fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 039
مشترکین
+22224 ساعت
+3937 روز
+1 35930 روز
آرشیو پست ها
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ​ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር​ ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የትግሉን ቁመና በተመለከተ ውይይት አካሄደ !!   ጥር 25/2018 ዓ.ም አፋብን ደቡብ አመራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለማርያም ክ/ጦር ወቅታዊ የትግሉን ቁመና አስመልክቶ የከሰም ፪ኛ ኮር ከፍተኛ አመራሮች እና የክፍለጦሩ አመራሮች በተገኙበት አመርቂ ውይይት ተካሂዷል ። የአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት ተነፍጎ ከአረመኔው አብይ አህመድና ምስለኔዎቹ ለመላቀቅ ትግል ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በሸዋ ምድር በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኘውን የሥርዓቱን ጡት ቆራጭ  ኮማንዶና "ጥምር ጦር" ተብሎ የሚጠራውን ቅጥረኛ ኃይል በመደበኛና በደፈጣ ውጊያዎች በማድቀቅ፤ ፀረ-አማራ የሆነውን የብልፅግና ሥርዓት ለማፍረስ የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ። ​በመሆኑም በሸዋ፡ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ስር በሚገኘው የቡልጋ ቀጣና ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ እንደመገኘቱ የማይቀርውን የአማራን ነፃነት ለማረጋገጥ ወጣቱን በማሰልጠንና በማደራጀት ሰፊ የትግል እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ ።​ ሆኖም ከአንድነቱ ማግስት ጀመሮ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ​ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ ኮር ​ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር አንዳንድ የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ የአማራን ትግል በጀግኖች የቁርጥ ቀን ልጆች ጥረት ወደ አንድ በመሰብሰብ ፥ አንድ ወጥ አታጋይ ድርጅት መመሥረቱን ተከትሎ፤ ክፍለ ጦሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ወቅታዊ የትግል እንቅስቃሴንና የአንድነትን አስፈላጊነት በተመለከተ ሰፊ ውይይት አካሂዷል ። በውይይቱም የጋራ አቋም በመያዝ የቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቋል ። በውይይቱም ላይ የክፍለ ጦሩና የኮሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል ። 1. ​አርበኛ ፻ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ዋና መሪ 2. ​አርበኛ ደጉ ተስፋዬ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ 3. አርበኛ እንዳልካቸው ግርማ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ሲቪል አስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ 4. አርበኛ ፶ አለቃ ጎሽመው ኃይሌ ---  የከሰም ፪ኛ ኮር ዋና ወታደራዊ አዛዥ 5.​ አርበኛ ፲ አለቃ ሙሉጌታ ፍቅሬ --- የከሰም ፪ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ፡ እንዲሁም በተጨማሪም አንድነታችን ለአማራ ህዝብ የመኖር ነፃነት ዋስትናችን በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የክፍለ ጦሩ አመራሮች በውይይቱ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል ። ​ድል ለአማራ ፋኖ !! ድል ለአማራ ሕዝብ !!! ጥር 25/05/2018 ዓ.ም ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ደቡብ አማራ ቀጠና ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ሪፖርተር አርበኛ ኃቀኛው ይታፈር

በአገዛዙ በሀይል ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ተቋም የገቡ ምልምል ሰልጣኝ ወታደሮች ፋኖን ተቀላቀሉ!! =========================== ፋሽስቱ አብይ አህመድና አገዛዙ ስልጣኑን በኢትዮጵያውያን ህጻናት ደምና ጉልበት ለማቆዬት ከተለያዬ የመዝናኛ ቦታ እንዲሁም ከትምህርት ቤት አፋኖ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ያስገባቸው ምልምል ወታደሮች ከብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም በመክዳት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ። አገዛዙ በሀይል አግቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ካስገባቸው በኃላ ከከዳችሁ ፋኖ ያርዳችኋል፣ይቆራርጣችኋል እያለ የማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳ እንደ እንደሚነገራቸው ሰልጣኞች አክለው አስረድተዋል። ዳሩ ግን የ109ኛ ኮር ከተለያዬ የሀገሪቱ ክፍሎች ታፍነው የሚመጡ ሰልጣኞችን ልዩ እንክብካቤ በማድረግ የትራንስፖርት ወጭያቸውን በመሸፈን ከ136(አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት) በላይ ምልምል ሰልጣኞችን ወደ ትውልድ ቀያቸው በክብር በመሸኘት እና ከወላጆቻቸው ጋር በማገናኘት የወገን አለኝታ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል። ➡️ወደ ማሰልጠኛ ታግተው የገቡት ኢትዮጵያውያን ዕድሜያቸው ከ15-17 የዕድሜ ክልል እንደሚገኙ ምልምል ሰልጣኞች ለፋኖ አስረድተዋል። 👉በኢትዮጵያውያን ታዳጊ ህጻናት ጉልበትና ደም ጸንቶ የሚኖር ስልጣን(ዙፋን) የለም!!! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ! 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት ጥር 26/2018 ዓ.ም

በመተማ መስመር ታይተዋል እያሉ፡ ጎንደር ፋሲለደስ ታይተዋል እያሉ፡ ምንነው ወደ ወሎ ባልመጡብን አሉ፡ የእነ አፄዎቹ ዘር የኛ የወርቅ አምባር ፡ ምን አለ አገራችን ምንስ አለ ጎንደር፡ አባይን አቋርጠህ በድል ስትሻገር፡ የእነ አፄወቹ ዘር ሄደ ገሰገሰ ፡ ያነን የሾህ አጥር እየደመሰሰ፡ በወሎ ምድር ላይ ደሙን አፈሰሰ፡ እየተባባልን በቀን 19 /4/2018 ዓ ም እኔ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ አኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ እና ወንድሜ ታማኙ የዘመናችን ጀግና እና የልጅ አዋቂው የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ፣ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባት ኮር ዋና አዛዥ ፋኖ አመኑ አለማንተ አንድ ላይ ተገናኝተን ወንድም አማችነትን እና ወንድማዊ አንድነትን ጥብቅ ትስስር በሚል መሪ ቃል ላይ ውይይት እያደረግን ባለንበት ቦታ የአማራ ህዝብ ቋሚ ጠላት የሆነው ብልፅግና ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ከቡግና ወረዳ ወደ ብርኮ የሚባል ቦታ እንቅስቃሴ ያደርገ ቢሆንም በወሎ አናብስቶች እና በጎንደር ጀግኖች ተመክቶ ሊያፍን የመጣው ታፍኖ ብርኮ በተባለ ቦታ አብዛኛው ጠላት የያዘውን ተቀብለን ላይመለስ እስከዛኛው ሽኝተነዋል፡፡ ከጧት 4፡00-10:00 ሳዓት ድርስ በወሰደው አውደ ውጊያ ጠላት የሰው ሁይሉን በጣም ያጣበት፣ በርካታ ክላሽ ፣ ብሬን እና ተተኳሹን እንዲሁም የክፍለ ጦር የሰው ሀይል አመራር ተመቶ የማርክንበት እና ቅስሙን የሰበርንበት የተቀናጀ የሁለቱ ኮሮች የቅንጅት ውጊያ ያደረግንበት ነበር፡፡ እኛ የላስታ አናብስቶች እና የጎንደር አንበሶች በወሎ ምድር ላይ ያሳየነው ተጋድሎ በወሎ ሰማይ ስር ብዙ አሳምነው በጎንደር ብዙ ቴወድሮስ እንዳለ ያሳየንበት ድንቅ የውጊያ ጥበብ በየልምዳችን ተጠቅመን ጠላትን አንገት ያስደፋንበት ውጊያ ነበር፡፡ በዚህ ውጊያ ጠላትን ያከሰርንበት እኛ ያተርፍንበት እና የተማርንበት ወንድሜ አርበኛ አመኑ እና ያሉ የሰራዊት አባላትን ከኛ ከጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጋር በጥብቅ ያስተሳሰርንበት ነው፡፡ በነበርው አውደ ውጊያ የሁለቱ ኮሮች ቅንጅታዊ ውጊያ ስመለከት አማራ አሁንም በርካታ አሳምነው እና ቴዎድሮሶች እንዳሉ እና ትግላችን አጠናቀን የህዝብ ጠላት የሆነው ብልፅግና የምንቀብርበት ሰአዓት እሩቅ እንዳልሆነ ተርድቻለው፡፡ የተማርኩት እና የተርደውት አንድነት የሁሉም አሸናፊ እንደሆነ ነው፡፡ በነበርው ውጊያ ጠላትን አከርካሪውን የመታነው በአንድ አላማ በአንድ ልብ አንድን ቋሚ ጠላት ላይ ተናበን ሰለነበር ነው፡፡ ባጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ እየሆነ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋን ልንመክተው የምንችለው ፣ ስራቱንም ማሸነፍ የሚቻለው አንድ ሁነን ስንቆም ብቻ እንደሆነ ተምረንበታል። አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀነራል አሳምነው ፅጌ ኮር ምክትል አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙሉየ !!!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ተናዳፊ ተረቮች

የፋኖ ደጋፊ ነህ በሚል ሰበብ የአንድ ግለሰብ ሰብል በአገዛዙ ብልፅግና አመራሮች ተወረሰ! በአገዛዙ ብልፅግና መንግስት ጥርስ ውስጥ የገባው የአማራ ህዝብ ይገደላል፣ ይፈናቀላል፣ ሐብት ንብረቱ ይዘረፋል፤ ጌቶቹ ህጋዊ ድሃ አድርገነዋል አሉ፤ የጌቶቹ ሎሌዎች የእኛዎቹ ጥቁር አማራዎች ሁነኛ ማስፈፀሚያ ከሆኑ ውለው አድረዋል። በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የቡግና ወረዳ 01 ቀበሌ አይና እየሱስ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን የ65 ዓመት አዛውንት አቶ ይመር ገበያው የተባሉትን ግለሰብ በ2017 ለ2018 ዓ/ም የምርት ዘመን አርሰው፣አርመው፣አጭደውና ከምረው ያስቀመጡትን ከዛሬ ነገ ወቅቼና አምርቼ ቤተሰቦቼን አስተዳድራለሁ ያለትን የስንዴ ክምር ጥር:-25/2018 ዓ/ም በሌሊት በመውቃትና በማምረት 13.5 ኩንታል ስንዴ የቡግና ወረዳ ብልፅግና ካቢኔዎች ለግላቸው እንደተከፋፈሉት ታውቋል። የአዛውንቱ እህል የተወረሰው የፋኖ ደጋፊ ነህ፣ፋኖ ጋር ግንኙነት አለህ በሚል ሚዛን እማይደፋ ምክኒያት ሲሆን በሌሊትና በግዴታ የግለሰቦችን ከብቶችና አህያወች በማስወጣት በወረዳው ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ባለሙያዎች አስተባባሪነት፣ በብልፅግና የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪ ጌታየ ካሳውን ጨምሮ፣ ውበት ገናኑ ድርጅት ኃላፊ፣ ሻምበል አስረሴ ሞላ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ፣ ውለታው ምስጌ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ፣ ኮሎኔል ዘውዱ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊና አንዳንድ ሚሊሻዎች እንዳስተባበሩት ታውቋል። በጠራራ ፀሐይ ሐብት ንብረታቸው የተዘረፉት አቶ ይመር ገበያው የአንድ ወንድና የአራት ሴቶች ልጆች አባት የሰባት ቤተሰብ አስተዳዳሪ ሲሆኑ በአሁኑ ጊዜ እርሳቸው በሦስት እግር እየሄዱ አርሰው ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩበትን እህላቸውን በግልፅ ሲቀሙና ሲዘረፉ እያየን ብልፅግና ዛሬም ነገም በእያንዳንዳችን ቤት የአይናችሁ ቀለም አላማረንም እየተባልን መዘረፋችን አይቀርም ሲሉ አንዳንድ የአይን እማኞች አስተያየታቸውን ገልፀዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  ህዝብ  ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥር 26/2018 ዓ/ም

አማራነትን የምንኖረው እንጅ የምናወራው አይደለም በማለት ለሌሎች ንፁሃን አማራዎች ነፃነት የተከፈለ መስዋዕትነት!! ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል!! አፋብን ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀኔራል አሳመነዉ ፅጌ ኮር አካል የሆነው በመደራጀት ላይ ያለው ራስ አንቺም ክፍለ ጦር  ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የሆነው ጓዳችን አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ጥር 25/2018 ዓ.ም በሰ/ወሎ ፍላቂትና ገረገራ ከተማ በቅርብ ርቀት አግሪት ዙሪያ በነበረዉ እልህ አስጨራሽ ዉጊያ ብዙ ባንዳዎችን እስከ ወዲያኛዉ ሸኝቶ በጀግንነት የክብር መሰዋትነትን ተቀብሏል። ጀግናው አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ከአባቱ ከወታደር ሙላቴ አማረ እና ከእናቱ ወ/ሮ ደናዬ አበበ በ1985 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 026 ቀበሌ በጎጨረቃ ተወለደ። ከልጅነቱ ጀምሮ በሀገር ፍቅር ስሜት ተከትቦ ያደገው አርበኛ ማንዴ ሙላቴ በ2013 የሰሜኑ ጦረነት በወቅቱ በቀረበው ሀገራዊ ጥሪ የመከላከያ ተቋም ውሰጥ በመግባት ከ1 ዓመት በላይ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ለህዝብ ክብር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ታግሏል አታግሏል። እጅግ ሲበዛ ቆራጡ አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በመከላከያ ተቋም በቆየበት ወቅት በብሬን ተኳሺነት እና በድሽቃ ተኳሽነት የሚታወቅ ሲሆን በጀግንነቱ ፣  በስነ-ምግባሩ እና በስራ አክባሪነቱ አርዓያ እንደነበር ጓድኞቹ እና ባልደረቦቹ በቁጭት ይናገራሉ።              " ማንደፍሮ መጣ ስናይፐር ታጥቆ"         " ጠላት ራደ ልቡ ተጨንቆ " ተብሎ የተገጠመለት ጀግናው አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ ከ 2015 ዓ/ም ጀምሮ በመቄት ወረዳና ዙሪያው የአማራ ፋኖን ከጓድኞቹ ጋር ሆኖ የመሰረተና ያደራጀ ሲሆን  ትግሉን ከተራ አባልነት እሰከ ተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ጓዶቹ የጣሉበትን ሁለተናዊ ኃላፊነት በቅንነት ፣ በታማኝነት ፣ በፅናት እና በጀግንነት ተወጥቷል።  ይህ ብቻም ሳይሆን የትግሉ መሰረት ከሆነው የሺምቅ ውጊ እስከ ፊት ለፊት በርካታ አውደ ውጊያዎች ልቡን የተማመነው ጀግናው አርበኛ ታግሏል አታግሏል። የቅርብ ጓድኞቹ አርበኛውን ሲገልፁት ጦረኛ ብቻ አይደለም እግጅ ሲበዛ ደፋር ልቡን የተማመነ ባህር ሰንጣቂ ፣ ወንዝ አሻጋሪ እንደነበር የዥጣና ፣ ሾደብ እና ተከዜ ወንዞች ምስክሮች ናቸው ይላሉ ።                    "ዝናቡ ቢጥል ወንዙም ቢሞላ"            "ግንድ ቢያገላብጥ ቢመስል አተላ"            "ማንዴ ያሻግራል አዝሎ በገላ" ቆራጡ አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በመቄት ወረዳና ዙሪያው  በፋኖ አደረጃጀት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በቅንነት እና ትግሉ በሚፈልገው የስነ ምግባር ደረጃ ታግሎ ያታገለ ሲሆን በኃላፊነት ደረጃ ለአብነት ለማንሳት ያህል የአንድነት ሻለቃ ሻበል አዛዠ ፣ በውባንተ አባተ ክ/ጦር በመቄት ም/ዘመቻ መምሪያ እና የራስ አንቺም ክፍለጦር ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ በመሆን ስኬታማ የአመራር ሰጭነት ሚናውን በብቃት ተወጥቷል። አርበኛ ማንደፍሮ ሙላቴ በተሰማራበት አውደ ውጊያ እና የአመራር ሰጭነቱ ውጤታማ ከመሆኑም በተጨማሪ በስነ- ምግባሩ እና በአላማ ፅናቱ የተመሰከረለት የመልካም ስብዕና ባለፀጋ የነበረ ቆራጥ ፣ታታሪ፣  ከመልካም ተክለ ቁመናው ጋር የወገን ኃይል የሚሳሳለት  የጠላት ጦር ግን   አርበኛ ማንዴ ሙላቴ መጣ ሲባል የሚደነብርበት ጀግና ታጋይና አታጋይ ነበር። ራስ አንቺም ክ/ጦር  ከሌሎች አሃዶች ጋር በጋራ  ከአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ባንዳ ጋር በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 018 ቀበሌ አግሪት ዙሪያ በተደረገው ትንቅንቅ በርካታ የግል ወንበር ዘበኞችን ደምስሶ ጀብድ በመፈፀም ጥር 25/2018 ዓ.ም በክብር ተሰውቷል። "የጀግና ታሪክ ሁሌም ከመቃብር በላይ ነው!!" መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የክፍለጦሩ ቃል አቀባይ 50/አ መንግስቱ ካሳ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምናልክ ዕዝ ላስታ ጄ/ አሳምነው ፅጌ ኮር ራስ-አንችም ክፍለ-ጦር ጥር 26/ 2018 ዓ.ም

የጠላትን አባል ግንባሩን ብሎ ወደ ወንድሞቹ የተቀላቀለው ወንድማችን አቀባበል ተደርጎለታል። ወታደር ስንታየሁ ይባላል። ከ9ወር በፊት በግዳጅ ነበር ወደ ውትድርና በአገዛዙ ታፍሶ የገባው ከዛም ምስራቅ
+1
የጠላትን አባል ግንባሩን ብሎ ወደ ወንድሞቹ የተቀላቀለው ወንድማችን አቀባበል ተደርጎለታል። ወታደር ስንታየሁ ይባላል። ከ9ወር በፊት በግዳጅ ነበር ወደ ውትድርና በአገዛዙ ታፍሶ የገባው ከዛም ምስራቅ እዝ 99ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሎ ለ3ወር የቆየ ቢሆንም አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርገው በደል እረፍት ስለነሳው የጠላ.ትን ተረኛ ጥበቃ (ዋርድያ )ግንባሩን ብሎ ከነ ሙሉ ትጥቁ አፋብሓ ቴዎድሮስ እዝ105ኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል ። ©️ምስጌ ዘድንግል የ55ተኛ ክ/ጦር ሕ/ግ ሀላፊ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና (አሳምነው ዕዝ) ምክትል መሪ አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ እና ሌሎች የዕዝ እንዲሁም የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አመራሮች፤ በተገኙበት የዓፄ ዘር ዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ሰባት ለሰባ ክፍለጦርን የውስጥ አንድነትን በማጠናከር እና ወቅታዊ የፖለቲካ ግንባት በመጠት ተሀድሶ ተደረገ። የአብይ አሕመድን መንግሥት ክፉኛ እየፈተነች ያለችውን የ'ሰባት ለሰባ' ክፍለ ጦርን የውስጥ አንድነት ከማፅናት ባለፈ፣ ክፍለ ጦሯ እንደ ንስር ታድሳ እንድትወጣ እና ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጁ እንድትሆን ተደርጓል። ​በመሆኑም በክፍለ ጦሯ መዋቅር ውስጥ ያለን የአደረጃጀት ጥንካሬ እና ተከታታይ የለውጥ ሂደት ላይ ነጥቦቹን እንደሚከተለው በዝርዝር በማየት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ የክፍለጦሩ አመራሮች ገልፀዋል። በዚህም ​የአመራር ሚና፡የአሳምነው ዕዝ ከፍተኛአመራሮች ወታደራዊ ስልትን ከፖለቲካዊ ንቃተ-ህሊና ጋር በማጣመር የክፍለ ጦሩን አቅም የሚገነባበት ሂደት በአፅንኦት እዲሰሩ ሲሉ ለክፍለጦሩ አስታላልፈዋል። ​የውስጥ አንድነትን ማፅናት፡ በአንድ የጦር ግንባር ውስጥ ውጤታማነት የሚመጣው ከመሣሪያ ብዛት ይልቅ በታጋዮች መካከል ካለው ጽኑ አንድነት ነው። አመራሮቹ በክፍለ ጦሩ ውስጥ ያለውን መተማመን እና ዓላማን የማስረጽ ሥራ ቅድሚያ ሰጥተውታል። እንደ ንስር መታደስ ንስር አርጅቶ ሲደክም ላባውንና ጥፍሩን አውልቆ በመጣል ራሱን እንደሚያድስ ሁሉ፣ የ'ሰባት ለሰባ' ክፍለ ጦርም ካለፉት ውጊያዎች ያገኘውን ተሞክሮ በመጠቀም፣ ድክመቶቹን በማረም እና አዳዲስ ስልቶችን በመቀየስ ጠንካራ ሆኖ መውጣቱን እንዲችልና ለአሳምነው ተናዳፊ ተርቮች ጋር ሰፊና ጠለቅ ያለ የፖለቲካ እና የአንድነት አቋም ተይዟል። ከዚህ በተጨማሪም ​ስልታዊ ጠቀሜታ ይህ ክፍለ ጦር የመንግሥትን ጦር ክፉኛ የሚፈትን "የራስ ምታት" ከመሆኑም በላይ ፣ በደቡብ አማራ አካባቢ ያለውን ወታደራዊ ሚዛን የፋኖ አንደምታን ትልቁን ሚና እንዲጫወት የሚያደርግ መህኑን ከአመራር እስከታች ያለ ጦር ማሳየቱን የተበታተነው የአማራ ፋኖ ወደ አንድነት መምጣት ያስደሰታቸውና በዝግጅቱ ላይ የተገኙት እንግዶች፤ ከሰባት ሰዓት በላይ የሚፈጅ መንገድ ተጉዘው በመምጣት ድጋፋቸውን ገልጸዋል እንግዶቹ ባስተላለፉት መልዕክት 'በማንኛውም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ሁሉ ከጎናችሁ እንሰለፋለን፤ የሚፈለግብንን ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ እንሰጣለን። ይህ አንድነታችሁ ለእናንተ ብቻ ሳይሆን ለመላው አማራ ሕዝብ ትልቅ ትርጉም አለው' በማለት አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!, ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ጥረ 26/05/2018 ዓ.ም

'' እርምጃ ውሰዱበት ተብለናል" የአገዛዙ ፖሊሶች! "ከተቃጣብኝ የግድያ ሙከራ ለጊዜው ብተርፍም ፣ መላው ቤተሰቤ ግን አሁንም አደጋ ላይ ነው" ዘሪሁን ገሠሠ! የቀድሞው የአብን ፓርቲ መስራች አባልና አመራር የነበረው፡ በኋላም የሕዝቤን ጥያቄ በምስር ወጥ አለውጥም በሚል በአቋሙ በመፅናቱ ከእስራት ጀምሮ አያሌ ግፍና መከራ የተፈፀመበት ፖለቲከኛው ዘሪሁን ገሠሠ "ህዝብ_ይወቅልኝ" በሚል ትናንት ጥር 25/2018 ዓ/ም የተፈፀመበትን ግፍ በሚከተለው መልኩ ገልጿል። ህዝብ_ይወቅልኝ! በዛሬው እለት ማለዳ ለስራ ከወጣሁበት ስልክ ተደወለልኝ። ''አባቴ ቤታችንን ሊያፈርሱብን ነው!'' የሚል የልጆቼ ድምፅ ነበር። የዛሬ ሁለት አመት በመከላከያ (ኮማንድ ፖስት) ተይዥ ወደአዋሽ አርባ ከመሄዴ በፊት '' አባቴ ኪራይ ቤቱን በ3 ቀን ለቃችሁ ውጡ ተባልን!'' ብለው በገለፁልኝ የለቅሶ ድምፅ ነበር። ከነበርኩበት በፍጥነት ደረስኩ። ስደርስ ግን ''ሀሰን'' በሚባል አየር ማረፊያ አካባቢ በሚኖር የኮምቦልቻ ከተማ #ሚሊሻ የሚመራ የታጣቂ ቡድን ግሬደር አስገብቶ ማፍረስ ጀምሯል። ወጉ አይቀርምና ''በህግ አምላክ!'' ብዬ ለማስቆም ሞከርኩ። '' መላ ቤተሰቤን ገድላችሁ ካልሆነ ፣ በአመታት ጥረት በይዞታዬ ላይ የሰራሁትን ቤት ከህግ አግባብ ውጪና ተገቢውን ካሳ ሳትከፍሉ አታፈርሱም!'' በማለትም ለማስረዳት ጣርኩ። ሀሰን የሚባለው የቡድኑ መሪ ግን '' እርምጃ ውሰዱበት ተብለናል። አይተኩሱም ብለህ እንዳታስብ!'' በማለት አፈሙዝ ወደደረቴ አነጣጠረ። መላው የአካባቢው ማህበረሰብ ሁኔታውን በለቅሶ ታጅቦ ይከታተል ነበር። ''እሺ አፍርሱ'' ብዬ ሂደቱን በካሜራዬ ለመቅረፅ ስጀምር ሁሉም የታጠቁ ሀይሎች በህብረት እላዬ ላይ ሰፈሩ። ባለቤቴን ጨምሮ የስድስት ወር ህፃን ልጄ ተፈነከተች። ግፍን ተሸክሜ ከምኖር መሞትንም በደስታ ስለምቀበለው ፣ በእኔ ላይ የደረሰውን ልተወውና መላው ቤተሰቤ ግን እጅጉን ተጎድቷል። ግብግቡ ከቀጠለ በኃላ በበርካታ ታጣቂዎች ታግቼ ውያለሁ። ሂደቱ የቤቱን አጥር በማፍረስ ለጊዜው የቆመ ቢሆንም ፣ ''በቀጣይ ቀናት እናፈርሰዋለን!'' የሚል ዛቻ ተነግሮኛል። ለዚህ ሁሉ መነሻ የሆነው በአካባቢው የሚሰራው የአስፋልት መንገድ ሲሆን የመንግስት አመራሮች '' ካሳ የምንከፍለው ገንዘብ የለንም። ገንዘብ ስናገኝ እንከፍላለን። መንገዱ ግን እስከምርጫው ማለቅ ስላለበት ፣ እናንተ በ15 ቀን ውስጥ ቤታችሁን አፍርሳችሁ ጎዳና ውደቁ!'' የሚል ውሳኔ ይዘው መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን ፣ ሌሎች አርሶደሮችና ባለይዞታዎች በተባለው አግባብ ፈርተው ያለአንድ ብር ካሳ ሲያፈርሱ ፣ የኔ ልጆችና ቤተሰቦቼ ግን የምንወድቅበት ሌላ አማራጭ ስለሌለን '' በህግ አግባብ በተቀመጠው መልኩ ይፈፀም። አለበለዚያ እኛን ገድላችሁ ቤቱን በላያችን ላይ አፍርሱት'' የሚል ውሳኔ በመወሰናችን ነው! ምንም እንኳ መጠነኛ ጉዳት ባስተናግድም ከታጣቂዎቹ እገታ ለጊዜው ነፃ ወጥቻለሁ። መላው ቤተሰቤ ግን በዚህ ጨለማ '' ምን ቤት አለንና ...'' ብለው ፤ በረንዳ ላይ እየተላቀሱ በስጋት ላይ መሆናቸውን ደውዬ አረጋግጫለሁ። ይህ ዛሬ የግድያ ሙከራ ያደረገ ቡድን ነገ ምን እንደሚያደርጋቸው አላውቅም! ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ ብቻ - አግተው ከስራ አሰናበቱኝ ፣ ቤተሰቤን ከተከራየንበት ቤት እንዲወጡ በማድረግ ጎዳና በትነው የበቀል ጥማታቸውን ተወጡ ፣ ከአስር ወራት የአዋሽ አርባ ቆይታ በኃላ ከእስር ብወጣም ፣ '' የፌደራል ኮማንድ ፖስት ቢለቅህ እኛ እንፈልግሀለን'' ተብዬ በጊዜው የተያዙብኝ ስልኮችና ሌሎች ንብረቶችን ጨምሮ እስካሁን አልተለቀቁልኝም። የባንክ አካውንቴ ከታገደ ሁለት አመት አለፈው። ''ልቀቁልኝ'' ብዬ ስሄድ '' ስናፈላልግህ ነበር'' ተብዬ ታሰርኩ ፣ መልሼ ተፈታሁ። በመጨረሻም አካባቢውን ለቅቄ መሄድን መረጥኩ። አሁን ደግሞ ልጆቼን በገዛ ይዞታቸው ላይ ቤት ሰርቼ ''ከኪራይ ቤት ወጡ'' ስል ሞልቶ አልፈስ ያላቸውን የግፍ ቁና ሊሰፍሩ መጥተው ፣ ይህ ኢ-ሰብአዊና አረመኔያዊ ወንጀል ተፈፅሟል። ይህን ከመቻል በላይ የሆነውንና አደባባይ ለማውጣት የተገደድኩበትን ግፍ ስለፍትህ የቆመ ሁሉ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ! ምናልባትም በእኔም ሆነ በቤተሰቤ ላይ ከዚህም የከፋ ነገር ቢከሰት ተጠያቂዎቹና ይህን የፈፀሙትን አካላትም ከወዲሁ ለማሳወቅ እወዳለሁ!

በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብይ አህመድ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ቢኖር ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ለማውራት የሚያስችል የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን ነው። አብይ ለሀገርና ለታሪክ ካላቸው ትልቅ ቦታ አንጻ
በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብይ አህመድ ሊገነዘበው የሚገባው ነገር ቢኖር ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ታሪክ ለማውራት የሚያስችል የሞራል ብቃት የሌለው መሆኑን ነው። አብይ ለሀገርና ለታሪክ ካላቸው ትልቅ ቦታ አንጻር ሲታይ፣ የእሳቸውን የእግር ጥፍር ያህል እንኳን ሊመጥን የማይችል ፍጡር ነው። ​በመቀጠልም፣ ‘ባንዳ’ የሚለውን ቃል በተመለከተ፤ አማራን እንደ ከብት እያሳረድክ ያለኸው አንተ ራስህ ሆነህ ሳለ፣ ሌላውን ባንዳ ብለህ ለመፈረጅ እንዴት ትደፍራለህ? እውነተኛው የባንዳነት ባለቤት አንተ ራስህ መሆንህን ለምን ረሳኸው? ይህ የታሪክና የህዝብ ተጠያቂነት በቅርቡ የሚያገኝህ ይሆናል።

አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለመላው የፋኖ አመራሮች!" ​"ከብልፅግና የደህንነት መሥሪያ ቤት (ከቁጥር 604) ለፋኖ አመራሮች ስልክ እየተደወለ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛውም የአመራር አካል ከዚህ ቁጥር የሚመጣን ጥሪ በፍጹም እንዳያነሳ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። ይህ መረጃ ለሁሉም አመራሮች እንዲደርስ በከፍተኛ ፍጥነት 'ሼር' (Share) በማድረግ ተባበሩ።" ​ ​ይህ መልዕክት ለምን አስፈላጊ እንደሆነና ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎችን በሦስት ዋና ነጥቦች ማየት ይቻላል፡ ​1. የደህንነትና የመረጃ ጥበቃ ​የደህንነት መሥሪያ ቤቶች አጭር ቁጥሮችን (እንደ 604) ተጠቅመው የሚደውሉት መረጃ ለመሰብሰብ ወይም የአንድን ግለሰብ ማንነት ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል። ስልኩ በሚነሳበት ጊዜ ተደዋዩ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ (Location) በቴክኖሎጂ ለመለየት ስለሚያመች፣ ጥሪውን አለማንሳት ለደህንነት ሲባል ተመራጭ ነው። ​2. የስነ-ልቦና ጫና (Psychological Tactics) ​እንዲህ ያሉ ጥሪዎች በአመራሮች መካከል ጥርጣሬን ለመፍጠር፣ ግራ ለማጋባት ወይም "ድርድር እንጀምር" በሚል ሽፋን መረጃ ለማውጣት ሊደረጉ ይችላሉ። ጥሪውን ባለመቀበል የጠላትን የመረጃ ምንጭ መዝጋት ይቻላል። ​3. የመረጃው ተደራሽነት (Urgency) ​"ሼር አድርጉ" የሚለው ጥሪ መልዕክቱ በፍጥነት ካልተሰራጨ፣ አንድ ወይም ሁለት አመራሮች ባለማወቅ ጥሪውን አንስተው ለአደጋ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ነው። በመሆኑም መረጃውን በየደረጃው ላሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ማድረስ አስፈላጊ ነው። ​በተጨማሪም ለጥንቃቄ ያህል፦ አመራሮች የዲጂታል ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስልካቸውን በየጊዜው "Airplane Mode" ላይ ማድረግ ወይም ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ሰዓት መዝጋት ይመከራል።