es
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

Ir al canal en Telegram

Bashewam School Grade 1-8

Mostrar más
2 771
Suscriptores
+524 horas
+157 días
+6530 días
Archivo de publicaciones
የ2016ዓም የመጀመሪያ የትምህርት መክፍቻ ቀን በባሸዋም ትምህርት ቤት First Day Back To School, 07/01/2016E.C Wel Come To Your Second Home!

ለባሸዋም ትምህርት ቤት የተማሪዎች ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ ፡ ፡ ውድ የባሸዋም ተማሪዎች እና ወላጆች እንኳን ለ2016ዓም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ፡ እያልን ከዚህ በታች ባለው መመሪያ መሰረት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኩልን በአክብሮት እንጠይቃለን ። የ2016ዓም ትምህርት ከኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል ነገ ሰኞ መስከረም 7/2016ዓም ይጀምራል ። መስከረም 7 እና 8/2016ዓም ትምህርት የሚሰጠው ለግማሽ ቀን በመሆኑ ወላጆች ልጆቻችሁን ከቀኑ 6:45 ትምህርት ቤት በመምጣት እንድትወስዱ እናሳስባለን ። ትምህርት ከጠዋቱ 2:30 ስለሚጀመር ተማሪዎች ቀደም ብለው ከጠዋቱ 2:00 በፊት ትምህርት ቤት መገኘት ይኖርባቸዋል ። ከኬጂ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፡ ወላጆች ትምህርት ቤት በመምጣት ልጅዎን በየክፍሉ ለተመደቡ ረዳት መምህራን በአግባቡ እንዲያስረክቡ በጥብቅ እናሳስባለን። ከአፀደ ህፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ምሳ እቃ እና ቦርሳቸው ላይ ስማቸው መፃፍ አለበት ። ሁሉም ተማሪዎች የተማሪ የደንብ ልብስ Uniform አሟልተው መምጣት አለባቸው ፡ ዩኒፎርም ሳይለብስ የሚመጣ ተማሪ ትምህርት ቤት ውስጥ የማናስገባ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን ። ማንኛውም ተማሪ ከመስከረም 9/2016ዓም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት የሚገባው የተማሪ መታወቂያ በማሳየት በመሆኑ ልጅዎ መታወቂያ ይዞ(ዛ) ወደ ትምህርት ቤት መምጣቱን(ቷን) እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን ። ጀማሪ ተማሪዎች መታወቂያቸውን አንገታቸው ላይ ማንጠልጠል አለባቸው ። ወላጆች ትምህርት ቤት ሲመጡ የህፃኑን(ኗን) መታወቂያ መያዝ አለባቸው ። የትምህርት ቤት የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ተጠቃሚ ወላጆች ወይም መጠቀም የምትፈልጉ ፡ ረቡዕ መስከረም 9/2016ዓም አገልግሎት መስጠት ስለምንጀምር፡ መጠቀም የምትፈልጉ መስከረም 7 እና 8/2016ዓም በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ እና ክፍያ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን። ባሸዋም ትምህርት ቤት ፡ "ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ ነን"። መስከረም 6/2016ዓም

+9
GRADE 8 AMHARIC.pdf4.50 MB

+9
GRADE 7 AMHARIC.pdf4.49 MB

+5
GRADE 6 AKABABI SCIENCE.pdf21.36 MB