ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 132
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+4577 روز
+1 19430 روز
آرشیو پست ها
የምኒልክ ዕዝ 2ኛ ዙር የፓለቲካ መኮነን ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ::
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ "ፀሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ" የፓለቲካ መኮነኖች ማሰልጠኛ ማዕከል በምዕራብ ወሎ ግንባር ሰሞኑን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
ይህን አስመልክቶ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ቃለአብ ወርቅዬ መልዕክት አስተላልፏል::
በቅድሚያ ውድ የዛሬ ተመራቂዎች እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን::
ከምረቃው በተጨማሪ በምዕራብ ወሎ ግንባር ስምንት ወረዳዎችን ያካለለ የማጥቃት ቅንጅታዊ ዘመቻን ተከትሎ በኮራችን ሰራዊት በተፈፀመው የጦር ሜዳ ጀብዱ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፦ ለክርስትና እምነት ተከታይ አርበኞች እና ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ የመልካም የገና በዓል ምኞቴን የምገልፅላችሁ "የእዳ ደብዳቤያችን ይቀደዳል፣ አማራ ዳግም ይወለዳል!" በማለት የዕዛችን የፖለቲካ መምሪያ ያሰራጨውን የበዓል መልዕክት አርዕስት በማስታወስ ጭምር ነው::
የዕዛችን የፓለቲካ መምሪያ በመልዕክቱ የድርጅታችን እና በተዋረድ ያለዉ መላው የፖለቲካ አመራሩ ወታደራዊ ኃይሉ ያገኘውን ድል በፖለቲካውም መድገም ግድ ነው። ስለሆነም እንደ ትናንቱ ሁሉ ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ህዝብን ማደራጀትና ንቅናቄ መፍጠር፣ አዲስ ኃይል መመልመል፣ የህዝብ ተቋማትን በመጠበቅ፣ የሲቪል አደረጃጀት ማዋቀር እና ሌሎች ፖለቲካዊ ተግባራት አበክራችሁ እንዲትሰሩ በጥብቅ እናሳስባለን ማለቱ ይታወሳል:: ይህን የአደራ መልዕክት እና የዕዛችንን የፓለቲካ መምሪያ ትዕዛዝ በማክበር ተቆጥረው የተሰጡ ስራዎችን በእውቀት እና በእውነት መስራት የሚችል ብቁ እና ንቁ ኃይል ለማፍራት በማሰብ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ እንደነበር ልብ ይሏል::
በዚህም መሰረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የፓለቲካ መምሪያ ከዕዙ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ጋር በመተባበር ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር 5 ክፍለ ጦሮች ለተውጣጡ አርበኞች የፓለቲካ መኮነንነት ስልጠና ሲሰጥ መሰንበቱ ይታወቃል:: ብቃት ያላቸውና የመውጫ ፈተናውን ከግማሽ በላይ ውጤት በማምጣት ማለፍ የቻሉት ሰልጣኞች በትናንትናው እለት ለምረቃ ዝግጁ ሆነው ቀርበው ሊመረቁ ችለዋል::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ የመደባቸው ባለሙያዎች ስልጠናውን ሰጥተዋል::
ስልጠናው ፓለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ወታደራዊ መልክ የነበረው ሲሆን ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጭምር ለሰልጣኞች ልምዳቸውን አካፍለዋል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ኮማንዶ ዮሴፍ አስማረ እና ምክትሉ ኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይ በአካል ተገኝተው ለፓለቲካ መኮንኖች የወታደራዊ ስልት ስልጠና ሰጥተዋል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ባለሙያ እና አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞው አማራ ልዩ ኃይል የአባይ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር ሻለቃ ክንዱ ሰውነት እንድሁም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሜካናይዝድ ሞርተር አሰልጣኝ መቶ አለቃ ታደሰ አስፋው ለፓለቲካ መኮንኖች ወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና ሰጥተዋል:: ሰልጣኞች በፓለቲካው ብቻ ሳይሆን በወታደራዊው ዘርፍ ብቁ እንድሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል::
የጀመርነው የህልውና ትግል በትጥቅ የታገዘ የፓለቲካ ትግል እንደመሆኑ መጠን ፓለቲካው ጠብመንጃውን ማዘዝ እንዳለበት፣ እያንዳንዱ የምንተኩሰው ጥይት የፓለቲካ ውጤት ስሌት ውስጥ መግባት እንዳለበት፣ ጦርነቱ በፋኖ በኩል ፍትሐዊ ጦርነት ሊባል የሚችል ስለሆነ የፍትሐዊ ጦርነት መለኪያዎችን በሙሉ ከግምት ባስገባ መልኩ ትግሉ እንድቀጥል ማድረግ እንደሚገባ፣ ፋኖ የአማራ ህዝብ ተስፋ እና የደህንነት ዋስትና ሆኖ እንድቀጥል ሁሌም የህዝብን ፍላጎትና ክብር መጠበቅ እንደሚገባ፣ ትግሉ በእውቀት፣ እውነት እና በጠንካራ አመክንዮ መመራት እንዳለበት፣ ለፋኖ የሚያስፈልግ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አሰባሰብ ሂደት መቀየር እንዳለበት እንድሁም ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንድሰፍን፣ የአማራ ህዝብ ራሱን በራሱ እንድያስተዳድር፣ ፋኖ በሲቪል አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ጣልቃ የማይገባበትና ህዝባችን ለአካባቢያዊ ችግር አካቢያዊ መፍትሔ የሚሰጥበት የፓለቲካ ምሕዳር እንዲፈጠር ወዘተ አይነት የትግሉ መፍትሔ የተባሉ ሀሳቦችን በተግባር መተርጎም ይችሉ ዘንድ የንድፈ ሀሳብ እና ፅንሰ ሀሳብ ስልጠና የተሰጣቸው የፓለቲካ መኮንኖች ከምረቃቸው ዕለት ቀደም ባሉት ተከታታይ 2 ሳምንታት ከ20 በላይ ህዝባዊ መድረኮችን እንድመሩ ተደርጓል።
ሰልጣኞች ፓለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የመንግስት ኃላፊነት ከምን እስከ ምን እንደሆነ ጭምር ተረድተው ትግሉን በእውቀት ለማስኬድ የሚችሉበት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ሰልጣኞች የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን የሰራ እና ሉዓላዊነቷን ያስከበረ ባንዲራዋንም ያላስደፈረ ህዝብ መሆኑን በአግባቡ ይገነዘቡ ዘንድ የሚያስችል ትምህርት የተሰጣቸው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ስለ ማህበረሰብ እና መንግስት ግንኙነት፣ ስለ ዜጎች መብት እና ነፃነት ስለ አማራ ብሔርተኝነት ውልደት እና እድገት፣ እድሎች እና ተግዳሮቶች፣ ስለ አማራነት እና ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ ፀረ አማራ ትርክት፣ ስለ አማራ ዘር ፍጅት እና የህልውና ትግል፣ ስለ ፋኖነት ከትናንት እስከ ዛሬ፣ ስለ አማራ ፋኖ ትግል ስረ ምክንያት፣በትግሉ ሂደት ማለትም ከ2015-2018 ዓ.ም ስለተስተዋሉ ችግሮች መነሻ እና ውጤት እንድሁም የማስተካከያ እርምጃዎችን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል::
የእምዬ ምኒልክን የአመራር ጥበብ በማስታወስ በምኒልክ መንገድ ሀገር የማትረፍ እና የመስራት እንድሁም አማራን ከፈጽሞ ጥፋት የማዳን ኃላፊነት የተጣለባቸው የዛሬ ተመራቂዎች ከፀሀፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የፓለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል ያገኙትን እውቀት ወደ መሬት አውርደው ችግር ፈቺ እንድሆኑና ፋኖን ከህዝብ ጋር ማቀራረብ እንድችሉ ይጠበቃል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
ልክ በዚህ ስዓት 8:20
በደብረ ማርቆስ ከተማ የደፈጠው የአረመኔው ሰራዊት አገልጋይ የሆነው ታዘብ ምን ይዋብ የተባለ ፖሊስ በራሱ ጓደኛ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል ቢገባም ህይወቱ አልፎ በሆስፒታሉ የአስክሬን ማውጫ በር በኩል በኬንዳ ተጠቅልሎ በፖሊሶች ታጅቦ እየወጣ ነው።
ሌላኛው የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው ሲሳይ ገነነ ደግሞ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ከመጠን በላይ በመጠጣት ተማሪዎችን እያመሳቸው መሆኑን አረጋግጠናል።
@ Baye Desta per
ሰበር የድል ዜና
🔶 ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር የቡድን መሳሪያዎችንና የመገናኛ ሬድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላትን ኃይል መማረኩ ታወቀ።
ዛሬ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች በምስራቅ በለሳዊቷ ጣይመን ከተማ ሰፍሮ የሚገኘውን የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በ3 አቅጣጫ ወደ ካምፑ ዘልቆ በመግባት ሲያበራዩት አርፍደዋል።
በጨበጣ ዉጊያ የጠላትን 2 ምሽጎች በመደረማመስ የአብይን ግብስብስ ኃይል እያራወጡ ሻምበል መሪዎችን በመደምሰስ ቁሪዎቹን አባላት ሙት ቁስለኛና በመጨረሻም ምርኮኛ አድርገዋቸዋል ።
🔶 በዚህ አውደ ዉጊያ ላይ የኮሩ ተወርዋሪ ኃይል ፣ አፄ እያሱ ክ/ጦር ፣ ዞዝ አምባ ክ/ጦርና የንስር በለሳ ክ/ጦር የተወሰኑ አካላት እንዲሁም የኮሩ የስራ አስፈፃሚ አካላት በውጊያው በመሳተፍ ጠላትን አንገት ያስደፋ ድል እንዲመዘገብና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የቆረጣ ውጊያ ስልትን በመጠቀም የጠላትን ኃይል አንገት አስደፍቶ እንዲማረክ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ።
🔶 በውጊያው ከተገኙ ድሎች መካከል
** 1000 የብሬን ተተኳሽ ተማርኳል
** 2000 የክላሽኮኘ ተተኳሽ ተማርኳል
** 100 የእጅ ቦንብ /f1 ማለት ነው /ተሟርኳል
** 2 የመገናኛ ሬድዮ
** 3 ብሬን /መትረየስ /
** ከ55 በላይ ክላሽኮኘ ጠመንጃዎች ተማርኳል።
ከወታደራዊ ቁሳቁሶች መካከል ገቢ የተደረጉ ሲሆን በሰው ኃይልም ከደረሰበት ኪሳራ መካከል
** 25 መከላከያ እስከ ሙሉ ትጥቁ ተማርኳል።
** 37 በላይ መከላከያ እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል
** 35ቱ ደግሞ ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን በዚህ ምክንያትም የጓህላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና አርባያ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁም ታውቋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
ጥር 01 /2018 ዓ.ም
የገና በአል በመጫወትላይ በነበሩ 5 ህፃት በሚኒሻ ተተኩሶባቸው ቁስለኛ ሆነዋል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል እየፈፀመ ይገኛል ንፁሃንን ህፃናትን ሳይቀር እየቀጠፉ ነው የበዓል ጨዎታቸውን ተጫውተው መግባት አልቻሉም በዚህ ቀን ልጆቹ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ጨዋታዎችን የሚያደርጉበት ልዩ ስጦታ ቀን ነች።
የአማራ ባህል እንዲታይ አገዛዙ ፍፁም አይፈልግም በተግባርም ሰዴ ወረዳ ላይ በገና በዓል በአገዛዙ ትዕዛዝ ኃይማኖታዊና ባህላዊ የህፃናት ጨዋታ ስርዓት ላይ የተኩስ ሩምታ በመክፈት ህፃናት ቀስለኛ ሆናዋል።
ከአገዛዙ ትዕዛዝ ተቀበለው በህፃናት ላይ በጥይት የአካል ጉዳትና በህዝባችን ዘንድ የሞራል ስብራት አድርሷል ከ12 ዓመት በታች ባሉ ህፃናት ላይ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።
ሰዴ ላይ በሚሊሻ ተተኩሶባቸው የቆሰሉ ህፃናት ስም ዝርዝር ፦
1ኛ አታላይ ተሾመ =11ዓመት
2ኛ ኤርሚያስ ይርጋ=12ዓመት
3ኛ በቃሉ ሞላ=10ዓመት
4ኛ ይኸነው ስማቸው=9ዓመት
5ኛ ይረፉ አስናቀ=12ዓመት ሲሆኑ
ቀጥታ ከአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ትዕዛዝ ትዕዛዝ ተቀብሎ ህፃናትን ያቆሰሉ የሚኒሻ ስም ዝርዝር ፦
1ኛ በላይነህ 2ኛ ይገርማል 3ኛ ድረስ ግዛ 4ኛ ፈጠነ አድማስ 5ኛ ታረቀኝ አበባው የሚባሉ ናቸው። ከህዝባችን የሚሰወር አንዳችም ነገር የለም ሁሉም ዋጋቸውን የሚያገኙ ይሆናል።
አዲሱ ትውልድ፣በአዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም
በአገዛዙ በድሮንና በመድፍ የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችንና የሁለት ዕዝ ሰራዊትን ከሚኒሻና አድማ ብተና አባላት ጋር አጣምሮ አስልፎ የተዋጋበትና፡ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" የተባለበትን ሽንፈት የተከናነበበት አውደ ውጊያ!
ከላላ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የምዕራብ ወረዳዎች ላይ ታህሳስ 28/2018 ዓ/ ም ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት ከባድ ውጊያ መደረጉን በእለቱ መረብ ሚዲያ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገፆቹ መዘገቡ ይታወቃል።
በውጊያው፡ አገዛዙ ከድሮን ጀምሮ በመድፍና በቢኤም እንዲሁም በሞርተርና በዙ23 የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችን እና ከሁለት ዕዝ የተወጣጣ ሰራዊትን አሰልፎ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን "ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ" የተባለው አባባል ደርሶበት በጥቂት የፋኖ አሃዶች የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋምም ባለመቻሉ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራን ተከናቧል።
ውጊያው የተካሄደው በጃማ፣ በከላላ፣ በልጓማ፣ በደብረዘይት፣ በለገሂዳ፣ ገነቴ፣ በመኃል ሳይንት ደንሳ ከተማ፣ በተንታ አጅባር፣ በመቅደላ ማሻ፣ በጉጉፍቱ፣ ካቤ እና በሰኞ ገበያ ላይ ነው።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሶስት ኮሮች ማለትም ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ከልጅ እያሱ ኮር እና ከደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ ከሆነችው ከበላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች እና ከአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥምረት በመፍጠር ነው በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ጥቃት የከፈቱት።
በአገዛዙ በኩል በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ የ105ኛ እና የ107ኛ ክ/ጦር ኮማንዶዎችን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ801ኛ ኮር ሰራዊትና የ11ኛ ዕዝ ወታደሮች እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን "መከታዎቼ" ሲል የሚመካባቸው <ፓራ ኮማንዶ> የሚል መጠሪያ ያላቸው የሚኒሻ አባላትና የአድማ ብተና አባላት በወረዳ ካድሬዎች መንገድ መሪነት የድሮንና የመድፍ፣ የዙ23ና የሞርተር እንዲሁም የቢኤም ሽፋን እየሰጠ ያሰለፈ ቢሆንም፡ ነገር ግን "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ነውና ነገሩ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ ሽንፈትን ተከናንቦ ውሏል።
በውጊያው አራት ብሬን፣ አንድ ስናይፐር እና 170 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ ሁለት ወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪዎች ከነጫኑት ሬሽንና ተተኳሽ እና 146 ወታደሮችና በርካታ ወታደራዊ መገንኛ ራዲዮኖች በፋኖ መማረካቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በተጨማሪም የጠላት ብልፅግና ቡድን ከላላ ወረዳ ውስጥ ለገና በዓል ለእርድ አዘጋጅቷቸው የነበሩ አራት ሰንጋ በሬዎችና በርካታ ኩንታል የምግብ እህል በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
በዚህ ውጊያ ከተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሚኒሻ እንዲሁም የአድማ ብተና አባላት በተጨማሪ መንገድ ሲመሩ የነበሩ በርካታ የወረዳ አመራሮችም ተገድለዋል፡ከፊሎቹም በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል።
መከላከያን መንገድ ሲመሩ ተገኝተው ከተገደሉ የወረዳ አመራሮች መካከል የከላላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ሃላፊ አቶ አሚኑ አህመድ፣ የወረዳው ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊ አህመድ የሱፍ፣ እንዲሁም የወረዳው ሚልሻ ፅ/ቤት የሰላም አስከባሪ ሂደት ኃላፊ ሳጅን አልዩ አህመድ አብዲን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል።
ይሄንን ተከትሎ የከላላ ወረዳ አስተዳደር ከታህሳስ 28/2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ እስከ ትናንት ታህሳስ 30/2018 ዓ/ም ለአምስተኛ ጊዜ የሐዘን መግለጫ ማውጣቱን መረብ ሚዲያ ከወረዳው ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክቷል።
ወረዳው በመግለጫው፡ ከአመራሮቼ መካከል አንዳንዶቹ በተኙበት ነው የተገደሉት ያለ ሲሆን፡ ሌሎቹ ደግሞ በውጊያ መኃል የተገደሉብኝ ናቸው ማለቱን ነው መረብ ሚዲያ የተመለከተው።
(ምስል፦ በእለቱ በፋኖ ከተማረኩ የጦር መሣሪያዎች መካከል ጥቂቱ)
መረብ ሚዲያ
+1
የነፃነት ጽዋ በመከራ እሳት ትቀጠቅጣለች፤ ድል የጽኑዓን ናት!
በታሪክ ማኅደር ውስጥ የሰው ልጅ ሕልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ፣ ሁለት ዓይነት ሰዎች ይፈጠራሉ። የመጀመሪያዎቹ የግፉን ክብደት አይተው ተስፋ የሚቆርጡና ለአገዛዙ የሚያሸረግዱ ናቸው። ሁለተኛዎቹ ደግሞ "ከባርነት ይልቅ ሞት፣ ከመሸነፍ ይልቅ ተጋድሎ" ብለው የነፃነትን ችቦ የሚያበሩ የሕልውና ታጋዮች ናቸው።
ዛሬ፤ ውድ ዋጋ እየከፈላችሁ የምትገኙ የነፃነት አርበኞች ሆይ፤ ትግል እንደ ወንዝ ነው፤ ድንጋይ ቢገጥመውም ፈልፍሎ ማለፉ አይቀሬ ነው። ጠላት የሚደሰተው እኛ ስንከፋፈል ነውና የጋራ ህልውናችሁ ከቡድንና ከግል ፍላጎት በላይ መሆኑን ማውቅ አለብን። ስለሆነም፤ እንደ አየርላንድ አርበኞች መረጃን መቆጣጠር፣ እንደ ኢትዮጵያ አርበኞች መሬትን ማውቅ ይገባናል፤ ጀግንነት ያለ ብልሃት ግማሽ መንገድ ነው።
አዲስ ትዉልድ ፤አዲስ አስተሳሰብ ፤ አዲስ ተስፋ❗️
ኤልያስ በላቸው (የ109ኛ ኮር ከፍተኛ አመራር)
+1
5 የዘራፊው ብልጽግና አገልጋይ የነበሩ የሚሊሻና አድማ ብተና አባላት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ።
ጥር 01/2018 ዓ.ም
ሕልሙ ሁሉ እንደ ጉም ሆኖ ያመነው ሁሉ የሚከዳው የሌቦች መደራጃ የሆነው ኦሕዴድ መሩ የብልጽግና ሥርዓት በሕዝባችን ላይ እኩይ ተግባርን ይፈጽሙ ዘንድ ባሰለጠናቸውና ባሳደጋቸው ሠራዊቶቹ እየተከዳ እርቃኑን እየቀረ ይገኛል።
ከመደበኛ መስመራዊ ውጊያዎች እስከ ምስጢራዊ የቦምብ ጥቃቶች በሚደረጉ ኦፐሬሽኖች በርካታ ሠራዊቶቹን እያጣ የሚገኘው ይህ የዘረፋ ስብሰብ በሠራዊቱ እየተከዳ ይገኛል።
በትናንትናው ዕለትም 05 የብልጽግና ሠራዊት አባላት ከደብረ ማርቆስ ከተማና ሊባኖስ ቀጠና የ14ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
እነርሱም ፦
1/ አማረ ጥላየ---መከላከያ
2/ ይበልጣል አሞኘ-----መከላከያ
3/ ውበሸት ላመስግን-----ሚሊሻ
4/ በላይነህ አገይ-------ሚሊሻ
5/ በላይነው ተስፋ-----ሚሊሻ ሲሆን ፋኖ እያደረገ ያለውን የምሕረት ጥሪ በመቀበል ተቀላቅለዋል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
የ14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት
+3
ሻለቃ ሙላቴ ሲሳይ እንኳን ደህና መጣህ!!
ከዚህ ቀደም በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ (ጎጃም) በሙያውና በእውቀቱ አመርቂ ግልጋሎት ለአማራ ትግል እየሰጠ የቆየው ሻለቃ ሙላቴ ሲሳይ ለላቀ ግዳጅና አገልግሎት እንኳን ወደ አፋብኃ በላይ ዕዝ (ጎንደር) በሰላም መጣህ እንላለን።
ቀጣዩ ግዳጅና አገልግሎትህ የድልና የስኬት እንዲሆን እንመኛለን።
መልካም የስራ ጊዜ!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም
#ገዳዩ፣ሌባዉ እና ዘራፊዉ የአብይ ቅጥረኛ ሚሊሻ በጃዊ ፈንድቃ ከተማ ንፁሃን ዜጎችን በመግደል እና በመዝረፍ ላይ ተሰማርቷል!!!
ሰሞኑን በሁለት ቀናት ዉስጥ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ላይ የሚገኘዉ አረመኔዉ የአብይ ሎሌ ወገኑን የከዳ ጨካኙ ገዳይ እና ዘራፊ ቡድን የሚከተሉትን ዘግናኝ ተግባራት በማህበረሰቡ ላይ ፈፅሟል።
1.ሀብታሙ ደመላሽ የተባለዉን ሰርቶ የሚኖር ንፁህ ግለሰብ ከብት ገበያዉ ላይ በሚሊሻ ተገድሏል።
2.ታደለ ዘመኑ የተባለ የ18 አመት ልጅ ብር አምጣ በማለት ሀይ ስኩል ጀርባ ላይ በሚሊሻ ተገድሏል።
3.ለጊዜዉ ስሙ ያልታወቀ ግለሰብ ላይ 200,000 ብር ዘርፈዋል።
4.ከአንድ ግለሰብ ላይ 10,000 ብር እና ሞባይል ወስደዉ ግለሰቡ ፖሊስ ጣቢያ ለማመልከት ሲሄድ የዘረፈዉን ሚሊሻ አይቶት ይህ ነዉ የዘረፈኝ ሲል እንደገና ደብድበዉ ሰደዉታል።
5.አለሙ ይላቅ የተባለዉን ግለሰብ የ14 አመት ሴት ህፃን ልጁን አፍነዉ ሲወስዱ የገናን በዓል የሚያከብሩ ሰዎች ከብት እያረዱ እያለ አስጥለዋታል።
6.ጉባይ የሚባል ባለ አባዱላ መኪና ባለቤት በመደብደብ ህዝብ እንደጫነ ወደ ጃሂማላ መዉጫ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አካባቢ ዳንግላ በር አስፓልት ጫፍ ላይ የተሳፈረዉን ሙሉዉን ህዝብ ዘርፈዋል።
የህዝባችን መከራ እና ሰቆቃ በአብይ ተላላኪ ሎሌዎች አማካኝነት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!!
ይህ ደግሞ የሽንፈት ምልክት ነዉ!!!
አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!!
አራት የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት አባላቶች ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቀሉ::
የብልፅግና አገዛዝ መከላከያ ሰራዊት 11ኛ ዕዝ 104ኛ ኮር 35ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ አሃድ የሆኑ አራት አባሎች ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለ ሽርጡ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: የክፍለ ጦሩ አመራሮችም አቀባበል አድርገውላቸዋል::
ፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና አውደ ውጊያን ጨምሮ በብዙ የጦር ግንባሮች የማፈራረሱ ሁለንተናዊ ተጋድሎ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ሰራዊቱን የማፍረሱ ተግባር ደግሞ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበበት ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም
"ጠላትነት ወይንስ ንፅህና"
206ኛ ኮር ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም
===================================
እነዚህ ደግሞ ጭናቸውንም፣ ልባቸውንም ጭንቅላታቸውን ለብልፅግና ስርዓት አከራይተው ወልዶ ባሳደጋቸው ህዝብ መከራና ስቃይ ጮቤ የሚረግጡ ከጀነራሎችና ኮረኔሎች ጋር ውስኪ እያወረዱ ደስ ሲላቸው በባሎቻቸው አልጋ ከፈለጉም በደብረ ማርቆስ ከተማ በጃከራዳ፣ fm እና ጎዛምን ፈረሰኛው ሆቴሎች በአበባ በተንቆጠቆጡ መኝታ ቤቶች ቀናትን በር ዘግተው አንሶላ የሚጋፈፉ ነውረኛ የብልፅግና ባለሟሎች መጨፈሪያ ሹማምንትና ወይዛዝርቶች ናቸው።
በደብረ ማርቆስ ከተማ አሉ የሚባሉ ባለ ሀብቶችን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎችን ያሳፈኑ በማጎሪያ ጣቢያ ያሰቃዩ ሴትነታቸውን ለመኮንኖች አከራይተው የተለያዩ ስልጣን የተደጎሙ የመኳንት መደለቂያ የህዝብ ማሰቃያ የአብይ አህመድ ታማኝ ኤጀንቶች ናቸው ።
በሰሞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ሴቶችን በመሰብሰብና መሰል ፀያፍ ድርጊት እንዲፈፅሙ አስገድደው በጎዛምን፣ የቦቅላ፣ ዕረቡ ገበያ፣ ደብረ ኤልያስና አማኑኤል አካባቢዎች በርካታ የሴት ደህንነቶችን አሰራጭተዋል ።
ሴት ልጅ እናት፣ እህት፣ ሚስት እና ሀገር ናት ብለን ሴት ልጅ በልዩ እንክብካቤና ጥበቃ በምንይዝበት በዚህ ፈታኝ ዘመን ሴቶችን አስገድዶ በቡድን ለሚደፍረው፣ እናቶችን ለሚጨፈጭፈውና የአማራን ህዝብ በጅምላ ለሚረሽነው አብይ አህመድ የድሮን አስተኳሽ ሁኖ መገኘት ግልፅ ጠላት እንጅ ፆታን መከታ አድርጎ ሴትነት ብቻውን ንፅህና ሁኖ ሊቆም አይችልምና ያስቀዝፋል እያልን ነው።
ስንት ሴቶች ከጠላት ጋር ሁነው ይዋጉናል? ስንት ሴቶች የጠላት የመረጃ መረብ ሁነው ወንድሞቻችንን አስነጥቀውናል? ስንት እህቶቻችንን እናቶቻችንና ህፃናትን አስደፈሩ? እነዚህ በደማችን ላይ ቁመው ሴት ሁነው በንፅህና ሊታዩ የሚሞክሩትን ሞኞች በሏቸው ።
ከጠላት ጋር ያበረ የተጠላትን ተልዕኮ ተቀብሎ የተንቀሳቀሰው ሁሉ ጠላት ነው ለጠላት ደረጃ አውጥተን አንታገልም በፆታ፣ በዘር፣ በአካባቢና በዝምድና ለይተን አንዋጋም ጠላት ጠላት ነው ሰይፋችን በጠላት አንገት ላይ ማረፉ የማይቀር ነው እና ሴትነት ብቻውን መንግስተ ሰማያትንም እንደማያወርስ ሁሉ በንፅህና መቆም ከጠላት ተልዕኮ መራቅ ከህዝብ ወገን መሆን ያስፈልጋል ብለን እንመክራለን ።
እነዚህ ከታች የተደረደሩት ካድሬዎች አብይ አህመድን የበለጠ ለማገልገል ሴትነታቸውንም አከራይተዋል እንጅ ወገናቸውን ለማስጨፍጨፍ ሴትነታቸው አልገደባቸውም ሴትነቷ ሳይገድባት ለምትገድለን ሴት እኛስ እርህራሔውን ከየት እናገኘዋለን ብለን ብንጠይቅ ከወንጌሉም ከቁራኑም ምን ምላሽ ትሰጡናላችሁ?
1. ወ/ሮ ገነት በቀለ ምሰራቅ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፅ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ፅ/ቤት ኃላፊ
2. ወ/ሮፋንታነሸ አፈወርቅ የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር የሴቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ።
3.ወ/ሮ የውልሰው ወርቅነህ የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር ባህልና ቱሪዝም ተጠሪ ፅ/ቤት ኃላፊ።
4.ወ/ሮ አየሁአለም ያሳብ የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር ሲቪል ሰርቪሰና የሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ።
5.ወ/ሮ አሞኘሸ የምስ/ጎ ዞን ሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
6.ወ/ሮ ላቀች ሰማ የደብረ ማርቆሰ ከተማ የብልፅግና ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
7.ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር የአብማ ክፍለ ከተማ ሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
8.ወ/ሮ ትግሰት ልየው የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊ ከዚህ በፊት ሲቪል ሰርቪሰ ኃላፊ የነበረች አሁን ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊ
9. ወ/ሮ የናት ፋንታ አሰቻለ የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር ቅሬታ ፅ/ቤት ኃላፊ
10. ወ/ሮ ሶሊያና መሀሪ የደብረ ማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር ህንፃ ሹም ተጠሪ ፅ/ቤት ሃላፊ (የፋኖ ቤተሰቦችን መሬታችሁ ይነጠቃል ብላ መግለጫ አውጥታለች)
11. ወ/ሮ ኢትዮጵያ ከባዱ የደብረማርቆሰ ከተማ አሰተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ
12. ወ/ሮ ገነት በቀለ ምሰራቅ ጎጃም ዞን ብልፅግና ፅ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ፅ/ቤት ኃላፊ
13. ወሮ ዘርፌ ከበደ የተድላ ጓሉ ክ/ከተማ የብልፅግና ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ
14. ወ/ሮ እመቤት ማናየ የመንቆረር ክፍለ ከተማ ገቢዎች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሲሆኑ በብልፅግና ወንበር የሚፈላሹ በየደረጃው የተሰየሙ የብልፅግና ተሿሚዎች የአማራ ህዝብ የፍዳ ደብዳቤ አርቃቂ የገዳዮች ጉልበትና አቅም የህዝብ አፋኝ ጭምብሎች ናቸው።
እነዚህ እና መሰል ጥቅል መረጃዎች በሁሉም ወረዳዎች መንጥረን የምናወጣ ሲሆን ለጠላቶቻችን ደረጃ እንደማንሰጥ ማረጋገጥ እንወዳለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የብርሀኑ ጁላ የብልፅግና ሰራዊት መረጃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ታህሳስ 29/2018 ዓ/ም የብርሀኑ ጁላን መረጃዎች በቁጥጥር ስር አውሏል።
ከአማራ ማህበረሰብ የአለባበስና የእንቅስቃሴ ባህል ተመሳስለው የገናን የብዓል ስነ-ስርዓት ምክንያት በማድረግ ወደ እስታይሽ ከተማ ሰርገው በመግባት የአማራን ህዝብ በድሮን ለማስመታት እንቅስቃሴ ላይ እዳሉ በደጋው መብረቅ ኮር ደጀን ክፍለጦር ፋኖዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሶስት የመከላከያ ሰራዊት መረጃዎች ወደ ፋኖ ቀጠና ገብተው የጥፋት አላማቸውን ሊፈፅሙ ሲሉ በግስላ ፋኖዎች እጅ ከፍንጅ የዋሉ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በተለያዩ ቦታዎች በኮሩ አሀድ ፋኖዎች መሰል እኩያኖች በቁጥጥር ስር ውለው የአማራን ህዝብ መታደግ ተችሏል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት የብርሀኑ ጁላ መረጃዎች ለምን ተግባር ከፋኖ ቀጠና እንደገቡ ሲጠየቁ"የአማራ ህዝብ ተሰብስቦ የሚገኝበትን ቦታ ለላኳቸው አለቆቻቸው ለማሳወቅና ከዛም በድሮን ማህበረሰቡን ጭምርም ቢሆን መመታት እዳለበት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ ሊያጠፋ ፎክሮና ፎግሮ የገባው የብልፅግናው ጋንግስተር በአማራ ፋኖ በየወቅቱ በመጣበት የሀይል ምላሽ እየተደመሰሰ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
የደጋው መብረቅ ኮር ሚድያ ክፍል
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
+1
እኔ በልጅነቴ ቢያንስ 8 ዓመቴ ገደማ ወያኔ ትግሬዎች በሚፈሩበት ወቅት የአንዱን ወታደር ጭንቅላት በድንጋይ ፈልጨው በማምለጤ አገር መንደሩ ሁሉ ጉድ ያለበት ታሪክ አለኝ።
ንጹህ አማራ ስትሆን ጠላትህን ምንጊዜም ትቃወማለህ እንጅ አትለማመጥም አትሽቆጠቆጥም።
ንጹህ አማራ ስትሆን ትልቅ ነፃነት እና ነፃ ሐገር ፥ነፃ ሕዝብ ትመኛለህ እንጅ ለሆድህ ብለህ እንደ ፈረስ ጠላት አይጭንህም።
የጠላት ገረድ፥የጠላት ተላላኪ ሎሌ አትሆንም።
ከነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር የተሰጠ መግለጫ
ታሕሣሥ 30/2018ዓ.ም
እንደሚታወቀው አማራ የህልውና አደጋ ገጥሞት ትግል ተጀምሮ ከሁለት ዓመት በላይ እየተካሄደ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁንና የደረሰው ግፍ በአለም ታይቶ የማይታወቅ ፍጹም አረመኒያዊነት የታየበት በመሆኑ የአብዮቱ አጀማመር የሽምቅ ውጊያ አነሳስን ያልጠበቀ ሁሉም በየሰፈሩ የየራሱን ድርጅት ወጥኖ በመሠለው የትግል ስልት ሲመራ ቆይቷል። ይህንን ሁኔታ የተረዱ አንዳንድ በሳል የአማራ ታጋዮች ትግሉ ውጤታማ ይሆን ዘንድ በየቀበሌው ያሉትን ጥቃቅን ድርጂቶች አንድ ላይ ሰብስበው በሻለቃ በክፍለጦር አዋቅረው ፣ ክፍለጦሮችን አጣምረው ኮር መሥርተው ፣ ኮሮችን ደምረው እዝ መስርተው ፣ እዞችን አንድ አድርገው አንድ የአማራ ጦር ገንብተው በተጨማሪም ይህንን የአማራ ጦር የሚመራ አንድ መሪ ድርጂት ገንብተው አማራ ብሎም እንደ ሀገር የገጠመነን ችግር ለመቅረፍ እንደ አለምም የሰው ልጅ የገጠመውን ውስብስብ ችግር ለመፍታት የመፍትሄ አካል ለመሆንና ምድር ተፈጥሯዊነቷን ጠብቃ ለሰው ልጅ ምቹ መኖሪያ ሁና ትቀጥል ዘንድ አስተዋጽኦ ለማበርከት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።
ይሁንና ትግሉ በአለም ዘንድ ባልተለመደ መልኩ በየቀበሌው የተጀመረ በመሆኑ ጠላት ሰርጎ ገቦችን እንደልቡ በማስገባቱ አንድ ወጥ ድርጂት ሲመመሰረት ቀላል የማይባል ፈተና መኖሩ መራራ ዕውነታ ነው። በተለይ ልክ አሁን እንዳለንበት ጊዜ እነዚህን በራሳቸው አመራር ሲመሩ የነበሩ እና ጠላት እጁ ያለባቸውን አደረጃጀቶች ቀላቅሎ በአንድ ዕዝ ለማንቀሳቀስ በሚሰራበት ሂደት ላይ ብዙ አፈንጋጮችና ብዙ ፈርጣጮች መኖራቸው ይጠበቃል።
እነዚህ የቀበሌና የሰፈር መንግስቶች መንግስታቸው ሲፈርስ አኩርፈው ወደ ዘረፋና እገታ መግባታቸው ግልጽ ነው። በተጨማሪም ጠላት ብልጽግና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይህንን ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የራሱን ዘራፊ ቡድኖች አቋቁሞ ዘረፋና እገታውን አጧጡፎታል።
በተለይ እንደ ነበልባሉ ፎገራ ክፍለጦር ቀጠና ከጉማራ እስከ አለምሳጋ ጠላት በየኪሎ ሜትሩ ሀይሉን አስቀምጦ ለአጋቾችና ለዘራፊዎች እንዳናጸዳቸው ሽፋን በመስጠት ህዝቡን ቁሞ እያዘረፈው ፣ እያስገደለው እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም ህዝቡ ይህንን ተረድቶ በጠላቱ ብልጽግና ላይ መነሳት እንዳለበት እናሳስባለን። እኛም እንደክፍለጦር ችግሩን ለመቅረፍ ቅድሚያ ለሌቦች ሽፋን የሚሰጠውን የብልጽግና ወታደር ላይ እርምጃ በመውሰድ ህዝባችን ከዘራፊዎችና ከአጋቾች ለመከላከል እየሰራን እንደሆነ በያ ሰሞን ያደረግነው ሌባ የማጽዳት ዘመቻ ማሳያ ነው።
እነዚህ ብልጽግና እርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ያደራጃቸው ዘራፊ ቡድኖች በቀጠናው አባታቸው ብልጽግና ከሌለ ህልውናቸው ያከትማል። አካባቢውን ከብልጽግና ዘራፊዎችና አጋቾች ነጻ ለማድረግ የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና ስላለው ህዝባችን ቀጣይ ፋኖ በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የሌቦችን አባት ብልጽግናን ለማጥፋት እንድትተባበሩ እያሳሰብን ቀጣይ ለምናካሂደው ሌባ ብልጽግናን የማጥፋት ዘመቻ መረጃ በመስጠት በመዝመትም ጭምር እንድትሳተፉ እናሳስባለን።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን✊
አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ነበልባሉ ፎገራ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ
ፋኖ መምሕር አብዩ መልኬ
የሠራዊቱ አባላት ፋኖን እየተቀላቀለ ነው‼️
ፋግታ ከተማ መሽጎ ካለው የአረመኔው ሰራዊት አባላት በቀን 30/04/2018 ዓ.ም ዐፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር የ55ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀሉ።
ፋኖን የተቀላቀሉት አባላት፦ከ304ኛ ኮር 1. በለጠ መልካሙ 99ኛ ክ/ጦር፣ 5ኛ ሻለቃ፣4ኛ ጋንታ አባል 2.ጀማል አለሙ ይመር 99ኛ ክ/ጦር፣5ኛ ሻለቃ፣2ኛ ጋንታ የነበሩ አባላት ናቸው።
አባላቱም እንዲህ በማለት ምስክርነታቸውን አጋርተውናል። ጸረ -አማራው ስርዓት በአማራ ክልል፣ በመከላከያ ስም ያሠፈረው አረ,መኔ ሰራዊት ሴቶችን በጂምላ ሲደፍር፣ንጹሀንን በጂምላ ሲረሽን፣የሀይማኖት አባቶችን ሲገድልና በየቀኑ የአማራን ህዝብ ንብረት ሲያወድም በዓይናችን ስናይ ስላልቻልን ወደፋኖ መቀላቀል ችለናል ብለዋል።
አባላቱም የመዋጋትና የመሞት ምራል የለውም፣እርስበርሱ የሚጠራጠርና የማይተማመን ሆኗል፣ስለዚህ የድሀ ልጂ ለአንድ ግለሠብ ስልጣን ተብሎ መሞት እንደሌለበትና ፋኖን በመቀላቀል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጸር የሆነውን ዘረኛ ስርዓት ማስወገድ መቻል እንዳለባቸው መልክት አስተላልፈዋል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ‼️
የዐፋብኃ ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
