Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
رفتن به کانال در Telegram
This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
نمایش بیشتر4 440
مشترکین
-124 ساعت
-417 روز
-8230 روز
آرشیو پست ها
የአዲስ አበባ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየተደረገ ስላለው የመብት ጥሰትን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ደብዳቤ አስገባ
ህብረቱ ለተቋሙ ባስገባው ደብዳቤ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው "የተማሪዎች የሥነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ውስጠ ደንብ" ላይ ማንነትን ለመለየት በሚል ኒቃብ መልበስን መከልከሉ እና ይህም እህቶቻችን በትምህርታቸው ላይ ከፍተኛ እንግልት እንዲደርስባቸው ማድረጉ ገልጿል። በተጨማሪ ህብረቱ ለዩኒቨርሲቲው አመራር ምክንያታዊ አማራጮችን ቢያቀርብም፣ የዩኒቨርሲቲው አመራር ይህንን ሳይቀበል ቀርቷል።
ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት የተቀመጡትን የሃይማኖት ነፃነት፣ የእኩልነት እና የመማር መብቶችን የሚጥስ ከመሆኑም በላይ፣ እንደ UDHR እና ACHPR ያሉ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም የሚጋጭ መሆኑ ተብራርቷል። በመጨረሻም ህብረቱ ጉዳዩን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቅርበት እንዲከታተለው፣ ፈጣን ምርመራ እንዲያደርግ እና በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርቧል።
በተጨማሪ ህብረቱ የደብዳቤውን ግልባጭ ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ለማስገባት የሞከረ ቢሆንም ነገር ግን ደብዳቤውን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል
ህብረታችን የተማሪዎችን መብት ለማስከበር በሰላማዊ እና በህጋዊ መንገድ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።
#እንደለበሰች_ትማራለች
@aaumsu
የAAU ሙስሊም ተማሪዎችን የሰብዓዊ መብት ጥያቄ አስመልክቶ ዶክተር ሳሙኤል በሰጡት መልስ ላይ የተነሱ ጥያቄዎች እና መጠነኛ ማብራሪያዎች:-
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደ ኒቃብ ያሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን የሚገድብ መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ፣ ለቀረቡ ጥያቄዎች የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የሰጡት ምላሽ ከመንደርደሪያ እስከ መደምደሚያው መሠረታዊ የሕግ እና የፅንሰ-ሐሳብ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ሆኖ ተገኝቷል። ፕሬዚዳንቱ ትምህርት ማህበራዊ ልማት ስለሆነ ከባህል፣ ከሃይማኖት እና ፖለቲካ ተፅዕኖ ውጪ ይፈፀማል በሚል መንደርደሪያ ንግግራቸውን ቢጀምሩም፣ አንዲት ሙስሊም ተማሪ ኒቃብ በመልበሷ በትምህርት ሂደት ላይ የምታሳድረው "ሃይማኖታዊ ተፅዕኖ" ምን እንደሆነ ግን ግልጽ አይደለም። ሴኩላር እንዲሆን የሚፈለገው የትምህርት ስርዓቱ እንጂ የተማሪው ማንነት አለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። እንደ ኒቃብ ያሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን መገደብና "ካላወለቃችሁ አትማሩም" ወይም "የዩኒቨርሲቲውን አገልግሎት አታገኙም" ማለት ዓለምአቀፋዊ የሆነውን ሰብዓዊ መብት ከመጋፋትም በላይ፣ "ሃይማኖትህን ጥለህ ካልገባህ አትማርም" የሚል አግባብነት የሌለው ጣልቃ-ገብነት በመሆኑ የሴኩላሪዝምን መርህ ይጥሳል። ተማሪውንም ከሃይማኖቱ ነጥሎ ምን ዓይነት ትውልድ ለመፍጠር ታስቦ እንደሆነ የሚያጠያይቅ ሲሆን፣ ሃይማኖት አልባነትም ራሱን የቻለ እሳቤ መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች የሚሰወር አይሆንም።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ሳይንስ ሰውን ከመጣበት የዝግመተ ለውጥ (Evolution) ታሪክ አንጻር እንደሚያስተምርና ተማሪውም ይህ ከሃይማኖቴ ጋር ይጋጫል ብሎ "አልፈተንም" ማለት እንደማይችል ጠቅሰዋል። ይህ ትክክለኛ ገለፃ ቢሆንም፣ ከተማሪዎቹ የእምነት ነፃነት ጥያቄ ጋር ግን በቀጥታ አይገናኝም። ተማሪዎች እያነሱ ያሉት ጥያቄ "ትምህርቱ ከእምነቴ ጋር ስለሚጋጭ አልማርም" የሚል ሳይሆን፣ ትምህርቱን እየተማሩ እምነታቸው የሚያዘውን መለኮታዊ አለባበስ በተለይም የኒቃብ አጠቃቀምን የመተግበር መብታቸው እንዲከበር ነው። ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሳይንሳዊ እውቀትን እንዲቀስሙ የማድረግ መብት እንዳለው ሁሉ፣ የአንድን ተማሪ ሃይማኖታዊ አለባበስ "አውልቅ" ብሎ የማስገደድ ስልጣን ግን የለውም። እዚህ ጋ ማነው ሕገ-መንግስቱን፣ ዓለምአቀፍ ሰብዓዊ መብቶችን እና ከመማርና ሃይማኖትን ከመተግበር ጋር የተደነገጉ ሕግጋትን እየጣሰ ያለው የሚለው ነጥብ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል።
በተጨማሪም ትምህርት ማንነትን በግልፅ እንዲታይ እና መምህር የተማሪን ስሜት ማንበብ የሚችልበትን የፊት ለፊት ግንኙነት እንደሚፈልግ፣ ለዚህም ሲባል የኒቃብ አለባበስን የመተግባር መብት ሊገደብ እንደሚችል የቀረበው መከራከሪያ በዘመናዊው የትምህርት ዓለም ተቀባይነት ያለው አይደለም። መምህር የተማሪን ስሜት ማንበብ ግዴታ ከሆነ፣ በአሁኑ ወቅት በስፋት እየተሰጡ ያሉ የርቀት ትምህርቶች ስህተት ናቸው ሊባል ነውን? በዓለም ዙሪያ ያሉና በትምህርት ጥራት ከዩኒቨርሲቲያችን የሚልቁ የልህቀት ማዕከላት እንደ ኒቃብ ያሉ ሃይማኖታዊ አለባበሶችን ሳይከለክሉ ስኬታማ መሆናቸው እየታወቀ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይህንን እንደ ምክንያት ማቅረቡ አሳማኝ አይሆንም። ፕሬዚዳንቱ "ተማሪ Civic እንዲሆን እንፈልጋለን" በማለት የሰጡት መደምደሚያም ቢሆን፣ ሲቪክ መሆን ማለት ሃይማኖትን ከመተግበርና ከመከተል ነፃ መሆን ማለት ነው የሚል እሳቤ ካለው ወዴት እያመራን እንደሆነ ጥያቄ ያስነሳል። ሲቪክ መሆን እና አማኝ መሆን እርስ በእርስ የሚደጋገፉ እንጂ የሚቃረኑ እሴቶች አይደሉም።
ሰብዓዊ መብቶች ሊገደቡ የሚችሉት በፓርላማ በሚወጣ አዋጅ እንጂ ተቋማት በሚያወጡት መመሪያ ብቻ ሊሆን አይገባም። በዚህ ጉዳይ ፓርላማው አዋጅ ሳያወጣ ወይም ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሳያፀድቅ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተለይቶ መብቶችን የሚገድብ መመሪያ ያወጣው ለምንድን ነው? ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም ባወጣውና በያዝነው ዓመት ባሻሻለው የተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት፤ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብን፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች ደግሞ ነጠላን ለብሰው የዩኒቨርሲቲውን አገልግሎት እንዳያገኙ የሚከለክል አንቀጽ መኖሩን ልብ ይሏል። በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከትምህርታቸው የሚያዘናጋ አጀንዳ ከመስጠት ይልቅ፣ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በመውሰድ የተማሪዎችን ሰብዓዊ መብት በማክበር ለተሻለ የትምህርት ስርዓት ግብዓት እንዲሆኑ ማስቻሉ መልካም ነው።
©️ aaumsu
https://t.me/EHEMSU
"AAU ኒቃብን በመከልከሉ ምክንያት ለ15 ቀናት ከካፌ የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ነበሩ:: በFBE: Commerce: ያሬድ ካምፓሶች አትገቡም ተብለው ከበር የቆሙበት ጊዜም ነበር:: መማሪያ ክፍል ውስጥም የተለያዬ እንቅፋት የተፈጠረባቸው ተማሪዎች አሉ:: ይህ ሁሉ የሆነው ሕገ- መንግስታዊ መብቶችን በማፈን በወጣው መመሪያ ምክንያት ነው:: እስካሁን የደረሰባቸው መበደልም ቆሞ ለመብታቸው ዋስትና የሆነን መመሪያ በማውጣት ሊካሱ ይገባል::" - ተማሪ ሙሐመድአሚን ካሳው ETV ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ከተናገረው
ሆኖም ግን ከተለቀቀው ፕሮግራም እንደተገነዘብነው ይህ እና መሠል የተማሪዎችን ጥያቄ የሚገልፁ መልዕክቶች ተቆርጠው ቀርተዋል:: ይህም በመሆኑ የጥያቄው ሙሉ መንፈስ ሊንፀባረቅ አልቻለም::
ለመሠል ፕሮግራሞች ሽፋን የሚሰጡ ሀገራዊ ሚዲያዎች ለተቋም ግንባታ ያላቸውን አስተዋፅዖ ታሳቢ አድርገው ተማሪዎች እየጠየቋቸው ያሉትን የመብት ጥያቄ ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ እንዲያስተላልፉ እንጠይቃለን:: የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የሰጡት ምላሽም በተማሪዎች ዘንድ ሰፊ ጥያቄን በማስነሳት ላይ ያለ ከመሆኑም ባሻገር ለመልሳቸው በራሱ ብዙ ጥያቄዎች አሉን:: ስለሆነም ETVም ሆነ ከእርሱ ውጪ ያሉ የመንግስት ሚዲያዎች: ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የተቋቋሙ ሚዲያዎች እንዲሁም ስለ ሰብዓዊ መብት የሚጠይቁ አካላት ሁሉ ከፀደቀ ጀምሮ የሙስሊም ተማሪዎች መብት እንዲጣስ እያደረገ ስላለው የAAU መመሪያ እንዲጠይቁ እና ፍትሐዊ የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡ እንጠይቃለን::
@aaumsu
የAAU ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ኒቃብን እና ሌሎች የተማሪዎች ሕገ-መንግስታዊ መብቶችን አስመልክቶ ከተማሪ ሙሐመድአሚን ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡት መልስ ነው:-
"መምህር የተማሪን ፊት ማየት እና Emotion ማንበብ አለበት:: ተማሪዎች Civic መሆን አለባቸው:: አለባበሶች እና የግል ሁኔታዎች ሊገደቡ ይችላሉ:: ተማሪዎቻችን ተማሪ እንዲመስሉ እንፈልጋለን:: ተማሪን Civic ማድረግ ሕገ-መንግስታዊ ሁኔታዎችን አይጋፋም:: በዚህ ረገድ ሕገ-መንግስታዊ መብቶችን መገደብ እንችላለን::"
ሙሉውን አዳምጡት
ተማሪ ተማሪ መሠለ የሚባለው መች ነው? ተማሪ Civic ሆነ የሚባለውስ መች ነው? ሕገ-መንግስታዊ መብቶችን ከፓርላማ ውጪ ያሉ ተቋማት መገደብ የጀመሩት ከመች ወዲህ ነው?
We have a question !
@MohammadamminKassaw
ኢዜማ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የራሱን ፖሊሲ ሲያስፈጽም መቆየቱን ገለጸ!
- ሀሩን ሚዲያ፥ ታህሳስ 8/2018 ዓ.ል
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሱን የፓርቲ ፖሊሲ ሲያስፈጽም መቆየቱን በይፋ አስታውቋል።
ፓርቲው ማክሰኞ ታኅሣሥ 7 ቀን 2018 ዓ.ል ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፤ የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ሆነው በተሾሙባቸው ባለፉት አራት ዓመታት የኢዜማን የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጿል።
የፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኢዮብ መሣፍንት እንደተናገሩት፤ ሚኒስትሩ "ያመኑበትን ሲሰሩ ነው የቆዩት" ያሉ ሲሆን፣ ይህም ለቀጣዩ ምርጫ ቅስቀሳ የሚጠቀሙበት ትልቅ ስኬታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የኢዜማ ይፋዊ መግለጫ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋትና ጥያቄን ቀስቅሷል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሚኒስቴሩን በመሩባቸው የእነዚህ ዓመታት ጊዜያት በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዲሁም ኒቃብ እንዳይለብሱ ተከልክለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እያሉ ሰላት እንዳይሰግዱ/የሰላት ስነ-ስርዓት እንዳያከናውኑ/ በመከልከላቸው ከትምህርት ገበታቸው የተሰናበቱና ለእንግልት የተዳረጉ በርካታ ናቸው።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የእምነቱ ተከታዮች "ለእምነታችን ነጻነት ይከበር" በማለታቸው የአካልና የሞራል ጥቃት ደርሶባቸዋል።
ፓርቲው "ያለማንም ጣልቃ ገብነት የራሳችንን ፖሊሲ አስፈጽመናል" ማለቱ፤ ባለፉት ዓመታት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ሲፈጸም የነበረው አድልዎ እና የሀይማኖት ነጻነት መገፈፍ የፓርቲው እቅድ አካል ነበርን? የሚል መሠረታዊ ጥያቄ አስነስቷል።
ኢዜማ በምርጫ 2018 እንደሚሳተፍና እነዚህን ስራዎቹን ለቅስቀሳ እንደሚጠቀምባቸው ቢገልጽም፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ግን ይህ "የፓርቲ ፖሊሲ" የተባለው አካሄድ የእምነት ነጻነትን የሚጋፋና ዜጎችን ከትምህርት ገበታ የሚያፈናቅል መሆኑን በተደጋጋሚ ሲያመለክት ቆይቷል።
ባለፉት ዓመታት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የደረሰው የሂጃብ እና የሰላት እገዳ ከፓርቲው እቅድ ጋር ስለመያያዙ የገለጸው ነገር የለም!
© ሀሩን ሚዲያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን አስመልክቶ ምን አለ? ከፕሬዚዳንቱ ንግግር ይስሙ ...
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረትስ ምን ምላሽ ሰጠ? ከሕብረቱ ተወካዮች ያድምጡ
ኡስታዞችስ ምን አሉ? ኡስታዝ ካሚል ጣሃ ያሉትን ይከታተሉ
ሁሉም በዚህ አጭር ቪድዮ ውስጥ ተካቷል ... ለሌሎችም Share መደረግ እንዳይዘነጋ
ሙስሊሙ ተማሪ ጥያቄ አለው ... የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የዚህ ትውልድ አደራ ነውም ብሏል ! ! !
@aaumsu
"በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የእስልምና እምነት ተከታይ ተማሪዎች ላይ አድሎ ይፈፀማል በማለት የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ ተሳታፊ ሆኗል በሚል ክስ የቀረበብህ ስለሆነ ... !" - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ከሰጠው የክስ መጥሪያ ወረቀት
ዩኒቨርሲቲያችን ሙስሊም ተማሪዎችን የሚያገል መመሪያውን እንዲያስተካክል አሁንም ጥሪያችን ነው:: በግልፅ በመመሪያ በተቀመጠ ድንጋጌ ሙስሊም ኒቃቢስቶችን አግልሎ ሲያበቃ አድሎ ፈፅመሃል መባሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው ብሎ የሙስሊም ተማሪዎችን ተወካዮች መክሰስ አግባብነት የለውም:: ሙስሊም ተማሪዎች እንዲስተካከል እየጠየቁት ያለው የስነ-ስርዓት መመሪያው ክፍል በአንቀፅ 6.6 ላይ እንደሚከተለው ተቀምጧል::
"በዩኒቨርሲቲው ከሚከናወኑ የመማር ማስተማር ተግባራትና ከሚሰጡ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ማንነትን ለመለየት ሲባል በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ፊትን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑ አለባበሶችን መልበስ የተከለከለ ነው።"
ይህ በግልፅ ኒቃቢስት ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዳይገቡ የሚከለክል ድንጋጌ ነው:: ይህ መሆኑ ዛሬ በዩኒቨርሲቲው እየተማሩ ካሉት ባሻገር ሕልማቸውን በAAU ለመማር ያደረጉ ኒቃቢስቶችን ሕልም የሚያጨናግፍ ነው:: የአንድን ሕዝብ መገለጫ ማንነት የሚያገል ነው::
ስለሆነም አሁንም ቢሆን ይህንን ድንጋጌ በማሻሻል ለሙስሊም ተማሪዎች ደህንነት እውቅና የሚሰጥ እና ከለላ የሚያበጅ ድንጋጌ ይወጣ ዘንድ እንጠይቃለን::
የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ የዚህ ትውልድ አደራ ነው ... አይሻገርም !
@aaumsu
+2
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ከኢትዮጵያ ሙስሊም የሕግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ !
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
ህዳር 26 / 2018 ዓ.ል
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
ሙስሊም ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚደርስባቸውን ሰብዓዊ የመብት ጥሰት ለመከላከል እና በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን እንዲጠይቁ ለማድረግ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ለማስጠበቅ እና ያላቸውን አዎንታዊ አስተዋፅዖ ለማሰደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከኢትዮጵያ ሙስሊም የሕግ ባለሙያዎች ጋር ተፈራርሟል:: ስምምነቱን በሕብረቱ ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው እና በማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙህዲን ጀማል መካከል የተፈረመ ሲሆን ወደፊት በሚሰሩ ዝርዝር ተግባራትም ውይይት ተደርጎል::
አላህ ለመልካም ለውጥ እና ለተሻለ ሁኔታ ሰበብ ያደርገው ዘንድ ዱዓችን ነው ! ! !
ውድ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የሪሜዳል ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ!!
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ፦
Assalaamhwaalayiku worahmatullahi wobarakaatuhu፦
ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተመደባች የremedial) ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ እንደሚታወቀው በ2018 ዓ.ል ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የተመደቡ የሪሜዳል ሙስሊም ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ታህሳስ 02 እና 03 2018 አ.ል እንደሆነ ይታወቃል።
Nagaa fi nageenya insiniif haa ta'u!!
yaa barattoota Muslimaa gara yuuniversiti dabra Maarqoositti dirqamaa fi beekumsa dabalataa(remedial) itti fufsiifatan! Akukuma beekanu,barattoonni remedial 2018 wagga tti yuuniversiitii dabra maarqoositi dirqaman,guyyaa isaan mana barumsaa seenan Tasassa 02 fi 03 2018 ta'uu beekama.
ስለሆነም ይህን በማስመልከት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ሙስሊም ወንድምና እህቶቹን ተቀብሎ ማንኛውንም ዲናዊም ሆነ አካዳሚክ መረጃዎችን ለመስጠት እንዲሁም ስለሌሎች ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉ አዲስ ነገሮች በሙሉ የሚያስፈልጓችሁን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ሙሉ ዝግጅታቸውን አድርገው የናንተን መምጣት ብቻ በጉጉት እየጠበቁ ይገኛሉ።
Kannaf,kanarra ka'uudhaan, Gamaaleen Muslimaa Yuuniversiitii Dabra Maarkoos(jama'a) oggaantotaafi obboloota Muslimaa keessan fudhachuuf,beekumsa amantii,fi aadaa hunda isiniif kennuuf,fi haala haaraa kan muraasni isin tuqu danda'u irratti isin gargaaruuf,akkasumas deeggarsa isiniifi barbaachisu hunda kenyaaf dirqamaa qopheessee,seenaa keessan qofa eeggachaa jira.
ስለዚህ ስለሚያስፈልጋችሁ ማንኛውም አይነት ጥያቄም ይሁን ትብብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ስልኮች ደውላችሁ ሙሉ መረጃ ማግኘት እና ያለምንም እንግድነት ስሜት ውድ ጀመዐችንን መቀላቀል ትችላላችሁ ስንል ትብብራችንን እንገልጻለን።
አላህ እኛንም እናንተንም ሰላም አድርጎ
በሰላም እንዲያቀላቅለን እንጠይቀዋለን።
Kanaaf,yoo deeggarsa dandeessaa ykn gaaffii barbaachisa qabaatan, lakkoofsa bilbilaa aramaan qadii tuqiidhaan odeeffannoo guutuu argschuu fi gamaalee kenya jaalatamoo( jama'a) tii walqunnamtii mijeessuu dandeessuudhaan,deeggarsa keenya ifa baasna.
✅ወንድም አህመድ፦
📞0973780733
✅ወንድም ኑረድን፦
📞0968192873
✅ወንድም ጅብሪል፦
📞 0929628329
✅ወንድም አልይ፦
📞 0905951202
✅ወንድም አብዱል ሀሚድ፦
📞0935873486
*️⃣ መልካም ጉዞ። አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን!!!
*️⃣ Waa'ee keengaas,waa'ee keessaniifis naggan akku nu walsimu Rabbi hajedhu!!!
Imala gaarii rabbiin isin woliin haa ta'u.
*️⃣ የእህቶችን አድራሻ ለማግኘት፦
📞 0968192873
https://t.me/EHEMSU
AMBO UNIVERSITY MUSLIM STUDENTS JEMA'A
Aselamualeykum werhmetullahi weberekatu
በ 2018 ዐ.ል ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬሜዲያል(የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ህዳር 29 እና 30 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል::
የ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ (AUMSJ)እናንተን ሙስሊም ወንድም እና እህቶችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ያለ ሲሆን ከመምጣታችሁ በፊትም ይሁን በ መግቢያችሁ ቀን የሚያስፈልጋችሁን ማንኛውም መረጃ ለማግኘት ከታች በተዘረዘሩት የስልክ ቁጥሮች መደወል ትችላላችሁ::
Yuunvarsitiin Amboo akka beeksisetti, barattoonni sagantaa sirreeffama (remedial program) bara 2018 A.L.I Yuunvarsitii Ambootti ramadamtan, guyyaan gara mooraa seentan Sadaasa29 fi 30 ta'uu ibsee jira.
Jama'aan Barattoota Muslimaa Yuunvarsitii Amboo (AUMSJ) obboleewwan keenya Muslimoota dhiiraa fi dubartoota isin simachuuf qophii irra jira.
Odeeffanno barbaachisaa ta'e kamuu argachuuf lakkoofsota bilbilaa gadiitti tarreeffamanitti bilbiluun nu qunnamuu dandeessu.
## For Natural science( Hachalu Hundesa Campus)
1.Zaakir (Hachalu Campus)
+251913044612
2.Muhammad Arab (Hachalu Campus)
0904190352
## For social science (main campus)
📞 Saadaam Abdusamad– +251926630411
📞 Muusaa Ibraahim – 0917544231
📞 Jamaal Aliyyii – +251918934445
የእህቶችን ስልክ ለማግኘት +251926630411 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ::
Ambo University Muslim Students’ Jema’a
https://t.me/EHEMSU
የAAU ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት አመራሮች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት በሀሩን ሚዲያ ስለ ሙስሊም ተማሪዎች መብት ፕሮግራም ካቀረቡ ቡሃላ በAAU የፀጥታ አካላት የዲሲፕሊን ጥፋት ሰርታችሗል በሚል ቃላቸውን እንደሰጡ ተገለፀ !
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ህዳር 24 / 2018 ዓ.ል
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው የዩኒቨርሲቲው ጀመዓ ፕሬዚዳንት መሕፉዝ ነጋሽ: ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱልሐሚድ አሕመድ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ በሀሩን ሚዲያ ፕሮግራም ካዘጋጁ ቡሃላ የሕብረቱን ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት: በሕብረቱ የ6ኪሎ ጀመዓ አሚር የሆነውን አብዱረሒም አሚን እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዚዳንት የሆነውን ሙሐመድአሚን ካሳው የዩኒቨርሲቲው የፀጥታ አካላት ጠርተው "በሀሩን ሚዲያ ቀርቦ የዩኒቨርሲቲውን ስም በማጥፋት እውቅና ሳይኖራቸው የሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ነን በማለት: አገባብነት በሌለው መልኩ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ወዘተ... ::" በሚሉ ጉዳዮች እንደተከሰሱ በመግለፅ ቃላቸውን ተቀብለዋል::
ሕብረቱ መሠል አካሄዶች ሙስሊም ተማሪዎች ከአመት በላይ ሲጠይቁት የነበረውን የመብት ጥያቄ ችላ ያለ እና የሙስሊም ተማሪዎችን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የሚገድብ እንደሆነ በመጥቀስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ዘላቂ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል::
@MohammadamminKassaw
"በጅህልና ከመቀጣት በላይ ቅጣት የለም:: በጅሕልና ሊቀጡን ያሰቡትን ሰዎች ግን ልቀን ከትልቅ ደረጃ ደርሰን እናሳያቸዋለን::" - የጉንችሬዋ እህት
"በዚህ ምክንያት (በሒጃብ ክልከላ) ተባረናልም ተፈናቅለናልም (ከትምህርት)::" - ሸሕ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ
"በጅልባብ ምክንያት ማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩ ሴት ተማሪዎች ነበሩ:: በሒጃብ ክልከላ ምክንያት ተማሪዎች በገፍ ታስረው: ተባረው ተሳደው ነበር::" - ሙሐመድአሚን ካሳው
:- ሙሉውን አዳምጡት ... ለሌሎችም ማጋራት እንዳይዘነጋ ! ! !
@MohammadamminKassaw
"ማንም ሒጃብን ለበሰ ተብሎ መከልከል የለበትም:: ኒቃብ is a different story (ኒቃብ ሒጃብ አይደለም እንደማለታቸው ነው) ::" - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
"ይሄ ሒጃብ ነው ያ ኒቃብ ነው እንዴት ይላሉ? ማን ነው የለየላችሁ?" - ሸህ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ
" የትምህርት አካላት ኒቃብ እና ሒጃብን ለመለያየት ሲሞክሩ ሴኩላሪዝምን ሙሉ ለሙሉ እየደፈጠጡ ነው::" - ሙሐመድአሚን ካሳው
ዝርዝር ማብራሪያውን ከቪድዮው ይመልከቱ ... ለሌሎችም ያሰራጩ ! ! !
@MohammadamminKassaw
በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የመብት ጥሰት ... ከድሮ እስከ ዘንድሮ ... በሙሐመድአሚን ካሳው ! ! !
@MohammadamminKassaw
ኒቃቢስቶቹ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ደምቀዋል
ትግሉ ለዚህ ነበር
የታገሉት ለዚህ ነበር
የምንታገለውም ለዚህ ነው
ኒቃብን ለአመታት ከልክሎ በሙስሊም ተማሪዎች ትግል ክልከላውን በገታው ጅማ ዩኒቨርሲቲ "በጋራ ጎበዞቹን እንሸልም!" - ፕሮግራም ላይ ኒቃቢስቶቹ በጋራ ደምቀው ተሸልመዋል::
ዶክተር አይሻ ደኬቦ ... 3.89 በማስመዝገብ ከኮሌጇ ሰቃይ ሆናለኅ ... ደግሞ የአግሪ ካምፓስ ጀመዓ አሚራ ናት::
ሌላኛዋ ... ዶክተር ደሜ ቶላ ... 3.45 በማምጣት ተሸላሚ ሆናለች ... ይህችኛዋ ደግሞ የጀመዓው ሶሻል ሴክተር አሚራ ነች::
Congrats... 😍
በዚህ ውስጥ ለሁሉም ሰው ድንቅ ተምሳሌትነት አለ !
የእነዚህ እንቁ ልጆች ኒቃብ የመልበስ መብት በሕግ እስኪፀና እና ከለላ እስኪሰጣቸው ድረስ መታገል የሁሉም ሀገር ወዳድ ሀላፊነት ነው ! ! !
@MohammadamminKassaw
ከሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ጥያቄ እና መፍትሔዎች ጋር ተያይዞ በሐሩን ሚዲያ የተዘጋጀው ፕሮግራም ተለቋል ... በተከታዩ ሊንክ ገብተው ይከታተሉ::
https://youtu.be/fnbO4WjfM7E?si=Bbk3fvBoq5Bhutyi
በሙስሊም ተማሪዎች ሶላት እና ሒጃብን ሰበብ አድርጎ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ተዳስሷል ... የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው እንዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት መህፉት ነጋሽ እና ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱልሐሚድ አሕመድ ሰፊ ማብራሪያዎችን አስቀምጠዋል ! ! !
ምሽት 2:00 በሀሩን ሚዲያ እንገናኝ ! ! !
በመጅሊሱ የተቋቋመው ግብረ ሀይል ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዘላቂ መፍትሄ ለመምጣት ውይይት ማካሄድ ጀመረ
በትምህርት ተቋማት ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት እየተፈጠሩ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎችን በአለባበስ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የማፈናቀል ተግባር በቋሚነት እልባት ያገኝ ዘንድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግብረ ሀይል በማቋቋም እየተንቀሳቀሰ ይገኛል::
ይህ ግብረ ሀይልም ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የመጀመሪያውን ጥልቅ ውይይት ያካሄደ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ሊሰሩ በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::
@MohammadamminKassaw
