fa
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
3 537
مشترکین
+24824 ساعت
+5847 روز
+97230 روز
آرشیو پست ها
👉የትግራይ አዲስ አስተዳደር በአዲስ አበባ እየተቋቋመ ነው። 👉አዲስ አበባ የከተሙት የህወሓት ተቃዋሚ ጀነራሎች እና ፖለቲከኞች የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለመረከብ እየተዘጋጁ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ ነው። 👉በእነ ጀነራል ጻድቃን የሚመራው ሰብስብ ወደ ትግራይ ሰብሮ ለመግባት አፋር የመሸገውን ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል ወታደራዊ ክንፍ በሎጅስቲክ ፌደራሉ እያጠናከረ ይገኛል,ይኸ የሚሆነው ጀኔራል ታደሰ ወረደን የስልጣን ጊዜው እያበቃ ስለሆነ እሱ የሚባለውን ካልፈፀመ ለመተካት ነው። 🌈አዲስ አበባ የተደራጀው ኃይል ፖለቲካዊና ወታደራዊ ክንፉን በማጠናከር ወደ ትግራይ መግባት እና አሁን ያለውን ስርአት ወያኔን ማስወገድ, ካልሆነ ተገዳዳሪ ሀይል መፍጠር ችግሩ ከትግራይ እንዳይወጣ ማድረግ ነው። 👉 ይኸን ሀይል የሚመሩት ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ፣ ብርጋዴር ጀነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ)፣ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ)፣ ኢንጅነር አሰፋ አብርሃ እና ጀነራል ተክላይ አሸብር (ወዲ አሸብር) ናቸው ። 🌈ኹለት ሳምንት የሥልጣን ዕድሜ የቀራቸው ጀነራል ታደሰ ወረደን አስተዳደር ለመረከብ ተዘጋጅቷል የተባለው ኃይል ከወዲሁ ምክር ቤት እያቋቋመ ነው ። 🌈የጀነራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ጊዜ የሁለት ሳምንታት እድሜ የቀረው መሆኑን ተከትሎ፤ ትግራይን ለመረከብ እየተቋቋመ ነው በተባለው ምክር ቤት ብዙ የትግራይ ፓርቲዎችን ያቀፈ ሲሆን በጀነራል ጻድቃን የሚመራው “የትግራይ የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ” አባል የሆኑት፣ የጌታቸው ረዳ ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንጪ ሓቂ የተባሉ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። 🌈በአፋር የሚንቀሳቀሰው ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል በመባል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፣ ወታደራዊ ክንፍን ከመቸውም ጊዜ በላይ ማጠናከርና ወደ ትግራይ እንድገባ ይደረጋል 🌈አዲስ አበባ የተደራጀው ስብስብ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመቆጣጠር ጥረት ከፌደራል መንግስቱ ሲሆን፣ ለዚህም መንግሥታዊ ምክር ቤት እያቋቋመ ነው። 🌈ምክር ቤቱ የጀነራል ታደሰ የሥልጣን ጊዜ ከማብቃቱ በፊት፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ ይፋ እንደሚያደረግ ሊደረግ ይችላል። 🌈ይኸ ሁሉ የሚሆነው እነ ታደሰ ወረደን አውርዶ, ገብረፅዮንን ሀይል የሚገዳደርና የሚዋጋ ሀይል መፍጠር, ከዚያ የፋኖን ትስስር ከትግራይ ሀይል ያለውን ማቋረጥ ሲሆን ይኸን ለማድረግ የሀራ መሬት ታጋዮችን ማጠናከርና ተኩስ እንድጀምሩ ማድረግ ነው, አፋር ላይ ትኩረት ይጠይቃል ።

በርካታ የአገዛዙ ኃይል ወደ ደቡብ ወሎ ምዕራባዊ አካባቢዎች ገብቶ በንፁኃን እና በንብረታቸው ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን አጠናሮ ቀጥሏል‼️ ከደሴ በስተምዕራብ ከሚገኙት ወረዳዎች መካከል በአምስቱ ማለትም በመካነሰላም ዙሪያ ገጠር ወረዳ፣ በመሐል ሳይንት ወረዳ፣ በወረኢሉ ወረዳ፣ በአማራ ሳይንት ወረዳ እና ወግዲ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአገዛዙ እግረኛ ሰራዊት ተጨማሪ ኃይል እንድላክለት ተደርጎና የሜካናይዝድ ምድብተኞች ድጋፍ ተሰጥቶት ለተከታታይ ቀናት የንፁኃንን መንደሮች በመደብደብ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል:: አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ሰራዊት ሜካናይዝድ ምድብተኞች እና እግረኞች በተኩስ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ የበርካታ ንፁሃን አርሶ አደሮችን ትጥቅ ገፈዋል:: የንፁሃን ቤት እና ሱቅ ጭምር ተዘርፏል:: በዛሬው ዕለት መጋቢት 18/2018 ዓ.ም ደግሞ በአማራ ሳይንት ግንባር ወደ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም አቅጣጫ የጠላት ኃይል ሜካናይዝድ ምድብተኞች መድፍ እየተኮሱ ነው:: አቶ ደምለዉ ምንያህል የሚባል የአማራ ሳይንት ወረዳ 016 ቀበሌ ነዋሪ ተድባበ ማርያም ቀጠና ውስጥ ዛሬ ከጧቱ 3:00 ሰአት ላይ በጠላት ካባድ መሳሪያ ተመቶ ተሰውቷል። የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ሰራዊትን ክንድ መቋቋም ያቃተው የጠላት ኃይል የጦር ሜዳ ሽንፈቱን ለማካካስ ንፁሓን ላይ ጉዳት ማድረስን ባህሉ ስላደረገው ሰሞኑንም ይህንኑ የግፍ ግፍ በመፈፀም ላይ ይገኛል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 18/2018 ዓ.ም 18/ዐ7/2018 ዓ.ም

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ በብአዴን ካድሪ ላይ በወሰዱት እርምጃ የተገደሉ ከ50 በላይ የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች በከፊል 1).ደሳለኝ አስራደ (የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የኢኮኖሚ አማካሪ 2).ወርቅነህ እንደግ የክልሉ ምክር ቤት ህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ 3). ፍቅሩ አዱኛ   የእብናት ወረዳ  ወጣቶችና ህፃናት ሀላፊ 4). አዲሱ ቸኮለ የእብናት ወረዳ    ፀጥታ ሀላፊ 5)..አስሬ ጌትነት የእብናት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ 6).አቡየ  የእብናት ወረዳ ሚሊሻ ሀለፊ 7).አማረ    የእብናት ወረዳ የፓርቲ ኦዲት ም/ኋላፊ 8) ብርሀኑ  የእብናት ወረዳ  መንገድ ኋላፊ 9).ይላቅ አባተ የእስቴ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ሀላፊ 10). እያያ ዳኛው - የታች ጋይንት ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ 11).መቶ አለቃ ቢሰጥ አሰፋ - የስማዳ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ 12). ኢንስፔክተር ጌትነት አሻግሬ- የስማዳ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ 13) አበበ ወንድአፍራሁ - የላይ ጋይንት ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ም/ሀላፊ 14).. ፈንታው - የነፋስ መውጫ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት  ሀላፊ ደራ ወረዳ የተገደሉት ዝርዝር (ሁሙሲት ላይ ከባህር ዳር 35ኪሜ) 15).እስቲበል ጓዴ የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ 16). ፈንታሁን ድረስ የደራ ወረዳ ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ 17).. ተመስገን የሺዋስ የሐሙሲት ከተማ ከተማ ከንቲባ 28).አበበ አድማስ የደራ ወረዳ ፖሊስ ሰው ኃይል አስተዳደር 19)..ጌታቸው ሸርብ የደራ ወረዳ ፖሊስ  ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር  20) ታከለ እርቄ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ 21).. የአድማ ብተና ሻለቃ  ዋና ዘመቻ ኃላፊ 22)..ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ምስጋናው  የአርብ ገበያ ከተማ ፖሊሥ አዛዥ  23).ጋሻነው አበራ ደራ ወረዳ የሰላምና ደህንነት ም ኃላፊ 24).ም/ኮማንደር ፍታለው ጋይንት (የሻለቃ አዛዥ)  (የወያኔ ጦርነት የሚዳልያ ተሸላሚ) 25).ም/ኮማንደር ነጋሽ (ሻለቃ አዛዥ) 26).ም/ኮማንደር ደጀኔ (አበበ ሻለቃ አዛዥ) 27).ሻለቃ መላኩ ሲሳይ (የሻለቃ ዘመቻ መምሪያ) 28). አስናቀው ቆየሁ የወገዳ ከተማ ከንቲባ update 29).ገለጠ ተስፋየ የእብናት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ 30).አብራሪው የኔሰው ባህልና ቱሪዝም ኋላፊ 31).ነጋ ድረስ የወረዳው ሰላምና የፀጥታ ሃላፊ 32).ደስተው ነጋ ደብረታቦር ከተማ የጣይቱ ክፍለከተማ ሚሊሻ ሃላፊ 33). ደመወዝ አበበው ኮማንዶ የነበረ ደብረታቦር ከተማ የቴዎድሮስ ክፍለከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ 33). ጌጤ ካሳ እስቴ  ወረዳ የስራና ሰልጠና ኃላፊ 34). ገለጠ ተስፋዬ  የእብናት ወረዳ ገንዘብ ( ፋይናንስ ) ጽ /ቤት ኃላፊ 2nd #Update 35)..ይታፈር ጫኔ የሊቦ ከምከም ወረዳ ሚሊሻ ሀላፊ 36).ይታየዉ እርቁ የሊቦ ከምከም ወረዳ ሚሊሻ የስምሪት ቡድን መሪ 37)..ሁልጊዜ ሲሳይ የአንዳቤት ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ም/ሃላፊ  ተይዞ በዘግናኝ ሁኔታ የተረሸነ 38).መላኩ ደጀኔ የደቡብ ጎንደር ዞን የፀጥታ መረጃ ሃላፊ 39).ሃብታሙ የእስቴ ወረዳ የፀጥታ መረጃ ሃላፊ 40). ፲/አ ተሾመ  ፀጋየ የእብናት ወረዳ ሚሊሻ የስምሪት ቡድን መሪ 41).ኮማንደር የማታው ምህረቴ የዞን ፖሊስ ምርመራ ኃላፊ 42).ተመስገን አበበ የጉና ወረዳ ፀጥታ ምክትል ኃላፊ ይዘው በዘግናኝ ሁኔታ የገደሉት 43).ኢ/ር ጥላየ የደብረታቦር የአድማ መከላከል አዛዠ 44).ኢ/ር ወረደ የደብረታቦር የአድማ መከላከል አዛዠ 45).መጣልኝ ወርቁ የደራ ወረዳ ሚሊሻ ትጥቅ ቡድን መሪ 46).መ/አ እንዳለዉ የደራ ወረዳ ሚሊሻ ምልመላ ስልጠና ሃላፊ 47). ወርቅሰዉ ሲሳይ የመቀጠዋ ወረዳ ፀጥታ ምክትል ኃላፊ 48).አምሳ አለቃ ፈንታው ቢያድጌ ነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት 49). ኢ/ር አዲሱ አስናቀው የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ 50) . ኢ/ር ታደሰ ምንዋጋው የፉርጣ ወረዳ ፖሊስ ምርመራ ሃላፊ 51).ዋና ሳጅን አማረ የፋርጣ ወረዳ ፖሊስ ትራፊክ አስተባባሪ 52).አደራጀው መብራት የመቀጠዋ ወረዳ አስተዳዳሪ (አብዛኛዎቹ ከሰሞኑ የተገደሉ ናቸው።ከአንዱ በስተቀር ሁሉም አንድ ዞን ላይ ብቻ የተገደሉ ናቸው።) እነዚህ ሲገደሉ ነው Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ  አማራ ክልል ሰላም ነው የሚለን። የእነ ተመስገን የውሸት ሪፖርትና የተዛባ ፕሮፖጋንዳ ሲጋለጥ እንደዚህ ነው ለማነኛውም ፋኖ አሁንም ያሸንፋል የምንለው በምክንያትነት ነው ሸር ሸር አድርጉለት ለገለቴ

የስድስት ልጆች እናቷ ወይዘሮ የሽየ ጉቸ፤ በአገዛዙ ሰራዊት የደረሰባትን የቡድን መደፈር ግፍ መቋቋም አቅቷት ሕይወቷን አጠፋች! በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ድብኮ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችውና የስድስት ልጆች እናት ወይዘሮ የሽየ ጉቸ በለጠ፤ በአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባላት የደረሰባትን አሰቃቂ የቡድን መድፈር ግፍ መቋቋም አቅቷት መርዝ በመጠጣት ሕይወቷን ማጥፋቷ ተረጋገጠ። የ42 ዓመቷ ባለ ትዳርና እናት ወይዘሮ የሽየ፤ በዛሬው ዕለት መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የቀብር ሥነ-ሥርዓቷ ተፈጽሟል። ክስተቱ የተፈፀመው መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ የአገዛዙ ሰራዊት ወደ ቤታቸው በመምጣት ወንዶችን እያፈኑና ልብስ እያስወለቁ ይገርፉ በነበረበት ወቅት ባለቤቷ አርሶ አደር ታዴ ለማምለጥ ተገዷል። አባወራውን ያጡት የሰራዊቱ አባላት፣ እናቲቱን ከልጆቿ ነጥለው በመውሰድ በተራራ ላይ ለሁለት ቀናት (መጋቢት 15 እና 16) በተከታታይ ሲፈራረቁባትና ሲደፍሯት መቆየታቸውን የቤተሰብ ምንጮች በምሬት ገልጸዋል። መጋቢት 16 ቀን ወደ ማታ አካባቢ ወደ ቤቷ የተለቀቀችው ወይዘሮ የሽየ፤ ልብሷ በደም ጨቅይቶና በአካልም በስነ-ልቦናም ክፉኛ ተጎድታ ነበር ቤቷ የደረሰችው። የደረሰባትን በቃላት የማይገለጽ ውርደትና ግፍ መቋቋም ያቃታት ይህች የአማራ እናት፣ ጎረቤቶቿ ሊረዷትና ልብሷን ሊቀይሩላት ሲጣደፉ መርዝ በጥብጣ በመጠጣት "ልጆቼን አደራ" የሚል የመጨረሻ ቃል ተናግራ ከዚህች ዓለም በሞት ተለይታለች። ይህ አሰቃቂ ድርጊት በተፈጸመበት ወቅት የሰሜን ወሎ ዞንና የላስታ ወረዳ አመራሮች፣ የብልፅግናን የምርጫ ቅስቀሳ በማሳለጥና ለሥርዓቱ ታማኝነታቸውን በማሳየት ላይ መጠመዳቸው በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። እናቶች በቡድን ሲደፈሩና ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ የአካባቢው አመራሮች እነ መርሳው አራጌና ወንድምነው ወዳይ ሆዳቸውን ሞልተው መተኛታቸው የሞራል ዝቅጠታቸውን እንደሚያሳይ ተገልጿል። ይህ በላስታ እናት ላይ የደረሰው ግፍ በአብይ አህመድ ሰራዊት እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋትና የሴቶች መብት ረገጣ በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ዝምታቸውን ሰብረው ድምፅ እንዲሆኑ ተጠይቀዋል። የአማራ ሕዝብ በእንዲህ ዓይነት ውርደትና ግፍ ውስጥ ሆኖ የምርጫ ካርድ እንዲያወጣና ሥርዓቱን እንዲያገለግል የሚደረገው ግፊት፣ የሥርዓቱን አረመኔነት ይበልጥ የሚያጋልጥ ሆኗል።

የጓዱን ጥቁር ክላሽ ደርቦ ፋኖን ተቀላቀለ ። የአ.ፋ.ብ.ን ቴዎድሮስ ዕዝ የ 105 ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር አቤ ጉበኛ ሻለቃን የተቀላቀለው የ 99ኛ ክፍለ ጦር ጋንታ መሪ ሀብታሙ በላይነህ እንደ ተ
የጓዱን ጥቁር ክላሽ ደርቦ ፋኖን ተቀላቀለ ። የአ.ፋ.ብ.ን ቴዎድሮስ ዕዝ የ 105 ኛ ኮር 55ኛ ክፍለ ጦር አቤ ጉበኛ ሻለቃን የተቀላቀለው የ 99ኛ ክፍለ ጦር ጋንታ መሪ ሀብታሙ በላይነህ እንደ ተናገረው መከላከያ ሰራዊት አባላት ለአገር እና ለህዝብ በማይጠቅም አሰላለፍ ውስጥ መሆናቸውን ሁሉም ስለተረዳ ከተቋሙ ወጦ ፋኖን ለመቀላቀል አጋጣሚ ብቻ ነው የሚፈልገው ብሎ በአንደበቱ ተናግሯል ። እንበርታ !

በአማራ እናት ማህፀን ውስጥ በፅናት ተረግዞ፣ በጀግንነት እሳት ተገርፎና በሀገር ፍቅር ወተት ታሽቶ የወጣው ይህ ብርቅዬ መሪ፤ የትግል ማዕበል አምጦ ከወለዳቸው ታላላቅ የጦር ጠቢባን መካከል ተጠቃሽ ነው። ፊታውራሪ ድርሳን ብርሀኔ እርሱ ለጦር ሜዳው ሰይፍ፣ ለሀሳብ መድረኩ ደግሞ ብርሃን ነው። አርበኛ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔ ለሰራዊቱ መሪ ብቻ አይደለም፤ የሀሳብ መሀንዲስ እንጂ። በጭንቅ ሰዓት፣ ሁሉም ግራ ተጋብቶ መውጫ ሲፈልግ፣ እርሱ ግን በትክክለኛው የሀሳብ ሚዛን ችግሩን ሰንጥቆ መፍትሄ የማውጣት ልዩ ተሰጥኦ አለው። እርሱ የጦርነትን ምስቅልቅል ወደ ድል ስልት የሚቀይር የሀሳብ መሀንዲስ እንጂ። በጭንቅ ሰዓት፣ ሁሉም መውጫ አጥቶ በሚባክንበት ያንን የጥበብ ክር መዞ መፍትሄ የማውጣት ብቃቱ ተአምራዊ ነው። ሰይፍ የሚቆርጠው የሀሳብ ብልሃት ሲታከልበት ብቻ ነው። የሚል መመሪያ ያለው ይህ መሪ፣ ውሳኔዎቹ እንደ መብረቅ ፈጣን፣ እንደ አለት ደግሞ የማይናወጡ ናቸው። እንደ መምሪያ ኃላፊነቱ፣ የጠላትን ምሽግ በብልሃት ሰንጥቆ፣ ሰራዊቱን በልበ ሙሉነት ወደ ድል ማማ መምራት የእርሱ ልዩ የአመራር ጥበብ ነው።እርሱ በጦር ግንባር ሲቆም ተራራው የሚንቀጠቀጥለት፣ በውይይት መድረክ ሲቀመጥ ደግሞ ጠቢባን በተመስጦ የሚሰሙት ታላቅ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። ፊታውራሪ ድርሳን ብርሀኔ የምስራቅ አማራው ኮከብ፣ የጭንቅ ቀን ደራሽና የጀግንነት ተምሳሌት። ዛሬም ነገም በታሪክ ድርሳን ላይ ስሙ በወርቅ ቀለም እየፃፉ ይገኛል።Dawit Amhara ከንጉሶቹ መንደር!!

#አይበገሬዎች 64ኛ ክ/ጦር ከአባታቹህ የወረሱትን ጀግንነት በፉከራ እና በቅራርቶ ከጠላት ጋር በጨበጣ በመግጠም የጠላትን ካንፕ ተቆጣጥራቹህ በርካታ የጠላት ኃይል ደምስሰው አሳይተውናል። #አይበገሬዎቸች የሽፈራው ገርባው፣ የእጅጉ ዘለቀ የአባ ኮስትር በላይ ዘለቀ ልጆች መሆናቸውን ያሳዩት በተግባር ነው። በሸበል በረንታ መርገጭ ንዑስ ከተማ እና ቁይ ከተማ ድርጅቱ የሰጣቹህን ግዳጅ በልዩ ሁኔታ በመወጣት የጠላትን ካንፕ በመቆጣጠር የአገዛዙ ቅጥርኛ ሰራዊት እንደ ቅጠል አራግፈው የጠላት አስከሬን እንደ ጭድ ክምር ከምረው መጋቢት 16/2018 ዓ.ም በህዝባችን ፊት አሳይተውናል።  ካልነኩት የማይነካው ከደርሱበት የማይለቀው ደጉ የሸበል በረንታ መርገጭ ከተማ የሚገኝ ህዝባችን እንዲህ ይለናል። በመረገጭ ከተማ ብዙ ውጊያዎች ተካሂደው ያውቃሉ። እንደዛሬ አይነት ውጊያ አይተን አናውቅም? መርገጭ ከተማ በአራቱም መዓዘን በፋኖ ቁጥጥር ስር ለአራት ሰዓታት ውላለች ይለናል። ውጊያው ፍከራ የተሞላበት በየመንገዱ እና በየቤቱ ታዛ ብዙ አስከሬን የወደቀበት ውጊያ ነበር። በውጊያ ብዙ ታዝበናል? ህዝብን ያንገላቱ የነበሩ ማሊሻ እና ፖሊስ ከጥቂቶች በስተቀር አልቀዋል። ውጋያ እየጠነከር ሲሄድ የጠላት ኃይል ተጨማሪ ኃይል በማስገባት የተርፎትን ማዳን ችሏል። በመርገጭ ከተማ ብዙ የአገዛዙ ቅጥርኛ ሚሊሻ፣ ፖሊስ፣ ፋራ ኮማንዶ እና መከላከያ #በመርገጭ_ቅድስ_ስላሴ_ቤተክርስትያን እና የሙስሊም መቃብር #ሁጅቡ ኔትወርክ ሰፈር ሞለቻችንን በጅምላ ቀብረናል። በዚህ ውጊያ መስዋት የሆኑ የዘመኑ በላይ ዘለቀ ልጆች ጀግኖች ሞቱ አይባልም? ምክንያቱም ጀግኖች ለህዝባቸው በገቡት ቃል መሰረት ጠላትን ቅስሙን ሰብረው መንገዱን ሁሉ የጠላት አስከሬን አድርገው ነው በክብር የተሰው። በመጨረሻም በመርገጭ ንዑስ ከተማ የምንኖር የማህበርሰብ ክፍል እኛ ከትግሉ ጎን ነን በርቱ ሀገር የምትመር ህዝብን አቅፎ በሚገዛ መንግስት እንጅ ህዝብን በአሰከፊ ሁኔታ በሚመራ መንግስት አይደለም? 64ኛ_ክፍለ_ጦር ባአካሄደው ውጊያ በጣም ተደስተናል። ቀንደኛ የህዝብ ፀር የነበሩ መንገድ መሪ ሚሊሻ እና ፖሊሶች እሰከ ከወዳኘው ላይመለሱ ልካቹህልናል እጅግ አድርገን እናመሰግናለን🙏🙏🙏 ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት🙏🙏🙏

በላስታ ወረዳ በግጭት ለተከሰተ የነፍስ መጥፋት በፋኖ ሲቪል መዋቅር አስተባባሪነት በባህላዊ ስነ ስርዓት ዕርቀ ሰላም ተፈጸመ! በምስራቅ አማራ ቀጠና ላስታ ወረዳ ዐ11 ቀበሌ ጥራስ ፈሬ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዓመታዊ በዓል ላይ በሁለት ወጣቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ ለደረሰው የነፍስ መጥፋት፡ በፋኖ ሲቪል መዋቅር አስተባባሪነት የሀገር ሽማግሌዎችና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት መጋቢት 16/2018 ዓ/ም የነፍስ ዕርቅ ተፈፅሟል። በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር በሚተዳደረው በላስታ ወረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ ጥረት፡ ግድያው በተፈፀመ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ በሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓት እልባት እንዲያገኝ ተደርጓል። የነፍስ መጥፋት ድርጊቱ የተፈፀመው ጥር 27/2018 ዓ/ም ሲሆን፡ በወቅቱ በቤተክርስቲያኑ የንግስ በዓል ላይ ታድመው በነበሩ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ፀብ፡ አንድኛው ግለሰብ ሌላኛውን በዱላ በመምታቱና በዱላ የተመታው ግለሰብም የአፀፋ እርምጃ በመውሰዱ በዚህ መካከል የአንድኛቸው ሕይወት አልፏል። ይህ አጋጣሚ ተጨማሪ ማህበራዊ ቀውስና ውስብስብ ችግሮች እንዳያስከትል በማሰብ፡ የላስታ ወረዳ የፋኖ ጊዜያዊ አስተዳደርና የ303ኛ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር አመራሮች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ፍትሕ ለማስፈን ያለመታከት ሲሰሩበት ቆይተዋል። በዚህም መሠረት የሟችና የገዳይ ቤተሰቦች ለዕርቅ እንዲቀመጡ ተደርጎ፡ በአካባቢው በደም አድራቂ ሽማግሌዎች መሪነት በባህላዊ ወግና ስርዓት ዕርቁ ተፈጽሟል። የሟችና የገዳይ ቤተሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፋኖ ሲቪል መዋቅር የላስታ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የተከዜ ክፍለ ጦር ስራ አስፈፃሚዎች በተገኙበት የዕርቁ ስነ ስርዓት ተከናውኗል። ግድያው ድንገተኛ መሆኑ ታምኖበት ዕርቁ <በቀይ ደም> ሕግ መሠረት የተፈፀመ ሲሆን፡ ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁ የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል። የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አርበኛ አስር አለቃ ነጋ ፈንቴ፣ የወረዳው ፀጥታ ኃላፊ አርበኛ ሳጅን ሃብተማርያም አባተ፣ የሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደንበሩ አያሌው እና የተከዜ ክፍለ ጦር ምክትል ዘመቻ አዛዥ አብርሃም መልኩን ጨምሮ 13 የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የዕርቅ ሂደቱን መርተውታል። በመጨረሻም ዕርቀ ሰላም ያወረዱት የሟችና የገዳይ ቤተሰቦች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ፡ የሲቪል መዋቅሩና አስታራቂ ሽማግሌዎች ይህ የደም መፋሰስ ዘልቆ እንዳይቀጥል ላደረጉት ከፍተኛ ጥረትና ላሳዩት ትጋት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ምንጭ፦ በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ጄነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ስር የሚተዳደረው የላስታ ወረዳ ሲቪል መዋቅር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!

//የአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ 208ኛ ኮር መልሶ  ተደራጅቷል// አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ  ባወጀው የዘመቻ ማጥራት እና ማብቃት ግዳጅ በቀጠናው በተመደቡ በአርበኛ አስምሮ ፍቃዴ የሚመሩ ግብረሀይሎች ማጥራት እና ማብቃት ተልእኳቸውን ለሁለት ወር በማስቀጥል የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር ይባል የነበረው ኮር 208ኛ ኮር ተብሎ ተሰይሞ የመልሶ ማደራጀት ስራውን አከናውኗል። 1. ዋና አዛዥ................አርበኛ ወርቁ ሙሉ 1.1. ወ/ቃል አቀባይ.....አርበኛ ሳሙኤል አበራ 1.2. ጽ/ቤት ኃላፊ....አርበኛ አብረሃም ኢያሱ 1.3.ህግና ስነምግባር ክፍል......አርበኛ ጌታቸው ጌጡ 1.4. ወታደራዊ መረጃና ደህንነት..........##### 2. ምክትል ወ/አዛዥ..................አርበኛ ማሩ አዴ 2.1. ዘመቻ መምሪያ ....... አርበኛ ፶አለቃ አስራት ጌታቸው 2.2 ም/ዘመቻ መምሪያ.........አርበኛ የሽበር አስማማው 2.3. ልዩ ኦፕሬሽን ......አርበኛ መቶ አለቃ ባምላኩ ጌታቸው 2.4  መገናኛ ....... አርበኛ ኮማንዶ ስመኘው  ይስማው 2.5  ወታደራዊ ስልጠና ...... አርበኛ አለቃ አለሙ ሙሌ 2.6  ም/ወ/ስልጠና.............አርበኛ ሃብታሙ ምህረቴ 2.7  ቃኝና መሀንዲስ ............አርበኛ ጤናው አየነው 3. የፖለቲካ ኃላፊነት...........አርበኛ ፃዲቅ ዋለልኝ 3.1  ም/ፖለቲካ ኃላፊነት .........አርበኛ ማርሸት አሰፋ 3.2 ም/አደረጃጀት መምሪያ.............አርበኛ ንጉሴ አገኘሁ 3.3 ህዝብ ግንኙነት........አርበኛ ዘመነ ተሾመ 3.4 ህዝብ አስተዳደር ..........አርበኛ ፍቅሩ የማታው 3.5  ም/ህዝብ አስተዳደር..........አርበኛ የሽበር አጥናፉ 3.6  ቀጠናዊ ትስስር ...............አርበኛ ጥሩየ ቀናው 3.7 ትም/ትና ስልጠና.......አርበኛ እሸቱ ዘነበ 3.8 ም/ትም/ትና ስልጠና........ቄስ ገ/ስላሴ  ነሲቡ 3.9 ወጣቶችና ሴቶች ........አርበኝት ኮማንደር አታላ አለሙ 4.      ወ/አስተዳደር ኃላፊ ........አርበኛ ይርጋ ክቡሬ 4.1.   ም/ወ/አስተዳደር  ........አርበኛ ሰፊው ሙላት 4.2.    የሰው ሀይል...........አርበኛ እማምነው መርቆ 4.3.    ፋይናንስና ግዥ .........አርበኛ ማርሸት ንጋት 4.4   ም/ፋይናንስና ግዥ............አርበኛ ጌጡ መልካሙ 4.5   ሀብትና ንብረት አፈላላጊ .......አርበኛ በውቀት አላቸው 5.   ሎጂስቲክ ኃላፊ ...........አርበኛ በሬ አወቀ 5.1.  ም/ሎጀስቲክ ...........አርበኛ ብርሀን ወርቄ 5.2.  ኦርዲናንስ ............አርበኛ ማርየ በለጠ 5.3. ህክምና ክፍል ሀላፊ .......አርበኛ ዶ/ር ቢልልኝ መሳፍንት 6. ኦዲት ክፍል ሰብሳቢ .......አርበኛ ሻንበል ጣመ ዋለልኝ በመጨረሻም ለአመራሩ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ  የቀጠና የስራ ስምሪት በስራ አመራሮቹ በኩል የተሠጠ መሆኑን ተገልጿል። ከበላይ ዕዝ 208ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት መምሪያ!!! ድል ለአማራ ፋኖ

"የፋኖ ደጋፊ በሚመስሉ ሰዎች በኩል! አማራን በሚመስሉ ሰወች በኩል! እኔ አንድ ነገር ማስቀመጥ እፈልጋለሁ! እንደው አራት አርበኞችን  ምሳሌ ላንሳ!"   ይላል አርበኛው ለአማራነት ካለው ጥልቅ የፍቅር ውቅያኖስ ሀሳቦቹን እየጨለፈ። "ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋን ላንሳ ወይ ምሬ ወዳጆን ወይ ሄኖክ አድሴን ላንሳ ዝናቡ ልንገረውን ላንሳ እራሴንም አንድ አድርጌ ላስቀምጥና ከዚህ! ሳሚን  ሰቅሎ አሞግሶ ዝናቡ ልንገረውን የሚሰድበውና የሚያቋሽሽ ሰው አማራ አይደለም።ይሄ ምድነው ሳሚን አቋሾ ዝናቡን ወይም ሄኖክ አድሴን የሚያቀናጣ የሚያጀግን ሚድያ ለአማራ አይጠቅምም። ለወጣንለት አላሣ ልክ ትግሉ ምን ያስፈልገዋል ብሎ መስራት  ይገባዋል እንጅ! እኔን የሚያወድሰኝ ጎደሬነትን ሊወክል አይችልም። እያጠፋሁ ሊደግፈኝ ስለማይችል። ዝናቡን የሚደግፈው ሁሉ ጎጃምን አይወክልም። ምክንያቱም ባጠፋውና በሰራው ልክ ነው ሊመሰገን ያለያም ሊጠየቅ የሚገባው።" ይላል! አርበኛ ሳሚ በዚህ ንግግሩ ውስጥ የወንጀለኛ ጎጥ የለውም። ማንነት የለውም። ከማናችንም ጎን አይደለም። አማራነትን አይወክልም። በአማራ ትግል ላይ በጎጥ ተወሽቀው የአማራን ትግል ለማጨናገፍ አንዳችንን ደግፈው ሌሎቻችንን የሚነቅፉ ከሆነ የጥላትን አላማ የሚያሳኩ ከኛ ወገን ያልሆኑ ናቸው ይላል። እውነት ነው። ጥልቅ በሆነ በሀሳብ መነፀር የታዬ ንግግር ለታሪክ የሚቀመጥ የአማራነት ጥልቅ የሞራል ልዕልና ነው። አርበኛው ከአንደበቱ የሀሳብ ዥረቶች በዜማና በሀያሲያን እንደተቀረፁ ሆነው እያበለበለው ቀጠለ። "ለትግሉ በሚጠቅመው፤ለአማራ ህዝብ በሚጠቅመው ሳይሆን እርስ በርሱ በፉክክር ውስጥ የፋኖን አሰላለፍ በመፈረካከስና ጭራሽ ሀገር እሰራለሁ ብሎ የወጣውን ሀይል በመክፈል እየተቀሳቀሰ ያለ ሀይል አለ። ይሄ አማራ አይደለም። ብልፅግና የሚከፍለው ተከፋይ ቡድን ነው። አማራን ለማጥፋት የሚከፈላቸው አካላቶች ናቸው ይሄንን በእርግጠኝነት ነው የምናገረው።ምክንያቱም ውጤቱ ምድነው ነው።" ይላል አርበኛ ሳሚ ባለእድል የከፋፋዮችን አላማ በተመሐከተ በመመርመርና በመተንተን ይቀጥላል። "ጎንደርን ከወሎ፤ወሎን ከሸዋ፤ሸዋን ከጎጃም የሚከፋፍል ቡድን ካለ ይሄ ተከፋይ ቡድን ነው።ለሁሉም እንድደርስ እፈልጋለሁ! ላያታግል የሚችል ገፊ ሀሳብ ካለ ይህ አማራ አይደለም። ስለዚህ ጥላት ገንዘብ በጅተናል ብሏል። አወ ለነደነዚህ አይነት ሰዎች ነው የሚከፍላቸው። ጎጃም  ነኝ ብሎ ሌላውን የሚያጥረገርግ ከሆነ፤ጎደር ነኝ ብሎ ሌላኛውን የሚያጥረገርግ ወሎ ሸዋ ነኝ እያለ ሌላውን የሚያጥረገርግ ከሆነ ፤ ታጋዮችን በልዩነት የሚያጥረገርግ ከሆነ በፍፁም ወንድሞቸ ሲሰደብ ይከፋኛልጅ አልደሰትም።ምክንያቱም ከትግሉ ውስጥ አለሁ ብዬ ስለማስብ። ስለዚህ ትግሉ ውስጥ ያሉ ወንድሞቸን እንደዚህ ማድረግ አጠቃላይ ብልፅግና አሁን አስቦ ጎንደርን እንሞሽር የሚለው ነገ ጎጃው ወሎ ሸዋን የሚያዘጋጁ ሀይሎች ናቸው እነዚህ። ተከፋይ ሰዎች እራሱን መጠበቅ ይገባል የሚል ሀሳብ አለኝ።" ካለ በኋላ ተጨማሪ መልክትን በትንግርታዊ ልሳኑ ይቀጥላል። " ይሄንን የክረምት ወር በአግባቡ መጠቀም አለብን በሚገባ ዝግጅቶቻችንን የምንፈፅምበት የክረምት ወቅትን  የሚሰሩ ጠንከር ጠንከር ያሉ ኦፕሬሽኖች ይኖራሉ። ስለዚህ ህዝቡ በስነ-ልቦናው ተዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል።በትጥቅም በስቅም በየትኛውም አጋር ድጋፍ ዝግጁ መሆን ይጠበቅበታል።ከዚህ በኋላ ለባንዳ የሚራራ ልቦና የለንም። ስለዚህ በባንዳነት ሊሳተፍ የሚችል ሀይል ከየትኛውም አቅጣጫ ከባንዳነቱ ሊቆጠብ ይገባዋል። ሚኒሻ አድብተና ፖሊስ መከላከያ ከባንዳነት ተግባራቸው መቆጠብ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውን ለማዳን የታጠቁትን ትጥቅ እየያዙ ባይችሉ ትጥቅ ሳይዙ በአገኙት የፋኖ አደረጃጀት እጅ እየሰጡ እራሳቸውን ማዳን ይገባቸዋል። ይህ ወቅት ስር ነቀል የምናፀዳበት በመሆኑ መጠን ከዚህ ጥፋት እራሳቸውን ማዳን ይጠበቅባቸዋል።ምክንያቱም መኖር አለብን! ህዝባችን መኖር አለበት! ብልፅግና ተናግሯል። አፈርሳችኋለሁ አጠፋችኋለሁ ብሏል። እኛ ደግሞ መፍረስም ሆነ መጥፋት አንፈልግም።ተደራጅተናል። ይሄንን ወቅት ተጠቅመን የቆየንበት የረዥም ጊዜ ዝግጅት በሙሉ ወደ ማጥቃት ዘመቻ መግባታችን ስለማይቀር ማንኛውም ሀይል እራሱን ማዘጋጀት እዳለበት እና ወደ ፋኖ እየተካተተ ለዚህ ህዝብ የህልውና ዘመቻ ስምሪት እየተቀበለ ወደ አሸናፊነት ሁኔታ መሄድ አለብን። ማህበረሰቡም እራሱን በዚህ ልክ ያዘጋጅ። ጥሪዬን አቀርባለሁ!!!"  አመሰግናለሁ!!" ብሎ በአማራዊያን የስነ-ሞራል ምጥንነት መልክቱን ደመደመ!!! #እኛም መልክታችን ስለሆነ በቃል የተላለፈውን የአርበኛውን ሀሳብ ወደ ፅሁፍ አስፍሬ ለኤፌቢ አንባቢያኖች ጀባ ብያለሁ! #መጋቢት 18/2018 ዓ/ም! #እሸቱ አባተ(ፋኖ) ነኝ

ሾልኮ በወጣው የብፅግና ሰነድ ስለፋኖ የተነሳው ሀሳብ‼️ የብልፅግና ፓርቲ የህልውና ስጋቶች ትንተናና ስትራቴጂክ የመፍትሔ አማራጮች በሚል ዕርስ የተዘጋጀውና ሾልኮ በኢትዮ ሰገነት ሚዲያ ተለቆ የተመለከትነው ባለ 11 ገፅ ሰነድ ውስጥ በተራ ቁጥር 2.3 (#ፋኖና_የአማራ_ክልል_የትጥቅ_ትግል) በሚል የተነሳውን የሰነዱ ሀሳብ እንደወረደ ከታች ተየይዟል👇👇👇👇👇 በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የፖሎቲካ መረጋጋት ላይ እጅግ አሳሳቢና ፈታኝ ሆኖ የቀረበው የፋኖ እንቅስቃሴ፣ ከቀላል የክልል ግጭት ባለፈ የሥርዓቱን መሠረት #እየነቀነቀ ያለ ብሔራዊ ስጋት ሆኗል። ፋኖ ቀደም ሲል በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት የፓርቲያችንም ሆነ የመከላከያ ሠራዊታችን እንደ ዋነኛ ደጋፊና አጋር ሆኖ ቢያገለግልም፣ አሁን ግን የሥርዓቱ #ቁጥር_አንድ የደህንነት ስጋት ሆኖ ተሰልፏል። ይህ ለውጥ የመጣው በፓርቲያችንና በክልሉ ልኂቃን መካከል በነበረው አለመግባባት ብቻ ሳይሆን፣ መንግሥት የወሰዳቸው አንዳንድ ወታደራዊና ፖለቲካዊ እርምጃዎች በሕዝቡ ዘንድ የተሳሳተ ትርጉም በማግኘታቸው ነው፡፡ በተለይም የመከላከያ ሠራዊት መልሶ ማደራጀትና የክልል ልዩ ኃይሎችን የመበተን ውሳኔ፣ በአማራው ልኂቅ ዘንድ ‹‹ክልሉን ለጥቃት የማጋለጥ ሴራ›› ተደርጎ በመወሰደ ለፋኖ መጠናከር ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኗል፡፡ የፋኖ እንቅስቃሴ #አደገኛነት የሚመነጨው በጫካ ካለ የሽምቅ ውጊያ አልፎ፣ በከተሞችና በገጠሩ ማህበረሰብ ውስጥ ጥልቅ የሆነ ‹‹የህልውና ተቆርቋሪነት›› ስሜት መፍጠሩ ነው፡፡ ይህም የመንግሥት መዋቅር በክልሉ ውስጥ እንዳይሠራ፣ የግብር አሰባሰብ እንዲቋረጥና የአካባቢው አስተዳደሮች #እንዲፈራርሱ አድርጓል፡፡ ከዚህም በላይ፣ ፋኖ ከህወሓትና ከሻዕቢያ ጋር ‹‹የጋራ ጠላት›› በሚል ሰበብ ስልታዊ ትብብር ለመፍጠር እያሳየ ያለው ፍላጎት የፓርቲያችንም ሆነ መንግሥታችን እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ቀደም ሲል በታሪክና በፖለቲካ የማይገናኙት እነዚህ ኃይልች በብልጽግና ላይ ያላቸው ቂም አንድ እንዱሆኑና የመረጃ እንዲሁም የትጥቅ ልውውጥ እንዲያደርጉ ዕድል ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህ የታጠቁ ኃይሎች ጥምረት በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለውን ቀለበት በማጥበቅ፣ ሥርዓቱ በኃይል #እንዲወገድ ግፊት ማድረጉን ቀጥሏል፡ ፡ ሌላው የፋኖ መጠናከር ምክንያት የሆነውና በሰነደ ውስጥ በልዩ ሁኔታ ሊታይ የሚገባው ጉዳይ፣ የአንዳንድ ከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች ያልተገባ ዛቻና ንግግር ነው፡፡ በሕዝብ ላይ የሚሰነዘሯቸው እላፊ የወጡ ዛቻዎች፣ ፋኖን እንደ ሽፍታ ሳይሆን እንደ ‹‹ሕዝብ ጠባቂ›› እንዲታይ አድርገውታል፡፡ ይህ የኮሙኒኬሽን ስህተት መንግሥት በክልሉ ያለውን የሕዝብ ድጋፍ #ሙለ_በሙለ እንዲያጣና ወጣቱ በብዛት ወደ ትጥቅ ትግሉ እንዲቀላቀል ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ፋኖ አሁን ላይ ያለው የትጥቅ አቅምና የሰው ኃይሌ በክልል ያለ ዋና ዋና መሠረተ ልማቶችንና የመንግሥት ተቋማትን እስከመቆጣጠር የደረሰ በመሆኑ፣ ይህንን ኃይለሰ በወታደራዊ እርምጃ ብቻ ለመደምሰስ መሞከር የሰሜኑን ጦርነት ዓይነት አዙሪት ውስጥ ከመክተት ባለፈ ለሥርዓቱ #ምንም_ዓይነት_ድል አያመጣም ሲል ሰነዱ ያትታል😁 በሚዲያ ፋኖ የለም ፣ተበትኗል በማለት ቢደሰኩርም በውስግ ግምገማቸው ግን ፋኖ  የብልፅግናን ስርዓት #መሰረት_እየነቀነቀ ያለ ብሔራዊ ስጋት መሆኑን አምነው የመፍትሄ ሀሳብ ፍለጋ እየባዘኑ ነው😂 ወጥር ፋኖ💪 18/ዐ7/2018 ዓ.ም

በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴወድሮስ ፭ኛ ኮር ታላቅ ተጋድሎ አደረገ ትናንት 17/07/2018 ዓ.ም የአፋብን በላይ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ኛ ኮር  ከአዘዞ መገንጠያ ወደ ዳባ ማርያም ሬሽን ጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረን መከላከያ፣ አድማ ብተና እና ሚሊሻ ጥምር ኃይል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፦ በላይ ዘለቀ እዝ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ (፭ኛ) ኮር፣ የጠላት መቅጫ ነበልባሎቹ የታድሎ ብርሐን ክፍለጦር ሠራዊት አባላት ልዩ ቦታው ዳባ በተባለ ቦታ ላይ ደፈጣ በመጣል  እና ከበባ ዉስጥ በማስገባት  አመድ ሲያደርጉት ውለዋል።ወኔ እርቆት እና የፍርሀት እንቅጥቅጥ እያዛመዉ  የመጣዉ ሞራለቢስ ሰራዊት የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ እየፈረጠጠ ተመልሷል። በተጋድሎዉም አናብስቶቹ የበላይነትን በመዉሰድ በጥምር ተላላኪ ሀይሉ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ እና  ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰዉበታል።     በጥቃቱ  ቁጥሩ በእውን የማይታወቅ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ከመደረጉም በላይ አስከሬኑንና ቁስለኛውን ትቶም እንዲፈረጥጥ ተደርጓል። በዚህ አዉደ ዉጊያ ከፍተኛ የወረዳ አመራሮች የተደመሰሱበት እና ቁስለኛ የሆኑበት ግንባር ነበር።በዚህ አስደናቂ መብረቃዊ ኦፕሬሽን  አስከሬኑን እንኳን በቅጡ ሳያነሳ ወደመጣበት ፈርጥጦ ተመልሷል። ከዚህ በተጨማሪ የተማረኩ የሚሊሻ አባላትና የነፍስወከፍ መሳሪያዎችም መገኘታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አስከሬንና ቁስለኛ ለማንሳት ከፍተኛ ጥረት ያደረገው ይህ ጨፍጫፊ የጠላት ሰራዊት በአይበገሬዎቹ የታድሎ ብርሃን ክፍለጦር ረመጦች ህልም ሲሆንበትና የበለጠ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራ ሲደርስበት በብስጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የከብት እረኛ ንፁሃንን ረሽኖ በመውጣት አሸባሪ ግብሩን አሳይቷል።        ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።          አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ            ህ/ግንኙነት ክፍል                መጋቢት18/2018 ዓም