cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Al EHSAN አል_ኢህሳን

የቻናሉ አላማ 1 ባለን አቅም እስልምናን በአግባቡ ለኡማው ማድረስ 2 ሙስሊሞችን በድናቸውም ይሁን በዱኒያ እውቀታቸው የነቁ እንድሆኑ መገፋፋት 3 ለወጣቶች ምክር 4 በልዩ መልኩ ሴቶችን ማንቃትና ሌሎቹም አለማዊና መንፈሳዊ ት/ቶች ይገኙበታል። ውድና የተከበራቹ የአል ኢህሳን ቻናል ቤተሰቦች ሆይ ውብና ማራኪ የሆኑ ሀሳብ አስተያያታቹ እንዳይለይን ♥♥ ለአስተያት @S1u9l አሁኑኑ ይቀላቀሉን 👇

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
194
مشترکین
-124 ساعت
-37 روز
-630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

በሱፊያው ዓለም በርካታ የሚመለኩ ቀብሮች አሉ። ቀብሮቹ ዘንድ በመሄድ ልጅ፣ ዝናብ እና የተለያዩ ሐጃዎችን ይማፀናሉ። የሞተ ሰው እንኳን የነሱን ጉዳይ ሊፈፅም ከራሱ፣ ከተሰራለት ዶሪሕ እንኳ መከላከል አይችልም። ይሄው ይሄ "ወሃቢ" የሆነ ጎርፍ ዶሪሑን ነቅሎ እየወሰደው ነው። { أَیُشۡرِكُونَ مَا لَا یَخۡلُقُ شَیۡـࣰٔا وَهُمۡ یُخۡلَقُونَ (191) وَلَا یَسۡتَطِیعُونَ لَهُمۡ نَصۡرࣰا وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ (192) } "ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)?" [አልአዕራፍ፡ 191-192] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
አሠላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች ይች እህታችን ስሟ ተምሬ አራጋው ጎቸል ትባላለች ከፓስፖርቱላይ እንዳለው በጠለብ ከአራትና አምስት ወር በፊት ሳኡድ ጂዳ ከተማ ገብታ ነበር እናም አሰሪዋ መንገድ ላይ ጥላታለች አሉን። አእምሮዋም ትክክል አይደለም ቪዶወውላይ እንደምታዩት።የቀረጿትም ልጆች ልንወስዳት ስንል ሴትየዋ እምቢአለችን አሉ በሰአቱ ዘወር ብለው ሲመለሱም ከቦታው እንዳላገኙዋት ነው የተናገሩት እና ጂዳ አካባቢ ያላችሁ በተለይ እባካችሁ ይችን እህታችንን ያያት ካለ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን። አላህ ሁላችንም ይጠብቀን እሷንም ያስገኛት!! እኔ የሰፈሯ ልጂ ነኝ ካገኛችኋት 0532053175 Bint Mohammed በዚህ ቁጥር በዋሳብም ወይም በመስመር ያገገኙኛል ይደውሉ የሠማችሁም አደራ ሸር አድርጉልኝ
نمایش همه...
ጓደኛህ ማነው? ~ ጓደኛህ ወደ ተሻለ የምትወስደው ወይም ወደተሻለ የሚወስድህ ይሁን። ካልሆነ ግን ወይ ያጠፋሀል። ወይ ታጠፋዋለህ። ወይ ተያይዛችሁ ትጠፋላችሁ። ሰው ውሎውን ይመስላል። ውሎህ የት ነው? ከማን ጋር? ሰዎች ጠጪ የሚሆኑት በጓደኛ ሰበብ ነው። ቃሚ፣ አጫሽ የሚሆኑትም በጓደኛ ተፅእኖ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" የሚባለው። ከመጥፎ ሱስ መውጣት፣ ባህሪህን መግራት ትፈልጋለህ? ከልብህ ከሆነ ውሎህን አስተካክል። ልጅህ ከመጥፎ አዝማሚያ እንዲመለስ፣ መስመር እንዲይዝልህ ትፈልጋለህ? ሰበብ ሳታደርስ ጠዋት ማታ አትጨቃጨቅ። ይልቁንም ውሎው ላይ አጥብቀህ ስራ። ካልሆኑ ጓደኞች ጋር ገጥሞ ከሆነ የምትችለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ለየው። ለብዙዎች በዲንም ይሁን በዱንያ መቃናት መልካም ጓደኛ ትልቅ ድርሻ አለው። እስኪ በህይወት ጉዟችሁ ላይ አነሰም በዛ ላገኛችሁ ስኬት ወይም መልካም ለውጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ለአፍታ አስቧቸው። በተቻለ መጠን ውለታ መላሽ ሁኑ። እሱ ቢቀር አመስጋኝ ሁኑ። ከዚያም በላይ በዱዓእ አስታውሷቸው። ጓደኝነት ኣኺራን ከነጭራሹ ሊያጨልም፣ ኩ. ፍ. ር ላይ ሊጥል ይችላል። በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ለተረዱት እውነት እጅ መስጠት አቅቷቸዋል?! በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ውስጣቸው እያወቀ እምነት ቀይረዋል? ስንት ወንዶች ሴት ተከትለው፤ ስንት ሴቶችም ወንድ ተከትለው ዘላለማዊ ህይወታቸውን አጨልመዋል?! የተሰጠን እድል ከእጃችን ሳያፈተልክ፣ ነፍሳችን ሳትሾልክ በፊት ሳይመሽ እናስብበት። እንወስን በጊዜ። ነገ ፀፀት እንዳይበላን። ጌታችን እንዲህ ይላል:- { وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا (27) یَـٰوَیۡلَتَىٰ لَیۡتَنِی لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِیلࣰا (28) لَّقَدۡ أَضَلَّنِی عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَاۤءَنِیۗ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِلۡإِنسَـٰنِ خَذُولࣰا (29) } {በዳይም፡ «ምነው ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)። «ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ። (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)። ሰይጣንም ለሰው በጣም ለውርደት አጋላጭ ነው።} [አልፉርቃን፡ 27-29] (ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 2/2016) = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

መራር እውነታ!
نمایش همه...
የሴት ልጅ መስተካከል የማህበረሰብ መስተካከል ነው!! 📌 ሸይኽ ፈውዛን ሀፊዘሁሏሁ እንዲህ ይላሉ: ሴትን ልጅ በተጨባጭ ካየናት ለማህበረሰቡ እንደ መርህ ልታገለግል የምትችል አካል ነች እሷ ቀጥ ካለች ከተስተካከለች ማህበረሰቡ ይስተካከላል እሷ ከተበላሸች ማህበረሰቡ ይበላሻል። ምንጭ: (التعليق القويم على كتاب إقتضاء الصراط المستقيم ) 📌 ይህን ያሉበትን ምክንያት ካየን ልጆችን አንፃ ምታሳድገው አብራቸው ምትውለው ሴት ልጅ ነች ከአላህ በታች የነገው ትውልድ እጣ ፋንታ የወደቀው በሴት ልጅ እጅ ነው  እና የሴት ልጅ ስነ-ምግባሯ ተበላሸ ማለት ዲንን ሀገርን የሚረከበው ትውልድ ተበላሸ ማለት ነው ስለዚህ ሴት ልጅ እራሷን ችላ የቆመች አንድ መድረሳ ነች ማለት እንችላለን ይህ መድረሳ የተበላሸ ከሆነ ላሸክ ከዚህ መድረሳ ተመርቀው ሚወጡትም ተማሪዎች የተበላሹ ስለመሆናቸው የቀደምቶችንም ታሪክ መለስ ብለን ካየን አሁን ላይ አኢማዎች ብለን ምንጠራቸው የመልካም እናቶች ውጤት ናቸው እነ ኢማሙ አቡ ሐኒፋን እነ ኢማሙ ሻፊኢን እነ ኢማሙ አህመድን እነ ኢማሙል ቡኻሪን ይመስል ሌሎችም 📌 እና ሴት ልጅ የያዛችው(የተሸከመችው) ሀላፊነት ከባድ ነው ሀገርን አለምን ነው መገንባት የያዘችው ነገር ግን አንዳንድ ዘምነናል የሚሉ የተፈጠሩበትን አላማ የዘነጉ ፌሚኒዝም በሚለው ልክፍት የተለከፋ ሴት ልጅ እቤቷ ቁጭ ብላ ልጆቻን መንከባከቧ ማነፃ እንደ ሗላ ቀርነት የሚያዩ አካላቶች አሉ ይህ ከእስላም አስተምህሮ ፍፁም የማይገናኝ አስተሳሰብ ነው ሗላ ቀር ማለት የተፈጠረለትን አላማ የዘነጋ ሰው ነው እና እህቶች ያለባችሁን ትልቅ ሀላፊነት በማወቅ ሀላፊነታቹን በተገቢው መልኩ ልትወጡ እና አላህንም በዚህ ነገር ላይ እንዲያግዛቹ ልጠይቁት ይገባል። አቡ ዐብዱ-ር'ረሕማን
نمایش همه...
🥰 1
"ሁሉም ሰው በፖለቲካ ተጠምዷል። ፖለቲከኞች ሲቀሩ። እነሱ ግን በንግድ ነው የተጠመዱት።" * ዐብዱል መሊክ አልኢብቢ * · · መሪር ሐቅ!! አብዛኞቻችን የፖለቲካው ማእበል ወስዶን ከዚያ ከዚህ እያላጋን ነው። አንዳንዱማ ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን እያስቀደመ የቆሻሻ ፖለቲካ ጎርፍ ወስዶታል። ፖለቲከኞቹስ? አብዛኞቹ የሞቀ ንግድ ላይ ናቸው። እንጀራቸውን ሊያበስሉ ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ከመንግሥት በተቃዋሚ ስም፣ ከህዝብ በነፃነት ትግል ስም፣ ከውጭ በሰብአዊ መብት ቅስቀሳ ስም ከያቅጣጫው ይዘርፋሉ። ለምስኪን ተፈናቃዮች የተሰበሰበን እርዳታ ይነጥቃሉ። በነሱ የፖለቲካ ጦስ የሚሞተው፣ የሚፈናቀለው፣ የሚጎዳው ግን ፖለቲከኞቹ ሳይሆኑ ህዝቡ ነው። ለዘመናት ተዋልዶ፣ ተጋምዶ የኖረ ህዝብ የፖለቲከኞች ድግምት ከተደገመበት በኋላ ፍፁም በማይታሰብ መልኩ አንዱ ሌላውን ያርዳል፤ ይሰቅላል፤ ያቃጥላል፤ ይወግራል፤ በጅምላ ያፈናቅላል። ፖለቲከኞቹ ግን በህዝብ እልቂት ገበያቸው ይደራል። በህዝብ መፈናቀል ንግዳቸው ይደምቃል። በኛ ስም በጮሁ ቁጥር ለኛ የተቆረቆሩ እየመሰለን ጆሯችንን እንሰጣቸዋለን። "ማንም በክፉ አይንካቸው" እንላለን። ፎቷቸውን አሳትመን እንለብሳለን፤ እንለጥፋለን፤ እንሰቅላለን። ግና ህዝብ እየከሳ እነሱ ይደልባሉ። ህዝብ እየተፈናቀለ እነሱ ለአይን ከሚያሳሳ ሰገነት መግለጫ ይሰጣሉ። የህዝብ ልጅ ወደ ትግል፣ የነሱ ልጆች ወደ ውድ ትምህርት ተቋማት። ህዝብ ወደ ታች እነሱ ወደ ላይ። (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 9/2011) = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

ጫት ከሌሎች ዘርፎች የተሻለ ትርፍ እንዳለው ይታወቃል። የጫት ንግድ ማለት ለወገን ገዳይ መርዝ እየሰጡ በምትኩ ገንዘባቸውን መውሰድ ነው። ይሄ ንግድ በወገን ህይወት ላይ መጫወት ያለበት እርኩስ ንግድ ነው። ትርፉ ሳያማልላችሁ ኣኺራችሁን በማስቀደም እንዲህ አይነት ውሳኔ የወሰናችሁ ጀግኖች ኒያችሁን፣ ልፋታችሁን አላህ ይቀበላችሁ። ለሌሎች ምሳሌ ያድርጋችሁ። ለዱንያም ለኣኺራም የሚጠቅማችሁ የተሻለ ሐላል ሪዝቅ ይስጣችሁ። የበዛ፣ የጣፈጠ በሆነ የጀነት ሲሳይ ያንበሻብሻችሁ። በዚህ ውሳኔ ላይ ድርሻ ያላችሁን ሁሉ አላህ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይመንዳችሁ። በነገራችን ላይ ጫት በመብላትም፣ በማብላትም፣ በማጓጓዝም፣ በመነገድም፣ ለጫት ንግድ በማከራየትም የተሰማራችሁ ሁሉ ወንጀል ላይ ናችሁ። አላህን ፈርታችሁ ከድርጊታችሁ ታቀቡ። = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
#Update በጎረቤት ሀገር #ኬንያ ለሳምንታት በዘለቀ ከባድ ዝናብ እና ጎርፍ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 228 መድረሱን የኬንያ የሀገሪር ውስጥ ሚኒስቴር አሳውቋል። ደብዛቸው የጠፋ በርካታ ሰዎች እንዳሉም ተነግሯል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ እንመለስ የእኛ ትልቁ ችግራችን ከሌሎች አለመማር ነው በሌሎች የሙስሊም ሀገራት ላይ የምደርሰው እልቂት ለማሳሌ፧ ቱርክ፣ሰዑዲ፣ሱዳን፣ሶማሊ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ ለምሳሌ፣አውሎ ንፋስ መከሰት፣ በጦርነት መብዛት የምደርስባቸው መከራ ለኛ ለሙስሊሞች ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደውል ነበር ከተማርንበት ግን ችግሩ እኛን በቀጥታ እስነካን ድረስ እኛን አይለከትም አይነት ነገር ነው ምላሻችን የሰሞኑን ጎርፍ ተልከቱ አድስ አበባ 4 ሰው ጎረቤት አላባ 5 ሰው በጎርፍ ተወሰደ እየተባለ ነው ሀላባ ለይ የመሬት መሰንጠቅ ጭምር ነው የተከሰተው ከዚህ በላይ ምን ይሁን የምያስደነግጠን ሰዎች? አሁንም እድሉ ያለን እኛ ወደ አላህ እንመለስ ለማንም ሳይሆን ለራሳችን ስንል መጥፋት የአንድ ቀን ክስተት ነው ሁለተኛ ዬለውም
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" የ2 ሰዎችን አስክሬን እየፈለግን ነው " - የዞኑ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ በሀላባ ዞን ንፋስ እና በረዶ ቀላቅሎ የጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከሰው ህይወት መጥፋት ባለፈ በአዝእርትና በብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህ ሁሉ ጉዳት የደረሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከዝናቡ ጋር በተያያዘ የተከሰተው የመሬት መሰንጠቅ በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ  መፍጠሩ ተነግሯል። በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊው አቶ ሸምሰዲን ጉታጎ ፥ " ሁኔታዉ እጅግ አስደንጋጭ ነው " ብለዋል። በጎርፍ አደጋው የ5 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ሲሉ ገልጸዋል። " አሁንም በጎርፍ ተወስደዉ ከሞቱት 5 ወገኖች መካከል የሁለቱን  አስክሬን ማግኘት አልቻልንም " ብለዋል። የአስከሬን ፍለጋው ሻላ ሀይቅ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን እና የኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተለይ ዋናተኞች እያገዟቸዉ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም አደጋው በርካታ የግለሰብ ቤቶችን እንዲሁም ዌራ ወረዳ ያለን ሆስፒታልን ሙሉ በሙሉ ከስራ ዉጭ እንዳደረገው ገልጸዋል። በዞኑ በበርካታ ቦታዎች ላይ የተፈጠረው የመሬት መሰንጠቅም በህብረተሰቡ ዘንድ ድንጋጤ መፍጠሩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። #TikvahEthiopiaFamilyHawassa @tikvahethiopia
نمایش همه...