ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر2 955
مشترکین
+424 ساعت
+127 روز
+38830 روز
آرشیو پست ها
ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረ የብልፅግና ሰራዊት በደፈጣ ተመታ!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር አካል የሆነው 30ኛ ክፍለ ጦር ቃኝዎች ባደረጉት የደፈጣ ጥቃት ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ ይጓዝ የነበረውን የብልፅግና ሰራዊት ሰኞ ገበያ ከምትባል ቦታ ደፈጣ በመጣል ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዲያስተናግድ ተደርጓል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ግንቦት 06/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ ጧቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን ሁለት መድፍ፣ አምስት ኦራል፣ ሁለት ሲኖትራክ፣ ስድስት አይሱዙ፣ ሶስት ፓትሮል ከነሙሉ ቁሳቁሱ ግራና ቀኝ አጅቦ ለማሳለፍ በተንቀሳቀሰበት ጊዜ ፋኖዎቹ ገዥ ቦታና ደፈጣ በመያዝ የጠላትን ኃይል ሲያራግፉት አርፍደዋል።
በተደረገው የደፈጣ ጥቃት ኦፕሬሽን 16 የተደመሰሰና 11 የቆሰለ ሲሆን በደረሰበት መብረቃዊ የደፈጣ ጥቃት የተደናገጠው የብልፅግና አገዛዝ ጦር ዙ-23 መሳሪያን በመጠቀም በዘፈቀደ በመተኮስ የሁለት(2) አርሶ አደሮችን ቤትና ንብረት ማቃጠሉ ታውቋል።
መዳረሻዉ ድል እና ነፃነት የሆነዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃውን አድርሷል።
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 06/2018 ዓ/ም
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር የ49ኛ ክፍለጦርን ከበባ ውስጥ ለማስገባት የመጣውን የጥላት ሀይል ሰብሮ በመውጣትና በመልሶ ማጥቃት ድል ተቀናጁ!
በዛሬ ግንቦት 06/2018ዓ/ም ሌሊት በስድስት(6) አቀጣጫ ዙ-23 ማራኪዎቹን የ49ኛ ክፍለጦርን ከበባ ውስጥ ለማስገባት በቃሊም፣ በሮቢት፣በአሚድ መድሀኒያለም፣ በበቅሎ ማነቂያ፣ በላኪኬና በለጋይሶራ ለማጥቃት ከበባ ቢያደርግም ሳይሳካለት ውርደትን ተከናንቦ ተቀጥቅጦ ተመልሷል።
የቀድሞው የካላኮርማ ክፍለጦር የሰራዊት አባላት የአሁኑ የ49ኛ ክፍለጦር ልማደኞቹ የሰራዊት አባላት በሁሉም አቅጣጫ የመጣውን ግሪሳ የአብይ አህመድ ቅልብተኛ ወታደር በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት ወደ መጣበት አስፈርጥጠውታል።
በልበ-ሙሉው አርበኛ ለገሰ ሰማው የሚመራው የ49ኛ ክፍለጦር በሻለቃ በመከፋፈል በሁሉም አቅጣጫ የመጣውን ከ4 ክፍለጦር በላይ ቅጥረኛና ወራሪ የጠላት ሀይል ላይ ቀድሞ ገዥ ቦታዎችን በመያዝ በሞርተርና በድሽቃ እንዲሁም በመትረየስና በስናይፐር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።
ስግብግቡ፣ በእውር ድንብር የሚመራውና ስሌት የሌለው የብልፅግና ጨፍጫፊ አገዛዝ በአቀደውና በአለመው ልክ ሳይሳካለት ሙትና ቁስለኛውን ሳያነሳ እያንጠባጠበ ክንደ ብርቱዎቹን የምስራቅ ኮከቦች መቋቋም አቅቶት ወደ መጣበት በሽንፈት መመለስ ተችሏል።
የ102ኛ ኮር ኮከቦች ዙ-23 ማራኪዎቹ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች የ49ኛ ክፍለጦር የሰራዊት አባላት የጦር ሰፈራቸውን ሳያስቀሱ ዛሬም እንደትናንቱ ክብራቸውን በማስጠበቅ ህዝባቸው አንገቱን ቀና በማድረግ በኩራት እንድኖር አድርገዋል።
በመጨረሻም ጥላት ከሰዓት በኋላ በቃሊምና በአስገዳይ ጥሶ ለመውጣት የመጨረሻ ሀይሉን ቢጠቀምም የ49ኛ ክፍለጦር አናብስቶች አምስተኛ ሻለቃ በቦንብና በጨበጣ ውጊያ ባደረገችው ብርቱ ፊልሚያ ሙትና ቁስለኛውን በማንጠባጠብ በሁሉም አቅጣጫ ወደ ኋላ እየፈረጠጠ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ወዱ አስቻለው ደሴ ክፍለ ጦርና በረራ ክፍለ ጦር የጠላትን ሃይል እየደቆሱት ይገኛሉ።
ቀን 6/9/2018 ዓ/ም
የአገዛዙ ስልጣን ጠባቂ ሰራዊት በሽዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ አውራጃ የመዘዞንና የባሽ ህዝብን ለመጨፍጨፍና ለመዝረፍ በአራት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ ሲሆን
1,ከሞላሌ ከተማ ወደ ባሽ
2,ከመሀል ሜዳ ከተማ ወደ ባሽ
በሌላኛው ግባር
3,ከጣርማበር ወደ መዘዞ
4,ከደብረሲና ከተማ ወደ መዘዞ ቢቀሳቀስም
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ወንዱ አስቻለው ደሴ ክፍለ ጦርና በረራ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ሻበሎች በባሽ የመጣውን የጠላት ሃይል በማር ማረፊያ፥ቁርጥ አምባና ቴሌው አካባቢ በነበልባሎቹ ብርቱ ክንድ በጨበጣ ውጊያ ሙትና ቁስለኛውን ማንሳት አልቻለም አባት አርበኛው መካሽ ንጉሴ ብርጌድ በባሽ ማርያም የገባውን ጠላት እየደቆሱት ይገኛሉ።
በሌላኛው ግንባር በመዘዞ በኩል ከይስማ መስክ እስከ አሞራው ገብርኤል የገባውን ጠላት ከወንዱ አስቻለው ደሴ ክፍለ ጦር የተውጣጡ ሻበሎች ድባቅ ሲመቱት የመዘዞ ክላስተር አባት አርበኞች ሃይሌ ብርጌድ በኮረብቲት የገባውን የጠላት ሃይል ከፋኖ ጋር በመናበብ አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው መልሰውታል።
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር አምበላ ቀበሌ በመመሸግ ህዝብ ሲዘርፍ በነበረው ሚሊሻ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ
ጠላት ጥምር ጦር እያለ ያሰባሰበው የሚሊሻና የአድማ ብተና ሀይል የአዊ ዞን አዮ ጓጉሳ ወረዳ አምበላ ቀበሌና የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲዘርፍ፣ሴቶችን ሲደፍርና ንጹሀንን በአደባባይ ሲረሽን መቆዬቱ ይታወቃል። ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በትኩረት ሲከታተል የቆዬው የቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 88ኛ ክ/ጦር በሰራው አስደናቂ ኦፕሬሽን አምበላ ቀበሌ ከጥዋቱ 12:00 ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት የጠላትን ካምፕ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የማያዳግም እርምጃ ወስዷል። በዛሬው አውደ ውጊያ ስድስት ሚሊሻና አድማ ብተና የተሸኘ ሲሆን ከ10 በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግም ተችሏል።
ከጠላት የተገኘ ምርኮ፡
➡️1200 የብሬን ተተኳሽ
➡️የብሬን ሸንሸል
➡️ቁጥሩ ያልታወቀ የክላሽ ተተኳሽ
➡️የጠላት ሎጀስቲክስ በክንደ ነበልባሎች 88ኛ ክ/ጦር ተማርኳል
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
ክፋት ለማንም፤በጎነት ለሁሉም!!!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም
የአገዛዙ በርካታ የሰላም አስከባሪ አመራሮችና አባላት የአፋብንን የምህረት አዋጁ በመቀበል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን ተቀላቀሉ!
የአገዛዙ የጀርባ አጥንት ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩና በመርሓቤቴ ወረዳ መቀመጫዋ ፌጥራ ከተማ የነበሩ በርካታ የሰላም አስከባሪ አመራሮችና አባላት፣ የቀረበላቸውን የምህረት አዋጅ በመቀበል የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ፣ አፄ ዘርያዓቆብ ኮር ስር የሚገኘውን ናደው ክፍለ ጦርን በሰላም ተቀላቅለዋል።
መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው የወገንን ኃይል የተቀላቀሉት እነዚህ አመራሮችና አባላት፤ "ምንም እንኳን ቢረፍድም፣ ከጥፋት መንገድ ተመልሰን የበደልነውን ሕዝብ ለመካስና ከወገናችን ጎን ለመቆም በማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ ነን" ሲሉ ገልጸዋል።
የአሳምነው ዕዝ አመራሮች በበኩላቸው፣ ሌሎች አሁንም በአገዛዙ ስር ሆነው ሕዝብን እየበደሉ ያሉ ታጣቂዎች የቀረበላቸውን የምህረት ጥሪ ተጠቅመው ወደ ወገን ኃይል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ የአመራሮችና አባላት ወደ ፋኖ መቀላቀል በአካባቢው ለነበረው የአገዛዙ መዋቅር ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።
የተቀላቀሉት አመራሮችና አባላት ዝርዝር፦
* አማረ ንጉስ – የሰላም አስከባሪ ከፍተኛ አመራር
*ካሡ ኮላስ – የሰላም አስከባሪ ተወርዋሪ መቶ መሪ
*ብዛየሁ ሽታው – የሰላም አስከባሪ ሻምበል አመራር
* ባልከው ቢጡ – የሰላም አስከባሪ አባል
• ሸዋንግዘው አበበ – የሰላም አስከባሪ አባል
• አባብዬ አበራ – የሰላም አስከባሪ አባል
• ዘርጋው ይርደው – የሰላም አስከባሪ አባል
• እማምዬ ገምሽር – የሰላም አስከባሪ አባል
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ
#የድል አውድማው ምስጢራዊ ኃይሎች፡ «7/70» — የምድር ድሮኖች!❤
በአማራ ህልውና ተጋድሎ ታሪክ ውስጥ ስማቸው በደመቀ ቀለም የሚፃፍ፣ ግብራቸው ግን በዝምታ የታጀበ ጥቂት ጀግኖች አሉ። እነዚህ ጀግኖች የሰማይ ድሮኖች በማይደርሱበት፣ ቴክኖሎጂ በማይገምተው ፈጣን ግስጋሴና ስልታዊ ጥቃት ጠላትን አመድ የሚያደርጉ «የምድር ድሮኖች» ናቸው—እነሱም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር የ 7/70 (ሰባት ለሰባ) ክፍለ ጦር አባላት!!
የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አባላት ለጠላት የማይታዩ፣ ለወዳጅ ግን የፅናት ምሰሶዎች ናቸው። #በማጀቴ ዙሪያ፣ #በወጀድና #በአርብ ገበያ (መስቀል በር) ተራሮች ላይ እንደ ንስር እየበረሩ፣ እንደ አንበሳ እየተቆጡ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታትን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው አድርገውታል። መልክዓ ምድሩን እንደ መዳፋቸው የሚያውቁት እነዚህ ብርቅዬ ልጆች፣ መሬት ጠብ በማይል ወታደራዊ ስልት የጠላትን ወረራ መክነው እንዲቀሩ ያደርጋሉ።
የእውቀትና የጥበብ ማማ ይህች ክፍለ ጦር የጦር ሜዳ ጀግኖችን ብቻ ሳይሆን፣ ነገ ኢትዮጵያን ሊረከቡ የሚችሉ አስተዋይና ትሁት መሪዎችን ያፈራች የጥበብ ማዕከል ነች። እንደ አርበኛ #ኢሳያስ #ደመቀ ያሉ የአንበሳ ልብ የታጠቁ፤ እንደ ጀግናው ባለ #ድግሪው አርበኛ #አማር #ታዘዘ ያሉ የእውቀት ባለቤቶች፤ እንደ ፖለቲካ ባለምጡቁና አይሰበሬው #ኤፍሬም #ባዬ ያሉ ስትራቴጂስቶችን ያቀፈ የጀግኖች ስብስብ ያፈራች ነች።
እነዚህ «የአሳምነው ልጆች» #በጎጃም፣ #በጎንደር፣ #በወሎና #በሸዋ ለሚገኘው መላው አማራ ተምሳሌት የሚሆኑ፣ በወታደራዊ ሳይንስና በስነ-ምግባር የታነጹ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። የትግሉ ጅማሮ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬዋ ሰዓት ድረስ፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኮር የሰባት ለሰባ 7ለ70 ክፍለ ጦር ከአብይ አህመድ ኃይሎች ጋር ያልተፋለመበት አንድም ቀን የለም። ለዚህም ታላቅ ገድል የሸዋ ተራሮችና ሸንተረሮች የደም ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።
ማርከው እንጂ ተማርከው የማያውቁት እነዚህ ጀግኖች፣ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዛሬ ላለበት የጥንካሬ ደረጃ የጀርባ አጥንት እንደሆኑ የምስራቁ ንጉስ ፊታውራሪ ድርሳን ብርሃኔ ምስክርነት ሲሰጥ ከአንደበቱ ሰምቻለሁ። ይህችን የአማራ የመኖር ተምሳሌት የሆነች ክፍለ ጦር፣ ከዚህ በላይ ታድሳና በዘመናዊ ትጥቅ ጎልብታ እንድትመጣ የሁላችሁም ደጋፊነት ያስፈልጋታል ብዬ አስባለሁ። ሆኖም በውጭ የምትኖሩ የአማራ ተቆርቋሪዎችና ባለሀብቶች፣ ለእነዚህ የቁርጥ ቀን ደራሾች በምታደርጉት ድጋፍ የታሪክ ተባባሪ እንድትሆኑ ጥሪዬን በጓዳዊ ወንድምነት አስተላልፋለሁ።
ታሪክን የሚሰሩት በዝምታ የሚጋደሉ ጀግኖች ናቸው።የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዓሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኮር የ7/70 ክፍለ ጦር አባላት ደግሞ የዚህ ታሪክ ዋነኛ ጸሐፊዎች ናቸው #Dawit Amhara ከንጉሶች መንደር!!
ለሕዝብ ሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለዓላማ ፍጻሜ፣ የምታስቡ የሕዝብ ልጆች እውነት የጎጃም እናት ወልዳ የጎጃም ሽማግሌና ብሩክ ሕዝብ አሳድጓችሁ ከሆነ እንደ ማኅበረሰባችሁ አስቡ።
ውሸተኞች፣ አስመሳዮችና በፌክ አካውንት ወንድምን በወንድም ላይ እንዲነሣ የምታደርጉ እኩያትን ካልሆናችሁ ትልቁን ጉዳይና ነገ ሊመጣ የሚችለውን ተዋርዶና እልቂት አስባችሁ ዝም በሉ። እኔ ሰሞኑን ብዙ ሰዎችን ከገጼ አባርሬያለሁ። ገናም አባርራለሁ።
ሰላምን የማይሰብክ በተለይ በወንድሞቻችን መካከል የተፈጠረውን ጥል የባሰ ላምባ እያርከፈከፈ እሳት ሊያደርግ የሚሞክር ሁሉ አመራርም ሆነ ተራ አባል ወይም ተመልካች እርሱ የሕዝብ ጠላት ነው።
ተቋም አለ፤ በምሁራን የሚመራ የሽምግልና ቡድን አለ። ይኸ ሁሉ ሥራ እየሠራ ነው። ይህ ባለበት አጋና መንጋ ይዞ መነታረክ አላስፈላጊ መረጃዎችን ለሚድያ ስድድብ ፍጆታ ማዋል በጣም ያሳፍራል፤ ይጎዳል።
አሁን ላይ ጣት መቀሳሰሩ በፌክ አካውንት ሰው በሚሳደቡትና በለው ገንጥለው ለየው በሚሉ ጎጥና አካባቢ ለይተው በሚሳደቡት ላይ ይሁን። እነርሱን እየለያችሁ አውግዙ።
እባካችሁ ሥራ እንሥራበት አድቡ!
ከዚህ በታች ያያዝሁት የመሪያችን ቃል አሁንም መፎክራችንና የመሐላ ቃላችን ይሁን።
@ዲ/ን በአንተአምላክ
አንድ ሰው ምን ሲል ሰማሁት፤
በገንፎ ተጀምሮ በንፍሮ ለሚያልቅ ህይወት ራሳችሁን አታስጨንቁ። ይኸውላችሁ ልክ ስትሞቱ እገሌ እኮ ሞተ ተብሎ መነጋገሪያ ከመሆንና ከቀብር ሰዓት በኋላ ደግሞ የካርታ መጫወቻ ምክንያት ከመሆን ውጪ ማንም ስለናንተ ደንታ የለውም። ተገናኝቶ ለማያውቅ ቤተሰብ እንኳን የመገናኛ ምክንያት ነው የምትሆኑት። የመጣው ቤተሰብ እናንተን አጥቶ ለተጎዳ ወላጅ ወገን ለመሆን ነው፤ እኛ እንደርሳለን ይላሉ፣ ከሳምንት በኋላ ግን ይጠፋሉ። ያኔ ተረሳችሁ በቃ።
ይኸውልህ ማንም ይክፋው፣ የመጣውም ይምጣ፣ የሄደም ይሂድ፣ ህይወትህን እየተጋፈጥክ ኑራት። ተዋረድክ? አንድ ሰሞን ነው።
ቅሌት ምናምን አሉህ አይደል? እሱም አንድ ሰሞን ነው። ሁሉም በውስጡ ጉዱን ሸፍኖ ነው የሚኖረው። ቀለል አድርጋችሁ ስኬታችሁን እያባረራችሁ ኑሩ። ማርያምን ህይወት ይቀጥላል። እናንተ ብቻ ይህን አለም አትኮፈሱ፣ ይህን አለም ራሳችሁን አትጣሉ። መኖር ብዙ ያሳያችኋል። እንዳትኖሩ፣ እንዳያልፍላችሁ፣ የሆነ ጊዜ ተሰብራችሁ እንድትቀሩ ለሚፈልጉ ሰዎች ስትሉ ጠንካራ መሆን አለባችሁ። አለቀ!! Dawit Amhara ከንጉሶች መንድር
የጥንቃቂ መረጃ‼
✍
የድሮን አሰሳ እየተደረገባቸው ያሉ ቦታዎች፦
✅ከደብረ ታቦር እሥከ ማሕደረ ማርያም
✅ከደብረ ታቦር ዓለም በር
✅ከደብረ ታቦር -መሎ ሐሙሲት
✅ከደብረ ታቦር -ጋሳኝ
✅ከአምበሣሜ -ዋንዛዬ
✅ከአምበሳሜ-ጉራምባ
✅ከአምበሳሜ - ገላውዴዎሥ
ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው
‹‹እስካሁን አማርኛ እናውቃለን ስንል ኖረናል፡፡ አሁን ግን በሽግግር መንግስቱ በአዲስ መልክ መማር ሊገባን ነው›› ሲል ምጸቱን ገልጾ ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተጠርተው በ50 ሺህ ብር ዋስና ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ተጥሎባቸው ተለቀቁ፡፡ በዚያው ዓመት ከጎጃም ከመጡ አርሶ አደሮች ጋር አሲረዋል በሚል ‹‹ለጥያቄ ይፈለጋሉ›› ተብለው ሐምሌ 5 ቀን 1985 ዓ.ም ተጠርተው ለ24 ሰዓታት ከታሰሩ በኋላ በ20 ሺህ ብር ዋስትና ተለቀቁ፡፡ ከዚያ በኋላ ሐምሌ 12 በነበረው ተለዋጭ ቀጠሮ ዋስተናቸው ተነስቶ ለ43 ቀናት ከታሰሩ በኋላ ነሐሴ 24 ቀን 1985 ዓ.ም ሊፈቱ ችለዋል፡፡
በወቅቱ በተደጋጋሚ እየተጠሩ ዋስትና ከመጠየቃቸው የተነሳ ‹‹የዋሶች ባንክ ማደራጀት ሳይኖርብኝ አይቀርም›› ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ከተደጋጋሚና አሰልች የፍርድ ቤት ምልልስ በኋላ ሰኔ 20 ቀን 1986 ዓ.ም የዋለው ችሎት ከጎጃም ገበሬዎች ጋር አሲረዋል በሚለው ክስ የሁለት ዓመት እስር ተፈረደባቸው፡፡ ሐገራቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በታማኝነት ያገለገሉ ሽማግሌ በጡረታ እድሜያቸው ከርቸሌ ወረዱ፡፡ በወቅቱ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ፕሮፌሰሩን ‹‹የህሊና እስረኛ›› ሲላቸው የፍርድ ሒደቱንም ‹‹መረጃ አልባ›› ሲል አጣጥሎታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በእንጥልጥል የቆየው ደብረ ብርሃን ንግግር ክስ ተቀስቅሶ በሳምንት እስከ ሁለትና ሶስት ጊዜያት ፍርድ ቤት መመላለሱ የሰላቻቸው ፕሮፌሰር አስራት ለችሎቱ ‹‹የምታውቁትን ውሳኔ የዛሬ 6 ወይም 9 ወር ከምትሰጡኝ ዛሬውኑ አሳውቁኝና እስር ቤት ቁጭ ብዬ መጽሐፍ ላንብብ›› ሲሉ በምሬት ተናግረው ነበር፡፡ ታህሳስ 18 ቀን 1987 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፕሮፌሰሩን የ3 አመት አስር በየነባቸው፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ ፕሮፌሰር አስራት ከ150 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል፡፡ ከርቸሌ ታስረው በነበረበት ወቅት ከፖለቲካ እስረኞች ተለይተው ከፍታብሔር እስረኞች ጋር እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን፤ መጽሃፍትና ጠያቂም በፈለጉት መጠን አያገኙም ነበር፡፡
የእስር አያያዛቸው የከፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ1972 ዓ.ም የጀመራቸው የልብ ሕመማቸዉ ተባብሶ እንዲሁም የስኳር መጠናቸው በመጨመሩ ከፍተኛ የጤና ችግር ላይ ወደቁ፡፡ ለብዙ በሽተኞች መድኀኒት የነበሩት አስራት ህክምና ተከልክለው የበሽታ መጫወቻ ሆኑ፡፡ ከስኳራቸው ከፍ ማለት ጋር ተያያዞ አይናቸው ማየት ተሳነዉ፡፡ ሰውነታቸውም እንደፈለጉ ሊታዘዛቸው አልቻለም፡፡ የልብ ድካማቸው እየጨመረ ሲመጣ ሕክምና እንዲያገኙ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ደብዳቤ ጻፉ፡፡ መፍትሄ ግን አላገኙም፡፡ የኋላ ኋላ ሲዳከሙ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህመማቸው ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ በመሆኑ መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ታህሳስ 18 ቀን 1991 ዓ.ም ወደ ውጭ ሐገር ሄደው እንዲታከሙ ተፈቀደ፡፡ በከፍተኛ ሁኔታ በመድከማቸው አውሮፕላን ውስጥ በሐኪሞች እየታገዙ ወደ ለንደን ሆስፒታል በረሩ፡፡ ከ3 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ አሜሪካ ሆስተን አመሩ፡፡ በአሜሪካ ቅዱስ ሉቃስ ኤጲስቆጳል ሆስፒታል በነበሩበት ወቅት እንደተሻላቸውና ከልቡ ሲያስባቸው ለነበረው ህዝብ መልዕክት አስተላልፈው ነበር፡፡ ትንሽ እንደተሻላቸው ዘመዶቻቸው ወደሚገኙበት ፊላደልፊያ ከወር በፊት ተዛውረው በነበረበት ወቅት ባልታወቀ ምክንያት ህመማቸው ተባብሶ ተዳከሙ፡፡
ሞትን ድል ሲያደርጉት የኖሩት ሐኪም ግንቦት 6 ቀን 1991 ዓ.ም ፊላደልፊያ በሚገኘው ፔኒሲለቫኒያ ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዕለተ አርብ በተወለዱ በ71 ዓመታቸው አረፉ፡፡ በወቅቱ የፕሮፌሰሩን ሞት ትልልቅ የዓለም መገናኛ አውታሮች ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ነበር፡፡ የፕሮፌሰሩ አስከሬን ታላላቅ እንግዶች፤ ቤተሰቦቻቸውና አድናቂቆቻቸው በተገኙበት ግንቦት 15 ቀን አሸኛኘት ተደርጎለት ከዋሽንግተን ዲሲ ጉዞ ጀመረ፡፡ ግንቦት 15 ቀን 1991 ዓ.ም የተነሳው የፕሮፌሰሩ አስከሬን ሮም አርፎ ግንቦት 17 ቀን 1991 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30ጰ ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰ፡፡ በስፍራው ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ አስከሬኑን በከፍተኛ አጀብ ለገሐር ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አደረሰው፡፡ በመኖሪያ ቤታቸውም ሌሊቱን ጸሎተ ፍትኃት ሲደረግ አድሮ በማግስቱ አስከሬናቸው በመሠረቱትና በኋላም በሞቱለት ድርጅታቸው፣ መዐህድ ጽ/ቤት ጥቂት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል አመራ፡፡
በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ፍትሃትና ጸሎት ከተደረገላቸው በኋላ ቅድስት ስላሴ እንዳይቀበሩ መንግስት በመከልከሉ ምክንያት ግንቦት 17 ቀን 1991 ዓ.ም በባለወልድ ቤተክርስቲያን እንዲያርፉ ተደረገ፡፡ ከ18 ዓመታት በኋላ በ2009 ዓ.ም በባለወልድ ቤተከርስቲያን የነበረው አጽማቸው ወደ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተዛውሯል፡፡
ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሁለት ወንዶች ልጆች አባትም ነበሩ፡፡
06/ዐ9/2018 ዓ.ም
🕯️የታላቁ ኢትዮጵያዊ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም 27ኛ ዓመት ሙት ዓመት መታሰቢያ 🕯️
#አጭር የሕይወት ታሪክ
አስራት ወልደየስ ከአባታቸው ከአቶ ወልደየስ አልታዬና ከእናታቸው ከወይዘሮ በሰልፍይዋሉ ጽጌ ሰኔ 12 ቀን 1920 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፡፡
የአስራት አባት አቶ ወልደየስ አልታዬ በጸሓፊ ትዕዛዝ ኃይሌ ወልደ-ስላሴ አስተዳደር ውስጥ በጸሐፊነትና በአስተዳደር ተግባር የተሰማሩ ነበሩ፡፡ እናታቸውም በአነስተኛ ንግድ የተሰማሩ ነበሩ፡፡ ፕሮፌሰር አሥራት የሶስት ዓመት ህጻን እያሉ ወላጆቻቸው በፍች ምክንያት ስለተለያዩ ከእናታቸው ጋር ወደ ድሬዳዋ አቀኑ፡፡ አስራት ድሬዳዋ በነበሩበት ወቅት ጣሊያን ኢትዮጵያን ወረረች፡፡ በዚህ ወቅት በእነ ሞገስ አስግዶምና አብርሃም ደቦጭ ግራዚያኒ ላይ የተደረገ የግድያ ሙከራን ለመበቀል ከግራዚያኒ በተላለፈ በቀል በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ33 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዶማ፤ በአካፋና በገጀራ ተጨፍጭፈው ሲገደሉ የአስራት አባት አቶ ወልደየስ አልታዬም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተጨፍጭፈው በአርበኝነት ተሰዉ፡፡ እናቱ ወይዘሮ በሰልፍይዋሉ ጽጌም የባለቤታቸው የአቶ ወልደየስ ሞት ተጨምሮበት ብዙም ሳይቆዩ ታመው ከሕጻን ልጃቸዉ በሞት ተለዩ፡፡ ወላጆቹን በሞት የተነጠቀው ታዳጊ ከአያቱ ከወይዘሮ ባንቺወሰን ይፍሩ-ለሱሲሉ ጋር መኖር ጀመረ፡፡ አጎቱ አቶ ዘውዴ ወረደወርቅ እዚያው ድሬዳዋ ይኖሩ ነበርና ታዳጊውን የቄስ ትምህርት እንዲማር አስገቡት፡፡ የቄስ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት በቀለም አቀባበሉ ጎበዝ ነበር ይላሉ አስተማሪው አለቃ ለማ፡፡ ምስክርነታቸውን ሲሰጡ ‹‹አስራት በልጅነት በጣም ጎበዝ በመሆኑ ዓመት ሳይሞላው ወንጌሉን ከቁጥሩ አንበልብሎ፤ ከፍካሬ እስከ ነቢያት ደግሞ ድቁና ተቀበለ›› ይላሉ፡፡
ከቄስ ትምህርቱ ጎን ለጎን ድሬዳዋ ይገኝ ከነበረው ፈረንሳይ ሚሲዮን ገብቶ ቀለም መቁጠር ጀመሮም ነበር፡፡ የእናቱ አባት ቀኛዝማች ጽጌ ወረደወርቅ ታዋቂ አርበኛ ነበሩ፡፡ በመሆኑም ጣሊያን አርበኞችን ወደ ጣሊያን ሐገር ወስዶ በሚያስርበት ወቅት ቀኛዝማች ጽጌም አንዱ ታሳሪ ነበሩ፡፡ ቀኛዝማች ጽጌ ከሶስት ዓመት ተኩል እስር በኋላ ሐገራችን ነጻ ወጥታ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ አስራትን አዲስ አበባ አስመጥተው በ1934 ዓ.ም ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አስገቡት፡፡ ትምህርት ቤት በገባ በአመቱ በ1935 ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ከአጠቃላይ ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት የካሜራ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በወቅቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል ላቅ ያለ ውጤት ያስመዘገቡትን ወደ ውጭ ሐገር ልኮ ማስተማር ተጀምሮ ነበርና አስራትም በዚሁ የትምህርት ዕድል ምክንያት ግብጽ ወደሚገኘው የእንግሊዞች ቪክቶሪያ ኮሌጅ ተላከ፡፡ በቪክቶሪያ ኮሌጅ ለአምስት ዓመታት ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በስኮላርሽፕ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ወደ ታላቋ ብሪታኒያ እስኮትላንድ ኤደንብራ ዩንቨርስቲ አቀና፡፡ በወቅቱ ህግ እንዲያጠና ከትምህርት ሚንስቴር ቢነገረውም አሻፈረኝ ብሎ የህክምና ኮሌጁን ተቀላቀለ፡፡
ትምህርቱን እንደጨረሰም ፈጥኖ ወደ ሐገሩ ተመለሰ፡፡ በወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚንስተር የነበሩት እውቁ አርበኛ ደጃዝማች ፀሐይ እንቁስላሴ አስጠርተው የጤና ሚንስትርነቱን ቦታ እንዲይዝ ይጠይቁታል፡፡ ዶክተር አስራት ግን አይሆንም ሲል ተቃወመ፡፡ በዚሁም የተነሳ የልዕልት ጸሃይ ሆስፒታልን ተቀላቀለ፡፡ ለአምስት ዓመታት በልዕልት ጸሐይ ሆስፒታል ካገለገለ በኋላ ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ታላቋ ብሪታኒያ ሐገር አቀና፡፡ አደንብራ ዩንቨርሲቲ ገብቶ ቀዶ ህክምናን አጠና፡፡ በቀዶ ህክምና ዘርፍ አስራት የመጀመሪያው ኢትየጵያዊ ሐኪም ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ አስራት በእድሜም በማዕረግም እያደገ ስለሆነ አንቱ አያልን አንናገራለን፡፡ እነ ዶክተር አስራት እስኪተኩት ድረስ የሀገራችን የህክምና ዘርፍ በነጮች የተያዘ ነበር፡፡ ዶክተር አስራት ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የህክምና ማሰልጠኛ እንዲከፈት በመወትወታቸው ምክንያት የጥቁር አንበሳን ሆሰፒታል እውን አደረጉ፡፡ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሲቋቋም የቴክኒክ ኮሚቴውን የመሩት ዶክተር አስራት ነበሩ፡፡ እ.ኤ.አ በ1965 ዓ.ም የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እውን ሲሆን ዶ/ር አስራት ተባባሪ ፕሮፌሰር በመሆን የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ዲን ሆኑ፡፡ በደርግ ወቅትም በካድሬዎች ይደረግባቸው የነበረውን ከፍተኛ ጫና ተቋቁመው ሐገራቸውን ሳይለቁ ህዝባቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በወቅቱ በተደጋጋሚ ወደ ዘመቻ የተላኩ ሲሆን፤ የሄዱበትን ዘመቻም በክብር ለመወጣት በቅተዋል፡፡ በዚህም መሠረት በ1968 ዓ.ም በቀዶ-ጥገና ሐኪምነት በቃኘው ሆስፒታል፣ አስመራ፤ በ1969 ዓ.ም በድጋሚ በቃኘው ሆስፒታል፣ አስመራ፤ በ1970 ዓ.ም በራዛ ዘመቻ በቀዶ-ጥገና ሐኪምነት እና ቡድን መሪነት በመቀሌ ሆስፒታል፤ እንዲሁም በሰኔ 1971 ዓ.ም በቀዶ-ጥገና ሐኪምነት ምጽዋ ዘምተው ግዳጃቸውን ተወጥተዋል፡፡ በህክምናው ዘርፍ ‹‹አስራት የተባለ ጸበል ፈልቋል›› እስከመባል የደረሰ አንቱታን ያተረፉ ብቁ ሐኪም ነበሩ፡፡ ኢህአዴግ ‹‹በብቃት ማነስ›› በሚል ከሌሎች 41 ምሁራን ጋር ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በ1985 ዓ.ም እስከሚያባርራቸው ድረስ ዩንቨርስቲውን በትጋት ያገለገሉ የሐገር ባለውለታ ነበሩ፡፡ በሙያቸው የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኙ ሲሆን፤ ጥቂቶቹን ለመዘርዘር ያክል የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ የፈረሰኛ ደረጃ፤ የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን የፈረሰኛ ደረጃ፤ የአብዮታዊ ዘመቻ ዓርማ፤ ዓለም አቀፍ የወርቅ ሜርኩሪ (በግል አስተዋጽኦ)፤ የቀይ ባህር ኒሻን አንደኛ ደረጃ ይገኙበታል፡፡ የደርግ ሥርዓት ተሸንፎ ኢህአዴግና ሻዕቢያ ስልጣኑን በተቆጣጠሩበት ወቅት ሰኔ 24 ቀን 1983 ዓ.ም በተደረገው የሽግግር መንግስት ቻርተር ውይይት ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ወክለው የተገኙት ፕሮፌሰር አስራት ‹‹ሐገር ላስገነጥል ተወክዬ አልመጣሁም›› በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ቆራጥ ጀግና ኢትዮጵያዊ ብቸኛው ሰው ነበሩ፡፡ ‹‹ይህ ጉባኤ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ምንም ጉዳይ ሊወስን፤ ሊያግድ ወይም ሊሰርዝ አይችልም›› በማለት ጉባኤው እያደረገው ያለው ውሳኔ ኢ-ዲሞክራሲያዊ መሆኑን አስረግጠው ሞገቱ፡፡ በዚህ ንግግራቸውም የተነሳ ከጉባኤው ሲወጡ ብዙ ማስፈራሪያና ዛቻ ያካሂዱባቸው ነበር፡፡
በወቅቱ በኮንፈረንሱም ሆነ በሽግግር መንግስቱ ምንም ውክልና ያልነበረው የአማራ ህዝብ በየአካባቢው ግፍና መከራን ማስተናገድ ጀመረ፡፡ ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸው ምሁራን በመነጋገር የመላው አማራ ህዝብ ድርጅትን ታህሳስ 2 ቀን 1984 ዓ.ም መሰረቱ፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበርም ፕሮፌሰር አስራት ሆነው ተመረጡ፡፡ ፕሮፌሰር አስራት የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት በሐገር ውስጥና ከሐገር ውጭ ድርጅታቸውን ማስተዋወቅና የተቃጣውን የዘር ፍጅት ለመመከት ጥረት አደረጉ፡፡ ከሐገር ውጭ ጉዞ በማድረግ በስዊድን፤ በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ፤በሎሳንጀለስና በኒዮርክ በመዟዟር የድጋፍ ቻፕተሮችን አቋቋሙ፡፡ በሐገር ውስጥ በነበረው የህዝብ ጥያቄ መሰረት በደብረ ብርሃን ዘርያዕቆብ አደባባይ ታህሳስ 11 ቀን 1985 ዓ.ም በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ታሪካዊ ንግግር አደረጉ፡፡ የድርጅታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተቀባይነት ማግኘት እረፍት የነሳው የሽግግር መንግስት ፕሮፌሰሩን ‹‹ጦርነት ቀስቃሽ ንግግር›› አድርገዋል ሲል ከሰሳቸው፡፡ የዚህን ንግግር ጦርነት ቀስቃሽ መባል የሰማ የአካባቢው ህዝብም
የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር የአመራር ብቃትና የ6 ወራት ስልታዊ ክንውን ግምገማ በስኬት አካሔደ!!
ግንቦት 06/2018 ዓ.ም
የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው 201ኛ ኮር፣ ባለፉት ስድስት ወራት ያስመዘገባቸውን ወታደራዊ ድሎችና ድርጅታዊ ግቦች የገመገመበት ጥልቅ መድረክ አካሄደ። ለተከታታይ ስምንት ቀናት የቆየውና በአመራር ሂስና ግለ-ሂስ የታጀበው ይህ መድረክ፣ የኮሩን የቀጣይ ጊዜ ጉዞ የሚያመላክቱ ቁልፍ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።
በዚህም በሦስት ዋና ዋና ዘርፎች (ወታደራዊ፣ ፋይናንስና አስተዳደር) ተከፋፍሎ የቀረበው የኮሩ የ6 ወራት ሪፖርት፣ ድርጅታዊ ተልዕኮዎችን ከመፈጸም አኳያ የታዩ ስኬቶችን በዝርዝር ዳስሷል። መድረኩ ትኩረት ካደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦
1. የወታደራዊ ግስጋሴ ውጤቶች፦ ኮሩ ባለፉት ወራት ያካሄዳቸው አውደ-ውጊያዎች፣ የተመዘገቡ ስኬቶችና የክፍለ ጦሮች የመልሶ ማደራጀት ቁመና በጥልቀት ተፈትሸዋል።
2. የሰው ኃይልና የደጀን ግንባታ፦ ተተኪ ኃይልን በማሰልጠን፣ የኋላ ደጀን ጦርን ለይቶ በማደራጀትና ሰራዊቱን በዕውቀት በማብቃት ረገድ የታዩ ለውጦች ተገምግመዋል።
3. የሀብትና ሎጅስቲክስ አስተዳደር፦ የፋይናንስ፣ የሎጅስቲክስና የኦርዲናንስ አጠቃቀምን ይበልጥ ውጤታማና ግልጽ ከማድረግ አኳያ ጥብቅ ቁጥጥርና ግምገማ ተካሂዷል።
ሆኖም አመራሩን የመፈተሽ ሂደት ሂስና ግለ-ሂስ በአርበኛ እሸቱ፣ አርበኛ ይትባረክ፣ አርበኛ ስለሺ እንዲሁም የአፋብን ም/አዛዥ ለወ/አስተዳድር ሻለቃ ዝናቡ ልንገርው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ አንድ ቀን በመገኘት፣ ሥራዎችን ከመገምገም ባለፈ በአመራሩ ጥንካሬና ድክመት ላይ ያተኮረ ሂስና ግለ-ሂስ ጠንከር ያለ ወታደራዊ ይዘት ያለው ሃሳቡን አስቀምጧል። ይህም የ201ኛ ኮር አመራሩ ራሱን እንዲያነጽ፣ የሥራ ቅንጅቱን እንዲያጠናክርና ለቀጣይ ተልዕኮዎች በላቀ ወኔ እንዲነሳ ዕድል መፍጠሩ ተመልክቷል።
የስድት ወሩ ሪፖርቱ በዋናነት ካነሳቸው ነጥቦች አንዱ የሰራዊቱና የሕዝቡ መስተጋብር ነው። ከጊዜያዊ መንግሥት ጋር ያለውን የሥራ ግንኙነት ማጠናከር፣ በኮሩ ስር ባሉ አካባቢዎች የፍትህ ሥርዓት አሰጣጥን ማሻሻልና የሕዝብን ደህንነት በጽኑ መሠረት ላይ መገንባት የቀጣይ ጊዜ የትኩረት አቅጣጫዎች ሆነው ተቀምጠዋል።
ለተከታታይ ስምንት ቀናት የቆየው ጥልቅ ውይይት፤ የተለዩ ክፍተቶችን የሚደፍኑ ስልታዊ መመሪያዎችንና አዳዲስ የሥራ ስምሪቶችን በመስጠት ተጠናቋል። 201ኛ ኮር የተጣለበትን ታሪካዊ ኃላፊነት በላቀ ወታደራዊ ዲሲፕሊንና ድርጅታዊ ጥንካሬ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በአጽንኦት አረጋግጧል።
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤ አዲስ ተስፋ"ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉ"
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
