ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 401
مشترکین
+124 ساعت
+757 روز
+1 40730 روز
آرشیو پست ها
የምኒልክ ዕዝ የስልጠና ጥሪ!
የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ትንቅንቅ ከጀመረ ዓመታትን እንዳስቆጠረ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያወቀዉ የአደባባይ እዉነታ ነዉ።
በመሆኑም ይህን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ሰራዊታችን እና የጦር መሳሪያዎችን እያዘመንን ወደፊት እየገሰገስን ሲሆን ተጨማሪ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደሚያስፈልጉን ስላመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ ከጥቅምት 29/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን።
1 ) እድሜ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ /የሆናት
2 ) የአማራ ተወላጅ የሆነ / የሆነች እና በብሔርተኛነት ትግሉ ሙሉ በሙሉ ያመነ / ያመነች
3) ማንኛውንም ሃይማኖት ማክበር የሚችል /የምትችል
4 ) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ግሉል የሆነ አባልም ያልነበረ/ ያልነበረች
5 ) ስለተወለደበትና ስለሚኖርበት አካባቢ ( የትዉልድ ቦታ ) ሙሉ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል / የምትችል
6 ) ምንም አይነት ሱስ የሌለበት
7) ከአካል ጉዳት ነጻ የሆነ / የሆነች
8 ) ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ / የሆነች
9 ) ማንበብና መፃፍ የሚችል / የምትችል
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
🔥በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ በተደጋጋሚ ፋኖ ድል እየቀናው የጠላት ሀይል እየተሽመደመደ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል‼️
በትናንትናው እለት ጥቅምት 27/2018 የአገዛዙ አገልጋይ ጡት ቆራጭ ሀይል መነሻውን ቁጥር አንድ አድርጎ ወደ አርባጅራ እየተጓዘ ባለበት ስአት አይበገሬዎቹ የበረሀ ፈርጦች የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ፋሲል ብርጌድ በአርበኛ ሳሌ ግርማ እና በአርበኛ ባንዴራው እየተመራ እንዲሁም የክ/ጦሩ አመራሮች በተሳተፉበት ስምሪት ሌላ 3ኛ ዙር ከታጉር እና ጓንግ ከተሰራው ጀብድ የቀጠለ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት ይህንኑ ግብስብስ የብልፅግና ስርአት አስፈፃሚ የማፊያ ቡድን ከቀኑ 9:00_11:30 ክፉኛ ሲያበራዩት እንደ ተለመደው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ አርባጅራ ፈርጥጧል።
በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የአጣናው ዋሴ ክ/ጦ የህ/ግ አርበኛ ግዛት አለበል እንዳሳወቀን ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ለጊዜው የደረሰን የአገዛዙ ሀይል ሙትና ቁስለኛ ከዚህ በታች ከጠቀስነው በላይ እንደሚሆን የውስጥ መረጃዎች አድርሰውናል ሲል አሳውቋል።
ሙት = 18
ቁስለኛ = 26
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
©አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር የህ/ግ ኃላፊ ፋኖ መ/ር አስተዉል አምሳሉ
28/ዐ2/2018 ዓ.ም
+1
#የጥንቃቄ_መልዕክት‼
ደም ግብሩ የሆነዉ ሰወ በላዉ ስርዓት ዛሬም ሌላ የጥፋት አዋጅ በማወጅ የድሃ ልጆችን በማፈን ወታደራዊ ግዳጅ ውስጥ እየማገደ ይገኛል።
ይህ ምትመለከቱ ፎቶ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዉን አስመልክቶ ያለፈዉን የጥፋት ዘመን ለመድገም ቲሊሊ ከተማ ላይ ወጣቱን ለማፈን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ማሳያ ነዉ።
ስለሆነም መላዉ የአማራ ህዝብ፤ የቲሊሊና አካባቢ ማህበረሰብ ህፃናት ልጆቻችሁን፣ ወጣቱ ከወትሮ በተለየ ንቃት እራሱን መጠበቅና መከላከል የዘወትር ስራ ሊያደርገዉ ይገባል።
በዚህ ሰሃት በማህፀን ያለና በደመነፍስ የሚንቀሳቀስ የብአዴን ርዝራዥ ካልሆነ በስተቀር የትኛውም አማራ ለዚህ አራጅ ወንበዴ ስርዓት ፈቃደኛ ሁኖ አደለም ለመሞት ለደሞዝም የሚጠጋው አለመኖሩ የታወቀ ስለሆነ በአራቱም አቅጣጫ የህልም ሩጫ ላይ ያለዉ ሀይል በተለይም መልካ ምድር በስርዓት የማያዉቁ፤ ሊያመልጡና ልከዱ የማይችሉ የጥይት ማብረጃ ብቻ የሚሆኑ ህፃናትን እምቃዊ አፈሳ መጠቀማቸው ግዴታ ውስጥ ወድቋል። ባለፉት ሁለት አመታት በኦሮሚያ፣በደቡብና በአዲስ አባባ አዳማ አካባቢዎች ሲያደርግ እንደነበረዉ የይዞ መዉደቅ እርምጃ በቀሪዉ የአማራ ክልል ይሄን እርምጃ ከጀመረ ሰነባብቷል።
ስለዚህ ያሁኑ ከባለፈዉ የከፋ ስለሆነ በከተሞች አካባቢ ያለዉ መላው ህዝባችን ልጆቹንና አካቢዉን በጥንቃቄ እንዲከታተል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ መልዕክታችን ነዉ‼
ላናሸንፍ አልጀመርነዉም ድላችን ቅርብ ነዉ‼
ፋኖ አለበል አወቀ የቲሊሊ ዘንገና ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
ቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ‼️
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ በዛሬዉኑ ዕለት ይስማላ ከተማ ላይ መሽጎ ያለዉን የጁላ ሰራዊት በሌሊት በመግባት ከ7:00-8:30 አዉደ በቆየዉ ዉግያ ሙሉ ከተማዉን ፋኖ ተቆጣጥሮት አድሯል‼️
ከተኛበት ላይ የደረሱበት የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን አናብስቶች ካምፑን ዶግ አመድ አድርገዉታል።
በዚህም ዉግያ በዉል ያልታወቀ ጡት ቆራጩ ሰራዊት እስከወዲያኛዉ ተሸኝተዋል።
በዚህ የተጨነቁት ሆድ አደር አመራሮች ይስማላ በተተኮሰዉ ተከበናል ብለዉ ሊበን ላይ ሲቃዡና ሲተኩሱ አድረዋል።
ፋኖነት አሸናፊነት‼️
ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ፤ ዕቃቤ ሕግ ፣ ሕግን በመቃረን ማስረጃ አቀረበ!
በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ አምሳ አንድ (51) የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ቀርበው ነበር።
ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ በማስረጃነት በፍርድ ቤት አቅርቦ ፣ የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ላይ ሞት እና ዕድሜ ልክህ ለማስፈረድ ካለው ፅኑ ፍላጎት በመነሳት ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረቡ በችሎት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ እና ክርክር ተነስቷል።
ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምጽ ቅጂ ከዚህ ቀደም ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አቅርቦ በማስረጃነት እንዲያዝለት ያቀረበውን ጥያቄ ፤ የተከሳሽ ጠበቆች ዐቃቤ ሕግ በስልክ የተጠለፈ የድምፅ ቅጂ በምን አግባብ ነው ?! ጠለፋውን ለማከናወን የሚያስችል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለው ወይ ?! በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ፤ ዐቃቤ ሕግ በሰጠው ምላሽ ከ2 ዓመት በፊት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቼ ነው ጠለፋውን ያደረጉት በማለት ምላሽ በመስጠቱ ጠለፋ የተደረገበት መዝገብ እንዲቀርብ በተደጋጋሚ ጊዜ ቢቀጠረም ፤ መዝገብ ጠፍቷል የሚል ምላሽ ከፍርድ ቤት ሪጅስትራል እና መዝገብ ቤት ተገልጿል ።
ይህ ከሆነ በኋላ ዐቃቤ ሕግ ከፍርድ ቤት አመራሮች ጋር በመነጋገር ፤ የጠፋው መዝገብ በሕግ ወጥ መንገድ እንዲደራጅ ካስደረገ በኋላ ፣ መዝገብ ጠፍቷል ከተባለ ከ2 ዓመት ከ9 ወር በኋላ ፤ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በመቅረብ በችሎቱ ውስጥ በተከሳሾች በኩል ከፍተኛ ውዝግብ ተቀስቅሷል ።
ይህም በመሆኑ ፤ ችሎት ከቀጣይ ቀጠሮ በኋላ ከአመራሮች ጋር በመነጋገር በፕላዝማ እንዲሆን አደርጋለሁ ። በማለት ችሎቱን ለመበተን የሞከረ ቢሆንም ፣ በተከሳሾች እና በጠበቆቻቸው በኩል በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንስጥ በሚል ችሎቱን ቢጠይቁም የቀረበው ማስረጃ ሚስጥር በመሆኑ አንስጥም የሚል ምላሽ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል ።
የተከሳሽ ጠበቆች ፤ ደንበኞቻችን ሞት እና ዕድሜ ልክ በሚያስፈርድ ፍርድ ተከሰው ክርክር እያደረግን ነው የስልክ ጠለፋ ለማድረግ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስፈልጋል ፣ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ የተደረገ የስልክ ጠለፋ ከሕግ አግባብ ውጪ በመሆኑ ተከሳሾች ሊጠየቁበት አይገባም ፤ ዐቃቤ ሕግ እንዲያቀርብ የተጠየቀው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመሸሸግ የፈለገው በእኛ በኩል የምናቀርበው መከራከሪያ የሚደገፍ ስለሆን ነው። መዝገቡ እንዳይቀርብ የተደረገው በማለት ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል ።
የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች ፤ ለችሎት ምሬት እና ብሶት ባዘለ መልኩ ፤ በአማራዊ ማንነታቸዉ እንዲሁም በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለምን ብለው በመጠየቃቸው ብቻ ፤ እየደረሰባቸው ያለው ፍርድ ገምድል አካሄድ በችሎት አምርረው ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተቃውሞአቸውን አስምተዋል።
በዚህም ምክንያት ችሎት በፍትሕ ጠያቂዎች ፣የፖለቲካ እና የኅሊና እስረኞች እና ፍትሕን በሚደፈጥጡ መካከል ፤ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ተፈጥሯል ።
ፍርድ ቤት የውዝግብ ውጥረት እያየለ መምጣቱን ተከትሎ ፤ ለኅዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን ፤ከወዲሁ ችሎት በፕላዝማ እንደሚሆን እና የተከሳሾችን ፍርድ ቤት ቀርቦ የመከራከር መብት የሚጋፋ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሰጥቷል ።
©ይድነቃቸው ከበደ
ቀን 29/02/2018 ዓ/ም
የኮማንዶስልጠና የጥሪ ማስታወቂያ !!!
የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከአፓርታይዱ ስርዓት ጋር ትንቅንቅ ከጀመረ ዓመታትን እንዳስቆጠረ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያወቀዉ የአደባባይ እዉነታ ነዉ ።
በመሆኑም ይህን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገርስሶ ለመጣል ሰራዊታችን እና የጦር መሳሪያዎችን እያዘመንን ወደፊት እየገሰገስን ሲሆን ተጨማሪ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እንደሚያስፈልጉን ስላመን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በሙሉ ከጥቅምት _27/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 14_ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን ።
1 ) እድሜ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ /የሆናት
2 ) የአማራ ተወላጅ የሆነ / የሆነች እና በብሔርተኛነት ትግሉ ሙሉ በሙሉ ያመነ / ያመነች
3) ማንኛውንም ሃይማኖት ማክበር የሚችል /የምትችል
4 ) ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ግሉል የሆነ አባልም ያልነበረ/ ያልነበረች
5 ) ስለተወለደበትና ስለሚኖርበት አካባቢ ( የትዉልድ ቦታ ) ሙሉ መረጃና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል / የምትችል
6 ) ምንም አይነት ሱስ የሌለበት
7 ) ከኤች አይ ቪ ፣ ከልብ ኬዝ ፣ ከስኳር ፣ ከደም ግፊት ነጻ የሆነ / የሆነች
8 ) ከአካል ጉዳት ነጻ የሆነ / የሆነች
9 ) ከማንኛውም ወንጀል ነፃ የሆነ / የሆነች
10 ) ማንበብና መፃፍ የሚችል / የምትችል
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ወጣቶች ይህ የስልጠና ጥሪ እንዳያልፋችሁ!!!
ኅልዉናችን በተባበረ ክንዳችን !!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ
ከምቾት ያልተፈታው ልሂቅ ገበና ሁሉም ሰው ሸር አድርጉት
************
ደም የገበርንበት ትግል አሳልፈን አንሰጥም ስንለው ይበሳጫል ??
ዋጋ የከፈልንበትን ትግል ለማሳነስም ይሞክራል??
ጫካ ሆነው እንደት በስልጣን ይጋጫሉ፣
እርስ በእርሳቸው እየተዋጉ ነው!!
ሌባ እና ገንዘብ ሰብሳቢ ናቸው፣
ፀንፈኛ ናቸው ወዘተ ወዘተ በማለት ትግላችንና ተግዳሮቱ ሳይገባው ሲፈለግ ሻይ ቤት፣ሲፈልግ ሆቴል ቤት፣ሲፈልግ ቢሮ፣ሲፈልግ ቤተ ክርስቲያን፣ሲፈልግ መስጊድ ቤት በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ልክ እንደ ጠላት እረ ከጠላቶቻችንም በላይ ያሙናል፣ይሰድቡናል፣ይተቹናል፣ክብራችን ሁሉ ያጥላሉታል እረ ስንቱን ብቻ ግን እኛ አለን🙏💪
ስለዚህ የአማራው ልሂቅ በተግባር ሰርቶ ዋጋ እየከፈለ ያለውን የአማራ ፋኖን ተውት እና ፅናትን ከእኛ ብትማሩ ታተርፋላችሁ??
በክብር መስዋዋትን እና በዓላማ መፅናትን ከእኛ ተማሩ እንላችሗለን!!
ለመሆኑ ልሂቃችን ከምቾት ሳትወጡ የአማራ ፋኖን ትግል የመውቀስ፣የመተችት እና የመክሰሱን ሞራል ከየት መጣ??
በአማራ ህዝብ ስም ከተደራጁት 116 ፓርቲዎች ውስጥ የአማራን ብሔራዊ መብት እና ጥቅም ለማስከበር ጥቂቶች ታምነው ዋጋ ከፍለዋል እንጅ ብዙሃኑ ግን ከምርጫ ቦርድ በሚወረወርለት ሺርፍራፊ ሳንቲም ህዝቡንም ማንነቱንም ጭምር እየተው በራስ ጠልነት አዙሪት የሚንከላወስ ነው።
በተለይም የአማራው ልሂቅ የባንዳ ምልክቱ የሆነውን ብልፅግናን ጨምሮ ምቾትን የሚወዱ ነገር ግን ደግሞ የህዝብን ትግል በማሻሻጥ፣ዋጋውን በማሳነስ፣ስም በመስጠት፣በመፈረጅ፣በማሰይጠን እና በማጠልሸት ህዝብን በማደናገር ለነፃነት የሚታገሉትን ሁሉ አሳልፋችሁ ስትሰጡ በኩራት ነው።
የሚያስቀው ነገር ደግሞ ሃገር ፈርሳ በብተናዋ ጫፍ ላይ ሆናችሁ "ባዳ እና ባንዳ" በሚል አድስ ትርክት ህዝብን ለማደናገር ስትሞክሩ ስናይ አፍረናል!!
በእርግጥ ሁሉ ነገራችሁ ከተምኔታዊነት ውጭ ገቢራዊ የሚሆን አጀንዳ ኖሯችሁ አያውቅም!!
የሃገርን ዳር ድንበር ማስከበር ያልቻለ ሰራዊት እና ፓርቲ ውስጥ እያገለገላችሁ እንደት ስለ ባንዳነት አጀንዳ ታወራላችሁ??
ባንዳነት በእናንት ላይ ካልተገለፀስ በማን ይገለፃል??
ሰሞነኛው የብልፅግናና የልሂቁ ወሬ ደግሞ ፋኖ እንደ 1983 ዓም እንዳይሸወድ ፣አማራ ብቻውን መቆም አለበት ፣ትግሉ ውስብስብ ነው። ምና ምና ምን ሲሉ እንሰማለን
ወዳጀ ! የአማራ ፋኖ ትግል በርካቶችን እየገበረ በደሙ የፀና ድርጅት ነው።
ደም የገበርንበትን ትግል አሳልፈን አንሰጥም የምንለው ዓላማችንን በቁርጠኝነት ከመደገፍ ይልቅ በየስርቻው የደም ዋጋችንን ለማሳነስ ከጠላትም ፤ ከወዳጅም ጋር መቆም የማትችል ስብስብ መሆንህን በደንብ ስለምናውቅ ነው።
አሁንም ተስፋችሁ በፋኖ መስዋአትነት ስልጣን መያዝ መሆኑን ስለምናወቅ ነው።
የምንታገለው ጥሬ ስልጣን ለመያዝ ነው ብለን በድፍረት የተናገርነውም ከዚህ በሗላ በአማራ ሰማይ ስር ለህዝብ የሚታመኑ እና የደም ዋጋችንን ለሚያከብሩ ብቻ መሆኑን በአፅንኦት ተናግረናል።
ዓላማችን ግልፅ ነው።
የትግል መስመራችን፣የትግል ስልታችንና እና የመዳረሻ ግባችንን በሚገባ የታወቀ ነው።
ምክንያቱም የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ለሁሉም ግልፅ እና ውለው ያደሩ አጀንዳዎች ናቸው።
በህልውና ትግላችን ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጠው ነገር ቢኖር በህይዎት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ነው።
ሰለዚህ ልሂቁ ከምቾት ሳትወጣ ትግሉን በአግባቡ ሳትደግፍ ዓላማችንና ዋጋችንን ብታሳንሰው ሃፍረቱ ለአንተ እንጅ ለእውኘተኛው የህዝብ ልጅ ጆሮም አንሰጠውም!!
ስለ ፋኖ ከማውራትህ በፊት አንተ ለትግሉ ምን አድርገሃል??
በስንፍናችሁ እና በፍርሃታችሁ መስራት ያልቻላችሁትን ሁሉ እየሰራነው እያያችሁ እንደት ፋኖ ፀንፈኛ ነው የማለት ሞራሉን ከየት አመጣችሁት??
ፀንፈኛ ማለት የአማራ ብልፅግና፣ፀንፈኛ ማለት አብይ አህመድ፣ፀንፈኛ ማለት ጡት ቆራጩ መከላከያ ሰራዊት እና ከምቾት ያልወጣው ልሂቅ እንጅ ለአማራ ህዝብ ደጀን ሆኖ የአማራን ህዝብ የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የሚታገለው የአማራ ፋኖ አይደለም።
"ለህዝብ ውግንና መታገል ፀንፈኛ ካስባለ"
አዎ ፀንፈኞች ነን🙏🙏
ህዝብ እየፈለሰ እና ሃገር እየፈረሰ ቁጭ ብሎ የሚመለከተው የአማራ ልሂቅ በመጨረሻው ስዓት እንኳን መንቃት አለመቻላችሁ የድኑዛዜው ልኬታችሁ ሙሉ ስሜታችሁን እንደተቆጣጠረው ግን በግሌ መገንዘብ ችያለሁ😂😂😂
ታላቋ ሶቪየት ህብረት ስትፈርስ የመጀመሪያው መነሻ ነገር የታሪክ ሺሚያ እና የኔ የሚል ዕሳቤ በዝቶ ነበር ።
ጥቂት ሳትቆይም ፍርክስክሷ ወጣ!!
ሃገራችንም የገጠማት ልክ እንደ ሶቪየት ህብረት ነው።
በብልፅግና የጠቅላይነት ዕሳቤ ሃገር እየፈረሰች የወል ተቋማቱም ተንደው አልቀዋል።
ሃይማኖት፣ባንድራ፣ኢኮኖሚ፣ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የፓለቲካ ስልጣን እና ህገ መንግስት ሁሉም በሚባል ደረጃ በብልፅግና ጥላ ስር ውስጥ ተጠልለው በመፍረስ ላይ ናቸው።
በአሁኑ ስዓት ኢትዮጲያ እንደ ሃገር ድንበር አልባ፣ስርዓት አልባ፣በፓለቲካ ሙስና እና የጠቅላይነት ዕሳቤ በተጠናወታቸው መሪዎች ዕጅ ወድቃለች።
ስለዚህ የሃገሬ ልሂቃን ሆይ ከምቾት በመወጣት ሃገርን ከመፍረስ፤ህዝብህን ከመፍለስ ታደጓት እንላለን!!
መዳረሻው ድል እና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ያሸንፋል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ጥቅምት 27-02-2018
ሰበር ይስማላ ጊዎርጊስ‼️
ነበልባሉ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ💪💪💪
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ ‼️
በዝርዝር አመለሳለሁ.......
አማራ ተዘግቶ አይኖርም፤አማራ ተራራ ላይ ተሰቅሎ አይኖርም።
አማራ ርስቱን ተነጥቆ አይኖርም የበጌምድር አማራ ከዳሽን ተራራ ላይ ወርዶ ወልቃይት ላይ መክተም አለበት፤ሁመራን ማረስ አለበት፤ከብቶቹ ተከዜ መጠጣት አለባቸው። የጎጃም አማራ ከዳሞት ተራራ ላይ ወርዶ መተከል መኖር አለበት፤በሮቹን ህዳሴ ግድብ ላይ ማጠጣት አለበት፤አሳውን ከግድቡ ወርቁን ከአፈሩ ውስጥ እያወጣ መጠቀም አለበት። ቤተአማራ ከአምባሰል ተራሮች ወርዶ ራያ ሜዳ ሄዶ መኖር አለበት። የሸዋ አማራ ከመንዝ ተራሮች ወርዶ የግራርያ ሜዳ ላይ ፈረሶቹን መጋለብ አለበት፤ፈጠጋርን ማረስ አለበት፤የሸዋ ገበሬ በሮቹን አዋሽ ማጠጣት አለበት። አማራ ወደ መናገሻ ከተማው መትመም አለበት።
በመተማ ዮሐንስ ወረዳ ጓንግ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተደረገ ውጊያ የፀረ አማራው ብልፅግና ኃይል ከባድ ሽንፈተ መከናነቡ ተገለፀ!
በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ዙሪያ በምትገኘው መተማ ዮሐንስ ወረዳ ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ውጊያ እየተካሄደ ይገኛል።
በወረዳው ያለፉት ሁለት ቀናት በተደረ ውጊያ ከባድ ጉዳት ለደረሰባቸው የአገዛዙ ወታደሮች እገዛ ለማድረግ መነሻውን ከምዕራብ አርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ያደረገ ተጨማሪ ኃይል ወደ መተማ እየተጓዘ እንዳለ መተማ ዮሐንስ ወረዳ ልዩ ስሙ ጓንግ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ላይ ሌላ ያልታሰበ ድንገተኛ ጥቃት ተከፍቶበታል።
በዚህ ድንገተኛ ጥቃት በርካታ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ሲነገር፡ ከውጊያው በኋላ አንድ አይሱዙ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ሙሉ የጠላት አስከሬንና ሁለት አምቡላንስ ሙሉ ቁስለኛ ተጭኖ ወደ ማሰሮ ደንብ ተወስዷል ነው ያለው በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ።
በዛሬው ውጊያ መይሰው ካሳ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦ ስር የሚገኙት የተካ ብርጌድ አባላት ናቸው በጠላት ላይ ቅፅበታዊውን እርምጃ በመውሰድ ድል የተቀዳጁት ብሏል ዕዙ።
በተመሣሣይ በዚኽው በመተማ ዮሐንስ ወረዳ ልዩ ስሙ ታጉር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ጥቅምት 25/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ለሦስት ሰዓታት በዘለቀው ውጊያ 27 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከ35 በላይ የሚሆኑት ስለመቁሰላቸው መረብ ሚዲያ የዕዙን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋቢ አድርጎ መዘገቡ አይዘነጋም።
ትንቅንቁ ትናንትናና ዛሬም ቀጥሎ ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፡ በውጊያው የፋኖ ጦር አቅም እምርታዊ እድገት የታየበትና በአንፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ጦር ከከባባድ ሜካናይዝ መሣሪያ ጀምሮ እስከ አየር ኃይል ታጥቆ ነገር ግን እራሱን መከላከል እንኳን የማይችልበት ደረጃ መድረሱ በጉልህ የታየበት ነው ሲሉ የአይን እማኞች ገልፀዋል።
+1
አርበኛ ስለሽ ከበደ
የ206ኛ ኮር የ14ኛ፣24ኛ፣34ኛ ክፍለጦር አደረጃጀት ተጠናቋል።
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ24ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት እንዲሁም የጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር አወቃቀር እያደራጀ ይገኛል።
በዚህም በአዲስ አደረጃጀት የ24ኛ ክፍለጦር በቀደመው አደረጃጀት ቦቅላ አባይ ብርጌድ ፣ የስናን አባጂሜ ብርጌድ እና የደባይ ጮቄ ብርጌድ በጋራ በአንድ ሆኖ ተመስርቷል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃዎች በጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር የተደራጀ ሲሆን ለቀጣይ ለሚሰጣቸው ድርጅታዊ ስምሪትም ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የጊዜያዊ መንግስት አሰተዳደር ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
ክፍለ ጦሩን መልሶ ለማደራጀት የተገኙ የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች
1 አርበኛ ምናልባት ይታየው የዲያሰፖራና ውጭ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ
2 አርበኛ ሰለሺ ከበደ የቴዎድሮሰ ዕዝ ም/አደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ
3 መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ የቴዎድሮሰ ዕዝ የሰው ሀይል ኃላፊ እና የ206 ኮር አመራሮች በተገኙበት የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ስር የሚገኙ የ14ኛ፣24ኛ፣34ኛ ክፍለጦር ምስረታ አጠናቋል ።
ድል ለአማራ ፋኖ!!
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
ጥቅምት 27 /2018 ዓ.ም
መርአዊ ከተማ ላይ ጥቃት ተፈፀመ
አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ የ102ኛ ኮር አካል የሆኑት ኮረኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ሻምበል መማር ጌትነት ሻለቃ አባላት መራዊ ከተማ ላይ የተሰገሰገውን የአብይ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወሰደበት
በተጠና የከተማ ኦፕሬሽን በጠላት ምሽግ ላይ ከባድ የቦንብ ዝናብ በማውረድ 12 የስርዓቱ ወንበር ጠባቂ ሚሊሻና አድማ ብተና እስከወዲያኛው የተሸኙ ሲሆን ከ20 በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
በዚህ መብረቃዊ ጥቃት የመከላከያ ጦር አዛዡ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ማምለጥ ቢችልም ሌሎች የብልፅግና ሆድ አደር ካድሪዎች ነፍሴ አውጭኝ በማለት ወደ ጦር ካምፕ ፈርጥጠውል በጥቃቱም ከፍተኛ ድንጋጤና የጦር መረበሽ እንደተፈጠረ ለማወቅ ችለናል በርካታ ሙትና ቁስለኞችን ህዝቡ እንዳያይ ቤት እየዞሩ በማዘጋት ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።
በመጨረሻ አሁንም አልመሸም እዳላቹህን ተጠቅማቹህ ወደ ማንነታቹህ ተመለሱ በማለት ለሚሊሻ እና አድማ ብተናወች መልክት አስተላልፈዋል።
ጥቅምት 27/2018ዓ.ም
