Bashewam Primary & Junior School 1-8
رفتن به کانال در Telegram
2 771
مشترکین
+524 ساعت
+157 روز
+6530 روز
آرشیو پست ها
የ2016ዓም የመጀመሪያ የትምህርት መክፍቻ ቀን በባሸዋም ትምህርት ቤት
First Day Back To School, 07/01/2016E.C
Wel Come To Your Second Home!
ለባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪዎች ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡
፡
ውድ የባሸዋም ተማሪዎች እና ወላጆች እንኳን ለ2016ዓም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ፡ እያልን ከዚህ በታች ባለው መመሪያ መሰረት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ።
የ2016ዓም ትምህርት ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል ነገ ሰኞ መስከረም 7/2016ዓም ይጀምራል ።
መስከረም 7 እና 8/2016ዓም ትምህርት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን በመሆኑ ወላጆች ልጆቻችሁን ከቀኑ 6:45 ትምህርት ቤት በመምጣት እንድትወስዱ እናሳስባለን ።
ትምህርት ከጠዋቱ 2:30 ስለሚጀመር ተማሪዎች ቀደም ብለው ከጠዋቱ 2:00 በፊት ትምህርት ቤት መገኘት ይኖርባቸዋል ።
ከኬጂ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፡ ወላጆች ትምህርት ቤት በመምጣት ልጅዎን በየክፍሉ ለተመደቡ ረዳት መምህራን በአግባቡ እንዲያስረክቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
ከአፀደ ህፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ምሳ እቃ እና ቦርሳቸው ላይ ስማቸው መፃፍ አለበት ።
ሁሉም ተማሪዎች የተማሪ የደንብ ልብስ Uniform አሟልተው መምጣት አለባቸው ፡ ዩኒፎርም ሳይለብስ የሚመጣ ተማሪ ትምህርት ቤት ውስጥ የማናስገባ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ።
ማንኛውም ተማሪ ከመስከረም 9/2016ዓም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት የሚገባው የተማሪ መታወቂያ በማሳየት በመሆኑ ልጅዎ መታወቂያ ይዞ(ዛ) ወደ ትምህርት ቤት መምጣቱን(ቷን) እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን ።
ጀማሪ ተማሪዎች መታወቂያቸውን አንገታቸው ላይ ማንጠልጠል አለባቸው ። ወላጆች ትምህርት ቤት ሲመጡ የህፃኑን(ኗን) መታወቂያ መያዝ አለባቸው ።
የትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ተጠቃሚ ወላጆች ወይም መጠቀም የምትፈልጉ ፡ ረቡዕ መስከረም 9/2016ዓም አገልግሎት መስጠት ስለምንጀምር፡ መጠቀም የምትፈልጉ መስከረም 7 እና 8/2016ዓም በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ እና ክፍያ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን።
ባሸዋም ትምህርት ቤት ፡ "ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን"።
መስከረም 6/2016ዓም
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
