ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 387
مشترکین
+124 ساعت
+757 روز
+1 40730 روز
آرشیو پست ها
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
ከቀኑ 9:15 አገዛዙ ከጅጋ 8 ታታ(መኪና) ኃይል ወደ ቋሪት አንቀሳቅሷል ስለሆነም መረጃው ለወገን ኃይል ይድረስ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል‼️
02/ዐ3/2018 ዓ.ም
የአርበኛ ጌትነት መሳፍንትን መስዋዕትነት አስመልክቶ ከዋርካው ምሬ ወዳጆ የተላለፈ መልዕክት!
ዘመናትን ተሻግሮ የመጣውን የአማራ ህዝብ ግፍና በደል ለማስቆም ህዝቡንና መላ ቤተሰቡን አስተባብሮ ሲታገል የኖረው የትግል አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ዛሬም የዘመናት ግፉ ወደ ዘር ማጥፋት አድጎ የህልውና አደጋ ውስጥ የገባውን የአማራ ህዝብ ለመታደግ እየተደረገ ባለው ተጋድሎ ከባድ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል::
በዚህ መራር ዋጋ እየተከፈለበት ባለ ትግል ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ አጅሬ የተሰኘች ታዳጊ ከተማ የሰሜን አምባራስ ክፍለጦር አዛዥና የራስ አሞራው 3ኛ ኮር አስተዳደር ሃላፊ የሆነው አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉ መስዋዕትነት የከፈለ ሲሆን በዚህም ከባድ ሃዘን እንደተሰማኝ ለመግለፅ እወዳለሁ::
ትግላችን እስከቀራኒዮና አባታችን አርበኛ መሳፍንት ተስፉ እስከ ቤተሰብዎ ለአማራ ሕዝብ በደማቅ የደም ቀለም እየተጻፈ ነውና ትውልድ በጀግንነትና ለአማራ ሕዝብ የተከፈለ እውነተኛ አማራነት ነውና ለእሱ በግሌ አመሰግናለሁ ማለት እወዳለሁ። ይህ መስዋዕትነት የአንድ ጀግና መስዋዕትነት ብቻ ሳይሆን ለአማራነት ዋጋ መክፈል ምን ማለት እንደሆነ በሕይወት እያሉ ህያው ምስክር ነዎት!
የአማራ ፋኖ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል፣ የወንድማችን አርበኛ ጌትነት መሳፍንት ተስፉና በአውደ ውጊያ በወደቁ ጀግኖቻችን ዘመቻ አውጀን የአብይ አህመድን አገዛዝ ድባቅ እንደምንመታው ወደ ድልና ነጻነትም እንደምንሸጋገር ከምስራቅ አማራ ቀጠና ሁኜ ይሄን መልዕክት ሳስተላልፍ በታላቅ ቁርጠኝነትና ቁጭት ሁኜ መሆኔን መግለጽ እፈልጋለሁ።
በመጨረሻም ለአርበኛ መሳፍንት ተስፉ፣ ቤተሰቦቹ፣ እና መላው የትግል ጓዶቹ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብኃ ማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የምኒልክ ዕዝ ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ
አሳዛኝ ዜና!!
ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮችን የብልፅግና ሰራዊት በግፍ ጨፈጨፋቸው ።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ የደረሰ ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ ከ10 በላይ ንፁሀን አርሶ አደሮች በጡት ቆራጩ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሀይል ስራ ላይ እንዳሉ በወጡበት ተገድለዋል ።
አርሶ አደሮቹ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር አካል የሆነው ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር የሚንቀሳቀስበት ቀጠና ነዋሪ ሲሆኑ በዚህ አካባቢ የጀግኖች ፋኖዎቻችን ምትና ሀይል በተደጋጋሚ መቋቋም ያቃተው ሆድ አደሩ የብልፅግና ሰራዊት ዛሬም የበቀል በትሩን እንደተለመደው ንፁሀን ላይ በማሳረፍ የደረሰ ሰብልላቸውን በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶአደሮችን በጥይት ሀሩር ገድሏቸዋል ።
ይህ አማራ ጠል የሆነው የብልፅግና መንግስት ተብየው በቀጠናው ምንም ጦርነት ባልነበረበት ሰዓት ሆን ብሎ አልሞና አቅዶ አርሶአደሮችን በመግደል ዛሬም አማራን ከምድረ ገፅ የማጥፋት ስራውን ቀጥሎበታል።
ከተገደሉት ንፁሀን አርሶ አደሮች መካከል ጥቂቶቹ
1; አቶ ሞላ ደርብ ዕድሜ 56 ቀበሌ ሚጦ
2; አቶ ይርዳው ዘመነ ዕድሜ 28 ቀበሌ ሚጦ
3; ወጣት እያያለም ውዱ ዕድሜ 16 ቀበሌ ሚጦ
4; አስማረ በላይ ዕድሜ 38 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
5; አለምነህ ቀኔ ዕድሜ 60 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
6; ድረስ ፀሐይ ዕድሜ 62 ቀበሌ ጭልፋ ወንዝ
7; መልካሙ አለሙ ቁስለኛ ጭልፋ ወንዝ
8; ታደሰ ይግዛው ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ
9; አዋጅ በላይ ቁስለኛ ቀበሌ ሚጦ ሲሆኑ እንዲሁም ወ/ሮ ካሳየ ያለው የተባለች እናታችን ሳንቃ ጥቅም ቀበሌ የፋኖ አገርነው እናት ሰባት ልጆችን ያለ አባት ስታሳድግበት የነበረው ቤቷ ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዲወድም በማድረግ ከእነ ልጆቿ ሜዳ ላይ እንድትወድቅ አድርገዋል።
በአጠቃላይ በዚህ ጭፍጨፋ በርካታ የቁም እንስሳትን በመግደል እና ንብረታቸውን ሽጠው የገዙትን የጦር መሳሪያ ጭምር በመቀማት አርሶአሮችን ለከፍተኛ የሆነ ሰባዊ፣ ቁሳዊና ስነ- ልቦናዊ ጉዳት አድርሶባቸዋል ።
ስለሆነም የሰባዊ መብት ተሟጋች ቦታው ድረስ በአካል በመገኘት ጉዳዩን አጣርተው ለአለማቀፋ ማህበረሰብና መንግስታት ይህ አምባገነን የሆነው የአገዛዙ ስርዓት በእየ ጊዜው ምን ያህል የገዛ ዜጎቹን እየፈጀ እንደሆነ እንዲያውቁልንና እንዲያሳውቁልን ጥሪ እናቀርባለን።
ለሟቾች ነብሳቸውን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍልን ቤተሰቦች ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን ።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓም
+1
ጠንካራ ድርጅት በመፈጠሩ በየአካባቢው ተሰግስገው ህዝብን ሲዘርፉ የነበሩ ግለሰቦችን የማፅዳት ስራ ተሰርቷል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ በደቡብ ወሎ የንጉስ ሚካኤል ኮር በያዛቸው ቀጠናዎች ጠንካራ የፋኖ አደረጃጀት በመግንባት የአካባቢውን ቀጠና ለማስተካከል ተችሏል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና የምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ እና የምኒልክ እዝ ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ ትዝታ
ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ይዞ ጎንደሬ በጋሻዎችን ተቀላቀለ
የአማራ ክልል አድማ ብተና አባል የነበረው ዳዊት ሀብታሙ የተባለው ወጣት ሁለት ክላሽንኮቭ መሳሪያዎችን ይዞ በጀግንነት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሀይል (አፋብኃ ) ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴውድሮስ /አምስተኛ/ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር አካል የሆነውን አፄ ፋሲለደስ ብርጌድ ተቀላቅሏል።
ዳዊት ሀብታሙ አዲስ ተመራቂ ሲሆን ከተመደበ ሁለት ሳምንት ሳይሞላው ከጠዳ ከተማ መገጭ ግድብ በለሊት ተነስቶ ዛሬ ህዳር 2/2018 ዓ/ም አማራ ህዝብ ላይ አልተኩስም በማለት የጓዱን መሳሪያ ጨምሮ በመያዝ ጎንደሬዎቹን በጀግንነት ተቀላቅሏል።
ወጣቱን የአድማ ብተና አባል የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ አርበኛ ሞላ ከፌ ፣ የገስጥና ይላቅ ሻለቃዎች አመራሮች በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
ዳዊት ሀብታሙ "ወደ አድማ ብተና የገባውት መሳሪያ ለመታጠቅ ስለነበረ ሰልጥኘ አንድ ጥይት ህዝቤ ላይ ሳልተኩስ ምኖቴን ሁለት ክላሽ በማምጣት አሳክቻለሁ" ብሏል።
የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ አርበኛ ሞላ ከፌ የአድማ ብተና፣የመከላከያ፣ የሚኒሻ እና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ እስካሁን በተለያየ ጊዜ ከ50 በላይ አባላት ክፍለ ጦራችን መርጠው የተቀላቀሉ ሲሆን እንደየ ምርጫቸው የሚታገሉ እየታገሉ የሚሸኙም የተሸኙ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሰላም ተቀላቅለዋል።
አርበኛ ሞላ ከፌ አክሎም የአድማ ብተና፣የመከላከያ፣ የሚኒሻ እና የፖሊስ አባላት አገዛዙ ፀሀይ እየጠለቀችበት ስለሆነ አሽከርነታቸውን አቁመው ህዝባቸውን መርጠው ህዝባዊ ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓም
እያንዳንዱ የዚህን የዘንዶ አርማ ምልክትነት የተቀበለ ሰው ሁሉ… ከሀዲ እና የመፍዙዝ ሰለባ ነው።
ድንቅ የሆነ ክህደት አላየንም።
ከ30 ዓመት በፊትም አቡን ተብለው በወያኔ በተሾሙት አባ ጳውሎስ የአምሓራ ጀኖሳይድ መካዱን እናስታውሳለን፣ ዛሬም ጭፍጨፋውን ለማውገዝ ሀቅም ያጡት አቡን የጳውሎስ ትክ ሹመኛ የወያኔ ቅጥር ሰው ናቸው። ለአክሱም የግፍ ተጨፍጫፊዎች በጓሮ ያነቡ፣በህገወጥ መንገድ ለሚዲያ ተቋም ድምፅ የሰጡ አባት፣ ዛሬ አርምሞ የመረጡት እንዲሁ አይደለም። ልባቸው ደንድኖ ነው።
የህንድ እና ራሽያ፣ አርመኒያ አባቶች በግላጭ እየወጡ ሲያወግዙ አባ ማትያስ የት ገቡ?
አባ አብርሃም የት ተሰለቡ
አባ አሪዎስ የት እየጠጡ ነው?
+2
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ ጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር አቤ ጉበኛ ብርጌድ ‼️
የብልፅግና ሚሊሻ እየፈረሰ ነው ‼️
የአቤ ጉበኛ ብርጌድ ግዙፍ እና የጠላት እራስ ምትሀት ብርጌድ መሆኑ ይታወቃል ።በመሆኑም ከጨፍጫፊው አማራ ጠል ስርዓት በውስጥ ቀኜወቻችን እገዛ ጭምር ትልልቅ ጀብዶችን እየተጎናፀፈና በርካታ ከሚሊሻ እስከ መከላከያ አባልና አመራሮች ድረስ ስቦ በመምታትና በማስከዳት አንጋፋ ብርጌድ ሲሆን ስራችን ምስክር እንደሆነ ከምንሰራቸው ስራወች መረዳት ይችላል።
ከዱርቤቴ ከተማ ወደ ፋኖ የተቀላቀሉ ሚሊሻወች፦
1.አስማማው አስረስ
2. እስከዚያው አበበ
3.ቦጋለ አባት
4.አወቀ ፈረደ
ይቀጥላል ገና......
ምኒልክ ዕዝ የአደረጃጀት ዜና!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምንሊክ ዕዝ ልጁ እያሱ ኮር ራሱን እንደ ንስር ማንቆሪያውን እና ጥፍሩን አድሶ ላባውን ቀይሮ በአዲስ አደረጃጀት በአዲስ ስያሜ እና በአዲስ የድል መንፈስ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የአመራር ሪፎርም በማድረግ ብቅ ብሏል፡፡
ትግሉን እና ዘመኑን መዋጀት ለምናደርገው ረጅም እና ፈታኝ የትግል ጉዞ ትልቅ ስንቅ እና ጡንቻ እንደሚሆን ግልፅና የማይካድ ሃቅ ነው።
የልጅ እያሱ ኮር ከፍተኛ የኮር አመራርን ጨምሮ በውስጡ የሚገኙቱን
** ራንቦ ክፍለ ጦር
** ቤተ አማራ ክፍለ ጦር
** ራስ አሊ ክፍለ ጦር
** የጁ ክፍለ ጦር ከሻለቃ መሪ በላይ ያሉ አመራሮችን ትግል በሚፈልገው ደረጃ በጥልቀት በማወያየት እና በማገማገም ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት እና ለችግሮቹ የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ጉባዔውን አጠናቋል፡፡
ጉባዔው በታቀደው መሠረት ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ከድርጅት በመጡ የወታደራዊ እና የፖለቲካ ክንፍ አመራሮች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
በስፍራው በተገኙት የድርጅቱ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊው አርበኛ በለጠ ሸጋውን (ተራራው) ን ጨምሮ የድርጅቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና ምክትል ሃላፊ የሆኑት አበበ ቀዮ እና አሰፋ መሰለ (አሳምነው) በተገኙበት ጉባዔ እጅግ ድንቅ እና ለቀጠናው አስተማሪ የሆነ ሪፎርም ለመስራት ተችሏል፡፡
በሪፎርሙ ከኮር አመራርን ጨምሮ የክፍለ ጦር አመራር ለውጥ ከማድረግ ጀምሮ አራቱን ነባር ክፍለ ጦሮች መጠሪያቸውን ስም ጭምር በመቀየር ሠራዊታቸውም አዲሱ አመራር በፈለገው ሂደት ተሰባጥሮ ወደ ሁሉት ግዙፍ ክፍለ ጦር እንዲታጠፉና መጠሪያ ስያሜያቸውም ወደ ቁጥር በመለወጥ የልጅ እያሱ ኮር 23ኛ እና 24ኛ ክፍለ ጦር እየተባሉ እንዲጠሩ ተወስኗል፡፡
በቀጠናው የመጀመሪያ የሆነውን እና ፈር ቀዳጅ የሆነውን የሠራዊት ውህደት እና የቁጥር ስያሜ ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን ታምኗል፡፡
በሪፎርሙ መሠረት የኮሩ ወታደራዊ ክንፍ ላይ ሠፊ ሪፎርም የተደረገ ሲሆን የቤተ አማራ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው እንዳሻው ወታደራዊ አዛዥ ሆኖ ሲሾም የየጁ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ፶ አለቃ ሞላ አባተ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ በመሆን ኀላፊነታቸውን ተረክበዋል፡፡
አዲሱ መዋቀር
1 አርበኛ ሰለሞን አሊ ሰብሳቢ
2 አርበኛ እንዳሻ ጌታሁን ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ
3 አርበኛ ሲሳይ አየለ (ሳተናው) ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ኀላፊ
4 አርበኛ ፶ አለቃ ሞላ አባተ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ
5 አርበኛ ዳንኤል አስረስ አስተዳደር
6 አርበኛ ቦጋለ ሞሌ ምክትል አስተዳደር
7 አርበኛ ሽመልስ አወል ሎጅስቲክ
8 አርበኛ እርገት አያሌው ም/ሎጅስቲክ
9 አርበኛ ሱሃሊ ሸኩር ዘመቻ
10 አርበኛ ዳንኤል ዋጋው ህዝብ ግኑኝነት
11 አርበኛ መሃመድ ፈንታው ኦርድናንስ
12 አርበኛ አሰፋ አባተ የሰው ኀይል
13 አርበኛ ዮሃንስ ከልክሌ ፋይናንስ
በማድረግ ነባሩን እና አዲሱን አመራር በማጣመር ኮሩን በታላቅ ኀላፍነት ክብሩን እና ሞገሱን አሁን ካለው በላይ በማግዘፍ በጥበብ በማስተዋል እና በፍፁም አማራዊ ስነልቦና እንዲመሩ ቃለ መሃላ ጨምሮ አደራም ጭምር ተሰጥቷቸዋል፡፡
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 2/2018 ዓ.ም
+1
የድሮን ጥቃት በሰከላ ወረዳ
√ √ √
ሰከላ ወረዳ አጉት የመጀመሪያ ት/ቤትን በድሮን ዛሬ በ2/3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ በ2:00 ሰዓት ያፈረሰው ሲሆን ትምህርት ቤት አጥር ግቢ ሳር አጨዳ ላይ የነበረች አንድ ንፁሀን ሴት ከማቁሰል ውጭ ሌላ የደረሰ ጉዳት የለም ።
ዝርዝር መረጃውን በቪድዮ ይዘን እንመለሳለን ።
‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወደ ማይቀረው የድል ጉዞ ደረጃውን አሳድጎ እየመጣ ነው። ታማኝ መረጃዎች ለማግኘት ከታች ባለው የሚዲያ ድምፆች፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
‼️‼️ሰበር ዜና‼️‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወደ ማይቀረው የድል ጉዞ ደረጃውን አሳድጎ እየመጣ ነው። ታማኝ መረጃዎች ለማግኘት ከታች ባለው የሚዲያ ድምፆች፡፡
ተቀላቀሉት Join👇👇
"በዚህ ሊንክ ግቡ 👇👇
https://t.me/abcdefghijklmnopqrstuvwxyz07116
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ይህ ትውልድ የነፃነታችን ቀይ መስመራችን ነው አለቀ
አማራነት እስከ ቀራኔዎ ድረስ የምንወጣበት ሰፊው የነፃነት ተምሳሌትነ ነው አንድ ሙህር ስለ አገሩ ታሪክ ሳያቅ ሰል አውሮፓና አሜሪካ ታሪክ ያቃል ማለት በቅሎ አባትህ ማነው ቤሉት ፈርስ አለ እንደማለት ነው።
ፋኖነት የአማራው የነፃነት መንፋሳዊ እስትራቲጀካዊ ፖለቲካዊ መዋቅርን ያካተተ የአዲሱ ትውልድ ማሳያ መሳሪያችን ነው ።
ለሕዝብ ታምኖ መታገል የበለጠ ክብርና ሞገስ እንዳለው በተግባር ማስረዳት ይጠበቅብናል!
ፖለቲካ ቁማር ሳይሆን ጥበብ ነው፡፡
ጥበብ መሆኑን ዘንግተው በፖለቲካው ለሚቆምሩ ድኩማን ፣ እውነትን ሁሌ ስለምንይዝ እንበልጣለን እንጅ አናንስም፤ እንሸንፋለን እንጅ ፣ አንሸነፍም፤ ለሴራ ፖለቲካ እጅ አንሰጥም፤ከመሽኮርመም ፖለቲካ ወጥተን ለአማራ ህዝብ የማይቀሬ የአንድነት ህይወታችንን ትልቁን ቤታችንን ለመስራት ዝግጁ ነን!!
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ዳዊት
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያ አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ልጇን ያጣች እናት ወደ ፋኖ ገባች!!
የሴቷ አርበኛ ሳራ ትባላለች:: በምዕራብ ወሎ ግንባር ጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ ነዋሪ ስትሆን ምግብ ቤት ከፍታ ቤተሰብ ስትመራ ኖራለች::
ፋኖ ሮቤል ካሳዬ የሚባለውን ልጇን የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት አስፋልት ላይ እየገተተ አሰቃይቶታል:: ነጋ ጠባ ልጇን ዘረኛው ሰራዊት ሲያሰቃይባት እና ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሞበት ቁስለኛ አድርጎት በስተመጨረሻም 5 ወር ከ15 ቀን ጮሪሳ አስሮ የግፍ ግፍ ፈጽሞበት ሲያበቃ ለቆት ወደ ትውልዲ አካባቢው ከተመለሰ በኋላ ወደ ፋኖ ገብቶ ነበር:: በነገራችን
በዚያን ቅጽበት እስኪ ቢያንስ ቁስልህ ይዳን በማለት ዘመድ ወዳጅ ሲመክረው ከወላጅ እናቱ ጋር ስለውሳኔው በሚያወጋበት ወቅት እናቴ የልብ ቁስል ነው እንጅ የማይድነው ሰው የሚያየው የገላው ቁስልማ ቀላል ነው እንዳላት ታስታውሳለች:: ልቤ ቆስሏል ከእንግዲህ እነሱን እስከ ሞት ድረስ መዋጋት ነው ያለብኝ ብሏታል::
በዚህ ውሳኔው መሰረት በጃማ ግንባር የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ ኃይል ተቀላቅሎ በፊታውራሪነት ታግሏል::
ፋኖ ሮቤል ሞትን የማይፈራ ጀግና ታጋይ እንደነበር ጓዶቹ ይመሰክራሉ::
ሞት አይፈሬው ፋኖ ሮቤል በጃማ ግንባር ማሞ ቆላ (ወደ ሸክፍ መሄጃው ላይ) በተደረገ ትንቅንቅ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ካደረሰ በኋላ አንድ ጥይት ስትቀረው ራሱን ማጥፋቱን ነው ለማረጋገጥ የቻልኩት::
እኔ ለእናንተ እጄን አልሰጥም ብሎ ራሱን አጠፋ ያሉት ጓዶቹ ፋኖ ሮቤል እጅግ በጣም ደፋር መሆኑን ነው የመሰከሩት::
በጣም ልቤን የነካኝ ነገር ቢኖር ፋኖ ሮቤል ለእናቱ ይህ ፎቶ ማልቀሻ ይሆንሻል ብሎ አሳጥቦ ግድግዳ ላይ መስቀሉን ሲነግሩኝ ነው:: ሞትን አልፈራም የወጣሁት ልሞት ነው ይል የነበረው ጀግናው ወንድማችን ወላጅ እናትን የደጎሎ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች ከማፅናናት ይልቅ ይሄኔ ልጅሽ የመንግስት ሚሊሻ ቢሆን ኖሮ በካሳ መልኩ ብር ታፍሽ ነበር ይሏት እንደነበርም ነው የሰማሁት:: እሷ ግን እንኳንም ለአማራ ህዝብ ጠላት ሆኖ ታሪኩን እና ታሪኬን ያላበላሸ እንጅ ልጄን በገንዘብ የምሸጥ ሆዳም አይደለሁም እንዳውም እኔም ለአማራ እሞታለሁ ብላ ጠብመንጃ ነከሰች::
አሁን ላይ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ዋሲል ክፍለ ጦር ፊታውራሪ ናት!!
በድል ይመልስሽ እህትዋ:: የወንድማችንንም ነፍስ ይማርልን!
