cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የ ቤዛ ግጥሞች

ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ፣ግጥም በድምጽ፣የተለያዩ መፀሐፍት pdf ያገኛሉ። እናመሰግናለን። ግጥሞችን ለማጻፍ Contact: @g_Aster16

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
248
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#አሣ_አጥማጅነት : : ጠይም አሣ መሳይ፤ ገፀበረከቴ የኔነቴ ሲሳይ፤ ደጋግመህ ብለኸኝ፤ እኔን ተላላዋን አንተስ አሞኘኸኝ። : : ቁጭ አሣ መሳይ ነሽ፤ ከሰው የተለየሽ፤ የሚለው ድምፅህን አጅበ በዜማ፤ ልበቢሱ ልቤም ደጋግሞ ቢሰማ፤ እውነት መስሎት ቃልህ ነገን በማሰቡ፤ ከጣልኸው ትብታብ ውስጥ ገባ ከመረቡ። : : አንተ ግን ስታውቀው እመረብ መግባቴን፤ ልብሶቼን ገፈኸኝ ቀረው እራቁቴን። ከዚያስ መቼ ሰከንክ፤ አካሌን ብታየው እየተብከነከንክ፤ ፈጥነ በችኮላ፤ አሣ መሳይ ስትል ያወጅኸውን ገላ፤ ርሀብ አትችል ጥጋብ አጣጥመ በላ። : : አሣ መሳይ ሚለው፤ ፍቅር የሚመስለው፤ ያንተው ቃል ሲለካ፤ አሣ አጥማጅነት ሙያክ ኖሯል ለካ። (እንደ ፍቅር ተፋቅረን እንደ ፍቅር አንድ አካል እንሁን) #ሄኖክ_ብርሃኑ @getem @getem @getem  
نمایش همه...
አታዉቅም . . ትመጣለህ ብዬ አመታት ቢያልፉም፤ እመነኝ ዉድዬ ይህን ሁሉ አታዉቅም። በመናፈቅ ብዛት ልቤ እንደታከተ፤ ጠረንህ ርቆት ዝሎ እንደዋተተ። ፍቅርህን ተርቤ በጠኔ እንደማቀኩ፤ ከትዕግስቴ ጋራ ጦር እንደተማዘዝኩ። በፋሲካ ማግስት ሱባዔ እንደገባሁ፤ ባዕቴን ዘግቼ ተስዬ እንደመጣሁ። የሀዘን ድርብርብ ቤት እንደሰራብኝ፤ መድሀኒት የሌለው ደዌ እንዳገኘኝ። አይሽርልኝ ቁስሌ እያመረቀዘ፤ ህመሜን አባሰዉ እየጠዘጠዘ። ቁር ያቆረፈደዉ ሽብሽቡ ቆዳዬ፤ በእንባ ሞጭሙጮ የደከመው አይኔ፤ በዘመናት ንጉደት ፀጉሬ ቢሸብትም፤ መንጋጋዬ ረግፎ በድዴ ብቀርም፤ ጉልበቴ ተዳክሞ ወገቤ ቢጎብጥም፤ አንተን የሚያልመዉ ልቤ አላረጀም። ድንገት ባጋጣሚ ልትመጣ ካሰብክ ከበራፉ አለሁ ጥለኸኝ እንደሄድክ እደጅ ተቀምጬ እጠባበቃለሁ፤ አይንህን ለማየት ሠርክ እናፍቃለሁ። በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ(@ediwub) @getem @getem @getem
نمایش همه...
Repost from ሥነ-ግጥም
¶ዝምተኛ ልቦች ግጥም _ ጌትነት እንየው ድምጻዊ _ ሚካኤል በላይነህ አምነው የወደዱ፣ ወደው የተካዱ፣ ተክደው የራዱ፣ ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣ የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው? የትነው መድረካቸው? ማነው አጃቢያቸው? እንዴት ነው ምታቸው? የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣ የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው? የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣ ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣ ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣ ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣ ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው? ከየት ነው ጥሪያቸው? በየት ነው ጉዟቸው? የት ነው መድረሻቸው? እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣ የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው? መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣ ከእምነት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣ ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጠሩ፣ ተገፍትረው ወድቀው፣ ደቀው እንዳይቀሩ፣ በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ። @amharic_poems
نمایش همه...
💚 መቼ ትመጣለህ   💚 ፀሀይ ስትዘቀዝቅ ስታዞረው ፊቷን ጨረቃ ስትስቅ ስናይ ፈገግታዋን ሲከፋኝ ስታመም ስምህን ሳነሳ ስላንተ ሳወጋ ፍቅርህን ሳወሳ አልበላ ሲለኝ ባር ባር ሲለው ሆዴን ንገረኝ መቼ ነው እማየው አይንህን ለሊት አልጋዬ ላይ ሆኜ እንቅልፌ ሲጠፋ መኖር አስጠልቶኝ ልቤ ሲቆርጥ ተስፋ ስልኬን አነሳ እና ፎቶህን አያለሁ ትመጣለህ እያልኩ በርበሩን አያለሁ ከቀጠርከኝ ቦታ ቀድሜ ብደርስም ቆሜ ብጠብቅም አንተ ግን  የለህም ትመጣለህ አደል አትቀርም ልጠብቅ ዝናቡ ቢዘንብ ቢወርድብኝ መብረቅ ነይ ካልከኝ ቦታ ላይ ቆሜ አንተን ስጠብቅ ጎርፍ ወስዶ ቢጥለኝ ባካል ካንተ ብርቅ ስቃዩ ቢበዛ ቢከብድም ንፋሱ ሳትስመኝ አልሞትም ከንፈሬን በስሱ ባንተ ሳልታቀፍ ህሜን ሳልነግርህ አትቀርም ልጠብቅ መቼ ትመጣለህ🤔 https://t.me/+4oRgKfx0afBhMjM8        💚@Quotes_Amharic💚
نمایش همه...
አገባህ ነበረ…………… ቆሎ 'የቆረጠምን እኖራለን ውዴ ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ አንቺ ውሀ አጣጬ የእግዜር ባለ አደራ እሺ በይኝ ላግብሽ ፍቅራችንም ይድራ:: አለኝ የኔ ሚስኪን..............                አገባህ ነበረ.................. ቆሎ ባልቆረጥም እርሀብ ባይደፋኝ ሊያውም በዚ ዘመን.......... ቆሎ ያልከው ውዴ ዝም ብለህ ስታየኝ የኤርፎራ ዶሮ እመስላለሁ እንዴ? ጭራሹን................. ልጅ በልጅ ሆኜልህ አንዱን ከኃላዬ ሌላውን ከፊቴ ገሚሱን በግራ ገሚሱን በቀኜ እሪ እምቧ ሲሉብኝ መንምኜ መንምኜ የድስት ፍቅፋቂ በጋራ ስንበላ ጎረቤት ቢረበሽ ይደብራል ኃላ እኔም ተማርሬ እግዜር ከሚከፋዉ ቆሎህን ለብቻህ ተደብቅህ ብላው::😉😁😁😁😂😂😂😂😂😂 በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ (@Tizita21) @beza_getem @beza_getem @beza_getem
نمایش همه...
አንቺ ተዪ ተዪ ተይ አልኩሽ አይደለ አምላክሽ አምላኬን እንደማታመልኪው ለምን በሁዳዴ አምብርቴ አከባቢ በስሱ ምትነኪው? አሁን ወጥ ረገጥሽ አበዛሽው አቦ ጠረንሽ ሲጠራኝ ገላሽን አስውቦ ይወሰውሰኛል አይደለውም ፍፁም በሀሳቤ ገድፌ  እንዴት ብዬ ልፁም? *-----------* @beza_getem @beza_getem @beza_getem
نمایش همه...
📢 አድዋ! ፈረስ ሲያስገመግም፣ጦር ጎራዴው ሲፋጅ ፣ተዘከር አድዋ ሰው በነጻ ሊኖር ሰው እየተሰዋ! አድዋ ትናንት ነው ፣ ዛሬ ነው ፣ነገ ነው የእድሜ ዘመን ጸጋ ከአያት የወረስነው አድዋ ታሪክ ነው አድዋ ተራራ ባንድ የዘመተበት ሰው ከፅላት ጋራ! አድዋ "እምነት ነው" የሰማዕት ገድል ስጋ ብቻ አይደለም መንፈስም ሰው ጥሏል! አድዋ "ሸማ ነው" ጠቢብ ያሳመረው ክፉ የማይፍቀው ዘመን ያላስረጀው! አድዋ ኩራት ነው  ሰው የመሆን ክብር በጥቁር ተሰብሯል ነጭ የገራው ቀንበር! አድዋ ጸሀይነው ሰው ያነጸው ጮራ ከሮም ብርሀን ነጥቆ ለጦብያ ያበራ! አድዋ "በትር ነው" ጠላት የሞተበት "አልሞት ባይ ተጋዳይ"  ድል የከጀለበት! አድዋ "ቅርስ ነው" አድዋ ስንክሳር ለኛ ጆሮ ሀሴት ለዚያ ጎራ ሀሳር! ይናገር ምኒሊክ ይናገር ይመስክር እምነትና ግዛት እንዴት እንደነበር!!! ክብር በዓድዋ ተራራ በባዶእግራቸው በጦርና ጎራዴ ዘመናዊ መሳርያን ከታጠቀ ወራሪ ጋር ታግለው ዛሬ በየ ፊናችን "አድዋ አድዋ..." እያልን እንድንዘምር ዋጋ ለከፈሉልን ለኒያ ጽኑና ጀግኖች አባቶቻችን ይሁን!!! እንኳን ለ 127ኛው የጥቁር የነጻነት ቀን አደረሳችሁ ! ©ታደሰ ደምሴ ━━━━━━━━ @beza_getem @beza_getem @beza_getem
نمایش همه...
ብቻ አልሙት እንጅ…………✍ ....እኔ አልሙት እንጂ......ከሞትኩ ተዐምር ይፈጠራል ....ድንቅ ተዐምር .....አዎ እኔ አልሙት እንጂ ከሞትኩ ለሰርጌ ያልወጡ ሺ ብሮች ለሀዘኔ ይባክናሉ....... ብቻ አልሙትእንጂ የሞቴን ቀን ሲቆጥሩ የነበሩ ባላንጣዎቼ በእምባ ታጥበዉ ...ጥቁር ተከናንበው እኔን እኔን እያሉ ይመጣሉ..... አልሙት እንጂ ከሞትኩ ክፉ ናት ያሉኝ ሁላ የዋህ ሰዉ አጣን እያሉ ደረታቸዉን ይወግራሉ .......ከምር አልሙት እንጅ አበድሩኝ ብዬ ፊት የነሱኝ ሁሉ የሬሳ ሳጥን ለመግዛት ያዋጣሉ ...."ለ'ሷ ያልሆነ" ይላሉ ...... ብቻ አልሙት እንጂ እኔ ከሞትኩ...... "ምን አዉቅልሻለሁ...ገደል ግቢ"....አላዉቅልሽም እያለ ያጥላላኝ ተፈቃሪዬ .....ከሀዘን ማቅ ስገባ እንደዋዛ የገፋኝ ተፈቃሪዬ ...በህይወት ሳለሁ እንዲሰጠኝ የለመንኩትን አበባ መቃብሬ ላይ ሊያስቀምጥ ይመጣል ....በህይወት ሳለሁ ያላለኝን አፈር ለሆነዉ ገላዬ ያወራል ............. ብቻ እኔ አልሙት እንጂ እነዛ "ይቺ እብድ ስታስጠላ "ብለዉ ያሙኝ ሁላ ስኳርና ዳቦ ይዘዉ "ወይኔ ጓደኛዬ" እያሉ ይመጣሉ ..... ስኖር ደዉለዉ ያልጠየቁኝ አራስ እያለሁ ሚያዉቁኝ ዘመድ አዝማዶች ሁሉ ...."ምነዉ በለጋነቷ" ልጄን፣እህቴን  እያሉ ይጎርፋሉ ................ ብቻ አልሙት እንጂ ብዙ የአፍቃሪ እንባዎች ብዙ የድራማ እንባዎች ይፈሳሉ ........"ለእኔ መስሏቹ ነው ለራሳቸው" እኮ ነው…ምናለ እንዲህ ባደረግንላት ይላሉ......"ብመለስምኮ አይቀየሩም" ግን አንደማልመለስ ስለሚያዉቁ እንድመለስ ይፈልጋሉ .....አንዳንዴ ብሞትና አልቃሾቼን አይቼ ብመለስ እላለሁ ......ግን አይሆንም እሞታለኋ አላያቸውም ስሞት ያልነበሩ ነገሮች ይኖራሉ ....ስኖር ያላስታወሱኝ ስሞት ይናፍቁኛል....ስኖር የገፉኝ ሳልኖር ይፈልጉኛል....የአብሮነቴ ትርጉም ይገባቸዋል… ይጎድላሉ …ግን አልኖርም… አልመለስም… ዛሬ ግን አለሁ ስሞት የምትፈጥሩትን ተዐምር ዛሬ መፍጠር አትችሉምን??????
نمایش همه...
"ግን" . . በንግግር መሐል ከቁብ የማንቆጥራት፤ አብራ የታከለች "ግን" የምትል ቅንጣት፤ ጎልታ ባትሰማም እልፍ ነው ትርጉሟ፤ ብትሸፋፈንም ስዉር ነው ህመሟ። አያሌ ነገራት በዉስጧ ደብቃ፤ ስንቱን አሰመጠች ጥላ አሳስቃ። የቃሏ ግብር ስቃይን ወልዶ፤ በቁም ይገድላል በራስ ተንዶ። ደስታ የተለየው የሀሰት ፈገግታ፤ ማንባት የከጀለዉ የማስመሰል ፌሽታ። የዉስጥ ሀዘን የዋይታ ስላቅ፤ በጉም ተደብቆ የተዳፈነ ሳቅ። @beza_getem @beza_getem @beza_getem
نمایش همه...
👉ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ። @beza_getem
نمایش همه...