዝብ ማሸነፍ ስለማይችል እና በተሸናፊነት ለሚያጠናቅቀው ብልፅግና በመላላክ እና በራስ ወገን ላይ በመተኮስ የታሪክ፣ የህሊና እና የፍትህ ተጠያቂነትን ከማስተናገድ ለመዳን ሲባል፤
፬) አገዛዙን በጋራ ታግለን በማሸነፍ ለህዝባችን ሰላም ማምጣት የትውልዱ ግዴታ በመሆኑ፤
፭) እንዲሁም የምንታገለው ለአማራ ህዝብ ህልውናና መዳን እንደመሆኑ መጠን የፋኖ ትግልም የአማራ ህዝብ ትግል ስለሆነ በሁሉም ጎራ ላሉ አማራዊ ወንድሞች ጥሪ ማድረግ እና ማታገል የድርጅታችን ተልዕኮ በመሆኑ፤
ይህንን የምህረት አዋጅ በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ስራ አመራር ውሳኔ መሰረት ለህዝብ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
መ) የምህረት አዋጁ አተገባበር
፩) የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ካላይ በተራ ቁጥር "ለ" ስር የተዘረዘሩት የምሊሻ፣ አድማ ብተና፣ መከላከያ እና ሌሎች የታጠቁ የብልፅግና ኃይሎች እንዲሁም በየደረጃው ያሉ አመራሮች በየአካባቢያቸው ላለው የድርጅታችን መዋቅር እና ለዚህ ጉዳይ በተቋቋመው ግዜያዊ ግብረ ኃይል በአካል ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ።
፪) ምህረት ጠይቀው ወገናቸውን ለመካስ የሚመጡ ግለሰቦች የአካል ደህንነት ዋስትና ይሰጣቸዋል። በተዘጋጀላቸው ማረፊያ የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ይደረጋል።
፫) ለትግል አገልግሎት ከሚዉል የጦር መሳሪያን ጨምሮ ማንኛውም የምህረት ጠያቂወች ንብረት በባለቤቶች እጅ ይቆያል።
፬) ምህረት የተደረገላቸው ግለሰቦች ድርጅቱ ባዘጋጀው ፎርም መሠረት ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሊሰሩ ካልተቻለም ከጠላት ወገን ላይሰለፉ ቃለ-መሃላ ይፈፅማሉ።
፭) አቅሙ እና ፍላጎቱ ያላቸው የምህረት ተጠቃሚወች የወገንን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መዋቅር ተቀላቅለው ለህልዉና ተጋድሎው የበኩላቸውን ድርሻ ይወጡ ዘንድ በሌላ ማናቸውም ለህዝብ ጠቃሚ በሚሆኑ ተልዕኮወች ላይ ይሰማሩ ዘንድ ድርጅቱ ሁኔታወችን ያመቻቻል።
፮) ይህ የምህረት አዋጅ ከዛሬ የካቲት 04 ቀ 2018 ዓ.ም ላሉት ተከታታይ 15(አስራ አምስት ቀናት) ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል።
ሠ) የምህረት አዋጁን በማስፈፀም የሰራዊታችን እና የድርጅታችን አመራር ግዴታ
፩) የምህረት አዋጁን አፈፃፀም ለመከታተል በማዕከል የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመመሪያዉን አተገባበር ይከታተላል፤ መረጃወችን ይሰጣል፤ መፍትሔ ያስቀምጣል።
፪) የድርጅቱ መዋቅር አመራር እና ሰራዊቱ ለምህረት ጠያቂወቹ የአካል ዋስትና መስጠትን ጨምሮ በእንክብካቤ በማስተናገድ በፍፁም ጨዋነት አዋጁን ይተገብራል።
፫)በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ወዲያውኑ ለግብረኃይይሉ ያሳውቃል፣ የተሰጠዉን የመፍትሔ አቅጣጫ ይተገብራል።
፬ በግል ቂም ቁርሾ ወይም በሌላ ግላዊ እና ቡድናዊ ፍላጎቶች ምክንያት ከዚህ አዋጅ በተቃረነ መንገድ በማንኛውም ምህረት ጠያቂ ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ ወይም ንብረት መቀማት ፍፁም የተከለከለ ተግባር ነው።
109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር በርካታ ጠላት በመደምሰስ ታላቅ ጀብድ ሰራ
አፍብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር የተቀበለውን ግዳጂ ለማክሸፍ ጠላት ለብዙ ቀናት ያደረገውን ከበባ ከአጋር ሀይሎች ጋር በመሆን የጠላትን እቅድ አከክሺፈውታል፡፡ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት በማድረስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ጀግናውና አይበገሬው 77ኛ ክ/ጦር ከአጋር ሀይሎች ጋር በመሆን ረጅም ጉዞ በመጓዝ ወደ ጠላት ምሽግ ሰርገው በመግባት የጥይት ናዳ አውርደውበታል በዚህም አስራ አምስት(15)ሙት ሲሆን ከሀያ(20) በላይ ቁስለኛ ሆኗል፡፡
በዚህ የተናደደው የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት የመጨረሻው አማራጩን ኔትወረክ በመዝጋት አምልጧል፡፡
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !
አፋብን| ቴወድሮስ ዕዝ 77ተኛ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
የካቲት 05/6/2018 ዓ.ም
በኦሮሚያ ክልል በተካሄደ የአመራሮች ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚከተለውን ሀሳብ አጋርተው ነበር፦
ከዓመታት በፊት ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር በመሆን ሕወሓትን መትተን ከሰበርን በኋላ፣የአማራ ልዩ ኃይሉ እንዲፈርስ አድርገናል። አሁንም በአማራ ክልል እየሰለጠነ ያለውን የአድማ ብተና ኃይልና ሚሊሻ፣ ፋኖን ከወጋን በኋላ ወይ ማፍረስ ወይም በሴራ መምታት ይኖርብናል። ያ ካልሆነ ነገ አፈሙዙን ወደ እኛ ሊያዞር ስለሚችል 'Plan B' ሊኖረን ይገባል ።
ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነጥቦች ለቆሙለት ዓላማ ውድ መስዋዕትነት ለከፈለው ያላዘነው የአማራ ልዩ ኃይል ፣ ዛሬ ላለው የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አባላት ቅንጣት ታክል ርህራሄ አይኖራቸውም። እንዲሁም የአማራን ህዝብ እርስ በእርስ እንዲባላ በማድርግ ሰፊ ሰራ መስራት አለብን የሚል ጠጠር ያለ ኃሳብ አንስቷል
አሁን ላይ የአማራ ፋኖ እንቅስቃሴ የክልሉ የጸጥታ መዋቅር እንደ ስጋት እንጂ እንደ አጋር እንደማይታይ ነው።በመጨረሻም ጊዜው ሳይረፍድ በአድማ ብተና እና በሚሊሻ ውስጥ የምትገኙ ወንድሞችና አባቶች፣ ሁኔታዎችን በንቃት እንድትከታተሉ ይገባል። እያንዳንዱ አማራ በተገኘው አጋጣሚ እነዚህ የጸጥታ አካላት ከአረመኔው አብይ አህመድ መዋቅር እንዲወጡና ከህዝባቸው (ከፋኖ) ጎን እንዲቆሙ ሊመክራቸው ይገባል።
አስቸኳይ መረጃ
በርካታ መኪና
ከመኮድ የተነሳ ሀይል አሁን ወደ ጎንደር እየወጣ ነው ደፈጣ አዛምቱ
አሁን ህወሓት ሆነች ሻእቢያ የሚሸዉደዉ የሚያባብለዉ አማራ የለም። አሁን 1966 ወይም 1983 አሊያም 1997
ወይም 2010 የሿሿ ዘበን አዶለም።
አሁን 80 ሚሊዮን አማራ ዉለታ በሰራላት ሀገር የተገፋበት ትርክቶቹን የገመገመበት፣ ጠላቶቹን የለየበት፣ ክፉና ደጉን ያወቀበት ጥቃት መካች ልጅቹ ከአፍ እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቁበት ዘመን ላይ ነዉ።
ቴግባባን ኧደል? ዠለስካ፥ እንዴዣ ነገር ኖ።
አማራ ገስግስ ወደፊት!
የአፋብን፣ ቴዲ ዕዝ፣ 102ኛው ኮር ውሎ፦
ቀን፦ የካቲት 04/2018 ዓ.ም
በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) በምዕራብ አማራ ቀጠና ስር የሚንቀሳቀሰው የቴዎድሮስ ዕዝ፣ 102ኛው ኮር ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።
የኮሩ ስብጥርና የክዋኔ ቀጠና
102ኛው ኮር የሚሸፍናቸው፦
• ወረዳዎች፦ ቋሪት፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ይልማና ዴንሳ (አዴት)፣ ሜጫ( መርሐዊ) እና ባህርዳር ዙሪያ።
• የተካተቱ ብርጌዶች፦ የገረመው ወንዳውክ (የቋሪቱ) ፣ የአርበኛ ዮሐንስ አለማየሁ(የጎንጅ ቆለላ)፣ የሻለቃ አንሙት ያዛቸው( ይልማና ዴንሳ)፣ የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ( መርሐዊ)፣ የጣናው መብረቅ እና የባህርዳር ብርጌድ (ባህርዳርና ዙሪያው)።
የተመዘገቡ ስኬቶች
ኮሩ የአደረጃጀት ስራውን አጠናቆ ለከፍተኛ መልሶ ማጥቃት ራሱን እያዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ተከታታይ ጥቃቶችን በመሰንዘር የሚከተሉትን ቀጠናዎች ከጠላት ነፃ አድርጓል፦
1. ከአዴት ቀጠና (11ኛ ክፍለ ጦር)፦ ዴንሳ ባታን።
2. ከባህርዳር ቀጠና (22ኛ ክፍለ ጦር)፦ ደና ማርያም፣ ጭስ አባይ እና ጎንባትን።
የጠላት ወቅታዊ ሁኔታ፦
በኮሩ ወታደራዊ የበላይነት የተደናገጠው የገዥው ስርዓት ሰራዊት የሚከተሉት ምልክቶች እየታዩበት ይገኛል፦
• መፈራረስና መሸሽ፦ በየካምፑ ያሉ የጠላት ኃይሎች ከፍተኛ መዋከብ ላይ ሲሆኑ፣ በባንክ ያሉ ጥሬ ገንዘቦችን በመሸከፍና ጓዛቸውን በመኪና በመጫን ለመሸሽ እየተዘጋጁ መሆናቸው ተረጋግጧል።
• ክህደትና ተሳትፎ፦ የሰራዊቱን መዳከም የተረዱ በርካታ የአድማ ብተና እና የሚሊሻ አባላት ስርዓቱን በመክዳት ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
• ተጨማሪ ትጥቅ፦ በዛሬው ዕለት ብቻ በርካታ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የታጠቁ ኃይሎች የትግሉ አካል ለመሆን 102ኛውን ኮር ተቀላቅለዋል።
መረጃው፦ የወንድም ታደሰ ነው።
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር። ዝርዝሩን ወደኋላ አቆይተን መሪያቸውን እንዴት በስስት እንደሚያዩት ይገርማል። ስሜቱ,,,,,,አንድ ህጻን ልጅ ከአባቱ ትክሻ ላይ ተቀምጦ መውደቅ እንደማይችል፣ለመውደቅ ቢሞክርም አባቱ እንደሚያተርፈው አይነት ነው። በአባቶቻችን ትክሻ ላይ ስንሆን የሚሰማን በራስመተማመን ልዩ ነው። እነዚህ ጀግኖችም እንደዛ ናቸው።
የአፋብን ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በጎንደር አማራ ቀጠና ኮማንድ ካሉ አመራሮች እና ነበልባል ተዋጊዎች ጋር 💪💪
ያልተነገረለት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዲሽቃ ተኳሹ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው እሸቱ በቀለ
አርበኛ "እሸቱ በቀለ በሸዋ ደቡብ አማራ ኤፍራታ አማራ ፋኖ ውስጥ በጀግንነቱና በልዩ የዲሽቃ ተኩስ ብቃቱ በተለይም በቅርብ ጊዜያት በነበሩት ውጊያዎች ላይ ያሳየው ፅናትና የጦር ሜዳ ብቃት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፎለታል።
አርበኛ እሸቱ በቀለ የጀግንነቱ መገለጫ አርበኛው ተራ ተዋጊ ብቻ ሳይሆን፣ የከባድ መሳሪያ (ዲሽቃ) አጠቃቀም ላይ ልዩ ጥበብ ያለው አርበኛ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ዲሽቃን እንደ ቀላል መሳሪያ ተሸክሞ፣ ጠላትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ይታወቃል። የእሱ ልዩ የሚያደርገው የልብ ትርታ በከባድ ጥይት ዝናብ ውስጥ ሳይበገር መቆሙ። ትክክለኛ ኢላማ የዲሽቃ ጥይትን በቁጥብነትና በትክክለኛ ኢላማ ላይ የማሳረፍ ችሎታው ነው።
ለጓደኞቹ ያለውን የውጊያ ወኔ የመቀስቀስ አቅሙ እና የውጊያ ውሎ የሽዋ ተራራማና ገደላማ ስፍራዎች በከባድ መሳሪያ ታጅቦ ከሚወዳቸው ፋኖዎች ጋር ሆኖ የጠላትን እንቅስቃሴ አልሞ የመምታት እይታው አጅጉን ማራኪም ነው።
አርበኛ እሸቱ በቀለ በአንድ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ አደላድሎ ይይዛል። የጠላት ጦር መስመር ሰብሮ ለመግባት ሲሞክር፣ እሸቱ "ቁጭ ብሎ" ሳይሆን በቆራጥነት መሳሪያውን በማንቀሳቀስ ተኩስ ይከፍታል። የዲሽቃው ድምፅ ብቻ የጠላትን ስነ-ልቦና ይሰብራል። አርበኛ እሸቱ የዲሽቃ ጥይት የሚተኩሰው በዘፈቀደ ሳይሆን፣ የጠላትን አሰላለፍ እየመረጠ በመምታት ግስጋሴያቸውን እንዲገታ ያደርጋል።
መስዋዕትነትና ፅናት ብዙ ጊዜ በቪዲዮዎች ላይ እንደሚታየው፣ ዙሪያውን ጥይት እየዘነበ እሱ ግን በእርጋታና በፈገግታ የታጀበ የጀግንነት ተግባር ሲፈፅም ይታያል። ይህ ለደጋፊዎቹ "የማይበገሩት ጀግኖች" ተምሳሌት አድርጎታል ተምሳሌታዊነቱ
እሸቱ በቀለ ዛሬ ላይ ለአማራ ፋኖ ትግል የፅናት ምልክት ሆኗል።ጀግንነቱ የጥንካሬው መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
የጀግናው ውሎ በየጊዜው በሚለቀቁ የመረጃ አውታሮች ላይ የሚዘገብ ሲሆን፣ የእሱ ተጋድሎ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ የአማራን ህዝብ የመኖር ህልውና ለማስከበር ትልቅ ተጋድሎ እያደርገ ይገኛል።
