fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 443
مشترکین
+824 ساعت
+657 روز
+91030 روز
آرشیو پست ها
ሰበር የድል ዜና ከምዕራብ ወሎ ግንባር! 7ተኛ ቀኑን የያዘው ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በምዕራብ ወሎ ግንባር አመርቂ ድል ተመዘገበ:: ለተከታታይ 4 ቀናት በተደረገው ትንቅንቅ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መካነሰላም ቀጠና ውስጥ በሰራው ኦፕሬሽን ቁልፍ የጠላት ኃይል አመራሮች ተደመሰሱ:: በዛሬው ዕለት ማለትም መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም በማለዳው የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ አጥር ስር ወንዝ ዳር የአንድ ከፍተኛ የጠላት ኃይል አመራር አስከሬን ተገኝቶ በከፍተኛ ተኩስ ታጅቦ ተነስቷል:: በሰሞኑ ኦፕሬሽን የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪን ጨምሮ የቦረና ወረዳ ሚሊሻ ፅ/ቤት አቶ ሻምበል ሀይሉ፣ የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰይድ አብዬ፣ የሚሊሻዎች መቶ መሪ አቶ አረጋው ክብረት ምበል ሀይሉ እንዲሁም ከእነዚህ ጋር በምድሩ ከ75 በላይ የጠላት ኃይል ተደምስሷል:: የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 801ኛ ኮር 45ተኛ ክፍለ ጦር አንድ ሬጅመንት ሰራዊት ጁኒየር ትምህርት ቤትን ካምፕ አድርጎ ተቀምጦ የነበረ ሲሆን የኮሩ ሰራዊት ወደ ከተማይቱ መጠጋቱን ተከትሎ ቀድሞ ሲፈረጥጥ ጥቁር አማሮች የተሰባሰቡበት የአድማ ብተና ኃይል እና መንገድ መሪዎቹ የሆኑት ፓሊሶች እና ሚሊሻዎችን ለእሳት ዳርጓቸዋል:: የአድማ ብተና ኃይል 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል በሰሞኑ ኦፕሬሽን ተደምሷል:: የሚሊሻ ፅ/ቤት መረጃና ደህንነት ስራዎችን ሲያከናውን የነበረውና የሚሊሻዎች ጠርናፊ የነበረው አቶ ሞገስ አብዬ (በቅጽል ስሙ ቡላ የሚባለው) በውጊያ መሀል በኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጌታሰው አስረስ ብርጌድ ተወርዋሪዎች የተማረከ ሲሆን የ45ተኛ ክፍለ ጦር አመራሮች ቡላ ከሚማረክብን ዙ-23 እና ዲሽቃ ቢማረክብን ይሻለን ነበር ማለታቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል:: ቡላ የባንዳዎች ቁንጮ የሚባል አደገኛ የጠላት መጠቀሚያ ግለሰብ ሲሆን በየንፁሓን መንደሮች እየገባ ይህ የፅንፈኞች ደጋፊ ነው፣ ይህ አንድ ፅንፈኛ ዘመድ አለው ወዘተ እያለ ሲያስረሽን እንደነበር ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት:: ቡላ አሁን ላይ በፋኖ ቁጥጥር ስር ይገኛል:: የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ በበኩሉ አቶ ታከለ ይፍሩ የሚባለውን ቀንደኛ ሚሊሻ እና ሰላቶ ከተደበቀበት ቤት በመግባት ከነ ትጥቁ በቁጥጥር ስር አውሎታል:: ከአቶ ታከለ ይፋሩ እና ከአቶ ሞገስ አብዬ (ቡላ) በተጨማሪ አቶ ሀሰን እሸቴ እና አቶ አከለ ተሰማው ከሌሎች 5 ባንዳዎች ጋር በፋኖ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ:: የጥላሁን ፈንታው ብርጌድ የአድማ ብተናን ካምፕ ከቦ ባደረገው ትንቅንቅ ካምፑን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ተተኳሽ፣ ኢናርጋ የሚባል 2 ዘመናዊ መሳሪያ፣ የአስለቃሽ ጭስ መተኮሻ መሳሪያ፣ የህክምና ቁሳቁሶች፣ ሬሽን እና ሌሎች የጠላት ንብረቶችን መረከብ ችሏል:: የኮሩ አካል የሆነው የወግዲው መብረቅ ክፍለ ጦር አንድ ሻለቃ ኃይል እና ከአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ክፍለ ጦር የመጣው አንድ ሻለቃ ኃይል በአርበኛ በፍቃዱ ገንብር ከሚመራው ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር 2 ብርጌዶች ከተውጣጡ አሃዶች ጋር በመሆን መስከረም 17 ቀን በሰሩት ኦፕሬሽን ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩ ሲሆን በማግስቱ ማለትም መስከረም 18 ቀን የወግዲው መብረቅ ክፍለ ጦር አንድ ሻለቃ ኃይል አየር ማረፊያ በተባለ ቦታ 20 ወታደሮችን ሊደመስስም ችሏል:: የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ አበበ መኩሪያ እና የኮሩ ዘመቻ መሪ አርበኛ ጌትነት ኦፕሬሽኑን መምራታቸውም ተገልጿል:: በዚሁ በመካነሰላም ግንባር መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሌላ ድል ተመዝግቧል:: የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር አካል የሆነው ጌታሰው አስረስ ብርጌድም በተለምዶ ሰኞ ገበያ በተባለ ስፍራ አንድ ቲም የሚሆኑ የ45ተኛ ክፍለ ጦር ወታደሮችን እስከወዲያኛው ሸኝቷል:: የብርጌዱ አዛዥ አርበኛ ዱቤ እና ምክትሉ አርበኛ ሻምበል አብዬ የመሩት የሰኞ ገበያው ኦፕሬሽን ስኬታማ ስለነበር ጠላት ተንከሳክሶ ሊመለስ ችሏል:: በደረሰበት ሽንፈት የተደናገጠው ጠላት ወደ ንፁሀን ሞርተር አስወንጭፎ ትናንት መስከረም 19 ቀን የግፍ ግፍ የፈፀመ ሲሆን ተዋ በሚባል ቀበሌ ውስጥ መኖሪያ ቤት ተቃጥሎ አንድ እናት ተሰውታለች:: በቃጠሎው ቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ላይም ጉዳት ደርሷል:: ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር እና መብረቅ ክፍለ ጦር የተውጣጡ አሃዶች ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 9ኛ ሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አሃድ ጋር በመቀናጀት ትናንት ለዛሬ ሌሊት በመካነሰላም ግንባር የጠላትን ኃይል በመደምሰስ፣ በማቁሰል፣ በመበተን እና በመማረክ ከጥቅም ውጭ አድርገው መካነሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውለዋል:: በኦፕሬሽኑ የአድማ ብተና 23ተኛ ክፍለ ጦር በርካታ ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን የመካነሰላም ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅ/ቤት አመራር የሆነው አቶ ሰይድ አብዬን ጨምሮ ሌሎች ባንዳዎች እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል:: በድምሩ ከ45 ያላነሰ ጠላት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ቆስለዋል:: ውጊያው ሲጀመር ራሱን ለመከላከል አስቦ በአየር ማረፊያ፣ በለገአማራ ወንዝ እና በከተማይቱ መሀል በቡድን መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው ጠላት የጀግኖችን ክንድ ቀምሶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል:: መካነሰላም ከተማ ውስጥ የሚገኘው የቦረና ማረሚያ ቤትን በመክበብ ፋኖ ባደረገው ትንቅንቅ በርካታ እስረኞችን ማስለቀቅም ተችሏል:: በዚሁ በመካነሰላም ግንባር ከትናንትት በስቲያ የኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ጥላሁን ፈንታው ብርጌድ ኮሎኔል ሀብታሙ አሰፋን ጨምሮ ሌሎች 3 ባንዳዎችን መማረኩም ይታወሳል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መስከረም 20/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ጥብቅ አስቸኳይ መረጃ‼️ ወደ ቦሩ ከደሴ 4 ፓትሮል የጁላ ጦርና መድፍ አሁን አልፏል‼️ 20/ዐ1/2018 ዓ.ም

#ሰበር_የድል_ዜና‼️ ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ አባናደው ተንታ አጅባር ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ቤተ አምሓራ ክ/ጦ
+2
#ሰበር_የድል_ዜና‼️ ተጠናክሮ በቀጠለው ዘመቻ አባናደው ተንታ አጅባር ከተማ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገባች! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ቤተ አምሓራ ክ/ጦር ዛሬ መስከረም 20/2018 ዓ/ም በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ አጅባር ከተማን በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱን መረብ ሚዲያ ከኮሩ ኮሚዩኒኬሽን ክፍል ለማረጋገጥ ችሏል።።ግስጋሴው ቀጥሏል። #ዘመቻ አርበኝ አደም አሊ/አባ ናደው/ ተጠናክሮ ቀጥሏል። 20/ዐ1/2018 ዓ.ም

⚫️⚫️#አሳዛኝ_መረጃ!⚫️⚫️ ከወደ ምስራቅ ወለጋ አርጆ ጉደቱ ከተማ የሚወጡ መረጃዎች ይረብሻሉ። በከተማዋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ስምሪት ሰጭነት በምታየት መልኩ የደቦ ፍርድ እየተፈፀመባቸው ነው። ፅንፈኛ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ድርጊቱን እያባባሱ አይዟችሁ እያሉ እያበረታቱ ይገኛሉ። በከተማዋ የአማራ ተወላጆች ታድነው እየተገደሉ ነው። አርጆ ጉደቱ ማለት...በምስራቅ ወለጋ ዲጋ ወረዳ ስር የምትገኝና የዞኑ መቀመጫ ከሆነችው ነቀምቴ ከተማ በስተ ምዕራብ በኩል በግምት 60km ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። (ከነቀምት ጊምቢ.. አሶሳ ባለው የፌደራል መስመር ከዴዴሣ በቅርብ ርቀት የምትገኝና እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆት የሚኖሩባት ከተማ ናት። 20/ዐ1/2018 ዓ.ም

#አፋብኃ_ምኒሊክ_ዕዝ_ጤና_መምሪያ‼️ በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የጤና መምሪያ ስር የሚገኘው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሰጭ ቡድን በየቀጠናው እየተዟዟረ ለቁስለኛ ምኮኞች የሕክምና አገልግሎች እየሰጠ ይገ
+2
#አፋብኃ_ምኒሊክ_ዕዝ_ጤና_መምሪያ‼️ በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የጤና መምሪያ ስር የሚገኘው የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሰጭ ቡድን በየቀጠናው እየተዟዟረ ለቁስለኛ ምኮኞች የሕክምና አገልግሎች እየሰጠ ይገኛል‼️ 19/ዐ1/2018 ዓ.ም

እጅ ከፍንጅ ተያዙ‼️ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ዛሬ መስከረም 19/2018ዓ.ም ከጥዋቱ 12:30 በጎንደር ከተማ በማራኪ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ገፎ ቁጭ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የተደራጁ ሌቦች ፦ 1
+3
እጅ ከፍንጅ ተያዙ‼️ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ዛሬ  መስከረም 19/2018ዓ.ም ከጥዋቱ 12:30  በጎንደር ከተማ በማራኪ ክፍለ ከተማ በተለምዶ  ገፎ ቁጭ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር የተደራጁ ሌቦች ፦ 1.አደነ ተሾመ 2.ሙሉ ወንድሙ ባዘዘው 3.ይታየው ገቢያው 4.በረከት ይታያል እና 5.ማርቆስ ተሻገር በመሆን በአንድ እናት ቤት በመግባት የቤት ዕቃዎችን በመዝረፍ ላይ እያሉ በአካባቢው ነዋሪዎች እና የፀጥታ ሀይሎች  ርብርብ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

አሁን ከመሸ ከደሴ ወደ ወልዲያ 5 መኪና መከላከያ ሄዷል የዘገዬ መረጃ 1:30 ላይ ነው የተንቀሳቀሰው!! ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

🔥ዛሬም ነጻ በወጡ ቀጠናዎች ሕዝባዊ ውይይት እየተደረገ አዲስ የአስተዳድር መዋቅር እየተዘረጋ ነው‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ነፃ ባጣቸው የሰሜን እና የደቡብ ወሎ ዞን እና ወረዳ ከተሞች ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶች በማድረግ የከረፋውን የብአዴን መዋቀር እየናደ የራሱን መዋቀር እየዘረጋ ይገኛል፡፡ ዛሬ በዕለተ ማክሰኞ በቀን 19/01/2016 ዓም በሰሜን ወሎ ዞን በሃብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ከነዋሪው ጋር ህዝባዊ ውይይት በማድረግ እና ማህበረሰባዊ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ባማረ መልኩ ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ የተነሱ ኮር ሃሳቦች 1 የትግሉ መነሻ ምክኒያቶች ምን ነበሩ?   * ትግሉ አሁን ያለበት ጠቅላላ ሁኔታ   * ትግሉ ያመጣው መልካም አጋጣሚ   * የትግሉ ተግዳሮቶች   * የትግሉ የቀጣይ አቅጣጫ 2 መንግሥት አሁን ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ   * በወታደራዊ ቁመና   * በፖለቲካ ተቀባይነት   * የዲፕሎማሲ አቅም እና ሌሎችም 3 በራስ አስተዳደር እና በፀጥታ ጉዳይ   * የሃገር ሽማግሌዎች የሰላም ኮሚቴዎች የቅሬ እና የእድር እንዲሁም የእምነት አባቶች ሚና እንዲሁም የወጣቱ ሃላፊነት   * የህዝብ እና የኛ ግኑኝነት ምን መሆን አለበት   * ከጠላት ጋር በጥቅምም ሆነ በፆታዊ ግኑኝነት እያደረጉ ባሉ ሰዎች ጉዳይ 4 ይህን ትግል እንዴት የራሳችሁ እንደሆነ አምናችሁ ኮትኩታችሁ ታሳድጉታለችሁ? በሚሉ አንኳር ጉዳዮች ተነስተው ሰፊ ውይይት በማድረግ ህዝብ ላይ የነበረን የተዛባ አረዳድ እና ስሁት እሳቤ ለማጥራት ተመኩሯል፡፡ በውይይቱም ህዝቡ ደስተኛ እንደነበር እና በተለይ ሙስሊም ጠል ናቸው በሚል አገዛዙ ትግሉን እንድንጠላው መንግሥት በፋኖ ላይ ትልቅ ጥላቻ እንዲኖረን ብዙ የሰራ ቢሆንም ከመቅረት ማርፈድ ይሻላል እና ዛሬ ጥርጣሬያችንን ለማጥራት ችላቹሃል በማለት ሃሰተኛውን የብልፅግና ስርዓት በጋራ ለመታገል ቃል ገብቷል፡፡ በቀጣይም ሰፊ ውይይቶች እንዲደረግ እየጠየቁ ቀጠናውን እናንተ በመያዛችሁ ሰላም አግኝተናል ስትባሉ የነበረውን የሃሰት ስም ማጥፋት በተግባር የህዝብ ልጅ መሆናችሁን አሳይታቹሃል እኛም ከመሳቀቅ ድነናል ሲሉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ 19/ዐ1/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

#ንግድ ባንክ ኦሮሚያ ባንክ ሆኗል‼️ ============================= የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገር ዐቀፍ ባንክ ነው። የፌደራል ተቋም ነው። የፌደራል መንግሥቱ የስራ ቋንቋ ደግሞ አማ
#ንግድ ባንክ ኦሮሚያ ባንክ ሆኗል‼️ ============================= የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገር ዐቀፍ ባንክ ነው። የፌደራል ተቋም ነው። የፌደራል መንግሥቱ የስራ ቋንቋ ደግሞ አማርኛ ነው። ባንኩ ግን ኦሮምኛን ከላይ፣ አማርኛን ሁለተኛና እንግሊዝኛን ሦስተኛ አድርጎ ሰነድ አዘጋጅቷል። ይህ የሆነው ኦሮምያ ክልል ይመስላችኋል? አይደለም። አዲስ አበባ ላይ ነው።  ኦሮምኛ የፌደራል የስራ ቋንቋ ተደርጎ በህገ መንግስት አልተቀመጠም። የፋሽስታዊ አገዛዙ  ጉልበተኞች ግን ሰይፋቸውን አማራን ይወክላል በሚሉት ነገር ላይ ሁሉ መዘዋል። ህግ ቢኖር ባንኩን መጠየቅ ይቻል ነበር። ህግ በሌለበት አገር ብቸኛው ተቃውሞን የመግለጫ ዘዴ ተዓቅቦ ( boycott ) ማድረግ ነው። Boycott Commercial Bank of Ethiopia. በአጭሩ ባንኩ የኦሮሚያ ባንክ ሆኗል !!

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር የተላለፈ መልእክት! በአሁኑ ሰዓት እራሱን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት /አፋህድ / እያለ የሚጠራው ቡድን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል / አፋብኃ / ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ አባላት ላይ ከስትራቴጅካዊ ጠላታችን ጋር ፍፁም በተናበበ መንገድ ለመደምሰስና ለማጥፋት እየሰራ መሆኑን ማሳወቅ እንፈልጋለን።     የአፋህድ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በጎንደር ቀጠና የሚገኙ የብልጽግና ሰራዊት ጀኔራሎችን በስልክ በመደወል በሁሉም የጎንደር ቀጠናዎች ለሰራዊታችሁ ትዕዛዝ ስጡልኝ እና ይህን ሌባ ቡድን በጋራ እንደምስሰው በማለት ውይይት አድርጓል። በዚህም የተነሳ በቆላደባ ፣ በአዘዞ ፣ በጠዳ ፣ በማክሰኝት ፣ በእንፍራዝና በደጎማ ጠላት ያለ የሌለ ኃይሉን በማንቀሳቀስ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ክ/ጦሮችን  ከበባ በመፈፀም ለመደምሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል።    በማክሰኝት ለምባና ጭህራ እንዲሁም ቀይ ድንጋይና ፈረንጅ ውሃ በጠዳ   ሮቢት፣ ወይና ጣናናጅዋና በደጎማ  ወደ ሚካኤል ደብር  የጠላት ኃይል የተንቀሳቀሰባቸው ቀጠናዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አዲስጌ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ከአፋህድ ጎን ተሰልፋችሁ ድጋፋችሁን አልሰጣችሁም በማለት አንድን አባት እስከ ልጁ በአሰቃቂ ሁኔታ በትላንትናው እለት ረሽኗል። የተረሸኑት አባትና ልጅ ስምም       1- ጀምበር ጌጤ በላይነህ       2- ማስተዋል ጌጤ ጀምበር ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ስማቸው ለጊዜው ያልታወቁ 4 ሰዎችን ረሽኗል። በትላንትናው እለት ጠላት ከአዘዞ በአንድ ፓትሮል የተጫነ የተለያዩ ተተኳሾችን ለደረጀ በላይ ሰጥተውት ተመልሰዋል። በአጠቃላይ የአፋህድ ኃይሎች ከብልጽግና አገዛዝ ጋር በቅንጅት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይልን ለማክሰምና ለመደምሰስ እየሰራ መሆኑን ህዝባችን እንዲያውቅልን እንፈልጋለን። ይህ ኃይል ከዚህ በፊትም ከበልጽግና አገዛዝ ጋር ወሎ ውስጥ ዳውንት ላይ ድርድር አድርገውም እንደነበር ህዝባችን የሚያውቀው ሃቅ ነው። በመሆኑም ይህን ድርጅት ከብልጽግና አገዛዝ ለይተን የማናየው እንደሆነም ለህዝባችን ማስገንዘብ እፈልጋለን። በስተመጨረሻም የአፋህድ ኃይሎች በተቋማችን በአፋብኃ ላይና በተቋማችን ሰራዊት ላይ እያደረጉት ያለው ጠላታዊ ድርጊት ትከሻችን መቻል ከሚገባው በላይ በመሆኑ የተቋማችን አመራርም ይሁን አባላት ከዚህ በኋላ ትግስታችንን የጨረሰን መሆኑን መላው ህዝባችን እንዲረዳልንና እንዲያውቅልን ስንል በአክብሮት እንገልፃለን።      ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ 5ኛ ኮር                       መስከረም 19/ 2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ታጋይ ይሞታል ትግል ግን ይቀጥላል እናታችን ይህን የአረመኔው አብይ አህመድ የመጨረሻ ውድቀት ሳያዩ በማረፈዎ ልባችን ተሰብሯል ነፍሰዎን በአፀደ ገነት ፈጣሪ ከደጋግ አባቶችና እናቶች ጋር ያኑርልን እኝህ እናት መቼም ለወገናቸውእረጅም ጊዜ ድምፅ ሲሆኑ ነው የኖሩት እዚህ ዋሽግተን ዲሲ ላይ! በብርዱም በሙቀቱም ጊዜ ሁልጊዜ ከፊት መተው ድምፅ እዳሰሙ ነው! ዛሬ ማረፋቸውን ሰማን የቀብሩን ቀን እና ቦታ በቅርቡ እናሳውቃልን እናታችን ነፍሰዎን ይማር

አስቸኳይ የጥንቃቄ መረጃ አዲስ አበባ አዲስ አበባ ላይ በወሎ ፋኖ ድል እየጨፈራችሁ ነው በሚል በስፒከር የዳኜ ዋሌን ዘፈን የከፈቱ ሰዎች እንዲሁም አዲስ አበባ ሳሪስ ሀናማርያም አካባቢ አፈሳ ለመጀመር ከ 40 በላይ ፖሊስ ከ  1 ፓትሮል ጋ በአሁኑ ሰዓት 11:55  እየተዘጋጀ ነው ከስራ አምሽቶ የሚመጣውን ወጣት ይበዛበታል በማለት በተለይም አማራዉ ያነጣጠረ አፈሳ ለማድረግ በትኩረት እየተዘጋጁ ነው አስቸኳይ ነው:: ቤተል እና ጦርሀይሎች አካባቢ የዳኜ ዋሌን ዘፈን ከፍታቹሀል ተብለው ሁለት የንግድ ሱቆች ተዘግተው ባለቤቶቹ እየተደበደቡ በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል ! ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ባሻ የተባለው የወራሪው የብልጽግና ሠራዊት አባል የነበረው ደምበጫ ከተማ ከተወሸቀው የአረመኔው ስብስብ እጁን ለቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ሰጥቷል። መስከ
ባሻ የተባለው የወራሪው የብልጽግና ሠራዊት አባል የነበረው ደምበጫ ከተማ ከተወሸቀው የአረመኔው ስብስብ እጁን ለቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ሰጥቷል። መስከረም 19/2018 ዓ.ም

ሰበር ዜና! የጎንደር ከተማ አካል በሆነችው ጠዳ ክ/ከተማ እና በጎንደር ዙሪያ ወረዳ  ማክሰኝት ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ተጋድሎ እየተደረገ ይገኛል። የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ከተለያዩ  ክፍለ ጦር የተወጣጡ    ጀግኖቻችን በጥምረት  ዛሬ መስከረም 19  /2018 ዓ/ም  ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በተመሳሳይ  ማክሰኝት ከተማ ዙሪያ እና  ጠዳ  ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአገዛዙ ወታደራዊ ቤዞች ላይ ያነጣጠረ  እርምጃ ተወስዷል። በአውደ ውጊያው በጠላት በኩል ከፍተኛ  የሆነ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን ወደ ገጠር ለኦፕሬሽን የላከውን ጥምር ሀይል በመኪና በማመላለስ ለመከላከል የሞከረ ቢሆንም ከሞትና ከቁስለት ሳይታደጋቸው ቀርቷል።     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ነው!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ   መስከረም 19/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

"ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል" እንዲሉ አበው እነ ጃንጥራር ዓባይ የታላቋ ኦሮሚያን ፕሮጀክት የሚያሳየውን ካርታ ዐውደ ርእይ መርቀው በደስታ ከፍተዋል። ተመልከቱ እንግዲህ እነዚህ ምስለኔዎች የአማራ
+1
"ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያበቅላል" እንዲሉ አበው እነ ጃንጥራር ዓባይ የታላቋ ኦሮሚያን ፕሮጀክት የሚያሳየውን ካርታ  ዐውደ ርእይ መርቀው በደስታ ከፍተዋል። ተመልከቱ እንግዲህ እነዚህ ምስለኔዎች የአማራ ህዝብ ተወካይ ሁነው ከሠላሳ ዓመት በላይ ከሕዝብ ትክሻ ላይ አልወርድ ያሉት።   ብአዴን አንድ የበሽታ አካል ነው። ብአዴን የሆነ ሁሉ የማይታከም በሽታ መያዙን ማወቅ ይኖርበታል።

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ ጉዳልማ ላይ ከ12:00-7:00 ሰዓት ከፍተኛ ትንቅንቅ የታየበት ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። በውጊ
+3
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክ/ጦር የደጅአዝማች ተድላ ጓሉ ብርጌድ  ጉዳልማ ላይ ከ12:00-7:00 ሰዓት ከፍተኛ ትንቅንቅ የታየበት ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። በውጊያው የአረመኔው አሽከር ምሊሻ፡አድማ ብተና እንደ ጌሾ ሲወቀጥ ውሏል። ነበልባሎቹ የተድላ ጓሉ ልጆች ለአረመኔው ሰራዊት የእግር እሳት የሆኑበት ሲሆን በውጊያው 19 የጠላት ሀይል ሲደመሰስ  21 ቁስለኛ ሆኗል። 7ክላሽ 1አብራረው በድምር 8 መሳሪያ ተማርኳል። 1.ጌቴ ሙሉዓዳም 2.እንዳላመው ያለው 3.ልጥገበው ጌቴ 4.ሙሉቀን ደምስ 5.ጌቱ ማሞ 6.አዝመራው መኩ የሚባሉ ምሊሻዎች ወደ ላይኛው ተሸኝተዋል። የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት:- 1.ተግባር ማናዬ የተባለ አርሷደር እረሽኗል 2.አበዋ ምህረቴ የተባለውን ሲያቆስል የግለሰብ ባጃጅ አቃጥሏል አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መስከረም 19/2018 ዓ.ም

4 ንፁሀን በድሮን ጥቃት ተገደሉ። አገዛዙ ባለፉት ቀናት ወልዲያ ከተማ ዙሪያ 11 የድሮን ጥቃት እንዳደረገ የተገለፀ ሲሆን፤ ዛሬ በራያ ቆቦ ወረዳ ቃሊም ከተማ 12ኛ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ የኢትዮ 2
4 ንፁሀን በድሮን ጥቃት ተገደሉ። አገዛዙ ባለፉት ቀናት ወልዲያ ከተማ ዙሪያ 11 የድሮን ጥቃት እንዳደረገ የተገለፀ ሲሆን፤ ዛሬ በራያ ቆቦ ወረዳ ቃሊም ከተማ 12ኛ የድሮን ጥቃት መፈፀሙ የኢትዮ 251 ሚዲያ ምንጮች ገለፁ። ዛሬ ማለትም መስከረም 19 ቀን ረፋድ 4:00 ላይ ራያ ቆቦ ቃሊም ከተማ ቃሊም ትምህርት ቤት አካባቢ አገዛዙ ባደረገው የድሮን ጥቃት 4 ንፁሀን እንደተገደሉ የአካባቢው ምንጮች ለ251 ገልፀዋል ። ምንጮቹ አክለውም 4 የአካባቢው ወጣቶች በአንድ ላይ ሲንቀሳቀሱ በነበረበት ወቅት ላይ የድሮን ጥቃቱ እንደተፈፀመ ገልፀዋል። በትላንትናው እለት ከላሊበላ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ከአንድ ቋጥኝ ተፈልፍላ በተሰራችው ገነተ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተመሳሳይ የድሮን ጥቃት እንደተፈፀመ ይታወቃል። ከትላንት ወዲያ እንዲሁ ሳንቃ ጤና ጣቢያ በፈፀመው የድሮን ጥቃት በሕክምና ላይ የነበሩ ንፁሀንን ጨምሮ የሕክምና ባለሙያዎች እንደተገደሉ የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል።

🔥ከዘመቻ አባ ናደው ጎን ለጎን ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር ከ100 በላይ አዳዲስ ፋኖዎችን አስመረቀ‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ክፍለ ጦር በመቄት  ከ100 በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ። በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገው የውባንተ ክፍለጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ጎበዜ በአውደ ውጊያ ጠላትን በማንበርከክ እና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው እየሰራ ያለው የውባንተ አባተ ክፍለጦር መደበኛ ሰራዊት በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ታሪካዊ ጀብድ ለመፈፀም ተዘጋጁ ብሏል። የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ አርበኛ ሸጋው ወርቄ በበኩሉ የትግሉን መሠረታዊ አላማ በንድፍ ሀሳብ በስልጠና ላይ ያገኛችሁትን ስልጠና በተግባር እንደምታረጋግጡ አልጠራጠርም ብሏል። አማራ እንደ ህዝብ የገጠመውን ስርዓታዊ እና መዋቅራዊ  ጥቃት ድባቅ በመምታት የአባቶቻችን ታሪክ እንድትደግሙ ታሪካዊ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ  ሲል የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ ፋኖ በሪሁን ደምሌ አደራዊ መልዕክቱን አስተላልፏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የኮሩ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 19/ዐ1/2018 ዓ.ም