cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ልሳነ-አምሃራ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
831
مشترکین
-324 ساعت
-167 روز
-3930 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
⭐️⭐️⭐️💡ዓውደ ፋኖ💡⭐️⭐️⭐️ 🫵 🫵 "#አይበገሬው ሰሜናዊ ኮከብ" ዝና፣ እና ክብር ዓለም ዓቀፍም ሽልማት በተገቢው ስፍራ እና ቦታ፣ በፍትሃዊ ማደሪያው ይገኝ ዘንድ ምድሪቷ በሀቅ መንገድ ብትራመድ ይሄን ብርቱ ከዐለት የጠነከረው #ሰው የሚያልፈው አንዳች ክብረ ሞገስ ባልኖረ… #ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ… አዎ፣ ስለርሱ ላወራችሁ ነው። የዛሬው የዓውደ ፋኖ ገፅ እንግዳዬ ነው። ስለዚህ፣ መንጋ እና ቲፎዞ አልባ ታጋይ ጥቂት ልል ብችል እንጅ… የዘመኑን ምልዐት፣ የትውልድ ውርስ በደም ዋጋ የታጀበ በሰቆቃ አመታት ውስጥ የተሻገረ፣ ዛሬው በተጋድሎ ዐውድ ላይ ስለሚገኘው መራራ መርህ መር ታጋይነቱን በዚህች ቅፅበት አትቼ አልጨርሰውም። እርሱ ግን፣ ፍፁም ትሁት ነው። እጁን ጨብጦ ከፍ በማድረግ "ትግልን ከኔ በላይ ለዐሳር" ሲል አታዩትም። ሲበዛ አይን አፋር እና የደግነት ባለ ፀጋ ነው። በጋዜጠኝነት ደሞዙ… 4 በኦሮሚያ ቤተሰቦቻቸው በግፍ የተገደሉባቸው ወላጅ አልባ ህፃናትን ያሳድጋል፣ እጅ ሲያጥረው በስሙ ይለምንላቸዋል። ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ ያልተገለጠ መፅሀፍ ነው። ይህ፣ ሰው… ለውጥ የተባለው ጎርፍ ገፍቶ ያመጣው ሰሞነኛ ፖለቲከኛ፣ የዩቲዩብ አማላይ ክፍያ ወደ ሜዳ ያወጣው ጋዜጠኛም አይደለም። ከዚህ በታች… የማወጋላችሁ በጀብዱ የተሞላው ታሪከ ማስታወሻው… ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ያልተዘመረለት ካባ ያልደረብንለት ፣ የሰራን ቆፍረን አክባሪ ያለመሆናችንን ያሳብቅብናል። አባይ ዘውዱ… ሰሜናዊ ነበልባል #ፋኖ ኮከባችን… በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ ዳግም በግፍ እስር ላይ የሚገኘው ዓባይ ዘውዱ ማን ነው⁉️ ስለ ዓባይ ዘውዱ አጠር ያለ መረጃ ለማጋራት ወደናል። ዓባይ ዘውዱ ደመቀ የተወለደው በድሮው አጠራር በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ ዳዋ ዳንጉራ ልዩ ስሙ መንደር ጊዮርጊስ በተባለ ለማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ አዋሳኝ በሆነውና መዳረሻውን ሱዳን ድረስ ያደረገው የጓንግ ወንዝ በሚለዬው ቀበሌ ነው። ዓባይ ምንም እንኳ በጭልጋ ወረዳ መንደር ጊዮርጊስ ይወለድ እንጅ እድገቱን ያደረገውና እስከ 6ኛ ክፍልም የተማረው በድሮው አጠራር ታች አርማጭሆ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለአስተዳደር ያመች ዘንድ በሚል ማዕከላዊ አርማጭሆ ተብሎ ራሱን በቻለው ወረዳ ማሰሮ ደንብ ነው። ዓባይ በልጅነቱ ወደ ማዕከላዊ አርማጭሆ የተወሰደው አባቱ አቶ ዘውዱ ደመቀን እና ቤተሰቦቹን "ለለውጥ እየታገሉ ነው፣ እምቢተኛ ናቸው፣ እየተገዙን አይደለም" በሚል ደርግ አባቱን ወደ ጭልጋ አፍኖ በመውሰድ ማሰር እና ማንገላታቱን ተከትሎ ነው። በወቅቱ ዘውዱ ደመቀ ብቻ አልነበረም ከመንደር ጊዮርጊስ ቀበሌ የታፈነው ምንም እንኳ ከአጭር ጊዜ የእስር ቆይታ በኋላ ከዳንጉራ እስር ቤት የተለቀቁ ቢሆንም አባቱ ደመቀ ሁነኛው፣ ታላቅ ወንድሙ መልካሙ ደመቀ እና ታናሽ ወንድሙ ጌጡ ደመቀም አብረው ታስረው ነበር። ዘውዱ ደመቀ ግን 'ይህ ነው ዋናው' በሚል ተፈርጆ ወደ ጭልጋ ወረዳ አይከል ማ/ቤት ተወስዶ ከ6 ወራት የግፍ እስር በኋላ መፈታቱን ተከትሎ ነው ባለቤቱን ባንች አምላክ በለጠን እና ልጆቹን ይዞ የጓንግን ወንዝ ከማዶ እና ማዶ ሶስትና አራት ረዣዥም እንጨት ጣል በማድረግ በሰራው ጊዜያዊ መሻገሪያ ድልድይ ተሻግሮ ወደ ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ያቀናው። የመጀመሪያ ወይም የበክር ልጅ የሆነው ዓባይ ዘውዱ በጭልጋ ወረዳ መንደር ጊዮርጊስ ተወልዶ በአርማጭሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ ሳንኪ ሚካኤል ነው እድገቱን ያደረገው። ዓባይ የተወለደበት ብቻ ሳይሆን ያደገበት አካባቢም በአብዛኛው በተራራ ሰንሰለት እና በተፈጥሮ የታደለ አካባቢ ነው። ዓባይ የት ተማረ? የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እስከ 6ኛ ክፍል የተከታተለው በማሰሮ ደንብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን የ7ኛ ክፍል ትምህርቱን ደግሞ በታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ት/ቤት ነው። ዓባይ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን የተከታተለው በባህር ዳር ነው። ይኸውም፦ 1) 8ኛ ክፍል_በባህር ዳር ቁልቋል ሜዳ ት/ቤት፣ 2) 9ነኛ እና 10ኛ ክፍል_በባህር ዳር ፋሲሎ ት/ቤት፣ 3) 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ትምህርቱን በባህር ዳር መሰናዶ ት/ቤት እንዲሁም 4) የዩኒቨርስቲ ትምህርቱንም በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ ካምፓስ የተከታተለ ሲሆን በጋዜጠኝነትና ግንኙነት (Journalism and Communications) ትምህርት ዘርፍ 3.66 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ እና በሽልማት ተመርቋል። የትግል ሁኔታን በተመለከተ? በተለያዩ ጊዜያት በልዩ ልዩ በመድረክ እና በጽሁፍ ሲያደርገው የነበረው ትግል እንዳለ ሆኖ በዋናነት ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ ነው የህወሀት እና ህወሀት ተሸናፊ እና ተንበርካኪ አድርጎ የሰራውን የብአዴን ስርዓትን አምርሮ በመጥላት አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)ን ተቀላቅሎ ታግሏል። በተለይ በህወሀት በሀይል ከአማራ የተወሰደው የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እና ራያ እንዲሁም በሱዳን በጎንደር በኩል የሀገር ሉኣላዊነት ተደፍሮ የተወሰደው ሰፊ ለም መሬት እና በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ላይ ይደርስ የነበረው ሁለንተናዊ ግፍ እና በደል ወደ አንድነት ትግሉ በመግባት ከብርቱ ለውጥ ፈላጊ እና የነቁ ጓደኞቹ ጋር በመሆን በአብርሃጅራ ከተማ ቢሮ በመክፈት ጭምር አገዛዙን እንዲታገል ገፋፍቶታል። በለውጥ ትግሉ መስዋዕት ከሆኑት ነፍሳቸውን ይማርና ከእነ ደስታው ተገኘ፣ አንጋው ተገኘ እና ታናሽ ወንድማቸው ባበይ ተገኘ ጋር በመናበብ አገዛዙን ይታገል ነበር። ደስታው ተገኘ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ አገዛዙን ለመታገል ሲመለስ በአብደራፊ/ምድረገነት አካባቢ ባጋጠማቸው ውጊያ ዶ/ር ብርሃኑ ከተባለ የትግል ጓዱ ጋር ስለ አማራ ህዝብ እና ስለ ሀገር ሲል በጀግንነት በክብር የተሰዋ ሲሆን ወንድሞቹ አንጋው ተገኘ እና ታናሻቸው ባበይ ተገኘ ደግሞ እምብኝ ለወገኔ በማለት በመጋቢት 2016 ዓ/ም ኦህዴድ መራሹን የብልጽግና አገዛዝ በነፍጥ ሲፋለሙ በክብር የተሰው ጀግኖች ናቸው። ዓባይ ከእነ እንግዳው ዋኘው፣ ስርዓቱ ለሰላማዊ ትግል ዝግጁ አይደለም በማለት ወደ ኤርትራ በማቅናት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርን ተቀላቅለው ሲታገሉ ከነበሩት ከእነ አብርሃም ልጃለም፣ ከአለልኝ እና ከሌሎችም ጋር በመሆን በምዕራብ ጎንደር ዞን አብርሃጅራ ሲታገሉ ነበር። ከእነ አለላቸው አታለል፣ ቀለብ ስዩም፣ ተገኘ ሲሳይ፣ በላይነህ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞ፣ ፈረጃ ሙሉ፣ ሰጠኝ ቢልልኝ፣ አወቀ፣ እንዲሁም ከአነ አግባው ሰጠኝና ከሌሎች ጀግኖች ጋርም በመናበብ አብሮ ለእውነተኛ እና ስር ነቀል ለውጥ ይታገል ነበር። ዓባይ ዘውዱ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ሲታገል ስለደረሰበት እስር፦ (1) በህወሀት ኢህአዴግ ዘመን ከጥቅምት 25/2007 ጀምሮ እስከ ህዳር 2010 ድረስ በፈጠራ የሽብር ክስ 4 ዓመት ከ2 ወር ተፈርዶበት ታስሯል። በአብርሃጅራ፣ በጎንደር 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ፣በባህር ዳር 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ፣ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ፣ በቂሊንጦ፣ በሸዋሮቢትና በዝዋይ በእስር ተሰቃይቷል። (2) በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ደግሞ ስለ ሰፊው የአማራ ህዝብ እና ስለተገፉ ወገኖች ድምፅ በመሆኑ 4 ጊዜ ታስሯል። ይኸውም፦ 1) ሀምሌ 10/2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ አውቶብስ ተራ እና በመርካቶ አራተኛ ፖሊስ ጣቢያ ስለምን ለአማራ ተፈናቃዮች ድምጽ ሆንክ በሚል ታስሯል።
نمایش همه...
2) ጳጉሜ 3/2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ እና በአባ ሳሙኤል ታስሯል። 3) መጋቢት 28/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ (ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) ታስሯል። 4) ነሃሴ 4/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሜክሲኮ፣ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ እና በቂሊንጦ ታስሯል፤ በአማራዊ ማንነቱ እና በጋዜጠኝነት ሙያው ለህዝብ ድምፅ በመሆኑ እና ስር ነቀል ስርዓታዊ ለውጥ እንዲመጣ በመታገሉ አሁንም በግፍ እስር ላይ ይገኛል። ዓባይ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ-ደቡብ እዝ መከላከያ ካምፕ ለ6 ወራት ያህል በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ታግቷል፤ በሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮም ከ2 ወራት በላይ ከሌሎች የአማራዊ ማንነት ታጋቾች ጋር በሩ እንዲዘጋ ተደርጎ ታስሯል፤ ከሜክሲኮ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተዛውሮም ታስሯል። ዓባይ አሁን ላይ የፈጠራ የሽብር ክስ ተመስርቶበት በቂሊንጦ እስር ቤት ይገኛል። 4 ዓመት ከ6 ወራት በላይ በታች አርማጭሆ እና በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች በባህል እና ቱሪዝም የፕሮሞሽን ባለሙያነት እንዲሁም በህዝብ ግንኙነት ሙያ ያገለገለው ዓባይ ዘውዱ ህዳር 1/2010 ዓ/ም ከዝዋይ ማ/ቤት ተፈታበት ጊዜ ጀምሮም በጋዜጠኝነት ሙያው በሽብር ተግባር የተሰማራውንና የህወሀት ኢህአዴግ ተቀጥላ የሆነውን የኦህዴድ ብልጽግን አገዛዝና የስሪቱን ገመና በማጋለጥ ጭምር እየታገለ ይገኛል። ዓባይ ዘውዱ እና ቤተሰቦቹ ስለ እውነተኛ ለውጥ በሚል ኢሰብአዊነትን በመቃወም የከፈሉት መስዋዕትነት ከባድ ነው። በማንኛውም ስርዓታዊ ፈተና ሁሉ ከጎኑ የቆሙ ወገኖችን በሙሉ በእጅጉ ያመሰገነው ዓባይ ህዝባዊ ትግል ማሸነፉ አይቀርም ይሏል። ፍትሃዊ የሆነው የአማራው የህልውና፣ የነፃነት፣ የክብር፣ የእኩልነት እና የአብሮነት ትግል ያሸንፋል! ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት ይሁን! ፍትህ ለሁሉም! #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://t.me/Moamediamoresh
نمایش همه...
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍

የቤተ-አምሓራ ነፃ ህዝብ የትግል ልሳን፣ ይከተሉን!

Photo unavailable
ትውልዱ እንዳይሳሳት‼️ በ2010 ዓ.ም በደም ዋጋችን የጠራነው ለውጥን፣ ለፋሽት ኦሮሞ ገዳዮች በሆዱ ሸጦ የደማችን ጎርፍ ይፈስስ ዘንድ የተወን፣ ብዐዴን እንጅ ሌላ አልነበረም፣ አይደለምም። ያኔ… ብዐዴን = አብን እና አዴፖ በሚል ጭንብል ተሸፍኖ ሲመጣ…የናፈቅነውን ነፃነትና ፖለቲካዊ እጣ ፋንታችንን ይወስን ዘንድ ከጌቶቹ ጋር ያሰለፍነው ጊዜ…ተሳሳትን። ብዐዴን… መልክ እና ቅርፁን፣ ስምና መሪ መሳዮችን፣ ኢጎ እና ሀብት፣ ወረቀት የሰበሰቡና ምላሰኞችን ከፊቱ እያስቀደመ ስንቴ ደጋግሞ ከዳን፣ ስንቴ ደጋግሞ ወጋን፣ ስንቴ ደጋግሞ አደማን፣ ስንቴ ደጋግሞ አቆሰለን! ዛሬም… የህልውናችንን ትንቅንቅ… የእጣ እድላችን ወሳኝ የሆነውን የፋኖ ትግል ለመጥለፍ የመጣበት መንገድ አስፈሪም፣ አስደንጋጭም፣ አስጊም እየሆነ ነው። ሚዲያው፣ በባዕዴናዊ ኩሊ እና ጎጠኞች እየተወረረ ነው። በወያኔ ቅጥረኛ ባለ አጀንዳዎች አየሩ እየተሞላ ነው። አላዋቂ ታዋቂዎች፣ በፋኖ ትግል ተጠቅልለው ለፍርድ የምንፈልጋቸው ወንጀለኛችን በክብር መስኮት ይዘው እየመጡ ነው። ትውልዱ፣ እንዳይሳሳት! ይህ እድልን ለብዐዴናውያን ከመስጠት ለጥቆ የሚመጣ ሌላ ጭላንጭል ተስፋ የለም። "ብዐዴን ጅብ ነው" ለሆዱ እና ጥቅም ሟች… በእርሱ አንገት እና ትክሻ ጭነት፣ ገመድ እና ሰንሰለት እንጅ የስልጣን ካባ፣ ካራባት እና ዘውድ አይስማማውም። ዳግም ለሆዱ እና ለጥቅም ይሸጠናል። መራራውን ፅዋ እንጋት ዘንድ ካልሻትን የብዐዴን ጉፋያን አምነን አንከተልም። እያንዳንዱ፣ የብዐዴን ኩሊ ጭንብላም እየገለጥን የምናሰጣበት ቀን ተቃርቧል። በአምሓራ ብሄርተኝነት ጭንብል የሸመቀው፣ ዳግማዊ የበለጠ ሞላ ምስለ #አብን በድፍረት አይኑን እየገለጠ ነው። በምንወደው እና በሆንነው #አምሓራነት እየማሉ… ሊያሳርዱን መለከት እየነፉ ነው። ንቁ!!!
نمایش همه...
#መረጃ በአገዛዙ ስርዓት ታፍሰዉ ብር ሸለቆ ማሰልጠኛ የገቡ ታዳጊ ለጋ ወጣቶች ፈንድቶ እየወጣ ይገኛል ቀደም ሲል በማንኩሳ ቢተዉ ሺ አለቃ  ፋኖ መንገድ ጠረጎ ካወጣቸዉ መካከል በቁጥር 109 የሚደረሱ ለሰፊው  ህዝብ ይፋ ማድረጌ ይታወሳል።በተመሳሳይ በደጃጅ አስቦ ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ስር በምትገኝ በአባይ ሺ አለቃ አማካኝነት ከብር ሸለቆ የወጡ ታዳጊ ለጋ ወጣቶችን ይፋ አደረጋለሁ። 1)ሞአዘ በድር- ከጅማ-ከመንገድ ላይ የታፈሰ-እድሜ-16- የትም/ደረጃ -6 ኛ ክፍል 2)ቢላል ከድር- ከሻሸመኔ- እድሜ-16- የትም/ደረጃ-3 ኛ ክፍል 3)ሃይሌ ወንድሙ-ጫንጮቢ-እድሜ-17-የትም/ደረጃ-7ኛ ክፍል 4)ገዳ ፈይሳ-ከሻሸመኔ-እድሜ-16-የትም/ደረጃ-5ኛ ክፍል 5)አብዲሳ ማህመድ-ከሻሸመኔ-እድሜ-17-የትም/ደረጃ-16 6)ሐረስ አባሳም-ከበደሌ-እድሜ-18-የትም/ደረጃ-8ኛ ክፍል 7)ከማል ኢነጌሶ-ከሻሸመኔ-እድሜ17-የትም/ደረጃ-3ኛ ክፍል 8)ተፈራ ለሜሳ- #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 5/11/16 ዓ.ም Https://t.me/justsfor
نمایش همه...
ፍትሕ ለአምሓራ!

ፍትህ ልብን ትጠግናለች! #እኛ፣ የፍትህ አወቅ አበው ልጆች ነን! የፍትህ አደባባዩን በክንዳችን እንፈጥራለን!

👍 1
የረፋድ ትኩስ መረጃ !! ዛንበራው ብርጌድ ደጀን ከተማ ሸብሸንጎ ቀበሌ ወደ ጎባያ መሄጃ መንገድ ሙጋ ወንዝ ላይ የአብይን ወራሪ ኃይል አመድ አድርገውታል። በጠላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ሐምሌ 05/2016 Https://t.me/justsfor
نمایش همه...
ፍትሕ ለአምሓራ!

ፍትህ ልብን ትጠግናለች! #እኛ፣ የፍትህ አወቅ አበው ልጆች ነን! የፍትህ አደባባዩን በክንዳችን እንፈጥራለን!

~ በአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ላስታ አሳመነው ክፍለጦር አድማ ብተናወችን በወታደራዊ አቀባበል በሰልፍ ተቀበለ። የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጥሪ የተቀበሉ የአድማ ብተና አባላት አንድ ብሬን እና ሌሎች የነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሪያዎችን እንደያዙ በወሎ የሚገኙ ፋኖዎችን መቀላቀላቸው ተሰማ! የአድማ ብተና አባላቱ ግፍን በመቃዎም ከአሃዳቸው በመውጣት ፋኖን ሲቀላቀሉ ደማቅ በሆነ ወታደራዊ  ሰልፍ አቀባበል እንደተደረገላቸውም ተገልጿል። ብርጋዲየር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ከትናንት በስቲያ ሐምሌ 03/2016 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ፡ "ፋኖ የሚዋጋው በማንነትህ የዘር ፍጅት ያወጀብህን የልጓም የለሹን የብልፅግና መንግስትን ለመደምሰስ መሆኑን በአፋጣኝ ተረድተህ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ከጠላት ጋር መሰለፍን አቁመህ ወደ ፋኖ እንድትቀላቀል" ሲሉ ለአድማ ብተናና ፖሊስ እንዲሁም ሚሊሻ አካላት ጥሪ አስተላልፈዋል። በተመሣሣይ ብርጋዴር ጀኔራሉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሲሉ ለጠሩት ኃይል "በአንተ ደምና አጥንት እየነገዱ የሀብት ማማ ላይ የወጡ ምንዝል አለቆችህ ላይ አፈሙዝ እንድታዞርና ከአማራ ፋኖ እና ከትግሉ ጎን እንድትቆም" በማለት ጥሪ አቅርበዋል። ይህ መልዕክት በተላለፈ ከጥቂት ሰዓታት ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአድማ ብተና እንዲሁም ሌሎች የአገዛዙ ፀጥታ አካላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆኑ ታውቋል። በሰሜን ወሎ ዞን የጋዞ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው እስታይሽ ከተማ ሰፍረው ከነበሩ የአድማ ብተና አባላት መካከል በቁጥር ከአምስት በላይ የሚሆኑት ከትናንት በስቲያ አመሻሹን አንድ ብሬን ከነ ሙሉ ሼንሼሉ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ሙሉ ትጥቃቸውን እንደያዙ ፋኖን መቀላቀላቸውን ነው የአድማ ብተና አባላቱን የተቀበሉ የፋኖ አዛዦች የገለፁት። የአድማ ብተና አባላቱን የተቀበለው አማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አሳምነው ፅጌ ክ/ጦር ስር የሚገኘው የተከዜ ብርጌድ ፋኖ ሲሆን ትናንት ከገቡት በተጨማሪ ሰሞኑን ለየት ባለ ሁኔታ በርካታ ቁጥር ያላቸው የአገዛዙ ወታደሮችን ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መቀበሉን የብርጌዱ አዛዥ ኮማንዶ ዘላለልም ተናግሯል። ከትናንት በስቲያ ማምሻውን የገቡት የአድማ ብተና አባላቱ ደማቅ በሆነ በወታደራዊ ሰልፍ የታጀበ አቀባበል እንደተደረገላቸውም ኮማንዶ ዘላለም ጨምሮ ገልጿል። Https://t.me/justsfor
نمایش همه...
ፍትሕ ለአምሓራ!

ፍትህ ልብን ትጠግናለች! #እኛ፣ የፍትህ አወቅ አበው ልጆች ነን! የፍትህ አደባባዩን በክንዳችን እንፈጥራለን!

Photo unavailable
አዎ፣ ለራሱ ጎጆ ምስረታ ሀቅም አልባ ውልክሽነት ለሚታይበት፣ ፖለቲካዊ እጣ ፋንታውን ከማይወዱት ጠላቶቹ ጋር አጣብቆ ከማሰብ ወዲህ… የራስ ቅሉ የማያስብለትን ከንቱ… ጣዖታዊ ኢትዮጵያን በአምልኮት የሚካድም ትውልድ ነፃ አይወጣም። ራስን ከመሆን የሚለጥቅ ራዕይ ተከባሪ ነው። ነፃ፣ የአምሓራ መንግስት በፍርስራሿ ላይ ማዋለድ የሚችል እፁብ ድንቅ የራሱን ሀገር ሰሪ ጥበበኛ አምሓራዊ ትውልድ እስካልታዬ… ተስፋችን ሩቅ ነው። #አምሓራ፣ ባለ ሀገርነት ይገባዋል!!! ይሄን ከማለም ወዲህ ያለው፣ ድንግዝግዝ ሀሳብ… ስልጣን ቢያቆናጥጠንም እንኳ፣ ነፃ አያወጣንም። መራራው ሃቅን ተጋፈጡት! የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ በኃይል ባፀናነው ግዙፍ ድርሻችን ላይ ቆመን እንመክርበታለን…! ወይ፣ ትቀጥላለች… አሊያ እራሳችንን በዋስትና እናፀናለን!!! አዲሱ ትውልድ አምሓራን የነፃ ሀገር ባለቤት ያደርጋል! #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ!!! https://t.me/Moamediamoresh
نمایش همه...
ሰበር ጎንደር _አዘዞ‼️ ©ሞዐ ሚዲያ ሐ 04/2016 ዓ.ም በደረሰን መረጃ አሁን በዚህ ሰዓት ጎንደር አዘዞ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው:: የወራሪ አዘዞ ኤርፖርት ጠባቂወች በፍኖ ተደምስሰዋል: የቀረውም ቦታውን ለቆ ፈርጥጧል።  አሁንም ውጊያው እንደቀጠለ ነው ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ያድርግ። #ድል-ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://t.me/Moamediamoresh
نمایش همه...
ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍

የቤተ-አምሓራ ነፃ ህዝብ የትግል ልሳን፣ ይከተሉን!

  • Photo unavailable
  • Photo unavailable
ሰበር ዜና ከቲሊሊ !! ዘንገና ብርጌድን ተቀላቀሉ ..‼️‼️ ትናንት ከምሽቱ 3:00 አስር(10) አድማ ብተና አባላት የስርዓቱን አሳፋሪነት በመጠየፍ ከድተዉ ዘንገና ብርጌድ ቲሊሊ ፋኖን ተቀላቅለዋል። ከእነዚህም: 1 ጌታሁን ገብሬ 2 መልካሙ ደሴ 3 አጉማሴ ባዘዘው 4 ተዋቸው ማሩ 5 ተመስገን አስማረ 6 አየነው መኮነን 7 ታዘበው ቦጋለ 8 ስማቸው ክንዴ 9 አምባቸው ዋሴ 10 ባየ ፍስሃ ይገኙበታል። እነርሱም  እኛን ያያችሁ ወንድሞቻችን የስርዓቱን አስከፊነት ታውቁታላችሁና ለቃችሁ ውጡ ሰፊው ህዝብና የህዝብ ልጅ ፋኖ በደስታ ይቀበላችኋል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል። @ዘንገና ብርጌድ ቃል አቀባይ አለበል አወቀ ቲሊሊ! #ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ! https://t.me/Moamediamoresh
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.