fa
Feedback
የፍቅር ጥቅስ

የፍቅር ጥቅስ

رفتن به کانال در Telegram

እንኳን ፍቅር ወደ ሆነው የፍቅር ጥቅስ ቻናል መጣችሁ በዚህ ቻናል ❤ስሜትዎን የሚገልፁ #የፍቅር ጥቅሶች ❤አጓጊ #የፍቅር ታሪኮች አንዲሁም ግጥሞች ያገኙበታል ይመቻችሁ

نمایش بیشتر
1 802
مشترکین
+324 ساعت
+67 روز
+3230 روز

در حال بارگیری داده...

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژوئیه '26
ژوئیه '26
+113
در 5 کانال‌ها
ژوئن '26
+109
در 26 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+94
در 23 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+136
در 30 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+220
در 5 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+158
در 7 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+246
در 47 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+220
در 37 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+159
در 43 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+167
در 44 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+145
در 43 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+140
در 41 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+169
در 47 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '25
+196
در 32 کانال‌ها
Get PRO
مه '25
+275
در 34 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '250
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '25
+251
در 1 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
31 ژوئیه+5
30 ژوئیه+2
29 ژوئیه+1
28 ژوئیه+1
27 ژوئیه+6
26 ژوئیه+4
25 ژوئیه+8
24 ژوئیه0
23 ژوئیه+3
22 ژوئیه+4
21 ژوئیه+6
20 ژوئیه+1
19 ژوئیه0
18 ژوئیه+5
17 ژوئیه+7
16 ژوئیه+1
15 ژوئیه+3
14 ژوئیه+7
13 ژوئیه+5
12 ژوئیه+2
11 ژوئیه+1
10 ژوئیه+11
09 ژوئیه+7
08 ژوئیه+3
07 ژوئیه+6
06 ژوئیه+1
05 ژوئیه+2
04 ژوئیه+2
03 ژوئیه+3
02 ژوئیه+2
01 ژوئیه+4
پست‌های کانال
♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 13...🌹 . መንዳትም ተሳነኝ። ላስነሳ ስሞክር እንቢ አለኝ።  የኔም  ልብ  የባጃጄም   ሞተር እኩል ተረበሹ  መሰለኝ ባጃጃም እምቢ አለች  •••እኔም ለመንዳት •••ምኑን ቅድሚያ  ነክቼ ምኑን ማስከተል እንዳለብኝ  ጠፋብኝ እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ። ወደሌላ ቦታ እያየሁ ትንሽ ትንፋሽ ወሰድኩ። ወደነሱ ሳልመለከት በድጋሚ ቃል ስልክ ላይ ደወልኩ ••••ሶስቴ ቀና ብዬ ስምለከት ከቃል ጋር ያለው ልጅ ድንገት ለቀቃትና አስፖልቱን ተሻግሮ  ቀጥታ ከአስፓልቱ ዳር ወዳለች አንዲት አነስተኛ መደብር(ሱቅ) ሄደ። ቃልዬ ያችን ክፍተት ተጠቅማ እዛው ቆማ ልጅ የሚገዛውን ገዝቶ እስኪመለስ እየጠበቀችው ከኪሷ ውስጥ ሞባይሏን አዉጥታ ተመለከተች። ስልኳ 'ቫይብሬት' ላይ ነው ማለት ነው፣ ማን እንደደወለላት እየተመለከተች ነው። አይታው ትደውልልኝ ይሆን •••? ወይስ አጥፍታ ሞባይሏን ወደ ኪሷ ትመልሰው ይሆን•••? በሚል ጥያቄ  ልቤ እየዘለለች ጠበኳት። መደብሩ በር ላይ ወደቆመው ልጅ እየተመለከተች ስልኳን ወደ ጆሮዋ ጠጋ እንዳደረገችው ስልኬ ጠራ። "ሄሎ ቃል!" "ወዬ ኤፍዬ ደና ነህ•••?" "ደደደ••••አ•••••ዎ፣  ደ •••ደና ነኝ ቃልዬ!" "በኋላ መልሼ ደውላለሁ እሺ ኤፍዬ•••? አሁን የማይመች ሁኔታ ላይ ስለሆንኩ ነው!" "እ•••••እሺ ! እሺ ቃሌ!" "'ባይ 'ኤፊ እወድሀለሁ እሺ•••?" "እሺ ቻው•••እእእ  እኔ አፈቅርሻለሁ!" "ቻው!" አለችና ስልኩን  ጠረቀመችው። ጭውውውውው አለብኝ። የማይመች ሁኔታ!!! ምን ማለት ነው ቃሌ•••? ውሸት አልወድም ብለሽኝ ነበርኮ ቃልዬ? እየዋሸሽኝ መሆኑን ማመን አልቻልኩም።ቆይ ቆይ ልጁ አግቶሽ ነው እንዴ? እና ታግተሽ ነው እንደዚህ ወገቡ ላይ ጥምጥም ብለሽ የታቀፍሽው•••? ምን ማለት ነው የማይመች ሁኔታ •••? ትናንትና እኮ ነገ አይመቸኝም፣ አርብ ወይ ቅዳሜ ነው የምንገናኘው ብለሽ ያልሽኝ እራስሽ ነሽ። ቀጠሮ ይዘሽ ነው እንዴ የማይመችሽ ሁኔታ ውስጥ የተገኘሽው ። ከማየው ነገር በላይ ቃልዬ የተናገረችው ነገር አንጨረጨረኝ። ደሞ ከመች ወዲህ ነው በስልክ እወድሀለሁ ብላኝ የምታውቀው•••?  ለወትሮው ከቃልዬ አንደበት እወድሀለሁ! ፣ አፈቅርሀለሁ ፣ የሚል ቃል የነፍሴ ረሀብ እስኪመስለኝ ድረስ እንዳልናፈቀኝ አሁን ሰስማው ስድብ መስሎ ተሰማኝ። ወድያው ያ•••• ቃልዬ ለሷ እንዲከራከር ጥብቅና ቀጥራው ውስጤ ያስቀመጠችው እስኪመስለኝ ድረስ ቃልዬን ወግኖ የሚከራከርላትና የሚሞግተኝ የስሜቴ ክፍል ••••• "ኧረ ባክህ ተረጋጋ ኤፍሬም! ምን ነካህ•••? ! ቆይ ቆይ ቃልኪዳን ገና ለገና ካንተ ጋር ፍቅር ስለጀመረችና ያንተ ስለሆነች የአዳም ዘር መቅረብና ጓደኛ ማድረግ አትችልም ማለት ነው እንዴ•••? ከዚህ በፊት ሴት ጓደኛ አይወጣልኝም በቃ ሴቶች እጣ ክፍሌ አይደሉም ብላ ነግራኻለች፣ ስለዚህ ከወንዶች ጋር በህት በወንድምነት ልትቀራረብና ጓደኛ ልታደርጋቸው እንደምትችል ግልፅ ነው ። ምንም የተለየ  ያየኸው የሰማኸው ሳይኖር አብረው ሲሄዱ ስላየኻቸው ብቻ ሌላ ድብቅ ግኑኝነት አላቸው ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ምን ይሉታል•••?" አለኝ። ባክህ ዝም ብል ወደዛ!  እኔ መች ወንድ አይጠጋሽ አይቅረብሽ የሚል ነገር ወጣኝ። ለምን መደባበቁ አስፈለገ ነው ዋናው ጥያቄ! ደሞ ጓደኛዋ ከሆነ እጁ አንገቷ ላይ ምን ያደርጋል •••? ለምን ያቅፋታል•••? ከወንድ ጋደኛዋ ጋር በከዚራ ጥላ ስር ሽር ብትን ለማለት ነው ሀሙስ ሀሙስ የማይመቻት •••? ከዚህ በላይ ምን የተለየ ነገር ልይ•••? ሁኔታቸው በሙሉ ሌላ ነገር እንዳላቸው ያሳብቅ የለ እንዴ? !?" አልኩ ጮክ ብዬ ። ወይኔ ኤፍሬም ልለቅ ነው እንዴ? በርግጥ ሰው በሂወት ዘመኑ ከሰው ጋር ከሚያወራው ብዙ እጅ የሚበልጠውን ከራሱ ጋር እንደሚያወራ ግልፅ ነው። ቃልዬን ካወቅኩባት ምሽት ጀምሮ የተፈጠረው የውስጤ ሙግት ግን ለኔ አዲስ ሆነብኝ። ልጁ ከመደብሩ የገዛውካርድ ስልኩ ላይ ሞልቶ ስልክ በመደወል እዛው መደብሩ በር ላይ ቆሞ እያወራ ነው። ቃልዬም ካአስፖልቱ ማዶ አንዱን የከዚራ እድሜ ጠገብ ዛፍ ደገፍ ብላ እየጠበቀችው ነው። "ንዳው ንዳው፣  ቀጥ ብለህ ሂድና ትይህ!" የሚል ስሜት ሲገፋኝ ባጃጇን አስነስቼ ቃልዬ ወደቆመችበት አቅጣጫ መንዳት ጀመርኩ። ትንሽ ጠጋ እንዳልኩ ውስጧ ነግሯት ይሁን••• ስላየው ልጁ ነይ ብሎ ጠርቷት ብቻ  ወደግራም ወደቀኝም አንዴ ገልመጥ ገልመጥ አለችና አስፓልቱን ተሻግራ  ወደ ልጁ በመሄድ ለመንገዱ  ጀርባዋን ሰጥታ ከሱው ጋር ማውራት ጀመረች። ሳልፍ አላየችኝም። ልጁን ግን ከግር እስከራሱ በደንብ አየሁት።  የድሬ ልጅ አለመሆኑን ለማወቅ ••••ፊቱ አዲስ መሆኑ፣ ፀፀጉር እስታይሉ፣ ፍርክርክ ያለው አለባበሱ፣ በዛ በሙቀት ያደረገው ከቁርጭምጭሚቱ ወደላይ በጣም ከፍ ያለ ትልቅ እስኒከር ጫማውን ማየት በቂ ነበር ለኔ። ጆሮው ላይ ሎቲ አጥልቋል። ሁኔታው 'ራፐር' እንጂ ተማሪ ባያስመስለውም እዛው ቃልዬ የምትማርበት ዩንቨርስቲ የሚማር ሳይሆን እንደማይቀር ገመትኩ።  ገና ፈነዳድቶ ያልወጣለት ወጠጤ ነገር ነው። አልፊያቸው በግምት መቶ ሀምሳ ሜትር ያህል ራቅ አልኩና ጥግ ይዤ በባጃጄ የጎን መስታወት መከታተሌን ቀጠልኩ። አሁንም እዛው ቆመዋል። ለምን የሚገዙትን ገዝተው እንደማይሄዱና እየተደዋወሉ እዛው ቆመው ማንን እንደሚጠብቁ ግራ ገባኝ። የዚህ ነገር መጨረሻ  ምን እንደሚሆን ሳስበው ጨነቀኝ ። ቆይ ምን እያደረኩ ነው ከጀርባ ተከትያት ምን ስታደርግ ላያት ነው•••? እሺ ምንም ስታደርግ ልያት ቆይ ከዛስ? ከቃልዬ ጋር ልጣላ ነው ማለት ነው•••? ከዛስ ከተጣላኃት በኋላስ ሰላም እሆናለሁ•••? ገና ለገና •••እሷን ማጣት አልፈልግም ካጣኋት ሰላም አልሆንም  ብዬ አሁን ያየሁትን እንዳላየሁ ሆኜ ማለፍ አልችል። ባልፈውስ?  እንዳሻት ትሁን ብቻ አልያት ብዬ አሁን መከታተሌን ትቼ ወደስራዬ ብሄድስ ሰላም ሆኜ መስራት እችላለሁ እንዴ•••?/ ኧረ አልችልም። ሁለቱም ያውና አንዳይነት ነው። ቆይ ከዚህ ሁሉ ቀጥ ብዬ በመሄድ ሰላም ብያት••••• ከማን ጋር  ቆማ፣  ምን እየጠበቀች እንደሆነ ብጠይቃትስ•••? ክፍል 14  ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍

2
ሰላሙ የሚባል የድሮ ጓደኛ ነበረኝ። የሆነ ሰሞን ሲጠፋ ጊዜ ተጨንቄ "ሰላሙ የጠፋ ሰው" ብዬ ሜሴጅ ላኩለት But sadly he replied "ያንተው ሰላም ይጥፋ" and blocked me. አይ አማርኛ! 😂😂
56
3
እኔው ታግዬ...+1
እኔው ታግዬ...
100
4
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...            .            . 🌹...ክፍል 12...🌹 "ምን ልበልሽ ቃልዬ •••? አብረሽኝ ሆነሽ እንኳ እንደምትናፍቂኝ እንደምናፍቅሽ•••ሁሌ በየሰከንዷ እንደማስብሽ እንደምታስቢኝ እኔ አንቺን ሳላይ መዋል እንደማልችለው ሁሉ አንቺም እንደዛ እንደሚሰማሽ?  አብሬሽ ስሆን ደስተኛ እንደምሆነው ሁሉ አንቺ ደስ እንደሚልሽ•••በቃ ስንቱን ልግለፅልሽ ቃልዬ••••" ስላት በዝምታ ••• ያንን ፍቅር እየረጨ  ልብ የሚያሳሳውን አስተያየቷን ስታየኝ ቆየችና በረጅሙ ተንፍሳ ••• "ኤፊዬ እነዚህ ያልካቸው በሙሉኮ ታድያ መውደድ ውስጥ አሉ እኔ እወድሀለሁ ስልህ እነዚህ ስሜቶች እኔም ጋር አሉ ማለት አይደለም እንዴ ኤፍዬ•••? ምናልባት እኔ ለፍቅር አዲስ ስለሆንኩ ስሜቴን የመግለፅ ችግር ሊኖርብኝ ይችላል!"ቃልዬ እኔም እኮ ከዚህ በፊት አፍቅሬ አላውቅም!" "ይሁንልህ!" "ይሁንልህ ማለት አላመንኩህም ማለት ነው ቃሌ•••?" "ኪኪኪኪኪኪ •••ኧረ በጌታ ኤፍዬ ተወኝ ወሬ አልቆብህ ነው እንዴ•••?" "እንዴት ቃልዬ •••? ይሄ ወሬ ሲያልቅ የሚወራ ነው እንዴ•••? " እንጃልህ እብድ•••!" "ካካካካካ ቃልዬ ሙች አሁን ገና በትክክለኛ ስሜ ጠራሽኝ!" "ምን••••? ማለት•••?" "እብድ ነኛ ! አብጃለሁኮ ! ያበድኩት ግን ባንቺ ፍቅር ነው!" ስላት ሳብ አድርጋ ከንፈሬን  oh በከንፈሯ ጎርሳው ምጥጥ ስታደርገኝ ነፍሴን መንጭቃ ያወጣቻት መሰለኝ።ደንግጫለሁ። ከዛ በኋላ ምንም አላወራሁም። ልንለያይ ስንል እየሳቀች ••• "ኪኪኪኪኪ ኤፍዬ ካሁን በኋላ በምን ዝም እንደማስብልህ መላውን አውቂያለሁ ለማንኛውም ነገ አይመቸኝም እምንገናኘው ወይ ቅዳሜ ወይ አርብ ነው እሺ ቻው !" ብላኝ ስትሄድ •••"እሺ ቻው!"  ከማለት በስተቀር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም። "ለምንድን ነው ነገ አንገናኝም ያለችኝ ብዬ እራሴን የጠየኩት ግቢ አድርሻት እየተመለስኩ ብዙ ከራቅኩ በኋላ ነው። ብዙ ግዜ ቃልዬ  ሀሙስ እና ቅዳሜ የማይመቻት ግን ለምንድን ነው ። ቆይ እጠይቃታለሁ እስቲ•••• ግንኮ ቃልዬ ጥያቄ ሲበዛባት አትወድም ። በቃ ይቀራላ አልጠይቃትም። ስማ እንደዚህ ያቀለጠችኝ ከዛ ብትሻገር ምኔ ሊተርፍ ነው? •••• በሚወዷት ፣ በሚያፈቅሯት ልጅ መሳም ግን እንዲህ ይለያል•••? የመጀመሪያው እና  ድንገት ሲሆን ደግሞ ልብ ይሰውራል። አወይ ጥፍጥናሽ ቃልዬ ። አፈቅርሻለሁ አቦ ! እያልኩ ከቃልዬ ጋር  ፍቅር በጀመርን  በአራተኛው ወር የተሳመውን ከንፈሬን ደግሜ እየመጠጥኩ፣   ባጃጇን ለጉድ እየጋለብኩ፣  ሰፈር ደረስኩ። ሀሙስ በጥዋት ነው ስራ የጀመርኩት እስከ ሰባት ሰአት ስስራ ቆይቼ ምሳ ቃልዬ አጠገቤ  ሳትኖር ብቻዬን ውጪ መብላት ስለደበረኝ እህቴ ጋር ገባሁ። ምሳ በልቼ ብና ጠጥቼ ስወጣ ስምንት ሰአት ሆኗል ። ከሼል ወደ ገንደቆሬ ሰው ጭኜ ሄድኩ። እነሱን እንዳወረድኩ አንዲት ወጣት ሴት ሽንሌ ኬላው ጋር በ ኮንትራት እንድወስዳት ጠየቀችኝ። " ሁለት መቶ ብር ትከፍያለሽ •••?" ስላት ••• "አቦ  ሙጫ ••••! መቶ ሀምሳ ይበቃሀል!" ብላኝ መስማማቴን እንኳን ሳልገልፅላት ነበር ዘላ ባጃጁ ውስጥ የገባችው ። ቸኩላለች። ትንሽ እንደሄድን ካራ ማራ አከባቢ ሁለት ወጣት ወንዶች ሊያስቆሙኝ እጃቸውን ሲዘረጉ ። "በኛ መስመር ከሆኑ ያዛቸዋ ችግር የለውም!" አለችኝ ። ኮንትራት የያዘችኝ እሷ ስለሆነች ጫንም አትጫንም የማለት መብቱ የሷ ነው። ጫንኳቸው። ሁለቱ ወጣት ወንዶች በትግርኛ ያወራሉ። እኔና እሷ በፀጥታ እየተጓዝን ነው ። የድሬ ዳዋን ቤተመንግስት አለፍ እንዳልን ድንገት ወደ ግራ ዘወር ስል •••አይኔ ያየውን ማመን!•••• እውነት ነው ብሎ መቀበል!••••እስኪሳነኝ ድረስ ባየሁት ነገር  ክፉኛ ደነገጥኩ። ባጇጇን ከህግ ውጪ በሆነ መንገድ እያስጮኩ ቀጥ አድርጌ አቆምኳት። ደግሜ ተመለከትኩ አዎ እራሷ ነች ቃልዬ ከአንድ ወጣት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ረጋ ባለ እርምጃ ወደ ታች እየሄዱ ነው። ውረዱልኝ አልሄድም አልኳቸው ተሳፋሪዎቹን ። ድምፄ ግን እንኳን ለነሱ ለራሴም አልተሰማኝም ። ማውራት መናገር ውረዱ ማለት ሁላ አቃተኝ። ዘወር ብዬ አየኋቸው። ሁለቱ ወንዶች እርስ በርስ በትግርኛ •••• "እዛ ኲርኲር ተነፋኒፋ ጠጠው ዝበለት ታኵይና ድያ?" "እንድእላ! ተሃዊኻ ድያ ናኣ በል ቅሩብ እዩ ዝትረፈና ብእግርና ንኸይድ !" ተባባሉና ብሬን ሰጥተውኝ ወረዱ። ኮንትራት ከያዘችኝ ሴት ጋር ተፋጠጥን ። ውረጅ ልላት እንደሆነ ገባት•••አቦ ሙጫ ምን ሆነህ ነው የቆምከውሳ እንሂድ እንጂ እኔ እኮ እዛ ሰው እየጠበቀኝ ነው እቸኩላለሁ ሀይ!" አለችኝ። "አቦ በቃ አልሄድም ሌላ ባጃጅ ያዢና ሂጂ!" አልኳት። "አቦ አልወርድም ! እዚህ ጋር ባጃጅ ኬት አገኛለሁ ይልቅ አድርሰኝና ሂሳብህን ውሰድ!" "ምንም አትክፈይኝ ብቻ ውረጂልኝ አልኳት!" ባጃጁ ለመውረግረግ ባይመቻትም እየተውረገረገች በጭራሽ እንደማትወርድ ስትነግረኝ ስልኳ ጠራ አነሳችውና•••• "ሄሎ ••••!  ዱፌ ዱፌ •••ጢቂሾን ናኣፌ•••ገሩሞ መራታ ተኮ ከረራ  ገዲናቡኢ ናጀቱ ••ጅራ•••ሀይ! " አለችና ስልኩን ዘግታ  ከፊት ለፊታችን በቅርብ ርቀት የቆሙትን ሁለት ትራፊኮች አየት አርጋ ••• "ሲደውሉብኝ እየሰማህ ነው አደለም ባባ ባጃጁን አስነሳ እንሂድ ምንድን ነው ዝም ብለህ የምታየኝሳ•••?" "አቦ አፍቅረሽ ታውቂያለሽ•••?" አልኳት። "ሀሀሀሀሀሀይ ምን እያልክ ነውሳ•••?" "እሺ ፍቅረኛ አለሽ •••?" "አቦ እየቀለድክብኝ ነው እንዴ•••?" አለች ብስጭትጭት ብላ ። "እየቀለድኩ አይደለም ለምን እቀልዳለሁ ለስራ አይደል እንዴ የወጣሁት በቃ  ፍቅረኛዬ ከሌላ ወንድ ጋር ስትሄድ አይቻት ነው ለዛ ነው!" "ሀሀሀሀሀሀይ እንደዛ ነው እንዴ••••? ታድያ ቀድመህ አትናገርም ፣ እኔ መች ገባኝሳ ፣ አቦ እኔ ባጃጅ ባጣም በግሬ እሄዳለሁ ችግር የለውም እንካ መቶ ብር በሀምሳ ብር የሚያደርሰኝ አላጣም ፣ ሂድ ተከተላት ፣ ደሞ እንዳትጣላ እሺ አይዞህ!"  ብላኝ ወረደች። "ሀዬ አመሰግናለሁ!" ብያት ባጃጇን አዙሬ ቁልቁል ወረድኩ። ቃልዬ እና ልጁ በከዚራ ጥላ ስር ተጣብቀው ፣ እርስ በርስ ቁልፍልፍ፣ ትስርስር  ብለው፣ በእርጋታ ሲሄዱ ተመለከትኩ። አይኔን ጨፈንኩ፣ መልሼ ገለጥኩ ህልም አይደለም እውነት ነው። እሱ አንገቷን አቅፏታል፣ የኔ ቃል ወገቡን ያዝ አድርጋዋለች። በቃ ተቃቅፈው በከዚራ መንገድ ላይ የግር መንገድ እያደረጉ ነው። ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላት ሳልኳን ከጅንስ ሱሪ ኪሷ ውስጥ  አውጥታ ማን እንደደወለላት ማየት አልፈለገችም ።  ቃልዬ እቅፉ ውስጥ ነች ፣ ስልኬን ሳታነሳው ጠርቶ ጠርቶ ዘጋ ።  እያየኋቸው •• በደንብ አየኋቸው •••እንኳን አየኋት ሳይሆን ባላየኋት ብዬ ተመኘሁ። ግን ልጁ ምኗ ነው? የት እና ከመቼ ጀምሮስ ይሆን የምታውቀው•••አቦ ምን አውቃለሁ። ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ነው እንዴ ? ኡፍፍፍፍ •••••"ዝም ብለህ ፊት ለፊትህን እያየህ  ብትነዳ ምናለበት ኤፍሬም ?"  አልኩት እራሴን  ምን ማለት ?  ምን ማድረግ?  እንዳለብኝ ግራ ሲገባኝ በቀስታ እየነዳሁ ልከተላቸው አሰብኩና.. ክፍል 13  ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍  
160
5
♥️ ተማሪዋ ♥️ ...            .            . 🌹...ክፍል 11...🌹 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! ነፍሷን ይማረው እና እማዬ•••••" ኪኪኪኪ ኤፊዬ ቅናተኛ ነው። ልጅ እያለም መሽቶ በተኛን ቁጥር  አባቱን ተነስ ከማዬ አጠገብ! •••• እማ ከኔ ጋር ብቻ ነው የምትተኛው! ••• ውረድ ካልጋው ላይ እያለ ይጎትተው ነበር!" እያለች ብዙ ግዜ ታወራ ነበር ። "አቦ ተያ እማዬ ደሞ!" አላለሁ እቤት ውስጥ ያለውን እንግዳ፣ ታላቅ እህቴን እና  አባዬን በፈረቃ እየተመለከትኩ። ኤፍዬ ሙት እውነቴን እኮ ነው ኪኪኪኪኪ ለብዙ ግዜ አባትህ አንተ ካልተኛህ በቀር አጥገቤ ድርሽ አይልም ነበር ኪኪኪኪ ይህ የሁሉም ልጅ ባህሪ እኮ ነው ኤፍዬ ያንተ ግን ጫን ያለ ነበር ትልቅ ሆነህም ላንተ ሳይገዛ ለህትህ ልብስም ጫማም ከተገዛ መች ታስደርጋታለህ  አይ ኤፍሬሜ !" ትላለች። አንድ እህት ነው ያለኝ።  በሰባት አመት ትበልጠኛለች። እማ ልክ ነች እቀናለሁ  ቃልዬ ለምን ታስቀናኛለች ••••? ለምንድን ነው ሁሉንም የሚደወሉላትን ስልኮች አጠገቤ እያናገረች  ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እኔ አጠገብ ሆና የማታወራው አንድ  ስልክ የኖራት•••። የደዋዩን ስም አይቼዋለሁ። ዛኪ ብላ ነው የመዘገበችው። ዛኪ በሚል ስም የሚደወልላትን ስልክ አንድም ቀን አጠገቤ ሆና አናግራ አታውቅም። አጠገቤ ሆና አለማናገሯ ብቻ አይደለም ያንን ስልክ ካወራች በኋላ እንደምትቀየረም አስተውያለሁ። እየሳቀች የነበረችው ልጅ ያንን ስልክ አናግራ ስትመለስ ሳቋ ብቻ ሳይሆን  መረጋጋቷም ጠፍቶ ድውክውክ ትላለች። ምነው ስላት መልሷ ምንም••• ምን ሆንኩ?  ነው። ምን ሆንሽ እንደምላት ግራ ይገባኝና ዝም እላለሁ። መጀመሪያ የመሄድ ሀሰብ ያልነበራት ልጅ አብረን ልናመሽ ከተነጋገርን በኋላ ያ ዛኪ የተባለ ሰው ከደወለ በቅፅበት ውስጥ  ልሂድ በቃ ኤፍዬ ብላ ለመሄድ የምትነሳው ነገር ደግሞ ይበልጥ ያናድደኛል።ቢሆንም ቃልዬን አፈቅራታለሁ። ቀኑ እሁድ ነው። የተኛሁበት ክፍል ገና በጥዋት ሲንኳኳ ነበር እህቴ እንደሆነች ያወቅኩት። በባጃጅ ስራው በየሳምንቱ የሚጣል እቁብ አለ። ከቃልዬ ጋር ከመተዋወቃችን በፊት አንድ ቀንም አጉድዬ አላውቅም እንደውም ከሚፈለገው በላይ አጠራቅሜ በየሳምንቱ ቅዳሜ ማታ ወስጄ ለህቴ እሰጣታለሁ ። ወላጆቻችን በሂወት ስለለሉ ከህቴ ጋር ነበር የምኖረው ይህን ስራ ስጀምር ነው አንድ ክፍል እዛው ሰፈር ውስጥ ተከራይተን ከጋደኛዬ ጋር አብረን መኖር የጀመርነው። አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ውጤቴ ዩንቨርስቲ ለመግባት ባያስችለኝም በማታው መርሀ ግብር እዛው ድሬ ዩንቨርስቲ ከፍዬ ላስተምርህ ስትለኝ አልፈልግም ባጃጅ ግዢልኝ ብዬ ነው ያስገዛኋት። ቅዳሜ ማታ ከኔ ብሩን ትቀበል እና እሁድ ጥዋት ወስዳ ትጥላለች። ትናንትና ፣ ቅዳሜ ማታ ግን አልሄድኩም ብሩንም አልሰጠኋትም። ትናንት ብቻ አይደለም ለተከታታይ አራት ሳምንታት የቁቡን ብር እየናድኩት ስለሚጎድል እህቴ ጋር ሳልሄድ ድምፄን አጥፍቼ ገባና ተኛለሁ። እሁድ ጥዋት ትመጣለች ። "ስላልሞላልኝ እኮ ነው ዝም ያልኩሽ እቴትዬ!" ስላት••• "ምነው ኤፍዬ •••? ሰሞኑን ስራ የለም•••? ነው ባጃጇ ረብሻህ ለገራዥ ወጪ አወጣህ•••?" ትለኛለች ። "አዎ እቴትዬ " እላታለሁ። ያለውን ትቀበለኝ እና ከራሷ ሞልታ እቁቡን ትጥላለች። እውነቱ ግን ባጃጇ ምንም አለመሆኗ ገራዥም አለመግባቷ ነው። የታመምኩት እኔ ነኝ። ከህመሜ የምትፈውሰኝ መካኒኳ ደግሞ ቃልዬ ናት። እሷን ሳገኛት አይደለም የእቁቡን ብር ባጃጇንስ  ባጠፋት መች ልክ ያልሆንኩ መች ያጠፋሁ ይመስለኛል •••? ብዬ ለ እቴትዬ አልነግራት  ነገር የማይባል የማይነገር ሆነብኝ። ዛሬም በጥዋት የመጣችው ያንኑ መከረኛ የቁብ ብር ልጠይቀኝ ነው። ኪሴ ውስጥ ያለው ከሚያስፈልገው ግማሹ ነው።  በሩን ደጋግማ ስታንኳኳ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተኛሁ። ከተኛ የማይሰማው ጓደኛ እንዴት ዛሬ እንደሰማ እንጃለት ብቻ ተነስቶ ከፈተላት። "ተኝቷል እንዴ•••? ቀስቅሰው እና የቁቡን ብር ይዞልኝ ይምጣ እሺ ኪያዬ ድስት ጥጃለሁ አሁኑኑ ቀስቅሰው!" ብላው ሄደች። " እሺ!" ብሏት ዘወር ሲል ተነስቼ ፍራሼ ላይ ቁጭ ማለቴን ተመለከተ። "እንዴ •••••? እየሰማህ ነው እንዴ ዝም ያልካት ኤፊ••••?" "እንኳን እኔ አንተም ሰምተሀል እንቅልፎ!  " አልኩትና  ቀጠል አድርጌ " ባክህ የቁቡን ብር ረሚም አድርጌዋለሁ ለዛ ነው " አልኩት። "አንተ ልጅ ግን ምን ጀመርክ ስራ ለጉድ እየሰራህ ነው ባጇጇ ለስከንድ ገራጅ ገብታ የማታውቀውን ገራጅ ገባች ምናምን እያልካት ነው ኧረ ይደብራል ኤፊ !" "ዝም በል ወደዛ ! ወሬህን ተውና ይልቅ ብር ካለህ አበድረኝ ሞልቼ ልስጣት!" አልኩት ። ሰጠኝ ። ሰጠኋት። ከቃልዬ ጋር ሰኞም ማክሰኛም ተገናኝተናል ። ዛሬም ምርጥ ቦታ ወስጄ ምሳ ልጋብዛት ተቀጣጥረናል። እየመጣች ነው ። እኔም ወደዛው እየሄድኩ ነው። ተገናኝተን ምሳ እየበላን እኔ የባጥ የቆጡን ሳወራ እሷ እንደሁልግዜው ስትስቅ ቆየንና በመሀል •••• "ቃልዬ !" አልኳት። "ወዬ ኤፊ!" "አንድ ነገር ልጠይቅሽ•••?" "ለምን አንድ ብቻ  ••••? ሁሌ አንድ አንድ እያልክ ከምጠይቀኝ ሰብሰብ አርገህ በጅምላ ብጠይቀኝ አይሻልም ኤፊዬ••••?" "እባክሽ አትቀልጂ ቃል•••?" "እሺ ምንድን ነው•••?" "ምኑ•••?" "ጥያቄህ ነዋ!" "እ•••••ማለት •••? ቃዬ ምን መሰለሽ ••••እኔን የሚሰሙኝን ስሜቶች ማለት እኔ ስላንቺ የሚሰሙኝን ስሜቶች አንቺ ጋር በከፊል እንኳን ያሉ ይመስልሻል•••?" "ሰው እንዴት አንድ አይነት ስሜት ይሰማዋል አንተም የራስህ እኔም የራሴ!" "እኔማ የኔ አይደለሁም!" "እና የማን ነህ?" "ያንቺ!"  "ኪኪኪኪ እኮ አንተ ለኔ የሚሰማህ ስሜት እኔ ላንተ ከሚሰማኝ ስሜት ጋር አንድ መሆን አለበት•••?" "እንዴት ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?" "እኔ እንጃ!" "እሺ እሱን ተይው ቆይ ትወጂኛለሽ •••? ማለት ታፈቅሪኛለሽ•••?" "ኪኪኪኪኪ•••••"እየፈጩ ጥሬ!"  አለች አያቴ!" "አያትሽ ደሞ ምን ነካቸው" "ምንም!" "እቦ ታድያ እየፈጩ እንዴት ጥሬ ይሆናል•••••?  ከተፈጨ ዱቄት አይደል እንዴ የሚሆነው!" "ኪኪኪ •••ጥሬው ያንተ ቢጤ ሆኖ ይሆናላ!" "ቢጤ••••! ምንድን ነው ደሞ ቢጤ••••?" "ካካካካካካካካ ኧረ በጌታ አታዝገኝ ኤፊዬ!" "አንዴ ጥሬ አንዴ ቢጤ እያልሽ እየተሳደብሽ ያለሽው እኮ አንቺ ነሽ ቃልዬ!" "ለምን ሰድብሃለሁ ኤፍዬ በጭራሽ አልሰደብኩህም ግን ኤፊ እኔ ካንተ ጋር ሁሌ የምገናኘው እና አብሬክ የማሳልፈው ምንህ ስለሆንኩ ነው•••?  ከአንደበት በላይ እኮ ተግባር ነው ለእውነቱ የሚቀርበው አይደለም እንዴ ኤፍዬ•••? ካልነገርኩህ አታምንም•••?" "ብትነግሪኝስ ምን አለበት አያስከፍል ቃልዬ! " "እሺ ወድሃለሁ!" "እሺ ወድሀለሁ አልሽ እህህ በጣም ደስ ይላል!" "እንዴ እጠላሃለሁ አላልኩህ ለምን ደስ አይልም•••?" "አይ አባባልሽ ከውስጥ ተቀድቶ በወጣ ስሜት ሳይሆን ለጥያቄዬ መልስ ለመስጠት ያህል የተባለ መስሎ ስለተሰማኝ ነው!" ስላት ፊቷን ቅጭም አርጋው ትክ ብላ ስትመለከተኝ ቆየችና ••• "ኤፊዬ!" "ወዬ ቃል!" "ምንድን ነው ማወቅ የፈለከው•••?" "እኔን የሚሰማኝ ሁሉ አንቺን እንደሚሰማሽ? " ለምሳሌ ምን•••?" . . . . ክፍል 11 ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍
199
6
🔥🔥 ምን ፈልጋቹ አጥታቹሀል??? ኧ🧐 🚀 እጅግ ውብ የሆኑ ዋልፔፐር እና ፕሮፋይል ፒክቸር??? 🚀 አስተማሪና አዝናኝ ታሪክ / ልቦለድ ???? ቀልዶች?? ሁሉንም ያሟላ ቻናል ልጠቁማቹ 🥰 �
🔥🔥 ምን ፈልጋቹ አጥታቹሀል??? ኧ🧐 🚀 እጅግ ውብ የሆኑ ዋልፔፐር እና ፕሮፋይል ፒክቸር??? 🚀 አስተማሪና አዝናኝ ታሪክ / ልቦለድ ???? ቀልዶች?? ሁሉንም ያሟላ ቻናል ልጠቁማቹ 🥰 👇👇👇
195
7
♥️ ተማሪዋ ♥️ ... 🌹...ክፍል 10...🌹 . እያልኩ ከግቢያቸው በር ላይ በሀሳብ መወዝወዝ የጀመርኩ ሳይታወቀኝ ሰፈር ደረስኩ። ውስጤ ሌላ ኤፍሬም ያለ እስኪመስለኝ ከትናንት ማታ ጀምሮ ቃልኪዳን አምናህ ነውና የተኛችው ጫፏን እንዳትነካት እያለ ሲሞግተኝ የነበረ አንድ ሌላ ስሜት እኔ ያሻኝን አስቤ ፍቅርን ከስሼ እስካበቃ በጥሞና ሲያደምጠኝ ቆየና  እንደጭረስኩ  ድንግገት ተከስቶ ••• የፈለገ ቢሆን ማታ አግኝተኻት ጥዋት አፈቀርኩሽ ! የኔ ሁኚ ስትላት ማመን ቢከብዳት ጭራሽ ሹፈት እና ስላቅ ቢመስላት በሷ አይፈረድም። አንተም አሁን ውስጥህ የተቀጣጠለው ስሜት በውሃ የሚጠፋ ግዚያዊ እሳት ይሁን ምንም የማያጠፋው እውነተኛ ፍቅር ለመለየት ግዜ ያስፈልግሀል። ምን አጣደፈህ•••? እውነቷን ነው እኮ ቃል •••በጣም ተጣደፍክ እኮ! ቆይ ያንተ ካላት የት ትሄዳለች•••? ተረጋጋ ኤፊ ተረጋጋ •••እያለ ሲሞግተኝ ጆሮዬን አልይዘው አልደፍነው ነገር ንግግሩ  ከውስጤ እንጂ ከደጅ አይደለምና ተቸገርኩ። አይ ቃል እሷ ጨቀጨከኝ ትላለች ። እኔ ኤፍሬም አንድ ሆኜ ሳለ እኩል ሁለት ቦታ ሰንጥቃ ከራሴ ጋር እያጨቃጨቀችኝ እንደሆነ አንድ ቀን ይገባት ይሆናል እያልኩ ባጃጄን በር ላይ አቁሜ ገባሁና ፍራሼ ላይ ተጠቅልዬ ተኛሁ። እኔና ቃል ከሷ ካልመጣና ግድ ካልሆነብኝ በስተቀር በስተቀር በየቀኑ አገኛታለሁ። አብረን የተወሰነ ሰአት አሳልፈን እንለያያለን። ከዛች ቀን በኋላ በየቀኑ ሁሌም ባገኘኋት ቁጥር •••እንደማፈቅራት፣ ቀሪ ህይወቴን በሙሉ ከሷ መለየት እሷን ማጣት እንደማልፈልግ ስልነግራት የመሸም የነጋም ቀን የለም።የሷ መልሶች ግን  እጥር፣ ቁጥብ ያሉ ናቸው። ቃልዬ የውስጧን ስሜት ዘክዝካ በግልፅ የማትናገር ልጅ ነች ። ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከአንደበቷ ይልቅ ሁኔታዋ  አስተያየት እና ስሜቷ ነበር የኔ እንደሆነች የሚነግረኝ። የኔ ፍቅር ስላት ያንተ አይደለሁም የእናት እና የአባቴ ነኝ ማለቷን ትታ ወዬ ኤፍዬ ማለት የጀመረችባትን ቀን መቼም አረሳትም ። እንደዛ ማለት ከጀመረች ሁለት ሳምንት ሆናት። ቢሆንም የፍቅር ጥያቄህን ተቀብያለሁ ፣ ያንተ ሆኛለሁ፣ ብላ በአንደበቷ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ። በቃ ያንን መስማት እና ማረጋገጥ ሁሌም እፈልጋለሁ። ቃልዬ አውቃለሁ የኔ ነሽ ግን ከአንደበትሽ መስማት እፈልጋለሁ እባክሽ ንገሪኝና ልቤን አሳርፊያት ስላት ••• "እንዴ ኤፍዬ እቺ ልብህ ዛሬም እየዘለለች ነው  እንዴ ኪኪኪኪኪ" በቃ ትስቃለች ። እኔን እያስጨነቀች መሳቋ ያናድደኝ እና እንደማኩረፍ እላለሁ። ያኔ መለስ ትልና••• "እሺ ኤፍሬሜ እንድነግርህ ከፈለክ ደግመህ ጠይቀኝ?" "ምንድን ነው እምጠይቅሽ?" "በቃ የባለፈው ጥያቄህ ግዜ ስላለፈበት አሁን ያለህን ስሜት ትክክለኛውን በደንብ ንገረኝና ድጋሚ ጠይቀኝ !" ትለኛለች። የልቤን ያንጀቴን ፍቅርና መውደዴን ፣ ስስይና ናፍቆቴን ሁሉ አንድ ባንድ ስነግራት ምስጥ ብላ ስታደምጠኝ ትቆይና ••• "እ ንገሪኛ •••?" ስላት። " አይ  ኤፍዬ•••••" ትልና ያን ፍልቅልቅ ሳቋን በረጅሙ ትለቀዋለች !። ወንዝ እያሳሳቀ ይወስዳል እንዲሉ እሷ እየሳቀች እኔ አበቃልኝ። አይደለም ገንዘብ እና ጉልበቴን ፣ አይደለም ሀሳብ እና ማንነቴን ነፍሴን እስከመስጠት የምሳሳላት የልቤ ንግስት ሆና አረፈችው። እሷ አጠገቤ ስትኖር እና ሳትኖር ያለኝ ማንነት ተራራቀ። ሲላት ብዝት ትልልኝና በፈለኳት ሰአት ሁሉ አገኛታለሁ። ሲላት ጥፍት ፣ ድርግም ፣ ስልካንም ጥርቅም ታደርገውና ነፍሴን በናፍቆት ሲቃ ታዋትታታለች ።ከሁሉም በተለየ ሁኔታ እኔ አጠገብ ሆና የማታናግረው አንድ ስልክ ናላዬን ያዞረው ጀምሯል። ማነው•••?  ምንድን ነው? ለምን እንደሌሎቹ ስልኮች አጠገቤ ቁጭ ብለሽ አታናግሪም ብያት አላውቅም ። ልላትም አልፈልግም። ምክንያቱም ቃልዬ ጨቅጫቃ ወንድ አትወድም። እሷ ምንም ታድርግ እኔ ውስጥ ያለው ፍቅር  ሀይሉን እየጨመረ ፣ አጠገቤ ስትኖር በፍቅር እያሰከረ፣ ሳትኖር በናፍቆት ልብና አንጀቴን እየቦረቦረ ••••ፍቅር በዘፈን ይብስ እንደሁ እንጂ ላይቀንስ ላይወጣ ነገር••• ብክን ••• ብክንክን ፣ ብትን••• ብትንትን ያደርጋል ወይ መውደድ••••?  ያደርጋል ወይ ፍቅር የሚል ዘፈን ••• በየመንገዱ ያዘፍነኝ ጀመር ... በቃ ከሷ ውጪ ማሰብ፣ ከሷ ውጪ ማውራት፣ እሷ ጋር ካልሆነ ማንም ጋር መሄድ ከማንም ጋር መዋል አስጠላኝ።እሷን ለማግኘት ስል የማታ ስራዬን ወደ ቀን ቀየርኩት። ለስራ ስወጣ የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኔ ባጃጅ ላይ በኮንትራትም በመደበኛው ሂሳብም ወደፈለገበት አቅጣጫ ለመሄድ የኔን ባጃጅ  የሚጠቀም ማንኛውንም ግለሰብ በእኩል አይን ማየት ቢኖርብኝም ወደነቃል ዩንቨርስቲ አቅጣጫ የሚሄድ ተሳፋሪ ግን ለኔ ንጉስ ነው። በኮንትራት ሂሳብ ከሆነ ከየትኛውም የድሬ ዳዋ ሰፈር ወደ ግቢ አቅጣጫ ለሚሄድ ሰው ግን ሂሰቤ ቅናሽ ነው። እዛ ሄጄ ቃልን ባላገኛት እንኳን እዛ አከባቢ ደርሼ ያለችበትን ግቢ አይቼ መመለስ ልዩ ደስታ ይሰጠኛል። የሚያስተውለኝ ተሳፋሪ የለም እንጂ ቢኖር  ወደ ግቢ ስሄድ የማሳየው ፈገግታ፣ ተሳፋሪውን የማጫውተው ጫወታ፣ባጄጅ ውስጥ የምከፍተው ሙዚቃም ፣ የማስከፍለው ሂሳብም ከሌላው ይለያል። እስካሁን አላጋጠመኝም እንጂ አንድ ቀን ወደ ግቢ ወይም ወደዩንቨርስቲው አከባቢ ያደረስኩት ያው ሰው በሌላ ግዜ  ሌላ ቦታ እንዳደርሰው ቢሳፈር••••" ሹፌር ምነው ባለፈው ስትስቅ ስትጫወት አልነበር እንዴ ዛሬ አኩርፈሀል በሰላም ነው•••? ችግር አለ እንዴ•••? "  ብሎ መጠየቁ የማይቀር ነው። የምን ችግር እንዲህ ያደረገኝ ፍቅር ነው እለው ይሆን ? የጠየቀኝ የለም እንጂ እለዋለሁዋ! ቃልዬን እንዴት እደማፈቅራት ቀኑን ሙሉ ባወራ መች ይሰለቸኛል። ምናልባት የሚሰማኝ ካልሰለቸው በስተቀር እኔ አይሰለቸኝ። ነገር ግን አብሮኝ ለሚኖረውና በጣም ለምወደው ጓደኛዬ እስካሁን ስለቃልና ስለኔ ትንፍሽ  አላልኩም። ብዙ ግዜ በተለይ "  ኤፊ ምነው እንቅልፍ እንቢ አለህ እንዴ?" ብሎ ሲጠይቀኝ  ልነግረው ይዳዳኝና••• ገና ••••••" አንድ ቀን ሸኝቻት ስንሰነባበት  ፍቅር ሲያደናብረው አቅጣጫ በሳተው ከንፈሬ ከሳምኩት  ከግማሽ ከንፈሯ ውጪ እስካሁን  ምኗንም አልነካሁም" ብዬ እንደተናገርኩ  ••• " እና እስከዛሬ ከቃል ጋር ምንም አላደረጋችሁም ኤፊ ? ፈዘዝክ፣ ቀዘዝክ ፣ቀዘቀዝክ እያለ ወቀሳ አይሉት ሙገሳ፣ ምክር አይሉት መፈክር ••••  ብቻ •••••" ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንዲሉ የፍቅሬን ክብደት ሳይሆን የኔን ፈዛዛነት እያነሳ የሚያዥጎደጉድብኝን ያን ምላሱን  አስበውና እፈራለሁ። ይቅርብኝ  ቃልዬ እንዴት በፍቅር እንደነደፈችኝ •••? በዚች አጭር ግዜ ውስጥ ከምን ውስጥ አውጥታ ምን ውስጥ እንደከተተች እንኳን ለሱ ላብራራለት እና ላስረዳው ለራሴስ መች በቅጡ ገባኝ ! ይቅርብኝ !" እልና መናገሬን እተወዋለሁ።የውስጤን ትኩሳት ከራሴ ጋር ብቻ  እያወራሁ መታመሜን ቀጥያለሁ። አይ ቃልዬ እንዴት እንዴት ነው ያፈቀርከሽ ግን•••?  ሰው ለካ እንደዚህ በፍቅር ጨርቁን ጥሎ  ብን••• ብትን •••ብትንትን  ይላል። ግን ህመሙ ደስ ይላል።  እየታመሙ መደሰት ፣ እየተደሰቱ መታመም የሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው። ሀያ አምስት አመት ሙሉ ስኖር ይሄን ፍቅር አላውቀውም ። ....ክፍል ቶሎ11 ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍            
252
8
«የምትወደው ሰው እና አንተን የሚወድህ ሰው መቼም መቼም አንድ ዓይነት ሰው አይደሉም። ©Chuck Palahniuk SHARE||@tksa_tks
244
9
♥️ ተማሪዋ ♥️ .. 🌹...ክፍል 9...🌹 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . "ምንሽን ማለት•••? ኪኪኪኪ ••••ምኔን ማወቅ ፈለክ •••? እርስ በርስ ፣ ባህሪ ለባህሪ እንተዋወቅ ነው የምልህ!" "አቦ ታድያ እኔ አውቄሻለሁ በቃኝ  አልኩሽ አይደል እንዴ•••ከዚህ በላይ አልፈልግም ••••ነው አንቺ እኔን አላወቅሽኝም!" "አዎ!" "አዎ ማለት•••?" "እንዴ በአንድ ምሽት ውስጥ ስድስት አይነት ሰው ሆነህብኝ እንዴት ብዬ ነው የማውቅህ•••?" "ምናልሽ ቃል••••? ስድስት አይነት እኔ ስድስት አይነት ሰው ሆንኩብሽ የምርሽን ነው•••? " እንደውም ቀንሼልህ ነው?" "ሀዬ ይሁንልሽ እሺ •••• እና ከስድስቱ አይነት የትኛው ተመቸሽ?" "ኪኪኪኪ•••• ጨወነትህ ብቻ !" "በቃ በጨዋነቴ ቀጥላለሁዋ ምን ችግር አለው!" "ሌሎቹንስ እንደምትተዋቸው በምን አውቃለሁ ለምሳሌ ጨቅጫቃነትህን •••••?ኪኪኪኪኪ•••!" "ቃልዬ ሙች ጨቅጫቃ አይደለሁም!" "አሁን ምን እያደረክ ነው•••?" "አሁንማ ከቃል ኪዳን ጋር ቁርስ እየበላሁና እያወራኋት ነዋ ሀይ !" "ሌላስ•••?" "ሌላ ምን•••?" " እየተጨቃጨክ መሆኑ አልታወቀህም አደል•••? ውጋት ነገር ነህ !፣ ውጋት ሆንክብኝኮ!" "የምን ውጋት•••?" "የጎን ውጋት!" "ቃልዬ ሙች እኔ አልነካሁሽም ! ምናልባት ለሊት ስትከፋፈቺ ብርድ መቶሽ ይሆናል እንጂ እኔ መች ደረስኩብሽ•••? ስላት ያንን ሳቋን ደገመችው። ከቃልኪደን ጀርባ የጠረጴዛ መወልወያ ጨርቅ ይዛ ግርግዳውን ተደግፋ የቆመችው አስተናጋጅ የቃል ኪዳን ሳቅ ተጋባባት መሰለኝ ቃልንም እኔንም እያየች ትስቃለች። ቃልም እያረፈች ስትስቅ ቆየች። እኔም በልቤ  " በጭቅጭቅ ከልቧ የምትስቅ ሴት አንቺን አየሁ ቃልዬ !" እያልኩ ሳቋን እስከምትጨርስ ጠበኳት•••• " እህም አይ ኤፍሬሜ ••••ቆይ  ተከፋፍተሽ ማለት ምን ማለት ነው ግን •••? እሚከፍት ይክፈትህና!" "አቦ ካንቺ በላይ የሚከፍተኝ ኬት ይመጣል •••? ልቤንም አፌንም ከፋፍተሽው ይሄው ጨቅጫቃ እስከምባል እያወራሁ አይደል እንዴ!" "እሺ ያንተ አፍህ ነው የተከፈተው የኔስ•••?" "ያልተከፈተውን ብጠይቂኝ አይቀልም!" "እስቲ ቃል ኪዳን ሙች በለኝ•••!" "አልልም!" "እና ኤፊ•••?" "እና ምን•••? " አየኸኝ••••?" "መች•••? አሁን•••? ምንሽን•••? " ተገላልጠሽ ነበር አላልክም ያኔ ነዋ!" "አዎን በደንብ ነዋ ያየሁሽ!" "እኮ ምኔን•••?" "አቦ ምንሽን ልበልሽ•••? ያው ወንድ ልጅ የሚያየውን ነዋ!" "ወንድ ልጅ የሚያየው የተለየ ቦታ አለ እንዴ •••?" "ያንን የማታውቅ ሴትስ አለች እንዴ ቃልዬ •••? ያንን ባታ ስለምታውቁማ ነው •••፣ ብቻ ይቅር •••ለምንድን ነው ሌላ ነገር እያስወራሽኝ ዋናውን ጥያቄ የምታረሻሽኝ ቃልዬ•••? "ብዙ ነገር ስላየኽ ስንቱን እነግራታለሁ ብለህ ነው አደል እሺ ምኔን ነው ያላየኸው•••? ስትለኝ እኔንም ሳቅ አፈነኝ። " ካካካ •••ያላየሁትማ ውስጥ ያሉትን ብቻ ነው!" "ውስጥ ያሉትን ማለት•••? " ጨጓራ፣ ሳንባ ፣ ልብ ገለመሌሽን ነዋ?" ስላት ትን እስኪላት ሳቀች። እኔ ልቤ ተሰቅሏል። እሷ እያስለፈለፈችኝ ትስቃለች ። በሀይል ስትስቅ አፏ ውስጥ አየዃት እና •••• "እሄው የቀሩኝንም አሁን አየዃቸው !" አልኳት! "ሂሂሂሂ ምኖቹን ?" "ሳንባና ጨጓራሽን እንዲህ እየሳቅሽ ላይታዩ ነው እንዴ አልታይ ያለኝ ልብሽ ብቻ ነው! እሱን ለምን ደበቅሽው ቃልዬ?" "እሱ ቁልፍ ነው፣ ለመክፈት ብዙ ይቀርሀል ሞክር!" "ምን ልሞክር ቃልዬ?" "ሰው የሚልህን ለመስማት ሞክር!" "እሺ ሰማለሁ እና ምን አልሽኝ•••?" "አሁን ግዜው አይደለም ትንሽ እንተያይ •••?" "ምንም የቀረኝ የለም  ሁሉ ነገርሽን አይቼዋለሁ አልኩሽ እኮ ማሬ!" " ኪኪኪ•••• ሳይፈቀድልህ  ማየትህ ብልግና ነው እሺ ባለጌ!" እያለችኝ እጇን ለመታጠብ ስትሄድ ተነስቼ እየተከተልኳት •••"ብልግና ከተባለም ያሳየችውም ያየውም ነው ባለጌ በተለይ ያሳየችው!" አልኳት። "አሁን ትሸኘኛለህ ወይስ ሌላ ባጃጅ ይዤ ልሂድ•••?" "በቃ ልትሄጂ ነው ቃልዬ ምናለበት የሰቀልሻትን ልቤን አውርደሻት ብትሄጂ!" "ተሰቅላ ትቆይ እኔ እስካወርዳት ማንም እንዳያወርዳት እሺ!" "እሺ ቃልዬ ካልሽ ይሁን!" ብያት ወደ ግቢ መጓዝ ጀመርን። መለያየቱ ቅር እያለች ስልክ ቁጥሯን እንድትነግረኝ ጠየካት። ነገረችኝ። ስደውል ዝግ ነው ይላል። "ዝግ ነው እንዴ ቃልዬ!" "አዎ ማታ ነው እኮ የዘጋሁት ገና አንተን ሳላገኝህ !" "ለምን•••?" "ሌላ ግዜ ነግርሀለሁ አሁን ግቢ እየደረስን እኮ ነው!" "ሌላ ግዜ ማለት •••? ዛሬ ማታ አንገናኝም እንዴ•••?" "የጎን ውጋት ማለት ይሄ አደል ታድያ ••••? ውጋት ነገር ነህ በል ቻው አመሰግናለሁ እሺ ኤፊዬ እንደዋወላለን ቻው!" ብላ ጉንጯን ከጉንጬ ጋር አላትማ ስትለየኝ ከመቅፅፈት ነበር  የብቸኝነት ናዳ ሲናድብኝ የታወቀኝ። ግቢ ገብታ ከአይኔ እስክትሰወር ባጉንጯ ዳብሳው የሄደችውን ጉንጬን በመዳፌ ደግፌ ስመለከታት እሷም በተወሰነ ርቀት ልዩነት ዘወር እያለች ታየኝ ነበር። የማታዋ ቅፅበት ከቃል ጋር ያሳለፍኳት ለሊት ደግማ ደጋግማ  እንድትከሰት እየተመኘሁ ባጄጄን አዙሬ መመለስ ጀመርኩ። አንድ ነገር ትዝታ ለመሆን ከተከሰተ እስኪታወስበት ያለው እድሜ ምን ያህል መሆን እንዳለበት አላውቅም። የኔ እና የቃል ቆይታ  ግን በትዝታ ይሁን በትውስታ እኔን ለመናጥ እድሜና ቆይታ አላሻውም ነበር። ወድያው ፣ ከቃል ጋን ያሳለፍኳትን ፣ ያቺን ቅፅበት እያስታወስኩ ፣  ያለችኝን ነገር በሙሉ ደግሜ ደግሜ እያደመጥኩ ፣ መጓዝ ጀመርኩ.. ቸኮልክ !" አለች ቃልዬ! ...ቆይ እኔ ምን ላድርግ•••? የቸኮልኩት እኔ ነኝ እንዴ•••? እኔ አይደለሁም እኮ •••የቸኮለው ፍቅር ነው። ፍቅር ነው በሰአታት ውስጥ ሁሉ ነገሬን ለመቆጣጠር የተጣደፈው! ፣ ፍቅር ነው እኔን ባንቺ ፍቅር ለማንበርከክ፣ ከነሙሉ ትጥቁ ከነሙሉ ወታደሩ የወረረኝ። ተው እንጂ ፍቅት ምነው ተጣደፍክ•••? .ገና መተዋወቃችን አይደለም እንዴ•••? ምነው አድፍጦ ሲጠባበው እንደነበረ ጠላት አጋጣሚውን ስታገኝ ዘለህ አናቴ ላይ ፊጥ ለማለት ተንገበገብክ•••? ስንቶቹ  አመት ሁለት አመት ፣ አምስት አመት እየተዋወቁ ፣ እየተቀራረቡ ፍቅር በደረሱበት የማይደርስባቸው አሉ አይደል እንዴ•••? ምነው እኔን የመተያያ እና የመቀራረቢያ ግዜ እንኳን ሳትሰጠኝ ባንድ ቅፅበት እጅ ወደላይ ልታስብለኝ ተራሯጥክ •••? ብዬ እንድነግረው እና እንዲረጋጋ  እንኳን የምናገርበት የማስብበት  እድል ሰጥቶኛል እንዴ ቃልዬ•••? ገና እንዳየሁሽ እኮ ነው መጥቶ የተከመረብኝ። እኔ ፍቅር ላንተ አዲስ ነኝና እስክንተዋወቅ ትንሽ ግዜ ልስጥህ ብሎኛል እንዴ••? ጭራሽ ውጋት ሆንክብኝ አለችኝ  አይደል ቃሌ•••? እኔ እሷ ላይ የጎን ውጋት የሆንኩት ፍቅር የተባለ ነገር የልብ ውጋት ሆኖብኝ እንደሆነ እንዴት ላስረዳት•••? . . . . ....ቶሎ ቶሎ እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ቤተሰብ ♥️👍
326
10
አንዳንድ ሚስቶች ግን 🥵😂
አንዳንድ ሚስቶች ግን 🥵😂
386
11
♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 8...🌹 Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . "ለዚህ ነው ስነርቺኝ ያደርሽው !" "ኪኪኪኪ እሱን አልክድም አርፌ እንደማልተኛ ታላቅ እህቴ ብዙ ግዜ ትነግረኝ ነበር" "ሌላስ ማንም ነግሮሽ አያውቅም•••?" "ሌላ ማለት•••?" "ሌላ ማለት ••••?ሌላ ማለት••••? እንደኔ ባለ ፍሬ የሆነ ነዋ!" "ካካካካካካ••••ታናሽ ወንድም ነው ያለኝ ግን አብሮኝ ተኝቶ አያውቅም!" ስትለኝ •••" በለው በለው እቺ ልጅ ድንግል ነች ማለት ነው•••? እሄ ማለት  ወንድ አላውቅም ማለት አይደል•••?  ነው እንጂ !  ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል ፣ ገና ብዙ ስራ አለብህ ኤፍዬ!" አልኩ በልሆሳስ አጎንብሼ ጫማዬን እያጠለኩ። "እ••? •ምን አልክ ኤፊ•••?" "ወንድምሽ ካንቺ ጋር ያልተኛው ፈጣሪ ሲጠብቀው ነው፣ በእውነት  እኔ ያልቻልኩትን እርግጫሽን አንድ ፍሬ ልጅ በምን አቅሙ ይቋቋመዋል!" "ኪኪኪኪ ወሬ አለብህ ለማንኛውም  ወንበሩ ላይ ቁጭ ብዬ ፀጉሬን ሳስተካክል ቁልፍና ቦርሳህን ትራስህ ስር አድርጌልሀለሁ ፣ አገኘኸው••••? " አለችኝ ሁለት እጆቿን ሽቅብ ሰቅላ እየተንጠራራች ። የጇን ወደላይ መወጠር ተከትለው እኔ ላይ የተቀሰሩትን ጡቶቿን ስመለከት ተኩሰው የሚመቱኝ ይመስል ልቤ ፍርስ ስትል ታወቀኝ። "ጉድህ ፈለ ኤፍዬ ፍቅር መረቡን ጥሎ እያጠመደህ ነው! "አልኩ በልቤ አይኖቼን ጡትና ከጡቷ ስር ባለው ቀጭን ወገቧ ላይ እያንከራተትኩ ሳያት የተሰማኝ ስሜት ከዚህ ቀደም ተሰምቶኝ አያውቅም።  የመረታት ፍርሀት ወረረኝ። " አንስተኸዋል አደል•••? አለችኝ ደግማ ቁልፍ እና ቦርሳውን ወዳስቀመጠችበት እየተመለከተች። "አዎ አንስቼዋለሁቆንጆ አመሰግናለሁ!" "ኧረ ባክህ ••••! ያንተ ቆንጆማ አይደለሁም!" "እና የማን ነሽ•••?" "ኪኪኪኪ ለግዜው የማንም አይደለሁም የእናት ያአባቴ ብቻ!" "እስከመቼ•••?" "እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም!" "እኔ ግን አውቃለሁ!" "ምንድን ነው የምታውቀው•••? እስከመቼ እንደሆነ•••?" "አዎ የኔ እስክትሆኚ ነው!" "እ. ን. ዴ. ኪኪኪኪ ••• ያንተ እንደምሆን በምን አወቅክ•••? " ውስጤ ነገረኝ!" "ታድያ የኔስ ውስጥ ለምን አልነገረኝም•••?" "ነግሮሻል ባክሽ ለመደበቅ እየሞከርሽ ነው!" "ተው ባክህ እኔ እስካሁን ምንም የሰማሁት የውስጥም የውጪም ድምፅ የለም!" "እሄው እኔ እየነገርኩሽ አይደል እንዴ•••?" "ምን ብለህ•••?" "የኔ ነሽ ብዬ ነዋ!" "ኪኪኪኪ ጭራሽ ••••ከየኔ ነሽ የኔ ሁኚ አይቀድምም•••?" "እሺ የኔ ሁኚ!" "ለምን•••?" "እንዴ እንዴት ለምን ስለወደድኩሽ ነዋ!" "ኪኪኪ ባንድ ለሊት ትናንት ማታ እኮ ደስ አልሽኝ ብቻ ነበር ያልከው!" "ደስ ያላለ ነገር ይወደዳል እንዴ ቃልዬ ደስ ስላልሽኝ እማ ነው የወደድኩሽ!" "ትንሽ አልቸኮልክም•••? "አዎ ቸኩያለሁ ምን ላድርግ ቃልዬ አሁን ተለይተሽኝ ወደ ግቢ ስትሄጂ አንዱ ላፍ የሚያደርግብኝ መስሎ ተሰማኝና ፈራሁ ለዛ ነው!" ። "ተው ባክህ••••ኪኪኪ•••እስከዛሬ አንዱ ላፍ ያላደረገኝ አንተ እየጠበከኝ ነበር እንዴ?" "አዎ እየጠበኩሽ ነበር ሁሉም እኮ የግራ ጎኑ ማን እንደሆነች ባያውቅም እየጠበቃት ነው የሚኖረው!" "ላፍ ያልተደረኩት ነው ያልኩህ ባክህ!" "ላፍ ያልተደረግሽው እማ ያው ፈጣሪ እኔ እስከማገኝሽ ድብቅ ክልል አድርጎልኝ ነዋ!" "እንደዛ ካመንክ ታድያ ታድያ አሁን ለምን ፈራህ!?" "ያው ሰውኛ አስተሳሰቤ ካየሁሽ በኋላ ሀያ አመት ሙሉ ያስቀመጠልኝን በሀያ ደቂቃ የማጣሽ እየመሰለኝ ነዋ!" "ለዚህ ነዋ ሁሉ ነገርህ ሱሪ ባንገት የሆነው!" "አቦ ይሄን ያዲስ አበቤዎች ተረትሽን ተይልና ወደዛ የምን ሱሪ ባንገት ነው ሱሪ እማ በእግር እንጂ በአንገት ላይ እንዴት ሆኖ ይሆናል•••? የማይሆነውን!" "ኪኪኪ አታላግጥ እሺ ! ምን እንዳልኩ በደንብ ታውቀዋለህ ሁሉ ነገርህ ጥድፍድፍ አለኮ!" "ለምሳሌ ምን••?" "ምነው ከተገናኘን በኋላ የሆነው ሁሉ በዚች አጭር ግዜ እንዲህ የሚሆን ይመስላል!" "ምን ሆነና ነው•••?  አብረን እራት ስለ በላን•••?  አብረን አንድ ክፍል  ውስጥ ስላደርን•••?" "ምነው ከዛ በላይም ፈልገህ ነበር•••?" "አቦ ብፈልግማ ማን ከልክሎኝ •••? አንቺ•••?" "በነገራችን ላይ ኤፍዬ ጭዋነትህን ወድጄዋለሁ፣ አመሰግናለሁ እሺ ኤፍዬ!" እያለች ጠጋ ብላ ጉንጬን ሳም ስታደርገኝ ከንፈሬን  አጣብቃ ምላሴን የወሰደችው ይመስል መልስ መስጠት ተስኖኝ ፍዝዝ ድንግዝ ብዬ ሳያት ••• "ተነስ እንውጣ ባክህ ታለምጣለህ አይደል •••? ለምንድን ነው እንደዚህ የምታየኝ•••? ተነስ እንውጣ!" አለችኝ።ሁኔታዬ ግን ማልመጥ ሳይሆን እውነት ነበር።  ለሷ እያለመጥኩ መስሎ ስለታያት  ደስ ቢለኝም ስትስመኝ የተሰማኝ ስሜት ግን የተለየ ነበር እራሴን ታዘብኩት። እሷ ከፊት እኔ ከጀርባዋ ተከታትለን ከክፍሉ ወጣን። ማታ ያየሁት የቃል ውበት እንደጥዋቷ ፀሀይ ቀስ እያለ የሚፈልቅ፣ ቀስ እያለ የሚሞቅ፣ ቀስ እያለ የሚፈካ ይመስል አብሪያት በቆየሁ ቁጥር ይበልጥ ውብ እየሆነችብኝ ግራ ተጋባሁ ፣ ምናልባት መውደዴ እየጨመረ፣ እሷን የማይበት መነፅርም እየተቀየረ ይሆን•••? ዛሬውኑ አሁኑኑ የኔ ትሁን አትሁን ቁርጤን ማወቅ ፈለኩ። ቁርስ አብረን እየበላን ነው። "ቃልዬ!" "ወዬ ኤፊ!" "ቆይ አንድ ወንድ የፍቅር ጥያቄ ለማንሳት ፣ ማለት•••የወደዳትን የኔ ሁኚ ብሎ ለመጠየቅ ቸኮልክ የማይባለው ከተዋወቃት ከስንት ቀን በኋላ ሲጠይቅ ነው•••?" "ኪኪኪኪ እኔ እንጃ!" "ካላወቅሽ ታድያ ለምን ቸኮልክ አልሽኝ•••?" "ስለቸኮልክ!" "እባክሽ አትቀልጂ ቃሌ!" "ኤፊ ሙት እየቀለድኩ አይደለም!" "ለማንኛውም እኔ የልቤን ተናዝዣለሁ አንቺ የማሰቢያ ግዜ ከፈለግሽ እሺ!" "እእእእእ በችኮላ የተሰነዘረ ጥያቄ ስለሆነ እንዳልሰማሁህ አስበው፣ ለኔ ብቻ ሳይሆን ላንተም የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግሀል!" "ምንድን ነው የማስበው •••? የምን ግዜ•••?" "እኔን የማወቂያ!" "ከዚህ በላይ ላውቅሽ አልፈልግም!" "እኔ ግን እፈልጋለሁ!" "እሺ የናትሽ ስም ማነው•••?  ስላት ሳቋን ለቀቀችው• "ምን ላድርግ ቃልዬ ስምሽን ከነአባትሽ ከመታወቂያሽ ላይ አውቂያለሁ፣ የቀረኝ የናት ስም ነው ብዬ እኮ ነው!" "እህህ አየ አንተ እና የቤተሰብ ስም ማወቅ ታድያ እኔን ማወቅ ማለት ነው ••••? እ ኤፊ የምር እንደዛ ነው የምታስበው•••?" "ሀይ••••! ታድያ ምንሽን እንዳውቀው ነው የምትፈልጊው? ክፍል 9 ቶሎ እንዲለቀቅ አንብበው ሲጨርሱ  Like ❤
397
12
ኧረ ዝናቡ ግን ፍቅር አበዛብኝኮ🥹🫠😁
372
13
​ከማንም ጋር አትወዳደሪ የትላንት ማንነትሽን ማሸነፍ ከቻልሽ አንቺ ቀድመሻል 😊
441
14
♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 7...🌹 ምንጭ =- ከደራሲያን አለም ✍ ሴቶች በተለይ በመጀመሪያው ቀን በአንደበታቸው እሺ ከማለት ይልቅ በአካላዊ እንቅስቃሴ ፍቃዳቸውን መግለፅ ይቀናቸዋል። ካካሆነም ወንዱ ገፋ አድርጎ እንዲመጣ ይፈልጋሉ። አየህ ክብር የሚባል ነገር አለ።ዛሬውኑ አግኝተሀት  ካንተ ጋር አንሶላ ለመጋፈፍ ፍቃደኝነቷን በአንደበቷ ትገልፅልኛለች ብለህ ከጠበቅክ ሞኝ ነህ። ሴትን ልጅ አታውቃትም ማለት ነው። ምክንያቱም ተገናኝተን ሀያ አራት ሰአት ባልሞላ ግዜ ውስጥ ጭኔን ብከፍትለት •••ክብሬን የማልጠብቅ ርካሽ ሴት አድርጎ ያስበኛል፣ ይንቀኛል፣ በየአጋጣሚው ካገኘሁት ወንድ ጋር በቀላሉ የምጋደም  ሴት አስርጎ ይቆጥረኛል ብላ ትፈራለች። ስለዚህ ካንተ ጋር ወሲብ መፈፀም ብትፈልግ እንኳን ይህ ፍርሀቷ ሳትወድ በግዷ እንድትግደረደር ያደርጋታል። በርግጠኝነት በቀላሉ እሺ ብትልህ አንተም እንደዛ ማሰብህ የማይቀር ነው። ወደድክም ጠላህም የፈራችው ወይ ያልፈለገችው ማድረጉን ሳይሆን እንዲዚህ ማሰብህን ነው። ስለዚህ በአንደበቷ አይሆንም አይደረግም ትልሀለች። ያላት አማራጭ  አንተ ሀላፊነቱን ወስደህ ያሻህን እንድታደርግ ላንተ መተው ነው። እንደዚህ እየተፈታተነችህ ዝም ካልካት ደግሞ ••••ምኑ ቀዝቃዛ ነው ባካችሁ. ፣ በረዶ !  ፣ አፍ ብቻ ነው እንዴ ለካ ያለው፣ ይሄማ አይደለም በውስጥ እግር እና በጣት በክሬንም የሚነሳ አይመስልም ትልሀለች። ነግቶ ከተለያያችሁ በኋላ አይደለም ድጋሚ ልታገኝህ ኤፍሬም ተብሎ የሚጠራ ወንድ በሙሉ የወንድ አልጫ መስሎ ነው የሚታያት። ያንተስ ይሁን ለምን ባንተ ስም የሚጠሩትን ወንዶች ታስንቃለህ•••? ደሞ ወድጃታለሁ የኔ እንድትሆን እፈልጋለሁ ትላለህ ዛሬ እንዲህ የተኛች መስላ እየተገላለጠችና እየነካካችህ ወንድነትህን ካላሰየዃት ዘወር ብላ እንደማታይህ አታውቅም•••? በርግጠኝነት አንዴ ደፈር ብለህ ብትጀምራት እንዴት እንደዚህ ታደርጋለህም ተውም አትልህም። ብትልህም ለይስሙላ ስለሆነ•••ምን ላድርግ ቃልዬ መብራቱ አይጥፋ ያልሽው አንቺ ነሽ ፣ መብራት ካልጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም እኔ ሳልተኛ አንቺ ተኝተሽ መገላበጥ ሳይሆን መከረባበት ጀመርሽ ፣ ወደ ግራ. ስዞር ወደ ግራ ወደ ቀኝ ስዞር ወደቀኝ እየተከረባበሽ ስትገላለጪ ሳልተኛ አይኔን ጨፍኜ መቆየት ደከመኝና አየሁሽ ፣ አማትቤ ጣራው ላይ አፈጠጥኩና አንቺን ላለማየት ሞከርኩ ፣ ወድያው እግሮችሽን እያፈራረቅሽ የማይሆን ቦታ ትነካኪኝ ጀመር ፣ አልቻልኩም ከዛ በኋላ እንዴት ዞሬ አንቺ ጋር እንደመጣሁ እንዴት እንዳደረግን ትዝ አይለኝም አንቺም እስክጨርስ ጠብቀሽ ምን እያደረክ ነው ማለትሽ ልክ ነው ቃልዬ•••? እኔኮ ዝም ስትይ የተመቸሽ መስሎኝ ነው ትላታለህ ። በቃ አለቀ ጉደኛ ነህ ኤፊ ከማለት በስተቀር ምንም ክፉ ነገር አትናገርም። ተነስ ! ልብስህን ወለቅ ወለቅ አድርግና ብድግ አድርገህ አለሟን አሳያት። " አለኝ ። ሁለቱንም ሀሳብ እያፈራረቀ የሚነግረኝ ውስጤ ነው ። እውነት አሁን ደፈር ብዬ ብጀምር ዝም ትል ይሆን •••? ብዬ ሳስብ ያው መከረኛ ገረዥ የሚሰራ ጓደኛዬ እዛው የሚሰራበት ገራዥ መኪናውን ሊያስጠግን ከመጣ የአይሱዙ ሹፌር ሰማሁ ብሎ  የነገረኝ ነገር ትዝ አለኝ•••ሹፌሩ ሚስቱን ጋቢና ረዳቱን ከላይ ብርድ ላይ ጭኖ በለሊት እየተጓዘ ሽፍታ ያጋጥመዋል። ሽፍቶቹ የሚፈልጉትን ወስደው ብቻ አልሄዱም የሹፌሩን ሚስት አስገድደው ባሏ እያየ ከረዳቱ ጋር ወሲብ እንድትፈፅም ያደርጋሉ። ታድያ ሹፌሩ በሌላ ግዜ ይህን አጋጣሚ ለአንድ የቅርብ  ወዳጁ ሲያወራለት •••የገረመኝ ወሲብ ማድረጋቸው ሳይሆን የሚስቴ በርታ እያለች መነቃነቋ ነው!" አለው አለኝ። እና ቃል ኪዳንም አንዴ ከጀመርኩ በኋላ በርታ እያለችመነቃነቋ ነው!" አለው አለኝ። እና ቃል ኪዳንም አንዴ ከጀመርኩ በኋላ በርታ እያለች ትነቃነቅ ይሆን•••? እያልኩ ገና ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ጠጋ ስላት  ብንን አለችና ••••" ምነው ኤፊዬ እስካሁን አልተኛህም እንዴ •••?" አለች። አልጋ ልብሱን ጎትታ ከወገቧ በታች እየሸፈነች። ብስጭት ብዬ "ታድያ እንድተኛ ከፈለግሽ ምን ያበላቅጥሻል አርፈሽ አተኝም !" ልላት ምንም አልቀረኝም።  "ኧረ በለው ቆይ አንቺ ግን ዩንቨርስቲ የምትማሪው ካራቴ ነው እንዴ?"አልኳት። "የምን ካራቴ•••?" "እህህህ በንቅልፍ ልብሽ ቻይንኛ የመሰለ ቋንቋ እየለፈለፍሽ ስትፈራገጪ ነበርኮ፣ ፊኛዬን ብለሽ ልትገላግይኝ ነው እንዴ•••? ዘለሽ ፊኛዬን ፣ ዘለሽ ፊኛዬን ፣ ሌላ ቦታ አይታይሽም እንዴ•••? ማነች አኮላሽልኝ ብላ የላከችሽ•••?" ስላት••••ፈገግ አለችና •••"ይሄ ሳቅ ይደርልኝ ጥዋት እስቃለሁ፣ ና በቃ እሺ በዚህ ጋር ተኛ፣ ቆይ እንደውም እኔ በዛ ጋር ልሁንልህ !" አለችና  ትራሷን ይዛ ወደኔ በመምጣት አልጋ ልብሱን ተጠቅላላ ሁለት ጉልበቶቿን እንደሚሳኤል በእንብርቴ ትዩዩ ቀስራ በግርግዳው በኩል  ተኛችና •••" ተኛ በቃ ከፈለክ መብራቱንም አጥፋው!" አለችኝ ፈገግቷዋን አሳይታኝ ይኗን እየጨፈነች።  "ቀላል ተኛለሁ እንዴ አንቺም እዛው ከግርግዳው ጋር ተደባደቢ !"እልኳትና መብራቱን ደረገምኩት። ጥዋት ከረፋዱ ሶስት ሰአት አከባቢ ያለንበት ክፍል በሀይል ተንኳኳ!።"ማነው?"  አልኩ ከጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ በርግጌ በመነሳት። " እኔ ነኝ !" አለ የወንድ ድምፅ። ወደ ግራ ስዞር ቃል ኪዳን አልጋው ላይ የለችም። ወደቀኝ ስዞር ማታ ከኪሴ አውጥቼ ወንበሩ ላይ ያደረኩት ዋሌት ቦርሳዬ እና የባጃጄ ቁልፍ ወንበሩ ላይ የለም.. የጉድ ቀን አይመሽም ይባል ነበር ድሮ የጉድ ቀን አይነጋም ሊሆን ነው ዘንድሮ!" እያልኩ ተፈናጥሬ ከአልጋው ላይ በመውረድ በሩን ከፈትኩና ••• •" ምን ነበር•••?"አልኩት።"ሰላም አደርክ•••? አንሶላ አጣቢዋ እኮ ባንኳኳ ባንኳኳ አባ ከና የሚለኝ አጣሁ ስትለኝ ነው እኔ የመጣሁት ። ሶስት ሰአት ሊሞላኮ ነው! ያው እኩለ ለሊት ካለፈ እንደገባችሁ ነግረውኛል፣ ቢሆንም አንሶላው መታጠብ አለበት፣ ለዛ ነው የቀሰቀስናችሁ ይቅርታ!" አለኝ። "እሺ ችግር የለውም!" ብዬው  ለራሴ" እድሜ ለቃል ኪዳን  መች ውስጥ ገብተን ተኛን እና ነው የምታጥቡት?"  እያልኩ ወደ አልጋው ተመለስኩና ከአልጋው ላይ አንሶላውን ገፍፌ ሳነሳው ዋሌት ቦርሳዬና ቁልፉ ከኔው ትራስ ስር ወደ  መሬት ወደቁ። አመዱ ቡን ያለው ፊቴ በፈገግታ እንደተሞላ አንሶላውን ሰጥቼው ስመለስ የመታጠቢያ ቤቱን የበር እጀታ ቁልቀል ዘወር አድርጌ ገፋ ሳደርገው ከውስጥ ተከርችሟል። "አቦ በዚች ሰከንድ ውስጥ ስንት ቦታ ሄድኩ፣ ስንቱን አሰብኩት በፈጣሪ!" እያልኩ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ብዙም ሳትቆይ ቃልኪዳን እርጥብ ፊቷን በፎጣ እያደራረቀች ወጣች። "ደና አደርክ ኤፊ ተነሳህ እንዴ?" "እህህህህ አዎ ተነስቻለሁ ግን ደና አላደርኩም!" "ኪኪኪ•••ምነው ጥሩ ህልም አላየህም •••? ነው ቅዥቱ አላስተኛ አለህ•••? " ተይ ባክሽ ••••! ህልምም ቅዠትም የሚኖረው ሲ'ተኛ እኮ ነው ስደበድቢኝ አድረሽ ቤት በኩል ልቃዥ? አሁን እንደወጣሁ ሃኪም ቤት መሄድ አለብኝ!" "እንዴ ለምን•••?" "ሁለቱም ፍሬዎቼ ጤነኛ እንደሆኑ ማረጋገጥ አለብኝ!" "እንዴ ሁለት ፍሬ ነው እንዴ ያለህ? አንድ አይበቃም ሁለት ምን ያደርጋል?".. ክፍል 8 ቶሎ እንዲለቀቅ  Like ❤
517
15
♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 6...🌹 ባጭሩ እኔ ኤፍሬም ሴት ልጅ ፈልጋና ፈቅዳ ካልሆነ በስተቀር እንኳንስ ገላዋን የቀሚሷን ጫፍም መንካት አልፈልግም ! •••ይህንን ፈርተሽ ከሆነ ከወንበሩ ላይ ንቅንቅ አልልም ያልሽው ስጋት አይግባሽ ። ይልቅ አሁን ተነሽና ገብተሽ ተኚ!" አልኳት። "ኪኪኪኪ ምን ውስጥ ነው የምገባው•••?" "አልጋ ስር!" "ሂድ ወደዛ ብሽቅ ! ለማንኛውም አንተ እንደዛ አስበኻል ማለቴ ሳይሆን ያው አለ አይደል•••"እያለች  ከወንበሩ ላይ ስትነሳ ••• " በቃ ልተኛበት ወሬ አልፈልግም!" አልኳት ኮስተር ብዬ። "ኧረባክህ  ማን ሲያስተኛህ ፣ገና እናወራለን፣  ደሞ አንጣው አንዱን ትራስ እኔ በዚህ በኩል ነው የምተኛው ፣ ከነ ልብሴ፣  ከላይ ነው የምተኛው ••••" አለችና ። በፈገግታ እያየችኝ አንዱን ትራስ በግርጌ በኩል አድርጋ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች። እኔ በራስጌ እሷ በግርጌ ከነልብሳችን ከላይ ተኛን። መብራቱን ላጠፋው ስል •••"ተወው ይሁን !" አለችኝ። "እንዳልሽ!"  አልኩና በጀርባዬ ተንጋለልኩ። "ኤፍ ተኛህ እንዴ?" "አልተኛሁም!" "ምነው ዝም አልክ ታድያ•••? " ተኝቼ!" "ኪኪኪኪኪ አድርቅ ! አድርቅ ነገር ነህ!" "እስካሁን ያደረቅኩትን ላርጥበው ስልሽ  እንቢ ያልሽው አንቺ አይደለሽ እንዴ•••? "  ልላት ብዬ ካፌ መለስኩት። ዝም አለች ፣ አተነፋፈሷም ተቀየረ፣  እንቅልፍ ወሰዳት። መተኛት የለም አዋራኝ እያለች ቀድማኝ ተኛች።ምስኪን ለዚቹ ነው ያ ሁሉ ጫጫታ አያልኩ ቀና ብዬ ሳያት  እጥፍጥፍ ብላ ተኝታለች። ትንሽ ቆይታ መዘረጋጋት ጀመረች። መጀመሪያ አንድ እግሯን እዛው አስቀርታ አንዱን ዘረጋችው። ተጀመረ አልኩ በልቤ። ትንሽ ቆይታ ሁለተኛውን ደገመችው•••ትንሽ ቆይታ እግሯን ከፈተችው። ትንሽ ቆይታ መገለባበጥ ጀመረች። እኔ እስካሁን ከቦታዬ ንቅንቅ አላልኩን እሷ ሶስት መቶ ስልሳ ድግሪ መሽከርከር ጀምራለች። በዚህ ሁኔታ እንቅልፌ እንኳንስ በዛ ሰአት በማግስቱ እራሱ የሚመጣ አይመስለኝም። ወደ ግራ ገልበጥ አልኩና አይኔን ገለጥ አድርጌ  ቁልቁል ስመለከት••••ከአንገቷ በገመድ ወርዳ ፣ ጡቶቿን በቪ ቅርፅ አስጎብኝታ፣ ከጉልበቷ በላይ የምትቀረው ፣ ፣ ከእንብርቷ ተስቦ ወገቧ ላይ የሚቃጠር ሁለት ተንጠልጣይ ገመድ ያላት፣  ቀይ ሮዝ አበባ ጣል ጣል ያለባት ደብዛዛ ነጭ ቀሚሷ፣  እሷ በተገላበጠች ቁጥር ተስባ ተስባ እምብርቷ ላይ ደርሳለች ፣ እግራ ተከፍቷል።  በጠይሙ ንፁህ እና ውብ ገላዋ ላይ በጭኖቿ መሀል ላይ ያረፈውን ደማቅ ቀይ ሽፏኗን ስመለከት እንደስጋቤት አንፖል አይኔ ላይ ተንቦገቦገብኝ። •••አይኔን ጨፈንኩ ፣ መልሼ ገለጥኩ፣ ከአጠቃላይ የአካል ክፍሌ አብዛኛውን ቦታ የሸፈነ ከባድ ንዝረት ነዘረኝ..!! ይቺ ልጅ ከራሴ ጋር ልታጣላኝ ነው ። እንደዛው ተኝቼ እሷን አለማየትም እሷን እያየሁ መቆየትም የማልወጣው አቀበት ሆነብኝ። ያለው አማራጭ መጀመሪያ እንደነበርኩት በጀርባዬ መንጋለል እና እንቅልፌ እስኪመጣ ጣራ ጣራውን ማየት ብቻ ነው።  እንደዛው አደረኩ። እንቅልፌን ለማምጣት እየታገልኩ  ውስን ደቂቃዎች አለፉ። ልክ እንቅልፌ እንደመምጣት ሲል ብቻ  ገልበጥ ገልበጥ አለችና እግሯን ቀጥታ በእግሮቼ መሀል ለመሀል ልካ  ፈንጂ ወረዳው ላይ ጫነችው። እቺ ናት ጫወታ••••! እቺ ልጅ አርፋ አተኛም ማለት ነው። እዚህ ቤት ውስጥ  ፈንጂ አምካኝ  ከሷ ውጪ አለመኖሩን እያወቀች ፈንጂ ረግጣለች እንግዲህ ሀላፊነቱን እራሷ ትወስዳለች። አይቻት ከምሳሳት ባላያትስ ብዬ ከራሴ ጋር ስታገል ከማየትም በላይ ፈታኝ የሆነ ወረዳ ውስጥ ሰተት ብላ ገብታለች ፣ ከዚህ በኋላ እዚህ ቤት ውስጥ ለሚከሰተው ነገር በሙሉ እኔ ተጠያቂ አልሆንም። አትንካኝ ያለችው እራሷ ነች።  አትንካኝ ካልሽ አልደፍርሽ እንግዲህ ካልፈለግሽ ይቅራ አልኩ። አሁን በንግግር ተስማምተን የዘጋነውን ጉዳይ በእግር እየነካኩ መቀስቀስ ምን ይሉታል እስቲ። ይህ  ሰውን  ለስሜትም፣ ለስተትም ፣ ለፀፀትም የሚያነሳሳ ተግባር  አካላዊ ትንኮሳ ካልተባለ ምን ሊባል ነው••? በየሰከንዱ እየተገላበጥሽ እርቃኑን ባስቀረሽው ገላሽ ምክንያት የተጋረጠብኝን ከባድ ፈተና በጀርባዬ ተኝቼ ጣራ ላይ በማፍጠጥ ልቋቋመው ስጣጣር፣ ጭራሽ  በውስጥ እግርሽ ፍሬዬን በግሮችሽ ጣቶች ፍሬኔን እየነካከሽ ሞተሬን እያሞቅሽው እንደሆነ እወቂው  ። "ሆዴ ጭሶ ጭሶ የነደደ እንደሆን •••አለ ሰውየው ። ከዚህ በላይ እንዴት ሆኜ ልተኛላት። ስልጠናው ቅዥት ሆኖበት በእንቅልፍ ልቡ አሳርፍ!!!  ተጠንቀቅ !  እንደተባለ ወታደር እግሬን ገጥሜ አልተኛ እንግዲህ •••እያልኩ  ከጭኖቼ መሀል  የእግሯን አውራ ጣት ይዤ አነሳሁትና  ወደ ጎን አደረኩት። ትንሽ ቆይታ ሌላኛውን እግሯን አነሳችና ባልጠፋ ቦታ እዛው ከምብርቴ በታች ጫነችው። አለቀ ነካክታ ነካክታ አንዱን ኤፍሬም ሀለት ቦታ ከፍላኝ አረፈችው። ሁለት ኤፍሬም ሄንኩ•••ውስጤ በሁለት ተቃራኒ ሀሳቦች ጭቅጭቅ ገጠመ። አንደኛው ስሜቴ  ዝም ብለህ ለመሳሳት ሰበብ አትፈልግ ባክህ !! ፣ አደብ ግዛ!  ገና ለገና በእንቅልፍ ልባ ስትገላበጥ ነካችኝ ብለህ ከሰው ወደ እንሰሳነት ልትቀየር ይቃጣሀል እንዴ•••? አታፍርም•••? እንቅልፍ የወሰዳት እኮ ስላመነችህ ነው። እግሯን ስትዘረጋ ነካችኝ ብለህ ምን ልትሆን አማረህ•••? አሁን በጉልበትም በምንም ያሻህን አደረክ  ነገ እንዴት ብለህ አይኗን ልታይ ነው•••?  ይልቅ ከወደድካትና አብራህ እንድትቀጥል ፍላጎት ካለህ ስሜትህን ግዛ!። እንደማትነካት ቃል ገብተኽላታል፣አምናሀለች። ለቃልህ ስትታመን ላንተ ያላት አመለካከት ጥሩ ይሆናል። ያለ በለዚያ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ፣ ሴትን ልጅ ጉልበቱን ተጠቅሞ አስገድድዶ የሚደፍር አውሬ አድርጋ ነው የምታይህ እንኳን ያንተ ልትሆን በሂወት ዘመና ካንተ በላይ የምትጠየፈው ወንድ አይኖርም። ብትታመንላት ግን ይቺ ለሊት የሷን ልብ ለመክፈት እና  ለማሸነፍ  አንዷ ቁልፍ ትሆናሀለች ። ወደሃታል፣ ስለዚህ ማሸነፍ የምትፈልገው ልቧን ነው። ልቧን የምታሸንፈው ደግሞ ስታከብራት ነው። ያለፍቃዷ ገላዋን መንካት ግን ንቀት ነው። አለኝ። የጋለው ስሜቴ የተቆጣጠረው ሌላኛው ኤፍሬም ደግሞ  በተቃራኒው እንዲህ ይለኛል••• " አይ ኤፍሬም እውነትም ያ አብሮህ የሚኖረው ጋደኛህ እንደሚልህ አንተ አራሯጭ ነህ እንጂ ሯጭ አይደለህም ። እስከዛሬም ብዙ ሴት ትቀርባለህ ታጫውታቸዋለህ ፣ ታስቃቸዋለህ ፣ አብረኻቸው የተወሰነ ግዜ ትቆያለህ  ፣ ሁሌም እነሱ መግደርድራቸው አይቀርም ፣ ሲግደረደሩ እውነት እየመሰለህ  ምን አስቸኮለኝ እያልክ ዝም ትላለህ ፣ ሳትነካቸው ለሌላ ወንድ አስረክበህ ትቀመጣለህ ። ከዚህ በላይ ምን አሯሯጭነት አለ። አሁን ባንተ ቤት ቃል ኪዳን የእውነት የተኛች  መስሎሀል አይደል•••? በፍፁም አልተኛችም ። በዚች ደቂቃ ውስጥ ይሄን ያህል እራሷን እስክትጥል ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ የገባች ይመስልሀል•••? አትሞኝ ባክህ ኤፊ •••እንደዚህ የምትገላለጠውም አንዴ ቀኝ እግሯን አንዴ ግራ እግሯን እየላከች የማይሆን ቦታ የምትነካካህም ሆን ብላ ነው !። አይገባህን እንዴ •••? ቆይ ከዚህ በላይ ፍቃደኝነቷን በምን ታሳይህ••• ክፍል 7 ቶሎ እንዲለቀቅ  Like ❤
420
16
ወንድ ልጅ በሕይወቱ ውስጥ ከፍቅር በላይ መከበርን ይፈልጋል። ክብር ካጣ ፍቅር ቢሰጠው እንኳን ባዶነት ይሰማዋል። ሴት ልጅ ደግሞ ከክብር በላይ መወደድንና ትኩረትን ትፈልጋለች። ወንድ ልጅ ሳይከበር መውደድ አይችልም፤ ሴት ልጅ ደግሞ ሳትወደድ ማክበር ይከብዳታል።ስለዚህ ለወንዱ ክብር ስጪው፤ ለሴቷ ደግሞ ትኩረት ስጣት፤ ያኔ ፍቅራችሁ ሰላማዊ ይሆናል።
394
17
ሰላም... ሰላም... ፋሚሊ .. እጅግ ምርጥ የሆነ አዲስ ልቦለድ ተጀምሯል...... እ 👀 እንዳያመልጣቹ ጆይን እያላቹ.👇👇👇
ሰላም... ሰላም... ፋሚሊ .. እጅግ ምርጥ የሆነ አዲስ ልቦለድ ተጀምሯል...... እ 👀 እንዳያመልጣቹ ጆይን እያላቹ.👇👇👇
485
18
♥️ ተማሪዋ ♥️ 🌹...ክፍል 5...🌹 እንደገባን ከእቅፌ ውስጥ አፈትልካ ወጣችና ከአልጋው እራስጌ በስተግራ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። "እንዴ እዚህም ገብተሽ ቁጭ አይንሽ እኮ በእንቅልፍ ማጣት ደክሟል አተኝም እንዴ ተማሪዋ•••? " ተማሪዋ አትበለኝ አትሰማም•••?" "ትትክክለኛ ስምሽን እስክትነግሪኝ አማራጭ የለኝም!" "ሰላም አልኩህ እኮ!" "የስንቱን ሰላም በውበቷ የምትረብሽ ልጅ ሰላም ልትሆን አትችልም ! ውስጤ ነግሮኛል ፣ስምሽ ሰላም እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ!" "ትገርማለህ ግን ! ••ይሄው ስሜ!•••  የዋሸሁክ መስሎህ ነው አደል•••?  አለችና ከሞባይሏ ላይ ከቨሩን አንስታ በሞባይሏ ጀርባ ላይ ያስቀመጠቻትን የድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ  ተማሪ መሆኗን የምትገልፅ መታወቂያዋን አንስታ ሰጠችኝ። " ካካካካካ እሄው እንደዋሸሽኝ መች አጣሁት •••ቃል ! ነው ስምሽ!  ቃልኪዳን ሰመረ !  ካሁን በኋላ ተማሪዋ መባልሽ ይቆማል!•••••እና አሁን ከወንበሩ ላይ  ተነስተሽ አተኝም ቃል!" አልኳት። ትከሻዋን ወደ ላይ ሰብቃ አልተኛም አለችኝ። ነፃ ሆና ማውለቅ ያለባትን አውልቃ እንድትተኛ ብዬ  ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባሁላት። ከደቂቃዎች ቆይታ በኋላ ስመለስ ጭራሽ ጫማዋን አውልቃ እግሯን ወንበሩ ላይ ሰቅላ ተቀምጣለች። ጉድ ፈላ  እዚሁ ወንበሩ ላይ ነው የማድረው ልትለኝ ነው እንዴ•••? እያልኩ በሆዴ  ጠጋ አልኩና•••"  ቃልዬ አተኝም እንዴ•••?" አልኳት።"ቁጭ በል!" አለችኝ••• አልጋውን በአገጯ እያመላከተችኝ። ቁጭ አልኩ። ተፋጠጥን። የሆነ የሆነ ሰአት የምታየኝ አስተያየት ልቤን ስልብ ሲያደርገው ይታወቀኛል። ያ አስተያየት አልፎ አልፎ የሚመጣ መሆኑ በጀኝ እንጂ ዘለግ ላለ ደቂቃ እንደዛ ብታየኝ የልቤን ትርታ ታቆመው ነበር። "እእእ ••••እእእእ•••" እያለች ልትናገር ያሰበችውን አፏ ላይ አድርሳ  መልሳ ትውጠው ይመስል ለመናገር ስታምጥ ቆየችና••• "እእእእ እኔ በጣም የምታዘበው ባስ ሲልም  የምጠላው ምን አይነት ባህሪ ያለው ወንድ እንደሆነ ታውቃለህ ኤፊ•••?" ስትለኝ ••••" አዎ አውቃለሁ ! በደንብ ነዋ የማውቀው!" አልኳት። "ምን •••? እንዴት ልታውቅ ትችላለህ•••?  አታውቅም!" አለችኝ ። "አውቃለሁ ባክሽ •••አንቺ የምትጠይው ወንድ እንደኔ  ገና ለገና መቶ ሀምሳ ብር ሂሳብ አልከፈልሽም ብሎ መቶ ሀምሳ ዘፈን ካልዘፈንኩብሽ ፣ የሀረርጌን ሸጎግን አትጥይኝ ባህርይ በፍፁም እንደዛ አይደለም። እውነቱን ለምናዘዝ እኔ ገና መጀመሪያ ላይ ቆመሽ እንዳየሁሽ ነው ደስ ያልሽኝ ••••" ብዬ ልቀጥል ስል በሳቅ አቃረጠችኝ ••••"ኪኪኪኪኪ ደስ ያልኩህ አደል በቃ ከዛ አያልፍም  ኪኪኪ" "አስጨርሽኛ ቆይ እና ባንዴ እንዳየሁሽ ነው ያፈቀርኩሽ ብልሽ ያንን ማለት ይቻል ይሆናል እኔ ግን በቃ እንድታምኝኝ ስለምፈልግ እውነቱን ነው የምነግርሽ ደስ አልሽኝ ወይም ወደድኩሽ በቃ በቃ ምንድነው ለማንኛውም መሄድ ጀምረን ግማሽ መንገድ ላይ ሂሳብ የለኝም ስትይኝ አንቺ እንደምታስቢው ወይም እኔ እዛ ጋር እንዳስመሰልኩት አልተናደድኩብሽም እንደውም አንቺን የምግባባበት አጋጣሚ ስለተፈጠረልኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ። ባጭሩ እንደዛ ያካበድኩት እንደዚህ አሁን እንደተግባባነው እንድንግባባእንድንቀራረብ ነው። ብር የለኝም ስትይኝ ችግር የለውም ሲኖርሽ ትከፍያለሽ ብዬ ባደርስሽ እኔ እንኳን ባልረሳሽ አንቺ ሲነጋ ትረሽኛለሽ!" "ገብቶኛል ኤፊ!••• አቋረጥከኝ እንጂ እኔም ጨቅጫቃ ወንድ ምናምን ልልህ አልነበረም። ይህን ሁሉ ከምትናገር እኔን ብታስጨርሰኝ ምን ነበረበት•••?" "የቱጋ •••? እዛው ወንበሩ ላይ•••? "ስላት ••••"የምን ወንበር •••?" አለች ግር እያላት። "የማስጨርስሽ ነዋ! ወንበር ላይ ነው እንዴ የሚመችሽ እኔ መች ገባኝ ••! አልገባኝም ነበር እኮ እያልኩ ከላይ የለበስኩትን ቲሸርት ሳወልቅ" "ካካካካካካካካ ••••ሂድ ወደዛ ! ሞዛዛ !! ሞዛዛ ነገር ነህ እሺ እንዴ ኪኪኪኪኪ ደሞ  ፍጥነትህ ትገርማለህ እሺ! ፣ እኔ ወሬዬን እስክጨርስ ብትጠብቀኝ ምናለበት ነው ያልኩት ፣  ዝም ብልህ ነገር አታጣምም!" "ግንኮ ከለሊቱ አስር ሰአት ሆኗል፣ በዚህ ሰአት ወሬ አይከብድም •••? ነገ ብናወራስ•••? አሁን እንተኛ ባክሽ ነገ እናወራለን !" "አአአ•••አሁን ከመተኛታችን በፊት ነዋ ማውራት ያለብን ኤፊ!" "እህህ••••ገባኝ! አሁን እናውራ ፣ በቃ እናወራለና ምን ችግር አለው •••• እሺ ምንድን ነው•••?""እእእ••••እኔ የሚጫነኝ ወንድ አልወድም ኤፍ ••ማ•••ማ  ማለት•••" "አቦ ተይው አታስረጂኝ  በቃ ይበቃል! ፣ ይህን ምን ማብራራት ያስፈልገዋል! እንደገባኝ ያው  የሚጫንሽን  ወንድ ሳይሆን መጫኑን ነው የምትጠይው መፍትሄው ከላይ መሆን ነው አንቺ ከላይ ከሆንሽ ወዴት ይጫንሻል•••?" "ኧረ በፈጠረህ••••! ላለማውራት  ሆን ብልህ ነው አደል ነገር የምታምታታው አውርቼ እስክገላገለው ብጠብቀኝ ምናለበት•••?" ስትለኝ እስክገላገለው የሚለው ቃል ሰቀጠጠኝ። ምን ልታወራኝ ነው ይቺ ልጅ ••• አውርቼ እስክገላገለው ስትል ምን ማለት ነው•••? እያልኩ ••• "እሺ ምንድን ነው ንገሪኝ!" አልኳት። "ኤፊ በቃ እኔ በጣም የሚያናድደኝ ወንድ የኔን መጥፎ አጋጣሚ ከፍላጎቴ ውጪ በሆነ መልኩ ለመጠቀም የሚፈልግ ወንድ ነው ! " ስትለኝ ምን አስባ እንደሆነ ገባኝ። ለምን እንደሆነ አላውም ውስጤ የንዴት እሳት ሲጫር ተሰማኝ።  ብልጭ አለብኝ። ወድያው ስሜታዊ ሆኜ ክፉ ነገር ልናገራት አልፈለኩም። ምክንያቱም ወድጃታለሁ። ግኑኝነታችን እንዲቀጥል እፈልጋለሁ ። ወደፊት የሚሰማኝን እና የሚሆነውን ባላውቅም አሁን ላይ ዛሬን ብቻ  ሳይሆን ነገ ከነገወድያም ላገኛት እንደምፈልግ ነው የሚሰማኝ።ባዶው ወለል ላይ አፍጥጬ ዝም አልኩ።  "ልልህ የፈለኩት ገብቶሀል አደል ኤፊዬ•••?"ገብቶኛ ቃል! •••በደምብ ገብቶኛል •••በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ግንኙነቶች በአጋጣሚ በተፈጠረ  ቅፅበት የሚጀምሩ ናቸው !። ያ አጋጣሚ ደግሞ ጥሩም መጥፎም አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አጋጣሚውን ተጠቅሞ መተዋወቅ ፣ መቀራረብና መግባባት አንዱ የህይወት ገፅታ ነው። ያ በራሱ ምንም ክፋት የለውም። የተቸገርሽበትን ወይም ጥሩ አጋጣሚ ላይ ያልሆንሽበትን ግዜ ተጠቅመው ችግርሽን ለመፍታት አልያም ከዛ መጥፎ አጋጣሚ ለመውጣት ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እነሱ መሆናቸውን ሲያውቁ ያንን ክስተት አንቺን ያለፍላጎትሽ ያሻቸውን ለማድረግ የሚጠቀሙበት ወንዶች የሉም ብዬ አልልም። በሌላ መልኩ  ሰው ስለሆንሽ ብቻ ካንቺ ምንም ሳይፈልጉ አንቺን በመርዳታቸው ብቻ ደስ የሚላቸው ወንዶችም ብዙ ናቸው። ሁሌም ረጂ ወንዶች ተረጂ ሴቶች ናቸው ብሎ ማሰብም ትልቅ ስህተት ነው ። ያው እንደየሁኔታው ይቀያየራል። እኔ ግን ቃል ኪዳንን ወይም አንቺን በመጥፎ አጋጣሚ የተዋወኩሽ መስሎ አልተሰማኝም ነበር። እኔና አንቺ የተዋወቅነው በመጥፎ አጋጣሚ ነው ብዬ በጭራሽ አላሰብኩም ነበር። በርግጥ እኔ ሳላገኝሽ በፊት እዛ ብርድ ላይ በምን ምክንያት እንደቆምሽ በዝርዝር አላወራንም ። ንገሪኝ ብዬያልወተወትኩሽም አንቺን ማጨናነቅ ስላልፈለኩ ነው። ግቢ ያላደረስኩሽም በግድ ተጭኜሽ ነው ብዬ አላስብም። በቃ ደስ ስላልሽኝ ፍቃድሽ ከሆነ አብረሽኝ እንድትዝናኚ ስለፈለኩ ነው ያስቀረሁሽ ክፍል 6 ቶሎ እንዲለቀቅ  Like ❤
506
19
ስለ ታላቁ ተጫዋች የእግርኳስ ንጉስ ስለሆነው ብዙ ክብሮች ኖሮት ስለ ራሱ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ለማይለው ብዙዎች ሪከርድ ሲያሳዱ እሱ ግን ሪከርድ የሚያሳደው እግርኳስ ምን አይነት እንደሆነ ላሳየን
ስለ ታላቁ ተጫዋች የእግርኳስ ንጉስ ስለሆነው ብዙ ክብሮች ኖሮት ስለ ራሱ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ለማይለው ብዙዎች ሪከርድ ሲያሳዱ እሱ ግን ሪከርድ የሚያሳደው እግርኳስ ምን አይነት እንደሆነ ላሳየን ስለ Lionel Messi ብዙ የሚተነተንበት ቻናል ነው ተቀላቀሉን 👇👇👇 https://t.me/+AdT2NXE-3CkzODVk
412
20
♥️ ተማሪዋ ♥️ ክፍል 4...🌹 ምንም ሳንቀምስ ቅልጥ ያለ ጭፈራ ቤት ይዣት ከምገባ ሰከን ረጋ ያለ ቤት ትንሽ ብንሟሟቅ እንደሚሻል አሰብኩና ጫጫታ የለለበት ፣ሰፋ ባለው ግቢው ውስጥ ጥንዶች በነፃነት ዘና የሚሉበት የጥንዶች ማቆያ (couple house) ያለው ረጋ ካለው ሙዚቃው ጋር ረጋ ብልን መጨዋወት ወደምንችልበት ሀያ አራት ሰአት ወደማይዘጋ ሆቴል ይዣት ገባሁ። ቢራ አልጠጣም ብላ ትንሽ ብትሟገተኝም እንደምንም አስጀመርካት። ወድያው ጫወታ ለመጀመር ያህል •••"እና ስምሽን አትነግሪኝም ማለት ነው•••?" አልኳት በድጋሚ። ኪኪኩኩ እሺ ትንሽ ለምነኝና እነግርሀለሁ!" "አቦ እኔ መለመን አልችልበትማ!" "ቀረብሃ ካለመንክ ማን ይሰጥሀል!" "ካካካካ እሺ ከለመንኩስ ምን ይሰጠኛል?" "ኪኪኪ •••እኔ ካልለመንክ ማን ይነግርሃል ለማለት ፈልጌ ነው ባክህ" "እሺ እንድትሰጪኝ  ምን ብዬ ልለምንሽ  !" "ጭራሽ እኔ ልንገርህ ምነው ፍቅረኛህ ትንሽ እንኳን ሳታስለምንህ ነው እንዴ ሁሉን ነገር የምታቀርብልህ?" "ካካካካካ ምንድን ነው የምታቀርብልኝ•••? ለምሳሌ ምን •••?" "ኪኪኪኪ እኔ እንጃልህ እስከዛሬ የሰጠችህን አንተው ነህ የምታውቀው?" "ቆይ አንቺ እኔ ፍቅረኛ  አለኝ የሚል ነገር አልወጣኝ ፍቅረኛ  ይኑረኝ አይኑረኝ  በምን አወቅሽ•••? " በግምት ነዋ!  ••• ባታገባም ፍቅረኛ አታጣ!" "የለኝም ! ያው እንደነገርኩሽ እኔ መለመን አልችል ካለመንኩ ፍቅረኛ ኬት ይመጣል•••?" "ነገሩ አንተ እንደሽማግሌ መጨቃጨቅ እና ማስጨነቅ እንጂ መለመን እንደማትችል ታስታውቃለህ አምኜሀለሁ ኪኪኪኪ•••"እንዴ አንቺ ልጅ እየሰደብሽኝ እኮ ነው ታውቆሻል!" "ሲያንስህ ነው ••••ኪኪኪኪ•••• እንዴ • ሲያዩህ እድሜህ ሀያ አምስት እንኳን የሚሞላ አይመስልም ስትጨቃጨቅ ግን የሰባ አመት ሽማግሌ ነው የምትመስለው ኪኪኪኪኪኪ•••" አለችና ረጅም ሳቅ ሳቀች። በቃ በአንድ ምሽት ለወራት እና ለአመታት የምንተዋውቅ ያህል ተቀራረብን። ፍርሀት እና ንዴቷ  ፣ ድንጋጤ እና ጭንቀቷ ፣ ድፍረትና ነፃነቷ ፣ ሳቅና መልኳ ••••በቃ  ሁሉ ነገሯ ወደድኩላት ሴት ልጅ እንደዚህ በፍጥነት ቀርቤም ወድጄም አላውቅም። "ሁሉ ነገርሽ ደስ ይላል!" ስላት " እንኳን !" አለችኝ። "ስምሽን ንገሪኛ •••?" "አልነግርም!" "የኔንም አልነግርሽም !" "ያንተንማ ሰማሀት እኮ ያቺ ክፍት አፍ የሆነች አስተናጋጅ ኤፍዬ ስትልህ ያልሰማሁ መሰለህ !" አለችኝ። አነጋገሯም አኳኋናም በጣም ነበር ያሳቀኝ። በዚህ ሁኔታ እየተጨዋወትን እኔ በላይ በላይ ብጠጣም እሷ ግን ጥንቃቄዋ ይገርም ነበር። ሁለት ቢራ ላይ እንደቆመች እኔ ብዙ ጠጣሁ። ግን ሞቅ አለኝ እንጂ አልሰከርኩም። "እሺ ስሜ ሰላም ይባላል !" አለችኝ በጫወታ መሀል ሳልጠይቃት። "ሰላም እንዳልሆነ ስምሽ እርግጠኛ ነኝ ደሞ ማን ንገሪኝ ብሎ ለመነሽ !" አልኳት።ኮርኪ ከጠረጴዛው ላይ አንስታ በመወርወር መታችኝ። ተሳሳቅን። "ኧረ በቃ እንሂድ ሸኘኝ ኤፊ ሊነጋ እኮ ነው!"  አለች። "ካካካካካ " ከነዱ አይጠጡ፣  ከጠጡ አይንዱ" የሚለውን ማስታወቂያ ሰምተሽ አታውቂም ማለት ነው?" ስላት "ም••••••ን ?" አለች። "ከማስታወቂያው ስር በጥቃቅን ፅሁፍ ሌላ የተጨመረችውን መልክትስ አንብበሻት አታውቂም•••ምን ትላለች መሰለሽ " ከነዱ አይጠጡ፣ ከጠጡ አይንዱ " ከሚለው ትልልቅ ፅሁፍ ስር በደቃቁ•••" ከጠጡ በኃላ መንዳት የሚችሉት አልጋ ላይ እንጂ መኪና አይደለም!" የምትል መልክት አለች። ትቀልጃለሽ እንዴ መሄድ ከፈለግሽ እንጠጣ ስልሽ ለምን ተስማማሽ ካካካካካ  አይ የምሬን ነው  ጠጥቼ ስነዳ አኔንም አንቺም ይዤ ገደል ከምገባ ከሌላ ተሽከርካሪ ወይ ከግንብ እና ከግንድ ጋር  ከምጋጭ ••• እዚሁ እንደጀመርነው  የቢራ ጠርሙሳችንን እያጋጨን ብንጠጣ አይሻልም •••? ትንሽ ቆይተን ደግሞ ወደያዝኩት ክፍል ገብተን  ወይ እኔ አንቺን ወይ አንቺ እኔ ብገጭኝ አይሻልም  የኔ ቆንጆ  ካካካካ? አልጋ ይዣለሁ እኮ እሄው ቁልፉ!"  ብዬ ሳሳያት••• "ምናልክ ኤፊ •••?" አለች በድጋሚ እንቅልፍ ባስለመለማቸው  አይኖቿ ተስለምልማ እየተመለከተችኝ ። " እንቅልፍሽ መጥቷል አደል••••?  ነይ በቃ  ወደክፍላችን እንግባ!"  ብዬ  እጇን ይዤ ከተቀመጠችበት  አነሳኋትና ሳብ አድርጌ አቀፍኳት። ድምፅ የለም። ይዣት ስሄድ •••• "ኤፊ እኔ ••••" ብላ ልትናገር ያስበችውን ሳጨርሰው ከንፈሯ ላይ የግራ እጄን  ሁለት ጣቶች በስሱ ደገፍ አደረኳቸው። ዝም አለች ።ጠበቅ አድርጌ እንዳቀፍኳ ተያይዘን ወደያዝኩት ክፍል ገባን.... ክፍል 5 ቶሎ እንዲለቀቅ  Like ❤
534