cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ነፀብራቅ ✨ የኪነ-ጥበብ ቡድን

ይህ channel የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎች የሚቀርቡበት ለምሳሌ :- ግጥም ፣ተውኔት፣ስዕል እና ጥበብ ነክ የሆኑ ስራዎች የሚገኙበት ነው

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
188
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-1430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailable
ወድሀለው ያልኩት የዛን እለት ማታ አጥብቄ የያዝኩህ ልብህ እስኪመታ ደጋግሜ ፍቅሬን ጮኬ እየነገርኩህ አንገትህን ስቤ ከንፈርክን የሳምኩህ ትዝ ይለኛል ዛሬም እንደሆነ ትላንት ከንፈርክ ማር ነበር የሚያጣፍጥ ስሜት ደሞ በመሳምህ ኮርተህ ጀመርክ አሉ ጉራ እየዞርክ ተረከው ጀብዱ እንደተሰራ እወቁልኝ እያልክ ተው ማውራቱ ይቅር እማታውቀው አለ አንድ ያልገባህ ነገር ተፈቀርኩ ብለህ ሀገር ያዙ አትበል ያንን ሁሉ ያረኩት ሰክሬኮ ነበር😊 ✍️የተክልዬዋ @semetnbegtm @semetnbegtm @semetnbegtm
نمایش همه...
ለኔ እኮ አንቺ፣    ከ 10 ቱ ትዕዛዛት ልክ እንዱ ትእዛዝ እንደ ሙሴ የእስራኤልን ህዝብ    ይዞ እንደመጓዝ ለኔ እኮ የሆንሺብኝ፣ እንደ ቤተክርስቲያን ደዉል፣ አዛን ማዉጣት መካ ላይ ከ ቢላል  እኩል፥ ምን ስሆን ትወጂኛለሽ..?!!? ራስ ዳሽን ወጥቼ ያንቺን ምስል ልስቀል ከዛ ላይ ወደ ታች በአፍጢሜ ልተከል የቱን ሀገር---በስምሽ ላሰይም...!? የልቤ ሀገር ባንቺ ስም ነዉ ለአንቺ ባይታይም ምን አድርጌ ምን ሰርቼ ነዉ ምታፈቅሪኝ..? እንደ ነቢያቱ ላንቺ እየፃፍኩኝ እንደ እየሩሳሌም አንቺን አመለኩኝ አንቺ እንድቶጂኝ... ሁሉንም ሁኛለዉ ያልሆንኩት የለኝም አንቺን ስል ያልሄድኩበት ቦታ አይገኝም ስምሽን አምልኬ ስጋዬን በጾም ቀጣዉ፥ ጸሎቴም አንቺ ሁነሽ መጀመሪያዉ..ማሳረጊያዉ። አንቺ እንድቶጂኝ... ጨረቃ ላይ ልዉጣ ኮከብ ላዉርድልሽ እንደ ዶክተር አብይ መግለጫ ላዉጣልሽ ቴዲ አፍሮን ወይስ ጥላሁንን ሁኜ ላዚምልሽ ወይስ እንደ ባዓሉ ግርማ መጽሃፍ ልፃፍልሽ ንገሪኛ ...የኔ ፊያሜታ🇪🇷 ምን ስሆን ነዉ ባንቺ የምፈቀር?? የኤርትራን ባህር ዋኝቼ ልሻገር   ያንቺን  ምስል ልስቀል አዉርጄ ባንዲራ 🇪🇷 ወይስ በእግሬ ልምጣ ከመቀሌ አስመራ?!! ንገሪኛ መልሺልኝ...ምን ስሆን ነዉ ምታፈቅሪኝ     ''ካህን ሁኜ ተቀምጬ ገዳም ደሃ ሁኜ ወይስ ሀብታም ዳኛ ሁኜ አያስታራቅኩ..." ወይስ እንደ ዮሃንስ ህዝቡን እያጠመኩ' እንደ ጳዉሎስ አንቺን እየሰበኩ''። እያፈቀርኩ ልጠብቅሽ...ልፈልግሽ ለልቤ ዕረፍትን ትሰጪያለሽ...?   ግን መቼ ትመጪያለሽ...?!! ✍️ከዳዊት @eliyasshitahun @betagitim @betagitim
نمایش همه...
👍 1
ትርጉም ! (በረከት በላይነህ) .. "አስቀያሚ፣ አሰጠሊታ ፣ መልከ  ጥፉ፤ እንደ ደሀ  ቀዬ መስቦችህ የረገፉ! የማትባል  እዚህ ግባ ፣ የሰው ፍራሽ  ፣ ማማር አልባ! ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር! የጭራቅ ሳቅ  ያይጥ ፞ ድምር               ባትታይም የማታምር! !!" እረ !  ሌላም፣ ሌላም፣ ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤ አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ! ለምን ብትይ? መልኬ ከሸለመሽ  የማይሽር ጥላቻ ፤ ደስታ  አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ @astawesegnregasa @astawesegnregasa
نمایش همه...
😁 1
  • File unavailable
  • File unavailable
ክፉ ቃል ......ያን ጊዜ ያን ጊዜ ልንተወው ልባችን ያልቻለው ፍቅርን አልነበረም ጥል ፀባችንን ነው ..........እኔም እኔም ስትሄጂ ቃላትን አውጥቼ መንገድ ሰርቻለው .....አንቺም አንቺም ፈቅደሽ እንደተውሺኝ አስታውሰዋለው ......ልሂድ ስትይኝ እሺ ያልኩት የራሴ ልብ ላይ ክደት የፈፀምኩት ለምን ነበር ተይ ያላልኩት? ......ለምን? አሁን ከሰማሺኝ ጆሮ ከሰጠሺኝ ትንሽዬ ጠጠር ችግር ተሰንቅራ አለያይታናለች ክፋት ተንኮል ጭራ እያልኩኝ ለምክንያት አልደረድርም ቃል ያኔ ያወጣሁት ክፉ ቃል ይበቃል ክፉ ቃል   ✍ቴዳ
نمایش همه...
ያን ጊዜ ቴዳ.mp38.47 KB
ክርስቶስ በገብረ ክርስቶስ ደስታ.mp31.96 MB
➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿➿ ፍቅሬን ሳልገፅላት!! ------------------------------ ያቺ! ውብ ከፍጡራን በላይ፤ የውቅያስ ጥበብ የዓይን አማላይ፤ የምሽት ጨረቃ የመዓልቱ ጮራ ፤ ውበቷን ሊያነፁ ቢተጉ በተራ፤ ምስሏን ሊቀርፁ ጠቢባን ቢለፉ፤ በምናብ ሀዲድ ቢከንፉ፤ ብዕር ብትተፋ !ለዛች ዓይነ-ግቡ፤ ይሄድ ይሄዱና መባቻ ጠፍቶአቸው፤ አንክሮ ይላሉ ውበቷ ደንቋቸው። ያኔ በለጋነት ስንሄድ በአደባባይ ፤ ሽርፍራፊ ቅኔ በሚያፍር ዓይን ላይ፤ ማዕቀብ ወርዶበት ላይወጣ በገሃድ ፤ ዘመን በበረረ በትግስት መንገድ፤ የኑዛዜ ወኔ ድፍረት ሲያጣጥር፤ ዝንተዓለም ወድጄያት ፍቅሬን ሳልናገር፤ እሷስ ሄደች አሉኝ ወደ ትዳር ህይወት፤ በብዙ ባስባት አሳቅፋኝ ናፍቆት። ** በ dt (dtvote12) 9/6/2013E.C እንደተፃፈ
نمایش همه...
............አንድ ሰው አለ...........   ✍ገጣሚ ➖በውቀቱ ስዩም አንባቢ ቴዲ እርጅና ሲጫንሽ እድሜ ተጠራቅሞ እንደ አስም ሲያፍንሽ ሽበት እንደሙዳይ በጭንቅላትሽ ላይ በድንገት ሲፈላ ያይንሽ ከረጢቱ በንቅልፍሽ ሲሞላ ምድጃ ዳር ሆነሽ መፃፍሽን ከፈተሽ ያለፈውን ዘመን ገልጥ ስታነቢ የኔን ቃል አስቢ እወድሻለው ያልኩሽን ከልብሽ አንብቢ ስንቶአፈቀሩት በሀይቅ በይስሙላ የገጽሽን አቦል የውበትሽን አፍላ ግን አንድ ሰው አለ ከሌሎች ወንዶች ጋ ያልተመሳሰለ በዕጽብ ድንቅ ፍቅርሽ የነደደ የመልክሽ ፀደይ ሲያልፍ ልክእንደመስቀል ወፍ ጥሎሽ ያልነጎደ። 〰〰〰〰〰〰〰
نمایش همه...
አንድ ሰው አለ.mp39.89 KB
እሷን መልሱልኝ እግዜር ከሰዉ ለይቶ እንደሰራት እንደ ማህተብ ከልቤ ያነጻት በፍቅር ደቂቃ ሰኮንዶች የሆነችኝ ሀሁ በላ ፍቅርን ያስቆጠረችኝ ሀገር ምድሩ የመረቃት ከእኔም ልብ ዘመናት ያቆያት ጠፊ ሁና የዉሃ ሽታ ሁለመነዋ ሊቀር በትዝታ ልቤ ሳይደፈን ሳይዘጋ ማንም ላይገባበት እሷን መልሱልኝ የልቤን ነገር ዳግም ታስብበት ✍️ዳዊት ============================ @eliyasshitahun @eliyasshitahun @betagitim @betagitim
نمایش همه...
#በዚህ_ጊዜ እሬሳ ቀለለ ሞትም እረከሰ፣ የሰው ልጅ ክብር ከእንስሳ አነሰ። ወንድም ወንድሙ ላይ ጦር እየሰበቀ፣ መኖር ብርቅ ሆነ ጥል እየደመቀ።     @Henilogy [ገጣሚ ሄኖክ ፀጋዬ] ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @eliyasshitahun
نمایش همه...
🎤ስላለው መች ኖረ                                ሁሉም ያያል እንጅ ጣፋጭ መራራውን በፈረቃ ሕይወት ማጣት ማግኘትን ስላጣም አልጠፋ ስላለው አልኖረ የከፋው ሰው ሞቶ የደላው መች ቀረ።                            ✍Nahom @semetenbegtm @semetenbegtm @semetenbegtm
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.