ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 389
مشترکین
+2924 ساعت
+2547 روز
+1 45030 روز
آرشیو پست ها
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሕዳር 25/2018ዓ.ም
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ለወራት ያሰለጠነውን የ፩ኛ ኮር ''ቃኝና መሐንዲሥ'' ሰራዊት በደማቅ ሁኔታ አሥመርቋል። የምርቃት መርሐ ግብሩ ሲከወን የበላይ ዕዝ መሪዎች፣ የ፩ኛ ኮር ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የክፍለ ጦር እና ብርጌድ መሪዎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።
በመረቃ ስነ ስርዓቱ የአፋብኃ በላይ ዕዝ ከፍተኛ አመራርና የ፩ኛ ኮር አስተባባሪ ግብረ ኃይል አርበኛ አንተነህ ድረስ እና ሌሎች ከፍተኛ የኮርና የክ/ጦር አመራሮች ተገኝተው አስመርቀዋል።
ለተመረራቂዎች እና ለመላ ሰራዊቱ መልዕክት ያስተላለፈው አርበኛ አንተነህ ድረስ አማራዊ አንድነት የድል መሳሪያችን ነው ሲል አፅንኦት በመስጠት ንግግር አድርጓል።
ጋፋት ባንድ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች በማቅረብ የመርሃ ግብሩ ድመቀት የነበረ ሲሆን ተመራቂዎች በስልጠና ያገኙትን አቅም ተጠቅመው ለተሻለ ግዳጅ አፈፃፀም በአካላዊ፣አአዕምሯዊና ስነ ልቦናዊ ክህሎት ብቁ ሁነዋል ሲሉ የስልጠናው አስተባባሪዎች አረጋግጠዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
#የወምበርማ ጊዜዊመንግስት አሰተዳድር ከመምህራን ጋር ዉይይት አደረገ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድርስ ዕዝ 109 ኮር 88 ክ/ጦር ጊዜአዊ መንግስት በወምበርማ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ መምህራን ጋር ውይይት አካሄዱ።
በውይይቱም መምህራንም መንግስት ተፅዕኖ በማረግ ወደ ፋኖ በመሄድ በማስፈቀድ ትምህርት ጀምሩ በማለት የላካቸው መሆኑን በይፋ የተናገሩ ሲሆን የጊዜአዊ መንግስት
አመራሮችም ጥያቄቸዉን ተቀብለዉ አወያይተዋል ።
የመጡትን መምህራን ጥያቄም ፦
1ኛ የትውልድ ክፍት እየገጠመን ስለሆነ ህፃናት ትምህርት ይጀመር ?
2ኛ ከወምበርማ ወረዳ ከ 22 ቀበሌ 20ዎን ቀበሌ እናንተ ነዉ ? ምታስተዳድሩት ስለዚህ በእናንተ ቀጠና እናስተምር ?
3ኛ እኛም መታገል እንፈልጋለን ? እኛም አማራ ነን ፣ የአማራ ጭቆና ይገባናል ?
4ኛ መምህራን ከፓለቲካ ነፃ ነን እናስተምር ፍቀዱልን ?
የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥልቅ ዉይይት ተካሒዷል ።
በዉይይቱም የተገኙት አርበኛ ኢ/ር ሙሉዓለም በእዉቀት 109 ኮር የ88ኛ ክ/ጦር ጊዜዊ መንግስት ሰብሳቢ እና ፲ አለቃ መንግስቱ መርጊያዉ የ88 ክ/ጦር ም/ሰብሳቢ አሁን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰዉ ባለዉ የማንነት ጥቃት መመከት እና መደራጀት ፣ በተባበረ ክንድ መተጋገዝ እና ድል ማድረግ እንጂ ትምህርት ለመጀመር አስቻይ ሁኔታዎች የሉም ብለዉ ገልፀዋል ።
በተጨማሪም ስርዓቱ ት/ቤቶችን በድሮን እና በቡድን መሳሪያ አዉድሟቸዋል ፣ መፃሐፍት ተዘርፈዋል ፣ ተበትነዋል ፣ እንዲሁም ት/ቤቶችን ስርዓቱ ካፕ አድርጓቸዋል በዚህ ሁኔታ ማስተማር አይቻልም ።
ድርጅታችንም ባወጣዉ መግለጫ መሰረት ትምህርት ለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎች ተብሎ በዝርዝር መስፈርቶች ተጠቅሰዉ ነብር ነገር ግን ሁኔታዎችን ማሟላት አልተቻለም ብለዉ አክለዉ ተናግረዋል ።
የወምበርማ - ወረዳ -ጊዜዊ መንግስት ኮሚኒኬሽን
206ኛ ኮር ከጠላት ጋር በማበር በሰራዊቱ ስም የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅም በነበረው አባል ላይ እርምጃ ወሰደ።
ህዳር 26/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር ጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባል የነበረው ዳንኤል አዳሙ የተባለው ግለሰብ የጠላትን ተልዕኮ በመቀበል በሰራዊቱ መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ አፍራሽ አሉባልታዎችን በመንዛት፣ ለጠላት ወታደራዊ ሚስጢሮችን አሳልፎ በመስጠት፣ የሰራዊት አባላትን በማስከዳት፣ የአማራን ህዝብ ባህል፣ ሀይማኖት፣ ታሪክና እሴት የሚንድ አስተምሮን በማህበረሰቡ ዘንድ በማሰራጨትና በማስተማር፣ ከ25 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች አስገድዶ ገንዘብ በመቀበል እንዲሁም፦
በድርጅቱ የተሰጠውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከ,700 000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ የድርጅት ገንዘብ በመዝረፍ፣ ደብረ ማርቆስ ከመሸገው የአረመኔው ሰራዊት ጋር በጥቅም እና በንግድ በመገናኘት የጥይት የትጥቅ ሽያጭ ላይ የተሰለፈው ዳንኤል አዳሙ ከጠላት ካድሪዎች ማለትም--
1ኛ .ከደብረ ማርቆስ ከተማ መረጃና ደህንነት ሙሉሰው
2ኛ. ከደብረ ኤልያስ አስተዳዳሪ ሀብታሙ
3ኛ. በደብረ ኤልያስ ከተማ ከመሸገው የመከላከያ መረጃና ደህንነት ሰለሞን
የተሰጠው ተልዕኮ ጨርሶ እጅ ለመስጠት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን በተደረገበት ምርመራ ወንጀሉን ፈፅሞ የተገኘ መሆኑ ተረጋግጦ ግለሰቡም በሰራዊት ፊት ወንጀሉን ከጠላት ተልዕኮ ተቀብሎ መፈፀሙን በእምነት ክህደት ቃሉማረጋገጡን ተከትሎ 206ኛ ኮር የድርጅቱን ህግና ደንብ መሰረት በማድረግ በቀድሞው የጅበላ ሙተራ ሻለቃ አባል ዳንኤል አዳሙ ላይ እርምጃ ወስዷል።
ኮሩ በጠላት የተቀነባበሩ ወንጀሎችን በመመርመር ፈፃሚ አካላትን በመለየት በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ የጀመረ ሲሆን በትግሉና በሰራዊቱ መካከል እንዲገቡ ተደርጎ ተልዕኮ የተሰጣቸውን አባላት፣ አመራሮችና ፣የህብረተሰብ ክፍሎችን በመከታተል አቢዬታዊ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የትግሉን ህልውነት ለማረጋገጥ የሰራዊታችንን ደህንነት አጥብቀን እንከታተላለን ።
አዲስ ትውልድ !አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
ሀዘን የማይገስፀው ፡ ምክር የማይሰማ ፡ ቃለ መሀላ የማይጠብቅ ፡ ድንግርግር ምንግርግር የሆነ ሰው ይህችን ግራ እግር ማስረሻ ሰጤን አየው !
አረ በፈጣሪ እጅግ እጅግ ከየት ፈተው የለቀቁብን ፋጡር ነው!!
እስኪ ሃሳብ ስጡበት ቤተሰቦች ሰው እንዲት ትንሽ አማራነት ልብ አይኖረውም!!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የፖለቲካ ሞት !
አርበኛ ዘመነ ካሴ ሲታሰር ያኔ በጥዋቱ የህዝባዊ ኃይል ም/ል ሰብሳቢ የነበረው ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ መሪያዎቻችን ፣ ድርጅቱን እና በህዕቡ የተደራጀውን ኃይል በትኖ ከስርዓቱ በተሰጠው መኪና ደብረ ማርቆስ ዮኒቨርስቲ ትምህርት ሲጀምር ነበር ከአዲሱ ትውልድ አዕምሮ የወጣው ። የፖለቲካ ሞትን የተለማመደው ያኔ ነበር ።
በቅርቡ ሁሉም የአማራ ህዝብ አንድነቱን እየናፈቀ ባለበት እና የቤተ-አማራዎች ከአብይ ወንበር አስጠባቂ ኃይል መሣሪያ ፣ተተኳሽ ፣አልባሳቱን እና ቁሳቁሱን እየማረኩ እና ነፃ ቀጠናዎች እያሰፉ ባለበት ወቅት ፤ በዚህ ድልም መላው አማራ ያለምንም ልዩነት ደስታውን በሚገልፅበት ወቅት ካፒቴን ማስረሻ ግን በጣም የተናደድክ ነበር የምትመስለው ። ለዚህም ይመስለኛል ድርጅትህ እና ጓዶችህ ሳይፈቅዱ እና እውቅና ሳይኖራቸው በአጃቢህ ሞባይል የሚልኩህን ሰዎች ልብስ በመልበስ ደርዝ የሌለው ህዝባችንም ሰራዊታችንም የማይፈልገውን ፣ ጠላት ግን የሚጠቀበትን ሐሳብ ማንፀባረቁ የአንተን ካህዲነት ለማያውቁህ በደንብ የተገለጥክበት ጊዜ ነው ። በአንተ መግላጭ የሚቀር ድልም ሆነ አንድነት ግን የለም ።
ቤትህን ጠርገህ ቆሻሻውን ሳታቃጥል ወይ ሳትቀብር ከግቢ ውጭ ከጣልከው ምግብ ስትበላ ወይም በሰርክ ስራህ የቆሻሻው በሽታ አመጪ ባክቴሪያዎች ተመልሰው በ ዝንብ አማካኝነት እየመጡ ቤተሰቡን በሙሉ በሽታ ለማስያዝ ይሰራሉ ። እኛ ግን በመርህ ላይ የተመሠረተ የአማራን ህዝብ መብት እና ጥቅም በአከበረ መንገድ ጉዟችን እንቀጥላለን ።
ካፒቴን መጀመሪያ ጫካ የወጣው የአማራ ህዝብ ምን ጎደለበት ብሎ ነው ? ለአማራ ህዝብ ምን አሳክቶ ተመለሰ ? ....?
ዝና እና ነጭ ሻሽ በስሕትት ይጎድፋል ፣
ጋን ሙሉ ወተትም በአንድ ዝንብ ይደፋል ።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ !
አርበኛ ግሩም ምሳሌ
የአፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ም/የፓ/መምሪያ ሃላፊ
ሐውጃኖ ክፍለጦር የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሪፐብሊካን ጋርድ ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ::
ምስራቅ አማራ ኮር 1 ሐውጃኖ ክፍለጦር ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ከሪፐብሊካን ጋርድ ጋር በመፋለም ከ50 በላይ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በተጋድሎው ጠላት ከራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ተነስቶ በዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ወደ ሐውጃኖ ክፍለጦር ቀጠና ማጥቃት ያደረገ ሲሆን ክፍለጦሯ ሁለት ሻለዎችን ተጠቅማ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ከ50 በላይ ሪፐብሊካን ጋርድ ሙትና ቁስለኛ በማድረግና ቀጠናቸውን በማስከበር ጭምር ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
በርካታ ሃይሉ የተመታበት የፋሽስቱ አብይ አህመድ የመጨረሻ ምሽግ ሪፐብሊካን ጋርድ ከግራም ከቀኝም ተጨማሪ ሃይል በማያገኝበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ራያ አላማጣ ጥሙጋ ከተማ ት/ቤት ውስጥ በከፍተኛ ድንጋጤና ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ይገኛል::
በሌላ በኩል ለሪፐብሊካን ጋርዱ ተጨማሪ ሃይል ማስገባት ያልቻለው አገዛዙ ሰራዊት ከራያ ቆቦ ጮቢ በር ሆኖ ኦራል ላይ የተጠመዱ ሁለት ቻይና ሰራሽ 155 Mm መድፍ ወደ ራያ ቆቦ ባይባወ እና ኩቢ ቀረንሳ እያስወነጨፈ ንፁሃን ላይ ጉዳት እያደረሰ አምሽቷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 25/2018 ዓ.ም
በተጨባጭ እኔ በወቅቱ ስለ ማስረሻ ሰጤ ያረጋገጥኩት!!!
ማስረሻ ለብልጽግና የፈረመ 2014 ነው።
አርበኛ ዘመነ ካሴ ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ሆኖ ሳለ ሰኞ ቀን መስከረም/ጥቅምት 2014 ለነበረው ቀጠሮ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ተፈጥሮ ችሎቱ ለመገኘት የነበረውን ሁኔታ ብዙ አማራ የሚያስታውሰው ነው።
እኔም ያኔ ከአዋበል ወረዳ ገጠራማ አካባቢ ጓደኞቼን አሰባስቤ እሁድ ቀን ለሰኞው የፍ/ቤት ቀጠሮ ለመገኘት ጉዞ ጀምሬአለሁ።
መንገዱን ስናጣራ በማርቆስ ያለውን መንገድ እነ ኮማንደር አያልነህ ማዘጋታቸውን መረጃ ደረሰንና ጉዟችንን በቢቸና ሞጣ አድርገን ከእኩለ ቀን አካባቢ ጀምረን እየተጓዝን ስንሄድ ሞጣ ስንደርስ ከምሽቱ 1:00 ሆነብንና አድረን ጠዋት እንደርሳለን ብለን ሞጣ ማደሪያ ፈልገን ሁላችንም አንድ አካባቢ አልጋ ያዝን።
በተኛንበት ከሌሊቱ 7:00 እኔ ያለሁበት ክላስ ተንኳኳና ክፈት ተባልኩኝ ስከፍተው ወደ 15 አካባቢ ፖሊስ ከቦናል።ልብስ ልበሱ ተባልና ሁላችን ወደ ጣቢያ ተወሰድን፥ምን አጠፋን ስንልፀጉረ ልውጥ ናቹህ ተብለን ነው ነገ እናጣራና እንለቃቹሃለን ተባልን።በነጋታውም ማንም አልጠየቀንም።እንዲያ እንደሆንን ከሳምንት በላይ አለፈን።ለካ ያስያዙን የአዋበል ወረዳ ካድሬዎች ተደዋውለው ወደ አርበኛ ዘመነ ችሎት እንዳንሄድ ለማድረግ ነሯል።
በሗላ አማራጭ ሳጣ የፖሊሱን ስልክ ለምኘ ሞጣ የታሰርንበትን ቦታ ጠቅሸ መያዛችንን ገልጨ በfb ሁኔታውን ለሚያሳውቁ ንቁ አማራዎች ጉዳዩ እንዲደርስ አድርጌ በዛ ምክንያት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጉዳዩ ሲራገብ ያዩ የነቁ አራት አማራ ወንድሞቼም(ጀግናው በላይ እምቢያለ አጋዥ ፣ጀግናው ሻንበል ባለምላይ፣እሱባለው ብርሃን፣አንዱን ስሙን ለጊዜው ልተወው) ወዲያው ካለንበት ጣቢያ ደርሰው ለምን አሰራቹሃቸው ብለው ከአሳሪዎቻችን ጋር ተፋጠጡና ጣቢያው ትርምስምሱ ወጣና እኛ በዚያ አጋጣሚ ሁላችንም ክስ ተከፍቶብን በፖሊስ ተይዘን ወደ ፍ/ቤት ቀርበን በ 20,000 ብር ዋስ እንድንወጣ ሆነ።
እኛ ስንለቀቅ ስልካቹህ የሁላቹህንም እነ ኮማንደር ግርማ ደ/ማ ይፈልጉታል።እኛ እንልከዋለን እናንተ ሂዱ ተብለን በሌላው ቀን ዞን እነ ኮማንደር ግርማ ጋ ተሰባስበን ሄድን።
~ቢሮ ተቀምጠን ምክር መሆኑ ነው እናንተ እንዴት ህዝብ እየቀሰቀሳቹህ ከደጀን ጀምራቹህ እስከ ሞጣ ትሄዳላቹህ?
~ዘመነ ካልተፈታ እያላቹህ በfb ጭምር ዘመቻ ስታደርጉ ሰንብታቹህ ወደ ሞጣ መስመር ስትሄዱ ከመነሻቹህ ጀምረን እየተከታተልናቹህ ነበር። ~ዘመነ የጀመረውን ትግል እኛም እንደግፈዋለን ግን እርሱ ሲታሰር ምክትሉ አሁን የት እንዳለ ታውቃላቹህ አለኝ ኮማንደር ግርማ?
∞ጆሮዬን ቀስሬ ሳዳምጠው መሪው ሲያዝ ትግሉን ማቀጣጠል የነበረበት ምክትሉ ካፒቴን ማስረሻ ትግሉን ትቸዋለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ ብሎ ወረቀት በፊርማው አረጋግጦ ማስገባቱን መዠረጥ አድርጎ አሳየኝ፥አንተ በተለይ የእሳት እራት እንዳትሆን ተረጋጋ?ከወረዳ የሚደርሰን ስላንተ ከባድ ነው አለኝ ኮማንደር?
እውነት ለመናገር በጣም ውስጤ አዘነ፥ይኸ ጉዳይ እየከነከነኝ ነበርና ወደ ካፒቴን እህት አዲሴ ሰጤ ደውዬ ማስረሻ እንዴት እንዲህ ያደርጋል ብዬ ጮህኩባት፥እርሷም "ግዝሽ እመነኝ ከሚገሉት ብዬ ፊርማውን ተለማምጄ ያሳዩህን ወረቀት ያስገባሁት እኔ ነኝ፥ማስም ይኸንን አያውቅም ብላ ልታሞኘኝ ፈለገች?"ኸረ ባክሽ ብዬ ከዚያ ወዲያ ከእርሷም ጋር ያለኝ እምነት አቆመ።ማስረሻም ጓዱንም፣ትግሉንም፣እኛንም እንደካደን በተጨባጭ አረጋገጥኩኝ።
ሗላም ተጨማሪ ሂደቶችን ሳጣራ ማስረሻ መንግስት ከፍሎለት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ዘና ብሎ ይማራል።ሌላም ሁለት ታጋይ ነን ይሉ የነበሩ ስማቸውን ልተወውና ተከፍሎላቸው ደብረ ማርቆስ እየተማሩ እንደነበር ከቦታው ሄጀ አረጋገጥኩኝ።
እና ሰውዬው የበለፀገ ገና አርበኛ ወደ ሰባታሚት በገባበት ወቅት ነው።
እንጅ ያኔ እኔ ትግሉን ትቼዋለሁ ብሎ በፊርማው ወረቀት አስገብቶ?
ተከፍሎለት መንግስት በሚመራው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ዘና ብሎ ይማር ነበር ወይ?
ጠበቃ አስረስ ያን ሁሉ መከራ ተቋቁሞ አባይ ሸለቆ ዘብን ሲያደራጅ ማስረሻ ማርቆስ ዘና እያለ ነበር?
እና አሁን እኮ እኝኝኝ የምትሉ ምን ይሁን ብላቹህ ነው?
©ግዛቸው መንበር ህብስቴ
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
በዛሬው እለት የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰ ሲሆን ሰሞንኛ አጀንዳው ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 25/2018
አሳዛኝ ዜና!
አገዛዙ በአፋኝ ቡድኑ በኩል ከእስር ሲለቀቁ ለ6 ቀናት ያህል ያሳፈናቸውን እነ አቶ አብዱረኽማን አህመዲንን ጨምሮ ~ 3 የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስገድዶ ወደ ቂሊንጦ መለሰ ፤ አገዛዙ የፍትህ ስርዓቱን አደጋ ላይ ጥሎታል።
ኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ የፍትህ ሂደቱን አደጋ ላይ ጥሎታል ፤ ፍ/ቤት ውሳኔ በግልጽ እና በማንአለብኝነት በመጣስ ነጻ የተባቡና በዋስትና የተፈቱ ንጽሃንን ዳግም እያፈነ ነው ፤ በፍትህ ስርዓቱ ላይ ሕዝብን ጨርሶ ተስፋ እያስቆረጠ ነው።
አገዛዙ በአፋኝ ቡድኑ በኩል ከእስር ሲለቀቁ ለ6 ቀናት ያህል ያሳፈናቸውን እነ አቶ አብዱረኽማንን ~ 3 የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን ያለ ፍ/ቤት ትዕዛዝ አስገድዶ ወደ ቂሊንጦ መልሷቸዋል።
የዋስትና ክርክር ካደረጉት ከ19 ሰዎች መካከል የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ አብዱኽማን አህመዲን ፣ መኮንን ደሳለኝ እና ግዛቸው ታምር የተባሉ የግፍ እስረኞችን በተመለከተ ቋሚ የሕክምና ክትትል እንዳለባቸው አረጋግጦ እያንዳንዳቸው በ200 ሽህ ብር ዋስትና ሕዳር 18/2018 ከእስር እንዲፈቱ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መወሰኑ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ በማግስቱ ሲለቀቁ ከቂሊንጦ ማ/ቤት በር ላይ አገዛዙ እንደለመደው በአፋኝ ቡድኑ አሳፍኖ ወደ ፌ/ፖሊስ ወ/ም/ቢሮ ሜክሲኮ በመውሰድ ለቀናት አፍኖ እና አግቶ ካቆዬ በኋላ ሕዳር 24/2018 ወደነበሩበት ለ 2 ዓመት ገደማ ያለፍትህ ወደ ታሰሩበት ቂሊንጦ ማ/ቤት አሰገድዶ መልሷቸዋል።
አቶ አብዱራኽማን በቂሊንጦ ዞን 4 ሲገቡ ፣
ግዛቸውና መኮንን ደግሞ ወደ ዞን ሁለት 10ኛ ቤት እንዲገቡ ተደርጓል ተብሏል ።
ለሕዳር 30/2018 በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ቀጠሮ እንዳላቸው ታውቋል፡፡
ፍትህ ለአማራ!
ፍትህ ለሁሉም!
(አውሎግሶን አንድነት ፣ ሕዳር 24/2018)
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር
በዛሬው እለት የአገዛዙ ጥምር ሀይል መነሻውን ከአለፋ ወረዳ ሻሁራና አፀደማርያም ከተማ ፣ ከሰሜን አቸፈር ሊበን ከተማ እና ከቋራ ወረዳ ደለጎ በማድረግ ወደ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የተንቀሳቀሰ ሲሆን ሰሞንኛ አጀንዳው ፋኖን በየቀጠናው አፅድቻለሁ በህዝቡ ላይም የተሻለ ቅቡልነት አግንቻለሁ እያለ ቅዠት ላይ ያለ ቢሆንም አሁን ላይ በጨለማ በመንቀሳቀስ የአርሶ አደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ዘረፋ ለመፈፀም አቅዶ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ፣ ማህበረሰቡ ከፋኖ ሀይል ጋር መረጃ ቀድሞ በመለዋወጥ ከፋኖ ጎን በመሆን በሁሉም ቀጠና ማለትም በአለፋ ወረዳ እየተንቀሳቀሰ ያለውን የፋሽስት ሰራዊት አድዋ ክ/ጦ ከማህበረሰቡ ጋር በመጣመር የጠላትን እቅድ ከማክሸፍ ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ሲቻል ከደለጎ ከተማ ተነስቶ ወደ ኮሩ ቀጠና የገባው በቋራ ኦሜድላ ነብሮ ብርጌድ አማካኝነት በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ በትር ማሳረፍ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ የፋኖ ሀይል አሰላለፉን በመቀያየር የአገዛዙን ሰራዊት ከበባ ውስጥ በማስገባት መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።አውደ ውጊያው አሁንም እንደ ቀጠለ ይገኛል አህዛዊ የድል ዜናዎችን በቀጣይ የዜና ጥንቅራችን የምናቀርብ ይሆናል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ፋኖ መ/ር አስተውል አምሳሉ
ህዳር 25/2018
#ሰበር_ዜና_ግሽ_አባይ_ሰከላ ‼
#የብልፅግና_ባንዳ_ስሩ_ተቆረጠ_በሰከላ‼
በአፋብኃ ቴዎድሮስ እዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ሰከላ ላይ በወሰደዉ እርምጃ የሰከላ ወረዳ አስተዳድር ዋና ባንዳ #ይልማ_ጥላሁን ጨምሮ ከሁለት ደርዘን በላይ የሚነሻና የመከላከያ አባላት ተወግዷል።
የስቦ መምታት ጥበበኞች 44ኛ ክፍለ ጦር ጠላትን #ከሰከላ #ከማንኩሳና #ከቡሬ በመተንኮስ ወደ ቀጠናቸዉ ድረስ ሰተት አድርገዉ በማስገባት #ሰከላ ላይ የቀረዉን ሰፈር ጠባቂ፣ ዘራፊ ሚኒሻና ሆድ አደሩን የብልፅግና አመራር መሃል ሰከላ ላይ አራምጠዉታል።
"ፋኖን ባለበት አሳድጄ አጠፋዋልሁ" እያለ ሲፎክር የነበረዉ ዋና አስተዳድር እና አምስት ሚኒሻ ሲማረክ ብዛት ያለዉ ሰራዊት ደግሞ እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።
አረመኔው ቡድን በአጉትና ባሽፋ ከማንኩሳ ፔንፔ፣ዘ_23 ከሰከላ ግትልትል ሰራዊቱን በማስከተል #ምላስና #ብልት በመቁረጥ የስድስት ንፁሃንን ህይወት በቀጠፈበት ቀጠና እየተልከሰከሰ የባህር ኩበት በሆነበት ሰሃት ጀግኖቹ የ44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች ሰከላ ከተማ የሚገኘውን የብልፅግና ጦር በመቀጥቀጥ #12 ክላሽንኮፍና በሺዎች የሚቆጠር ተተኳሽ ማርኳል።
ከዚህ በተጨማሪ መንግስታዊ ስርዓት አስቀጥላለሁ በሚል ሃሳዊ ህልም ሲገለገልባቸዉ የነበሩ ኮምፒወተሮችና ላብቶቦች ማተሚያ ማሽኖች ሲማረኩ፤ የወረዳዉ መገልገያ ተቋም በሙሉ ፓትሮሎችን ጨምሮ ከጥቅም ውጭ ሁኗል።
ከተማዋ ላይ የተሰገሰጉ በመረጃነት የሚያገለግሉ እንቁላል ቀቃይ ባንዳዎች መዉጫ መግቢያ ጠፍቷቸዉ ብዙዎቹ ተሸኝተዋል።
ቁሞ መግጠም ያልቻለዉ አረመኔ ቡድን ከተለያ የቦታ እያፈነ እስረኛ ያደረጋቸዉን የሰከላ ወረዳ 25 ንፁሃን እስረኞችን ጭምር ከአረመኔዉ መንጋጋ ማስለለቅ ተችሏል።
በተደጋጋሚ ቀጠናዉን እየረገጠ የጣለዉን እየጣለ ቁስለኛዉን ጭምር ሳያነሳ ወደ ቆፈረው ጉድጓድ የሚሮጠዉ አረመኔው ቡድን ዛሬም እንደልማዱ ከግሽ አደባባይ ጀምሮ እስከ ድንጋይ ገበጣ ሩጦ በመግባት ህይወቱን ሊተርፍ ችሏል።
ዛሬ ህዳር 25/2018 ዓ.ም 44ኛ ክፍለ ጦር ባደረገዉ ትንቅን በተደጋጋሚ ጀብደኝነቱን ያስመሰከረ፣ የጠላትን ቅስም የሰበረ፣ ብዙ ባንዳዎችን ቀልብ የቀየረበት፣ የድል ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።
#በተደጋጋሚ_ተናግረናል_ጀምረናል_እንጅ_አልጨረስነዉ‼
#ላናሸንፍ_የጀመርነዉ_ትግል_የለም_ድልችን_ቅርብ_ነዉ‼
የ44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት
ፋኖ አለበል አወቀ።
