fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)

رفتن به کانال در Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

نمایش بیشتر
4 124
مشترکین
+224 ساعت
+4287 روز
+1 25730 روز
آرشیو پست ها
"የአቅጣጫ መሳት" ትርክት እና የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስትና ደጋፊዎቹ "ትግሉ አቅጣጫውን ስቷል" የሚል ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ በስፋት ሲያሰራጩ ይስተዋላል። ይህ ትርክት በተለይም በገንዘብና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ተደልለው እጃቸውን ለሰጡ ጥቂት የቀድሞ የፋኖ አባላት እንደ ስክሪፕት ተሰጥቷቸው በየመንግስት ሚዲያው እንዲደጋገም እየተደረገ ነው። ይሁን እንጂ ይህ "ትግሉ አቅጣጫ ስቷል" የሚለው የፌዘኝነት ንግግር፣ የአማራ ህዝብ ላለፉት ዓመታት ሲያሳልፍ የቆየውን መከራና የደረሰበትን የህልውና አደጋ ሆን ብሎ የሚዘነጋ ነው። መንግስት ትግሉ አቅጣጫ መሳቱን ከመናገሩ በፊት፣ የአማራ ህዝብ በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልልና በተለያዩ አካባቢዎች በማንነቱ ምክንያት በጅምላ ሲጨፈጨፍ ለምን ዝምታን መረጠ? የሚለው ጥያቄ የትግሉን መሰረት ያረጋግጣል። መንግስት በወለጋ፣ በቤኒሻንጉልና በሌሎችም ስፍራዎች ለተፈጸሙ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎች ተገቢውን ጥበቃ ሳያደርግና ለተጎዱትም ፍትህ ሳይሰጥ መቆየቱ፣ ህዝቡ በራሱ ክንድ ለመከላከል እንዲገደድ አድርጎታል። በመሆኑም ትግሉ "የአቅጣጫ መሳት" ሳይሆን፣ መንግስት ህዝቡን የመጠበቅ ሃላፊነቱን መወጣት ባለመቻሉ የመጣ የህልውና ግዴታ ነው። ከጦር ግንባር ውጪ ያለው መንግስታዊና መዋቅራዊ ጫናም የዚህ ተጋድሎ ሌላኛው ምክንያት ነው። በአዲስ አበባ ከተማ "የኮሪደር ልማት" በሚል ስም የሚከናወነው ሰፊ የማፈናቀል ስራ፣ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ምሁራንንና ጋዜጠኞችን ያለምንም ምክንያት ማሰር፣ እንዲሁም ወደ ዋና ከተማዋ እንዳይገቡ የሚደረገው መዋቅራዊ መገለል ህዝቡ በገዛ ሀገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንዲቆጠር ማድረጉ ግልጽ ነው። ይህ ስልታዊ ማገለልና ጥቃት ደግሞ ትግሉ ግልጽ የሆነ "የመኖር መብት" ጥያቄ እንጂ አቅጣጫ የሳተ አመጽ አለመሆኑን ያረጋግጣል። መንግስት በጥቂት "ተስፋ የቆረጡ" ግለሰቦች አማካኝነት ትግሉ እየፈረሰ እንደሆነ ለማሳየት ቢሞክርም፣ በቅርቡ በጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም (January 17, 2026) የታወጀው የፋኖ ሃይሎች ውህደት ሌላ እውነታን ይነግረናል። የጎጃም፣ የጎንደር፣ የወሎ እና የሸዋ ፋኖዎች በጋራ "የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ" (አፋብን) በሚል መደራጀታቸው፣ ትግሉ ካለበት የመከላከል ደረጃ ወደ ተደራጀ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ተቋም መሸጋገሩን ያሳያል። ይህ አንድነት ደግሞ በመንግስት በኩል የሚቀርበውን "የመበታተን" ወሬ ውድቅ የሚያደርግ ታሪካዊ ምላሽ ነው። ባጠቃላይ፣ የአማራ ህዝብ ተጋድሎ የመነጨው መንግስት በህዝብ ደም ላይ ካሳየው ዝምታና በመዋቅር ከዘረጋው መገለል ነው። ትግሉ አቅጣጫውን የሳተው ሳይሆን፣ ህዝቡ በገዛ ሀገሩ በክብር ለመኖርና ከጥፋት ለመዳን የያዘው ብቸኛ የህልውና መስመር ነው። መንግስት ለገደላቸውና ለተገደሉበት ህዝቦች ፍትህ መስጠትና መዋቅራዊ ጥቃቱን ማቆም ሲገባው፣ በትግሉ መሪዎች ላይ የሚያካሂደው የባህርይ ማጠልሸት ዘመቻ የህዝቡን ቁጭት ከማባባስ ውጪ የሚያመጣው ሰላም አይኖርም።

በጋምቤላ ክልል ከዋና ከተማዋ በስተቀር አብዛኻኛው የክልሉ አከባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የጋምቤላ ታጣቂ ኃይል ጥምረት በሀገራዊ ጉዳይ ከፋኖ ጋር አብሬ መስራት እፈልጋለሁ አለ! ታጣቂ ኃይሉ ባወጣው
በጋምቤላ ክልል ከዋና ከተማዋ በስተቀር አብዛኻኛው የክልሉ አከባቢዎችን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የጋምቤላ ታጣቂ ኃይል ጥምረት በሀገራዊ ጉዳይ ከፋኖ ጋር አብሬ መስራት እፈልጋለሁ አለ! ታጣቂ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ፡ ከሰሞኑ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ለሃገራዊ ፀረ ብልፅግና ኃይሎች ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ነው አብሮ መስራት እንደሚፈልግ የገለፀው። ፋኖ ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር የብልፅግና ቡድን ጭቆና የደረሰባቸው ብሔር ብሔረሰቦች ጭምር ተስፋ አድርገውታል። የፋኖን እንቅስቃሴ በተስፋና በጉጉት እየጠበቁት የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የምስራቅ አፍሪቃና የቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን የሚሹ ኃይሎች ሁሉ አይናቸውን ፋኖ ላይ ተክለዋል።

3ቱ የፍጥነት መንገዶች! በአለም ላይ አንባገነናዊ መንግስታትን ለማስወገድ የተደረጉና ታሪክ መዝግቧቸው ያለፉ የትጥቅ ትግሎችን ስንመለከት አንዳንዶቹ በጥቂት ቀናትና ሳምንታት አላማቸውን አሳክተው የተጠናቀቁ ፣ ወራቶችንና ጥቂት አመታትን ብቻ የፈጁ ብሎም ከአምስትና አስር አመታትም ተሻግረው ስልሳና ሰባ አመታትን ያስቆጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህን አጭር ፣ መካከለኛና ረዥም ጊዜ ብለን ልንጠቅሰው እንችላለን! እጅግ በጣም አጭር በሆነ ወይም በአጭር ጊዜ ስኬታማ የሆኑ አብዛኛዎቹን የትጥቅ ትግል ያካሄዱ ኃይሎችን ስንመለከት ፥፦👇 1. ውስጣዊ ወታደራዊ ጥምረትና ትብብርን የፈጠሩ ( የሚታገሉትን ስርአት ወታደራዊ ሀይል ጭምር ድጋፍና አጋርነት ያገኙ ) 2. የተሻለ ውጫዊ ድጋፍና አጋርነት ያላቸው 3. የትጥቅ ትግሉን ከህዝባዊ አመፅ (እምቢተኝነት) ጋር አቀናጅተው መምራት የቻሉ ሆነው እናገኛቸዋለን። በዋናነት እነዚህ ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች የትግልህን እርዝማኔ የመወሰን አቅም አላቸው! አንባገነናዊ መንግስታት የሚታገሏቸው ኃይሎች '' ስለትብብርና አንድነት'' ሲያወሩ በአንድ ጊዜ ላብ የሚዘፍቃቸውም ለዚህ ነው! ጠዋት ማታ '' የእከሌ ሀገር ተላላኪ ፣ የእከሊት ሀገር ተወካይ'' እያሉ የጠነዘለ ፕሮፓጋንዳ ከመስራት የማይቦዝኑትም ይህኑ ስለሚፈሩ ነው! ህዝቡ ታጣቂ ሀይሎችን እንዳይደግፍና የከተማ አመፅ እንዳይቀሰቀስ በመፍራት እንቅልፍ አጥተው ሲቃዡ የሚኖሩበት ጭብጥም ሌላ ነገር የለውም!

#የድል_ዜና‼️ አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሰምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር‼️ የአገዛዙ የብልጽግና ሰራዊት /እራሱን ጥምር ብሎ የሚጠራው የአብይ ምስለኔ  በኮረማሽ ንዑስ ወረዳ ሰላም ሰው ሻለቃ ላይ በምትንቀሳቀስበት አካባቢ ከበባ ለምፈፀም ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል። የእግዚአብሔር  አብ የንግስ ክብረ በዓልን አስመልክቶ በ13/05/18 የህዝብ ክብር በዓል በሚያከብሩበት የንግሥ ቦታ የዘወትር ክህደቱንና ሀገር በጥባጭነቱን ለመፈፀም ቢሞክርም በኃይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በሻለቃ 3(ሰላም ሰው) በተደረገበት ከፍተኛ ፊልሚያና ትንቅንቅ የንግሥ በዓሉን ፋኖዎች ማሥከበር ችለዋል። በዚህ አውደ ውጊያ አልሳካለት ሲል በ14/5/2018 በቀጥታ ከቱለፋ እና ከሀገረማሪያም ወረዳ  ያለ የሌለ የሚሊሻና የመከላከያ ምንጣፍ ጎታች ሀይሉን አግበስብሶ  ከንዑስ ወረዳ ከሆነው ከሰም ኮረማሽ በእምዬ ሚኒሊክ የጦር ግምጃ ቤት ካምፕ ያለውን ጦር ጭምር በማሰለፍ በ3 ግንባር ማለትም በወይን አምባ,  በሸረርና በሰወሥት አምባ የጦር ግንባሮች ወረራውን አድርጎ በሞርተር እና በድሽቃ የታገዘ ጦርነት ቢከፍትም አልሳካ ሲለው የዘውትር የዘረፋ ተግባሩንና መንገድ ላይ የተገኘ አርሶ አደር በመደብደብና በማሰር የማህበረሰብ ንብረት እንደ በርበሬ ፣ሽሮ፣ እንቁላል፣ ልብስ ፣ስልክ፣ጫማ፣ አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ በግድ አርሶ አደር አስገድደው 10,000  ሽህ ብር ዘርፈውና ይህን ግፍ ፈፅመው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት ተመልሷል። በሌላ ግንባር የኮረማሹን ውጊያ ለማስቀየስ ወደ ዛላ ዘባባ ከሀገረማሪያም ቀረውን የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት አሰልፎ ቢንቀሳቀስም በቀጣናው በነበሩ አባት አርበኞች አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ የተመለሰ ሲሆን:-በዚህም ውጊያ አንድ የሚሊሻ አባል የሆነውን ስሙ ጌታሁን ተረፈ የተባለውን ባንዳ እረምጃ ተወስዶበታል።   ኃልውናችን በተባበረ ክንዳችን💪💪💪 ©አፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር ኃይለማሪያም ማሞ ክ/ጦር ሪፖርተር ክፍል 15/ዐ5/2018 ዓ.ም

የወለጋ ፋኖን ማጥፋት አልቻልኩም :- ሽመልስ አብዲሳ‼ ኦህዴድ 4-ኪሎ እንደገባ በነጋታው ነበር የወለጋ አማራዎች የተጨፈ*ጨፉት። የአማራ ሴት ተማሪዎች በዚያው በወለጋ ታግተው ደብዛቸው ጠፋ‼ የአማራ
+1
የወለጋ ፋኖን ማጥፋት አልቻልኩም :- ሽመልስ አብዲሳ‼ ኦህዴድ 4-ኪሎ እንደገባ በነጋታው ነበር የወለጋ አማራዎች የተጨፈ*ጨፉት። የአማራ ሴት ተማሪዎች በዚያው በወለጋ ታግተው ደብዛቸው ጠፋ‼ የአማራ ህዝብም ባህርዳር ጨምሮ ሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች አትግደሉን የሚል ሰልፍ አደረገ። ከኦህዴድ የተሰጠው መልስ:- ሙሾ አውራጅ ፣ አልቃሻ የሚል ነበር። ከወለጋ ተፈናቅሎ በደብረብርሃን እና በደሴ ፣ በሐይቅ ከተማ በሸራ እየኖረ ይገኛል። ግማሹ ደግሞ በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነው ከምግብ ቤቶች ተመላሽ እየበሉ በስቃይ ይኖራሉ። አሁን ላይ የወለጋ አማራዎች ሞት በቃን ብለው ታጥቀው እራሳቸውን እየመከቱ ይገኛሉ። በዚህም ኦህዴድ ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል። ጉድጓዱን ስትቆፍር አታርቀው ማን እንደሚገባበት አይታወቅም ይላል አማራ ሲተርት። ዛሬ የሽመልስ አብዲሳ አስተዳደር የወለጋ ፋኖ ማጥፋት አልቻልኩም ፣ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖብኛል ብሏል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል 80% የሚሆነው በወለጋ ይገኛል። ባለፈው ህፃን አዛውንት ሳይል መጨፍጨፉ ይታወሳል። የኦህዴድ ሚዲያዎችም ጀግናው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በወለጋ ፋኖ ላይ የማያዳግም እርምጃ ወሰደ ሲሉ ዘግበው ነበር። ዛሬ ደግሞ ማጥፋት አልቻልኩም ብሏል። በደም የተገነባው የወለጋ ፋኖ አስገራሚ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አሁንም በተቀናጀ ሁኔታ በአንድ ዕዝ ተዋቅረው የአፋብን አካል ሁነው ይጠነክሩ ዘንድ መሰራት አለበት። ድል ለአማራ ፋኖ

የአገዛዙ ሰራዊት እየፈራረሰ ነው‼️ የንድነቱ መመስረት ተከትሎ ሚሊሻ እና የመከላከያ አባሎች ወደ ቀድሞ ማንነታቸው እየተመለሱ ነው ➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧ 1ኛ. ከድር አ
+5
የአገዛዙ ሰራዊት እየፈራረሰ ነው‼️ የንድነቱ መመስረት ተከትሎ ሚሊሻ እና የመከላከያ አባሎች ወደ ቀድሞ ማንነታቸው እየተመለሱ ነው ➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧➧ 1ኛ. ከድር አብዲ 2ኛ.ገመቹ ገመዳ 3ኛ. ሀይሉ ሙንየ እንግዳ 4ኛ. ምኒችል ቡችል ፀጋ ኮር 601ኛ ኮር 52ኛ ክፍለ ጦር እና 6ኛ ዕዝ 605 ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር 5ኛ.ጌታው መሌ ሸበል በረንታ ደንሲት መረዛምባ ሚሊሻ 6ኛ ታደሰ ደሴ ሸበል በረንታ ደንሲት መርዛምባ ቀበሌ ሚሊሻ ➧ ሁለት ክላሽ ➧ አንድ አብራርው ➧ ከ150 ተተኳሽ ጥይት ➧ 2 ካዘና የወገብ ትጥቅ ➧ 2 ኤፍ1 ቦንብ በመያዝ 64ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል። ➺➺➺የሚሊሻወች ፎቶ እንደደረሰን የምናጋራቹህ ይሆናል ጥር 15/2018 ዓ.ም አዲስትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የ14ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ጥቃት ፈጸመ! ጥር 14/2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ከየቀጋት ተነስቶ ወደ ጎፍጭማ እየተጓዘ በነበረው ግብስብስ የብልጽግና ሠራዊት ላይ ጥቃ
የ14ኛ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ ጥቃት ፈጸመ! ጥር 14/2018 ዓ.ም የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ከየቀጋት ተነስቶ ወደ ጎፍጭማ እየተጓዘ በነበረው ግብስብስ የብልጽግና ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈጽማለች። ማምሻውን ወደ ጎፍጭማ ቀበሌ እንቅስቃሴ ማድረጉን የሰሙ ነበልባሎቹ የፋኖ አባላት ቦታ በመያዝ በጠላት ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ቁጥር ያለው የወራሪውን ሠራዊትን ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል። ድል ለአማራ ፋኖ! የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል

ሁለት የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባላት ኮብልለው ፋኖን ተቀላቀሉ:: የአብይ አህመድ ስርዓትን የተቀዋወሙ ሁለት የመከላከያ አባላት ለአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጀ/አሳምነው ኮርሜ
+1
ሁለት የአገዛዙ መከላከያ ሰራዊት አባላት ኮብልለው ፋኖን ተቀላቀሉ:: የአብይ አህመድ ስርዓትን የተቀዋወሙ ሁለት የመከላከያ አባላት ለአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ  ላስታ ጀ/አሳምነው ኮርሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ክ/ጦር በመቄት እጃቸውን ሰጥተዋል። በክፍለ ጦሩ ህግ ክ/ኃላፊ አርበኛ አንደበት በየነ አቀባበል የተደረገላቸው የ65ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ የመከላከያ አባላት ለፋኖ እጅ መስጠታቸው እና በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው አብዛኛው ሰራዊት በስርዓቱ እኩይ ተግባር  እንደተማረረም ገልፀዋል። የመከላከያ አባላቱ በግድ ተጋፎ የገባው ሰራዊት እየፈረሰ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ለመቀላቀል እንደወሰነም ገልፀዋል። የሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ክ/ጦር አዛዥ ኮማንዶ አማን ጎበዜ አሁንም  በአፓርታይዱ ስርዓት ውስጥ ሆነው የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፉ ላሉ አካላት ከፋሽስቱ ወንበር አስጠባቂነት ወጥተው ወደ ትክክለኛው  የፋኖ ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ ጥር 14/2018 ዓ.ም

​ጨቅላው አብይ አህመድ በፋኖ አንድነት ምስረታና ጥንካሬ ተደናግጦ ያስተላለፋቸው ቀጥተኛና አስቸኳይ ትዕዛዞች 👇 ​ፅሁፎቹ ቃል በቃል አይደለም በአስቸኳይ በ Zangi ተደውሎ ከውስጥ መረጃ ሰጪ በፍ
​ጨቅላው አብይ አህመድ በፋኖ አንድነት ምስረታና ጥንካሬ ተደናግጦ ያስተላለፋቸው ቀጥተኛና አስቸኳይ ትዕዛዞች 👇 ​ፅሁፎቹ ቃል በቃል አይደለም በአስቸኳይ በ Zangi ተደውሎ ከውስጥ መረጃ ሰጪ በፍጥነት የተነገረኝ ስለሆነ ጭብጡን ብቻ እንዲወሰድልኝ እፈልጋለሁ። ​ትዕዛዞቹ እነሆ፦ ​በአስቸኳይ ራያና ወልቃይት ሙሉ ለሙሉ ለህወሓት ይሰጡ። ​የህወሓት ህጋዊ ሰውነት ተመልሶ በትግራይ ምርጫ እንዲካሄድ ይመቻች። ​አስፈላጊው በጀት ተመድቦ በፋኖዎች አንድነት ምስረታ ላይ የውሸት ምስረታ መሆኑን ለማሳመን ዘመቻ ይጀምር። ​ትግራይ በተቻለ መጠን እርስበርስ እንዲዋጉና የውስጥ ውጥረት እንዲፈጠር ከፍተኛ ስራ ይሰራል፤ እንዲሁም በአማራ ታጣቂዎች። ​በህወሓትና በፋኖ ጥምረት እንዳይፈጠር ስራዎች ይስሩ በተለይ በወልቃይትና ራያ አካባቢ ፋኖዎች በጎርፍ ላይ ሾልከው በመግባት ጥቃት ፈፀሙ እየተባለ ስራዎች በመስራት የሚያጋጭን እንዲያገኙ ይደረግ። ​ፋኖ የህወሓትና የሻቢያ ጉዳይ አስፈጻሚ ነው በማለት ስሙን በማጥፋት ከአማራ ህዝብ ለመነጠል ይሰራ። ​የባህር በር ከኤርትራ ለማግኘት እየሰራን እንደሆነና ፋኖና ህወሓት እንቅፋት በመሆን የአገር ጠላት መሆናቸውን በተደጋጋሚ በሚዲያ ይሰራል የሚልና የመሳሰሉ አጀንዳዎች በስፋት ከነበሩት የሚዲያ ስራዎች ይሰራል ተጨማሪ የሚዲያ ስራዎች ይቀጠር የሚል ትዕዛዝ ዛሬ ለኮሚኒኬሽን ቢሮ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ​በተጨማሪም የመከላከያ የክብር አባላት ተብለው የሸለምናቸው ስራ እንዲጀምሩና የመከላከያ ገፅ ግንባታ እንዲሰሩ ይደረግ ተብሎ ለጌትነት መልዕክት ተላልፎለታል።

ኢትዮጵያም ከመፈራረስ የምትድነው ፣የአማራ ህዝብ ህልውና እውን የሚሆነው በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ድርጅታችን ነው!! የአማራ ህዝብ ትግል ዋና ምክንያቶች;--- ፩ የአማራ ህዝብ ህልውና፣ ፪ የአማራ ህዝብ መፈናቀል፣ ፫ የአማራ ህዝብ ሃብት መዘረፍ ፣ ፬ የአማራ ህዝብ የዜግነት መብት መነፈግ፣ ፭ የአማራ ህዝብ የዲሞክራሲያዊ መብቱን መቀማቱ ፣ ፮ የአማራ ህዝብ የፓለቲካ ተሳትፎ መከልከል፣ ፯ የአማራ ህዝብ ርስትን እና ማንነትን መነጠቅ፣ ፰ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ዉስጥ የመኖር መብቱ አደጋላይ ስለሆ የመኖር መብቱን ማስከበር ስላለበት። ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ነጥቦች የስልታዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፍሬ ነገሮች ናቸው።እነዚህ መስፈርቶች አሟልቶ የአማራን ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አብይ አህመድና እና ግብረአበሮቹ በምድርም በሀገር መከላከያ የዳቦ ስም የጀ/ል ብርሃኑ ጁላ ጦር ሲሆን በሰማይም ደግም በጀነራል ይልማ መርጋሳ ትዕዛዝ ሰጭነት በድሮን እና በተዋጊ ጀቶች ፣ ታንኩንም በነጀነራል ሙሀመደ ተሰማ ሰምሪቶ ሰጭነት ፣ባንኩንም በአብይ አህመድ ትዕዛዝ ሰጭነት ይፋዊ ጦረነት ከአውጀው 30 ወራትን አስቆጠረ።የአማራ ህዝብ የአብራክል ልጅ የሆነው ፋኖም ላለመጥፋት የትግል መነሻውን ከሰፈር በሰባሰብ በመደራጀት ጠላት የከፈተውን ጦርነት ሲመክት ቆይቶ አሁን ከአካባዊ አደረጃጀት ወጦ ህዝብን ሊታደግ የሚችል አደረጃጀት በመፍጠር አንድ የጋራ ቤት ሰርቶ ገንብቶ የጋራ መጠለያ ቤት የሆነውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መሥርቷል።መሪውም ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ መርጧል። ብ/ጀ/አሳምነው ፅጌ ቃልህን አክብረን አማራን አንድ አድርገን አንድ ድርጅት አንድ መሪ እንዲኖረው አድርገናል።ሁላችንም በአለን ኃላፊነት ልክ እና እንደግልም የተሰጠንን የአደራ ቃል አክብረን የድርሻችን ተወጠናል።ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ህዝብ ጋር በጋራ በመተባበር ፣በመቀናጀት የአማራን ህዝብ ስልታዊ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ ያለውን የኦሮሙማ ሰራዓት ለማስወገድ ሁሉም ብሔር ብሐረሰብ በአፋብን የሚመራውን ትግል ነገ በእኔ በሚል በሂል ሁሉም ይህን ድርጀት በመደገፍና በመቀላቀል የህዝባችን ህልውና እንታደግ እንዲሁም ኢትዮጵያ ሀገራችንም ከመፈራረስ ለመታደግ ከኦሮሙማ ሰራዓት እናላቃት። ኢትዮጵያም ከመፈራረስ የምትድነው ፣የአማራ ህዝብ ህልውና እውን የሚሆነው በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ድርጅታችን ነው። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አንድ አማራ! እስከምፃት አማራ!! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!!

በውስጡ 9 ማህበራትን የያዘው የአማራ ማሕበራት ትብብር ተቋም በአፋብን ምስረታ መደሰቱን እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
+1
በውስጡ 9 ማህበራትን የያዘው የአማራ ማሕበራት ትብብር ተቋም በአፋብን ምስረታ መደሰቱን እና አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

10ሩ ኮማቾች ምን አሉ?😂 '' በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ Faኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መካከል እንደ #አዲስ የሰላም ስምምነት ተካሄደ። የሰላም ስምምነቱን በአዲስ ማካሄድ ያስፈለገው በመጀመሪያው ስምምነት ያልተካተቱ ጉዳዮች በመኖራቸው ነው!'' ከሚለው ዘገባ ስር ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል፦👇 ✅'' ባለፈው የተፈራረማችሁት ከቦኮሀራም ጋር ነበር እንዴ?'' ✅'' የአሁኑን ድራማችሁን ተመልካች የሚያሳጣው አፋህድ የሚባል ድርጅት በሌለበት የተደረገ በመሆኑ ነው!'' ✅'' ያው በፈሳ*ችሁም እንደማትዋጉ ስለማውቅ ፥ ከባለፈው ስምምነት ላይ ' ከክልሉ መንግስት ጋር ሁነን እንዋጋለን' የሚለውን አንቀፅ ያወጣሁት እኔ ነኝኮ!'' ✅'' ቁርስ ፣ ምሳ ፣ ራት ከሚለው ፖኬጅ ውጪ መክሰስ ለማስጨመር አዲስ ስምምነት መፈራረም ግን ፌር አይደለም!'' ✅'' ከየመንገዱ የለቃቀሟቸውን ወጣቶች በእናንተ ስም እየነዳችሁ ወደእሳት ለመማገድ ተስማምታችሁ የተፈራረማችሁት የስምምነት አንቀፅ ግን ፍፁም አረመኔነት ነው!'' ✅'' በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው የኮሪደር ልማቱን ቢያንስ 1000 ጊዜ ይጎበኛሉ የሚለው አንቀፅ የተካተተው ፣ በፈረስና በበቅሎ ስናጓጉዘው የነበረውን ኮሎኔል ፈንታው በመንገድ ወዝውዞ ድፍት ለማድረግ የታቀደ ነው!'' ✅'' ከሁሉ ከሁሉ የቆጨኝ ኮሎኔል ፈንታው በቁሙ መሞቱ ካልቀረ የጃል ሰኚን ያህል እንኳ ሰራዊት ሳይዝ ከአራት ወታደሮች ጋር እግሬ አውጪኝ ማለቱ ነው!'' ✅'' በስምምነቱ ላይ የጠጅም ሆነ የውስኪ ስም አለመጠቀሱ ለማስረሻ ሰጤ የተደገሰለትን ክፉ ድግስ አመላካች ነው!'' ✅'' እኛ የድራማ ተመልካቾቻችሁን እንዳታሰለቹን በየሚዲያው faኖን ለመፈረጅ ህወሓትና ሻዕቢያን ብቻ አትጠቀሙ። ቦኮሀራም ፣ አልሸባብ ፥ አይኤስ ፣ ታሊባን ፥ ...ወዘተን እያቀላቀላችሁ ተጠቀሙ!'' ✅'' ማስረሻ በስምምነቱ ሰሞኑን መከላከያ የገደ*ለው ወንድሙን የደም ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል የሚባለው እውነት ከሆነ 8ተኛው ሺ ከነገ ወዲያ ነው ማለት ነው!'' የቱ ኮማች ተመቻችሁ? የእናንተንም አስቂኝና ዘና የሚያደርጉ አስተያየቶች እስኪ አጋሩኝ!

የማታውቋቸው ካላችሁ ተዋወቋቸው "የአሳምነው ፅጌ አደራ አስቀጣዮች ናቸው"ከምሽግ ምሽግ እንደ አቦሸማኔ እየተወረወሩ ጠላትን አፈርከድሜ ያስበሉታል! እነሱ የተዋጣላቸው አለም የመሰከረላቸው ጦረኞች ናቸ
+3
የማታውቋቸው ካላችሁ ተዋወቋቸው "የአሳምነው ፅጌ አደራ አስቀጣዮች ናቸው"ከምሽግ ምሽግ እንደ አቦሸማኔ እየተወረወሩ ጠላትን አፈርከድሜ ያስበሉታል! እነሱ የተዋጣላቸው አለም የመሰከረላቸው ጦረኞች ናቸው ።ለወዳጆቻቸው ወዳጅ ናቸው! ለጠላታቸው ደግሞ እንደ አራስ ነብር ይሶረፋሉ እነሱ ሲስቁ እንጅ ሲቆጡ ቀና ብሎ ለማየት ያስፈራሉ ። ጅንን ቅብርር ያሉ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። ከቤተ አምሐራ ሰማይ ስር !

ስደተኛ የነበረውን የአማራ ትግል ጥርት ባለ የአማራ ብሔርተኝነት ፣ በራሳችን የትግል መልከኣምድር ፣ በራሳችን የተፈጥሮ ሐብት ፣ በራሳችን ህዝብ መትከል ስንጀምር መነቀል አለበት በማለት ባለፉት በር
+1
ስደተኛ የነበረውን የአማራ ትግል ጥርት ባለ የአማራ ብሔርተኝነት ፣ በራሳችን የትግል መልከኣምድር ፣ በራሳችን የተፈጥሮ ሐብት ፣ በራሳችን ህዝብ መትከል ስንጀምር መነቀል አለበት በማለት ባለፉት በርካታ ወራት እንደነዚህ ሰዎች የተፈታተነን አልነበረም ። ትውልዱ የጠንካራ አስተውሎት እና የውሳኔ ባለቤት በመሆኑ ከትግሉ ሜዳ ሲያባርራቸው የአብይ አህመድ የበየ አይነት ካምፕ ውስጥ ገብተው ግዙፉን የአማራ አብዮት ለማጥላላት ሲጋጋጡ እያየናቸው ነው ። ትግላችን ራስ በቅ ነው ! ትግላችን አብይን ከመጣል ባሻገር ነው ! ትግላችን የአማራን ህዝብ የልዕልና ከፍታ የተሸከመ ነው !

የብልፅግና አማራ ጠሉ አረመኔያዊ ስርዓት የፊስቡክ አካውንት ስለተዘጋ 2k እናስገባው ቻሌንጁን ተቀላቀሉ https://www.facebook.com/share/p/1BxouFFSAm/

የሀይማኖት ክሀድያን ሀይማኖቱ እንዳይቀጥል አያደርጉትም‼️ የሀይማኖት ክሀድያን የነበሩበትን የሀይማኖት ተቋም ከህደው በመውጣት የወጡበትን ሀይማኖት ተቋም ስም በመጥራት ፣የተቀደሠውን ቃልና ቦታ ማንቆሸሽና ማራከስ እንደክብርና እንደጽድቅ ይቆጡሩታል። ክሀድያኑ የወጡበትን ሀይማኖት እንዳይመለክ፣እንዲጠፋ አላደረጉትም፣ ሁሉም የሀይማኖቱ ተከታዮች ተሠልፈው እነሡ ወደገቡበት ሀይማኖት እንዲገቡም አላደረጉትም፣ይልቁንም የሀይማኖት ተከታዮች እንዲበረቱና ሀይማኖታቸውም ደግሞ የበለጠ እንዲጠነክር ያደርጉታል። የፋኖን ተቋም ክደው የሚወጡ ክሀዲ ባንዳዎችም ፣ቁልጭ ያለ መነሻና መዳረሻ ያለውን የአማራን የህልውና ትግል ክደው በመውጣት፣ውድ የአማራ ልጆች የረገፉበትን የህልውና ተጋድሎ ቆሻሻ ስም በመቀባትና በማራከስ አንድ ጋት ወደኋላ አይመልሱትም። ይልቁንም የበለጠ እንዲጠነክርና እንዲበረታ ያደርጉታል እንጂ። ፋኖነት አሸናፊነት ነው።ፋኖነት የተበርካኪነትና እጂን ዘርግቶ መሳሪያ ለጠላቶቹ የሚሠጥ ሳይሆን የመጨረሻዋን አንድ ጥይት ወደራሱ የሚተኩስ የጀግንነትና የአርበኝነት ጥግ ነው። ክብር ለአማራነታቸው ሲሉ ስቀው ለተሠው ሰማዕታት‼️

ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር መርሳ ከተማ አቅራቢያ የአገዛዙ ሰራዊት ላይ የአር ፒ ጂ ጥቃት በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚሊኒክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለ ሽርጡ ክፍለ ጦር በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት አደረሰ። ዛሬ ጥር 14/2018 ዓ.ም ከጧቱ 12:00 ላይ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ አቅራቢያ ሊብሶ ኤላ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ላይ የስርዓቱን ወንበር ጠባቂ ሰራዊት በአንድ ተሳቢ፣አንድ ሲኖትራክ እና አንድ ፖትሮ ከመርሳ ወደ ደሴ ሲጓጓዝ በባለሽርጡ ክፍለጦር ቃኝ በተያዘ ደፈጣ ሙሉ ለሙሉ በመደምሰስና በማውደም ታላቅ ድል ተጎናፀፈዋል። በዚህ 100% ኢላማውን በጠበቀ የአርፒጅ /RPG/ ጥቃት ከመርሳ ወደ ደሴ በአንድ ተሳቢ ፣በሲኖ ትራክ እና በአንድ ፖትሮል ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ጨፍጫፊ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከነ ተሽከርካሪው ማውደምና መደምሰስ ሲቻል፣ ስርዐቱ ሙትና ቁስለኛውን በአስር አንቡላንስ ወደ መርሳ ሆስፒታል ሲያመላልስ አርፍዷል። በዚህ አውደ ውጊያ ከተደመሰሱት የስርዓቱ ሀይሎች መካከል ለጊዜዉ ስማቸዉ ያልታወቀ ከፍተኛ አመራሮችም ይገኙበታል። በፋኖ ምት የተበሳጨዉ የጠላት ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃን ወገኖቻችን ኢላማ በማድረግ የአርሶ አደሮችን ህይወት ሲቀጥፍና በመንገድ እያስቆመ በመደብደብና ንብረትም ሲያወድም ውሏል። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ  አማራ ቀጠና ሚሊኒክ  ዕዝ ጥር 14/2018 ዓ.ም

#የጠላት_እንቅስቃሴ‼️   ብዛት ያለው የአድማ ብተና እና መከላከያ ጥምር ኃይል ከቀኑ 7:00 አካባቢ ከባህርዳር ከተማ ወደ ጎንደር መውጫ በር እየተጓዘ ነው መረጃው ለወገን ሀይል ይድረስ‼️ 14/ዐ5/2018 ዓ.ም

ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media) - آمار و تحلیل کانال تلگرام @mezmure122124