cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Melhik Bookclub 🕊⃤

⚡️𝐀𝐭𝐭𝐫𝐚𝐜𝐭𝐢𝐯𝐞 𝐏𝐚𝐠𝐞𝐬 𝐅𝐫𝐨𝐦 𝐭𝐡𝐞 𝐁𝐨𝐨𝐤.𝑾𝒆 𝒔𝒕𝒓𝒊𝒗𝒆 𝒕𝒐 𝒄𝒓𝒆𝒂𝒕𝒆 𝒂 𝒑𝒐𝒔𝒊𝒕𝒊𝒗𝒆 𝒈𝒆𝒏𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏. 𝑺𝒖𝒑𝒑𝒐𝒓𝒕 𝒐𝒖𝒓 𝒎𝒊𝒔𝒔𝒊𝒐𝒏 𝒕𝒐 𝒈𝒓𝒐𝒘 𝒕𝒐𝒈𝒆𝒕𝒉𝒆𝒓. 𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬 𝐨𝐧 𝐚𝐥𝐥 𝐨𝐮𝐫 𝐩𝐚𝐠𝐞𝐬. 🚥 ⚡

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
443
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+17 روز
-1530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from Jafer Books 📚
የጃዕፈር መጻሕፍት አዲስ ቅርንጫፍ አራት ኪሎ አብርሆት ቤተመጻሕፍት ጊቢ ውስጥ በኢክላስ ህንጻ በኩል ወይንም ዋልያ መጻሕፍት ጎን ከፍተናል :: ቅናሽ ሽያጮቹ እንደተጠበቁ ናቸው :: በ 30 ብር የምንሸጣቸው መጻሕፍትም እንዳሉ ናቸው ::
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
👏 4
“የሚሳም ተራራ “ የሚሳም መጽሀፍ (በእውቀቱ ስዩም) የሁለተኛ አመት ተማሪ ሳለን መሰለኝ፤ የሆነ አርብ ቀን ፥  ስድስት ኪሎ ባህል ማእከል  ውስጥ እንደ ልማዳችን  ታድመናል፤ የቀኑ የክብር እንግዶች ወደ አዳራሹ ሲገቡ ጭብጨባውና ፉጨቱ ደመቀ፤ የመጀመርያው  ፥ እግሮቹን እየጎተተ የሚራመድ ፥ የተወቀጠ እሚመስል ኮት  የለበሰ ሰውየ ነው፤  ዘናጭ፥ ፊቱ ላይ ፈገግታ የማይለየው ደልዳላ ወጣት ከሁዋላው ተከትሎታል፤ የመጀመርያው ሰውየ ስብሀት ገብረእግዚአብሄር፥ ሁለተኛው ፍቅረማርቆስ ደስታ እንደሚባሉ ተረዳሁ ፤ ዝግጅቱ ተጠናቆ ታዳሚው መበተን ሲጀምር እኛ   ተማሮች በሁለቱ ደራሲያን ፊት ተሰልፈን ደብተራችን ላይ ፊርማቸውን ለማስቀረት መራኮት ጀመርን ፤ በመሀል፥ ፍቅረማርቆስ ከተደናቂነት ወደ አድናቂነት ዞሮ ፥ስብሀትን  ፊርማ ጠየቀው፤ ስብሀት፥ አሁን በማላስታውሰው  መጽሀፍ ገጽ ላይ “ለወጣቱ ደራሲ” ብሎ ፈረመለት፤ አብዛኛው ደራሲ የብእሩን አፍ የሚፈታው ስለ ተወለደበትና ስላደገበት አካባቢ በመጻፍ ነው፤  ፍቅረማርቆስ ከዚህ በተለየ መንገድ ሄደ!  ” ኢትዮጵያ በረሳቻቸው እና ኢትየጵያን ረስተው በሚኖሩ ብሄረሰቦች’ ኑሮ ዙርያ የሚያጠነጥን ልቦለድ ጻፈ፤ ብዙ ሰው ወደደው! በብዙ አንባቢያን ፥ ወጣት ደራሲያን፥ ዘፋኞች ላይ ሳይቀር ተጽእኖ ፈጠረ፤ አመቶች አለፉ፤ ከእለታት አንድ ቀን ፥ ፍቅረማርቆስ ደስታ ፥ ከመለስ ዜናዊ እጅ ሽልማት ሲቀበል  በቲቪ አየሁ፤ ካልተሳሳትሁ፥ ከበአሉ ግርማ ቀጥሎ  መለስ ያከበረው የመጀመርያው ደራሲ ይመስለኛል ፤ብዙ አልቆየም፤ አገር ጥሎ መሰደዱን የሚገልጽ ዜና ሰማን፤ ነገሩ ግራ  አጋብቶኝ ፥ ካንድ ወዳጄ ጋራ ስናወራ፥ “ ፍቅረማርቆስ ፥ ምን  ብሎ ነው ጥገኝነት የሚጠይቀው ?” ስለው “ መንግስት እያሳደደ ይሸልመኛል ፥ ብሎ ነዋ”  ብሎ መለሰልኝ ፤ ዘመናት ሳያስፎግሩ በጽጥታ  ነጎዱ! በቅርቡ፥ ፍቅረማርቆስን አሜሪካን አገር  ቦስተን ውስጥ ወዳጆቼ ብሩክ እና ሕይወት ቤት ውስጥ  አገኘሁት፤ ግለታሪኩን  ጽፎ እያጠናቀቀ ነበር፤  መጽሀፉን ትናንት ማታ ጀመርኩት፤ እየጣመኝ፥ ገጾች ቶሎ እንዳያልቁብኝ እየቆጠብሁ ዛሬ ረፋድ ላይ ጨረስኩት፤ “የሚሳም ተራራ “  ግለታሪክ ነው፤ ግን በተለመደው መንገድ የሰውየውን ህይወት ከልደት እስከ ደረሰበት የሚተርክ አይደለም፤ ካሳለፈው ሕይወቱ ውስጥ የተወሰኑ  የትዝታ ቅንጣቶችን ቆንጥሮ  ይተርክና ኑሮ ያስጨበጠውን እውቀት ያካፍለናል ፤ ፍቅረ ማርቆስ በጊዜው  ፥ ተወዳዳሪዎቹ  ያልደረሱበት የሀብት እና የዝና  ከፍታ መውጣት ችሏል ፤ ከዚያ ደግሞ፥ ያልሰመረ ትዳር ፥ከስደት ጋር ተባብሮ   ወደ አስፈሪ አዘቅት  አውርዶታል፤ ግን ያሳለፋቸው ፈተናዎች  መራር አላደረጉትም፤ እንዲያውም እውቀት፥ ብስለትና የህይወት ፍቅር ጨምረውለታል፤ ለማንኛውም ሸጋ መጽሀፍ ማንበብ የናፈቃችሁ ባለንጀሮቼ  “የሚሳም ተራራን “  ጋበዝኳችሁ፤ መልካም ሰንበት! https://t.me/zemen_books
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የሚሳም ተራራ ◈ በፍቅረማርቆስ ደስታ!
نمایش همه...
"ለተሻለ ነገ እናንብብ" ዘመቻ ላይ ተሳተፉ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች የመፅሐፍት ምርጫዎቻቸውን አጋርተዋል፤ ምርጫቸው ለንባብ ምርጫዬ ተነሳሽነት ፈጥሮልኝ የተወሰኑ መፅሐፎችን ገዝቼ ለማንበብ ወስኛለሁ። "የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ" የሚለው የእጓለ ገ/ዮሐንስ መፅሐፍ ቀዳሚ የንባብ ዝርዝሬ ውስጥ አድርጌዋለሁ። ሌሎች መፅሐፎች ይከተላሉ። የዘመቻውም ዓላማ ይኸው ይመስለኛል-የንባብ ፍላጎትን ማነሳሳት፣ ማነቃቃትና መፍጠር። FM Addis 97.1 /ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ/ እናመሰግናለን
نمایش همه...
1
آرشیو پست ها