cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)

በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :- ፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን። ፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን። ፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን። ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
190
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-27 روز
-130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

نمایش همه...
$PRETON DROP

Preton community: @preton Preton community: @preton_cis Chat: @chat_preton Cooperation: @eleidans

+ ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ይህን ይጸልዩ + የግብፅ ቤተክርስቲያን በቅርቡ ማዕረገ ቅድስና የሠጠቻቸው ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡ ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ +++ ጸሎት +++ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡  ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! join shere👇👇 @mahbretsione @mahbretsione @mahbretsione                   ማኀበረ ጽዮን
نمایش همه...
- የሚሮጥ ዲያቆን - የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ገደማ ነው:: አቧራማውን የጋዛ ምድረ በዳ በፈጣን ሩጫ እያቦነነ የሚከንፍ አንድ ወጣት ታየ:: ሩጫው የነፍስ አድን ሠራተኞች ዓይነት ፍጥነት ያለው ነበረ:: አንዲትን ነፍስ ሳታመልጠው ለማትረፍ እየከነፈ ነው:: የሚሮጠው ደግሞ በፍጥነት በሚጋልቡ ፈረሶች የሚጎተት የቤተ መንግሥት ሠረገላ ላይ ነው:: በሰው አቅም ፈረስ ላይ ሮጦ መድረስ ባይቻልም ይህ ወጣት ግን ፈረሶቹ የሚያስነሡትን የጋዛን አቧራ በአፉ እየቃመ በአፍንጫው እየታጠነ እንደምንም ደረሰ:: በሠረገላው ውስጥ አንድ ጸጉረ ልውጥ የሩቅ ሀገር ሰው ተቀምጦ በእርጋታ መጽሐፍ እያነበበ ነው:: እግሩን እንደ ክንፍ ያቀለለው ሯጩ ዲያቆን ፊልጶስ ይባል ነበር:: በዚያ ምድረ በዳ ብቻውን ሲሮጥ የሚያጨበጭብለት ሰው የሚሸልመው ደጋፊ አልነበረም:: እንዲያውም ልብ የሚሰብ ኀዘን ላይ ነበረ:: እስጢፋኖስ የሚባል አብሮት ዲቁና የተሾመ የቅርብ ጓደኛውን በድንጋይ ወግረው በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉበት ገና አርባ ቀን አልሆነም:: "ቤተክርስቲያን ስደት ላይ ሆና ምን ስብከት ያስፈልጋል?" በሚል ቀቢጸ ተስፋ እጁን አጥፎ ያልተቀመጠው ፊልጶስ ግን የወንድሜን ኀዘን ልወጣ ሳይል የምሥራች ለማብሠር በበረሃ ሮጠ:: ቀርቦ ያናገረው ጃንደረባ ደግሞ "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" የሚል ኦሪትን ይዞ ትርጓሜ ፍለጋ የሚቃትት ፣ ጥላው ይዞ አካሉን ፍለጋ የሚጨነቅ ትምህርት የተጠማ ኢትዮጵያዊ ነበረ:: ስለዚህ ይህ ዲያቆን መዳን የምትሻውን የጃንደረባውን ነፍስ በመዳን እውቀት አረስርሶ አሁኑኑ ካልተጠመቅሁ አሰኛት:: ብቻውን የሮጠውና አንድ ሰው ያስተማረው ዲያቆን ፊልጶስ ሮጦ ያዳነው አንድ ሰውን ብቻ አልነበረም:: በአፍሪቃ ቀንድ ለምትገኘው ሀገር ኢትዮጵያና ሕዝቦችዋ የመዳን ቀንድ የሆነ ክርስቶስን አሳያቸው:: አንድ ኢትዮጵያዊ አጥምዶ በእርሱ ብዙዎችን ከማጥመድ በላይ ምን ሙያ አለ? ጴጥሮስን በጀልባው ላይ ከዓሣ አጥማጅነት ወደ ሰው አጥማጅነት የቀየረ አምላክ ገንዘብ ያዡን ባኮስ ነፍሳት ያዥ አድርጎ ሸኘው:: "የህንደኬ ሹም ባኮስ ሆይ ከአሁን ወዲህ በህንደኬ ገንዘብ ላይ ብቻ አትሠለጥንም ፤ የእግዚአብሔር ገንዘቦች የነፍሳት ግምጃ ቤት ላይ የሠለጠንህ የመንግሥተ ሰማያት በጅሮንድ አደርግሃለሁ" ብሎ ሾመው:: ይህ ከሆነ ሁለት ሺህ ዓመት አለፈ:: የጃንደረባው የልጅ ልጅ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሠረገላ አልፎ በፍጥነት በሚሔድ ብዙ ዓይነት መጓጓዣ ሊሳፈር ተሰለፈ:: ትዕግሥት አጥቶ በገንዘብ ላይ ከመሠልጠን ይልቅ ገንዘብ ሠልጥኖበት በፍጥነት ከነፈ:: አንዱ ፊልጶስ ብቻ ሮጦ የማይደርስበት እልፍ ሕዝብ ዛሬ ሠረገላውን አጨናንቆታል:: እንደ ጃንደረባው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሳይሆን ስልኩ ላይ ያቀረቀረ ፣ ስለ ትንቢት ትርጉም ሳይሆን ስለ ኑሮ ብልሃት የተመራመረ ትውልድ ተነሥቶአል:: የኢሳይያስ ትንቢት ስለማን ቢነግር የማይገደው የሕይወት ውጣ ውረድ ፍቺ የሚሻ ትንቢት የሆነበት ፣ በመንፈስ ጭንቀት የታወከ ምስኪን ትውልድ ተነሥቶአል:: በእርግጥ ይህ ትውልድ ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት የሚመራው ሳይኖር እንዴት ይቻለዋል? ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ፊልጶስ ከወዴት ይምጣ? ኸረ የዲያቆን ያለህ? ነፍስ አድን ፊልጶሳዊ ዲያቆን ሆይ ከወዴት ነህ? ነፍሳትን ለማዳን የሚያሳድድ እንጂ የሥጋ ምኞቱን የሚያሳድድ ዴማሳዊ ዲያቆን አልጠፋም:: እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ የሚወገር ዲያቆን እንጂ ድንጋይ አንሥቶ የሚማታ ዲያቆን አልጠፋም:: ሰረገላ ላይ ሆነው ግራ የተጋቡ ባኮሶች ብዙ ናቸው የፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ችግራቸውን ፈትቶ ጥያቄያቸውን መልሶ የሚሰወር ከሠረገላ አልወርድም ብሎ የማያስቸግር ፊልጶስ ግን እጥረት አለ:: ከእናንተ ቀድመን በተሾምን ዲያቆናት አንገትዋን የደፋች ቤተ ክርስቲያን በእናንተ ቀና እንድትል እንመኛለን:: የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ምእመናን እሱን ፍለጋ የሚሮጡለት ዲያቆን ሳይሆን ነፍሳትን ፈልጎ የሚሮጥ ዲያቆን ያድርጋችሁ:: ከመቅደሱ ጠፍቶ የሚፈለግ ሳይሆን ፈረስ የማያመልጠው ዲያቆን ያድርጋችሁ::
نمایش همه...
09:23
Video unavailableShow in Telegram
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል። እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ነበረች ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣለች። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች። በውጭም በሀገር ውስጥም ያላችሁ ወገኖቼ  ያለኝን ጨርሻለሁ አሁን ላይ ያለኝን ቀሪ ነገር ኩላሊቴን ልስጠው ነውና ገንዘብ ያለው በገንዘቡ የሌለው በሃሳብና በጸሎት አግዙኝ ወንድሜን አድኑልኝ ስለፈጣሪ ተባበሩኝ የሰው ህይወት በማዳናችሁ በፈጣሪ ታገኙታላችሁ።                    ፍሩታ አሻግሬ              የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ               1000629004045 ለበለጠ መረጃ ➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929 ➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
نمایش همه...
15.47 MB
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት
نمایش همه...
👍 2
Repost from N/a
#የአባቶች_ምክር #ሀሜት :- ያለመሳሪያ ሰውን መግደል ነው። #ማጉረምረም :- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው። #ቁጣ :-  ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው። #ብስጭት :- የተበሳጨንበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የኃጢያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነው። #መዋሸት :-  እውነተኛን ሰው ሳይታዩ የሚጎዱበት ረቂቅ የሰይጣን ጦር ነው። #መርገም :- አቅም ሲያንስ ወደላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው። #መሳደብ :- ህሌናን የሚያቆስል ቁስሉ ተሎ የማይድን አቅም የሌላቸው ሰዎች ዱላ ነው። #ዋዛ_ፈዛዛ :- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው። #የማይገባ_ሳቅ :- አላፊ አግዳሚውን የሚያጠምዱበት የአመንዝሮች ወጥመድ ነው። #መሳለቅ :- በአካል ጉዳተኛ ሰው ላይ የሚዘብቱበት  የመርገም ስንቁ ወግ ነው። #ዘፈን :- ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ክፉ ፈላጻ ነው። #ድንፋታ :- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ ነው። #መንፈግ :- የሚለምነውን ሰው የሚወጉበት የስስታሞች ፈላጻ ነው። #በክፉ_መንሾካሾክ :- ቀስ ብለው ሰውን የሚገሉበት የአሳባቂዎች ጩቤ ነው። #ነገር_ማመላለስ :- የሚዋደዱትን የሚለዩበት የዲያብሎስ የግብር ልጆች መሳሪያ ነው።
نمایش همه...
#ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ አይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው? ታድያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘለዓለም ሲወድቁ እንደ ምን እጃችንን የበለጠ አይዘረጋም?ወገኖቼ!በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰውን ስታዩ "ይህ የእኔ ሥራ አይደለም: የቀሳውስትና የመነኮሳት ሥራ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ሚስት አለችኝ: ልጆችንም አሳድጋለሁ" አትበሉ፡፡ እስኪ ምሳሌ መስዬ ልጠይቃችሁ እናንተም መልሱልኝ፡፡ አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ "ይህ እኔን አይመለከተኝም፡ ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ" ትላላችሁን? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሡት አይደለምን? ይህ ወደ ዘለዓለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ  እንዲወድቅ አትግፋት፡፡ እግዚአብሔር ይህን በተመለከተ በአፈ ያዕቆብ እንዲህ ብሏልና፡- "ወንድሞቻችን ሆይ! ከእናንተ ወገን ከጽድቅ ወጥቶ የበደለ ቢኖር መክሮ አስተምሮ ከበደሉ የመለሰው ቢኖር ራሱን አንድም ወንድሙን ከሞት እንዳዳነ ይወቅ፡፡ የራሱን አንድም የወንድሙን ብዙ ኃጢአቱን እንዳስተሠረየ ይወቅ፡፡ አንድም የወንድሙን ነፍስ እንዳዳነ ይወቅ"(ያዕ.5:19-20)፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
نمایش همه...
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ እስከማዕዜኑ ።.pdf3.57 MB
1
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።   የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈዋል። ቅዱስነታቸው ምን አሉ ? ቅዱስነታቸው ፥ " ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም  " ሲሉ ገልጸዋል። ፈተናው ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ እንደሚከባትም አመልክተዋል። " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ " ያሉ ሲሆን " የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች ሲሉ ገልጸዋል። የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት እንደሆኑ አሳውቀዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ፥ " ከጥንት ጀምሮ የነበረ ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩ ፦ ° ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ ° መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ° ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን #ተሰሚነትና #ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው " ብለዋል። " እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጥ ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል " ሲሉ ገልጸዋል። " የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል " ሲሉም አሳውቀዋል። ቅዱስነታቸው፤ " በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም " ያሉ ሲሆን " ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም " ብለዋል። ባለፉት ዓመታት አስከፊ የሆነ በደል መፈጸሙን የገለጹት ቅዱስነታቸው " አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " ሲሉ ገልጸዋል። " በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል " ሲሉም አስገንዝበዋል። ጉባኤውም በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል ብለዋል። (የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
نمایش همه...