fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 414
مشترکین
+1324 ساعت
+277 روز
+1 21530 روز
آرشیو پست ها
የገዳዩቹን ጀርባ እያከከ ለሚኖረው የ #አማራ_ልሂቅ የሚከተሉትን ልናስታውሰው እንወዳለን!! ህዝባችን ፈፅሞ ዘር መጥፋት አደጋ ውስጥ ነው ስንላችሁ ለማትሰሙን ማስተዋሻ ነው። "አማራ ደንቅ ህዝብ የጀግና ዕሴት ባለቤት ነው" ዳሩ እናንተን ታካኪዎቹንና በሆድ የምታመልኩትን ፈጣሪ ልቦና ይስጥለት እላለሁ!! የባንዳ ምልክቱ የአማራ ብልፅግና ህዝባችንን ከ1983 እስከ 2018 ዓም ድረስ እንዴት መጫዎቻ እና መሳለቂያ እንዳደረገው እንኳ አያርፍም!! ይልቁንስ ሰሞኑን ባዳ እና ባንዳ የሚል ትርክት በአሳዳሪዎቹ ተጭኖ እየዋተተ ይገኛል። "ፅንፈኛ እና ጃዊሳ" የሚለው ተቀይሮ ደግሞ ስናዳሪዎቹ ሌላ ስም ለመትከል እየተጉ ነው። እኛም እንላለን ህዝባችንን ከፈፅሞ መጥፋት መከላከል ፅንፈኛ ካስባለ አዎ ፅንፈኞች ነን እንላችሗለን። በመቀጠል ግን አማራ ምን ይሁንላችሁ ስናዳሪዎች?? በመጀመሪያ አማራው የሆነውን ነገር ስለምትረሱት የሆነውን እንኳን እስኪ እናስታውሳችሁ!! ❶ የካቲት 1983 ዓም ህፃናትን ጨምሮ 500 አማራዎች ት/ቤት ክፍል ውስጥ ተዘግቶባቸው ወለጋ ላይ በእሳት አልተቃጠለም?? ❷ 1984 አርሲ ላይ 250 የአንድ መንደር አማራዎች የታረዱ ሲሆን የአንድት እርጉዝ ሴት ሆድም ተቀዶ ፅንሱ አልወጣም ወይ?? ❸ ሰኔ 24/2004  ቤሻንጉል መተከል በአንድ ቀን 400 አማራዎችን በመጨፍጨፍ የ80 አማራዎችን ስጋ ጠብሰው የበሉ ሲሆን የሁለት አማራ ሴቶች ጉበት እና ኩላሊት በጥሬው አልተበላም ወይ?? ❹ ህዳር 29/2013 ጎንደር በ 1 ቀን 2500 አማራዎች አልተገደሉም ወይ?? ❺ ሰኔ 11/2014  ወለጋ ከ5ሺህ በላይ አማራዎች በአንድ ቀን ጀምበር የተጨፈጨፉ ሲሆን የታረዱ እናቶች ማህፀን በመሰንጠቅ ፅንስ አልወጣም ወይ?? ❻ ጥቅምት 24/2013/14 ሙሉ የአማራ ክልል የብልፅግና እና TPLF የጦር አውድማ ሆኖ ከ1 ትሪሊየን በላይ ሃብት አልወደመም ወይ?? ❼ ጥር 2015  ሻሸመኔ ላይ የቤተ ክርስቲያንን መርከስ ለመታደግ በተከላከሉ 52 ሰዎች ላይ በጥይት፣በስለት እና በድንጋይ ተወግረን አልትገደልንም ወይ?? ❽ የካቲት 25/2015 የአድዋ ድልን ለማክበር አራዳ ጊዮርጊስ በተሰባሰቡ አማራዎች የጅምላ ጭፍጨፋ በማድረግ የ 5 አማራዎች አስከሬን አአ ላይ አልተጎተቸም ወይ?? ❾ የካቲት 2015 ዓም አንድት እናት በሌሊት ቤቷ ፈርሶ ልጇ በጅብ አልተበላም ወይ ጣፎ ላይ?? ❿ መጋቢት 2015 ዓም ከ40 ሺህ በላይ ቤት አአ እና አካባቢው ላይ የአማራ ቤቶች ተለይተው አልፈረሱምን?? ⓫ ሚያዚያ 2015 ዓም ከ 60 በላይ ትጥቅ የፈቱ የአማራ ልዩ ሃይል ጀውሃ ላይ በኦነግ አልተረሸኑምን?? ⓬ የአማራ ልዩ ሃይልን ከመርህ ውጭ ትጥቅ እንዲፈታ አልተደረገምን ?? ⓭ ከሃምሌ 5/2015 ዓም ጀምሮ ደግሞ ፋኖን ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ የፈፀመው ወረራ ሙሉ ክልሉን እያወደመው አስከ አሁን ክልሉ የጦርነት አውድማ አልሆነምን?? በአጠቃላይ የአማራው ህዝባችን የዘር ፍጅት ማሳያው ምንድነው ትላላችሁ ልሂቃን?? በእውነት የህዝባችንን ፈፅሞ መጥፋት ተባባሪ ከመሆን እንኳ የምትቆጠቡት መቼ እንደሆነ ባላውቅም በመራራው ተጋድሎ ውስጥ የአብይ አህመድ እና ግብረ አበሮቹ እኩይ ሴራ በትውልዱ ፅናት ከሺፏል። የአማራው ስቆቃ መዋቅራዊ እና ሰው ሰራሺ ሆኖ እንዲቀጥል ያደረጋችሁ የአማራ ብልፅግናና ዕጅ አስታጣቢዎቹ ግን በታሪክ ጥቁር አማራ መሆናችሁን ልታውቁት ይገባል። በአጠቃላይ በመረረው እና በህልውና ትግላችን ባንዳነት እና ስናዳሪነት ታሪክ የሚሆንበት ጊዜው ቅርብ ነው። ለሁሉም ለህዝባችን እና ለብሔራዊ አንድነታችን ሲባል መንቃትን እንምረጥ እላለሁ!! ነቄው ትውልድ የህዝቦችን ነፃነት በማረጋገጥ አማራውን ይታደጋል!! አበቃሁ!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ ጥቅምት 19-02-2018 Ashenafi Genan

ወቅታዊ መረጃን ለማግኜት https://t.me/MEREWA_MEDIA

የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው:: ከዘመቻ አባ ናደው መጠናቀቅ በኋላ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎችና ዕዞች ወደ ቤተ-አማራ የገባው የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት እየፈረሰና እየኮበለለ ምኒልክ ዕዝን በስፋት እየተቀላቀለ ነው:: የኦሮሞ ብልፅግና ልዩ ሃይል ኦሮሚያ ላይ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲፈፅመው የነበረውንና ዛሬም እየፈፀመው ያለውን ግፍ በተመሳሳይ የመከላከያ መለዮ ለብሶ ወደ አማራ ክልል በመግባት የሚፈፅመውን ግፍ እያየን እኩል የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብለን ልንጠራ አንችልም ያሉ አባላቶቹ ባለፉት አስር ቀናቶች ብቻ 46 ክላሽ 4 ጀሌ 11350 የክላሽ ተተኳሽ እንዲሁም 90 F1 የእጅ ቦምብ በመያዝ ከ50 በላይ ሰራዊት ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል:: ፋኖን ከተቀላቀሉት የሰራዊቱ አባላቶች መካከልም 1 ሬጅመንት አመራር 6 ሻምበል መሪ እና 5 ምክትል ሻምበል መሪ አመራሮች ይገኙበታል:: በቀጣይም የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝን ሰራዊት የማፍረስና የማስኮብለሉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን። ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️ https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk ‎

ይህ ፎቶ ከአሩሲው ፍጅት በተአምር የተረፈች የ ፰ ዓመት ሕፃን ነው።
+1
ይህ ፎቶ ከአሩሲው ፍጅት በተአምር የተረፈች የ ፰ ዓመት ሕፃን ነው።

በምሥራቅ  አርሲ  ሽርካ  ወረዳ ሄላ  ዘባባ ቀበሌ  ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡ በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል። MK TV ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት  17 ቀን 2018  ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል። ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት  ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡ በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18  ቀን  2018  ዓ.ም  ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ  እስከ  2017 ዓ.ም  ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ  ሲሆን  27  ኦርቶዶክሳዉያን  ደግሞ አሁንም  ድረስ  ታግተው  ያሉበት  እንደማይታወቅ  ነዋሪዎቹ  ለጣቢያችን  ገልጸዋል። በግድያ  ያላበቃው  መከራና  ስቃይ  በሽርካ  ወረዳ  ብቻ  በዘጠኝ  ቀበሌዎች  በሺዎች የሚቆጠሩ  ኦርቶዶክሳዉያን  መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡ ይህ  በእንዲህ  እንዳለ በወረዳው  ካሉ 37 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ16 በላይ የሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውንና  ከእነዚህም  መካከል 3ቱ  መሉ በሙሉ መዘረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡ የኦርቶዶክሳዉያን  መገደል  እንዲቆም  ለሀገረ ስብከቱና  ለመንግሥት  አካላት  በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግም  ምላሽ  እያገኙ  አለመሆናቸውን  ያነሱት  ነዋሪዎቹ  በዚህም አካባቢው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል  ሲሉ  ተናግርዋል፡፡ በተለይም በሀገረ ስብከት ደረጃ ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍም  ሆነ  ማጽናኛ  ለማደረግ ጥረት ባለመደረጉ  ማዘናቸውን የአካባቢው  ምእመናን  ገልጸዋል፡፡ እየደረሰ ያለው  የሰው ሕይወት እልፈት ፣ መታገትና የንብረት ውድመት ችግር እልባት አንዲያገኝ  የቅድስት ቤተ ክርሰስቲያን እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት  አሁንም ትኩረት ሰጥተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ©ማኅበረ ቅዱሳን

በወቅታዊ ጉዳዮች ከአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!
+1
በወቅታዊ ጉዳዮች ከአፋብኃ ቢዛሞ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ!

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰው ልጅ ነፍስ እጅግ ረክሷል ሲሉ ዶልተር አረጋ አባተ ገለጹ። ዶልተር አረጋ አባተ በአርሲ ዞን በተደጋጋሚ ስለሚደረገው የኦርቶዶክሳውያንን ግድያ በተመልከተ ጠንከር ያለ ሐሳብ ሰጥተዋል። በተለይም ደግሞ ላለፉት ሰባት ዓመታት የሰውን ልጅ ሞት ከቁም ነገር የማይቆጥረው ይኸ ገዳይ ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም፣ የሃይማኖት አባቶችና ተቋሞቻቸውም ጭምር ናቸው ብለዋል ዶክተር አረጋ አባተ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የኦርቶዶክሳውያን ነፍስ በዚህ ዘመን ያለበትን ሁኔታ ለተመለከተ ነገሩ ለማሰብም የሚያስቸግር ነው፡፡ ኦርቶዶክሳውያንን በተመለከተ ግድያውና ጭፍጨፋው የተፈጸመበት ቦታ፣ ክልልና አካባቢ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ጸጥ ይባላል፣ እንዲያውም በላይ በላዩ ይደጋግሙታል፡፡ ከሟች ወገንም የሚያጉረመርም የለም፡፡ ልብ በሉ ኦርቶዶክሳውያን አማራ ክልልም፣ አሮሚያ ክልልም ቢገደሉ የሕዝቡም ስሜት የመንግሥትም ምላሽ ተመሳሳይ ነው፡፡ በጸጥታ ማሳለፍ፡፡ እርግጥ ነው በኦሮምያ ክልል ያለው ኦሮቶዶክሳውያንን ማጽዳት በተለይ የአርሲው ጭፍጨፋ ወደር የሚገኝለት አይደለም ነው ያሉት ዶክተር አረጋ፡፡  እርግጥ ነው ሙስሊምም ቢሆን ኦሮሚያ ክልል ቢገደል የተለየ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ ልዩነቱ ግን በስልትና በዕቅድ የሚደረግ የሙስሊም ግድያ አልሰማንም፡፡ እንዲያውም ሙስሊሙ አማራ ክልል አንድ ግድያ እንኳን ቢኖር የሚያደርገው ጩኸት ተሰሚነት ስላለው ነገሮችን ማስተካከል ሲቻል አይተናል፡፡ ጭቆናን ለሚቃወሙ ሙስሊሞች አድናቆት አለኝ፡፡ እኔ የምናደደው ከፍየሏም በላይ የሆነውን አማራ ክልል ለሚደረግ ነገር ያለውን የውሐብያ ከአቅም በላይ የሆነ ጩኸታቸውን እንጂ ግድያንና በደልን መቃወማቸው ላይ አንዳች ተቃውሞ የለኝም፡፡ የምወቅሳቸው ሌላው ክልል የሚደረገውን የሙስሊምም ሆነ የኦሮቶዶክሳውያን ግድያ ልክ እንደ አማራ ክልሉ አጀንዳ ባለማድረጋቸው ነው፡፡ ይኸንን ነው ሴራና ለሰው ነፍስ ከመጨነቅ የሚያደርጉት አይደለም የሚያስብለው፡፡ ዶክተር አረጋ አክለውም፤ ማንኛውንም ግድያን ያለ ሃይማኖት ልዩነት መቃወም አለብን፡፡ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን ወይም እምነት የለሽ፣ ሰው በመሆኑ ብቻ የሰዎችን ግድያ ሰዎች  መቃወም አለባቸው፡፡ ይኸ ሰውነት ይባላል፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ጨዋታ መተላለቅን የሚወልድና እኩይም ነው ብለዋል፡፡ ይኸን ሁሉ የምለው በኦሮምያ ያለው ማቆሚያ የሌለው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ የአጋጣሚ ሳይሆን ሲስተማቲክና በዕቅድ የሚደረግ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ነገሩ ፖለቲካውና በዐላማ የሚደረግ ነው፡፡ ገዳዩ ቢቀያየርም ወይም አንዱ በአንዱ ቢያሳብብም፣ ለተገደዮች ግን ለውጥ የለውም፡፡ ለተገዳይ ሸኔ ቢገድለው፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ቢገድለው ምን ልዩነት አለው? አሁን የተያዘው ያለ ይሉኝታ የሚደረግ የዕለት ከዕለት ጭፍጨፋ ነው፡፡ በአጭሩ አሁን ኦርቶዶክሳዊያን ያለንበት ዘመን ዘመነ አፀባ፣ ዘመን ሰማዕታት፣ ዘመነ መከራ ነው፡፡ ጸሎታችን መሆን ያለበት ዘመኑን እንዲያሳጥረው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሰማዕታቱን መከራ ማሰቡን እንኳን እንዳንዘነጋው ነው፡፡ መከራውን በልልምጥም ይሁን በሕግ ማስቆም የማይቻል መሆኑን አይተናል፡፡ የሰማዕታቱ ደም ወደ ፈጣሪ ደርሶ መከራውን ያሳጥረው ዘንድ እንጸልይ ሲል አጠቃለዋል ዶክተር አረጋ አባተ፡፡

"የአማራ ሕዝብ ሕልውናው እና በክብር የመኖር መብቱ በማያወላውል ሁኔታ እስኪረጋገጥ ድረስ፣ ፋኖ የጀመረውን ትግል አያቆምም።"              ለንደን ፋኖ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የፓርላማ ምላሽ ላይ ከለንደን ፋኖ የተሰጠ መግለጫ ቀን: ጥቅምት 18፣ 2018 ዓ.ም ለንደን ፋኖ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው፣ በለንደን ስለተካሄደው የኢትዮጵያ የምክክር ኮሚሽን ተቃውሞ የሰጡትን ምላሽ በጽኑ እንደሚቃወም ይገልጻል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የተቃውሞ ዓላማዎቻችንን በቅጡ ያልተረዳ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ግፍ ለመደበቅ ያለመ እና እውነቱን የካደ አሳፋሪ ተግባር ነው።  በአማራው ሕዝብ ላይ በጦርነትና በጭፍጨፋ የተነሳ የመኖር እና ያለመኖር የሕልውና ስጋት እያለ፣ የሕዝብ ወኪል አስሮ መደራደር እንደማይቻል እና ''የምክክር ኮሚሽን" የሚባለው ስብስብ የገዢው ቡድን ሥልጣን ማራዘሚያ እንጂ የችግሩን ሥር መፍታት ዓላማው እንዳልሆነ ለንደን ፋኖ በእርግጠኝነት ይረዳል።  በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የራሱን ዜጎች ''አላውቃችሁም'' የሌላ ሃገር ዜጎች ናችሁ በማለት እጅግ አሳፋሪ ክህደት የፈጸመ መሆኑን በአንክሮት እናሳውቃልን። በመሆኑም የጠቅላይ ሚኒስትር ''ነይ ባዩ" አነጋገር የችግሩን ምንጭ ከመፍታት ይልቅ፣ ሕዝብን የማዘናጊያ መንገድ ብቻ እንደሆነ እናምናለን።  የአማራ ሕዝብ ሕልውናው እና በክብር የመኖር መብቱ በማያወላውል ሁኔታ እስኪረጋገጥ ድረስ፣ ለንደን ፋኖ የጀመረውን ትግል አያቆምም።  በአማራ ሕዝብ ላይእየተካሄደ ያለው ጦርነት እስኪቆም፣ የጅምላ ጭፍጨፋው ፍጻሜ እስኪረጋገጥ እንዲሁም በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ለፍትህ እንኪቀርቡ ድረስ፣ የለንደን ፋኖ ድምፁን አጠናክሮ ለዓለም ማኅበረሰብ ማሰማቱንና ለሕዝቡ ድምፅ መሆኑን ይቀጥላል። ድል የሕልውና አደጋ ለገጠመው የአማራ ሕዝብ! ለንደን ፋኖ - ለንደን፣ እንግሊዝ  (አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 18/2018) 

⛔በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ሰኞ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ምሽቱ 4:00 ሰዓት አከባቢ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ በሚባል ስፍራ ላይ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውና ሌሎች ደግሞ ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። "…ሰሞኑን በደብረ ወገግ አሰቦት ቅድስት ሥላሴ ገዳምም ገሚሱን አርደው፣ ገሚሱን አግተው በሚልዮን የሚቆጠር ብር እየጠየቁ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን የእነ አቡነ ሳዊሮሷ ቤተ ክህነት የመንግሥታቸውን ገፅታ ስለሚያበላሽ ዜናው እንዳይነገር ጫና ሲፈጥሩ እንደነበርም ተሰምቷል። "…በአሩሲው ጭፍጨፋ ላይ ጨፍጫፊዎቹን ከየቤታቸው በማውጣት በአደባባይ የረሸኗቸው ሲሆን ርሸናውን የፈጸሙትም በኦህዴድኦነግ/ብልጽግና መዋቅር የሚደገፉ እና ራሳቸውን "የኦሮሞ እስላማዊ መንግሥት" ብለው የሚጠሩ ኃይሎች መሆናቸውም ተገልጿል። እስካአሁን ከተጨፈጨፉት ኦርቶዶክሳውያን መካከል ፩፥ ማሙሽ ደበበ ~ ዕድሜ ~ 30 ፪፥ ትግስት ጅማ  ~ ዕድሜ ~ 50 ፫፣ ግዛው ከተማ ~  ዕድሜ ~40 ሲሆኑ ሥርዐተ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት ጥቅምት 18/02/2018 ዓም በዚያወወ በዘምባባ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መፈጸሙም ተዘግቧል።  "… በሌላ በኩል ፩፦ አስታጥቄ ደርቤ ፪፥ ከተማ ተክሉ ፫፥ በኃይሉ አበባየሁ ፭፦ ሲሳይ ከተማ …የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል።

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮ በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዝተን እየተለማመድነው የመጣነው የኦርቶዶክሳውያን ሞት ሊበቃ እና የሰው ልጆች ሁሉ የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊረጋገጥ ይገባል። በአካባቢው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ በአማኙ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ሊያስቆሙ እና መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል። ለወደፊቱም ቢሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቁብንን በርካታ ሥራዎች አለመሥራታችን ትውልዱን ዋጋ እያስከፈለው እንዳይኖር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መሥራት የሚገባን አያሌ ተግባራት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም። በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸው አጽናኝ ቅዱስ መንፈስን ይላክላቸው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ ! ©ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ሰበር የድል ዜና!!! በማዕከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ እና በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ በሁለቱም አውደ ውጊያዎች ፋኖ ድልን ተቀናጀ። በትናንትናው እለት የሁለቱንም አውደ ውጊያ ዝርዝር መረጃ በኔት ወርክ ችግር ምክንያት ያላቀረብን መሆኑ እየታወቀ፣ የምርኮኛው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ከሽመልስ አብዲሳ ልዩ ሀይል እና ከአማራ ሆድ አደር ሚኒሻና የብልፅግና አሽከሮች ጋር በመሆን የኦሮሙማውን ፀረ አማራ አሰላለፍ የሙጥኝ በማለት አሁንም በምድር ሜካናይዝድ ጦር በሰማይ በድሮን በአማራ ህዝብ ላይ ያልተሰራ፣ ያልተፈፀመ፣ያልተመከረ ነገር የለም።ሆኖም ግን ከጊዜ ጊዜ በሁለንተናዊ ዘርፍ አሰላለፉን ያፈረጠመው የፋኖ ሀይል ወይ ንክች ብሎ የወንበዴውን የማፊያ ቡድን በሁሉም የአውደ ውጊያ ግንባር ከፍተኛ ፍልሚያ በማድረግ ድልን እየተጎናፀፈ ይገኛል። በትናንትናው እለትም የአገዛዙ ጥምር ሀይል ሰፍሮ ካለበት ፣ ስለ አማራ ሁሉን አቀፍ ጀኖሳይድ  ከሚዶልትበት ከተማ ከቋራ ደለጎ ፣ ከአለፋ ሻሁራና አፀደማርያም በልዩ ኦፕሬሽን የፋኖ ሰራዊት በተመሳሳይ በማታ ስአት ወደ ሁሉም ከተሞች በመግባትና በመጠጋት ተኩስ በመፍጠር  ወደ ሞት ቀጠና ስቦ በማስገባት ፣አናብስቶቹ የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ በአርበኛ በሊሁን እየተመራ እና ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፋኖ ሰራዊት በአርበኛ ክንዱ(ቆስቁስ) እየተመራ፣ግራና ቀኝ በመጣመር በደለጎ ከተማ የመሸገውን የጠላት ሀይል ክፉኛ ሙሉ ቀኑን ሲያበራዩት ውለዋል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድልን መጎናፀፍ ተችሏል። ይህ በንዲህ እንዳለ በከፍተኛ ጦር አመራሮች የጦር ጠበብቶች የሚመራው ይህ አውደ ውጊያ በተመሳሳይ ሁኔታ በአለፋ ወረዳ ሻሁራ ከተማና አፀደማርያም ከተማ ነበልባሎቹን የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በማሰማራት እና በአርበኛ ገ/ማርያም በየነ ሁለቱንም ከተሞች ግራና ቀኝ ክንፍ አጣምሮ ፣ በአንደኛው በኩል አርበኛ ጌጤንና አርበኛ ሙሉቀንን በማጣመር፣በሁለተኛው አሰላለፍ አርበኛ አበጀንና አርበኛ መኳንንትን በአንድ በማስተሳሰር፣በሁለቱም የውጊያ ቀጠና ሁሉም የክፍለ ጦሩ አመራሮች የተሰጣቸውን የአውደ ውጊያ ላይ ጥበብ በመጠቀም የአገዛዙን ግብስብስ የጭራቅ ስብስብም እያዟዟሩ ሲያበራዩት ውለዋል። በመጨረሻም በሁለት ቀጠና የወጣውን የአረመኔው ስርአት አስፈፃሚ ጥምር ሀይል መግቢያ መውጫ በማሳጣት ወደ አንድ  ቀጠና በመሰብሰብ ከበባ ውስጥ ማስገባት ተችሏል።በዚህም አውደ ውጊያ የአገዛዙ ሀይል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛን አስተናግዷል። በሁሉም አውደ ውጊያ የታዩ ከሞላ ጎደል ክስተቶች: የአገዛዙ ጦር አዋጊዎች ሰራዊቱን ካለ ፍላጎቱ በድንጋይና በዱላ ድብደባ እያዋጉ ያለውድ በግድ ወደ ሞት እማገዱት መሆኑ፣ ሀይል ሲሞትባቸውና ሲቆስልባቸው በየ ቤቱ የአርሶ አደሩን አልባሳት እየገፈፉና እየቀሙ እንደሚጠቀሙ ማረጋገጥ ችለናል። በደለጎ ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ እና በጎንደር ጠቅላይ ግዛት የፋኖ ሰራዊት ጥምር የተገኘ ድል: ሙት:ከ60 በለይ ቁስለኛ:ከ48 በለይ አሁንም የአገዛዙ ጥምር ሀይል በዚሁ ቦታ ከበባ ውስጥ ይገኛል። በአፀደማርያም ቀጠና በአድዋ ክ/ጦ የተመዘገበ ድል: 3ጊዜ በአምቡላንስ ሙትና ቁስለኛ አመላልሷል። እንዲሁም የውጊያውን ቀጠና ሙሉ በሙሉ ማስለቀቅ ተችሏል። በሻሁራ ከተማ ቀጠና በአድዋ ክ/ጦ በኩል የተገኘ ድል: ከ2ጊዜ በላይ በኦራል እየሸፈነ ሙትና ቁስለኛ አንስቷል። ሁሉም አውደ ውጊያ አሁንም ሁለተኛ ቀኑን እንደቀጠለ ይገኛል። ውጊያው እንደተቋጨ ከዚህ በተሻለ መንገድ ዝርዝር ጉዳዮችን ለህዝብ ጀሮ እናደርሳለን። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ    ጥቅምት 19/2018

+1
ለንደን ፋኖ ትችላላችሁ

"20 ሚሊዮን አማራ በወለጋ ምድር በሞትና በሕይወት መካከል ነው ያለው። ለዚህ አማራ ፈጥኖ ደራሽ እናንተው ናችሁ" በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አማካሪ ኮ/ል ሞገስ ዘገየ፡ በአርበኛ ዳንኤል አለሙ
"20 ሚሊዮን አማራ በወለጋ ምድር በሞትና በሕይወት መካከል ነው ያለው። ለዚህ አማራ ፈጥኖ ደራሽ እናንተው ናችሁ" በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ አማካሪ ኮ/ል ሞገስ ዘገየ፡ በአርበኛ ዳንኤል አለሙ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝቶ ለምልምል ኮማንዶ ሰልጣኞች ያስተላለፈው መልዕክት!

የአምሓራ ህዝብ ፈተና በዋናነት ሁለት እርስቱን ተቀራምተው ሉዓላዊ ሀገራትን ለማዋለድ በሚቃትቱ ተገንጣይ ወንበዴ ቡድኖች ቅዠት ላይ የታከከ ነው። ለዚህ ህልማቸው ደግሞ ሆድ አደር፣ ምንደኛ የክርስትና እምነት መሪዎች ዝብ በማደንዘዝ ተባባሪ ናቸው። በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም" 👉ለቤተክርስቲያን መኖር እንጂ በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ለቤተክርስቲያን ራስን አሳልፎ መስጠት እንጂ በቤተክርስቲያን መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ክርስቲያን መሆን እንጂ ክርስቲያን መስሎ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሚያምኑትን መኖር እንጂ የሚያምኑትን አስመስሎ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የቆብ ሕይወትን መኖር እንጂ ቆብ ደፍቶ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ጺምን መነጨት እንጂ ጺምን እየነቀሱ ቀሚስን እያንሰራፈፉ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉በመጽሐፍ ሕግ መኖር እንጂ መጽሐፍን እያነበቡ መኖር ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሚሰብኩትን መሆን እንጂ ሰብኮ ከዓውደ ምህረት መውረድ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የሰማዕትነት ደም እንጂ ደሞዝ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የአገልጋዮቿ ንጽህና እንጂ የአገልጋዮቿ ብዛት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የቅንነት አገልገሰሎት እንጂ የእልህ አገልግሎት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሃይማኖታዊ ቋንቋ እንጂ መንደራዊ ቋንቋ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ኦርቶዶክሳዊ ማኅጸነ ዮርዳኖሳዊ የማይጠፋ ክርስቶሳዊ ዘር ሐረግ እንጂ ሥጋዊ ምድራዊ ጎጣዊ ፈራሽ በስባሻዊ ዘር ሐረግ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉መንግስተ ሰማያዊ ማንነት እንጂ ምድራዊ ማንነት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉መንፈስቅዱሳዊ ጵጵስና እንጂ ኮታዊ ዘርዓዊ ቋንቋዊ ጵጵስና ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሰማያዊ ጽዮናዊ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቶስ ራስ የሆነለት ሕዋሳዊ አንድነት እንጂ መንደራዊ ጎጣዊ ምድራዊ ጥቅማዊ ኢኮኖሚያዊ ሥጋዊ አንድነት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉አስሩን ሕዋሳት በእግር እርግጥ በእጅ ጭብጥ አድርጎ ለእግዚአብሔር በማስገዛት እንጂ ባለ አስር አውታር በገና መደርደር  ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም ። 👉የሥነ ምግባር ካባን መጎናጸፍ እንጂ የልብስ ካባን መጎናጸፍ ኦርቶዶክሳዊ አስተሳስብን መጠምጠም እንጂ ነጭ ሻሽን መጠምጠም የወንጌልን ጫማ መጫማት እንጂ ቶርሽን ጫማን መጫማት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉እመቤታችንን መምሰል እንጂ ነይ ነይ እምየ ማርያም ማለት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉የማርያምን ስራ መስራት እንጂ እኔስ ማርያምን እወዳታለሁ ማለት ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉አስቦ መስራት እንጂ ሰርቶ ማሰብ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ሳይሆን መጮኽ እንጂ ከሆነ በኋላ መጮኽ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። 👉ደሟ እንዳይፈስ መጠበቅ እንጂ ከፈሰሰ በኋላ ደም መለገስ ቤተክርስቲያንን አያተርፋትም። "ነጽር ኀበ አይ መካን አዕረጋ ለቤተክርስቲያን ዘከመ ይእቲ ኵለንታሁ- ቤተክርስቲያንን በዚህን ያህል ክብር እንዳከበራት ዕወቅ ኵለንታ ባህርይዋ ገንዘቡ እንደመሆኑ" ሃይማኖተ አበው ዮሐ አፈ ፷፯÷፴፱ "ቤተክስቲያንን በሕይወታችንም በሞታችንም እንጠብቃለን"

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፅሞ 14 ንፁኋኖች መገደላቸው ተነገረ! ጥቃቱ
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ልዩ ቦታው ዘምባባ አርሴማ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፅሞ 14 ንፁኋኖች መገደላቸው ተነገረ! ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ጥቅምት 17/2018 ዓ/ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን፡ ከተገደሉት በተጨማሪ በርካቶች ታግተው መወሰዳቸው ተነግሯል። በዚህ ዞን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፀም ለበርካታ ጊዜ ሲሆን፡ ከሳምንታት በፊትም በተመሣሣይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ታውቋል።

ከደቡብ አፍሪካ ዜና‼️ አስደንጋጭ ክስተት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ! ጥቁር ቀን ለደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን! በደቡብ አፍሪካ ተወልደው ያደጉ ሁለት እህትማማቾች፣ * ዲቦራ መንግስቴ እና *
+3
ከደቡብ አፍሪካ ዜና‼️ አስደንጋጭ ክስተት በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ! ጥቁር ቀን ለደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን! በደቡብ አፍሪካ ተወልደው ያደጉ ሁለት እህትማማቾች፣ * ዲቦራ መንግስቴ እና * ኦፕራ መንግስቴ፣ ምንነቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱ ታውቋል። * እህትማማቾቹ በራሳቸው ክፍል ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል። * የሞታቸው ምክንያት እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። * ይህ አሳዛኝ ክስተት በደቡብ አፍሪካ የሚኖረውን መላውን የኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ በከፍተኛ ሐዘን ውስጥ ከትቶታል። ቤተሰቡ በጆሃንስበርግ፣ ኪስንግተን በሚገኝ ቦታ ላይ ለሐዘን ተቀምጦ ይገኛል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሁሉም ወገኖች መጽናናትን እንዲሰጡ ጥሪ እናቀርባለን። አምላክ ለሟቾቹ ቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ለሚኖረው መላው ወገናችን ሁሉ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። Via የኛ ሰው ሚዲያ ከደቡብ አፍሪካ