ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر2 955
مشترکین
+424 ساعت
+127 روز
+38830 روز
آرشیو پست ها
+3
ሰበር!!
አራት /4/ የአገዛዙ 54ኛ ክ/ጦር 402ኛ ኮር 2ኛ ሪጅመንት አባል የነበሩ የሰራዊት አባላት በዛሬዉ ዕለት በቀን 08/09/2018 ዓ/ም ከጃንሱማ በመነሳት ከነሙሉ ትጥቃቸዉ 305ኛ ጎቤ መልኬ ኮር 52ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
እኒህ የሰራዊት አባላትም እንደገለጹት የሃገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ ሲገባዉ አገዛዙ ግን ለፓለቲካ ጥቅም እና ስልጣን ማራዘሚያ እንደ መሣርያ በመጠቀም በአለም አቀፍ እውቅና እና ክብር ያለውን የመከላከያ ተቋም ክብር እንዲያጣ አድርጓል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን የወገናችን እና የአገራችንን ደህንነት ከውጭ ጠላት ለመጠበቅ እንጅ ራሣችን በራሣችን አጥፍተን እና ተጣፍተን ሀገራችን ለማፍረስ አላማ የለንም በሚል ዉሳኔ እንደመጡ ገልፀዋል።
አርበኛ አንደርግ ጫቅሉ!!
🌟የ77ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በጠላት ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈጽማለች!!
{ግምቦት 08/09/2018 ዓ.ም}
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት መነሻው ከቡሬ ያደረገውን ጠላት መምጫ መንገዱ ላይ ደፈጣ በመያዝ አከርካሬውን በመምታት ሙት እና ቁስለኛውን አሸክመው በመጣበት እግሩ እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።
ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ ጓዙን ጠቅልሎ ከቡሬ ወደ ደረቋ ከተማ እንቅስቃሴ ያደረገው ጠላት ከጥዋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ አንደኛ ሬጅመንት በከፈተችው ጥቃት 6 መከላከያዎች ሲገደሉ ከ10 በላይ ቀላል እና ከባድ ቁስለኛ ማድረጓን ሬጅመንቷ አስታውቃለች።
ከፍተኛ ጉዳትን እያስተናገደ የሚገኘው ከቡሬ የመጣውን ለማገዝ ከአጉት እንቅስቃሴ ቢያደርግም ከጥቃት አላዳናቸውም ስትል 1ኛ ሬጅመንት አክላ ገልጻለች።
✅የነገ ተስፋችን በእኛ እጅ ይፃፋል:- አርበኛ ዘመነ ካሴ ባውቄ💪
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
{ግምቦት 08/09/2018 ዓ.ም}
ቀን ግንቦት 07/2018 ዓም
ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች አሰመረቀ"
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በደማቅ አሰመርቋል። ዛሬ ይህን የምረቃ ፕሮግራም ስናካሂድ ጨፍጫፊው የአብይ ስርዓት በነፋስ መውጫ ከተማ የምርጫ ድጋፍ ሰልፍ በተለመደ የጭካኔ ክንዱ በዋቢ ድርጅት በር የረሸናቸውን አስከሬን እንዳይነሳ በመከልከል ላይ እያለ: ለወራት እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው የቆዩ የባጃጅ ሹፌሮችን በየቤታቸው ለድጋፍ በማስወጣት : የማንኛውም ንግድ ድርጅቶች በማዘጋት : ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ቢሮዎች ተዘግተው እንዲወጡ : በኑሮ ውድነት ዳሽቆ የሚገኘውን ማህበረሰብ እና ትናት ሳሊና ጎብጎብ ረሽነው የተረፋ ካህናትን እንዲሁም በግፋ የተገደሉባቸው ቤተሰቦች ጥቁር እንደለበሱ አስገድዶ በማወጣት ላይ እያለ ከከተማ በመውጣትም ወደ ፋኖ የቡድን መሳሪያዎችን በመተኮስ እንደለመደው እየወጣ እየገባ ከሚወሸቅበት ዋሻ ውሏል።
" ፅናት መሰረታችን ነው " የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አመራሮች ትናንት ለአማራ ህልውና ስንወጣ ነፃነት ለተገፋው አማራ ሀቀኛ እምነትና መተማመን ስለቻልን አብረውን ከጎን የነበሩ ወንድሞችን ስናጣ ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን የጀመሩትን በበላይነት ለማጠናቀቅ እንጅ ጀምረን ለማቋረጥ አለመሆኑን ሰራዊታችን እና ህዝባችን ሳይሆን ጠላቶቻችንም መስክረውታል ቁጥራችን: ድላችንና ትጥቃችን አበዛን እንጅ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
እናንተን አሰልጥነን በክህሎትና አስተሳሰብ አብቅተን ስናስመርቅ የአማራን የግፍ ፅዋ ለመሰበር አናንተን ለየፀና መሰረት አስቀምጠናል: የተፈተነው የከበርነውን የከበርነውን መሰረት : የፀናውን የማዕዘን ድንጋይ እናንተን በአላማ ስናንፅ ልናፍር ሳይሆን አምነን በኩራት ነው። ሞቱ የቀረበው ብልፅግና ከወላጅ አባቱ ኢህአዴግ ጎን ቅበሩኝ ያለው ከአፋፍ ጫፍ ሁኖ የሚናዘዘው የአማራን ህዝብ እንባ ብቻ ሳይሆን ደም ያፈሰሰው በርካታ ልቦችን የሰበረው ጊዜው ደርሶ በቅርብ ለዘላለም እንዲሰናበት ብአዴንም በሰላም አርፎ
በአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ ትዝታ በልብ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር የተሰጠው ቃለ መሀላ ፀንቶ ይኖራል።
# ድል ለአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
# ለራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ሻምበል ተስፋ ቃል አቀባይ
+1
የብልፅግናውን አገዛዝ ፍርክስክሱን ያወጡ ፣ የመርሳ ከተማን የፀጥታ መዋቅር እርስ በርሱ የማይተማመንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ያደረጉ እንዲሁም የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታማኝነት እና በሚስጥር እንዲፈፀም ያደረጉ የ35ኛ ክፍለጦር ስፔሻሊስቶቹ ተልዕኳቸውን በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኋላ ኸደ አሃዳቸውና ጦር ሰፈራቸው ሲመለሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አስራ ሶስት(13) ሚኒሻዎችን ዶግ አመድ ያደረጉት ፋኖ ሀሰን በንቲ እና ፋኖ ሁሴን ይማም በሰራችሁት ታሪካዊ ስራ ኮርተንባችኋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 08/2018 ዓ.ም
የአደረጃጀት ዜና
ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አደረጃጀትን የማዘመን ስራዎች በወሎ ቤተ-አማራ ተጠናክረው ቀጥሏል!
የአማራ ሕዝብ እያደረገ ባለው የሕልውና ተጋድሎ ዘመን አይሽሬ እና አንፀባራቂ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኘው የምስራቅ ኮኮቦቹ ስብስብ የሆነው ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር አንድ ሳምንት የፈጀ ጥልቅ የስራ ግምገማ በማድረግ የኮር አደረጃጀቱን በመስራት የአመራር መዋቅሩን ይፋ አደረገ!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ጥልቅ የስራ ግምገማ በማድረግ ለህልውና ትግሉ ስኬታማነት በሚመጥን መልኩ አደረጃጀቱን በመስራት መዋቅሩን ማዘመኑና ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞም በስሩ የሚገኙ ኮሮችን ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ በማድረግ እያደራጀ ይገኛል::
በዚህ መሰረት የምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ 101ኛ ኮር አንድ ሳምንት የፈጀ ጥልቅ የስራ ግምገማና ተሃድሶ በማድረግ የሰራው አዲሱ የአደረጃጀትና የአመራር መዋቅር እንደሚከተለው ይሆናል፦
1. ሰብሳቢ____አርበኛ ጌታሁን ሲሳይ
2. ወታደራዊ አዛዥ_አርበኛ ደባሽ መምሬ
2.1 ም/ወታደራዊ አዛዥ__አርበኛ እንድሪስ ጉደሌ
2.2 ዘመቻ መምሪያ__አርበኛ ካሳ አበበ
•ም/ዘመቻ መምሪያ_አርበኛ አድኖ ሲሳይ
•መገናኛ ሃላፊ_አርበኛ**
2.3 ሎጀስቲክስ_አርበኛ ጋሻው ንጉስ
•ስርጭት__አርበኛ ሞሃመድ ትኩ
•ኦርድናንስ____አርበኛ መቶ አለቃ ጥበቡ ታከለ
2.4 ስልጠና መምሪያ__አርበኛ አምሳ አለቃ ሲሳይ አሰፋ
3. ወታደራዊ አስተዳደር__አርበኛ ገብረፃዲቅ መሸሻ
3.1 ፋይናንስ_አርበኛ በላይ ንጋቴ
3.2 ኦዲተር___አርበኛ አብዱ ዘመን
3.3 ህክምና ሃላፊ___አርበኛ ንጉስ እያሱ
3.4 የሰው ሃይል___አርበኛ ጌታሁን ረዳይ
3.5 ሃብት አፈላላጊ___አርበኛ ወንድሙ እንዳሻው
4. ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ_አርበኛ ዝናቡ አድኖ
4.1 ህዝብ ግንኙነት __አርበኛ ንጉስ አበራ
•ሚዲያና ኮምንኬሽን_አርበኛ ጥላሁን ገሰሰ
4.2 አደረጃጀት ሃላፊ__አርበኛ አሰፋ መለሰ
4.3 ህዝብ አስተዳደር___አርበኛ ጌታየ ተስፋየ
4.4 ህግ ክፍል____አርበኛ ሰይድ የሱፍ
4.5 መረጃና ደህንነት___አርበኛ *
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ101ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኋላፊ አርበኛ ንጉስ አበራ መረጃውን አድርሷል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 8/2018 ዓ.ም
የአሳምነው አናብስቶች፦ ያቺ የግፍ ምድር ኤፍርታናግድም(አጣዬ) ያፈራቻቸው የሽምቅ ውጊያ ጥበብ ባለቤቶች!!
ውድ የትግል ጓዶቼ💪
በአማራ ምድር ላይ የጀግንነት ታሪክ አዲስ አይደለም፤ ታሪኩ ግን ዛሬም በአዲስ ምዕራፍ፣ በአዲስ ጀግኖች ብዕርና ደም እየተጻፈ ይገኛል። ከእነዚህ ድንቅ የታሪክ ባለቤቶች መካከል በኤፍራታ ግድም ወረዳ፣ ልዩ ስሟ አጣዬ ካራለጎማ በተባለችው ታሪካዊ ስፍራ ተወልደው፣ የምድርንና የሰማዩን የውጊያ ጥበብ አዋህደው የያዙት የነጻነት ቀንዲሎች ይገኙበታል። የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ስር የሚገኘውን ታላቁንና ስመ-ገናናውን የሰባት ለሰባን ክፍለ ጦር በመምራትና በማስተዳደር፣ ጠላት ስማቸውን ሲሰማ የሚንቀጠቀጥላቸው የጦር ሜዳው ፈርጦች አበባው ዘለቀ እና አረጋ ሙሉነህ!
አበባው ዘለቀ፦ የስትራቴጂው ንስር ዕቅድ በጭንቅላት ውስጥ ይጸነሳል፤ በጦር ሜዳ ላይ ደግሞ ፍጹም ሆኖ ይተገበራል!አበባው ዘለቀ በጦር ሜዳ ላይ ዝምተኛ ግን እንደ ንስር አርቆ የሚያይ መሪ ነው። ጠላት ባላሰበው አቅጣጫ ገብቶ ውዥንብር መፍጠር፣ የወታደራዊ ስልቶችን ድርና ማግ ማስተሳሰር የእርሱ ልዩ ተሰጥኦ ነው። በአጣዬ ካራለጎማ ተራሮች ላይ ያደገው ይሄ ጀግና፣ የኮረብታዎቹን አቀማመጥ ብቻ ሳይሆን የጠላትን ስነ-ልቦና ጠንቅቆ ያውቃል። እርሱ የሚመራው ክፍለ ጦር ወደ ውጊያ ሲገባ እንዲሁ በስሜት አይደለም፤ እያንዳንዱ ስጉድ፣ እያንዳንዱ የተኩስ መስመር አስቀድሞ በሂሳባዊ ቀመር የተሰላ ይመስል ፍጹም ነው። አበባው ዘለቀ ለአሳምነው አናብስቶች የመድኃኒት ያህል አስተማማኝ፣ ለጠላት ግን ጨለማን ይዞ የሚመጣ የጦር ሜዳ መሃንዲስ ነው።
ብረት በሰው እጅ ላይ ሲሆን መሳሪያ ነው፤ በጀግና እጅ ላይ ሲሆን ግን ታሪክ ሰሪ ነው! ስለ አረጋ ሙሉነህ ሲወራ የብረትና የእሳት ነጎድጓድ አብሮ ይነሳል። አረጋ በሜካናይዝድ የውጊያ ጥበብና ስትራቴጂካዊ እንቅስቃሴዎች ስሙ ገዝፎ የሚነሳ ድንቅ የጦር ሰው ነው። የቡድን መሳሪያዎችንና የጦር ታንኮችን እንደ እጁ ጣቶች አዟዙሮ፣ ጠላት የመሸገበትን ምሽግ አመድ ማድረግ የለመደው አረጋ፤ ሜዳውንና ጋራውን የብረት መጋረጃ የማልበስ ልዩ ጥበብ አለው። የእርሱ የጦር አመራር ብርቱና ማዕበላዊ ነው። ጠላት በሚመካበት የጦር መሳሪያና ኃይል ላይ ተመስርቶ የሚወረውረውን ጥቃት፣ አረጋ በማዕበላዊ የሜካናይዝድ አጸፋዊ ጥቃት ወደ ፍርክስክስነት ይለውጠዋል። አረጋ ሙሉነህ ሜዳ ላይ ሲያገሳ፣ ጠላት መሸሸጊያ ያጣል፤ ወገን ደግሞ በኩራት አንገቱን ያቀናል።
የሁለቱ ኃይሎች ውህደት አበባውና አረጋ አንዱ ጥበብና እቅድ፣ ሌላው ደግሞ ጉልበትና እሳት! እነዚህ ሁለት የአሳምነው አናብስቶች በአንድ ላይ ቆመው የሰባት ለሰባን ክፍለ ጦርን ሲመሩ ሰባት ለሰባ ክፍለጦር የማይበገረው የነጻነት ምሽግ ይሆኗል። ዛሬም በኤፍራታ ግድም ተራሮች ላይ፣ በአጣዬና በአካባቢው ሸለቆዎች ውስጥ የእነዚህ ጀግኖች ስም በክብር ይጣራል። ጠላት ስማቸውን ሲሰማ የሚደናበረውና የሚፈረካከሰዉ ያልምክንያት አይደለም፤ ከጀርባቸው የታሪክ እውነት፣ በውስጣቸው ደግሞ የአማራ ልጅ የማይበገረው የፋኖነት ወኔ ስላለ ነው!
ክብር ለአማራ ልጅ ፋኖ! ክብር ለሕዝብ ጋሻዎች! ከአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኮር ህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አማረ ታዘዘ ለውድ ጓዶቹ የተሰጠ ምስክርነት
ቀን ግንቦት 07/2018 ዓም
ራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች አሰመረቀ"
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ለወራት ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በደማቅ አሰመርቋል። ዛሬ ይህን የምረቃ ፕሮግራም ስናካሂድ ጨፍጫፊው የአብይ ስርዓት በነፋስ መውጫ ከተማ የምርጫ ድጋፍ ሰልፍ በተለመደ የጭካኔ ክንዱ በዋቢ ድርጅት በር የረሸናቸውን አስከሬን እንዳይነሳ በመከልከል ላይ እያለ: ለወራት እንዳይንቀሳቀሱ ታግደው የቆዩ የባጃጅ ሹፌሮችን በየቤታቸው ለድጋፍ በማስወጣት : የማንኛውም ንግድ ድርጅቶች በማዘጋት : ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ ቢሮዎች ተዘግተው እንዲወጡ : በኑሮ ውድነት ዳሽቆ የሚገኘውን ማህበረሰብ እና ትናት ሳሊና ጎብጎብ ረሽነው የተረፋ ካህናትን እንዲሁም በግፋ የተገደሉባቸው ቤተሰቦች ጥቁር እንደለበሱ አስገድዶ በማወጣት ላይ እያለ ከከተማ በመውጣትም ወደ ፋኖ የቡድን መሳሪያዎችን በመተኮስ እንደለመደው እየወጣ እየገባ ከሚወሸቅበት ዋሻ ውሏል።
" ፅናት መሰረታችን ነው " የራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አመራሮች ትናንት ለአማራ ህልውና ስንወጣ ነፃነት ለተገፋው አማራ ሀቀኛ እምነትና መተማመን ስለቻልን አብረውን ከጎን የነበሩ ወንድሞችን ስናጣ ተስፋ በመቁረጥ ሳይሆን የጀመሩትን በበላይነት ለማጠናቀቅ እንጅ ጀምረን ለማቋረጥ አለመሆኑን ሰራዊታችን እና ህዝባችን ሳይሆን ጠላቶቻችንም መስክረውታል ቁጥራችን: ድላችንና ትጥቃችን አበዛን እንጅ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
እናንተን አሰልጥነን በክህሎትና አስተሳሰብ አብቅተን ስናስመርቅ የአማራን የግፍ ፅዋ ለመሰበር አናንተን ለየፀና መሰረት አስቀምጠናል: የተፈተነው የከበርነውን የከበርነውን መሰረት : የፀናውን የማዕዘን ድንጋይ እናንተን በአላማ ስናንፅ ልናፍር ሳይሆን አምነን በኩራት ነው። ሞቱ የቀረበው ብልፅግና ከወላጅ አባቱ ኢህአዴግ ጎን ቅበሩኝ ያለው ከአፋፍ ጫፍ ሁኖ የሚናዘዘው የአማራን ህዝብ እንባ ብቻ ሳይሆን ደም ያፈሰሰው በርካታ ልቦችን የሰበረው ጊዜው ደርሶ በቅርብ ለዘላለም እንዲሰናበት ብአዴንም በሰላም አርፎ
በአማራ ብሎም ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ ትዝታ በልብ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር የተሰጠው ቃለ መሀላ ፀንቶ ይኖራል።
# ድል ለአማራ ህዝብ
# ድል ለአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
# ለራስ ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ሻምበል ተስፋ ቃል አቀባይ
በአማራ ህዝብ ጥላቻ ያበደው አገዛዝ፣ ዛሬም የዘመናችን ጨካኙ ጥቁር ሂትለር የንፁሀን አርሶ አደር መኖሪያ ቤትን ሙሉ በሙሉ በድሮን አውድሟል።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
ግንቦት 08/2018ዓ.ም
የኢተዮጵያ ህዝብ የመከራ ቋት የሆነው የ21ኛው ክፍለዘመን የፋሽስታዊ አገዛዝ ዛሬም እንደለመደው የአማራን ህዝብ በከፍተኛ የወለድ ብድር በገዛው ድሮን ህዝብን የመጨፍጨፍ መደበኛ ስራው ያደረገው አገዛዝ የንፁሀን አርሶ አደሮችን መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ ሲያወድም፣ በወስጡ የነበሩ የቤት እንስሳቶችን ጨምሮ የቤት ንብረቶች በተፈፀመው የድሮን ጥቃት ወደ አመድነት ተቀይረዋል።
ትላንት ግንቦት 07 ቀን 2018ዓ.ም በአማራ ህዝብ ጥላቻ ያበደው የኦሆዴድ መራሹ ብልፅግና አገዛዝ በሸዋ ጠቅለይ ግዛት ተጉለትና ቡልጋ አውሩጃ በሞጃና ወደራ ወረዳ በሳሲት ክላስተር ስር በሚገኘው በጋውና ቀበሌ ከምሽቱ 3:30 ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት የአቶ በቀለ ሸዋአበረ የተባሉ የጋውና ቀበሌ ነዋሪ የግል መኖሪያ ቤትን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን ዕዙ አረጋግጧል።
"ትረፊ ያላት ነፍስ፣መከራ አያጠፋትም!" እንዲሉ አበው ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት አቶ በቀለ ሸዋአበረ እና ቤተሰባቸው ለግል ማህበራዊ ጉዳይ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄዳቸው የሰው ህይዎት ባይጠፋም፤ ነገር ግን ሀብትና ንብረታቸው በተፈፀመው የድሮን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የአማራ ህዝብ መገልገያ ተቋማትን የጥቃት ኢላማ በማድረግ፣ ሀብትና ንብረቱን በመዝረፍ፣ የህዝባችንን የግል መኖሪያ ቤት በማውደም፣በአማራ ህዝብ ላይ ጅምላ ጭፍጨፋ በመፈፀም የሚታወቀው አረመኔው የብልፅግናው አገዛዝ ተጨማሪ የመጨፍጨፊያ የአገዛዝ ጊዜ ለማግኘት የይስሙላ የጨረባ ምርጫ ለማድረግ በድሮን እየጨፈጨፈ ያለውን ህዝብ "የይምረጡኝና ልግደላችሁ" ድምፅ እየጠየቀ ይገኛል።
በመሆኑም እንደ ህዝብ አማራ በመሆናችን ብቻ ሊያጠፋን የመጣውን ጨካኝ አገዛዝ ከጀግናው የአማራ ፋኖ ጋር በመቀናጀት በህዝባዊ ማዕበል እንቢተኝነት የጨፍጫፊውን አገዛዝ ዕድሜ ለማሳጠር ለሁለንተናዊ ትግል አማራዊ ግዴታህን ትወጣ ዘንድ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ለተከበረው ህዝባችን መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል።
ይህ በእንዲሕ እንዳለ የአገዛዙ ዙፋን አሥጠባቂ ሰራዊት በአሳግርት ወረዳ የማህበረሰብ የቁም እንስሳ መዝረፉን ነዋሪዎች ገለፁ። በአሳግርት ወረዳ ከጊናገር ከተማ ሜጢ ቀበሌ ልዩ ቦታው ጓላገር ጎጥ ተብሎ ከሚጠራው ስፋራ የአገዛዙ ሰራዊት የሁል ጊዜ የዘረፋ ተግባሩን በማህበረሰብ ላይ አድርሷል።
የተዘረፈባቸው የቀበሌው ነዋሪዎች:-
1ኛ. ጎሳ ልዑል ሰገድ ከ45 በላየ ከብትና ፍየሎች
2ኛ. ደመላሽ ሽመልሥ 36 ፍየሎችና 4 ከብቶች
3ኛ. ተገኝ ልሳነ 29 በጎችና ፍየሎች
4ኛ. ወንድዬ በለጠ 23 በግና ፍየል (5) ከብቶች
5ኛ. ልዩ ነች ወሰኔ ከ12 በላይ ፍየሎች እንደተዘረፉባቸው ተበዳዮች ገልፀዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 08/2018ዓ.ም
ጎንደር ✊💪
ደራርቦ ማራኪው ሜጀር ጀነራል ዉባንተ አባተ 1ኛ ኮር በትናንትናው ዉጊያ የተቀረፀ ቪዲዮ✌️
የአብይን የሴራ ፖለቲካ የምናጋልጥበት ሰፊውን ስራ ይወዘን ብቅ ብለና የፊስቡክ አካውንታችን ይወዳጁን!!
https://www.facebook.com/share/1CmD4FL3eb/
#ህዝብን_የካደ_መጨረሻው_ሞት_ነው‼️
የጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝና የአብይ ወንበር ለማስጠበቀ የተሰለፈና በገዛ ሕዝብ ላይ እልቂት እየፈፅሙ መኖር አብቅቷል።
አሁንም አልረፈደም፡ ከጠላት ጎን ተሰልፋችሁ የምትገኙና ወደ አሸናፊው ለመዝለል አጥር ላይ ተንጠልጥላችሁ የተቀመጣችሁ ሰዎች ባስቸኳይ ሕይወታችሁን አትርፉ።
ሲሆን የሕልውና ትግሉን ተቀላቅላችሁ ህልውናችሁን አስከብሩ፡ ካልሆነ ግን ለልጆቻችሁና ለቤተሰባችሁ ለመኖር ከአገዛዙ በመውጣት ሕይወታችሁን አትርፉ።
በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር በሰከላ ወረዳ አጉት ከተማ በፈፀመው ከባድ ጥቃት ከተገደሉ የመከላከያ ሻለቃ አዛዥ ጨምሮ ብዛት ያለቸዉን የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ ወታደሮች መካከል የጥቂቶች ምስል ነው።
#እጅ_ስጡ_አትለቁ‼️
#ከአንገት_በላይ #ስፔሻሊስቱ ፋኖ ይችላል💪
07/ዐ9/2018 ዓ.ም
