Dr. Estifanos(MD, Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ
رفتن به کانال در Telegram
ለ አዕምሮ ህክምና እና ምርመራ በ 0949476776 ይደውሉ በ Rama psychiatry & Rehabilitation center ያገኙኛል 📌ራማ የአዕምሮ ህክምና ማዕከል 📞+2519-85-52-88-88 📞+2519-99-67-68-69 📍:- Ayat Square,200m On the Main Road to Arabsa.(use google map).https://maps.app.goo.gl/yuEA1YiY76BCE6Q
نمایش بیشتر2 902
مشترکین
-224 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+1630 روز
آرشیو پست ها
+1
ዛሬ በተደረገው የአመቱ የ LinkedIn ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት: በ ''አዕምሮ ግንዛቤ ማስጨበጥ ዘርፍ'' ተሸላሚ መሆኔን ሳበስራችሁ ከታላቅ ደስታ ጋር ነው::
በዚህ የሽልማት ሂደት ድምጽ ለሰጣችሁኝ በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ:: ይህን ሽልማት ላዘጋጃችሁ አባላት አክብሮቴ ከፍ ያለ ነው::
ይህ ሽልማት በአዕምሮ ጤና ዙሪያ ለምሰራቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥርልኝ ነውና ከታላቅ አክብሮት ጋር ተቀብዬዋለሁ::
ያለ አዕምሮ ጤና: ጤና የለም!
ኒውማ ኢትዮጵያ (Pneuma Ethiopia) የበጎ አድራጎት ድርጅት 3ኛ የምስረታ ዓመቱን ባከበረበት ዕለት በዝግጅቱ የመታደም ዕድል ገጥሞኝ ነበር።
ኒውማን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅሁት የዛሬ ሶስት ዓመት በቀሲስ ዘክርስቶስ ቀስቃሽነት በሳህሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ጎዳና ላይ የነበሩ ወገኖቻችን ተነስተው ኮተቤ አካባቢ ወደ ነበረ ማቆያ ከገቡ በኃላ ነበር።
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሶስት አመታት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ስር የሚካሄደው የማህበረሰብ ድጋፍ አካል በመሆን ሙያዊ እርዳታ ሳደረግ ቆይቻለሁ።
በዚህም ተሞክሮ የመንፈሳዊው እና ዘመናዊው ሳይንሳዊ የአእምሮ ህክምና ጥምረት የሚያስገኘውን በጎ ውጤት ለመታዘብ ችያለሁ።
ኒውማ ኢትዮጵያ በቻይና ያየነውን የባህል/መንፈሳዊ-ዘመናዊ ህክምና ውህደት በአገራችን ያሉ ተቋማትም በመሞከር ላይ እንደሚገኙ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ከኒውማ ባሻገር መንፈሳዊ ህክምናን ከዘመናዊው የአእምሮ ህክምና ጋር አቀናጅቶ በመስጠት የሱስ እና የአእምሮ ህመም ያለባቸውን ወገኖቻችንን እያገዘ የሚገኘው ሌላው ተጠቃሽ ተቋም ይመለከተኛል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።
እናም እነኝህ በጎ ጅምሮች ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ እና እንዲስፋፉ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።
የኒውማ ኢትዮጵያ (Pneuma Ethiopia) የበጎ አድራጎት ድርጅት 3ኛ የምስረታ ዓመት ዝግጅትን መሠረት ያደረገ ዶኩመንታሪ እንድትመለከቱ ተጋብዛችኃል።
ሃገራዊ ምክክሩ ያጋጠመንን collective trauma(ማህበረሰባዊ ጠባሳን) እና Intergenerational Trauma( ትውልድ ተሻጋሪ ጠባሳ) እንዴት እንዲታከም አስቧል?
ምክክሩ በራሱ የፈውስ አካል ሊሆን እንደሚችል እሙን ነው..ግን ምክክሩ በዘዴ ካልተካሄደ Re-traumatization እንዳይሆንም መጠንቀቅ ያሻል::
💦 RAIN Technique ☔️
ከባድ ስሜቶችን ለመቋቋም እና ራስን በርህራሄ የሚረዳት ቀላል ዘዴ
R – Recognize (ስሜትን ማወቅ )🤝
ትንሽ ቆም ብለን በዚያ ቅጽበት የሚሰማንን ስሜት መለየት እና ስም መስጠት ።
ለምሳሌ፦ “አሁን ጭንቀት😠 ይሰማኛል” ወይም “አዝኛለሁ።”🙁
A_ Accept ( መቀበልእና መፍቀድ )👍
የሚሰማዎትን ስሜት ለመኖሩ ፍቃድ መስጠት። እራስን አለመዉቀስ ወይም ስሜቱን ለመግፋት አለመሞከርይ። ሁሉም ስሜቶች መኖራቸው ተፈጥሯዊ እንደሆነ መረዳት ነው።
I_Investigate(በርህራሄ መመርመር)
ለራስዎ ርህራሄ በማሳየት ስሜቱን መመርመር 🧠🫀
እራስዎን መጠየቅ፦
“ለምን እንዲህ ይሰማኛል?”
“ይህን ስሜት እንዲሰማኝ ያደረገዉ ምክንያት ምንድን ነው?”
N – Non-Identification (ከስሜትዎ ጋር ራስን ባህር ወይም ማንነት አድርጎ አለመዉሰድ )❌
ሀሳቦችንእና ስሜቶቻችን የማንነትሙሉ መግለጫ እንዳልሆኑ ማስተዋልና ከሚሰማዎት ስሜት የበለጠ እኛ እንደሆንንና ስሜቶች ጊዜያዊ ናቸው፤ ይመጣሉ፣ ይቆያሉ፣ ከዚያም ያልፋሉ።
💙 ለራስዎ ርህራሄ መሆን የድክመት ምልክት አይደለም፤ የስነ-ልቦና ጥንካሬ ምልክት ነው።
✍Tizta Ayele (psychologist)
https://t.me/TizuPsychology
ሰኔ 30.........
የልጅዎ ውጤት አሳስቦታል? ምክንያቱ የመማር እክል (Learning Disability) ሊሆን ይችላል!
የፈተና ውጤት ከወጣ በኋላ ብዙ ወላጆች በልጆቻቸው ውጤት ይደሰታሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ይጨነቃሉ። ዝቅተኛ ውጤት ሁልጊዜ የጥረት እጥረት ወይም የብልህነት ማነስ ማለት አይደለም፤ አንዳንድ ጊዜ የመማር እክል (Learning Disability) ሊሆን ይችላል።
🧠 የመማር እክሎ
የመማር እክሎች በመማር፣ መረጃን በማቀናበር እና የተለያዩ አካዴሚካዊ ክህሎቶችን በማዳበር ላይ ተግዳሮት የሚፈጥሩ የአንጎል የመረጃ ሂደት ልዩነቶች ናቸው። እነዚህ እክሎች የግለሰቡን የሰውነት ችሎታ ወይም ብልህነት አያሳዩም፤ ይልቁንም መረጃን የመማርና የማቀናበር መንገዳቸው የተለየ መሆኑን ያመለክታሉ። 🧠✨
📚 ዋና ዋና የመማር እክሎች
🔹 ዲስሌክሲያ (Dyslexia) – በማንበብ፣ በፊደል አጻጻፍ፣ ቃላትን በመለየት እና የተነበበን ምሁፍ በመረዳት ላይ ችግር ያስከትላል። 📖🚫
🔹 ዲስግራፊያ (Dysgraphia) – የእጅ ምሁፍ ያልተነበብ ሊሆን ይችላል፣ የፊደል አጻጻፍ ስህተቶች ይበዛሉ፣ ሐሳብን በተደራጀ ሁኔታ በጽሁፍ ማቅረብም ያስቸግራል። ✍️📝
🔹 ዲስካልኩሊያ (Dyscalculia) – የቁጥር ግንዛቤ፣ ስሌቶች እና የሂሳብ ችግሮችን መፍታት ላይ እክል ያስፈጥራል። 🔢➖
🔹 የድምፅ መረጃ ሂደት እክል (Auditory Processing Disorder) – የሚሰሙትን መረጃዎች በትክክል መረዳትና መተርጎም ያስቸግራል። 👂🔊
🔹 የእይታ መረጃ ሂደት እክል (Visual Processing Disorder) – ቅርጾችን፣ ፊደላትን እና ቃላትን በትክክል መለየትና መረዳት ላይ ችግር ያስከትላል። 👀👁️
🔹 በቃላት የማይገለፁ ነገሮች የመረዳት እክሎች (Non-Verbal Learning Disabilities – NVLD) በህብረተሰብ ግንኙነት፣ በቦታ አቅጣጫ፣ በግንዛቤ እና በእንቅስቃሴ ቅንጅት ላይ ችግር ያስፈጥራል። 🗣️🚫
🌐 መንስኤዎች
• የዘር (Genetic Predisposition) 🧬
• በአንጎል ውቅርና በነርቭ ግንኙነት የሚከሰቱ ልዩነቶች 🧠
• ከመወለድ በፊት ወይም በወሊድ ጊዜ የሚከሰቱ ጋጥሞ ሁኔታዎች 🤰
🧩 መፍትሄ
የመማር እክሎች የሚታወቁት በሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ በመምህራንና በሌሎች ባለሙያዎች በሚደረግ ቀጣይነት ያለው ክትትል እና የላቀ ዉጤት የመምህራን እና የባለሙያዎች ትብብር እጅግ አስፈላጊ ነው። 🤝
🎯 ሕክምና
• ለተማሪው ፍላጎት የተዘጋጀ የትምህርት ዕቅድ (IEP) 📋
• የንግግር፣ የሙያ እና የባህሪ ማረጋጫዎች 🗣️
• አጋዥ ቴክኖሎጂዎች (Assistive Technology)
• ግለሰቡ ጠንካራ ጎኖች ላይ በማተኮር ራስን መተማመንን ማጠናከር 💪
👨👩👧👦 በዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ የሚያሳድሩ ተፅዕኖ
የመማር እክሎች በትምህርት ውጤት፣ በራስ መተማመን፣ በስሜታዊ ጤና እና በህብረተሰብ ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ነገር ግን ተገቢ ድጋፍና ግንዛቤ ሲኖሩ ግለሰቦች በትምህርት፣ በሙያ እና በሕይወት ሌሎች ዘርፎች ስኬታማ ሊሆኑ ይችላሉ። 🌟🚀
መደምደሚያ
"እያንዳንዱ ተማሪ መማር ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ ወይም በተመሳሳይ መንገድ አይማሩም" — George Evans
በዚህ ክረምት ልጆቻችሁን በቅርብ ተከታተሉ። የመማር እክል ጥርጣሬ ካለ ከባለሙያ ጋር መማከር ቁልፍ ነው።🗝
✍Tizta Ayele (psychologist)
https://t.me/TizuPsycholog
በ Rama psychiatry & Rehabilitation center ያገኙኛል
📌ራማ የአዕምሮ ህክምና ማዕከል
📞+2519-85-52-88-88
📞+2519-99-67-68-69
📍:- Ayat Square,200m On the Main Road to Arabsa.(use google map).https://maps.app.goo.gl/yuEA1YiY76BCE6Q7A
