ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 490
مشترکین
+1024 ساعت
+847 روز
+87330 روز
آرشیو پست ها
ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ዜና❗️❗️❗️
=============
➢ ከቤተሰብ የመጣ አስቸኳይ መረጃ ነው ❗️
አንብቡት የዛሬ ውሎው👇ቢያንስ አንባቹ #ሼር አድርጉ ወገን!!
06/01/2017 ዓ.ም
የወንድማችን የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷለ።
👉 ማረሚያ ቤቱ ከሚፈቅደው ምግብ ውጪ እንዳይገባ ከልክለዋል።ለምሳሌ ማር፣አጥሚትና ሌሎች ፈሳሽ ነገሮች።
👉 የሚፈለገውና የሚያስፈልገው መድኃኒት እየገባለት አይደለም፣
👉 የተደረገለት ቀዶ ሕክምና በየጊዜው ስለሚተካ ወደ ሌላ ህመም(ካንሰር) ሳይተካ በጨረር ህክምና መጥፋት አለበት።ለዚህ ደግሞ የቅርብ ሐኪሞቹ ውጪ አገር ሄዶ መታከም እንዳለበት እያለቀሱ ሳይቀር ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ነግረዋቸዋል፣፣
👉 ያለበት ቦታ መጸዳጃ ቤትም ሆነ ሌላው ነገር ፈጽሞ ምቹ ካለመሆኑ የተነሣ ህመሙ ከመሻል ይልቅ እንዲብስበት እያደረገው ይገኛል፣፣
👉 ሰኞ፣ረቡዕ እና አርብ በቤተሰብ ይጠየቅ የነበረው ጭራሽ እንዲቆም ሆኗል፣፣
👉 የሚወስደው መድኃኒት ከመብዛቱ የተነሳ ለሌላ ተጓዳኝ ሕመም እየተዳረገ ነው፣፣
.
.
.ብዙ ብዙ ስቃይና መከራ እያስተናገደ ለሚገኘው ወንድማችን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች፣ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እና ሚዲያዎች አገዛዙ ላይ ጫና ፈጥረው ህክምና የሚያገኝበት መፍትሄ ካልተፈጠረ አደጋው ከዚህም የከፋ ስለሚሆን ርብርብ ታደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፣፣
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
የሂሳቡ ሊቅ አርበኛ መምህር ስማቸው ምንችል የጫካው ነብር‼
የሒሳብ መምህሩ የሀቅ ሰው ድምጻቸውን አጥፍተው በሙያቸው፣በዘርፋቸው እየሰሩ ነው።
ዛሬ በተደረገው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አንደኛ ክፍለጦር የሒሳብ ሹም ነው።
ፋኖ በትክክል መንግስት ሁኗል።
አርበኛ ስማቸውን የምናውቀው የሀቅ፣የመርህ ሰው መሆኑን ነው። በዘመነ ወያኔ በአምባገነኑ ኢህአዴግ ታስሮ፣ተሰቃይቶ ከሀገር ተሰዶ ነበር። ተገዶ ከስደት ቢወጣም በኋላ ወደሀገር ቤት ተመልሶ ወደ መምህርነቱ አገልግሎ ነበር።
ወቅቱ የሚፈልገውን የትግል አይነት ፈጥሮለታል።
#ጋሽ_ስማቸው_ምኒችል🌼🌺🌼
አርበኛ ስማቸው ምኒችል የአፋብሃ ቴዎድሮስ እዝ የ፩ኛ ክፍለ ጦር አመራርና ታማኙ የሕዝብ ልጅ ባለህበት እንኳን አደረሠህ።
የሒሳቡ ፈላስፋ አርበኛው መምህር ስማቸው ለትግሉ ካለህ ታማኝነትና ለአማራ ሕዝብ ነፃነት ካለህ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ የሞቀ ቤትህን ትተህ እንዲህ ተጎሳቁለህ፣ ያ ለማየት የሚያሳሳው ፈገግታና ውበትህ እንዲህ ጠፍቶ ያለው ለወገንህ ለሕዝብህ ነውና ባለህበት እግዚአብሔር ይጠብቅህ።
ድል ለአንተና ለትግል ጓዶችህ፤ ሽንፈትና ውርደት ለባንዳና ለሆድ አደር የብልፅግና እንቁላል ጠባሾች ይሁን።
እናሸንፋለን🙏🙏🙏
ከአንተው ተማሪ ጋዜጠኛ ኤልያስ ደባሱ
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+2
የትግሉ ሀይላችን የአማራ ብሄርተኝነታችን ነው !
ብዙ ዋጋ እና መፅዋትነት ሊያስከፍለን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኜ መናገር የምችለው ነገር ቢኖር የአማራ ትግል ያሸንፋል ። ይህንን ለማድረግ በጥንቃቄ መያዝ ያለብን ትልቁ ሀይላችን የሆነውን ብሄርተኝነታችንን ነው ። የአማራ ትግል ከብሄርተኝነት ትግል ወጥቶ መንገድ ከሳተ መታገል ብቻ ሳይሆን ድጋሜ አማራ የሚባል ህዝብ ተደራጅቶ እድር ማቋቋም እንኳን የማይችልበት ደረጃ ላይ የሚደርስበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል ። ስለዚህ የትግላችንን ትልቁ ሀይላችን የአማራ ብሄርተኝነታችን ስለሆነ በጥንቃቄ ልናራምደውና ልንጠቀምበት ይገባል ።
እናሸንፋለን
የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አብይ አህመድ የግብፆችን የዲፕሎማሲ ጫና ተቋቁመው ግድቡን አስጀምረው ያጋመሱትን መሪወች ለፈፀሙት ነገር እንጥፍጣፊ እውቅና ሊሰጥ አለመፈለጉ ብዙም አያስገርምም።
የፖለቲካ ካርዱን አሟጦ ጨርሶ ግድቡን ፖለቲካዊ ሸቀጥ ለማድረግ በመጣር ላይ ነው። ሆኖም አልተሳካለትም። የጉልት ገበያ የሚሰሩ እናቶችን ሳይቀር በብልፅግና መዋቅር አስገድዶ ሰልፍ ቢያስወጣም ለግድቡ ምረቃ እንግዳ ለመጋበዝ አለምን ቢዞርም፤ "ዓባይን የደፈረ" የሚል ጩኸት ቢያስተጋባም፣ የኑክለር ባለቤት እሆናለሁ ቢልም ማንም ጆሮ አልሰጠውም። ከዲፕሎማሲ እና ከፖለቲካ ኮስማናነት የሚያወጣ እውቀትም ተነሳሽነትም የለዉም።
አሁን የቀረው የቀይ ባህር ጉዳይ ነው። አብይ ደፍሮ ወደ ኤርትራ አይተኩስም። ይህንን ለማድረግ የሚያበቃ ዲፕሎማሲያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አቅም የለውም። አንዳንድ የዋሆች አብይ ይህንን የሚያወራው የሀገር ፍቅር ኖሮት ይመስላቸዋል። እውነታው ግን አብይ በመንግስትነት ስም ሽብርን እያስፋፋ እና እያፋፋ ያለ የአረመኔ አገዛዝ ቁንጮ ከመሆኑ ባሻገር ከአዲስ አበባ- ሐዋሳ፣ ከአዲስ አበባ- አሶሳ፣ ከአዲስ አበባ-ደብረ ማርቆስ ሰላማዊ የተሽከርካሪ ጉዞ እንዲኖር እንኳን ማድረግ ያልቻለ በራሱ ህዝብ ላይ ያመፀ የአዲስ አበባ ሸማቂ ነው። የተረከበውን ህዝብ እየጨፈጨፈ እና እየበተነ ያለ "መሪ" የባህር በር ያመጣል ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው።
አብይ የቴክኖሎጅ ብልጫ እንዳለው እና አሰብን እንደሚወስድ የሚያስቡም አሉ። ይሁን እንጅ አይደለም የቀይ ባህርን የባህር በር ቀርቶ አንዲትን መንደርም ያለ ፖለቲካዊ ቅቡልነት፣ ያለ ዲፕሎማሲ ብልጫ ይዞ መቆየት አይቻልም። ይህ እንደማይሆን አብይም በደንብ ያውቃል።
ታዲያ ይህ ሁሉ ሽር ጉድ ለምንድን ነው ከተባለ ዋነኛ ምክንያቱ የፋኖን ክንድ መቋቋም ስላቃተው የህዝቡን የትኩረት ማዕከል ለመበተን አስቦ የሚያደርገው ነው። ሆኖም ያ የሚሆንበት ግዜ አልፏል። ይህ ትውልድ እንደቀደምቶቹ የፖለቲካ ነሆለል አይደለም። የሚሰራውን እና ዋጋ የሚከፍልበትን አጀንዳ ጠንቅቆ ያውቃል። ኢትዮጵያም ሆነች የአማራ ህዝብ ከአሸባሪ የሚገኝ ቁልቁለት እንጅ ከፍታ እንደሌለ ይገነዘባሉ።
ስለሆነም አገዛዙ በተባበረ ክንድ ይደቆሳል።
አስረስ ማረ ዳምጤ
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ማዕከላዊ ኮማንድ
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሰልፉ ከሽፏል!
መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ አበው ነጹሐንን በመጨፍጨፍ፣ በማሳደድና በመዝረፍ ከሰባዊነት ደረጃ የወረደው የጥፋት ስብስቡ የብልጽግናው ቡድን በሰይጣናዊ ባሕርይው የጎሰቆለ መገለጫውን በንጹሐን ላብና ደም የተገነባው የሕዳሴ ግድብ ያድስለት ይመስል ዛሬ በየከተሞች የድጋፍ ሰልፍ በግዳጅ በመጥራት ሕዝቡን ሲያንገላታ ውሏል።
በመሆኑም የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ በሚያስተዳድራቸው ቀጠናዎች በደምበጫና በረቡዕ ገበያ የተደረጉ የማደናቆሪያ ሰልፎችን በጀግኖቻችን የተጠና ኦፐሬሽን ማክሸፍ ተችሏል።
በደምበጫ ከተማ ፋኖ በሰራው ኦፐሬሸን የተናደደው አረመኔ ሰብስብ ሁለት ንጹሐንን በግፍ የገደለና አምስት ንጹሐንን ያቆሰለ ሲሆን ሰልፉ በታቀደው ልክ ሳይደረግ ቀርቷል። በሌላ በኩል ረቡዕ ገበያ ሊካሄድ የነበረውን ሰልፍም ጀግኖቹ የስናን አባጅሜ ፋኖዎች በፈጸሙት በሞርተርና ዲሽቃ የታገዘ ኦፐሬሽን ሰልፉን መበተን ችለዋል።
ከህዝብ ፈቃድና ፍላጎት ውጭ የሚደረግ እንቅስቃሴ እና ስራ ተቀባይነት የለውም፤ እኛም የሕዝባችን ዋሶች ነን።
ድል ለሕዝባችን!
መስከረም 06:2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
እንኳን ነካክተውን ይቅርና....?
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
👉አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው እዝ ሀይለማርያም ማሞ ክፍለጦር የፋኖ አባላት ጋር የተቀላቀሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው።
👉እነዚህም ወጣት የመከላከያ ሰራዊት እንዳሉት ከቤታችን ከስራችን ላይ በግዳጂ ታፍሰን ሳንፈልግ 45 ቀን ሰልጥነን የመጣን ሲሆን ግዳጂ የተሰጠን ቦታ በግዳጂ የእርስ በእርስ ኢትዮጲያን የማጥፋት ዓላማ ያለው መንግስትን አንደግፍም ለነፃነት ለሀገር የሚታገለውን የአማራ ፍኖ ሰራዊትን መርጠን መተናል ብለዋል።
👉በመሆኑም ይህን የተረዳው አሳምነው እዝ ሀይለማርያም ማሞ ክፍለጦር አመራሮች አሥፈላጊውን ትብብር በማድረግ እንኳን ሲሆን መጣችሁ በማለት ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር የተሸኙም ሲሆን ትግሉ ውስጥ ገብተው መታገል የሚፈልጉትን በፍቃደኝነት በመጠዬቅ የተሳተፉም አሉ።
#ድል ለሰፊው የአማራ ህዝብ!!!
#ነፃነታችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የሀይለማርያም ማሞ ክፋለ ጦር ህ/ግንኙነት ክፍል!!!
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ከጳጒሜን 01 እስከ መስከረም 05/2018ዓ.ም ድረስ 117 በላይ የአረመኔው ሰራዊት አባላት ቴዎድሮስ ዕዝን ተቀላቀሉ ።
ጠላት በየቀኑ እየተበተነ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል። አረመኔው ሰራዊት የደረሰበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው ከነመሳሪያው ፋኖን እየተቀላቀለ ነው። በ10 ቀን ብቻ ከ117 በላይ የአረመኔው ሰራዊት አባላት እና አመራሮች በራሳቸው ጊዜ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝን ተቀላቅለዋል።
ብርሃኑ ጁላ ሕዝብ እንዲጨፈጭፍ በግዳጅ በማህበራዊ መከወኛ ቦታዎች እያፈሰ ቢያሰለጥንም የሰለጠነው ሰራዊት ግን ሕዝቤን አልጨፈጭፍም በማለት እየከዳ ፋኖን በገፍ እየተቀላቀለ ነው። ፋኖም በሰላም እጅ የሰጡትን በእንክብካቤ እየተቀበለ ይገኛል።
10 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሀዲስ አለማየሁ ብርጌድን ተቀላቅለዋል።
1.እውነቴ ላመስግን አብራጂት
2.ገብሬ ጌታ አብራጂት
3.ሀብታም መለሰ አብራጂት
4.በየነ ይገዝ አብራጂት
5.ዘውዱ ያየ ተድላ ጓሉ
6.አሳብ አንሙት ክ/ጦር
7.ፈረደ ተስፋ ክ/ጦር
8. 2መከላከያ አብራጅትን ተቀላቅለዋል።
15 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።
1, ታደሰ ጤናው -----ሚሊሻ
2, አሰፋ ጌታነህ. ""
3, እውነቱ ቸኮል. ""
4, አትንኩት ቢተው. ""
5. ያለለት እውነቱ. ""
6, አይተነው ሞገሴ. """
7, ,፲ አለቃ አስራት ማርቆስ (መከላከያ)
8, ካሳሁን ተረፈ - መከላከያ ዋና ድሽቃ ተኳሽ
9, ኑሬ አማን ---መከላከያ የድሽቃ ረዳት
ትጥቅ ይዘው የወጡ
10, ምስጋናው የሚባል
የአድማ ብተና የሻለቃው አጃቢየነበረ
11, ታድሎ የሚባል አድማ
12 ,ችሎ የሚባል የሚሊሻ ዋና አቀንቃ
13 , ም/ሳጅን ቸኮል መንገሻ- የም/ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘለቀ አጃቢ የነበረ
14, ,መሳ ሽና__መከላከያ
15,,ጁሬኛ ፈቃዱ- መከላከያ
11 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
1. ጌታሁን ፍሬው........... ሰለም አስከባሪ
2. ዋለልኝ ሞሴስ ....... " "
3. ስላንተ አሳየ .... .... " "
4. አብዱሪ ተማም ........ መከላከያ
5. መቶ አለቃ ሙሴ....... መከላከያ
6. አብዩ አወቀ ............. አድማ ብተና
7. አሊየ ቆሪቴ ...... መከላከያ
8. ገደፋው ይልቃል ..... አድማ ብተና
9. ሐብቴ አሌ ..... መከላከያ
10. ቀረብሕ ሲሳይ .... ሚሊሻ
11. ጓች ኑጡ ኢለማ .... መከላከያ
17 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።
አስራ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ
7_ሰላም አስከባሪ
5_ መከላከያ
አቤ ጉበኛ ብርጌድ
1_መከላከያ
ቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ
2_መከላከያ
ግዮን ብርጌድ
1_መከላከያ
ሸኝ አዝማች ስሜነህ ብርጌድ
1_ አድማ ብተና
29 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም 5ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ወርቅ አባይ ብርጌ
ከ23ኛ ክ\ር የአዱ
1-በሀይሉ[ዘመቻ መሪ) 2-ተመስጌን በቀለ
3-ጋዲሳ
4-ካሳሁን
ከ73 ኛ ክ\ር የከዱ
1-ፍቅሩ
2-ትግሉ
3-ደፋሩ አየለ
4-ቡርቃ
ቡሬ ዳሞት ብርጌድን የተቀላቀሉ
2 ሚኒሻ
3 አድማ
2 መከላከያ
በአረንዛው ዳሞት ብርጌድ የተቀላቀለ
2 ምኒሻ
የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን የተቀላቀሉ የመከላከያና የሚሊሻ አባላት ስም ዝርዝርዝር
1. በላይ ደረበው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ አባል ይዞት የወጣ መሳሪያ ሰደፍ ክላሽ
2. ሀብታሙ ጌታነህ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ ሻምበል መሪ ይዞት የወጣ መሳሪያ ታጣፊ ክላሽ
3. አብደላ አባራያ ከ59ኛ ክፍለ ጦር ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት ጥቁር ክላሽ
4. ሰለሞን አስራት ከ59ኛ ክፍለ ጦር ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት ጥቁር ክላሽ
5. አብርሀም ካሳ ሚሊሻ ጀሌ
6. ስማቸው ሞላ ሚሊሻ ጀሌ
7. ዘሪሁን መና ከ71ኛ ክፍለ ጦር ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት ጥቁር ክላሽ
8. ታደሰ ሞላ ከ71ኛ ክፍለ ጦር ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት ጥቁር ክላሽ
9. የኔሰው በላይ ሚሊሻ ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት አብራራው
10. ሙላት ቀሬ ሚሊሻ ጀሌ
11. የሻምበል ንብረት ሚሊሻ ይዞት የወጣ የመሳሪያ አይነት ኤስኬስ
12. ታፈረ አሰፋ _ሚኒሻ
14 የአረመኔውሰራዊት አባላት 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል።
1ኛ.በላይነህ ጎቼ ሚሊሻ
አባ ኮስትር ብርጌድ
2ኛ.ሳጅን መንበር ወዳጄ አድማ ብተና
አባ ኮስትር ብርጌድ
3ኛ.ተሸመ ክብሬ ሚሊሻ
ሽፈራው ገርባው
4ኛ.ውዱ አቡ ሚሊሻ
ሽፈራው ገርባው
5ኛ.ወንዳወክ ይሁን ሚሊሻ
ሽፈራው ገርባው ብርጌድ
6ኛ.ማናየ መኩየ ሚሊሻ
ሽፈራው ገርባው ብርጌድ
7ኛ.ናይፍ ጅማ መኬ
ደባይ ጮቄ ብርጌድ
8ኛ.ሳሜ ሙሳ መኬ
ደባይ ጮቄ ብርጌድ
9ኛ.ቤለማ በሀሩ መኬ
ደባይ ጮቄ ብርጌድ
10ኛ.አሸናፊ ቴብሱ መኬ
ደባይ ጮቄ ብርጌድ
11ኛ. ፻ አለቃ ግዛቸው አራገው መኬ
8ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር
14ኛ.3 የመከላከያ አባላት ከማህበረብረሃን ካንፕ እንዲሁም 1 አድማ ብተና ከጉብያ ካንፕ ጠፍተዋል።
11 የአረመኔው ሰራዊት አባላት አንደኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
1ላምነው መለሰ...... ሚሊሻ
2 ጌታቸው ይግዛው......➢➢
3 አግማሴ ገረመው.....➢➢
4 ምኒችል ምንባየው...➢➢
5 መንግስቱ ተላይነህ...➢➢
6 መካንት አስረስ....➢➢➢
7 ሞገስ አስናቀ ...አድማ ብተና
8 አበባየሁ የሻነህ...➢➢➢➢
9 ማንደፍሮ ታድሎ.....➢➢➢
10 አብርሀም ተሾመ....➢➢
11 ታየ ፈንቴ.....➢
24 የአረመኔው ሰራዊት አባላት ጃዊ መተከል 4ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።
የአረመኔው ሰራዊት አባላት ሳሙኤል አወቀ 9ኛ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል።
1,አዳም ጨሪ፦የጉጂ ተወላጂ
2,አቢቲ አታራ፦የጂማ ተወላጂ
3,ግርማ በዳሳ፦የጂማ ተወላጂ
4,አምዛ ያሰን፦የጂማ ተወላጂ
5,ዳግም አብዱረማን፦የሻሸመኔ ተወላጂ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት ከነሙሉ ትጥቃቸው ሶማ ብርጌድ ተቀላቅለዋል።
6,አሰፋ ማርኬ፦የዲያ ድንጁሚት ተወላጂ
7,ገቤ ጤናው፦የእነሸኝ ቀበሌ ተወላጂ
8,ንጉሴ ሰጤ፦የእናርጅ መስቀል ተወላጅ
9,እውነቱ ምትኩ ፦የጓሮ ገደል ተወላጂ
10,ይላቅ ቸኮል፦የጣሞ ዳሮ ቀበሌ ተወላጂ
11,ቢያርጌ አዳሙ፦ የጎል ውቅማ ተወላጂ የሆኑ የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ሶማ ብርጌድ ተቀላቅለዋል።
ሁሉም ለመክዳት እና ፋኖን ለመቀላቀል ምቹ ጊዜ እና ሁኔታ እየጠበቀ መሆኑን ገልፀዋል። በተለይ ከፍተኛ የመከላከያ አመራሮች እየደረሰባቸው ባለው መገለልና ጫና በሻለቃና በኮር ይዘው ወደ ፋኖ ሊገቡ እንደሚችሉ ማሳያዎችን አይተናል ሲሉ ፋኖን የተቀላቀሉ አባላት ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ሊደርስ በሚችል "በግፍ የመታሰር" (Wrongful Detentions) ስጋት ላይ ያተኮረ ያልተለመደ እና ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አውጥቷል። ኤምባሲው "የጉዞ ማስጠንቀቂያዎች ወሳኝ ናቸው" (TRAVEL WARNINGS MATTER) በማለት ዜጎቹ የስቴት ዲፓርትመንትን የጉዞ ማሳሰቢያዎች በጥብቅ እንዲከተሉ አሳስቧል።
🔴 ከ"በግፍ መታሰር" አስፈጻሚ ትዕዛዝ ጋር የተያያዘው ስጋት
የኤምባሲው መልዕክት ከዚህ ቀደም ከሚሰጡት አጠቃላይ የጸጥታ ማስጠንቀቂያዎች የተለየ ነው። በተለይ "በመንግስታት የሚፈጸም በግፍ የመታሰር" አስፈጻሚ ትዕዛዝን መጥቀሱ፣ ስጋቱ ከተራ ወንጀል ወይም ከሲቪል አለመረጋጋት የዘለለ መሆኑን ያመለክታል ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ይተነትናሉ።
ይህ የስቴት ዲፓርትመንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ፣ የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹን ያለ በቂ ህጋዊ ምክንያት በፖለቲካዊ አላማ ለሚያስሩ ሀገራት ምላሽ እንዲሰጥ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም በማሰሩ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣልን ሊያካትት ይችላል።
🔴 ወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ እና የኤምባሲው ስጋት
ይህ ማስጠንቀቂያ የወጣው በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ ባልተረጋጋበት፣ መንግስትም በአካባቢዎቹ "ህግ የማስከበር" ዘመቻ እያካሄድኩ ነው በሚልበት ወቅት ነው።
በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ፣ በተለይ የኢትዮጵያ ትውልድ ያላቸው አሜሪካውያን ዜጎች (ዳያስፖራው) ወደ ክልሎቹ ሲጓዙ በቀላሉ በተጠርጣሪነት ሊያዙ እንደሚችሉ ስጋት አለ። የኤምባሲው መልዕክትም እንዲህ አይነቱ እስር በአሜሪካ መንግስት እንደ "በግፍ መታሰር" ሊቆጠር እንደሚችል የሚያስጠነቅቅ ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ዲፕሎማቲክ ምንጮች ይናገራሉ።
የኤምባሲው መልዕክት በአሜሪካ እና በመንግስታት መካከል ሊኖር ስለሚችል የዲፕሎማሲ ውጥረት ፍንጭ የሚሰጥ ሲሆን፣ ወደ "የትኛውም ሃገር" የሚጓዙ አሜሪካውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ግልጽ ጥሪ ነው። ዘ-ሐበሻ ዜጎች ማንኛውንም ጉዞ ከማድረጋቸው በፊት በስቴት ዲፓርትመንት ድረገጽ ላይ የሚወጣውን የቅርብ ጊዜ የጉዞ ማሳሰቢያ እንዲመለከቱ ይመክራል ሲል ዘሐበሻ ዘግቧል።
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#ሰበር_ዜና‼️
ባለ ሽርጡ ክፍለጦር ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ ማስልጠኛ ካምፕን ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር አሰልጣኞችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር ሆድ አደር ሚሊሻ አድማ ብተናና መከላከያ በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር1 ባለሽርጡ ክፍለ ጦር በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ 024 ቀበሌ ልዩ ቦታው ጃራ ካምፕ እየተባለ የሚጠራውን አሁን ላይ በፋሽቱ ብልፅግና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ የሆነ ከበባ ውስጥ በማስገባትና ሙሉ ለሙሉ በመቆጣጠር በርካታ የብልፅግና ቡድን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻና አድማ ብተና እንድሁም የስርዐቱን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በመደምሰስ ፣ በማቁሰልና በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ለአመታት ከየጎዳናው፣ከየፑል ቤቱ፣ እንድሁም ከየመኖሪያ ቤታቸው፣ በሀይልና፣በግፍ እያስገደደ ወጣቶችን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎችን፣ በማሰልጠን ስልጣኔን ያስጠብቁልኛል ብሎ የሚያስበው የአረመኔውና የአማራ ጠሉ የአብይ አህመድ የግል ሰራዊትና የዚህን ጨፍጫፊ እና አገር አፍራሽ ሰራዊት የሚያግዝና መንገድ እየመራ ወገኑን የሚጨፈጭፈውንና የሚያስጨፈጭፈውን ባንዳ ሚሊሻና አድማ ብተና ሃይል መስከረም 5ለ6/2018 ዓ.ም ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶዎች ጃራ ካምፕ ውስጥ በከፈቱት ድንገቲዊና መብረቃዊ ጥቃት በርካታ የአድማ ብተና የሚሊሻ ፣እንድሁም የስርዐቱን ሀይሎች ገሚሱን በመደምሰስ፣በማቁሰልና በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል።
ከንጋት 10:00 ጀምሮ እስከ ንጋት 12:35 መስከረም 6/2018 በቆየ አውደ ውጊያ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ 024 ቀበሌ ጃራ ማሰልጠኛ ካምፕ መሽጎ የነበረውን ሆድ አደር እና የብአዴን ምንጣፍ ጎታች ሚሊሻን አድማ ብተና ሃይልን የማያዳግም እርምጃ በመወሰዱ ፋሽስቱ አገዛዝ በበርካታ አንቡላንሶች ቁጥሩ ያልታወቀ የአድማ ብተና የሚሊሻ ፣እንድሁም መከላከያ በአምስት ኦራል ወደ አፋር ክልል ጭፍራ ከተማ አጓጉዟል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ፋኖ መሀመድ ሞገስ አስታውቋል::
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
06/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#አሳዛኝ_ዜና_ደምበጫ‼️
በቁመናው የበሰበሰው የብልጽግና ሙታን ስብስብ ሲፈጽመው በኖረውና ዛሬም ድረስ እየፈጸመው ባለው አረመኔያዊ ተግባር ምክንያት ከሕዝባችን ልቡና ተተፍቶ የወጣበትን አራዊታዊ ገጸ ባሕርይ ለማደስ በኢትዮጵያውያን ላብና ደም በተገነባው የሕዳሴ ግድብ መመረቅ ምክንያት በማድረግ በየከተማው የሚገኘውን ማሕበረሰብ ኑ ሰልፍ ውጡና አመስግኑኝ በማለት እያሰገደደ ሰልፍ እንዲወጡ መከራ አድርጓል።
በዛሬው ዕለትም ደምበጫ ከተማ ተወሽቆ የሚገኘው የብልጽግና ወራሪ ስብስብ በጥዋት ተነስቶ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ደፋ ቀና የሚለውን ማሕበረሰብ በዱላ እየደበደበና እየጎተተ ሰልፍ እንዲወጡለትና አረመኔያዊ ተግባሩን እንዲያወድሱለት ለማድረግ ሙከራ እያደረገ ባለበት ሰዓት የምንጊዜም ጀግኖች የኢንጅነሩ ልጆች በሰሩት አፐሬሽን ሰልፉ ባሰበው ልክ ሳይሳካ ቀርቷል።
ይሁን እንጅ ሰልፉን ባሰበው ልክ ያላሳከው አረመኔውና ነፍሰ በላው የብልጽግና ስብስብ ወራሪ ሠራዊቱን አዝዞ በንጹሐን ላይ የጭካኔ በትሩን ሲያሳርፍ አርፍዷል። በዚህም መሠረት 2 ንጹሐን የከተማው ነዋሪዎችን በግፍ በመረሸን 5 የሚሆኑትን ደግሞ ከባድ ቁስለኛ አድርጓቸዋል።
በንጹሐን ደም የሰከረው የአራዊት ስብስብ የብልጽግና ሰራዊት የጀግኖችን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ንጹሐንን በመረሸን ለበላይ አለቆቹ ፋኖን አጽድተናል..የሚል የጅል ሪፖርትም እያቀረበ ይገኛል።
ድል ለሕዝባችን!
©ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ6ኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት
06/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በእነ ችሎት ይስማው መዝገብ ፍ/ቤቱ ከዋስትና መብት አንጻር የተደረገውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 9/2018 ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።
በእነ ችሎት ይስማው መዝገብ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በተከሳሾች እና በዐቃቤ ሕግ መካከል ከዋስትና መብት አንጻር የተደረገውን ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለፊታችን መስከረም 9/2018 ቀጠሮ መስጠቱ ነው የተሰማው።
በእነ ችሎት ይስማው መዝገብ ከ4 ከተከሳሾች መካከል ሁለተኛ ተከሳሽ ላቀው ሞገስ አስፋው መስከረም 5/2018 ፍ/ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል ፤ የሌሎቹ ሶስት ተከሳሾች ማለትም ፦
1) የችሎት ይስማው አላምረው ፣
2) ጽጌ ሀና ሀብተ ማርያም እና
3) ሀብታሙ ፈንታው መስከረም 5/2018 ፍ/ቤት ስማቸው አልደረሰኝም በማለት የቂሊንጦ ማ/ቤት በእለቱ በችሎት እንዳይገኙ አድርጓል።
ተከሳሾቹ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሀምሌ 30/2017 በተሰጠው ብይን መሰረት የተከሰሱበት አንቀጽ ወደ 9 (1) የተሻሻለላቸው መሆኑ እና ለታህሳስ 18/2018 ቀጠሮ መሰጠቱ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ በመሃል የዋስትና ክርክር እንዲደረግ በጠበቃ በኩል ነሃሴ 27/2017 አቤቱታ ያቀረበ ስለመሆኑ ተወስቷል።
የተከሳሾች ጠበቃ ባመለከተው መሰረትም ፍ/ቤቱ ዐቃቤ ሕግ በቀረበው የዋስትና ክርክር ይታይልን አቤቱታ ላይ ለመስከረም 5/2018 አስተያየቱን ይዞ እንዲቀርብ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ምላሹን በጽሁፍ ይዞ ቀርቧል።
በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የዋስትና ክርክር መርምሮ ብይን ለመስጠት በሚል ለመስከረም 9/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።
የቀረበው አቤቱታ እና የዐቃቤ ሕግ ምላሽ
ከስር ተመላክቷል።
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ አሳምነው ክፍለጦር ወልድያ ከተማ በምሽት የተሳካ ኦፕረሽን በመፈፀም ድል ተጎናፀፉ‼️
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ መስከረም 5/2018 ዓ.ም ምሽት 5:00 በመግባት አንድ ፓትሮል አድማ ብተና ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስና ሌሎች ጀብዶችንም በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈው አድረዋል::
በአርበኛ ዘውዱ ዘመላክ የሚመራው 5ኛ ሻለቃ በምሽት ወልድያ ከተማ ዘልቆ በመግባት በፓትሮል ይንቀሳቀሱ የነበሩ አድማ ብተናዎችን ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስ እና ሌሎች ጀብዶችን በመፈፀም ታልቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
የፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በደረሰበት ሽንፈት በመበሳጨት እንደተለመደው የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን በማዞር አንድ የግለሰብ መኖሪያ ቤት በብሬን በመደብደብ ንፁሃኖች ላይ ጉዳት በማድረስ መኖሪያ ቤቱንም አውድሟል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
06/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያው አቶ ሳምሶን ከበደ ከሀገር ተሰደደ።
ለረዥም አመታት በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ውስጥ: በተለያዩ የስራ ዘርፎች ሲያገለግል የነበረው ሳምሶን ከበደ ከሀገር መሰደዱን ምንጮች ገለፁ።
ባለሙያው የአማራን ህዝብ እየጨረሰ ላለው የየብልፅግና ፓርቲ አባል አልሆንም ማለቱን ተከትሎ በብልፅግና መንግስት ጥርስ ተነክሶበታል። በተያያዘም በስራ ላይ ብልፅግና የሚያስተላልፋቸው የሀሰት መረጃዎችን በመቃወሙ ምክንያት በስውር ደህንነት ተመድቦበት ስራውን ተረጋግቶ እንዳይሰራ ተደርጓል።
በአማራዊ ማንነቱ ምክንያት ልዩ ክትትል: ጫና እና ወከባ ሲፈፀምበት ነበር።
አገዛዙ በተለይም ፋኖ በሚዲያ የበላይነት በልጦኛል ብሎ መገምገሙን ተከትሎ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሏል።
አቶ ሳምሶን: የብልፅግና አባል ያልሆንከው የፋኖ ደጋፊ ስለሆንክ ነው በሚል ደሞዝ እንዲቀነስ: አላግባብ ከነበረው ሀላፊነት ዝቅ እንዲል በማድረግ የስነልቦና ጉዳት ተፈፅሞበታል።
በከፍተኛ ጫና ስራውን እየሰራ የነበረው ባለሙያው: እንደ አዲስ በአማራ እና በትግራይ ተወላጆች ላይ መፈፀም የተጀመረው ወከባ ተከትሎ አቶ ሳምሶን ማስፈራሪያዎች እና አካለዊ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል።
አቶ ሳምሶን አሁን ያለበት ቦታ በትክክል እንዳልታወቀ ምንጮች ገልፀው: አለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በ ኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ላይ የሚፈፀመውን ማሳደድ ትኩረት እንዲሰጡት ተጠይቋል።
የ ኢትዮጵያ መንግስት በዚህ 2 ወር ውስጥ ብቻ 2 የሪፖርተር ጋዜጠኞችን አፍኖ ደብዛቸውን ያጠፋ ሲሆን የነጋሽ ሚዲያ ባለቤት ጋዜጠኛ ነጋሽ በግፍ ማሰሩ ይታወሳል።
06/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#የወደቀው_አገዛዝ‼️
የወደቀው አገዛዝ ውድቀቱን ሰልፍ ይመልስለት ይመስል በመላው የአማራ ክልል ከተሞች በግዴታ ተሰለፉልኝ በማለት ቤት ለቤት በመዞሮ በዱላ እየከተከተ ወደ ሰልፍ እያስወጣ ይገኛል‼️
ገጥመናል ገጥመናል💪
በሰይፍ ዘመን ሰልፍ ‼️
06/ዐ1/2018 ዓ.ም
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ጥንቅቅ ያለ ወታደር ብሎም የጦር መሪ ነው። ከሱ ጋር ስትሆን ሰላም ይሰማሃል ሰላምም ይሰጥሃል። እርጋታው ጨዋታ አዋቂነቱ ልትለየው ያስፈራሃል። ላመነበት ደፋር ለዓላማው አንድ ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የማያመነታ በሰብእናው ሩኅሩኅ ሰው አክባሪና ለሰው አዛኝም ነው። ከሚጠበቅበት በላይ የሚያውቅ፣ ለመማር፣ ለማወቅም ዝግጁ እና ትጉህ አእምሮው ምጡቅና ለመቀበልም ክፍት የሆነ የወደፊት ተስፋ የሚጣልበት፤ የሚያገኘውን ትርፍ ጊዜ በማንበብ የሚያሳልፍ አቅሙ ከቀን ቀን ከብርሃን ፍጥነት በበለጠ እየጨመረ የመጣ የጦር ጠበብት ነው።
ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ደለለ በሥራና በሕይወት አጋጣሚ ከማውቃቸው ብሎም በሕይወቴ ቦታ ከምሰጣቸውና ከማደንቃቸው ጥቂት የጦር ጀኔራሎች እጅጉን ገዝፎ ካለው ልምድና እድሜ በላይ ልቆ ያገኘውት የወደፊቱ ስመጥር የጦር ጠበብት እንደሚሆን ተስፋ የማደርግበት የትግል አጋሬ፣ የማከብረው ወንድሜና ጓደኛየ ብሎም ብቁ መሪየ ነው።
ዝኔ ያለኝን አክብሮት ልገለፅ ነው እንጅ ይች ሐሳቤ አንተ ካለህ እምቅ አቅምና ስብእና ውቅያኖስን በጭልፋ እንደ መጨለፍ ነውና ብቻ ባለህበት ሰላምህን ያብዛው ዋጋ እየከፈልክበት ያለኸውን የትግል ፍፃሜ ለማየት የበቃህ ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው።
©ሻለቃ ሙላት ሲሳይ የሶማ ትምህርትና ሥልጠና ማእከል ሓላፊ
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ወንድም ሰው አርበኛ አበበ ፈንታው!
መርህ፣ እውነት፣ ቅንነት፣ ትህትና፣ ታማኝነት፣ ፅናት፣ ለሕዝብ አሳቢነት፣ ደፋር፣ ስትራቴጂካዊ አሳቢ፣ ድፍረት፣ ወንድምነት እና ክብር አዋቂነት የእነዚህ ሁሉ ባለቤት አርበኛ Abebe Fentaw ጋር ያሉ ናቸው፣ በርታልን ወንድም ሰው!
ውድ አማራዊያን ከግንባር መረጃዎቻችን ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
