fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 138
مشترکین
+724 ساعت
+2087 روز
+1 20130 روز
آرشیو پست ها
ለአባት አርበኞች ጦር ስልጠና ተሰጠ‼️ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ታህሳስ 21/2018 ዓ/ም የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር አመራሮችና የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራር በወረዳው ከሚገኘው የገደብ ቀበሌ አባት አርበኞች ስልጠና ተሰጥቷል ። በስልጠናውም፦ _ ስለ ፋኖ ትግል መሰረታዊ ምክንያቶች _ ስለ ፍትህ አሰጣጥ እና ስለቀበሌ አደረጃጀት _ ስለ አዲሱ ኮርና ክፍለ ጦር አደረጃጀት _ ትግሉ ስለደረሰበት ደረጃ በሰፊው ግንዛቤ የተሰጠ ሲሆን የተመረጡት አመራሮች በቀጣይ በቁርጠኝነት ፣በግልፀኝነትና በታማኝነት ድርጅታቸውንና ህዝባቸውን እንደሚያገለግሉ ቃል ገብተዋል። ህዝባቸውን እና ራሳቸውን ከጠላት ለመጠበቅ ከቲም ጀምረው እስከ ሻለቃ ድረስ በመደራጀት የጠላት መምጫ በሮችን በመለየት የሌሊት ደፈጣ በመስራት መተሳሰር እንዳለብን የጋራ መግባባት ተደርሷል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም የቴዎድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት

ታህሳስ 21/20018ዓ.ም የመንገድ እገዳው መነሳቱን ስለማሳወቅ የአማራ ብሔራዊ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ኛ ክፍል  ከዚህ በፊት            ➡️ከዱርቤቴ_ቁንዝላ ደለጎ                       ➡️ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ                        ➡️ከዱርቤቴ ዝብህስት ወገዳ                         ➡️ ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ                         ➡️ከዱርቤቴ _ዲላሞ ልሁዲ መንገዶች ተዘግቶ እንደ ነበር ይታወቃል አሁን መንገዶች የተዘጉባቸው ምክንያቶች የተወሰኑ ስለተቀረፉ እና የመጪውን በአል ምክንያት በማድረግ ከነገ ማለትም ታህሳስ 22/2018  ዓ.ም ጀምሮ በቦታዎች ላይ የጣላቸዉ የእንቅስቃሴ ገዶች የተነሱ መሆኑን ማረጋገጥ እንወዳለን ትዛዙን አክብራችሁ እገዳዎችን በትግስት ስጠባበቁ የነበራችሁ አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ባለሀብቶች ና መላው ህዝባችንን አሳያችሁት ጨዋነት ማመስገን እንወዳለን ። ፋኖ ምስጌ ዘድንግል የ 55 ተኛ ክፍል ጦር የህዝብ  ግንኙነት ሀላፊ

ትግላችን የጌቶች እራት ግብዣ ሳይሆን፣ የሕዝብ ሕልውናን የማስከበር መራራ ጉዞ ነው። ታላቁ አብዮተኛና የታጋዮች መሪ ማኦ ሴቱንግ እንዳለው "አብዮት የጌቶች እራት ግብዣ አይደለም!" አብዮት ጥልፍ የመጥለፍ ያህል ቅጥ ያጣ ትዕግስትም አይደለም። አብዮት በግፈኞችና በጭቁኛች መካከል የሚደረግ፣ ሕይወት የሚከፈልበት፣ ደምና ላብ የሚፈስበት የሕልውና ጦርነት ነው። ዛሬም በሀገራችን እያካሄድነው ያለው ትግል፣ በምቾት ወንበር ላይ ተቀምጦ የሚነጋገሩበት "የሊቃውንት ክርክር" ሳይሆን፣ መጪውን ትውልድ ከባርነት ቀንበር ለማውጣት የሚደረግ መሪር ፍልሚያ ነው። አምባገነኑ አገዛዝ ሰሞኑን በትግላችን ሂደት ውስጥ የተከሰቱ ጥቃቅን ስህተቶችን፣ የሰው ልጅ ባህርይ የፈጠራቸውን ድክመቶች መዝዞ እና የውሸት ታሪኮችን አቀናብሮ ፣ ሌት ተቀን በሚዲያዎቹ የፕሮፓጋንዳ ማሽን ሲያጮህ እያየን ነው። ይህ ድርጊት "ሌባ ቀድሞ ይጮኻል" እንደሚባለው ነው። በየቀኑ በድሮንና በከባድ መሣሪያ የንጹሐንን ደም እንደ ጎርፍ የሚያፈስ አገዛዝ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ እናቶችን ለረሃብና ለስደት የዳረገ አገዛዝ፣ ታሪክ የማይረሳውን የጅምላ ግድያ በሕዝባችን ላይ የፈጸመ አገዛዝ... ዛሬ ስለ ሰብዓዊነትና ስለ ሞራል ሊያስተምረን መሞከሩ በታሪክ የታየ ትልቁ የቀልድ ድራማ ነው። ሰፊውና የተከበረው ሕዝባችን እንደሚያውቀው፤;በትግል ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ስህተቶች የትግሉ ዓላማዎች አይደሉም። እነርሱ የጦርነት መራራ ገጽታዎች ናቸው። በእሳት መሐል አልፎ አበባን ሳይጠውልግ ማምጣት አይቻልም። የእኛ ዓላማ ሕዝባችንን ነፃ ማውጣት እንጂ ሕዝባችንን መበደል አይደለም። በስሜት፣ በስህተት ወይም በሁኔታዎች አስገዳጅነት የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ካሉ፣ እነዚህ ድርጊቶች የትግላችንን ዓላማ መነሻ መድረሻ እንዳልሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እኛ የእነዚህ ድርጊቶች ደጋፊዎች ሳንሆን፣ ስህተቶቻችንን የምናርም፣ ጥፋተኞችን የምንቀጣና ወደፊት የምንገሰግስ የሕዝብ ልጆች ነን። በአውሮፓ፣ በአሜሪካም ሆነ በአየርላንድ የታዩት ታላላቅ የነፃነት ትግሎች ሁሉ እንዲህ ዓይነት ፈተናዎችን አልፈዋል። ታጋዮች በስህተት የፈሰሰን እንባ በማበስ ነው ድልን የተቀዳጁት። አገዛዙ እኛን አቅፎና ደግፉ ከያዘን እንስፍስፉ ሕዝባችን ሊነጥለን ቢሞክርም፣ እኛ ግን ከሕዝባችን ጋር በጥብቅ የተሳሰርን ነን። የሰው ልጅ ስህተት ይሠራል። አምባገነኖች ግን ግፍን "መንግሥታዊ ፖሊሲ" አድርገው ይሠሩታል። በእኛና በእነሱ መካከል ያለው ልዩነት ይህ ነው። ስለሆነም፤ ለአስተዋዩና ጥበበኛው ሕዝባችን የምንለው ነገር ቢኖር፤ የአገዛዙን የፕሮፓጋንዳ መጋረጃ ቀደህ እውነተኛውን የታጋይ ልጆችህን ዓላማ እይ። ድክመታችንን አርመህ፣ ስህተታችንን መክረህ ከጎናችን ቁም! ካንተ የተለየን አይደለንም፤ እኛ የአንተ ቁጣና የነፃነት ፍላጎት ውጤቶች ነን። ዲሲፕሊን የድላችን መሠረት ነው። የሕዝባችን ጭቆና እንቅልፍ የሚነሳችሁ ታጋዮቻችንም፤ እያንዳንዱ ጥይትና እያንዳንዱ ርምጃ የሕዝብን ክብር የሚጠብቅ ሊሆን እንደሚገባ ለአፍታም መዘንጋት የለብንም። ጠላት የሚጠቀምበትን ክፍተትም መፍቀድ አይገባንም። በፕሮፓጋንዳ የምትገነባው የሐሰት ግንብ፣ በሕዝባዊ ጽናት መናዱ አይቀሬ ነው። የንጹሐን ደም የጮኸብህ አንተ እንጂ፣ ለነፃነት የወጣው ታጋይ አይደለም። ትግላችን የጌቶች እራት ግብዣ ስላልሆነ መስዋዕትነት ይኖረዋል፤ መስዋዕትነቱ ግን ወደ ታላቅ ድልና ነፃነት የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ነው። እንፅና! © Estibel Alemu Zerihun

የአገዛዙ ግፍ! የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አራጋው እንዳለ መኖሪያ ቤትን በብልጽግና አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ትናንት ታህሳስ 20/2018 ዓም በ
+3
የአገዛዙ ግፍ! የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ም/የፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አራጋው እንዳለ መኖሪያ ቤትን በብልጽግና አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ትናንት ታህሳስ 20/2018 ዓም በዶዘር አፍርሶታል። ልጆቹንና ሚስቱንም ሜዳ ላይ በትኖ የቤት እቃውን በሙሉ ጭኖ በዘረፋ መውሰዱንም የአይን እማኞች ተናግረዋል። 1. ሀብትሸት ሞገስ … የዳባት ከተማ ከንቲባ 2. ⁠ሻለቃ ዳንኤል ታረቀኝ… 3. ⁠አዲሱ ሙሌ … የዳባት ከተማ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ የቤት ማፍረሱን እና ዘረፋውን እንደፈፀሙና እንዳስፈፀሙ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

እጅ ሰጠ የተባለው ሀብታሙ ጌታሁን ማን ነበር? ══════════════❁✿❁══════════════ (ታኅሣስ 21/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ) የሀብታሙ ወደ ብልጽግና መሄድ ለትግላችን ግዙፍ እንቅፋን ማንሳት ነው‼ #ሀብታሙ_ማለት፦ ፩. አስቀድሞ በፋኖ ምሥረታ ግለሰቡ "የሥራ አስፈፃሚ አባል" ሆኖ ሲመረጥ "ብልጽግና ዋና አስተዳዳሪ እናደርግሃለን" የሚል ቃል ገብቶለት ስለነበር በፋኖ የተሰጠውን ሓላፊነት አልቀበልም ብሎ የብልጽግናን ቀቢፀ-ተስፋ ሲጠባበቅ የነበረ፤ ፪. ሁሉም ሥራ ለቅቆ በግልጽ የግምባር ትግል ሲጀምር የብልጽግና ዳረጎት በመዘግየቱ ወደ ትግላችን የተቀላቀለ ባለ ሁለት ልብ፤ ፫. በር ሚካኤል ቀበሌ በርካታ የግለሰብና የቀበሌ ሀብት ዘርፎ ማኅበረሰቡን ሲያማርር የነበረ፤ ፬. ከዘለቀ አላምረው ሆቴል ከግብር-አበሮቹ ጋር ተመግቦ አልከፍልም በማለት ቤቱን በጥይት መትቶ የወጣና በብርጌዱ የውስጥ አሠራር የተቀጣ፤ ፭. በትግላችን ውስጥ ገብቶም በገበዘማርያም ከተማ የባንዳ ሀብትና ንብረት እንዲወድም በማድረግ ፋኖን ከማኅበረሰቡ ለመነጠል ሙከራ ያደረገ፤ ፮. ማክሰኝን ላይ ተደብቆ ሕገወጥ ቀረጥ በመቅረጥ እና ወፍጮ ቤት ሳይቀር ከእናቶች መቀነት ሲዘርፍ በገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ተወንጅሎ በቅጣት የታለፈ፤ ፯. በተደጋጋሚ አስገድዶ መድፈር የተከሰሰ፤ ፰. የተወሰኑ ግብረ-አበሮቹን በመያዝ ከብርጌዱ ይሁንታ ውጪ የዓባይ ባንክ ሠራተኞችን በማገትና በመደብደብ ባንኩ ከወረዳችን ቅርንጫፉን ዘግቶ እንዲወጣ ያደረገ፤ ፱.በፋኖ ጊዜያዊ መንግስት የመዘጋጃ ቤት ሓላፊ ሁኖ ተመድቦ ለሕገ-ወጥ ቤት ግንባታ እና ለኮንቴይነር ብር እየተቀበለ ሲያሰራ ተደርሶበት ከሓላፊነቱ በቅጣት የተሰናበተ፤ ፲. ኀይል አፍርሶ ወደ በረሀ ሊበትን ሲሰናዳ ተይዞ በጥበበኛ መሪዎች እጅ ገብቶ ቅጣቱን ያገኘ፤ ፲፩. ችግሩ በአስተዋይ መሪዎቻችን የተፈታ ቢሆንም "የበረሓ ፋኖ እና የቋሪት ፋኖ" በማለት ልዩነት እንዲፈጠር በማድረግ 2016 ዓ.ም ላይ 3ኛ ሻምበል በሻለቃ የኔዓለም ላይ ፊቷን እንድታዞር ብጥብጥ ያስነሳ ብሎም የተወሰኑ ጀግኖቻችንን በማማረር ከትግል ያስወጣ፤ ፲፪. ከብልጽግና ተልኮ ተቀብሎ "በተደጋጋሚ የተወነጀልሁ የደጋ ዳሞት ተወላጅ ስለሆንሁ ነው" በማለት ሁለቱን ወንድማማች ብርጌዶች እና የብርጌዶችን መሪዎች ለማጋጨት የሞከረ፤ ፲፫. በእነዚህ ተደራራቢ የባንዳነት እንቅስቃሴዎቹ ለስድስት ወራት ታስሮ እስከ መረሸን የሚያደርስ ጥፋት መኾኑ ቢታወቅም ምሕረት ለማድረግ በማይሰስቱ አስተዋይ መሪዎቻችን "ነገ ይማራል" ተብሎ በድጋሜ ዕድል ተሰጥቶት ወደ ትግል የገባ፤ ፲፬. ከገባ በኋላ ከሕወሓት እስከ ብልጽግና በነበረው የአመራርነት ልምድ በአንዳንድ ቀበሌዎች የአደረጃጀት መዋቅር እንዲያስተካክል ተመድቦ ለውስን ጊዜያት የሠራ፤ ፲፭. በመጨረሻም ቆርቦ ባገባት ሚስቱ ላይ የጓዱን ሚስት አስገድዶ የመድፈር ሙከራ ሲያደርግ ቂጡን ተመትቶ ወደ አንድ ዓመት ያኽል ተኝቶ የከረመ፤ ፲፮. በቅርቡ ወደ ብልጽግና ለመግባት ድርድር ላይ እንደነበር ያወቁ ቀኘዎቻችን "እየተደራደረ ነው ፥ ያዙት" ብለው ሲወራበት "ሀብታሙ አልገባም ብለህ ፃፍልን" በማለት ለክፍለጦራችን የሕዝብ ግንኙነት ጥያቄ ያቀረበና ክትትል ሲደረግበት የነበረ፤ ፲፯. አሁን ግን ሲጠረጠርበት የነበረውን የባንዳነት ሥራ በግልጽ ያስመሰከረ ነው። ▶ ነገር ግን የብልጽግና ሚዲያዎች እንደሚሉት የዐፋብኀ ከፍተኛ አመራር ሳይሆን፤ መዋቅራችን አሽቀንጥሮ ከወረወረው አንድ ዓመት የኾነው እና በግሉ ለረዥም ጊዜ ሲደራደር ቆይቶ ዛሬ በይፋ የገባ ነው። ▶ ሲገባም ወይበይኝ ቀበሌ በግብርና ሥራ ይተዳደር ከነበረ የግል ታጣቂ የእናቱ ልጅ ጋር ገባ እንጂ፤ አንድም የድርጅቱ አባል እጅ አልሰጠም።

የአለማችን ቢሊየነርና የተንደላቀቀ የቅንጡ ኑሮ በየትም የአለም ክፍል መኖር እየቻለ ሂሳብ እንወራርዳለን ብለው ሲመጡ ሂሳቡን ቀድሞ የሠራው ወርቁ አይተነው ከ100% 101% ይገባዋል የምትሉ 101% እያላችሁ ፃፉለት!! የበላይ ዘር የአምሐራቱ ልጅ!!

'' ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በእስር ያሉ ሰዎች በይቅርታ ሊፈቱ ነው!” በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ “  ፍፁም ሐሰተኛ ነው! ” ሲሉ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ አስታውቀዋል! ጠበቃ ሰለሞን ከዚሁ ጋር አያይዘው - የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ በክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ የቀረበውን ምስክር ተከትሎ በዐቃቤ ህግ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየት ለመስጠት ለጥር 8 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱንም አስታውሰዋል! ©ዘር ይሁን ገሠሠ

#አሳዛኝ ዜና     #የአማራን ህዝብ ጀኖሳይድ እዬፈፀመ የሚገኘው የብልግና ሰራዊት በትናንትናው 19 የአማራ ተወላጆችን ሰብል በሚሰበስቡበት ቦታ ማለትም #በማንቡክ ወረዳ ልዩ ቦታ #ደቡብ#ኮከን  በሚባል አካባቢ በጅምላ የጨፈጨፈ ሲሆን አረመኔው የብልፅግና ሰራዊት  የጭካኔ ጥጉን ያሳየ አማራን ከምድረ ገፅ አጠፋለው ብሎ የተነሳበትን አለማ መግልፅ ያሳዬበት ነው።በግፍ ከተገደሉ የአማራ ተወላጆች ውስጥ:-                          1ኛ መልካሙ ባይህ..........የወምበርማ ወረዳ ተወላጅ                          2ኛ የሽዋስ አያሌው..........የወምበርማ ወረዳ ተወላጅ እና ለጊዜው ስማቸውን ያልደረሰን ወደፊት በስም ዝርዝር እና በፎቶ የምናመጣቸው17 የአማራ ተወላጆች በአንድ ጀምበር በግፍ ገድለዋቸዋል።              #የመጨረሻ መልክት የአማራ ህዝብ ሆይ በወለጋ፣በመተከል እና መሳሰሉት አሁንም የዘር ማጥፋት ዘመቻ#እንጀራ አንበላውም እያሉ ፀረ አማራ ከሚያቀነቅኑ እንደ #አበባዬሁ ዴሜ  እስከ ኦህዴድ ብልፅግና ድረስ ሊጨርሱህ እያወጁብህ ስለሆነ ራስክን ከ#ፋኖ ጎን በማሰለፍ#ነፃነትክን በክንድህ አስከብር። አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ             ©ዮሴፍ ሐረገወይን ታህሳስ 21/4/2018 ዓም

206ኛ ኮር የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው ለ9 ወራት መረጃ ሲያቀብሉ በነበሩ ባንዳዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ። ታህሳስ/2018 ዓ.ም ቃል ኪዳን እና ሙያነሽ ትውልዳቸው በደብረ ኤልያስ ወረዳ የቀጋት እና ጓይ ቀበሌዎች ሲሆን በጎዛምን ወረዳ የማይ አንገታም ቀበሌ ተወላጅ የሆነችው መልካም ጭምር በአረመኔው ሰራዊት ለመረጃ ደህንነት ተመልምለው በተለያዩ ቀጠናዎች መንቀሳቀስ የጀመሩት በመጋቢት 2017/ ዓ.ም መሆኑን ተናግረዋል። በመከላከያ ሰራዊት የመረጃ እና ደህንነት ክፍል በ፲ አለቃ ሲሳይ፣በሚኒሻ አስተባባሪዎች ዘውዱና ሀብቴ አማካኝነት የመረጃ ልውውጥ የሚያደርጉት ሶስቱ ሴቶች በደብረ ኤልያስ ወረዳ ፣ጓይ፣ማርዘነብ፣የቀጋት፣ገነት ከተማ እና ደጎልማ ከተማ የፋኖ ካምፕ አለበት በተባለበት ሁሉ እየተዘዋወሩ መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበር ተረጋግጧል። በደብረ ኤልያስ ወረዳ በረሀማ አካባቢ ጠሸት በረሀ፣ሰይጣን መልካ በረሀ፣አሱላ ገዳ በረሀ በመውረድ ባለሀብቶች ባዘጋጁት የሰራተኞች ካምፕ ሰርጎ በመግባት የሰሊጥ አጫድ እና የሰራተኞች ምግብ አብሳይ በመሆን በረሀውን በማሰስ  መረጃዎችን ካሰባሰቡ በኋላ ደብረ ኤልያስ ከተማ በመመለስ ለጠላት ግብዓት ሲሰጡ እንደነበር ተጠርጣሪዎች በአንደበታቸው መስክረዋል። ባለፉት የክረምት ወራት ጀምሮ በጓይ በረሀ የሚገኘውን የስላሴ አንድነት ገዳምን አስሰው መረጃ እንዲያመጡ ከዘውደ፣ ፲ አለቃ ሲሳይና ፣ከሀብቴ  የተሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው የፋኖን ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ ካምፕ እና ምሽግ በማፈላለግ ከወራት በላይ በገዳሙ አቅራቢያ ተደብቀው ሲሰልሉ እንደነበር አስታውቀዋል። የመልመያ መስፈርቱን ፆታዊ ግንኙነት በማድረግ አስነዋሪ ተግባራትን በመፈፀም የመረጃ ሰዎችን የሚያሰማራው የአረመኔው የመረጃ ቡድን በተጠርጣሪዎች ላይ ተመሳሳይ ተግባር ይፈፅሙ እንደነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት ሴት የደህንነት አባላት ገልጸዋል። በደብረ ኤልያስ ወረዳ የምትንቀሳቀሰውን የቀስተ ደመና ሻለቃን ለማጥቃት ያመች ዘንድ የተሰማሩ እነዚ ሴቶች ከመጋቢት 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 2018/ ዓ.ም ባሉት ዘጠኝ ወራት በደብረ ኤልያስ፣ደብረ ማርቆስ አማኑኤል ከተሞች ሰፊ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በጎዛምን ወረዳ የሚንቀሳቀሰውን የጅበላ ሙተራ ሻለቃ ለማስመታት በማይአንገታም፣ደምባ፣ቸርተከል፣እና ሊባኖስ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ መረጃ ሲያቀብሉ እንደነበረም ተረጋግጧል። -በሀብታሙ እሱባለው -----የደብረ ኤልያስ ወረዳ አስተዳዳሪ -በደምስ አለህኝ ----በደብረ ኤልያስ ወረዳ መረጃና ደህንነት ኃላፊ -መለሰ ኃይሉ-----የደብረ ኤልያስ ወረዳ ሚኒሻ ጽ/ቤት ኃላፊ - የ32ኛ ክ/ጦር አዛዥ በኮረኔል አለምሰገድ አስተባባሪነት የሚመራውን የጠላት የመረጃና ደህንነት ሰንሰለት ተከትሎ ፣ሴቶችን በልዩነት ከአድማ ብተና፣ከሚኒሻና ከአረመኔው ሰራዊት አባላት ጋር ፆታዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ በጀት በመመደብ ከተመለመሉት በርካታ ሴቶች መካከል የሚገኙት፣ቃልኪዳን፣መልካምና  ሙያነሽ ከጠላት የሰራዊት አባላት ጋር የፈፀሙት አስነዋሪ ድርጊት ለጠላት አገልጋይ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል። በደብረ ኤልያስ ከተማ እና ዙሪያ ቀበሌዎች በርካታ ሴቶች ፣የቤት ሰራተኛ፣ የቀን ሰራተኛ፣  አብሳይ፣ልብስ አጣቢ፣ሻይ ቤት የሚሰሩ በመምሰል የጠላትን ስምሪት ተቀብለው እንደሚንቀሳቀሱ የተናገሩ ሲሆን። የአረመኔው ሰራዊት አሰማርቷቸው ለ9ወራት  በተለያዩ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው በርካታ ስራዎችን ለጠላት ሲፈፅሙ የነበሩት እነዚህ ተጠርጣሪዎች በአለቆቻቸው ትዕዛዝ የቀስተ ዳመና ሻለቃ የምትሰጠውን የፋኖ ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱ ምልምሎችን በመመሳሰል በስልጠናው ተካተውለምዝገባ በቀረቡበት ወቅት በተደረገው ጥብቅ ክትትል በመጨረሻም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተጠርጣሪዎች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጠዋል። ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል አስፈላጊውን ምርመራ ያደረገው 206ኛ ኮር ባገኘው የስልክ ማስረጃ፣ የሰው ምስክርነትና ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን መፈፀማቸውን ማመናቸውን ተከትሎ የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው የወገንን ኃይል በመመረጅ ላደረሱት ክህደት፣በሰራዊቱ እና በህዝቡ ለደረሰው የህይወት፣የሀብት እና ንብረት ጉዳት ተጠያቂ በመሆናቸው  ሌሎችን ያስተምራል በማለት በተጠርጣሪዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል። የትግሉን እና የሰራዊቱን ደህንነት ማስጠበቅ ተቀደሚ ተግባር አድርጎ የሚንቀሳቀሰው 206ኛ ኮር የጠላትን ተልዕኮ ተቀብሎ የሚንቀሳቀስ ማንኛውንም አካል ተካታትሎ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ! የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ድል ለተገፋውአማራ ! ድል ለጀግናው ፋኖ 💪!!

ጉዳያችን አማራዊ ነው ስንል...# አማራ ሁነን በተግባር በመገኘት ነው!! የበላይ ዕዝ ...ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የበላይ ዕዝ ...ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናው
ጉዳያችን አማራዊ ነው ስንል...# አማራ ሁነን በተግባር በመገኘት ነው!! የበላይ ዕዝ ...ዋና ሰብሳቢ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የበላይ ዕዝ ...ም/ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናው

ሰበር ዜና የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር የዙፋን ጠባቂውን ከፍተኛ አመራር ከነ አጃቢዎቹ ፓትሮል ላይ ባለበት ጥቃት በመፈፀምና ያጀበውን ዙ23 በማቃጠል ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር ታላቅ ድልን ተጎናፅፏል! የአውደ ውጊያ ሜዳውን ከግሸን መገጠያ እስከ ተሪ ተራራዎች በዘረጋው በረሀ ላይ  ከፍተኛ አመራሩ፤ዙ-23ቱና የፓትሮሏ ሹፊር እድሁም በርካታ መከላከያ ተደመሰሱ:: ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም ፓትሮል ላይ የነበረ ከፍተኛ አመራር ሲቆስል የፓትሮሏ ሹፌር ተደምስሷል።ሰባት የመከላከያ ሰራዊቶች እድሁ ሲሸኙ ዘጠኙ ከባድ ቁስለኛ ሆነው ሌሎች ሶስቱ መካከለኛ ቁስለኛ ተደርገዋል። አንድ ዙ-23 ሙሉ በሙሉ በድሽቃ ተመቶ ተቃጥሏል። አመሻሽ ላይ በተደረገ አውደ ውጊያ የአካልና ቁስ እድሁም የሞራል ኪሳራን ያስተናገደው በህይወት የተረፈው የብርሀኑ ጁላ ቅጥረኛ ሰራዊት በረሀ ለበረሀ ፈርጥጦ በየ ጥሻው ተሸርኩቶ ነፍሱን አትርፎ ወደ ተንታ ወረዳ ሌቱ ሲነጋ የፈረጠጠ ሲሆን ሌሎቹ "ይዘገያል እንጅ አህያ የጅብ ናት" የሚለው ቢህል የገባው እጁን ለፋኖ እየሰጠም ይገኛል። የምርኮ በረከት የሆኑት የጦር መኮነኖች ኮሎኔሉና ሻለቃ መሪው ባጋጠማቸው ሞትና ውድመት የተነሳ በከዘራ ሲዛለጡም አድረዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም

#INBOX የጀኔራል ባጫ ደበሌ ነገር መቋጫ አግኝቷል'' ብቻ ያሳፍራል፣ አጭር ነች አንብቧት'' አምባሳደሩ ጀኔራል የተናገረው ይህን ማለት ፈልጎ ነው ጀነራል ባጫ ደበሌ "የጦርነት አስከፊነት የሚያውቀው የሞተ ሰው ብቻ ነው" ያለው የአንድ ታዋቂ ፈላስፋ በስሙ George Santayana የተባለ የተናገረውን እናገራለው በማለት በትክክል ሳይተረጉመው ወይም ገልብጦ ተርጉሞት ነው። ፈላስፋው ያለው እንዲህ ነው "only the dead have seen the end of war" ይህም ሲተረጎም የጦርነትን መጨረሻ ያየው ወይም የሚያየው የሞተ ነው። ይህም ማለት የጦርነት መጨረሻ ሞት ነው እንደማለት ነው'' ወደ አማርኛ ስንተረጉመው'' ነገር ግን ባጫ ደበሌ ያለው "የጦርነትን አስከፊነት የሚያውቀው የሞተ ነው" ነው ያለው ይህ ደሞ ሊሆን አይችልም የጦርነትን አስከፊነት በጦርነት የተሳተፈ፣ ያየ፣ የሰማ፣ ቤተሰቡ የሞተበት፣ የተጎዳ ሁሉም ደረጃው ቢለያይም ያውቀዋል። ግን የአንድን ግለሰብ ንግግር በአማርኛ ወይም በሚችለው ቋንቋ መተርጎም ወይም በትክክል መረዳት መግለጽ የማይችል ሰው እንዴት መፃፍ ሊጽፍ ይችላል። በነገራችን ላይ ሰሞኑን ባጫ መጽሐፍ አስመርቀዋል አስቡት መጽሀፉ ውስጥ ስንት እንዲህ የተወናበደ ነገር ጽፎ እንደሆነ በእውነት ያሳፍራል።