fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ጉዞ ወ ልቡና - Psyche Journey

ጉዞ ወ ልቡና - Psyche Journey

رفتن به کانال در Telegram

Glimpse Into My Eye's ✨ YouTube - https://youtube.com/@psychejourney1?si=uwzh2Wet @Lidetu_Psyche Lidetu Tesfaneh የነጻነትን ትርጉም የሚሰጥህ ገደብ ነው። አልያ ነጻነት ራሱ እስር ቤት ይሆናል

نمایش بیشتر
786
مشترکین
+924 ساعت
+157 روز
+1930 روز

در حال بارگذاری داده‌ها

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26
اکتبر '26
+472
در 2 کانال‌ها
سپتامبر '260
در 1 کانال‌ها
Get PRO
اوت '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '260
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '260
در 1 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '260
در 1 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '250
در 0 کانال‌ها
Get PRO
سپتامبر '25
+5
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اوت '25
+43
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '25
+284
در 1 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
22 اکتبر+16
21 اکتبر+9
20 اکتبر+1
19 اکتبر+7
18 اکتبر0
17 اکتبر0
16 اکتبر+1
15 اکتبر+1
14 اکتبر+4
13 اکتبر+1
پست‌های کانال
ለሚጎዳህ ነገር ሁሉ አራት ነጥብ አስቀምጥ፤ ነጠላ ሰረዞች አድካሚ ናቸው። Evangadi21

2
ዉስጡ ለጨለመበት ሰው የፀሐይ መውጣቷ ምን ትርጉም አለው? ጨለማው በዉስጡ ለደመቀበት የቀኑ መንጋት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ወጋገኑ፣ የፀሃዪ ዉብ የተላጠ የሚመስል ብርትኳንነቷ የዉስጡ ቀለም ለደበዘዘበት ሰው ምን ታደርግለታለች? ዉስጡ ያለው መጉደል ለሰፋበት ሰው ዉጪው ላይ ያለው መትፍረፍረፍ ምን ትርጉም ይሰጣል? ደግሞስ ዉስጡ ድቅድቅ ጥላ ለሆነበት የዉጪው ጨለማ እንዴት አይበረታ? የገዛ ሥጋችን (የገዛ ባይሆንም የምንኖርበት ቤት ነው) እጅ እጅ ቢለን ወዴት እንሄዳለን? በምን ቅመም ወደ መልካም ጠረኑ እንመልሰዋለን? ደራሲ እሱባለው - ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ? እንዳለው ፀሐይ ከጨለማችን ጉዳይ የላትም - ከነፍሳችን መጥቆር አንዱንም አታነጣም - የራሳችን የዉስጥ ንጋት የዉስጥ ብርሃን ለዓለም ከምታበራው ብርሃነ ፀሐይ ጋር ጉዳይ የለውም! የሚያስፈልገው ብርሃን ብርሃናት ሳይፈጠሩ በፊት ለፍጥረት ብርሃን የሆነውን ፈጣሪ ነው። በነዚህ መሃል ራስን መመልከት መልካም ነው - አፈጣጠራችን ዉስጥ አንዱ አካል መንፈስ ስለሆነ ያ አካልን ከዘነጋን ደግሞ የምናጣው ብዙ ነው - ከምናጣው መሃል ደግሞ ዋነኛው ራሳችንን ነው።
1 400
3
ሰው መሆን ቀላል አይደለም ሰው ለመሆን አለመሆንን ማወቅ የመጀመርያው መንገድ ነው - "ነን" ብለን ተናግረን፣ አውርተን፣ አምነን ሳንሆን ስናገኘው ደግሞ ሕማምና ቁስል ይሆንብናል - ለዛም ነው ራስን ማየት የሚያደክም ነገር ነው የምለው - ቢሆንም ሕይወት ዋጋ ያላት ከልብ ስንኖራት ነው - ያ ደግሞ የሚጀምረው ከአንዲት መነሻ ነው እሱም ትግላችሁ ከራሳችሁ ጋርና የምርም ከፈጣሪ ጋር ልባዊ ግንኙነት ሲኖራችሁ ነው።
1 422
4
https://youtu.be/A6Uu5f1wArU?si=94-fSP61R9H2Vy_E
180
5
ስንረካ የመጠማት፣ ስንጠግብ የመራብ አቅማችንን እየጨመርን ነው ምንመጣው። ብዙ ግዜ የነገሮች መጉደል ይታየናል። በእርግጥ ሕይወት ንፉግ ናት መሰለኝ ያንን ማድረግ አትችልም። የሰውን የጎዶለዉንና በመርካት አለመርካት ዉስጥ ያለዉን እዉነት በ myth ደረጃ ፕላቶን አንስቶታል። ነገሩ ስለ ዳናኢዴስ ሴቶች የሚነገረው ነው። እነዚህ ሴቶች ለባሎቻቸው የሚገባቸውን እምነት ሳይጠብቁ ቀርተው ሲወሰልቱ ተገኝተዋል። የጋብቻን ንጹሕነት በሚጠባበቁት አማልክት ፊት ተከሰው በደላቸው ታውቆ እንዲቀጡ ተፈረደባቸው። ቅጣቱም የተሸነቈረ ማድጋ በውሀ እንዲሞሉ ነበር። ከላይ ሲሞሉበት ከሥር ወዲያው ስለሚፈስ ማድጋው ምን ጊዜም አይሞላም። ስለዚህ እነዚህ ሴቶች ዘለዓለም ውሀ ሲያመላልሱ ይኖራሉ ይባላል። ፕላቶን ከዚህ ተረት ቀዳዳውን ማድጋ ወስዶ በሰው ይመስለዋል። የሰውን የምኞትና የተምኔት ብዛት ሲያዩት ልክ እንደሽንቁር ማድጋ ነው። በጨመሩበት መጠን እየጎደለ በረካ መጠን እየጠማው ነው የሚሔደው። ሁልጊዜ ካለው የበለጠ እንዲኖረው ይፈልጋል። (የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ) እዚች ጋር አንድ ነገር ያዙልኝ ነገሩን ስለመሙላት ሳይሆን የመራብና የመጠማት አቅማችንን የምንጨምረው እኛው ነን የሚለውን ነው ማንሳት የፈለኩት። ሰው ፍላጎቱን ባሟላ ቁጥር ያንን የማሟላት ቅጥሩን እያሰፋ ነው - ሆድ እንዳስለመዱት ነው - የመጉደል አቅም አቅሙን የሚጨምረው በምንሞላበት "አቅም ልክ" ነው - እንግዲህ ያለኝ ይበቃኛል ማለት ጥበብ ነው - ቢሆንም ግን ባሉበት መቆየት አይቻልም ወይም እያደጉ እየጨመሩበት መምጣት ነው ወይንም እንደ መመንኮስ አይነት መሆን ነው። ለዛም ይመስለኛል አንድን ነገር በጣም ለሟሟላት በጣርን ቁጥር የመጨረሻው አይበቃኝም ጫፍ ላይ የምንቆመው እናም ያን ጉድለት ልሙላ ቢሉት ከፈጣሪ በቀር የትኛውም ነገር የሚያረካ አይሆንም። "The more you get the more you want."
1 569
6
https://youtu.be/4Y6Tjqu4JvI?si=73XcaGEx3nUXb70y
258
7
Aim at something. Pick the best target you can currently conceptualize. Stumble toward it. Notice your errors and misconceptions along the way, face them, and correct them. Get your story straight. Past, present, future they all matter. You need to map your path. You need to know where you were, so that you do not repeat the mistakes of the past. You need to know where you are, or you will not be able to draw a line from your starting point to your destination. You need to know where you are going, or you will drown in uncertainty, unpredictability, and chaos, and starve for hope and inspiration. For better or worse, you are on a journey. You are having an adventure-and your map better be accurate. Voluntarily confront what stands in your way. The way that is the path of life, the meaningful path of life, the straight and narrow path that constitutes the very border between order and chaos, and the traversing of which brings them into balance. "Beyond Order - Jordan Peterson"
295
8
እያንዳንዱ ነገር በክፍያ ዉስጥ የሚያልፍ ነው። ነገሮች transactional ናቸው exceptional የሆኑ ነገሮች ቢኖሩም። እናም እያንዳንዱ ምርጫችን በነፃ ፈቃድ በኩል ክፍያ የሚፈፀም ነው። ባንፈልግም ነፃነታችንን አንቀው የሚይዙ ደግሞ የትላንት ትብታቦች አሉብን። የዛ ኃላፊነት ደግሞ ራሳችን ላይ ይወድቃል። ምክንያቱም still አሁንም በኛ ደምስር፣ ጅማት፣ አጥንት፣ ሥጋ በኩል አልፎ ስለሚወ'ሰን። ነፃነት የመምረጥ መብት ማግኘት ነው። ሰው ከፍሎ ከገባበት ነገር በነፃ አይወጣም - ከየትኛውም የገባንበት ባርነት ነፃነት ለማግኘት ነፃ ለመሆን ክፍያ አለው - ነፃነት ነፃ ስላልሆነ።
1 633
9
https://youtu.be/dSbqQ_Lwnxg?si=KD7UBX4xVNWBnEYd
540
10
An 18 year old kid had a car accident and this is በጣም heart breaking she was just a kid በሚያሳዝን ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ የወጣት ሞት እየበዛ ነው፤ ብዙ ወጣቶች በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን እያጡ ነው፡፡ በጣም የሚያስከፉና የሚያስቆጭ ሞት... ወጣት ሲሞት ሳይ እቅዶቼን እጠራጠራለሁ ወጣት ሲሞት ሳይ ነገን ማመን ያቅተኛል ወጣት ሲሞት ሳይ ስለ ሕይወት እጨነቃለሁ ወጣት ሲሞት ሳይ ተስፋዬ ከእጄ የሚርቅ ይመስለኛል ወጣት ሲሞት ሳይ የራሴን ነገ እፈራለሁ ወጣት ሲሞት ሳይ የምኖረው ህይወት የተሰጠኝ ሳይሆን እንደተበደርኩት ይሰማኛል ወጣት ሲሞት ሳይ የማላውቀው ነገ ያስጨንቀኛል። ✍️ Yohannes Getachew (IG)
388
11
https://youtu.be/W24o0l_S1sk
357
12
አንዳንዴ የሆኑ ነገሮች Unfair ናቸው - ራሷ ዓለም ሳትሆን፣ ራሳቸው ሰዎች ሳይሆኑ እኛ ራሳችን ለራሳችን - በእርግጥ ሕይወትን ከልብ እንዳንኖራት አዚም የሚያደርግብን ፖለቲካ, ኑሮ, ስራ, ሰዎች አይጠፉም - እነዚህ ሁሉ ራሳችንን ሆነን እንዳንገኝ ያደርጋሉ - እንግዲህ ብዙ ቅንብር ያለባት ዓለም ዉስጥ ነው የምንኖረው - ዓለም የሚያደክም ነገር አላት - ዉብ ነገርም በሽ ነው - በዚህ Tragedy መሃል ግን ከልብ ሕይወትን እንደሚኖር ሰው የታደለ የለም (ማን አድሎት ይሆን? አዳይ አለ ወይ? የት ነው የሚታደለው? እኛስ ለምን አልደረሰንም? ግዜያችን ገና ሆኖ ወይንስ መጀመሪያም ያልገባን ነገር አለ? ወይንስ አዳይ የለም?) ይሄን ያልኩበት ምክንያት ብዙዎቻችን የውሸት እኖርን የእውነት የምንሞት ስለሆነ ነው - የእውነት ለመኖር ደግሞ ልብ ይፈልጋል።
1 805
13
ሰው በተደጋጋሚ ስለራሱ የሚያወራው በዛ ነገር ዉስጥ ጉድለት ስላለበት ነው። አድሀኖም እንዳለው "ሃይለኛ ነኝ ፣ ሃይለኛ ነኝ ፣ ሃይለኛ ነኝ የሚለው ሰነፍ ነው ፣ ደካማ ነው ብለው እንዳያጠቁት ስለሚፈራ ይመስለኛል" የሆነውን የሆነ ሰው ስለሆነው ነገር የማውራት እድሉ አናሳ ነው - የሆነው ነገር ብቻውን አፍ መሆን ስለሚችል - ሰው መሆን ፈልጎ ያልሆነው ነገር አለ ያንን ያለመሆንና የማጣት ስሜት በማውራት ዉስጥ ለማጥፋት ይዳክራል - ልክ ብር ሳይኖረው አንድ ሚሊዮን ብር አለኝ እንደሚለው። አእምሮው የለህም እያለ ስለሚጮህበት ያንን ላለመስማት እንደሚታገል ሰው ይሆናል።
2 953
14
https://youtu.be/xD989ymusfU
449
15
https://youtu.be/DRWZQwtJ9T0?si=LQAbZ3w9FY_sKf4Y
1 058
16
ብዙ ግዜ ፊልም ላይ ያሉት villains የሆነ እውነት አላቸው - ልጅ እያለን ያለን fantasy በ heroው በኩል መሆን ነው - የመጡበትን ሳይሆን እያጠፉ ያለውን ነገር ስለምናይ - ስናድግ ግን በሆነ ያህል የምንረዳው ነገር አለ - maybe ሕይወት ዉስጥ ልጅ ሳለን ያልገባን ስናደድግ የሚገባን ነገር ይኖራል - ጠላት የምንለው አካል በነሱ ዉስጥ የተሰማቸውን ነገር የሚገልጡትና ፅንፍ ያለው ዉሳኔ የሚወስኑት ሌላ ሰው በነሱ ጫማ ዉስጥ የተሰማቸው ስለማይሰማው ነው እሱ ብቻ ሳይሆን George R. R. Martin እንዳለው "Nobody is a villain in their own story. We're all the heroes of our own stories." But everyone has the right and potential to be a villain ግን የማይመርጡትም አሉ በቦታው የነበረው ህመምና ስቃይ የተቋቋሙ። Villain የሌለበት ፊልም ጣዕም አይኖረውም። አስቡት Tom በ Jerry ሕይወት ዉስጥ ባይኖር ተሳዳጅና አሳዳጅ tragedy የመፍጠር ኃይል አላቸው። ትልቁ ልዩነት ያለው ግን villains ራስ ወዳድ በሆነ መልኩ ጥፋትን የሚያደርጉበት መንገድ ነው እንግዲህ እነርሱም ወደው አይደለም የመጡበት መንገድና ያቆሰላቸው ህመም እንጂ - ያለጠላት ደግሞ ጀግና መሆን አትችልም - አንድ ጀግና ወይም ጥሩ ቦታ ያለ ሰው አንድም የምናውቀው ባለው ጠላት ልክ ይመስለኛል - አንድ ግዜ ኤልያስ ሽታሁን "ጥሩ ነገር እያደረገ ብዙ መጥፎ ነገሮች comment ላይ የተፃፉለት ሰው power እንዳለው ያሳየኛል" ብሏል - አሁን algorithm ኡ በሆነ ያህል ቢቀየርም። ሁልግዜ ደግሞ ጀግና ሆነህ አትኖርም በሆነ ሰው ታሪክ ዉስጥ ጠላት መሆንህ አይቀርምና I think ያኔ ነው ሳንፈልግ የሆነን ነገር ሆነን የምንገኘውና የምንረዳው። ከምወደው አንድ የ Villain ጥቅስ መሃል Thanos ያላት ነች "The hardest choices require the strongest wills."/በጣም ከባድ ምርጫዎች በጣም ጠንካራ ፍላጎቶችን ይሻሉ። እናንተ የምትወዱት?
927
17
https://youtu.be/i-0jcl_HQws?si=nGhiC3lvZRG138sG
403
18
የሆነች የማስባት ነገር አለችኝ። ምናልባት የነፃ ፈቃድ ነገርን አግዝፌ ስለማያት ይሆናል። አብዛኛው ግዜ የሚፃፉትን መፅሀፎች ሳያቸው "the will to meaning, the will to power, the will to change, the will to live, the will to believe.... ወዘተርፈ) የሚሉ አሉ። ለሆነች ሃሳብ ወይም ነገር የምንሰጠውን ኃይል ለማውራት ይመስላል ሃሳቡ። እኔ ደግሞ what about the power of will - የነፃ ፈቃድ ኃይል በራሱ። በዚህ context ነፃ ፈቃድ (?) ስል በሆነ ቦታና ግዜ ወደኛ የሚመጡትን ነገሮች ልባችንን ከፍተንን አሜን የምንልበትን ሁኔታ ማለቴ ነው። ሌሎቹ የራስን ነፃ ፈቃድ ለሆነ አንድ ነገር መሰዋት መቻል ሲሆን ይሄ ደግሞ የሚመጡትን ነገሮች የመቀበል፣ ያለመቀበል ጉዳይ ማለቴ ነው። በእርግጥ ነፃ ነን ብንልም የታሰርንባቸው ነገሮች የትየለሌ ናቸው - ስለነገሩ እንዳስብ የሚያደርገኝ ሰዎች ብዙ ግዜ ሃሳብ ሲመጣባቸው ያን ሃሳብ የራሳቸው አድርገው እንግዳ የሆነዉን ቤተኛ ስለሚያደርጉት ነው። ጥቂት ቦታ የሰጠነው ነገር ደግሞ ቤትህን ካልወረስኩ ብሎ የሚገዳደረን ነገር መሆን ይጀምራል። ይሄን ያልኩበት ምክንያት ብዙ ግዜ በሕክምናው OCD (Obsessive Compulsive Disorder) የሚለውን ህመምና the way ነገሩ የሚጀምርበትን pattern ስመለከት ነው - ይሄ ህመም ተደጋጋሚ ፍርሃትን የሚጭሩ ሃሳቦች፣ ስሜቶች እንዲሁም ድርጊቶችን የተላበሰ ነው። እንደምሳሌ ያህል Contamination fear አንደኛው ነው እጅህን ካልታጠብቅ ትታመማለህ ትሞታለህ የሚል ጀርምን የመፍራት እንዲሁም ከመጠን ያለፈ ንፅህናን የመጠበቅ ድርጊት ዉስጥ ይገባሉ እጃቸዉን እስኪቀላ ድረስ ለብዙ ደቂቃ መታጠብን ያመጣሉ (ይሄ የሚነሳው መጀመሪያ ከፈቀድንለት ሃሳብ ይሆናል ቀስ እያለ ሃሳብ ስሜትን - ስሜት ድርጊትን እያለ ሌሎች ተያያዥ ነገሮችን መሳብ ይጀምራል - የሆነ ሃሳብ ሲመጣ ለዛ ሃሳብ ስነልቡናዊ መከፈት ሲኖራችሁ ለዛ ሃሳብ አለመገዛት የማችሉበት ግዜ አለ - ብዙ ግዜ "ነገር" ሲጀምር ይቀል ይመስላል - ሰው አንድን ሃሳብ መመዘን ካልቻለበት ለሆነ ችግር የመጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። ምክንያቱም ሰው የፈቀደውን ነገር ወደፈቀደለት ነገር ራሱን ይዘውራልና (What we allow we become.) ‎
1 552
19
‎ከእንቅልፌ ስነቃ በአይኔ በኩል የዝምታ ጩኸት ዉስጥ ሆኖ የሚያጮልቅ ጥያቄና ሃሳብ አለ። ጣሪያና ግድግዳዬ መልስ ይሰጡኝ ይመስል አፈጥባቸዋለው። እንቅልፍ unconscious ስለሚያደርገንና ንቁ አእምሮን ከእንቅልፍ ከተነሳን በኃላ ቀስ እያለ ስለሚያነቃው በሁለቱ መንቃት አለመንቃት መሃል ላይ አእምሯችን ይዋልላል - ምናልባት በዚህ ሰዓት እንደ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጉም ግድግዳ ላይ አፈጥበታለው ምኑን አለሌ ላከብኝ ማለቱ አይቀርም 😁 ሕይወቴ ጉዞው ወዴት ነው ? የምመርጠው ምርጫ ልክ ነው ወይ ? ሕይወትን እንዴት ነው መኖር ያለብኝ ? የመኖር ትርጉሜ ምንድነው ? ለምን ተፈጠርኩ ? የሕይወት አላማዬ ምንድነው ? ለምንድነው አንዳንዴ ነገር ሁሉ ባዶ ሆኖ የሚታየኝ፣ የሚሰማኝ? ሕይወት ባዶ ናት? ወይስ ትርጉም አላት? ትርጉም ሰጪዋ ማነው? ከየትስ አገኛለው? ያለ ትርጉም መኖር አይቻልም?..ይቻላል? የመኖሬ ህልውና በትርጉም ላይ መቆም አለበት? ከመቼ ጀምሮ ነው እንደዛ የሆነው? በልጅነቴ የሕይወት ትርጉሜ ምን ነበር? ዶክተር? ፓይለት? ወይስ ትልቅ ሰው መሆን? ትልቅ ሰው የመሆን መሻቴ ዉጤቱ ትርጉምን ፍለጋ መባዘን መሆኑስ? አሁን ልጅነት የሚናፍቀኝ አንዱ ምክንያት ትልቅ በመሆን ያጣዉትን ነገር ፍለጋ መሆኑ ነው? እንዲሁ ዝምብለን ነው ምንጋጋጠው? የምን'ገባባቸው ነገሮች ከዚህ የባዶነት ስሜት ለማምለጥ ነው? ታድያ መፍትሄው ምንድነው? እነዚህ ጥያቄዎች ይወቅሩኛል። አይኖቼ ግዑዝ ልሙጥ ነጭ ቅብ ብሎኬት ላይ ያፈጣሉ። አይኔን ከሱ አንስቼ ወደ ኮርኒስ አፈጣለው። እሱም ተወጣው ይለኛል መሰል ፀጥ ያለ ነው። አይኖቼን ወደ ክርስቶስ Icon እልካለው የክርስቶስ ዉበት ላይ ፈዛለው - ረዥም ዝምምምምምምታ.....አንዳንድ ጊዜ ጸጥታና ዝምታ እውነተኛው ትርጉም የሚገኝበት ቦታ ይሆናል። ‎ ‎የዘመኑ መንፈስ ይጠናወተናል - አንድ ላይ የሆነ ምጥ እናምጣለን። እዚህ ዘመን ላይ በተለየ መልኩ ይመስለኛል የሕይወት ትርጉም የሚነሳው - እየኖርኩበት ያለውት ይሄን ዘመን ስለሆነ - የመኖር ትርጉማችን ከሰዎች ጋር እንዳለን ጉዳይ ላይ የሚወሰን ነው። ለምን ከተባለ ማህበረሰባችን ቆሞ የነበረው በክርስትና አውድ ዉስጥ ነበር/ነውም - ነበር ያልኩበት Nietzsche እንደሚለው በሆነ መልኩ "God is dead. God remains dead. And we have killed him" እንዳለው ነው። ለምን ከተባለ የዚህ ዉጤቱ Individualism መሆኑ ነው - የመኖር ትርጉም ለሕይወት ጣዕም የሚሰጥ ነው። የሆነ የምንታገለው ነገር አለን ማለት ነው - የሌላውን ትግል ደግሞ እንደራሴ ትግል አለማየት ደረጃ መድረስና የሌላው ሰው suffering ምንተዳዬ ማለት ስጀምር ጉርብትነታችንን የሚያቆሙ value ዎች መሞት ጀምረዋል ማለት ነው። እነዛ የሚያገናኙን እሴቶች ቀስ በቀስ ገድለናቸዋል - ያንን ነው God is dead የሚለው - Individualistic ስንሆን አንዱ ችግር ደግሞ ደስታ የሚሰጠኝ ምንድነው? ወደሚለው ነገር ያመራናል። ያን ስናይ የምንሰበስበው ቁስ ዉስጥ መገኘት እንጀምራለን። ይሄን ስገዛ፣ ይሄ ሲኖረኝ የሚለው materialistic ላይ እንደርሳለን። ያ ያብስብናል እንጂ አያድነንም ምክንያቱም ይሰጠናል ብለን ምናስበው ነገር ስንይዘው ትልቅ ባዶነት ላይ ስለሚያደርሰን። ለዚህ መፍትሄ Albert Camus ሶስት መፍትሄዎች አለ ይላል። 2ቱን አይቀበልም እነርሱም የመጀመርያው Suicide ነው - ራስን ማጥፋት። 2ኛው Philosophical Suicide ወይንም ሽሽት በሉት ከዚህ ወለፈንድ ስሜት ለመውጣት ሰዎች ሃይማኖትን መሸሸጊያ/መደበቂያ ያረጉታል ነው። የመጨረሻው ግን እኛ የሕይወት ትርጉምን ብናምጥም ዓለም ያንን ስለማትሰጥ ያንን አምኖ መቀበል ነው ይለዋል። ምን ማለት ነው? ስንል የምር ሕይወት ትርጉም እንደሌላት ብታምን ምን አይነት ሰዉነት ላይ ትደርሳለህ? የምትወስነው ዉሳኔ ምን ይሆናል? ይሄን መቀበል ትችላለህ ወይ? ሰው መሆንህን የሚያሳጣ ከሆነስ? ያን የመሸከም አቅም አለህ? ያ ይወስነዋል! ‎ከዚህ ጋር ተያይዞ እሱ የሚለው የራስን ትርጉም መፍጠር ነው ግን መፍጠር እንችላለን ወይ? መፍጠር ስንል ምን ማለታችን ነው? ሰው እስከሆንን ከተፈጠሩ መሃል እንፈልጋለን እንጂ እንዲሁ Out of Existence አንድን ነገር Exist እንዲያረግ የማድረግ አቅም ያለን አይመስለኝም። ግን የራስ ትርጉም መፍጠር በሚለው ላይ ብንመጣ እንኳ ለኔ ትርጉም የሰጠኝ እኔን የሚያስደስተኝ ነገር ሌላውን የሚጎዳ ነገር ቢሆንስ? የሕይወት ትርጉም መለኪያው ምንድነው ? የሚሉት ጥያቄዎችን መመለሱ አስፈላጊ ይመስለኛል   - እኔ ጥሩ መፍትሄ ነው ብዬ ማስበው 2ኛውን ነው Philosophical Suicide ኡን Intentional ማድረግ ነው - ማለት ባላችሁበት የሃይማኖት ቅጥር ዉስጥ ያሉትን ነገሮች እንዲሁ በደፈናው ሳይሆን ነገርን መርምሩ እንዳለው መርምሮ በዛ ዉስጥ ለመኖር መታገል ይመስለኛል - መሸሽን መታገል... ለመሸሽ ለመደበቅ ሳይሆን እየተሰማን ያለውን ባዶነት ይዘን Authentically እንድንኖር የሚያደርጉንን Value ምንድነው የሚለው ብሎ መጠየቅ መመርመርና ማሰቡ ጥሩ ነው ሕይወት ትርጉም ላይኖራት ይችላል የሚለው ሸክም ችለን ግን መልሶ Redefine እያደረግን እንደ ተነገረው ንግርት ወይም ትርጉም ዉስጥ ለማስተዋልና ለመረዳት መሞከር ማለት ነው ለምን ከተባለ በነዚህ ቅጥር ዉስጥ ፅንፍ ግለሰባዊነት የለምና እንደ ሰው ሊያኖሩን የመኖርን ጣዕም የምናገኝበትን ነገር ይሰጣሉና እሱ ብቻ ሳይሆን እንኳ በነዚህ ቅጥር ዉስጥ ቀርቶ በዓለም ቅጥር ዉስጥ ያሉት ዉበት፣ ደግነት፣ እውነት የምንላቸው ነገሮች ከራሳቸው አልፈው የሚጠቁሙት አካል አለ ያ ብርቱካን ጣዕሙ እንዲህ ነው ከመባል ያልፋል ስትቀምሱት የምትረዱት ተሞክሮ አለና ወደ ቀደመ ነገሬ ስመለስ ሁለቱንም በአንድ ሰዉነት ዉስጥ ማስገኘት መቻል የራስን ትርጉም የተሻለ በሚለው በመንፈሳዊ ቅጥር ዉስጥ ፈልጎ ማግኘትን ያመጣል። ✍️ ልደቱ ተስፋነህ
2 654
20
https://youtu.be/s3yiA1QwCqQ
448