fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 136
مشترکین
+724 ساعت
+2087 روز
+1 20130 روز
آرشیو پست ها
በወለጋ 19 ሰው ተገድሏል። በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19 (አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
በወለጋ 19 ሰው ተገድሏል። በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19 (አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉ ትናንት ቅዳሜ ያገኘኟቸው 2 ሰዎች በስለት ተወጋግተው የተገደሉና ተጥለው የተገኙ ሲሆን ሌሎች የተሰወሩ ግለሰቦችንም በፍለጋ እያገኙ ስለመሆኑ አስረድተዋል። አካባቢው በልዩ ኃይሉ ከበባ የተደረገበት ሲሆን መግለጫው እስከሚወጣበት ጊዜ ባለው ቆጠራ ብቻ 562 የመኖሪያ እና መጠጥ ቤቶች እንዲሁም የእህል መጋዘኖች)፤ 29 ሞተር ሳይክሎች፣ 3 ባጃጆች፣ 1 በቆሎ መፈልፈያ ኮምባይነር ተቃጥለዋል። ነዋሪዎቹ "ልዩ ሀይሉ የሚፈልገውን አፍኖ እየጫነ ይወስዳል፣ የቀረውን በማንአለብኝነት ይገድላል" ብለዋል። በመንግሥታዊ መዋቅር በግልጽ ግፍ መፈጸሙ አዲስ ነገር ባይሆንም እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ - ኢሕአፓ የማን አለብኝነት ድርጊቱን በጽኑ ያወግዛል። ይህ ተግባር መንግሥት በዓላማና በሥውር የሚፈጽመው ደባ በመሆኑ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭፍጨፋውን እንዲያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን። የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ - ኢሕአፓ ታኅሣስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ24ስዓት የተጋድሎ  ውሎ ___፩ አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል ።     አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ 109ኛ ኮር  77ተኛ ክፍለጦር  ጡት ቆራጭ ጨፍጫፊውና አረመኔውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እንደቅጠል ሲያራግፈው ውሏል። በቀን 18/04/2018 ዓ.ም መነሻውን ከገነት አቦ ፣ከጂጋ እና ከፍኖተሰላም ያደረገው የጠላት ሀይል ማክሰኝን ላይ በ3 አቅጣጫ ዙ 23 ጨምሮ ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ለመግባት ቢሞክርም ክንደ ነበልባሉ የ77ኛ ክፍለጦር ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እሰከ 10:00 ሰአት  6ተኛ ሬጂመንት/ቃኝና መሀንዲስ / ፣3ተኛ ሬጂመንት፣1ኛ ሬጂመንት፣5ኛ ሬጅመንት እና ሌሎች የሬጅመንት አባላት በመቀናጀት የመጣውን ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ ሰራዊትን እያጨደ ሲከምረው ውሏል።   አማራን ከምድረገፅ አጠፋለሁ ብሎ ያቀደው ይህ አረመኔ ስረአት በክንደ ነበልባሎች የ77ኛ ክፍለጦር አናብስቶች ከጥዋቱ12:00-10:00 በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሻምበል አዛዡና መቶ መሪዎችን ጨምሮ  ከ40 በላይ የጠላትን ሀይል ደምስሰውታል።  ወደ አናብስቶቹ 77ኛ ክ/ጦር  ምሽግ ዘሎ የገባው የጠላት ሀይል መውጫ አጥቶ የድረሱልኝ ሲቃ ሲያሰማ ውሏል። ከበባ ውስጥ  የገባውን የጠላት ሀይል ለማስለቀቅ ከጅጋ ተጨማሪ ሀይል ወደ ማክሰኝን ለማስገባት ቢሞክርም በደፈጣ ስፔሻሊስቶች ሻለቃ 1 ቀደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን ጠላት ያሰበው ዕቅድ ሳይሳካለት ቀርቷል። የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው ጨፍጫፊው የጠላት ሀይል ግማሹን አስከሬን ቀብሮ ሌላውን ትቶ ጨለማውን ተገን አድርጎ በሦስት መኪና ቁስለኛውን ጭኖ ወደ ጅጋ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። በዛሬው ዕለት የአካባቢው ማህበረሰብ የጠላትን አስከሬን እያነሳ እየቀበረ ይገኛል።        -በዕለቱ ከ40 በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሷል        -ሦስት መኪና የጠላት ሀይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል        -በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ ተማርኳል የዕለቱ አውደውጊያ በክንደ ነበልባሎቹ በ77ኛ ክ/ጦር የበላይነት የተጠናቀቀ ሲሆን ማክሰኝን ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች። ___፪ የመከላከያ ኦፕሬተሩ እና የሞርተር ኦፒው ፋኖን ተቀላቅለዋል ደ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ሙሉ ጥቃቸውን በመያዝ ወደ  ፋኖን ተቀላቅለዋል። 1ኛ 10 አለቃ ሰለሞን አለምነው 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25 ክፍለ ጦር 6ኛ ሬጅመንት የሞርተር ኦፒ 2ኛ 10 አለቃ ደሳለኝ አባይ አፕሬተር 602ኛ ኮር  25ኛ ክፍለጦር  6ኛ ሬጅመንት ሲሆኑ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል።     ____፫ "ህግ የማስከበር እርምጃው እንደቀጠለ ነው"!! ➛የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ስር የነበሩ የድርጅቱን ወቅታዊ የአደረጃጀት የጦር ፕወዛ በማስመልከት #ቃልኪዳን_ሊቁ ከ64 ክፍለ ጦር በማፈንገጥ በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ ተቀምጠው የአካባቢው ማህበረሰብን የሚዘርፎ፣ ወጣት ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ፣ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ እና ማንቆርቆሪያ/አንስላል ቀበሌ የጭነት እና የህዝብ መኪኖችን ሹፊሮችን ተሳፋሪዎችን በማስቆም ለግል ጥቅማቸው እየዘረፉ የሚገኙ ግለሰቦችን በ64ኛ ክፍለ ጦር ህግ ማስከበር ዘመቻ በቁጥጥር ስር እያወሉ ይገኛሉ። ከእነዚህ የአፈንጋጭ ኃይሎች ውስጥ:- 1ኛ. ዘራፊ መልካሙ አየለ 2ኛ. ዘራፊ ማስተዋል አሠፋ 3ኛ. ዘራፊ ታዴ ዳምጤ የተባሉ ግለሰቦች በእነማይ ወረዳ ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ሲዘርፉ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ➛በእነማይ ወረዳ እድገት በአንድነት ቀበሌ ልዩ ቦታው የዳጓት ለአፈንጋጭ ኃይሉ መረጃ ይሰጥ የነበረ ግለሰቦች እና አፈንጋጮች በ64ኛ ክፍለ ጦር የህግ ማስከበር ዘመቻ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ውሏል ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ገብሬ ካሰቸው 2ኛ. ሸገው ላቃቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል። ➛በ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላትን የውሸት ትርክት በመስበክ የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ እና የተለያዩ ምክንያቶች በማስመልከት ወደ አፈንጋጩ ቡድን ገብተው የነበሩ ግለሰቦች ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ይሁን ጤነው እና 2ኛ. ፋኖ ሀብታሙ እንደግ አፈንጋጮችን በመታኮስ 64ኛ ክፍለ ጦር ጥሪ ተቀብሎ በሰላም እጅ ሰጥቷል። በ64ኛ ክፍለ ጦር የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ከጠላት ተልኮ በመቀበል የሚሰሩ ግለሰቦች በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍል አስገድደው ገንዘብ እንዲያግዝ በማድእግ እና አንዳንድ የፋኖ አባላት ቤተሰብ ለመጠየቅ እንደተንቀሳቀሱ የፋኖ አባላትን በአፈሙዝ በመደብደብ እና በማስገደድ የአፈንጋጭ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ አድርገዋል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ጌቴ አሻግሬ 2ኛ. ፋኖ ከባዱ ሰናይ 3ኛ. ፋኖ ትዋቸው ዳኜ ሲሆኑ ትዋቸው ዳኜ የ64ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበር ቢሆንም እጁን በጥይት በመምታት ህክምና እንዳያገኝ አድርገውት በህክምና እጦት ምክንያት በአፈንጋጭ ቡድኑ እየተሰቃየ ይገኛል። ➛በሌላ መረጃ ከ64ኛ ክፍለ ጦር ከጠላት ተልዕኮ በመቀበል በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ መቀመጫቸው አርገው የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲያሰቃዩ ከነበሩት አፈንጋጮች ውስጥ:- 1ኛ. አብረሀም ፍቃዱ የተባለ ግለሰብ የአገዛዙን ተልኮ ተቀብለው በ64ኛ ክፍለ ጦሩ የቆዩ ቢሆንም የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ ምክኛት በማድርግ ከክፍለ ጦሩ በማፈገጥ ቆሰቆስ ከሚገኘው የአፈጋጭ ኃይል ጋር በመሆን የአገዛዙን ተልኮ ተቀብሎ ሲሰራ የቆዩ ቢሆንም ተልኮውን ጨርሶ የትመን 01 ቀበሌ ከሚገኘው የጠላት ኃይል መግባቱ ተረጋግጦል። ➛ከጠላት ተልኮ ተቀብለው በዝርፊያ የተሰማሩ በእነማይ ወረዳ ስር እየሱስ፣ የትመን፣ ዘብች እና አካባቢው ቀበሌ የአካባቢው ማህበረሰብ የሚዘርፍ ማህበረሰቡን የሚያንጋጥጡ ጋጥ ወጥ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና በቁጥጥር ስር የማዋል ዘመቻዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። አዲስ ትውልድ፣አዲስአስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ! አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ            ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም

መብረቅ ክፍለ ጦር በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ ፓራ ኮማንዶዎች እና የፓሊስ አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ:: ትናንት ለዛሬ ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም አጥቢያ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ከወግድ ከተማ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ለሚ ተብላ በምትጠራው ታዳጊ ከተማ ውስጥ ካቢ የተባለ ስፍራ ላይ የፋሽስቱ አብይ አህመድ ወንበር ጠባቂዎች ክፉኛ የተመቱ ሲሆን 3 ፓሊሶች እና 10 ፓራ ኮማንዶዎች በድምሩ 13 የጠላት ኃይል አባላት ተደምስሰዋል:: ንስሮቹ በሰሩት በሌሊቱ ኦፕሬሽን ከ5 በላይ ፓራ ኮማንዶዎች ቁስለኛ ሲሆኑ 22 የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሽነት ገደል ገብተዋል:: ገደል ከገቡት መካከል በርካቶች በህይወት መትረፍ እንዳልቻሉም ለማረጋገጥ ተችሏል:: የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር ኮማንዶዎች ለሚ የሚገኘውን ፓራ ኮማንዶ እና ፖሊስ ለማትረፍ ከወግድ ወረዳ ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም መብረቆቹ መንገድን በእሳት ስላጠሩት ጠላት ምንም ማድረግ ሳይችል ቀርቷል:: ከመብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት መካከል 1ኛ (አዳነ ሀብትነው) ሻለቃ እና ከ2ተኛ (ደምሰው ጎጡ) ሻለቃ የተውጣጡ አሃዶች ሌሊቱን የፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱን ተከትሎ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ስለገጠመው በቅጥረኝነት ከያዛቸው ተዋጊዎቹ መካከል ከሌሊቱ መዓት የተረፉት ተስፋ ቆርጠው በየ ገጠር ቀበሌዎች ተበትነዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ታህሳስ 19 ቀን 2018 ዓ.ም

"#ህግ_የማስከበር_እርምጃው_እንደቀጠለ_ነው"!!      ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም ➛የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ስር የነበሩ የድርጅቱን ወቅታዊ የአደረጃጀት የጦር ፕወዛ በማስመልከት #ቃልኪዳን_ሊቁ ከ64 ክፍለ ጦር በማፈንገጥ በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ ተቀምጠው የአካባቢው ማህበረሰብን የሚዘርፎ፣ ወጣት ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ፣ በእነማይ ወረዳ ሁለት አምባ ዲቢሳ እና ማንቆርቆሪያ/አንስላል ቀበሌ የጭነት እና የህዝብ መኪኖችን ሹፊሮችን ተሳፋሪዎችን በማስቆም ለግል ጥቅማቸው እየዘረፉ የሚገኙ ግለሰቦችን በ64ኛ ክፍለ ጦር ህግ ማስከበር ዘመቻ በቁጥጥር ስር እያወሉ ይገኛሉ።ከእነዚህ የአፈንጋጭ ኃይሎች ውስጥ:- 1ኛ. ዘራፊ መልካሙ አየለ 2ኛ. ዘራፊ ማስተዋል አሠፋ 3ኛ. ዘራፊ ታዴ ዳምጤ የተባሉ ግለሰቦች በእነማይ ወረዳ ማንቆርቆሪያ ቀበሌ ሲዘርፉ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ➛በእነማይ ወረዳ እድገት በአንድነት ቀበሌ ልዩ ቦታው የዳጓት ለአፈንጋጭ ኃይሉ መረጃ ይሰጥ የነበረ ግለሰቦች እና አፈንጋጮች በ64ኛ ክፍለ ጦር የህግ ማስከበር ዘመቻ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በቁጥጥር ስር ውሏል ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል። ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ገብሬ ካሰቸው 2ኛ. ሸገው ላቃቸው የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል። ➛በ64ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላትን የውሸት ትርክት በመስበክ የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ እና የተለያዩ ምክንያቶች በማስመልከት ወደ አፈንጋጩ ቡድን ገብተው የነበሩ ግለሰቦች ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ይሁን ጤነው እና 2ኛ. ፋኖ ሀብታሙ እንደግ አፈንጋጮችን በመታኮስ 64ኛ ክፍለ ጦር ጥሪ ተቀብሎ በሰላም እጅ ሰጥቷል። በ64ኛ ክፍለ ጦር የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ከጠላት ተልኮ በመቀበል የሚሰሩ ግለሰቦች በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍል አስገድደው ገንዘብ እንዲያግዝ በማድእግ እና አንዳንድ የፋኖ አባላት ቤተሰብ ለመጠየቅ እንደተንቀሳቀሱ የፋኖ አባላትን በአፈሙዝ በመደብደብ እና በማስገደድ የአፈንጋጭ ቡድኑን እንዲቀላቀሉ አድርገዋል።ከእነዚህም ውስጥ:- 1ኛ. ፋኖ ጌቴ አሻግሬ 2ኛ. ፋኖ ከባዱ ሰናይ 3ኛ. ፋኖ ትዋቸው ዳኜ ሲሆኑ ትዋቸው ዳኜ የ64ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበር ቢሆንም እጁን በጥይት በመምታት ህክምና እንዳያገኝ አድርገውት በህክምና እጦት ምክንያት በአፈንጋጭ ቡድኑ እየተሰቃየ ይገኛል። ➛በሌላ መረጃ ከ64ኛ ክፍለ ጦር ከጠላት ተልዕኮ በመቀበል በእነማይ ወረዳ ስር-እየሱስ ቀበሌ እና ደጀን ወረዳ ቆሰቆስ ቀበሌ መቀመጫቸው አርገው የአካባቢውን ማህበረሰብ ሲያሰቃዩ ከነበሩት አፈንጋጮች ውስጥ:- #አብረሀም_ፍቃዱ የተባለ ግለሰብ የአገዛዙን ተልኮ ተቀብለው በ64ኛ ክፍለ ጦሩ የቆዩ ቢሆንም የክፍለ ጦሩን የጦር ፕወዛ ምክኛት በማድርግ ከክፍለ ጦሩ በማፈገጥ ቆሰቆስ ከሚገኘው የአፈጋጭ ኃይል ጋር በመሆን የአገዛዙን ተልኮ ተቀብሎ ሲሰራ የቆዩ ቢሆንም ተልኮውን ጨርሶ የትመን 01 ቀበሌ ከሚገኘው የጠላት ኃይል መግባቱ ተረጋግጦል። ➛ከጠላት ተልኮ ተቀብለው በዝርፊያ የተሰማሩ በእነማይ ወረዳ ስር እየሱስ፣ የትመን፣ ዘብች እና አካባቢው ቀበሌ የአካባቢው ማህበረሰብ የሚዘርፍ ማህበረሰቡን የሚያንጋጥጡ ጋጥ ወጥ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና በቁጥጥር ስር የማዋል ዘመቻዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። አዲስ ትውል፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!          ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም የአፋብሃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኘነት ኃላፊ

#ዜና_ወለጋ - 19 ሰው ተገድሏል! በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19(አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች ተገድለዋል። ትና
#ዜና_ወለጋ - 19 ሰው ተገድሏል! በምሥራቅ ወለጋ ጊዳ አያና ወረዳ፣ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና በደጋ ጅጊ ከተማ 01 ቀበሌ ከታኅሣስ 14 ቀን 2018 ጀመሮ 19(አሥራ ዘጠኝ) ሰዎች ተገድለዋል። ትናንት ቅዳሜ ያገኘናቸው 2 ሰዎች በጢሻ ተጥለው በስለት ተወጋግተው የተገደሉ ናቸው የሚሉት ነዋሪዎች ሌሎች እንዲኹ የተሰወሩ ግለሰቦችንም በፍለጋ እያገኙ እንደኾነ ነግረውናል። ልዩ ኃይሉ ከበባ አድርጎ እስከ አኹን ባለው ቆጠራ ብቻ 562 (መኖሪያ ቤት፣ የእህል መጋዘንና መጠጥ ቤቶች) ተቃጥለዋል፣ 29 ሞተር ሳይክል፣ 3 ባጃጅ፣ 1 በቆሎ መፈልፈያ ኮምባይነር ተቃጥሏል። የሚፈልገውን አፍኖ እየጫነ ይወስዳል፣ የቀረውን በማንአለብኝነት ይገድላል ብለዋል። ፓርቲያችን በመንግሥታዊ መዋቅር እንዲኽ በግልጽ ግፍ መፈጸሙ ያውም በተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እየተሰማ መደረጉ እጅግ ያሳዘነን ተግባር ነው። የማን አለብኝነት ድርጊቱንም በጽኑ እናወግዛለን። መንግሥት በዓላማና በሥውር የሚፈጽመው ደባ በመኾኑ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ጭፍጨፋውን እንዲያወግዝና ተጠያቂነት እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! እናት ፓርቲ ታኅሣስ ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም #የመከላከያ_ኦፕሬተሩ_እና_የሞርተር_ኦፒው_ፋኖን ተቀላቅለዋል ‼️ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ሙሉ ጥቃቸውን በመያዝ ወደ ፋኖን ተቀላቅለዋ
+1
ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም #የመከላከያ_ኦፕሬተሩ_እና_የሞርተር_ኦፒው_ፋኖን ተቀላቅለዋል ‼️ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦርን በዛሬው እለት ሙሉ ጥቃቸውን በመያዝ ወደ  ፋኖን ተቀላቅለዋል። 1ኛ 10 አለቃ ሰለሞን አለምነው 6ኛ ዕዝ 602ኛ ኮር 25 ክፍለ ጦር 6ኛ ሬጅመንት የሞርተር ኦፒ 2ኛ 10 አለቃ ደሳለኝ አባይ አፕሬተር 602ኛ ኮር  25ኛ ክፍለጦር  6ኛ ሬጅመንት ሲሆኑ በዛሬው እለት ፋኖን ተቀላቅለዋል። ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

3ኛው መልዕክት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ታህሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰሞኑ ብልፅግና የተቀናጄ ጥቁር ፕሮፓጋንዳ ሊሰራ ሲሞክር እየታዘብን ነው። በዙ_23 እና በእልፍ ሰራዊት ታጅቦ እንደምንም ተሽሎክሉኮ አንድ ቦታ ይደርስና ፥ብዙ ጊዜ መደበኛ አዳራሾችን ሸሽቶ የሆነ አሳቻ ቦታ የእድር ድንኳን አስጥሎ ሲያበቃ በተለያዬ ዘዴና ማስፈራሪያ የጠራቸው ወገኖቻችን ሰብስቦ በቻለው መጠን የተጠና ውሸት ሲበትን ሰንብቷል። በነዚህ ድራማዎች በአንዳንዶቹ በተለይ የኔ ስም ላይ ትኩረት ሲያደርጉ ተስተውሏል። የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ጉዳዮች ግን አስቂኝ መሆናቸው አልቀረም። ከነዚህ መካከል አብዱ ሁሴን የሚባል የብልፅግና ባለጅራት ሎሌ "ዘመነ ካሴ ፈሪ ነው" እና" ደውለንለታል" የሚሉት ገለፃዎች ግን ትኩረቴን አልሳቡትም ብዬ አልዋሽም። አብዱ ሆይ እንደምታስታውሰው  "እረኛ ባፍላው የአህያ መዥገር ይነቅላል" ሆኖበት ግርማ የሽጥላም እንደ አንተ ያደርገው ነበር።እናም የቢሮውን በርም ባልኮኒም ተደግፎ በቀን ብዙ ጊዜ ስሜን እያነሳ ሲራገም ይውል ስለነበር በ 2014 ዓ/ም ባህርዳር ከተማ ውስጥ በአንድ አጋጣሚ አግኝቼው የሚከተለውን አልሁት፥ "ግርማ! ዘመነ ሲናገር ብዙ ሰው የሚሰማው ዘመነ መለኮታዊ ኃይል ስላለው አይደለም፥ ዘመነን ሰው የሚሰማው መከራውንና ከመከራ መውጫ መፍትሔውን በድፍረት የሚናገርለት ስለሚፈልግ ነው። እና በቀን ለመቶ ሰላይ አበል እየከፈልህ ስትከተለኝ ከምትውል፥ቢሮም መጠጥ ቤትም ስሜን ስታነሳና ስትጥል ከምታድር ከጌቶችህ ጋር ቁጭ ብላችሁ ለትውልዱ ጥያቄዎች መፍትሔ አምጡ። ያኔ ዘመነ ልብሱን አውልቆ ጊዮርጊስ አደባባይ ላይ እርቃኑን ቆሞ ቢጮህ የሚሰማው አይኖርም። ትውልዱ መልስ ይፈልጋል...." አልሁት።አልሰማኝም።በመጨረሻም የሆነው ሆነ።በአምስት ዓመት ውስጥ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እሆናለሁ የሚለው ግላዊ ምኞቱም ባከነ። ዛሬም ተረኛው ሎሌ የገዛ ህዝቡን በድሮንና በታንክ እያስቀቀለ ሳያፍር ህዝብ ሰብስቦ"ዘመነ ፈሪ ነው" ማለቱን ሰማሁ።ባለፉት 14 ዓመታት አታውቀኝ ከነበር ጌቶችህን ጠይቃቻው። በ 64 ክላሽና በ አንድ ዲሽቃ ብቻ ከመሃል ባህርዳር እንደ በሬ ነድቼ  በታንክ ታጅበው ወደ አዲስ አበባ እንዲሮጡ ካደረግኋቸው አለቆችህ አንዱ ይህንን ጽሑፍ ስታነብ በእርግጠኝነት አጠገብህ ይኖራል።መሐል ባህርዳር ላይ ተቀምጨ መሐል ባህርዳር ላይ ኮሎኔል ማርኪያችኋለሁ። ረሳኸው? አንበሳ ድንገት ሽኮናው ክፍት ቢሆን እንኳን ልትበላው አትከጅልም። አትችልማ! ሌላኛው ትኩረቴን የሳበችው የአብዱ ቅጥፈት "ደውለንለታል" የምትለዋ ናት። በአብዱና ጓደኞቹ አእምሮ "ዘመነ ከብልጽግና ሰዎች ጋር በስልክ አውርቶ ያውቃል ማለት ነው"? የሚል ጥርጣሬና ግርምት ለመፍጠር ታስቦ መሆኑ ነው። እርግጥ አንድ ነገር አልዋሽም። እሱም፦ በ 2014 ዓ/ም አዲስ አበባና ባህርዳር የሚገኙ የአብዱ አለቆች በአብይ አህመድ ታዝዘው በሦስት ወራት ውስጥ አራት ጊዜ የሽማግሌ ቡድን ወደ እኔ ልከው ነበር። አራት ጊዜ የመጡት በአብዛኛው የሚቀያየሩ የሽምግልና ቡድኖች የሚከተሉትን "ስጦታዎች" ቅደም ተከተላቸው እንኳን ሳይቀየር ያቀርቡልኝ ነበር። ➡️ከክልሉ ፕሬዝዳንትነት ውጭ የምትጠይቀንን ስልጣን እንስጥህ። ➡️አውሮፓ ወይ አሜሪካ  ልከንህ ሦስተኛ ዲግሪህን ተማር። ➡️አስር ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ውሰድና የተወሰነው ክፍሉ ላይ እገሌ የተባለው ባለሃብት ግራውንድ ሲደመር ሁለት ቤት ይገንባልህ፥ የቀረውን እስከ 30 ሚሊዮን ስለሚያወጣልህ ሽጠህ ትጠቀማለህ። ➡️የፖለቲካ ፓርቲ መስርትና በሊቀመንበርነት ምራ፥ ትንሽ አረፍም ትላለህ። ታሪኩን ለማሳጠር እንደ "ስጦታው " ቅደም ተከተል ሁልጊዜም ተመሳሳይ መልሶችን እሰጥ ነበር። የአንዱን ብቻ ለምሳሌ ለማንሳት  የመሬትን ጉዳይ በተመለከተ  ደጋግሜ "አስር ሺህ ካሬውን ስንዴ ዝሩት ወይንም የከተማ ግብርና የምትሉትን አፋፍሙበት" በሏቸው ብያቸዋለሁ።ከግርማ የሽጥላ እስከ ሽማግሌዎቹ የኔና የብልጽግና ሰዎች የግንኙነት ታሪክ ይህ ነው።ስለዚህ እነ አብዱ ወደ እኔ የደወሉት በምናብ ነው።አብዱና አለቆቹ ትንሽ እንኳን ማሰብ የሚችል አእምሮ ቢኖራቸው ዘመነንና ጓዶችን ያሳደገና የሚያውቅ፥ አላማቸውን የሚረዳ ህዝብ ፊት እንደዚህ አይነት የሚያስገምት ቅጥፈት ባልተናገሩ ነበር።ከሚሰበስቡት ህዝብ ቢያንስ ግማሹ ቢያንስ ለአንድ ጊዜ ከድሮን ወይንም ከሌላ ከባድ መሳሪያ አደጋ በተአምር የተረፈ ነው። ድሮኖቹንና ከባድ መሳሪያዎቹን ደግሞ ዘር አጥፊዎቹ አብይና እነ አብዱ ሁሴን እንጅ ዘመነ አልተኮሳቼውም። ለዚህ ህዝብ ትዋሻለህ? ለሜጀር ጀነራል አዲሱ ሞሃመድ እንኳን እኔ መልስ መስጠት አይጠበቅብኝም።አንድ የመደብንለት የ 27 ዓመት ጀግና አዋጊ ፋኖ አለ ከሱ ጋር ይጨርሳሉ። አትድከሙ! ናዚ ፓርቲ ተመልሶ የጀርመንን ህዝብ መምራት እንደማይችለው ሁሉ ብልፅግና የሚባል የዘር አጥፊዎች ቡድንም ተመልሶ የዚህ ህዝብ መሪ መሆን አይችልም። ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለአመታዊ ለመልአኩ ቅዷ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሳችሁ!! ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም! አንድ አማራ! እስከምፃት አማራ! ቅንነት የአዲሱ ትውልድ የአመራርም የመኖርም ፍልስፍና ነው! አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፡!

# የጀግናዉ አመታዊ መታሰቢያ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት አርበኛ መምህር ደሳለዉ ሙሉጌታ ታህሳስ 19/04/2017 ዓ.ም አርበኛው
#  የጀግናዉ አመታዊ መታሰቢያ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ  5ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት አርበኛ መምህር ደሳለዉ ሙሉጌታ ታህሳስ 19/04/2017 ዓ.ም                  አርበኛው ለአማራ ህዝብ ካበረከታቸው ውስጥ                   1ኛ አማራን የሚያውድሱ ግጥሞችን እና ዜማወችን                     2ኛ የባህል ችፖዚየም                     3ኛ የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት መምሪያ በመሆን ድምፀ ነጎድጓድ በሆነ ቃል ለሚዲያወች ሲያደር የነበረ ታጋይ አታጋይ ነበር።                     በአጠቃላይ የአማራ ሕዝብ አንድ ጎጆ አንድ መሪ እንዲኖረው ያላሳለሰ ጥረት የሚያደርግ ታላቅ መሪ ነበር።                              አርበኛው ነፍስህን ከደጋጎች ጎን ፈጣሪ ያድርግህ😭😭😭😭😭😭                             ታህሳስ19/4/2018 ዓም

አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ተኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ድል ተቀዳጅቷል !! ============ 👉 አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ እዝ 109ኛ ኮር  77ተኛ ክፍለጦር  ጡት ቆራጭ ጨፍጫፊውና አረመኔውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት እንደቅጠል ሲያራግፈው ውሏል። በቀን 18/04/2018 ዓ.ም መነሻውን ከገነት አቦ ፣ከጂጋ እና ከፍኖተሰላም ያደረገው የጠላት ሀይል ማክሰኝን ላይ በ3 አቅጣጫ ዙ 23 ጨምሮ ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ለመግባት ቢሞክርም ክንደ ነበልባሉ የ77ኛ ክፍለጦር ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት እሰከ 10:00 ሰአት  6ተኛ ሬጂመንት/ቃኝና መሀንዲስ / ፣3ተኛ ሬጂመንት፣1ኛ ሬጂመንት፣5ኛ ሬጅመንት እና ሌሎች የሬጅመንት አባላት በመቀናጀት የመጣውን ጨፍጫፊ ጡት ቆራጭ ሰራዊት እያጨደ ሲከምረው ውሏል። 👉 አማራን ከምድረገፅ አጠፋለሁ ብሎ ያቀደው ይህ አረመኔ ስረአት በክንደ ነበልባሎች የ77ኛ ክፍለጦር አናብስቶች ከጥዋቱ12:00-10:00 በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ሻምበል አዛዡና መቶ መሪዎችን ጨምሮ  ከ40 በላይ የጠላትን ሀይል ደምስሰውታል።  ወደ አናብስቶቹ 77ኛ ክ/ጦር  ምሽግ ዘሎ የገባው የጠላት ሀይል መውጫ አጥቶ የድረሱልኝ ሲቃ ሲያሰማ ውሏል። ከበባ ውስጥ  የገባውን የጠላት ሀይል ለማስለቀቅ ከጅጋ ተጨማሪ ሀይል ወደ ማክሰኝን ለማስገባት ቢሞክርም በደፈጣ ስፔሻሊስቶች ሻለቃ 1 ቀደፈጣ መብረቃዊ ጥቃት የተሰነዘረበት ሲሆን ጠላት ያሰበው ዕቅድ ሳይሳካለት ቀርቷል። 👉የፋኖን ምት መቋቋም ያቃተው ጨፍጫፊው የጠላት ሀይል ግማሹን አስከሬን ቀብሮ ሌላውን ትቶ ጨለማውን ተገን አድርጎ በሦስት መኪና ቁስለኛውን ጭኖ ወደ ጅጋ እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል። በዛሬው ዕለት የአካባቢው ማህበረሰብ የጠላትን አስከሬን እያነሳ እየቀበረ ይገኛል።        ⛔️በዕለቱ ከ40 በላይ የጠላት ሀይል ተደምስሷል        ⛔️ሦስት መኪና የጠላት ሀይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል        ⛔️በርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ ተማርኳል ➡️ የዕለቱ አውደውጊያ በክንደ ነበልባሎቹ በ77ኛ ክ/ጦር የበላይነት የተጠናቀቀ ሲሆን ማክሰኝን ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ውስጥ ትገኛለች። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ‎ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም

አገዛዙን ያስጨነቀው የራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ተከታታይ መግለጫዎች ! የብልፅግና አገዛዝ በመሬት ላይ ካለው የፋኖ ክንድና ወታደራዊ ሽንፈት ለመሸሸግ የሚቧጥጠው የፕሮፓጋንዳ ገደል ማቆሚያ ያጣ ይመስላል። ሰሞኑን ካድሬዎቻቸው እነ ጌትነት ያስደመጡን አዲስ የፈጠራ ስራ ደግሞ ይበልጥ አስቂኝ ሆኗል። “አርበኛ ዘመነ ካሴ የሱዳን ጦርን እየመራ በጃዊ በኩል ሊገባ ነው” የሚል ትረካ ይዘው ብቅ ብለዋል። ይሄ ፌዝ አገዛዙ ከፋኖ ጋር እያደረገ ባለው ፍልሚያ የገጠመውን ወታደራዊና ሞራላዊ ውድቀት ለመሸፈን የሚደረግ የከሸፈ የፖለቲካ ቁማር ነው። አገዛዙ ለሚገጥመው ውርደት ሁሉ “የውጭ እጅ” መፈለግ ልማዱ ነው። ህዝብ መብቱን ሲጠይቅ “የውጭ ጠላት”፣ በውጊያ ሜዳ ሲገረፍ “የውጭ ጠላት”... ለመሆኑ ይሄ አገዛዝ ሽንፈቱን መቀበል የሚጀምረው መቼ ነው? ትናንት ምቱ ሲበረታባቸው “የግብፅ ጦር ነው የሚወጋን” ሲሉ የነበሩት እነዚህ አካላት ዛሬ ራስ አርበኛ ዘመነን የሱዳን ጦር አዛዥ አድርገው መሾማቸው የፖለቲካ ንቃተ-ህሊናቸው ምን ያህል ወደ አዘቅት እንደወረደ ማሳያ ነው። ነገ በመሬት ላይ በፋኖ ክንድ ሲቀጠቀጡ “የሱዳን ጦር መታን” ለማለት የሰሩት የቅድመ መሸነፍ ስክሪፕት መሆኑ ግልጽ ነው። ​በአሁኑ ወቅት አገዛዙ በአየርም በምድርም የጥፋት ድግሱን ቢደግስም የትረካ ስንቁ ግን አልቆበታል። በተለይም ወደ ጫካ ተልከን መረጃ ሰበሰብን ብለው የተመለሱት የአረጋ ከበደ ቅጥረኞች ድራማ ህዝቡን ማሸበር አልቻለም። እንደ አቸፈር፣ ሜጫና ደብረ ማርቆስ ባሉ ጀግና አብቃይ አካባቢዎች ላይ የCasting (የተዋናይ ምርጫ)ና የDirecting ችግር እንዳጋጠማቸው ህዝቡ በግልፅ እያወራ ይገኛል። ምክንያቱም ህዝቡ የእነዚህን ግለሰቦች ማንነትና ታሪክ ገና ከውልደታቸው ጀምሮ ስለሚያውቀው የካድሬ ትወናቸው ቅንጣት ታህል ተዓማኒነት ሊኖረው አልቻለም። አገዛዙ የቱርክን፣ የኤምሬትስን (UAE)ና የሌሎች አረብ ሀገራትን ድሮን ታጥቆ በገዛ ህዝቡ ላይ እሳት እያዘነበ መሆኑን ዓለም ካወቀው ውሎ አድሯል። የድሮን ኦፕሬተሮቻቸው የት እንደሰለጠኑና የማንን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ንፁሃንን እንደሚጨፈጭፉ እያወቅን እነርሱ ግን ስለባዕድ ጣልቃ ገብነት ሊሰብኩን ይሞክራሉ። የታሪክ አተላወች እኮ ናቸው። ቀልዱን ካልተዋችሁትማ እኛም ሌላ ስክሪፕት አለን ፥ ​“አርበኛው በቅርቡ የቱርክን ጦር እየመራ በሶማሌ ክልል በኩል ሊገባ ነው” ብለን ብናወራ ይበልጥ አሳማኝ አይሆንም? የድሮን ስልጠናውንና ትጥቁን ላየ ሰው ይሄኛው ቀልድ ይበልጥ ይስማማችኋል! የፖለቲካ ስልጣን በድራማና በፈጠራ ወሬ አይቀጥልም። የፋኖ ትግል ከህዝብ አብራክ የወጣ፣ በህዝብ ደጀንነትና በልጆቹ መስዋዕትነት የሚመራ የህልውና ጥያቄ ነው። አገዛዙ የቱንም ያህል ቢሊዮኖችን ለፕሮፓጋንዳ ቢያፈስ በመሬት ላይ ያለውን እውነት ሊለውጥ አይችልም። ይልቁንም በየመድረኩ የሚቀጥፉት ውሸት ለፋኖ ተጨማሪ የሞራል የበላይነትን እየሰጠው ይገኛል። ​የአማራ ፋኖ ትግል መድረሻውን ከማግኘት ወደ ኋላም አይልም።  የፋኖ ግርማ ሞገስ እነዚህን ቄስ ሞገሴዎችንና የብልፅግና ካድሬዎችን ማስቃዠቱን ይቀጥላል። ተለቃቅመው የሚጠረጉበት ቀን ደግሞ ሩቅ አይሆንም። ​ድል ለፋኖ ! © ይሄነው የሸበሉ

ቀናቶችን በወሰደው ተጋድሎ ባለሽርጡ ክፍለጦር በመደበኛ ውጊያ እና ደፈጣ ጥቃት አመርቂ ድሎችን አስመዘገበ:: ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ ማዕረጉ በውል ያልታወቀ የስራዐቱ ወታደር ከፍተኛ አመራር ከጊራና ወደ ፋጂ ሲንቀሳቀስ በተያዘ የተጠና ደፈጣ ጥቃት ከነ ፖትሮሉ እና ከአጀቢዎቹ ጋር በመደምሰስ ድል ተጎናፀፈ። በእብሪትና ትቢት ተሞልቶ የመጣውን የአብይ አህመድ ጭራቅ ሰራዊት በሀብሩ ወረዳ ፋጂ በተባለ ቦታ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አንድ ጓድ የስርዐቱ  ሀይሎችን በመደምሰስ እና ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ባንዳ የስርዐቱን ወንበር ጠባቂ ሀይሎችን ማቁሰልና መበተን ተችሏል።  ዛሬ ታህሳስ 18/2018 አ.ም ከቀኑ 11:30  በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት አመራሩን ከነተሽከርካሪው በመደምሰስና በማውደም አመራሩን ለማሳለፍ ግራና ቀኝ ቦታ ይዘው የነበሩትን የስርዐቱን ወታደር ጭምር በመደምሰሰና በማቁሰል የጥላትን ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ መሬት በግስላዎቹ ነፍጥ እየተፈለፈለ የረገፈ ሲሆን፤ ከፊቱ የሚነጠፈውን ጓዱን የተመለከተ ጥላት ለተዎሰነ ሰዓት ባለበት ቁሞ መሸሻውን ቢያማትርም ግስላው ፋኖ ወደ ፊት በማጥቃት"አንድ ጥይት ለአንድ ጥላት" በሚል የአማራ ብሂል ለአንድ ጥላት በአንድ ጥይት ግንባር ግባሩን ተመቷል። በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ያስተናገደው የአብይ አህመድ  ሰራዊት የሞራል ውድቀት፤የቁስ ክስረትን በማስተናገድ፣እና የደረሰበትን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ሁለት ንፁሀኖችን በዘፈቀደ ተኩስ በመግደል የዘወትር ግብሩንና አቅዶት የመጣውን የጥፋት ተልዕኮ ሳያሳካ ወደ መጣበት ወደ ጊራና   ከተማ መመለስ ተችሏል።አገዛዙ ክፉኛ የቆሰለውን ሰራዊቱን በአንቡላንሶች ወደ ጊራና ጤና ጣቢያ ሲያጓጊዝ አምሽቷል። ከዚህ ጋር ተያይዞም ቀናቶችን በወሰደው የመርሳ እና የአምባሰል ዙሪያ ተጋድሎ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ንጋት 12:00 ከውጫሌ ከተማ እና አምባሰል ዙሪያ ሮቢት አካባቢ በርካታ ሃይሉን ይዞ ወደ አበት ማጥቃት ያደረገ ጠላት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ድል አስመዝግበዋል:: ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በአጠቃላይ ባለፉት አንድ ሳምንት ተከታታይ ቀናቶች ያለማቋረጥ ተጋድሎ በማድረግ ጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት በማድረስ ብሎም የነፍስወከፍ ክላሾችን ጨምሮ በርከት ያሉ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማርከው ታላቅ ድል አስመዝግበዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ደምሌ መኮነን ታህሳስ 18/2081 ዓ/ም

ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም #ባንዳን_የማፅዳት_ዘመቻው_ቀጥሏል። ሞጣ ከተማ ሆስፒታል ካለው ሚኒሻ ካቋቋመው ኬላ የሚሰሩትን ንስሮቹ ሰርገው በመግባት #የ201ኛ_ኮር #54ኛ_ክፍለ_ጦር አንጠልጥለው አው
ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም #ባንዳን_የማፅዳት_ዘመቻው_ቀጥሏል። ሞጣ ከተማ ሆስፒታል ካለው ሚኒሻ ካቋቋመው ኬላ የሚሰሩትን ንስሮቹ ሰርገው በመግባት #የ201ኛ_ኮር #54ኛ_ክፍለ_ጦር አንጠልጥለው አውጥተዋቸዋል። #1_ባዩሽ_ገደፋው ሞጣ ቀበሌ 03 የትውልድ ቦታ ጨባ #2_ዳንኤል_ገላነህ ሞጣ ቀበሌ 03 የትውልድ ቦታ ደብረ ሚካኤል ሲሆኑ በሽርፍራፊ ጥቅም ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል እየሰሩ የነበሩ ሲሆን በቂ ክትትል በማድረግ ገቢ ሆነዋል የሞጣን ህዝብ እና ተሽከርካሪ ጋሪ ሳይቀር እየቀረፁ ህዝባችን በማሸማቀቅ ለአብይ አህመድ አሽከር በመሆን ፋኖን ከህዝብ በመነጠል ከርሳቸው ያስቀደሙ አማራወች የስርዓቱ የእንግዴ ልጆች በቁጥጥር ስር ውለዋል ። በቀጣይም የፋኖን ስም ለማጠልሸት በሚሰሩ ማንኛውንም ከውስጥም ከውጭም በተቋሙ የሚነግዱትን ተከታትለን ህግ የማስከበር ስራችን የሚቀጥል ይሆናል። አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

"እባብ ያዬ በልጥ በረዬ❗❗ በዚህ በእኛ ዘመን ብአዴንን የቀበረ እንጅ ያነበረ ኃይል አልተፈጠረም።አዲሱ ትውልድና አዲሱ አስተሳሰቡ ሁለተኝነትን አይቀበልም።(አዲስ ትውልድ የሚለው አገላለጽ የአስተሳሰ
+1
"እባብ ያዬ በልጥ በረዬ❗❗ በዚህ በእኛ ዘመን ብአዴንን የቀበረ እንጅ ያነበረ ኃይል አልተፈጠረም።አዲሱ ትውልድና አዲሱ አስተሳሰቡ ሁለተኝነትን አይቀበልም።(አዲስ ትውልድ የሚለው አገላለጽ የአስተሳሰብንና የፖለቲካ ርእይን እንጅ እድሜን አይመለከትም። የአማራን ብሔርተኝነትና የህልውና ትግሉን የተቀበለ የ99 ዓመት አንድ አለሙ የሚሰኝ አማራም የአዲሱ ትውልድ አባል ነው።) እና አዲሱ ትውልድ የማንም ሁለተኛ አይደለም ፥ማንንም ሁለተኛ ማድረግም አይሻም።ተከታይም አስከታም አይደለም። በፍፁም እኩልነትና ፍቅር ያምናል። ማንንም አንበርክኮ በማንም ተንበርክኮ መኖርን ለአንድ ቀን እንኳን አይፈቅድም። የአማራ ህዝብ ከሌሎች ኃይሎችና ህዝቦች ጋር የመስራት አዝማሚያ ባሳዬ ቁጥር "ተለጠፈ፥ ሁለተኛ ሆነ፥ ጁኔርነት ነው ወዘተ" የሚሉ ራስ ጠል ትርክቶችን መፍጠር ለአዲሱ ትውልድ አይመጥንም። ሰው እንዴት ራሱን ይዘልፋል!?ሰው እንዴት ራሱን በውርደት ጅራፍ ይገርፋል!? ጁኔርነትን፥ ሁለተኛነትን፥ የመብት ተመጽዋችነትንና ሽራፊ እጣፋንታ ለማኝነትን፥ ብአዴንን ስናስወግድ  አነጣጥረን መተን በአንድ ገንዘን ቀብረናቸዋል። ይህን ማረጋገጥ የሚፈልግ ቢኖር ምናልባት እዛ አካባቢ አሁንም ጠረናቸው ይኖራልና ከጠቀመው ሂዶ ይፈልግ። አንዳንድ ወገኖች "እባብ ያዬ በልጥ በረዬ " ሆኖባቸው ልጥ ሲያዩ እባብ መስሏቸው ቢደነግጡ እንረዳለን። የብአዴን ተንበርካኪነት የፈጠረው ጠባሳ አሁንም ግንባራችን ላይ ስላለ መስጋቱ ጤናማ ነው።..........

ፋኖ በአምባሰል ግንባር በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥ-ቃ-ት አንድ የአገዛዙ መድፍ ሲወድም አራት ተኳሾች መ-ገ-ደ-ላ-ቸው ታውቋል። አገዛዙ በአምባሰል ግንባር በታሪካዊቷ ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ደንካ ሚካኤል ላይ መድፍ አጥምዶ የዘፈቀደ ድ-ብ-ደ-ባ በመፈፀም የበርካታ ንፅኋንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ አያሌ ሀብት ንብረት ሲያወድም መቆየቱን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም። ፋኖ ትናንት ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥ-ቃ-ት፡ ን-ፁ-ኋንን ለእልቂት ሲዳርግ የነበረው የአገዛዙ መድፍ ከነ ተተኳሹ ዶ-ግ አ-መ-ድ ተደርጓል። በተጨማሪም አራት የመድፍ ተኳሾች በሞርተር ቅንቡላ ፍንጣሪ ተመተው ሕይወታቸው ማለፉን ምኒልክ ዕዝ  በላከው መረጃ አስታውቋል። በምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ስር በሞርተር ተኩስ ኢላማ "የሞርተር ቅምቡላን ከጥላት ኪስ ውስጥ መክተት ይችላሉ" የሚባልላቸው የ24ኛ ክ/ጦር ሜካናይዝድ ክፍል ምድብተኞች፡ በፈፀሙት ስኬታማ የሞርተር ጥ%ቃት ነው የጠላት መድፍ ከነ ተተኳሹና ተኳሾቹ የወደመው። በተያያዘ ዜና! በዚኽው በአምባሰል ቀጠና ከታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተደረገ የጨበጣ ውጊያ በርካታ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ተሰምቷል። መነሻቸውን ከውጫሌ ከተማና ከጎልቮ እንዲሁም ጭሳ አባዲማ ቀበሌዎች ያደረጉ ራሳቸውን "መከላከያ ሰራዊት" ብለው የሚጠሩ የፀረ አማራው አገዛዝ አገልጋዮች በሚኒሻና አድማ ብተና መሪነት በወረዳው አበት ቀበሌ ላይ ማጥቃት ከፍተው የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን የፀረ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቷቸው ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራ መከናነባቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል። በዚህ ውጊያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነ መንገድ መሪዎቻቸው ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን፡ አገዛዙ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ቁስለኞችን ለሕክምና ወደ ውጫሌና ሐይቅ ሲያጓጉዝ አድሯል።